Wednesday, April 29, 2015

የአንድነት ፓርቲ አባል የነበረው እስማኤል ዳውድ መታሰሩ ተሰማ

ismaelየአንድነት ፓርቲ አባል እና የሚሊየኖች ድምፅ አምደኛ የነበረው እስማኤል ዳውድ ትላንትና ከጠዋቱ ሁለት ሰአት ሲቪል በለበሱ ሰዎች ከመኖሪያ ቤቱ ተወስዶ ለእስር መዳረጉን ወላጅ እናቱ አስታወቁ፡፡
እስማኤል፣ ከጠዋቱ ሁለት ሰአት ሲቪል የለበሱ ሰዎች ቤቱ በመምጣት ‹‹ቃል ሰጥተህ ትመለሰላህ›› በማለት ከቤቱ ወደ አራዳ ፖሊስ ጣቢያ ከወሰዱት በኋላ ‹‹ቃሉን ሰጥቶም ቢሆን መለቀቅም እንደማይችል አስታውቀውት ወደ ወረዳ 9 ፖሊስ ጣቢያ መዘዋወሩን›› ወላጅ እናቱ ገልፀዋል። በትላንትናው እለትም ከአራዳ ፖሊስ ጣቢያ ስልክ ተደውሎላቸው ችሎት መድሃኒያለም አካባቢ ወደሚገኘው ወረዳ 9 ፖሊስ ጣቢያ መዘዋወሩን እንደተገለፀላቸው አስረድተዋል።
እስማኤል፣ በዛሬው እለት ፒያሳ በሚገኘው አራዳ ፍርድ ቤት ከረፋዱ 5፡30 የቀረበ ሲሆን በችሎቱ የተሰየመችው ዳኛ ‹‹በአራት ቀን ውስጥ ፖሊስ ምርመራውን አጠናቆ ለክስ የሚያበቃ በቂ ማስረጃ ካለው ፍርድቤት እንዲያቀርበው አለበለዚያ ግን በነጻ እንዲያሰናብተው›› ትእዛዝ አስተላልፋለች፡፡ ወላጅ እናቱን በምን ምክንያት ለእስር እንደተዳረገ ላነሳሁላቸው ጥያቄ ሲመልሱ ‹‹ከረቡዕ ሰልፋ ላይ በመገኘቱ ምክንያት እንደሆነና ከእሱም ሌላ ሁለት ጓደኞቹ ለእስር መዳረጋቸውን›› ገልፀዋል፡፡
ፖሊስ በረቡዕ ሰልፍ ላይ ተገኝተው ተቃውሟቸውን በመንግስት ላይ የገለፁ ወጣቶችን ከቤታቸው እያደነ በማሰር ላይ እንደሚገኝ እየተገለፀ ይገኛል፡፡ መንግስት በበኩሉ በረቡዕ ሰላማዊ ሰልፋ ላይ ለተነሳው ግጭት ሰማያዊ ፓርቲና ህገ-ወጥ ሲል የሰየመውንና በቀድሞ የፓርቲው ፕሬዝዳንት አቶ በላይ ፍቃዱ ይመራ የነበረውን የአንድነት ፓርቲ አባላትነትን ተጠያቂ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ስድስት አባሎቹ እንደታሰሩ ያስታወቀ ሲሆን ‹‹ህገ-ወጡ›› አንድነት በመባል በመንግስት የሚጠራውና በቀድሞ የፓርቲው ፕሬዝዳንት በላይ ፍቃዱ ይመራ ከነበረው አንድነት ውስጥ ለእስር የተዳረጉት ቁጥራቸው ሶስት ደርሷል፡፡ አቶ እስማኤል ዳውድ፣ አቶ ስንታየሁ ቸኮልና የፓርቂው የብሔራዊ ምክር ቤት አባል የነበሩት አቶ ዳዊት አስራደ ከረቡዕ ሰልፋ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ለማወቅ ተችሏል፡፡
አቶ እስማኤል ዳውድ፣ በትእግስቱ አወሉ በሚመራውና በበዙዎች ዘንድ ህገ-ወጡ አንድነት በመባል በሚታወቀው የፓርቲው አባላት አማካኝነት ስም የማጥፋት ክስ ተመስርቶበት ለሀያ ቀናት ታስሮ በዋስ መለቀቁ የሚታወስ ነው፡፡

ልብሴን እንዳወልቅ ከታዘዝኩ በኋላ ራቁቴን በወንድ መርማሪዎች ፊት ስፖርት እንድሰራ እገደድ ነበር›› ትላለች የዞን ዘጠኟ ማህሌት ፋንታሁን፡፡

medium_large.1418145809ፈቃዱ የተባለ በአሁኑ ሰዓት ቂሊንጦ ታስሮ የሚገኝ የሰማያዊ ፓርቲ የአርባ ምንጭ አስተባባሪ የነበረ ወጣት ማዕከላዊ በተባለ ማጎሪያ ቤት ታስሮ በነበረበት ወቅት ራቁቱን እንዲቆም ይደረግ እንደነበር ተናግሯል፡፡ ‹‹ወንድ መርማሪዎች ፊት ለፊት ራቁቴን ስቆም ሀፍረት እንደሚሰማኝ የተረዱት መርማሪዎች ይድነቅህ ብለው ሴት መርማሪዎች ፊት ከ3 ሰዓት ላላነሰ ጊዜ እርቃኔን እንድቆም እገደድ ነበር›› ይላል ፈቃዱ በወቅቱ ስለነበረው ነገር ሲያስረዳ፡፡ እንደ ፈቃዱ ምስክርነት ከሆነ ሴት መርማርዎቹ ፈቃዱን ፊት ለፊታቸው አስቁመው ጌም ይጫዎታሉ፡፡ ይሳሳቃሉ፡፡ ‹‹እኔን ራቁቴን ከሶስት ሰዓት በላይ እስቁመው ደብድበው ይሸኙኛል›› ይላል የሕሊና እስረኛው ፈቃዱ፡፡
በተመሳሳይ ‹‹ልብሴን እንዳወልቅ ከታዘዝኩ በኋላ ራቁቴን በወንድ መርማሪዎች ፊት ስፖርት እንድሰራ እገደድ ነበር›› ትላለች የዞን ዘጠኟ ማህሌት ፋንታሁን፡፡ ኤዶም ካሳዬም ተመሳሳይ ቶርቸር እንደተፈጸመባት ትናገራለች፡፡ መቸም ይህን ያክል በደል በወገኖቻቸው ላይ የሚፈጽሙ ሰዎች አንዳች ችግር ሳይኖርባቸው አይቀርም፡፡ ወንዶቹ ሴት አግብው ሴቶቹም ወንድ አግብተው ይኖራሉ፡፡ ወንድም ሆነ ሴት ልጆች አሏቸው፡፡ ታዲያ እንዴት ሴት ልጅ አቅፎ የሚያድር ገላ በሴት እህቶቻችን ላይ እንዲህ አይነት ብልግና ለመፈጸም ምን አስጨከናቸው? ወንድ ልጅ ደረት ላይ ተለጥፋ የምታድር ሴትስ ብትሆን እንዲህ አይነት ለአዕምሮ የሚከብድ ነገር ለማድረግ ጭካኔውን ከየት ተማረችው? ሀገራችንስ ወዴት እያመራች ነው? በእውነት እንደ ዜጋ ያሳዝናል፡፡ እንደ ሀገር ሲያስቡት ደግሞ ያሸማቅቃል፡፡ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ሴትን ልጅ እርቃኗን አስቁሞ ከመመርመር የወረደ ነገር ምን አለ፡፡ እንደ ሀገር ምን አይነት የሞራል ዝቅጠት ውስጥ እንደገባን አይነተኛ ማሳያ መስሎ ይሰማኛል፡፡
የተከበረውን የሰው ልጅ ገላ እርቃን እንዲሆን አድርጎ መደሰት ምንድን ነው ትርፉ? ቂም በቀልን ለልጅ ልጆቻችን ከማውረስ በቀር፡፡ እነዚህ ልጆች ለሀገራቸው ነግ ተጨንቀው፤ የመንግስት ዝርክርክ አሰራሮችን ለማስተካከል በልጅ አዕምሯቸው የመሰላቸውን ነገር ስለጻፉ፤ ስህተት ነው ብለው ያሰቡትን ነገር ስለተቹ ይህን ሁሉ ግፍ በአካላቸው ላይ መፈጸም ምን አመጣው፡፡
እኛ ውጭ ያለነው እስረኞችስ ብንሆን ይህን ነገር ለማቆም ምን አደረግን ብዬ ስጠይቅ ምንም የሚል መልስ አገኛለሁ፡፡ በቃ ቁመን ስንጠብቅ የእኛም ተራ ይደርስና እርቃናችን እንድንቆም ይደረጋል፡፡ ያኔ እንደ አዲስ ነገር ይወራል መልሶ በሳምንቱ ይረሳል፡፡ ይህ የክፋት አዙሪት እንዲቆም የበኩላችን አስተዋጽኦ ማድረግ የግድ ይኖርብናል፡፡ ያለ በለዚያ ግን አዙሪቱ እኛ ጋር መድረሱ አይቀርም፡፡

የወያኔ አፓርታይድ መንግሥት የሰማያዊ ፓርቲ አባላትን ጨምሮ ከ100 በላይ ሰዎችን ለመክሰስ ምርመራ ማጠናቀቁን አስታወቀ

47776b918f60714b042707a1fb44b846_Lሰማያዊ ፓርቲ መንግሥት ከስም ማጥፋት ዘመቻ ይታቀብ አለ
በኢትዮጵያውያን ላይ የአይኤስ አሸባሪ ቡድን የፈጸመውን አሰቃቂ ግድያ ለማውገዝ ሚያዝያ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. በተደረገው ሠልፍ ላይ፣ ሆን ብለው ብጥብጥ ያስነሱትና ሁከት እንዲፈጠር ያደረጉት፣ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና
አባላት መሆናቸውን ማረጋገጡን የፌዴራል ፖሊስ ገልጾ፣ ክስ እንዲመሠረት ለዓቃቤ ሕግ ማስተላለፉን አስታወቀ፡፡ በክሱም የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችንና አባላትን ጨምሮ ከ100 በላይ ሰዎች ተካተዋል፡፡
የፌዴራል ፖሊስ ጄኔራል ዳይሬክተር አቶ አሰፋ በዩ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ተዘጋጅተውና ልምምድ አድርገው፣ በንብረትና በሰው ሕይወት ላይ አደጋ ለማድረስ፣ የፖለቲካ እንቅስቃሴንና መላውን ዓለም ያሳዘነውን ሐዘን ሽፋን በማድረግ ሁከት ለመፍጠር ተዘጋጅተው የነበረ ቢሆንም፣ ሊከሽፍ መቻሉን አስረድተዋል፡፡
በወቅቱ ከ1,000 በላይ የሁከቱ ተሳታፊዎች በቁጥጥር ሥር ውለው የነበረ መሆኑን የገለጹት ጄኔራል ዳይሬክተሩ፣ ያለምክንያት በግርግሩ ውስጥ ከመገኘት ባለፈ ምንም ዓይነት ዝግጅትም ሆነ ሌላ ዓላማ የሌላቸውን በመለየት፣ በዕለቱ በየክፍላተ ከተማቸው በተደረገ ማጣራት አብዛኛዎቹ ተለቀው 100 ያህሉ ብቻ ታስረው እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡
በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ ከተደረገባቸው ተጠርጣሪዎች መካከል ረብሻውን በዋናነት በማቀጣጠል፣ በማደራጀትና በመምራት ከ20 በላይ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት በዋነኛነት ተሳትፊ መሆናቸው መረጋገጡን አቶ አሰፋ ተናግረዋል፡፡ አንዳንድ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ አባላትም እንዳሉ አክለዋል፡፡
ብጥብጡን ተቀላቅለው ንብረት ለማውደምና በሰው ሕይወት ላይ አደጋ ለማድረስ ተዘጋጅተው የነበሩ አክራሪዎችም እንደነበሩ የገለጹት አቶ አሰፋ፣ በአጠቃላይ ከ100 በላይ በሚሆኑ ሁከትና ብጥብጥ ፈጣሪዎች ላይ ክስ እንዲመሠረት የሚያስችል ምርመራ መጠናቀቁን አስረድተዋል፡፡
በወቅቱ በተከሰተው ብጥብጥና ሁከት በፖሊስ አባላት ላይ በተደረገ የድንጋይ ውርወራ 41 የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አባላት ጉዳት እንደደረሰባቸው የጠቆሙት ጄኔራል ዳይሬክተሩ፣ በተለይ አምስት አባላት ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው ተናግረዋል፡፡ ሦስት የሠልፉ ተሳታፊዎችም ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው አስታውቀዋል፡፡
መንግሥት በፖሊስ በተደረገው ምርመራ የብጥብጡ ዋና ምክንያትና አቀነባባሪ ሰማያዊ ፓርቲ መሆኑ መረጋገጡን ያስታወቀ ቢሆንም፣ ሰማያዊ ፓርቲም በበኩሉ የመንግሥት ፕሮፓጋንዳ በእሱ ላይ በዋናነት ያነጣጠረው ከምርጫው ለማስወጣትና ያለማንም ተቀናቃኝ ለማሸነፍ መሆኑን ገልጿል፡፡
ሚያዝያ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. በአሸባሪው የአይኤስ ቡድን በሊቢያ በግፍ በተገደሉ ኢትዮጵያውያን ምክንያት በመስቀል አደባባይ የተጠራው ሠልፍ በግጭት እንዲጠናቀቅ ያደረገው ሰማያዊ ፓርቲ ነው ለሚለው ውንጀላ መንግሥትን ወቅሶ ከእንዲህ ዓይነት ስም ማጥፋት ዘመቻው እንዲታቀብም ጠይቋል፡፡
ፓርቲውን ይህን ያስታወቀው ሚያዝያ 19 ቀን 2007 ዓ.ም. በጽሕፈት ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ነው፡፡
በዕለቱ መግለጫውን የሰጡት የሰማያዊ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ፣ የሕግ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ይድነቃቸው ከበደና የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ አቶ እያስፔድ ተስፋዬ ናቸው፡፡
‹‹ማንኛውም ክስተት ከምርጫው ጋር ተያያዘም አልተያያዘም የምርጫ ወቅት እስከሆነ ድረስ፣ ከምርጫው ጋር የሚያገናኛቸው በርካታ ጉዳዮች ይኖራሉ፤›› በማለት ከተቃውሞው ሠልፍ በኋላ የተፈጠረውን ክስተት፣ መንግሥት ፓርቲውን ለማጥቃትና ለማዳከም እየተጠቀመበት እንደሆነ አቶ ዮናታን ገልጸዋል፡፡
‹‹ከምርጫው ጋር በቀጥታ የሚያገናኘው ነገር በመኖሩ ፓርቲው ጉዳዩን በሕግ የሚያየው ይሆናል፤›› ያሉት አቶ ዮናታን፣ ፓርቲው ስሜን አጠፉ ያላቸው ተቋማትና ግለሰቦች ላይ ክስ ለመመሥረት እየተዘጋጀ እንደሆነ አክለው ገልጸዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም የፓርቲው ኃላፊዎች በመግለጫው ወቅት እንዳስታወቁት፣ ሚያዝያ 18 ቀን 2007 ዓ.ም. ምሽት የሁለት ሰዓት ዜና ላይ የፌዴራል ፖሊስ ሰባት ሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና ከ20 በላይ አባላትን ማሰሩን አስመልክቶ የሰጠው መግለጫ ‹‹ፈጽሞ ከእውነት የራቀ ነው፤›› በማለት ተቃውመዋል፡፡
በፌዴራል ፖሊስ የቀረበው የታሰሩ የአባላቱን ቁጥር ከመቃወም ባሻገር፣ ‹‹በአሁኑ ጊዜ በእስር ላይ የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ቁጥር ስድስት ብቻ ነው፤›› በማለት ፓርቲው አስታውቋል፡፡ ‹‹እነዚህ ስድስት እስረኞች የፓርቲው አባላት እንጂ አመራሮች አይደሉም፡፡ ስለዚህ የረቡዕ ዕለቱን ሠልፍ ተከትሎ ፓርቲው የታሰረበት አንድም አመራር የለም፤›› በማለት ገልጿል፡፡
ፓርቲው ሚያዝያ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. አውጥቶት በነበረው መግለጫ ስምንት ያህል አባላቱ መታሰራቸውን መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን፣ በመግለጫው ወቅት በቁጥጥር ሥር ውለው ከነበሩት አባላት መካከል ቀጨኔ አካባቢ ወረዳ 9 ታስሮ የነበሩት አቶ ብሩክ የኔነህ የተባሉ የፓርቲው አባል መለቀቃቸው ተገልጿል፡፡ አቶ ብሩክ ፍርድ ቤት ቀርበው የ12 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ተሰጥቶባቸው እንደነበርም እንዲሁ ተገልጿል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ከሠልፉ መጀመር ሰዓታት አስቀድሞ አባላቱ መታሰራቸውን የገለጸው ሰማያዊ ፓርቲ፣ ‹‹በሠልፉ ላይ ለተፈጠሩት ማንኛቸውም ድርጊቶች ፓርቲውን ተጠያቂ ማድረግም በእጅጉ መሠረተ ቢስ ነው፤›› በማለት ተቃውሟል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘም፣ ‹‹በፌዴራል ፖሊስና በመንግሥት የመገናኛ ብዙኃን አማካይነት ተደጋጋሚ የስም ማጥፋት ዘመቻ እየደረሰ ይገኛል፤›› ብሏል፡፡
መንግሥትና የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ከዚህ እኩይ ተግባራቸው የማይታቀቡ ከሆነ፣ የሰማያዊን ስም በሐሰት በማጠልሸት ሥራ ላይ የተሰማሩ የመንግሥት ተቋማትንና ግለሰቦችን በሕግ ፊት ለማቆም ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ ፓርቲው አስታውቋል፡፡

