
በዚህ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ባዘጋጀው ሰልፍ ላይ በአሁኗ ሰዓት በስደት ላይ ያሉ ወገኖቻችን በደቡብ አፍሪካ በየመንና በሊብያ የደረሰባቸውን ግፍና ጭካኔ በማውገዝ መፈክሮች ያሰሙ ሲሆን በወያኔ መንግስት በግፍ ታስረው በየወይኒ ቤቱ የሚገኙት የሕሊና እስረኞች ይፈቱ ዘንድ ጠይቀዋል በማያያዝም የኖርዌይ መንግስት ለአንባገነኑ የወያኔ መንግስት የሚያደርገውን ድጋፍ ያጤነው ዘንድ እንዲሁም የኖርዌይ ህብረተሰብ የሚከፍለው ታክስ ለጨኝቋ አገዛዞች እንዳይውል ይቆጣጠሩ ዘንድ በራሪ ወረቀቶችን በመስጠት አሳስበዋል።
No comments:
Post a Comment