በአማራ ክልል የሚገኙ የብ.አ.ዴ.ን/ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ከፍተኛ ባለስልጣኖች ስጋት የወለደው ስብሰባ አካሄዱ -

ethio-oppo-forcesበአማራ ክልል የሚገኙ የብ.አ.ዴ.ን/ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ከፍተኛ ባለስልጣኖች ስጋት የወለደው ስብሰባ ሲያካሂዱ መሰንበታቸውን የደረሰን መረጃ አመለከተ፣እንደምንጮቻችን መረጃ።- የብ.አ.ዴ.ን. /ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ከፍተኛ አመራሮች ሚያዝያ 6 እና 7 2007 ዓ/ም ለተከታታይ ሁለት ቀናት በተካሄደ ስብሰባ የአካባቢያችን ደህንንትና ሰላም ምን ይመስላል? የዚህ ክልል አለመረጋጋት ምክንያቱ ምንድን ነው? በሚሉና በሌሎችም ጉዳዮች ሲከራከሩ መቆየታቸውን የገለፀው መረጃው። በተለይ የትጥቅ ትግል የሚያካሂደው የአርበኞች ግንቦት 7 ድርጅት በመንግስታችን ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት ሊያደርግ ሰራዊቱን በሁመራና አካባቢው ላይ አስጠግቷል በሚል ፍርሃት የወለደው ስብሰባ ማካሄዳቸውን ለማወቅ ተችሏል፣
እኒህ ከፍተኛ ባለስልጣኖች በስብሰባው። መንግስት በአርበኞች ግንቦት 7 ላይ ተመጣጣኝ እርምጃ ሊወስድ ስለሆነ በክልላችን ስለድርጅቱ የሆነ መረጃ ያመጣ ሰው ለማበረታቻ የሚሆን ሽልማት ይሰጠዋል በማለት ህብረተሰቡን በማታለል ስራ ላይ ተጠምደው እንደሰነበቱ ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመለከተ፣
አሰግድ ታመን

ኤዶምንና ማህሌትን ብቻ ሳይሆን የ45 ሚሊዮን ሴቶች ክብርን ነው ያቀለሉት

z9ኤዶም ካሳዬ ጋዜጠኛ ናት። ማህሌት ፈንታሁን ደግሞ «ሰለሚያገባን እንጦምራለን» በሚል የአለም አቀፍም ሆነ የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት በሚፈቅድላቸው መሰረት፣ ብሎግ ከሚያደርጉ ዞን ዘጠኞች አንዷ ናት። ኤዴሞም ሆነ ማህሌት የጻፉት፣ የተናገሩት የተደበቀም ሆነ የተሸፈነ ነገር የለም። ለፍትህ ከመቆማቸው በቀር ያጠፉት ጥፋት የለም። ወንጀላቸው አገራቸውን መዉደዳቸው ነው። ሆኖም ሕወሃት «ሽብርተኞች» ብሎ ካሰራቸው ይኸው አንድ አመት ሆናቸው። ቢያንስ ከ27 ጊዜ በላይ ፍርድ ቤት ተመላልሰዋል። አስቡት በአንድ አመት ዉስጥ ቢያንስ 27 ጊዜ !!!!!
የአገሪቷ ሕገ መንግስት በማረሚያ ቤት ያሉ እስረኞች በምን መልኩ መያዝ እንዳለባቸው በግልጽ አስቀምጧል። በአንቀጽ 19 ንኡስ አንቀጽ አንድ ላይ፣ እያንዳንዱ ዜጋ ፣ እስረኞችን ጨምሮ፣ ኢሰብአዊ ፣ ጭካኔ የተሞላባቸዉና ክብርን የሚነኩ ቅጣቶች ሊቀበል እንደማይገባ ያስቀምጣል። ሆኖም ረእቡ ሚያዚያ 14 ቀን፣ የአዲስ አበባ ሰልፈኞች እንዳሉት፣ ለሕወሃት ሕገ መንግስቱ ወረቀት ብቻ ነው። እህቶቻችን ሞራላዊ፣ መንፈሳዊና የሴትነት ክብራቸውን በመድፈር ፣ ራቁታቸውን ሆነው በአረመኔ የሕወሃት ወንድ ምናምንቴዎች ፊት ስፖርት እንዲሰሩ መገደዳቸው ምን ያህል እንደ አገር መዝቀጣችንን የሚያሳይ ነው። በርግጥ ኤዶምና ማህሌትን ብቻ ሳይሆን ሕወሃቶች ከ40 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑትን የአገራችንን እናቶችና እህቶች ነው የደፈሩት።
ለሰብአዊ መብት ጉባኤ ኮሚሽን፣ ኤዶም ላሳዬና ማህሌት ፋንታሁን ከተናገሩት የተወሰነውን እንሆ፡
«ሙሉ ልብሴን እንዳወልቅ ተገድጄ ራቄቴን በወንድ መርማሪዎች ፊት ስፓርት አንድሰራ እገደድ ነበር ፡፡ “ሴትነትሽ አንዲህ ከሚዋረድ አመጽ እንዳነሳሳሽ እመኚ ተብያሁ”» ማህሌት ፋንታሁን
«በተለምዶው ከምመረመርበት ቢሮ ውጩ አንደኛ ፎቅ አዳራሽ ውስጥ ለምርመራ ተወስጄ ልብሴን እንዳወልቅ እና የተለያዬ ለመናገር የሚከብዱ ስፓርታዊ አንቅስቃሴዎችን እንድሰራ ተገድጃለሁ፡፡ እንዲህ ከምትዋረጂ አመጽ ልናስነሳ ነበር ብለሽ ለምን አታምኚም እያለ ይመታኝ ነበር » ኤዶም ካሳዬ
እንግዲህ የዛሬይቱ የሕወሃት ኢትዮጵያ ይች ናት። ይህ አይነቱን ኢሰብዊነት ማስቆም ካልቻልን እንደ አገር ሆነ እንደ ሕዝብ መቀጥል አንችልም። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ፣ ይህ አይነቱ ብሄራዊ ዉርድት እንዲቆም መነሳት አለበት። ፈረንጆችን እንደሚሉት “We have to claim back our country from these monsters” ። በተለይም እናቶችና እህቶች ፣ አዉቃለሁ ብዙ ግርግር አትወዱም። ግን አሁን እናንተም ከወንዱ ባልተናነሰ የምትነሱበት ጊዜ ነው።

የወያኔ ደህንነቶች ሰማያዊ አዋሳ ከተማ ውስጥ እንዳይቀሰቅስ ከለከሉ

semayawi-partyየገዥው ፓርቲ ደህንነቶች፣ ካድሬዎችና ፖሊሶች ሰማያዊ ፓርቲ አዋሳ ከተማ ውስጥ እንዳይቀሰቅስ እንደከለከሉ የሰማያዊ ፓርቲ ም/ሊቀመንበርና የምርጫ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ስለሽ ፈይሳ ለነገረ ኢትዮጵያገልጸዋል፡፡ ባለፉት ሁለት ቀናት በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች ሲቀሰቅስ ቆይቶ ወደ አዋሳ ያቀናውን የሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ ቡድን ዛሬ ጠዋት አዋሳ ሲደርስ እንዳይቀሰቅስ እንደተከለከለ የገለጹት አቶ ስለሽ ደህንነቶች የመኪናውን ባለቤት በማስፈራራት በእጅ አዙር ቅስቀሳችንን በማስቆም ከተማው እንድንወጣ ጫና እያደረጉ ነው ብለዋል፡፡
ከዚህም ባሻገር ‹‹አዋሳ ውስጥ መቀስቀስ አትችሉም፡፡ ከተማውን ለቃችሁ ውጡ፡፡ ለቃችሁ ካልወጣችሁ መኪናውን ለ10 ቀን እናስረዋለን፡፡ 10 ሺህ ብርም እንቀጣችኋለን›› እያሉ የመኪናውን ባለቤትና ቀስቃሾቹን እያዋከቡ እንደሚገኙ የቅስቀሳው ተሳታፊዎች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ደህንነቶች፣ ፖሊሶችና ካድሬዎች እያደረጉት ባለው ወከባም የመኪና ላይ ቅስቀሳው ለጊዜው እንደተቋረጠ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Tuesday, April 28, 2015

(የሊቢያው ጉዳይ) ‹‹አሁንም የመሄድ ሐሳባችንን አልቀየርንም›› በግፍ የተገደሉት የሠፈር ጓደኞች

yemane Nagishአሸባሪው አይኤስ ምንም ከለላ በሌላቸው ስደተኛ ኢትዮጵያውያን ላይ በሊቢያ ሜዲትራንያን ባህር ዳርቻ ላይ የፈጸመውን አሳፋሪ ድርጊቱን የሚያሳይ ቪዲዮ ከተለቀቀ በኋላ፣ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ተቀባብለውታል፡፡ ከሁሉም በላይ ግን ይኼ አስደንጋጭ ዜና ያጥለቀለቀው ማኅበራዊ ሚዲያውን ነበር፡፡ ሰላሳ ወጣት ኢትዮጵያውያን የዚህ አስከፊ ግፍ ሰለባ በመሆናቸው በተለያዩ አካባቢዎች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ቁጣ ቀስቅሷል፡፡ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ከፍተኛ ሥፍራ የሚሰጠው የዳግማይ ትንሳዔ በዓል ዕለት በአሸባሪው በአይኤስ የተለቀቀው ቪዲዮ፣ እስካሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ከተፈጸሙት አሰቃቂ የሽብር ድርጊቶች እጅግ የከፋው ነው እየተባለ ነው፡፡ ይኼ አረመኔያዊ ድርጊት ቀደም ብሎ በሌላ መጥፎ ዜና ከወደ ደቡብ አፍሪካ የታጀበ ነበር፡፡ የደቡብ አፍሪካ በዘር ጥላቻ የተለከፉ ግለሰቦች፣ ‹‹የውጭ አገር ስደተኞች ከአገራችን ይውጡልን፤›› በማለት ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ በርካታ አፍሪካውያን ላይ ጉዳት አድርሰዋል፡፡ የመንግሥት ባለሥልጣናት ምላሾች ተለሳልሰዋል በማለት ብዙዎችን ሲያበሳጭና ሲያናድድ አንድ ሳምንት አልሞላውም ነበር፡፡
ጥቃቱም በዚሁ አላበቃም፡፡ የመንግሥት ለመንግሥት ግንኙነት በልጦባቸዋል እየተባሉ ሲተቹ የቆዩት የመንግሥት ባለሥልጣናት ምላሽም በዚህ አላበቃም፡፡ በሊቢያ የኢትዮጵያውያን ምሥል እየታየ የተለቀቀው ቪዲዮ እውነትነት ጥርጣሬ ገብቶዋቸው ይሁን ወይም በሌላ ምክንያቱ ባይታወቅም፣ ብዙዎቹ በሊቢያ የተፈጸመውን ድርጊት ፈጥነው ማውገዝ አልቻሉም፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የአንዱ የአይኤስ ሰለባ እህት የወንድሟን አገዳደል ቀድማ መለየት በመቻሏ፣ በተለይ በተለምዶ ጨርቆስ (ቂርቆስ) በመባል በሚታወቀው አካባቢ ሐዘንና ቁጣ ቀሰቀሰ፡፡
በፀጉሩ ምክንያት ቤተሰቡ በቀላሉ መለየት የቻሉት ኢያሱ ይኩኖአምላክ ነው፡፡ ጓደኛው አብሮ መጓዙን የሚያውቁ የወጣት ባልቻ በለጠ ቤተሰቦችም መጠርጠር ጀመሩ፡፡ እሱም የሰለባው አካል መሆኑ ታወቀ፡፡ ድንኳኑ በጋራ ተጣለ፡፡ የቂርቆስ አካባቢም ድባብ በሐዘን ተዋጠ፡፡ ይህ የሆነው ሰኞ ጠዋት ሲሆን፣ መንግሥት የሰጠው መግለጫ አልነበረም፡፡ በተለይ ‹‹የሟቾቹን ማንነት እናጣራለን፤›› የሚል መግለጫ መባሉ ብዙዎችን አስቆጣ፡፡ በሐዘን ቤት የተገኙት ለቀስተኞች በመንግሥት መግለጫ ማዘናቸውን ገልጸው ነበር፡፡ ማኅበራዊ ሚዲያው ደግሞ ማውገዙን ቀጠለ፡፡ በኢሕአዴግ ደጋፊነታቸው የሚታወቁ ፌስቡከሮች ሳይቀሩ መንግሥትን አወገዙ፡፡ አንዱ፣ ‹‹መንግሥታችን ለመሆኑ የሰብዓዊ ፍጡር ስብስብ ነው ወይ?›› አለ የኢሕአዴግ የምርጫ ቅስቀሳ ሰኞ ማታ ሲተላለፍ አይቶ፡፡ በእርግጥ ወደ ኋላ መንግሥት ስህተቱን ያረመ ይመስላል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የሐዘን መግለጫ አሰሙ፡፡ በነጋታውም የአገሪቱ ፓርላማ የሦስት ቀናት ሐዘን አወጀ፡፡ የአገሪቱ ባንዲራም ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ ተደረገ፡፡ የመንግሥትን አቋም የለወጠው የማኅበራዊ ሚዲያ ንቅናቄ ሳይሆን አይቀርም የሚል ግምት ተሰማ፡፡
የሟች ኢያሱ እናት ወ/ሮ አኸዛ ካሳዬ፣ ልጃቸው ወደ ሊቢያ መጓዙን የሰሙት ዘግይተው ነበር፡፡ የበለጠ ቤተሰቦችም ቢሆኑ አላወቁም ነበር፡፡ ጉዳዩ በሁለቱ አብሮ አደጐችና ጓደኞች በሚስጥር የተደረገ ነበር፡፡ አሁን የሰሙትን መቀበል አቅቷቸዋል፡፡ የሰለባዎቹ ቤተሰቦች በሥርዓቱ አልነበረም የተረዱት፡፡ በፌስቡክና በዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ነበር ያወቁት፡፡
ሐዘኑ በዚህ አላበቃም፡፡ በትግራይ ክልል የእንትጮ ከተማ 02 ቀበሌ ነዋሪ የሆነው የ25 ዓመቱ ወጣት ዳንኤል ሐዱሽ ፎቶም ተለይቶ ተለቀቀ፡፡ ዳንኤል ባለፈው ዓመት ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በዲግሪ የተመረቀ ነው፡፡ በ1982 ዓ.ም. በአስመራ ከተማ የተወለደው ዳንኤል፣ የሁለት ዓመት ሕፃን ሆኖ ወደ አገሩ ወደ ኢትዮጵያ መምጣቱን ከቤተሰብ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ ተወልደ ተክሉ ከተባለው (አሁን ያለበት ሁኔታ አልታወቀም) ጓደኛው ጋር ነበር ወደ ሊቢያ የተጓዘው፡፡ በዚሁ አረመኔያዊ ድርጅት አራተኛ ልጃቸውን ያጡ እናት ወ/ሮ ዛፏ ገብረ ኢየሱስ እንደ ሌሎቹ እሳቸውም የልጃቸውን ወደ ሊቢያ መሄድ አያውቁም፡፡ ሑመራ የስኳር ፋብሪካ ውስጥ እንደሚሠራ ነግሯቸው ነበር የሄደው፡፡ ‹‹በአካባቢው ኔትወርክ አይሠራምና አልደወለም ብለሽ እንዳታስቢ፤›› ብሏቸው ጥር 25 ቀን 2007 ዓ.ም. መሄዱን ይናገራሉ፡፡ ሪፖርተር ያናገራት አንዲት ዘመዱ እንደምትለው፣ ‹‹ሥራ አላገኘሁም፡፡ ሰው በዘመድ ነው ሥራ የሚገባው፡፡ እኔ ዘመድ የለኝም፤›› ብሎ ነበር፡፡ ሑመራና መቐለ ተመላልሶ ሥራ በማጣቱ ምክንያት ስደትን አማራጭ አድርጐ መወሰኑን ትናገራለች፡፡
አሁንም መርዶ

በዚሁ አላበቃም፡፡ ባለፈው ሳምንት እሑድ ጀምሮ በሐዘን በቁጣና በተቃውሞ በተጨናነቀው ቂርቆስ፣ አሁንም ሌላ መርዶ ተሰማ፡፡ ከሦስት ወራት በፊት የካቲት 15 ቀን 2007 ዓ.ም. ቀደም ብለው ወደ ሊቢያ ያመሩት ሦስት ወጣቶች ከሰለባዎች መካከል መሆናቸው ታወቀ፡፡ ኤልያስ ተጫነ፣ ብሩክ ካሳና በቀለ ታጠቁ ይባላሉ፡፡ ሁሉም ኑሮ የከበዳቸውና ምንም የሥራ አማራጭ ያጡ እንደነበሩ የሠፈር ጓደኞቻቸው ይናገራሉ፡፡
ከእነዚህ መካከል የበቀለ ታጠቁ የአጐት ልጅ የሆነውን ታምራት ታረቀኝን ሪፖርተር አናግሮት ነበር፡፡ በቀለ ከወልቂጤ ነው የመጣው፡፡ ቤተሰቡ አሁንም ድረስ እዚያው ነው ያሉት፡፡ ሲሄድ አልነገረውም፡፡ መተማ ዮሐንስ እንደደረሰ ግን ደውሎ 11,000 ብር እንዲልክለት ይነግረዋል፡፡ ዱብ ዕዳ ሆኖበት አገር ቤት ልጆች በሰንበት ትምህርት ቤት ተሰብስበው ቲሸርት ያሳትሙ ነበር፡፡ ኃላፊውም በቀለ ራሱ ነበር፡፡ በቀጣይ ዓመት ተመሳሳይ ነገር ለመሥራት ያተረፉትን 3,600 ብርና የቀረውን ጨምሮ ይልክለታል፡፡ ቀጥሎም ከሁለት ቀናት በኋላ ሱዳን ካርቱም ላይ ሆኖ 34,000 ብር እንዲልክለት በደላሎቹ ያስነግራል፡፡ ካልሆነም ወንድሙ አደጋ ላይ እንደሚወድቅ ይነግሩታል፡፡ ሊያገናኙት ግን አልቻሉም፡፡ ወልቂጤ ድረስ በመሄድ ለወላጆቹ ነግሮ ከዚያም ከዚህም ተበድሮ አሰባስቦ አሁንም ሕይወቱን ለማትረፍ ይልክለታል፡፡ እንደምንም ደውሎ አንድ ጊዜ ድምፁን ሰምቷል፡፡ ከዚያ በኋላ አላገኘውም፡፡ አሸባሪው አይኤስ ይህንን ዘግናኝ ድርጊት የፈጸመ ዕለት እሑድ ታምራት አገር ቤት ነበር፡፡ ቀደም ብሎ ያያትን ልጅ ለማጨት ከጓደኛው ጋር ነበር የሄደው፡፡ እንደ አገሩ ባህል ሽማግሌዎች የላከ ሲሆን፣ ከመካከላቸው የሟቹ የወጣት በቀለ አባት አቶ ታጠቁ ይገኙበታል፡፡
እሑድ ከሰዓት በኋላ ‹‹ሰጠናችሁ›› ተብሎ እዚያው የደስ ደስ ፍንጥር አድርገው ነበር ያደሩት፡፡ ሰኞ እዚህ እንደመጣ ይህንን መጥፎ ዜና ታክሲ ውስጥ ይሰማል፡፡ ይደነግጣልም፡፡ ‹‹ቀልቤ ልክ አይደለም፤›› ይላል፡፡ በቀለ መሄዱን ከእሱ ውጪ እምብዛም ሰው አያውቅም ነበር፡፡ ለጓደኞቹ በቀለ እንደሄደ ነግሯቸው በፌስቡክ እንዲያዩ ይጠይቃቸዋል፡፡ ‹‹እኔ ማየት አልቻልኩም፡፡ ድፍረቱም የለኝም፤›› ይላል፡፡ ከዚያ ሐሙስ ጠዋት ሌላ አጐቱ ዘንድ በመሄድ እሱም ከሌሎቹ ጋር እንደሞተ ይናገራል፡፡ በኃላፊነት ከአገር ቤት አስመጥቶ በዕዳ የላከው ልጅ ሐዘን በርትቶበት እንባ እየተናነቀው፣ ከዚያ ውጪ መናገር አልቻለም፡፡ የሦስቱ ወጣቶች ሐዘን የተከናወነው በአንድ ድንኳን ሲሆን፣ የሌሎችም ታሪክ አሳዛኝና ተመሳሳይ ነው፡፡ አንዳች ዕርዳታና ድጋፍ ካልተደረገላቸው በቀላሉ የሚፅናኑ አይመስልም፡፡
በአካባቢው ከተቀመጡት ወጣቶች መካከል መናገር የሚፈልገው ነገር እንዳለ እያሳበቀበት ነው፡፡ ‹‹እባካችሁ ሕገወጥ ስደተኞች አትበሉ፡፡ ልጆቹ ሕገወጥ አይደሉም፡፡ እንጀራ ፈላጊ ናቸው፡፡ ሱዳን ኤምባሲ ከፌዴራል ፖሊስ ጽሕፈት ቤት መቶ ሜትር አይርቅም፡፡ በሕጋዊ መንገድ ነው የሚወጡት፡፡ በሰላምና በስካይ ባስ ነው ተሳፍረው በሱዳን የወጡት፤›› ይላል የሰለባዎቹ ጓደኛ ወጣት ያሬድ አሰፋ፡፡ ‹‹እዚህ አካባቢ ያለው ሰው በሙሉ መሥራት ይፈልጋል፡፡ መንጃ ፈቃድ ማውጣት ይፈልጋል፡፡ አልቻለም፡፡ ክፍያው ቀላል አይደለም፡፡ ለመንግሥት ንገሩልን፡፡ ይቀንስልን፤›› በማለት በተስፋ መቁረጥ መንፈስ ተናግሯል፡፡
የሠፈሩ ልጆች ብሎኬት አምርቱ ተብለው ለሥራ ተሰማርተው እንደነበር ያስረዳል፡፡ የሚሠሩበት የኮንዶሚንየም ሳይት ቃሊቲ አካባቢ በመሆኑ የባሰ ዕዳ አመጣችሁ ተብለው የመንግሥት ትራንስፖርት ተከልክለው በራሳቸው እንዲጓዙ መደረጋቸው፣ በዚህም ተስፋ ቆርጠው ሥራውን እንዳቆሙ ይናገራል፡፡
‹‹እኛም ለመሄድ ነው የምናስበው››
ሮቤል ደፋሩ የኤልያስና የብሩክ ጓደኛ ነው፡፡ ከዋሊያ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጀምሮ እስከ ስለሺ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አብሮአቸው ተምሯል፡፡ በ2002 ዓ.ም. በኮብልስቶን ሠልጥነዋል፡፡ ‹‹ነገር ግን ቁጭ ብለናል፤›› ይላል፡፡ ‹‹እኛም ለመሄድ ነው የምናስበው፡፡ ልንከተላቸው ነበር፤›› በማለቱ ‹‹አሁንስ ምን ታስባላችሁ?›› የሚል ጥያቄ ቀረበለት፡፡ ሮቤል ብቻ ሳይሆን አጠገቡ የነበሩት ሌሎችም የሠፈሩ ልጆች አንድ ላይ፣ ‹‹አሁንም እንሄዳለን፡፡ ምንም ተስፋ የሚሰጥ ነገር የለም፡፡ ዕድላችንን እንሞክራለን፤›› አሉ፡፡
በአሸባሪዎች ሊቢያ ውስጥ የተጨፈጨፉ ጓደኞቻቸውን እየተመለከቱ አሁንም ለመሄድ ያስባሉ፡፡ እዚህ አገር ባለው ነገር ተስፋ መቁረጣቸውን ይናገራሉ፡፡ ሄደው ጣሊያንና ጀርመን ገብተው ያለፈላቸው እንዳሉም ያስረዳሉ፡፡
አሸናፊ ቦጋለ የተባለው ወጣት ከመካከላቸው በጣም ተስፋ የቆረጠ ይመስላል፡፡ ‹‹እኛ ምርጫ በመጣ ቁጥር ነው መንግሥት የሚፈልገን፤› በማለት እሱም በኮብልስቶንም፣ በኤሌክትሪክም ሠልጥኖ ምንም መሥራት አለመቻሉን ይናገራል፡፡ ‹‹አንዳንድ ጊዜ የምናገኛትን ብር አጠራቅመን እንሄዳለን፡፡ ሕጋዊ መንገድ ተዘጋ፡፡ እዚህ ያለው ወጣት በሙሉ በዚሁ መንገድ ለመሄድ የተዘጋጀ ነው፤›› ይላል፡፡
ሪፖርተር በአካባቢው ተዟዙሮ ያነጋገርናቸው ወጣቶች ጥያቄያቸው ተመሳሳይ ነው፡፡ ምንም የሥራ አማራጭ እንደሌላቸው ይናገራሉ፡፡ ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ወሮአቸዋል፡፡ አንድ ስሙን መጥቀስ ያልፈለገ ወጣት፣ ‹‹ሌላስ ይቅር እባካችሁ መንግሥት ሊቢያ በአደጋ ላይ ያሉትን ሕይወት ለመታደግ ምን እየሠራ እንደሆነ ጠይቁልን፤›› ይላል፡፡ ‹‹አገር ውስጥ ስላለው ችግር ብናገር ምንም አዲስ ነገር ስለሌለው ባልናገር ይሻላል፤›› በማለት ተንሰቀሰቀ፡፡
ዓምደ ዲኖ የተባለው ሌላው ጓደኛው ግን ጣልቃ ገብቶ፣ ‹‹ስብሰባ ጠርተው ሃምሳ ሃምሳ ብር ሰጥተው ወጣቱ እየሠራ ነው የሚል ፕሮፓጋንዳ ከሚሠሩብን ምን አለ ሥራ ቢፈጥሩልን?›› በማለት ይጠይቃል፡፡
ዳዊት ላቀው የተባለው ሌላው ወጣት ግን ችግሩ ከመንግሥትም አቅም በላይ እንደደረሰ ይናገራል፡፡ ‹‹ምንም ዓይነት የሥራ ዕድል የለም፡፡ የሚወራውና መሬት ላይ ያለው ተጨባጭ ነገር ለየቅል ነው፡፡ ያልፍልናል ብለው ነበር የሄዱት፡፡ አሁን ግን ከቤተሰብም አልፈው አገር አሳዝነዋል፡፡ ከዚህ በፊት ብዙ ሰው ተሳክቶለታል፡፡ ያንን ስኬት አይተው ነው የተሳሳቱት፤›› ይላል፡፡ እሱም ከመንግሥት የሚጠብቀው አንዳች ነገር የለም፡፡
‹‹ምን ማድረግ እንደሚቻል አይታወቅም፡፡ መንግሥትም የሚቻለው ነገር አይመስለኝም፡፡ ስደት ይብቃ ብለህ የምታስቆመው አይደለም፡፡ ይህንን ያህል ሥራ አጥ ወጣት ማብቃት ከባድ ነው፡፡ መንግሥት እንዴት እንደሚቋቋመው አላውቅም፡፡ ከባድ የቤት ሥራ ነው ያለበት፤›› ብሏል፡፡
ሌላ ‹‹ሕገወጥ›› የሚለው አገላለጽ እጅግ ያስከፋው ወጣት፣ ‹‹ደልቶት ወይም ከመንግሥት ጋር ተጣልቶ አይደለም የሄደው፡፡ ይኼ ነገር ቢታረም ደስ ይለኛል፤›› ብሏል፡፡ የአንድ የመንግሥት ባለሥልጣን አነጋገርንም በመተቸት ‹‹እባክህ ምን አለበት አንድ የሚያሳርፍ ቃል ቢጠቀም፤›› ብሏል፡፡
‹‹ያመለጠው››
በአካባቢው ከተገኙት የሟቾች ጓደኞች መካከል ወጣት ልዑል ሰገድ ንጉሥ አንዱ ነው፡፡ ጉዳት ከደረሰባቸው ጓደኞቹ በፊት ከሌሎች ሦስት የሠፈር ልጆች ጋር ነበር ወደ ሊቢያ የተጓዘው፡፡ ታሪኩን ይናገራል፡፡ ከአዲስ አበባ ትኬት ቆርጠው ባህር ዳር ይደርሳሉ፡፡ ከዚያም መተማ ከደላሎች ጋር ተገናኝተው ወደ ገለባት ሄዱ፡፡ ገለባት ላይ የኢትዮጵያና የሱዳን ሲም ካርድ ተሰጣቸው፡፡ ሁለቱም ይሠራሉ፡፡ ከመተማ ወደ ካርቱም 12,000 ብር ተጠይቀዋል፡፡ ብሩ የሚከፈለው ካርቱም ሲገባ ነው፡፡ እዚህ ያለ ቤተሰብ ነው የላከለት፡፡ የሚቀበሉዋቸው ደላሎች ሱዳናውያን ሲሆኑ፣ አልፎ አልፎ ሐበሾችም አሉ፡፡ ጉዞ በመኪና በመሆኑ በሌሊት ነው፡፡ ገዳራት የሚባል ቦታ ላይ 15 ቀናት ያህል ቆይተዋል፡፡ ‹‹ምንም ምግብ አይሰጡንም፡፡ በረሃብ አልቀን ነበር፤›› ይላል፡፡
ከዚያ ካርቱም ላይ ከሚጠብቃቸው ልጅ ጋር ተገናኝተው፣ ከሌሎች በጐንደር አቋርጠው ከመጡ ሦስት ልጆችም ጋር ተቀላቅለው ሰባት ሆኑ፡፡ በልጁ ቤት አራት ቀናት ቆዩ፡፡ ከዚያ ወደ ሊቢያ ተነሱ፡፡ 28,000 ብርም ተጠየቁ፡፡ ‹‹የተጓዝነው በፒካፕ ሲሆን፣ ደህና ብር የከፈሉት ጋቢና ሌሎቻችን ከ30 በላይ የምንሆን ከኋላ ተጫንን፤›› ይላል፡፡
ለሁለት ቀናት ከተጓዙ በኋላ ሊቢያ ድንበር ላይ የሱዳን ፖሊሶች ይይዟቸዋል፡፡ ፖሊሶቹ ከደላሎች ጋር እያወሩ እንዲከፈላቸው ቢጠይቋቸው አልተስማሙም፡፡ ከዚያ ሦስት ጊዜ አስቁመው ጠየቁአቸውና አልተስማሙም፡፡ ቀጥሎ ወደ ፖሊስ ጣቢያ አስገቡዋቸው፡፡ እስር ቤቱ ውስጥ ብዙ ኤርትራውያንንና ኢትዮጵያውያንን ተመልክተዋል፡፡ አድራሻቸው አዲስ አበባ መሆኑን ተናግረው ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡ አምስት አምስት ጅራፍ ተገርፈው ወጡ፡፡
ከዚያ ለ15 ቀናት ‹‹ጉዳ›› የሚባለው ማረሚያ ቤት ላይ ታሰሩ፡፡ በቀን ሁለት ሁለት ቂጣና የተቀቀለ ምስር ይሰጡዋቸዋል፡፡ ‹‹እዚያ ውስጥ ብዙ ነገር ብዙ ፈተና ይገጥምሃል፤›› በማለት ለመናገር ያዳገተው ነገር እንዳለ ማስተዋል ይቻላል፡፡ ከዚያ ወደ ካርቱም መለሱዋቸው፡፡ ስደተኞች ካምፕ ውስጥ ገቡና ወደ ኢትዮጵያ ኤምባሲ ወሰዱዋቸው፡፡ እነሱም መክረውና የይለፍ ወረቀት ሰጥተው ወደ መተማ መለሱዋቸው፡፡
ልዑል ሰገድ እንደሚለው በዚሁ ጉዞ ላይ ምንም ዓይነት ሕጋዊ መታወቂያም ሆነ ፓስፖርት መያዝ አይቻልም፡፡ ለዚህም ነው መንገድ ላይ አደጋ ሲገጥም ሰው ማንነቱ የማይታወቀው፡፡ ሁለቱ ጓደኞቹ ከመተማ ተመልሰው ወደ ሊቢያ የሄዱ ሲሆን፣ እሱና ጓደኛው ወደ አገራቸው ተመልሰዋል፡፡ አንዱ ጓደኛው ጣሊያን ሲገባ፣ አንዱ ወደ ጣሊያን ለመሻገር መርከብ የሚጠበቅበት ሥፍራ ላይ መሆኑን ነግሮታል፡፡ አሁን የደረሰውን አደጋ እያሰበ ‹‹ለበጐ ይሆናል›› በማለት ታሪኩን ቋጨ፡፡ ዋይታው ግን ቀጥሏል፡

ኣባ ይፍቱኝ(በዉቀቱ ስዩም)

Bewketu Seyoum – Hagere Mariam (Maryland) USA [Must Listen)ኣባ ይፍቱኝ !
ሲኦል ኣለ ሲሉኝ፤ የለም ብየ ክጀ
የባልቴት ተረት ነው፤ በማለት ቀልጀ
ኣውቄ በድፍረት፤ በድያለሁና
ያንጹኝ በንስሃ፤ ያንሱኝ በቀኖና
ሲኦል ከነጭፍራው፤ በጉም ተሸፍኖ
እንዴት ሳላየው ኖርኩ፤ ካጠገቤ ሆኖ?
ኣባ ይፍቱኝ
ሰይጣን ብሎ ነገር፤ የተጭበረበረ
ዋዛ ነው ቧልት ነው፤ ብየ ኣስብ ነበረ
ይሄው እውነት ሆኖ፤ ዋዛና ተረቱ
ባይኔ በብረቱ
ዲያብሎስን ኣየሁት፤ በሸሚዝ ዘንጦ
እልፍ ግዳይ ጥሎ፤ ቸብቸቦ ጨብጦ፡፡
ኣባ
ልክ እንደ ብርሌ ፤ኣጥንት ሲከሰከስ
ኣባይን ኣዋሽን፤ የሚያስንቅ ደም ሲፈስ
ለምለም ፍጥረት ሁላ፤ ወደ ኣመድ ሲመለስ
ልክ እንደ ጧፍ ሃውልት፤ ምስኪኖች ሲጋዩ
ምድጃው ዳር ሆነው፤ ይሄንን እያዩ
ገሃነም ከላይ ነው፤ ብለው መሳትዎ
እስዎ እንደፈቱኝ ፤ እግዚሃር ይፍታዎ

በዚህ ሳምንት የተማርናቸው ሦስት ነገሮች) 1ኛ) “ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ለምን ኬክ አይበሉም?” … 2ኛ) የኢትዮጵያ መንግሥት ሲያፍን እንደ አንበሳ ሲጠብቅ እንደ ሬሳ ኾነ… 3ኛ) ፕሮፌሰር መስፍን ምሁራዊ አይበገሬ ናቸው

habesha in libya1ኛ) “ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ለምን ኬክ አይበሉም?”
ታዋቂው ገጣሚ እና ጸሐፊ በዕውቀቱ ሥዩም ከሦስት ዓመታት በፊት የለንደን ኦሎምፒክን በማስመልከት በተዘጋጀ የሥነ ጽሑፍ ፌስቲቫል ላይ ተሳታፊ ነበር። በጊዜው ካቀረባቸው ግጥሞች መካካል ከፍተኛ ተቀባይነትን ያገኘለት “ኀሠሣ ሥጋ” የተባለው ነበር።
“እልፍ ከሲታዎች ቀጥነው የሞገጉ ፥
በየሸንተረሩ በየጥጋጥጉ፥
“ስጋችን የት ሄደ?” ብለው ሲፈልጉ ፥
አስሰው አስሰው በምድር በሰማይ፥
አገኙት ቦርጭ ኾኖ ባንድ ሰው ገላ ላይ። ”
ግጥሙ በዩናይትድ ኪንግደም እና በሌሎች ያደጉ አገራት ወስጥ ኢ-እኩልነትን በሚመለከት የሚደረገው ክርክር እና የነበረው ጭንቀት በተጧጧፈበት ጊዜ የቀረበ ስለነበር የጊዜውን መንፈስ መያዝ ችሏል። በዚያን ወቅት ኦኩፓይ ዎል ስትሪት ንቅናቄ ናኝቶ ነበር። ከንቅናቄው ዋነኛ ዓላማዎች መካከል አንዱ የኢኮኖሚ ልዩነቱን ከነመዘዙ ለሕዝብ በግልጽ ማሳየት ነበር። አንዳንድ ጊዜ ፊት ለፊታችን ያለ ችግርን በጥሞና መመልከት ያዳግተናል። የበዕውቀቱ ሥዩም ግጥም ይህን ችግር በጣፋጭ እና አጭር ቋንቋ ያስቀምጣል።
የውስጥና የውጭ መሬት ነጣቂዎች እና ጥቂት ከበርቴዎች በተንሰራፉባት ኢትዮጵያ የኢ-እኩልነት እና የኢኮኖሚ መደብን ጉዳይ ማንሳት እና የፖለቲካ ኢኮኖሚ ፍጭት ዋነኛ አካል ማድረግ አግባብነት ያለው ቢኾንም እስካሁን በተገቢው መጠን አልተዳደሰሰም፤ ሙግት አልተደረገበትም። በ1995 ዓ. ም የጀመረው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት ሁሉንም የጠቀመ አይደለም። በርካታ የኢኮኖሚክስ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በእድገቱ የመጀመርያዎቹ ዘጠኝ ዓመታት የታየው አስደንጋጭ የዋጋ ግሽበት የድኻ ሠራተኞችን ኹነኛ ገቢ (real income) ክፉኛ ያዳቀቀ ነበር። በተጨማሪም እድገቱ ከኢንደስትሪያላይዜሽን እና በርካታ ሠራተኞችን ለመቅጠር ከሚችሉ የአገልግሎት ዘርፍ አካላት ጋር የተፋታ በመኾኑ በከተሞች የተንሰራፋውን ሥራ አጥነት ትርጉም ባለው ደረጃ ለመቀነስ እንዳይችል አድርጎታል። እነዚህ እና ሌሎች ምክንያቶች ተደራርበው በተለይ የከተማ ድኾች (urban poor) የእድገቱ ጦስ (development cost) ተሸካሚዎች ኾነዋል “አሁን ተሰውተን ለመጪው ትውልድ ሀብታም አገር ማውረስ” የሚለውን መፈክር ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ኹኔታ አንጻር ስንመረምረው መስዋዕትነቱን እንዲፈጽሙ የሚጠበቅባቸወቅም ኾኑ የተገደዱት የከተማ ድኾች ኾነው እናገኛቸዋለን። በተቃራኒው ይኼን መፈክር ጮኽ ብለው የሚያሰሙት ደግሞ በዋጋ ግሽበት በሰከረ እና በሥራ አጦች በተሞላ ዕድገት ተጠቃሚ የኾኑት ናቸው።
ይህ ግልጽ የኾነ የኢኮኖሚ እውነታ ቢኾንም ለብዙዎች ተሰውሮባቸው ቆይቷል። ነገር ግን ባለፈው ሳምንት በደቡብ አፍሪካ፣ በሊቢያ እና በሜድትራንያን-በኢትዮጵያ ስደተኞች ላይ የደረሰው ሞት እና እንግልት የቀሰቀሰው ብሔራዊ ሐዘን ሳይበርድ መዘራት የጀመረ አንድ አመለካከት አፍንጫችን ሥር ከነበረው የኢ-እኩልነት መዘዝ ጋር እንድንፋጠጥ ያደረገ ነው። የፌስ ቡክ እና ትዊተር ያላሰለሰ ተሳታፊ የኾኑትን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴዎድሮስ አድሃኖምን ጨምሮ በርካታ የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ የአገዛዙ ደጋፊዎች እንዲሁም የመንግሥት የፕሮፖጋንዳ ጣቢያዎች በተደጋጋሚ ካስተጋቧቸው አመለካከቶች አንዱ “ኢትዮጵያውያን ስደተኞች አገር ውስጥ ሠርተው መኖር ሲችሉ ከ40 እስከ 90 ሺሕ ብር እየከፈሉ አደጋ ላይ የሚጥላቸውን የስደት ሕይወት መርጠዋል “የሚል ነው። ነገር ግን ይህ አመለካከት የአገዛዙ ብቻ ነው ብሎ መደምደም ከእውነት የራቀ ነው። በተለይ በተለምዶ የመካካለኛ መደብ አባላት ተብለው የሚጠሩ ገቢያቸው የተደላደለ ኑሮ እንዲኖሩ የሚፈቅድላቸው አንዳንድ ኢትዮጵያውያን ሐሳቡን እንደሚጋሩት በተለያዩ መድረኮች በሚሰጧቸው አስተያየቶች ተስተውሏል።
የዚህ ሐሳብ ዋነኛ ችግር ጥያቄውን መጠየቁ ሳይኾን ‘ ርግጠኝነት የተሞላበት መልስ በቅጽበት ለመስጠት መሞከሩ ነው። ማኅበራዊ ሳይንቲስቶች ኢ-እኩልነት ሲጨምር ሁለት ነገሮች እየተሸረሸሩ እንደሚመጡ ይጠቁማሉ። አንደኛው ማኅበራዊ ንቃት (social consciousness) ነው። ይህ በአንድ ማኅበረሰብ ውስጥ ኾነን በምናደርገው የኢኮኖሚ መስተጋብር ምክንያት የሚፈጠር የጋራ ንቃት ነው። ይህ ንቃት ባልንጀሬነትን እና ወገንተኝነትን የሚያጸና ነው። የኢኮኖሚ መደብ ልዩነት እየሰፋ ሲመጣ እነዚህ ውጤቶች እየኮሰመኑ ይሄዳሉ። ኢ-እኩልነትን የሚሸረሽረው ሁለተኛው እሴት ደግሞ ማኅበራዊ ኅሊና (social conscience) ነው። ይህ ለፍትህ መጨነቅን፣ ራስን ሌላ ሰው ጫማ ውስጥ በማስገባት በበጎ ልቡና ለመረዳት መፈለግን (empathy) ወዘተ ይመለከታል። በዚህ ሳምንት ስደተኛ ኢትዮጵያውያን ላይ የተነሱ ችኩል ጥያቄያዊ ትችቶች የእነዚህ እሴቶች ቀስ በቀስ መሸርሸር ነጸብራቅ ነው። በብድር፣ በመዋጮ እና ጥሪት አሟጠው አገር ለቀው የሚሰደዱ ሰዎች እና ቤተሰቦቻቸውን በጥንቃቄ በመጠየቅ እና በማነጋገር ለመረዳት ከመጣር፣ ሕይወታቸውን ለመመርመር ከመሞከር እና የኑሯቸውን የትርፍ እና የኪሳራ ስሌት መዋቅር (risk and reward structure) በጥሞና ከማጥናት ይልቅ “ኢንፎርሜሽን የላቸውም፣ ተሸውደዋል፣ ያላቸውን ዕድል መጠቀም አልሞከሩም” ወዘተ የሚሉ መረጃ ላይ ያልተመሠረቱ-ከወንድማማችነት፣ ከወገንተኝነት እና ከባልጀሬ መንፈሶች ጋራ የተጻረሩ የሩጫ ፍርዶችን አስተውለናል። ከመደብ ልዩነት ከመነጩ ከእነዚህ ፍርዶች-በ13 ዓመት የእድገት ሂደት ውስጥ እንዲህ ያለውን ክፍፍል ካየን ጥቂት ቆይተን “ለምን ኬክ አይበሉም?” የሚል አሳፋሪ ትችትን ልንሰማ እንችላለን።
yilikal
2ኛ) የኢትዮጵያ መንግሥት ሲያፍን እንደ አንበሳ ሲጠብቅ እንደ ሬሳ ኾነ
የኢትዮጵያን የመንግሥት ሥርዐት ለመረዳት የሚፈልግ ሰው በዚህ ሳምንት የተፈጠሩ ሁለት ነገሮችን እና የእነርሱን ግንኙነት እንደ ምሳሌያዊ ማስተማርያ ሊወስድ ይችላል። የመጀመርያው፦ መንግሥት ሐዘንተኞች ከቁጥጥር ውጪ ወደኾነ ዐመጽ እንዳይገቡ የወሰደው ፈጣን እና ቁርጠኛ ርምጃ ነው። ሁለተኛው፦ የሐዘኑ ምንጭ ለኾነው የኢትዮጵያውን ስደተኞች ጥቃት ዘገምተኛ፣ አሻሚ እና የተዘበራረቀ መልስ መስጠቱ ነው። የመጀመርያውን የተመለከተ የኢትዮጵያን መንግሥት ብቃት (competence) ያስተውላል። ሁለተኛው ደግሞ የአስተዳደሩን ችግሮች አጉልቶ የሚያሳይ ነው። እነዚህ ልዩነቶች ከምን መነጩ? አምባገነን መንግሥታትን የሚያጠኑ የፖለቲካ ሳይንቲስቶች ከሚሰጧቸው መልሶች መካከል አንዱን እነኾ፦
የአምባገነን መንግሥታት ዋነኛ ዓላማ ዕድሜን ማራዘም (survival) ነው። ሌሎች ዓላማዎች ቢኖሯቸውም ሁሌም ከዕድሜ ማራዘም ያነሰ ቦታ ያላቸው ናቸው። ዕድሜ ለማራዘም ደግሞ ዋነኛ ስልታቸው አምባገነናዊ ቁጥጥር (authoritarian control) ነው። የአምባገነናዊ ቁጥጥር ሁለት መሣርያዎች አፈና (repression) እና ደልሎ መማረክ (co-optation) ናቸው። እነዚህ መንግሥታት ሁለቱን መሣርያዎች በጥንቃቄ እና በጥናት አቀናጅተው ይጠቀሙባቸዋል። የሁለቱ ቅንጅት ሚዛን ከጨቋኝ ጨቋኝ ይለያያል። አንዳንድ አምባገነኖች ከአፈናው ቀነስ፣ ከማባበያው ጨመር ያደርጋሉ። ሌሎቹ ደግሞ ወደ አፈና ያዘምማሉ። ለምሳሌ በሶቭየት ሕብረት አምባገነናዊ ቁጥጥር ላይ ጥናት ያደረጉት ዲሚትሪ ገርሸንሰን የቅንጅቱን ሚዛን በተመለከተ በስታሊን እና በብሬዥኔቭ መካከል ያለውን ሰፊ ልዩነት ያትታሉ። የአምባገነኖች ዓላማ ዕድሜን ማቆየት በመኾኑ አገዛዞቻቸው ከሁሉም በላይ ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጧቸው እና የሚያፋፏዋቸው እነዚህን ሁለት የቁጥጥር መሣርያዎች በተግባር የሚያውሉትን ተቋማት ነው። እነዚህ ተቋማት የተሻለ የሰው ኃይል እና ሌሎች እምቅ ሀብቶች (resource) ያገኛሉ፤ ተወርዋሪ እና አዳዲስ ነገሮችን መፍጠር የሚችሉ ይኾናሉ። በረዥም ጊዜ ዕውቀት እና ብልኃት ያከማቻሉ። ቀልጣፋም ይኾናሉ። ይህ ልዩነት ያለው በተቋማት መካከል (inter-institutional) ብቻ ሳይኾን በተቋማት ውስጥም (intra-institutional) ነው። አንዳንድ ተቋማት አምባገነናዊ ቁጥጥርን ከሌሎች ተግባራት ጋር ቀላቅለው ይሠራሉ። እንዲያ ሲኾን ይህን ሥራ የሚሠሩ ዲፓርትመንቶች እና ዴስኮች ከሌሎቹ ይልቅ ልዩ ትኩረት እና ክብካቤ ይደረግላቸዋል።
በዚህ ምክንያት ብዙ አምባገነን መንግሥታት አምባገነናዊ ቁጥጥርን የማይመለከቱ ድንገተኛ ቀውሶች እና ችግሮች ሲገጥሟቸው በዝግጁነት እና በአቅርቦት ችግር ምክንያት ፈጣንና ቁርጠኛ መልስ ለመስጠት ይቸገራሉ። በሜክሲኮ፣ በኒከራጓ፣ በበርማ፣ በግብጽ እና በሶቭየት ሕብረት የተሠሩ ጥናቶች እንደዚህ ዐይነቱን የተቋማት አለመመጣጠን እና የሚያስከትሉትን ችግር ይዳስሳሉ። ሙሉ ለሙሉ አምባገነንነት ውስጥ የተዘፈቀው የኢትዮጵያ መንግሥትም ከአምባገነን ቁጥጥር ውጪ ያልታሰቡ የቤት ሥራዎች ሲደነቀሩበት ቢንገዳገድና ቢውተረተር ሊያስገርመን አይገባም። ያልተዘራ አይታጨድም።
mesfin
3ኛ) ፕሮፌሰር መስፍን ምሁራዊ አይበገሬ ናቸው
የ82 ዓመቱ ማርክሲስት ፈላስፋ ሮበርት ፖል ዉልፍ በሳምንት ሁለት ጊዜ በታዋቂው ብሎጋቸው (The Philosophers Stone) የዘመኑን ፖለቲካዊ ጥያቄዎች እያነሱ የሰላ አስተያየቶች ይሰነዝራሉ። አልፎ አልፎ አወዛጋቢ ሐሳቦችን እያነሱ ተከታዮቻቸውን ያሟግታሉ። በተጨማሪም ግሩም መጻሕፍት ያሳትማሉ። አንዳንድ ጊዜ በየዩኒቨርሲቲው እየዞሩ ሌክቸር ይሰጣሉ። ከሁለት ዓመታት በፊት ሰማንያኛ የልደት በዐላቸውን ሲያከብሩ በአዛውንትነታቸው እንዲህ ያለ ሕይወት (vitality) ያለው የሐሳብ እና የኮሚዩኒኬሽን ኑሮ የሚኖሩበትን ምክንያቶች አቅርበው ነበር። አንደኛ፦ በእርሳቸው ትውልድ ካሉ ጓደኞቻቸው ይልቅ ከወጣቶች ጋር መዋል፤ ሁለተኛ፦ ከዩኒቨርሲቲዎች እና ከሐሳብ መድረኮች አለመራቅ፤ ሦስተኛ፦ ውዝግብን እና ሙግትን አለመፍራት፤ አራተኛ፦ በሶሻል ሚዲያ እና ሌሎች ሚዲያዎች ላይ በንቃት መሳተፍ።
በዚህ ሳምንት ድፍን ሰማንያ አምስት ዓመት የኾናቸው ፕሮፌሰር መስፍን ከሁለተኛው በስተቀር ሌሎቹን የሮበርት ዉልፍ መመርያዎች በሃይማኖታዊ ወኔ የሚከተሉ ናቸው። ሁለተኛውን መመርያም የገደፉት ተገደው እንጂ ፈቅደው አይደለም። 60 ዓመታት ከቆየ የአደባባይ ምሁራዊ ኑሮ በኋላም እንኳ ፕሮፌሰር መስፍን በሐሳብ እና በፖለቲካ ሕይወት ያለመታከት መሳተፋቸውን አላቆሙም። አሁንም ልክ እንደ ቀድሟቸው ይጎነትላሉ፣ ይነቁራሉ፣ ያወዛግባሉ፣ ያበሳጫሉ፣ ያስጨበጭባሉ። ሐሳቦቻቸውንም ይኹን የፖለቲካ አቋሞቻቸውን የሚቃወሙ በርካታ ናቸው። የፖለቲካ ተሳትፏቸው የውጤት ምስክር ወረቀት (scorecard) ቢመረመር በቀይ እስኪሪብቶ የተጻፉ ብዙ ውጤቶች ይገኛሉ። አሜሪካዊው ታላቅ ዳኛ ጀስቲስ ኦሊቨር ዌንደል ሆልምስ እንደሚሉት የምሁር ሕይወት “በማያቋርጥ የጥይት እሩምታ መካከል ውስጥ ኾኖ ማሰብ ነው” ፤ አንዳንዴ ጥይቱ ያቆስላል። ሕይወት ያለው ምሁር ቁስሉን ሲያክ እና ሲደባብስ አይቆይም። በፍጥነት ተነስቶ ወደ ፍልሚያው ይመለሳል። ዕድሜ ሲገፋ እንዲህ ዐይነቱ ጽናት እና ጉልበት እየቀነሰ ይመጣል። ለምሁራዊ ኑሮ መልካም ዋጋ የሚሰጡ ማኅበረሰቦች የአዛውንት ምሁራንን ጉልበት ለመደገፍ እና ጽናታቸውን ለማደስ ብዙ ነገሮች ያደርጋሉ። በዩኒቨርሲቲዎች፣ በጥናት ተቋማት እና በሚዲያዎች ተቀማጫ ፌሎው (resident fellow) እየተደረጉ ከወጣት ምሁራን እና ከተማሪዎች ጋራ ንቁ መስተጋብር እንዲያደርጉ ዕድል ይመቻችላቸዋል። በኮንፈረንስ እና በየሌክቸሮች ይጋበዛሉ። የምርምር ረዳቶች ተመድበውላቸው መጽሐፍ ይጽፋሉ። ፖለቲከኞች እና ፖሊሲ አውጪዎችን ያማክራሉ። ፕሮፌሰር መስፍን ይኼን ማጣታቸው ብቻ ሳይኾን በሐሳባቸውን እና በፖለቲካ ተሳትፏቸው ምክንያት በአዛውንትነታቸው ዘብጥያ ከመውረድ አንስቶ ብዙ እንግልት አስተናግደዋል። ከእነዚህ ገደቦች እና ጫናዎች ጋር ተገዳድረው በጋዜጣ፣ በመጽሔት፣ በመጻሕፍት፣ እና በማኅበራዊ ሚዲያዎች መሳተፋቸውን ቀጥለዋል። ይህን ጽናታቸውን ለማድነቅ የአይዲዮሎጂያቸው ወይም የሐሳቦቻቸው ደጋፊ መኾን አያስፈልገንም። ሕይወት ላለው ምሁራዊ ኑሮ ጽዋችንን እናነሳለን፤ ለፕሮፌሰር መስፍን ደግሞ መልካም ልደት!!

የ“ቆንጆ” መፅሄት ባለቤት ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ካሳ አገር ጥሎ ተሰደደ

20887_443039482529535_42744021382446654_nላለፉት አራት ዓመታት ለንባብ ሲበቃ የቆየው የ“ቆንጆ” መፅሄት ባለቤትና ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ካሳ አገር ጥሎ ተሰደደ፡፡ ጋዜጠኛው በተለያዩ ጊዜያት የመንግስት ደህንነቶች ቢሮው ድረስ በመሄድ ዛቻና ማስፈራራት ስላደረሱበትና ጉዳዩ ከአቅሙ በላይ በመሆኑ አገሩን ጥሎ ለመሰደድ መገደዱን እንደነገራቸው ምንጮቹ ገልፀዋል፡፡ የደህንነት ኃይሎች በየጊዜው ወደ ቢሮው እየሄዱ “ክስና እስር ይጠብቅሃል” እያሉ ያስፈራሩት እንደነበር የተገለፀ ሲሆን፤ ፕሬሱን የሚወነጅል ዘጋቢ ፊልም በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን እየተሰራ ስለመሆኑ፣ ዘጋቢ ፊልሙ ከሚሰራባቸው የህትመት ውጤቶች አንዱ “ቆንጆ” መጽሄት እንደሆነ መረጃ እንደደረሰውና ደህንነቶቹ በየጊዜው እየተመላለሱ የሚያደርሱበትን ጫና መቋቋም ባለመቻሉ አገር ጥሎ መሰደዱን ምንጮቹ ጠቅሰዋል፡፡ በመፅሄቱ ሰራተኞቹ ላይ በተለያዩ ጊዜያት ፍተሻዎች የሚደረጉ ሲሆን፤ ደህንነቶች በቅርቡ ቢሮ ውስጥ በመግባት የተለያዩ መረጃዎችን የያዘ ፍላሽ ዲስክ ሀርድ ዲሰኮች እና ሌሎች ሰነዶችን በኃይል ቀምተው መውሰዳቸውን ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ካሳ ተናግሯል፡፡
ጋዜጠኛው ከዚህ በፊት ምንም ነገር ቢመጣ ከአገሩ ሳይወጣ በፅናት ለመቆየት እንደሚፈልግ ይናገር የነበረ ሲሆን፤ በአሁኑ ሰዓት በቀደመው ፅናቱ የሚያስቀጥል ሁኔታ ስላላገኘ አገሩን ጥሎ መሰደዱን ተናግሯል፡ መፅሄቱ ከተመሰረተ አራት ዓመታት ያስቆጠረ ሲሆን የመፅሄቱ ባለቤትና ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ካሳ ከሀገር ከመሰደዱ በፊት 100ኛ እትሙን ለንባብ ማብቃቱ ታውቋል፡፡ ጋዜጠኛው ላለፉት 13 ዓመታት በጋዜጠኝነት ሙያ ላይ መቆየቱን ከተጨማሪ መረጃዎች ለማወቅ ተችሏል፡፡

ክርክር 6፡ ኢህአዴግ እና 1997 ስብርባሪዎች!!!! -ግርማ ሠይፉ ማረ

Girma Seifu Maruበዛሬው ሰድስተኛ ዙር የምርጫ ተብዬ ክርክር ጉዳዩ በመሰረተ ልማት ላይ ያተኮረ ነው፡፡ ኢህአዴግ ጎምቱ ያላቸውን ሹሞቹን ለክርክር ይዞ የቀረበበት ቢሆንም ለእኔ ግን ትኩረቴን የሳበው የተከራከሩበት ርዕስ ሳይሆን ተከራካሪዎቹ ሰዎች እና ፓርቲዎች ናቸው፡፡ ማለት የፈለኩት የመሰረተ ልማት በሚል ርዕስ ክርክር ስመለከት የተገነዘብኩት ጉዳይ ቢኖር ኢህአዴግ ክርክር እያደረገ ያለው የዛሬ አስር ዓመት ለሚዲያ ክርክር ድመቅት ይሰጥ ከነበረው ከቅንጅት ስብርባሪ ጋር አንደሆነ ተረዳሁኝ፡፡ ህብረትም ቢሆን አሁን በመድረክ በኩል በድሮ ግርማ ሞገሱ አይታይም፡፡ እውነቱን ለመናገር አሁን በክርክሩ ላይ የሚገኙት ሰዎች ኢህአዴግ በልኩ የሰራቸው፤ በእግራቸው ገመድ የተበጀላቸው ጭምር ናቸው፡፡ ምንም ቢሉ ማንም ምንም የማይሰማቸው፡፡
ኢዴፓ በ1997 ከተቀናቃኙ መኢህአድ ጋር ያለውን የውስጥ ግብ ግብ ቅንጅት የሚባል ፓርቲ እውን እንዳይሆን በማድረግ፣ አንድ አንዶቹን በግል ታሪካዊ የፖለቲካ ዋጋ አስከፍሎ አሁን ባለበት ደረጃ ይገኛል፡፡ ይህ የኢዴፓ አመራር ውሳኔ ኢትዮጵያ ሀገራችንም በመድበለ ፓርቲ ስርዓት ግንባታ ዋጋ እየከፈለች እንድትገኝ አድርጓል፡፡ በሁለት ሺ ሰባት ምርጫ ኢዴፓ እንደ ፓርቲ መንግሰት እንደማይሆን ቢታወቅም ወደፊት ፓርቲስ ይሆናል ወይ? የሚል ጥያቄ ሁሉ ማንሳት የግድ የሚል ነው፡፡ ይህ በፍፁም ሟርት አይያደለም በምድር የሚታይ ሀቅ ነው፡፡ ለማነኛውም ኢዴፓ የዛሬ አሰር ዓመት በ1997 ክርክር የቅንጅት ፈርጥ ሆኖ ክርክሩን ያደመቀ ቢሆንም ዛሬ ይህን ሊያደርግ አልተቻለውም፡፡ ኢህአዴጎች በጥርስና ጥፍራቸው ቅንጅትን ሲያፈርሱ ያተረፉት ሽራፊ ኢዴፓ አሰር ዓመት አፈር ልሶ መነሳት ሳይችል ቀርቷል፡፡ አሁንም በምድር ላይ እየዳከረ ይገኛል፡፡
ኢዴፓ ማህተም አላደርግም በማለት ያፈረሰውን ቅንጅት ቢያንስ በፍረስራሽ በቅጡ እንዳይሰራ ያደረገው ደግሞ አቶ አየለ ጫሚሶ ነው፡፡ መቼም ይህን ሰም የማያውቅ ያለ አይመስለኝም፡፡ “ቅንጅት”  በአቶ አየለ ጫሚሶ ተወክሎ ቅንጅት ቢመረጥ እንዲህ ያደርጋል ይህን ይፈጥራል ሲሉን እኛ የምናወቀው የ1997 ቅንጅት የሌለ መሆኑን፤ የፈለግነው ቅንጅት እንዳይኖር የተሰራው “ቅንጅት” እንኳን ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚጠቅም አጀንዳ አይደለም እንደ ድርጅትም ቁመናውን አስተካክሎ የሚሄድ እነዳልሆን እናውቃለን፡፡ እውነቱን ለመናገር እነርሱም በሚዲያ ቀርበው አይተናቸዋል፡፡ ለማነኛውም ይሉሹን በሰማሽ ገበያ ባልወጣሽ የሚባለው የዚህ ዓይነቱ ድርጊት ነው፡፡ የቅንጅት ምልክት የነበረው ሁለት ጣት አሁንም “ቅንጅት” ለሚባው ድርጅት ቢሰጥም በተግባር ግን በስራ ላይ እንደሌለ ይታወቃል፡፡ ትዝ ይላችሁ እንደሆን “ጣት እንቆርጣለን” እስክንባል ድርስ ይህች አስማተኛ ምልክት የዛሬ አስር ዓመት የሰራቸው ስራ በእውነት ግሩም ድንቅ ነበር፡፡ የእኛን ቅንጅት ነብስ ይማር ብለናል፡፡
መድረክ አሁን ባለው ቁመና የ1997 ህብረት ሰዎች በተወሰነ ደረጃ ቢይዝም ህብረትን የሚያክል አይደለም፡፡ በነገራችን ላይ ከምርጫ በኋላ ቅንጅት የሚባል እንዳይኖር የአሁኖቹ መድረኮች ያላቸው ጥላቻ ቀላል አይደለም፡፡ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ አሁንም ቢሆን ከቅንጅት መንፈስ ጋር ግብ ግብ ላይ እንዳለ ማወቅ የፈለገ የ1997 ጫወታ አንስቶ መሞከር ነው፡፡ በሌሎቹም የህብረት አባል ድርጅቶች እሰከ ፓርላማ የደረሰ ደባ በቅንጅት ላይ እንደሚሰራበት የሚታወቅ ነው፡፡ የዚህ ደባ ባለቤቶች አሁንም የመድረክ አባሎችና አመራሮች ናቸው፡፡ መድረክ አንድነትን ከሚጠላበት አንዱ ምክንያት በአንድነት ውስጥ የሚታየው የቅንጅት መንፈስ ጭምር ነው፡፡ የአሁኖቹ አመራሮች ከአንድነት ጋር ሲነነጋገሩ የሚሰማቸው ሰሜት በ1997 ህብረት ሆነው ከቅንጅት ጋር የሚያደርጉት ውይይት/ክርክር ነው፡፡ በክርክሩ ውስጥ ሁሌም ጠልፉ መጣል አለ!! የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ልዬ ችሎታ፡፡
አሁን ደግሞብ በብረት ሰንሰለት ተይዞ የሚገኘው ሰማያዊ ፓርቲ ነው፡፡ ሰማያዊ የት ድረስ ይጓዛል? አላውቅም፡፡ ሰማያዊ ፓርቲም ቢሆን የቅንጅት አብዛኛውን አመራርና አባል ይዞ የተመሰረተው አንድነት ፓርቲ ስባሪ ነው፡፡ ስለዚህ የቅንጅት አካል እንደነበር ማወቅ ያስፈልጋል፡፡  በሁለት ሺ ሁለት ምርጫ አንድነትን ምርጫው ላይ ውጤታማ እንዳይሆን ከኢህአዴግ ባልተናነሰ ገትረው የያዙት ልጆች ሳይዘገዩ በአምስተኛ ዓመቱ የምርጫ ፈተና ከኢህአዴግ ጋር እንዴት እንደሆነ እየቀመሱት ነው፡፡ በሆነ ባልሆነው ሰማያዊ የሚለው መንግሰትም ከሰማያዊ አልላቀቅ ብሎ ምን ሊያደርግ እንደሚችል እየተጠበቀ ነው፡፡ የኢህአዴግ ትልቅ ግብ በዚህ ምርጫ መንግሰት መመስረት የሚመስለው ካለ ተሳስቷል፡፡ ሰማያዊን ለማዋረድ ነው የሚሰራው፡፡ በኢቲቪ በሰማያዊ ላይ የተያዘው ዘመቻ የአንድ አንድ የህግ ባለሞያዎች ተብዬ አስተያየት ጥፍራችን ውስጥ እንድንደበቅ የሚያደርግ ነው፡፡ እረ በህግ መባል ያለባቸው ናቸው፡፡
ሌሎች ተሳታፊ ፓርቲዎችን ትተን ከላይ የዘረዘርናቸው ፓርቲዎችን ስንመለከት ኢህአዴግ የዛሬ አስር ዓመት ሰንገው ይዘውት ከነበሩ አሁን ግን ምንም ማድረግ ከማይችሉ ደካማ ስብርባሪ ፓርቲዎች ጋር ተራ ገብቶ እየተጫወተ ነው፡፡ ሁሌም እንደምለው ኢህአዴግ ብጤዎቹን በትክክል መርጦዋል፡፡ ከዚህ ከፍ ያለ ጫወታ አይችልም፡፡ ከዚህ ከፍ ካለ ኢህአዴግ ቀልድ አያውቅም ለሰፊው ህዝብ ጥቅም ሲል ታንክም ባንክም ለመጠቀም ወደኋላ የሚል አይደለም፡፡ አሁን ለጊዜው በቁጥጥር ስር ያሉ ሚዲያዎች እና ሆዳሞች ይበቁታል፡፡ ታንክ አያስፈልግም ማለቴ ነው፡፡ ሚዲያና ሆዳሙን ለመጥቀም ያህል ባንክ ይጠቀም ይሆናል፡፡
ቸር ይግጠመን!!!!!

ማሰር፣ ማሽበር፣ ማወክ የማይሰለቸው ግፈኛ አገዛዝ – ግርማ ካሳ


ገዢው ፓርቲ ሕወሃት/ኢሕአዴግ ማሻሻያዎች አድርጎ ለብሄርዊ መግባባት ራሱን እንዲያዘጋጅ ከተለያዩ ማእዘናት ጥሪ ቀርቦለታል። የሕሊና እስረኞችን እንዲፈታ በተደጋጋሚ ተጠይቋል። ሆኖም አገዛዙ እንኳን ሊሰማ እንደዉም በጣም እየባሰበት መጥቷል። ዜጎችን በማሰርና በማሸበር የሚረካው አገዛዝ ዛሬም በወገኖቻችን ላይ የሰቆቃ በትሩን እየያሳረፈ ነው።
በሊቢያ ለሚገኙ ወገኖቻችን አስቸኳይ ድጋፍና እርዳታ እንዲያደረግ እየተለመነ ያለው አገዛዙ ትኩርቱ ሕይወት ማዳን ላይ ሳይሆን በዜጎችን ላይ ስቃይ ማድረስ ሆኗል።
የሚሊዮኖች ድምጽ ንቅናቄ በፍቼ ሰልፍ ባደረገበት ወቅት በደህንነት አባላት ደም በደም እስኪሆን ድረስ የተደበደበውና የተሰባባረው መሳይ ምትኩ ፣ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ታማሚ ሆኖ በቤቱ ነበር የሚቀመጠው። «ከዚህ በፊት ተጎድቻለሁ፣ ትግሉ ይቅርብኝ» ሳይል ትግሉን ቀጠለ። ለምን አገሩን የሚወድ ነጻነትን የተጠማ በመሆኑ።
በቅርቡ ሕወሃት/ኢሕአዴጎች እንደገና አፈኑት። በማእከላዊ ተወረወረ። በዚያ ቶርቸር እየተደረገ እንደሆነም መረጃዎች ይጠቁማሉ።
በማእከላዊ እሥር ቤት በኤሌቲክ ገመድ ስይቀር እስረኞችን እንደሚገረፉ በቅርቡ የዞን ዘጠኙ ናትናኤል ፈለቀ ለጆን ኬሪ በጻፈው ደብዳቤ ገልጿል።
የረቡን ታሪካዊ ሰልፍ ተከትሎ ወይንሸት ሞላን ጨምሮ በርካታ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ታስረዋል። ወይንሸት ሞላ ስትታሰር ይሄ ሶስተኛ ጊዜ መሆኑ ነው።
sntayehu
ዛሬ ደግሞ ወንድም ስንታየው ቸኮልን አፍነዉታል። ስንታየው ድብቅ ነገር አይወድም። ንግግሩ ቀጥተኛ ነው። ሐሳቡን የመሰለዉን ከመናገር ወደ ኋላ የማይል ነው። ሞትና መታሰርን በጭራሽ የማይፈራ ፣ አገሩን የሚወድ ጀግና ኢትዮጵያዊ ። እርሱ በመታፈኑ፣ በዜጎች ስቃይ የሚደሰቱ እንደመሆናቸው፣ አሳሪዎቹ ሊደሰቱ ይችሉ ይሆናል። በሺሆች የምንቆጠር የትግል አጋሮቹ ደግሞ ልናዝን እንችላለን። ከስንታየው ጋር ወዳጆች ነን። ስለ ስንታየሁ ብዙ አወቃለሁ። አንድ ነገር አስረግጬ የምናገረው ነገር ቢኖር፣ ስንታየው ለአገርና ለህዝብ ሲል መታሰርን እንደ ትልቅ ጸጋና ክብር የሚቆጠር፣ ወኔና ጀግንነት የተሞላ ኢትዮዮጵያ ካፈራቻቸው ብርቅዬ ታጋዮች መካከል አንዱ መሆኑን ነው።
ገዢው ፓርቲ ማስሩን ባጠናከረ ቁጥር በፖለቲክ መክሰሩን፣ በሐሳብ መሸነፉን፣ መዉደቂያው መቃረቡን እያመላከተ ነው። ተስፋ እየቆረጠ ነው።
ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ስንታየው ቸኮሎች፣ ወይንሸት ሞላዎች፣ መሳይ ምትኩዎች አሏት። «ታጋይ ቢሞት ትግል አይሞትም» ነበር የሚባለው። ታጋይ ቢታሰርም ትግል አይታሰርም። ብርቱካን ሚደቅሳን አሰሩ፤ እነ አንዱዋለምን፣ እነ ርዮት አለሙን ተነሱ ። እነ አንዱዋለምን ሲታሰሩ እነ ሃብታሙ ፣ ዞን ዘጠኞች ተነሱ። እነ ሃብታሙ ሲታሰሩ ደግሞ እነ መሳይ ምትኩ እነ ስንታየሁ ተነሱ። የሕዝብ መሰረታዊ የለዉጥ ጥያቄን በኃይል ማፈን በጭራሽ አይቻልም።

Discusion on Ethio Immigrants in Libya, Yemen, S Africa Oslo 26 04 2015 ...

Discusion on Ethio immigriants in Libya Yemen South Af Oslo 26 04 2015 ...

Monday, April 27, 2015

በባህር ዳር መስቀል አደባባይ እና የህዝብ ተቋማት መፍረሳቸው ተረጋገጠ

Bahir Dar 2ባለፈው ታህሳስ 2007 ዓ.ም በባህር ዳር ከተማ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሀይማኖት ተከታዮች ሀይማኖታዊ በዓላትን የሚያከብሩበት (በተለይ ጥምቅትና መስቀል በዓላትን) ስፍራ መስቀል አደባባይ በከፊል እና የተለያዩ የህዝብ ተቋማት ‹‹ለመንገድ ልማት›› በሚል ሊፈርሱ ይችላሉ መባሉን ተከትሎ የከተማዋ ህዝብ ለተቃውሞ ወጥቶ ዜጎች በመንግስት ታጣቂዎች መገደላቸው የሚታወስ ሲሆን፣ እነዚህ ህዝብ የሞተላቸው ተቋማትና የሐይማኖት ቦታ ከሰሞኑ መፍረሳቸው እርግጥ መሆኑን የነገረ ኢትዮጵያ ዘጋቢ በቦታው ተገኝቶ በመመልከት አረጋግጧል፡፡
በከተማዋ ከአዝዋ ሆቴል እስከ ግዮን ሆቴል በሚወስደው መስመር የሚገኙት የባህር ዳር የህዝብ ቤተ-መጽሐፍት ሙሉ ለሙሉ፣ የባንክ ስራ የሚሰራበት እድሜ ጠገብ ህንጻ ሙሉለሙሉ፣ እና የህዝቡ ተቃውሞ ዋና ምክንያት የሆነው መስቀል አደባባይ በከፊል ፈርሰዋል፡፡ የከተማዋ ማዘጋጃ ቤት እና ሙሉዓለም የባህል ማዕከል ደግሞ አጥሮቻቸው እንዲፈርሱ ሆኗል፡፡
የነገረ ኢትዮጵያ ዘጋቢ በስፍራው ተገኝቶ ያነጋገራቸው የከተማዋ ነዋሪዎች እንደሚገልጹት ከተማ አስተዳደሩ እነዚህን የህዝብ ተቋማት ሲያፈርስ ዙሪያ ገባውን በፌደራልና በክልሉ ፖሊስ አጥሮና የሚቆረጡ ዛፎችንና ሌሎች ፍርስራሾችን በፖሊስ መኪና ብቻ እያጓጓዘ ነው፡፡ ይህም አስተዳደሩ ከፍተኛ የጸጥታ ስጋት ውስጥ ሆኖ ተቋማቱን ማፍረሱን ያመለክታል ይላሉ ነዋሪዎቹ፡፡
ታህሳስ ወር ላይ ተቀስቅሶ በነበረው የህዝብ ተቃውሞ ወቅት የባህር ዳር ከተማ ከንቲባ አቶ ላቀ አያሌው ‹‹ህዝብ ያልፈለገውና በተቃውሞ ድምጽ ያሰማበት ፕሮጀክት ተፈጻሚ አይሆንም፤ ስለዚህ ካልፈለጋችሁ ይቀራል›› በሚል ህዝቡን ለማረጋጋት መሞከራቸው የሚታወስ ሲሆን፣ አሁን ግን ህዝቡ ይሁንታ ሳይሰጣቸው ወደማፍረስ መግባታቸው ተመልክቷል፡፡
አስተዳደሩ ህዝቡን በኃይል እያስፈራራ ነው የሚሉት የከተማዋ ነዋሪዎች፣ የፌደራል ፖሊስ መስቀል አደባባይ ጎን በሚገኘው ሁለገብ የወጣቶች ማዕከል ውስጥ ከትሞ በተጠንቀቅ መቀመጡን ለንግግራቸው እንደ ዋቢ ያነሳሉ፡፡ ይህን የነዋሪዎችን ጥቆማ በማስመልከት ወደ ወጣት ማዕከሉ ያመራው የነገረ ኢትዮጵያ ዘጋቢም የፌደራል ፖሊስ አባላት በማዕከሉ በብዛት እንደሚገኙ ማረጋገጥ ችሏል፡፡
ዘገባው የነገረ ኢትዮዽያ ነው።

አይኤስን ለማውገዝ በተጠራው ሠልፍ ከፖሊስ ጋር በተፈጠረው ግጭት በርካቶች ታስረው ተፈቱ

9c43080680d37654411f246864041403_Lሠልፉን በዋነኝነት በጥብጠዋል የተባሉ ተለይተው ጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸዋል
-ሰማያዊ ፓርቲ መንግሥት ስሜን እያጠፋ ነው አለ
በሰሜን አፍሪካዊቷ ሊቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ አሰቃቂ ግድያ የፈጸመውን የአይኤስ የሽብር ቡድን ድርጊት ለማውገዝ፣ ሚያዝያ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. በመስቀል አደባባይ በወጡ የሠልፍ ታዳሚዎችና በፖሊሶች መካከል በተፈጠረው
ግጭት ከ900 በላይ ተሳታፊዎች ታስረው ተፈቱ፡፡ ሠልፉን በዋናነት በመበጥበጥ በሠልፈኞችና በፖሊስ አባላት ላይ ጉዳት አድርሰዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎች ተለይተው የ14 ቀናት ጊዜ ቀጠሮ በፍርድ ቤት ተጠይቆባቸዋል፡፡
አይኤስን የማውገዙ ሥነ ሥርዓት ሊጠናቀቅ ሲል ጩኸት፣ ስድብና ድንጋይ ውርወራ ሲጀመር የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት በወሰዱት ዕርምጃ በዕለቱ በሺዎች የሚቆጠሩ በቁጥጥር ሥር የዋሉ ቢሆንም፣ ማምሻውን እየተለዩ በሠልፉ ውስጥ ብቻ በመገኘታቸው ብቻ አብረው የታሰሩ ናቸው የተባሉ መለቀቃቸው ታውቋል፡፡
ብጥብጡ እንደተጀመረ ድንጋይ ውርወራ ስለነበር የሠልፉ ተሳታፊዎች ቁጥራቸው ባይታወቅም የተፈነከቱ፣ እግራቸው በከፍተኛ ሁኔታ የተጎዳ፣ የተወሰኑ ወጣቶች ደግሞ ራሳቸውን ስተው የወደቁ እንደነበሩና ፖሊሶችም በሩጫ የደረሱባቸውን በዱላ ሲዠልጡ እንደነበር በግርግሩ ወቅት ለማየት ተችሏል፡፡
በተለይ በአይኤስ የሽብር ቡድን አባላት አሰቃቂ ግድያ ከተፈጸመባቸው ኢትዮጵያውያን መካከል የሁለቱን ወጣቶች፣ የወጣት ኢያሱ ይኩኖአምላክና የወጣት ባልቻ በለጠን ስም እየጠሩ ከፍተኛ ተቃውሞአቸውን በመንግሥት ላይ ሲያሰሙ የነበሩ ወጣቶች፣ ተቃውሞአቸው ሙሉ በሙሉ በመንግሥትና ፊት ለፊታቸው በሚያዩዋቸው የፖሊስ አባላት ላይ ከመሆኑም በተጨማሪ፣ በድንጋይ ውርወራ የተጀመረው ግጭት አስፈሪ ነበር፡፡
በሺዎች የሚቆጠሩ የሠልፉ ተሳታፊዎች በትንሿ ስታዲየም፣ በቂርቆስ፣ በለገሀር፣ በአምስተኛ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ በአራዳ፣ በኮተቤ፣ በላምበረትና በሌሎችም ቦታዎች መታሰራቸውን የገለጹ ቢሆንም፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንም ሆነ የፌዴራል ፖሊስ ግን ከመግለጽ ተቆጥበዋል፡፡ ሪፖርተር የታሳሪዎቹን ቁጥር፣ ጉዳት የደረሰባቸውን የተሳታፊዎች ብዛትና የተጎዱ የፖሊስ አባላት፣ እንዲሁም በአንዳንድ ወገኖች እየተነገረ የሚገኘውን የአንድ ሠልፈኛ ‹‹ሞት›› የተባለውን ለማጣራት ያደረገው ጥረት ባይሳካም፣ ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የፖሊስ አባላት ስለሁኔታው አስረድተዋል፡፡
የሁሉም ኢትዮጵያውያን (በአገር ውስጥም ይሁን ከአገር ውጭ ያሉትን) ልብ የነካ ሐዘን ተከስቶ፣ ሁሉም ቁጭቱንና ሐዘኑን በሚገልጽበት ቀን ወደሌላ ብጥብጥ ማምራቱ እንዳሳዘናቸው የገለጹት የፖሊስ አባላቱ፣ በዕለቱ በርካታ ሰዎች ብጥብጡ ውስጥ ሲሳተፉ የተያዙ ቢሆንም፣ እየተጣራ በዕለቱ አብዛኛዎቹ መፈታታቸውን አስረድተዋል፡፡ ቁጥራቸው ከ900 በላይ የሚሆኑ በየክፍለ ከተማቸው በሚገኙ ፖሊስ ጣቢያዎች የተበተኑ መሆናቸውን፣ ፍርድ ቤት ቀርበውም ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን አባላቱ ገልጸዋል፡፡
በዕለቱ በሠልፉ የተሳፉና የተጎዱ ቢኖሩም፣ በአንድ ሰው ላይ ብቻ ከፍተኛ ጉዳት ከመድረሱ በቀር ቀሪዎቹ ከሚወረወር ድንጋይ ለማምለጥ ሲሯሯጡ እርስ በርሳቸው ተጠላልፈው በመውደቅ የተጎዱ ቢሆንም፣ ከፍተኛ ጉዳት እንዳልደረሰባቸው ገልጸዋል፡፡ የሞተ ሰው ግን አለመኖሩን አባላቱ ተናግረው፣ አስፈላጊ ከሆነም የሚመለከተው ተቋም [ዳግማዊ ምንሊክ ሆስፒታል] ሊጠየቅ እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡
በዕለቱ ከተሳታፊዎቹ በተወረወረ ድንጋይ ሰባት የአዲስ አበባና የፌዴራል ፖሊስ አባላት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው በሕክምና ላይ መሆናቸውን፣ ሌሎችም ሲቪል የለበሱ የፖሊስ አባላትም ጉዳት እንደደረሰባቸው አስረድተዋል፡፡
ለብጥብጡ መነሳት ወይም ሆን ብለው መንግሥትና ሕዝብ እንዲጋጭ በር ከፋች መሆናቸው ተረጋግጦባቸዋል የተባሉ ከ16 በላይ ተጠርጣሪዎች ተለይተው፣ ለብቻቸው በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መታሰራቸው ተጠቁሟል፡፡ ከእነዚህ ተጠርጣሪዎች ውስጥ አንዷ በቅርቡ ከካናዳ የመጣች መሆኗም ታውቋል፡፡
በዋና ተጠርጣሪነት የታሰሩትም ሆነ በየክፍላተ ከተማው ተበትነው የታሰሩት ላይ፣ ፖሊስ ፍርድ ቤት አቅርቦ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ የጠየቀባቸው ቢሆንም፣ በየክፍላተ ከተማው ያሉት አብዛኛዎቹ መፈታታቸው ተጠቁሟል፡፡
በዕለቱ በሠልፈኞቹና በፖሊስ መካከል የተፈጠረውን ግጭት አስመልክቶ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር አቶ ሬድዋን ሁሴን በሰጡት መግለጫ፣ አንዳንድ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሆን ብለውና ሲዘጋጁ ከርመው ብጥብጡን የሚያስነሱ ጥቂት ሰዎችን ማዘጋጀታቸውን መግለጻቸው ይታወሳል፡፡ የአቶ ሬድዋንን መግለጫ ተከትሎ ሰማያዊ ፓርቲም በዕለቱ መግለጫ አውጥቷል፡፡
የተወካዮች ምክር ቤት የጠራውን ሰላማዊ ሠልፍ በመደገፍ አባላቱ በሠልፉ ላይ እንዲገኙ ጥሪ ማስተላለፉን አስታውሶ፣ ጥሪውን መሠረት በማድረግ አመራሮቹና አባላቱ ገና ወደ መስቀል አደባባይ በመሄድ ላይ እያሉና በሠልፉ ላይም ከተገኙት ውስጥ እየተለቀሙ መታሰራቸውን ፓርቲው አስታውቋል፡፡
በርካታ ዜጎች በቁጭትና በሐዘን የተገኙ ተሳታፊዎች ተቃውሞአቸውን ‹‹ንግግር በሚያደርጉ›› ሰዎች ላይ በመግለጻቸው፣ መንግሥት ፕሮግራሙን በችኮላ እንዲጠናቀቅ ማድረጉን የገለጸው ሰማያዊ ፓርቲ፣ ለሕዝብ ተቃውሞና ቁጣ ተገቢውን ምላሽ መስጠት የማይወደው መንግሥት፣ በዜጎች ላይ የወሰደው ዕርምጃ እንዳሳዘነውና እንደሚያወግዘውም አስረድቷል፡፡
‹‹መንግሥት ሠልፍ ተጠርቶ በወጣው ሕዝብ ላይ የወሰደውን ዕርምጃ ለመካድና የሕዝብን ከፍተኛ ተቃውሞ ለመደበቅ፣ እንዲሁም የሕዝብን ቁጣና ሐዘንን የሰማያዊ ፓርቲ የፖለቲካ አጀንዳ እንደሆነ አድርጎ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጽሕፈት ቤት መግለጫ ማውጣቱ አሳዛኝ ነው፤›› ብሏል፡፡
‹‹መንግሥት በዜጎች ላይ በተደጋጋሚ የሚያሳየውን ቸልተኝነት በተቃወሙ ዜጎች ላይ የወሰደው የጭካኔ ዕርምጃ ሳያንስ፣ ከአንድ የፖለቲካ ድርጅት ጋር አዛምዶ ተቃውሞአቸውን ማጠልሸት ትክክል እንዳልሆነና ከመንግሥት የማይጠበቅ ስህተት ነው፤›› በማለት ሰማያዊ ፓርቲ በመግለጫው አስታውቋል፡፡
በሰላማዊ መንገድ የሥልጣን ሽግግር እንዲካሄድና የአመፅና የጦርነት አዙሪት እንዲከስም፣ ጭቆናን ተቋቁሞ የሚያደርገውን ትግል ለማኮላሸት መንግሥት መሞከሩ፣ የከፋ አደጋ እንዳለው ለማስገንዘብ እንደሚወድ ሰማያዊ ፓርቲ በመግለጫው አካቷል፡፡
የአይኤስ የሽብር ቡድን ድርጊትን ለማውገዝ የተወካዮች ምክር ቤት በጠራው ሠልፍ ላይ ለመሳተፍ ሲወጡ፣ በሠልፉ ውስጥ እያሉና የታሰሩትን ሊጠይቁ ሲሄዱ የታሰሩ አባላቱ የድርጅት ጉዳይ አባል ወይንሸት ሞላ፣ የ2007 አገራዊ ምርጫ ለተወካዮች ምክር ቤት የምርጫ ተወዳዳሪ ጠና ይታየው፣ የፓርቲው አባል ኤርሚያስ ሥዩም፣ የቂርቆስና የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተባባሪዎች ማስተዋል ፍቃዱና ዳንኤል ተስፋዬ፣ የአዲስ አበባ ምርጫ ጉዳይ ኮሚቴ ሕዝብ ግንኙነት ቴዎድሮስ አስፋው፣ በ2007 ምርጫ ለተወካዮች ምክር ቤት አባልነት ተወዳዳሪ እስክንድር ጥላሁንና ሌላው የተወካዮች ምክር ቤት ተወዳዳሪ ይድነቃቸው አዲስ እንደታሰሩበት አስታውቋል፡፡ በሠልፈኞቹ ላይ እስር፣ እንግልትና አሰቃቂ ድብደባ የፈጸሙና ትዕዛዝ ያስተላለፉ አካላት ለፍርድ እንዲቀርቡ እንደሚጠይቅም ሰማያዊ ፓርቲ ገልጿል፡፡
ምንጭ – ሪፖርተር

አማርኛ ቋንቋ የማይችሉ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ችግር ለመቅረፍ ምን እየተሠራ እንደሆነ ጥያቄ ቀረበ

amharic_flagከተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች የሁለተኛ ደረጃና የመስናዶ ትምህርታቸውን ጨርሰው ለዩኒቨርሲቲ ብቁ ሆነው የሚገቡ ተማሪዎች፣ የአገሪቱ የሥራ ቋንቋ የሆነውን አማርኛን በቅጡ የማያውቁ እየሆኑና ቁጥራቹውም እየጨመረ በመምጣቱ፣ ወደፊት ሊፈጥረው የሚችለውን ችግር ከመቅረፍ አኳያ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ምን እያከናወነ እንደሆነ ተጠየቀ፡፡
ሚንስትሩ ዶ/ር ሽፈራው ተክለ ማርያም የስምንት ወራት የሥራ አፈጻጸማቸውን ባለፈው ማክሰኞ ለፓርላማው ካቀረቡ በኋላ፣ ከምክር ቤቱ አባላት ማብራርያ የሚሹ ጥያቄዎች ቀርበውላቸዋል፡፡
ከቀረቡላቸው ጥያቄዎች መካከል ከላይ የተገለጸው አማርኛ ቋንቋ የማይችሉ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ቁጥር መጨመር ሊፈጥረው የሚችለውን ችግር በመቅረፍ ረገድ ሚኒስቴሩ ምን እያደረገ እንደሆነ፣ ወይም ምን ዓይነት መፍትሔ ሊሰጠው እንደሚችል የኢሕአዴግ አባል የሆኑት የፓርላማ ተመራጭ አቶ መሐመድ አብዶሽ ጥያቄ አቅርበውላቸዋል፡፡
አቶ መሐመድ በፓርላማው የግብርናና የአካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ናቸው፡፡ በኅብረ ብሔራዊ የፌዴራል ሥርዓት ግንባታ ውስጥ አንድ የፌዴራል ሥርዓቱ ቋንቋ መሆኑን የገለጹት አቶ መሐመድ፣ ባለፈው ዓመት ክረምት ወቅት በመላ አገሪቱ ከሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ጋር በተደረገ ውይይት ተማሪዎቹ ያረጋገጡት ታች ያለው ተማሪ አማርኛ ቋንቋ መናገር አለመቻሉን እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡
ተማሪዎቹ ወደ ዩኒቨርሲቲ መጥተውም በአማርኛ ቋንቋ ፈጽሞ መግባባት አለመቻላቸውን ጠቅሰው ጥያቄያቸውን በሚያደረጁበት ወቅት፣ ሌሎች የምክር ቤቱ አባላት ያሰሙት መጠነኛ ማጉረምረም ንግግራቸውን ለአፍታ ያህል ገታ እንዲያደርጉ አስገድዷቸዋል፡፡
ይሁን አንጂ አቶ መሐመድ ወደ ጥያቄያቸው በመመለስ ለችግሩ ትኩረት መስጠት ያለበት ምክንያት ናቸው ያሏቸውን ነጥቦች አብራርተዋል፡፡
‹‹በመንግሥት የረዥም ጊዜ ፕሮግራም በኢትዮጵያ አንድ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ማኅበረሰብ መፍጠር ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ደግሞ ብሔራዊ ቋንቋን ማወቅና በቋንቋው ማግባባት መቻል ወሳኝ ድርሻ አለው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ እነዚህ ወጣቶች የከፍተኛ ትምህርታቸውን አጠናቀው ወደ አገር ግንባታ ሥራ በሚገቡበት ወቅት ቢያንስ የፌዴራል ቋንቋውን መቻል አለባቸው፤›› ብለዋል፡፡
በእርግጥ የቀድሞ ሥርዓቶች በየማኅበረሰቡ ላይ ያደረሱት የመብትና የማንነት ረገጣ ተፅዕኖ ውጤት ሊሆን እንደሚችል የጠቆሙት የፓርላማው አባል፣ በክረምቱ ውይይት ወቅት ተማሪዎቹ እንዳስረዱት በየክልላቸው ከመጀመርያ ደረጃ ትምህርት ቤት ጀምሮ አማርኛ ቋንቋ እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት እንደሚሰጣቸው ማረጋገጣቸውን ጠቁመዋል፡፡
‹‹አሥራ ሁለት ዓመት የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ተምረዋል፡፡ ነገር ግን ምንም አያውቁም፡፡ ታዲያ ይህ ወደፊት አንድ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ማኅበረሰብ ለመፍጠር በምናደርገው ጥረት ላይ ተፅዕኖ አይኖረውም? ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ችግሩን ለመቅረፍ ምን እየሠራ ነው? ምንስ አስቧል?›› የሚል ጥያቄዎችን አቅርበዋል፡፡
ለቀረበው ጥያቄ ምለሽ የሰጡት ሚንስትሩ ዶ/ር ሽፈራው ተክለ ማርያም፣ ‹‹የፌዴራል መንግሥት የሥራ ቋንቋ እንዳለው ሁሉ ክልሎችም የራሳቸውን ቋንቋ መወሰን እንደሚችሉ ይታወቃል፡፡ ነገር ግን በእነዚህ ውስጥ ያሉ መስተጋብሮችን በተሟላ መንገድ አስተሳስሮ መሄድ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው፤›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡
‹‹ስለዚህ ከችግሩ ስፋትና ጥልቀት በየትኞቹ አካባቢ በስፋት የሚታይ ችግር ነው? ችግሩ ካለስ እንዴት ነው የሚፈታው? የሚባለውን በራሱ መድረክ ስናይ በሚመለከታቸው አካላት ውይይት ሊደረግባቸው ይችላል፤›› ብለዋል፡፡
ጉዳዩን በተመለከተ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የአዲስ አበባ ዮኒቨርሲቲ መምህራንና ተማሪዎች ችግሩ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሁሉም ካምፖሶች የሚታይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ይሁን እንጂ ተማሪዎቹ በመጨረሻዎቹ የዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው በአማርኛ መግባባት ችለው የሚወጡ በመሆናቸው ለችግሩ እስከዛሬ ተገቢውን ትኩረት ሰጥተውት እንደማያውቁ ገልጸዋል፡፡

Sunday, April 26, 2015

አደጋ ላይ ነን!! አደጋ ላይ ነን!!

አደጋ ላይ ነን!!ካስደነገጥኳችሁ አዝናለሁ ግን በጣም መደንገጥ አለባችሁ፡፡በመላው የአዲስ አበባ የመንግስት ሁለተኛ ደረጃ ትምርህት ቤቶች ማለት ይቻላል በነSave The Children ፊት አውራሪነት እየተሰጠ ያለው የግብረሰዶማዊነት ትምህርት ተጠናክሮ እየቀጠለ መሆኑን ሳረዳችሁ ከፍተኛ ሀዘን እየተሰማኝ ነው፡፡እስካሁን ከ40 በላይ የሚሆኑ የአዲስ አበባ ት/ቤቶች ውስጥ ለውስጥ በአንድ ክፍለ ጊዜ በ120 ብር በተቀጠሩ የየትምህርት ቤቱ የባዮሎጂና የአይሲቲ መምህራን አማካኝነት እየተሰጠ ነው፡፡ሁለት አይነት ነው ትምህርቱ፡፡Life Skill (ላይፍ እስኪል) እና Comprehensive Sexuality Education (ከምፕሬኤንሲቭ ሴክሽዋሊቲ ኤጁኬሽን) የሚባሉ፡፡በሁሉም ትምህርት ቤቶች የመጀመሪያ ዙር ስልጠናው አልቋል፡፡ሁለተኛ ዙሩ የተግባር ትምህርት ነው፡፡ በቪዲዮና በተግባር እንቅስቃሴ የተደገፈ፡፡ ከሚሰጡት ትምህርቶች መካከል FREE KISSING (በፍሪ ኪሲንግ) እና MASTERBATION (ማስተርቤሽን)የሚባሉ የልቅ ወሲብ አይነቶች አሉበት፡፡ ልቅ ስል በ FREE KISSING (በፍሪ ኪሲንግ) ጊዜ ጾታ ሳይለይ የፈለጉትን ደፍሮ መሳም ሲሆን በ MASTERBATION (ማስተርቤሽን) የሚለው ደግሞ ሴቶችም ወንዶችም በቪዲዮ የታገዘ የ Pornography (የፖርኖ) ፊልሞች እያዩ እንዲተገብሩት የታሰበ ነው፡፡ ለዚህም አላማ ከየትምህርት ቤቱ ጎበዝ የተባሉ ተማሪዎች ተመርጠው ተዘጋጅተዋል፡፡
ጉዳዩ እስከ ትምህርት ሚኒስተርና ቢሮ ቢደርስም እስካሁን መልስ ሊሰጡ አልቻሉም፡፡አንዳንድ የክፍለ ከተማ ሀላፊዎች እንዳሉት እነSave The Childern (ሴቭ ዘቺልድረን) በኢትዮጵያ የተለያዩ ስራዎች ስለሚሰሩልን አቁሙ ብንላቸው ግንኙነታችን ይበላሻል፡፡በላይ አመራሩም ዘንድ ያለው እሳቤና አቋም ይሄ ነው ብለዋል፡፡የተከበራችሁ የአዲስ አበባና በመላው ኢትዮጵያ የምትገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ፤ ወላጆች ፤ቤተሰቦች ይህ የምነግራችሁ ነገር ተራ አሉባልታ አለመሆኑን በተለያየ ጊዜ ለማሳያ የተለጠፉ መረጃዎችን አይታችሁ መፍረድ ትችላላችሁ፡፡ የተከበራችሁ ተማሪዎች ወላጆች እና በዚህ ጉዳይ እንደ እኔ የተንገበገባችሁ ሁሉ አደጋ ላይ ነን፡፡በተለይ ድርጅቶቹ ነገሩን እንዲሰሩላቸው የመረጧቸውን ሰዎች ለመግዛት እያወጡት ያለው ምራቅ የሚያስውጥ ገንዘብ በየክፍሉ ከሚያስተምሩላቸው መምህራንና ከተባባሪ የትምህርት ቤት አስተዳደሮችም አልፎ እስከ ላይ ድረስ ኪስ ሳያሞቅ አልቀረም፡፡ የእናንተ እርዳታ ቆፍጠን ያለ ውሳኔ ያስፈልጋል፡፡
ተማሪዎችና ወላጆች በአዲስ አበባ በብዛት የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ላይ ቢያነጣጥርም ነገሩ በኦሮሚያ፣ በአማራና በሌሎች ክልልሎች ግን እስከ ታችኛው ክፍል ድረስ በስነተዋልዶ፣በጸረኤድስና በስርአተ ጾታ ሰበብ የግብረሰዶማዊነት ትምህርት እየተሰጠ መሆኑን ሳረጋግጥላችሁ በአውነት ነው፡፡ ስለዚህም ተማሪዎች፣ ወላጆች የሚመለከታችሁ ሁሉ አይናችሁን ወደ ትምህርት ቤት አንሱ!! ተማሪዎች በገንዘብ በተደለሉ ግለሰቦች እተረጨባቸው ያለውን መርዝ አስቁሙ፡፡በተለይ በአሁኑ ወቅት አስረኛና አስራ ሁለተኛ ክፍሎች ትምህርት በጨረሱበት ጊዜ እየሆነ ያለው ተማሪዎችን በክረምት ትምህርትና ስልጠና ሰበብ ለዚህ ተግባር እየመዘገቡ ያሉ ትምህርት ቤቶች እንዳሉ ልነግራችሁ እችላሁ፡፡ሴቭ ዘቺልድረን በክረምት ወራት ትምህርት ቤቶችን በክረምት ትምህርት አሳቦ በመከራየት የሰዶማዊነት ትምህርት ሊሰጥ መሆኑን ስነግራችሁ ያለምንም ጥርጥር ነው፡፡አስካሁን የግብረሰዶማዊነት ትምህርት ሁለተኛ ዙር ለመስጠት ፈቃደኛ ሆነው ካሉ ትምር ቤቶች መካከል፡ ሚኒሊክ፤መድሀኒአለም፣ባልቻ አባነፍሶ፣ኤስኦኤስ፣ህዳሴ፣አፍሪካ ህብረት፣የካቲት 23 ፣መነን፣አየርጤና እና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡ይህ ነገር ሀሰትነው ብላችሁ የምትጠራጠሩ ከሆነ በተለይ ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች በተለይ ወላጆች አንደኛ በየክፍለ ከተማ የሚገኙ የስርአተ ጾታ ሀላፊዎችን ፣በአዲስ ትምህርት ቢሮ በተለይ አቶ ሀይለ ስላሴ የተባሉ የስራ ሀላፊን መጠየቅ ይቻላል፡፡በተጨማሪም በኢትዮጵያዊነት ድምጽ ላይ የተለጠፉ የመማሪያ ሰነዶችን ማየት ይቻላል፡፡ወላጆች ልጆቻችሁን አድኑ!!
የተከበራችሁ ተማሪዎች በየትኛውም አጋጣሚ በትምህርት ቤትም ሆነ ከትምህርት ቤት ውጪ በስነተዋለዋልዶና ስርአተ ጾታ ስም የሚሰጠውን ፍጹም የግብረሰዶማዊነት ትምህርት አንማርም ንድትሉ ብትሉም እራስን የማዳንና የመከላከል ተግባርና እርምጃ መሆኑን አውቃችሁ በዚህ ተግባር ላይ የተሳተፉ መምህራንም ሆኑ በገንዘብ ተደልለው ሊያስተምሩ የተዘጋጁ ተማሪዎችን አምርራችሁ እንድታገሉ ሁላችንም በፈጠረን አምላክ ስም እለምናቿለሁ!!
ኢትዮጵያ የግብረሰዶማዊነት መቀበሪያ ትሆናለች እንጂ መቼም ከግብረሰዶማዊነት ጋር አትጋባም!!
ጭንቀት ካደረበት መምህር

በጣም አስደንጋጭ ዜና .. ይህንን አስቸኳይ መልዕክት ሼር በማድረግ በየመን ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን እንዲደርስ እናድርግ!! በጣም አስደንጋጭ ዜና .. ይህንን አስቸኳይ መልዕክት ሼር በማድረግ በየመን ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን እንዲደርስ እናድርግ!!

በጣም አስደንጋጭ ዜና .. ይህንን አስቸኳይ መልዕክት ሼር በማድረግ በየመን ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን እንዲደርስ እናድርግ!!በጣም አስደንጋጭ ዜና ነው። ነገሩ እውነት ከሆነ በጣም ያስፈራል። ከሰሞኑ ሲያስጨንቀኝና አእምሮየን ረፍት ሲነሳው የነበረ ስጋት። የ ISIS ወደ የመን መግባት። በጦርነት የፈራረሱ አገራትን እንደ ምሽግ ተጠቅሞ ሰይጣናዊ የሽብር እንቅስቃሴውን እየፈጸመ የሚገኘው የ ISIS ቡድን ዛሬ የመን ሰንአ መግባቱን አወጇል። አውሬዎቹ ISIS ሶች ዛሬ በለቀቁት የ 9 ደቂቃ ቪዲዮ የሁቲ አማጽያንን አንገት ልንቆርጥ የመን ገብተናል ሲሉ ዝተዋል። ዝርዝሩን ከታች ያስቀመጥኩት ሊንክ በመጠቀም አንብቡት።
ስለዚህ ከዛሬ ጀምሮ በየመን የሚኖሩ አያሌ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን ከመቼውም ጊዜ በላይ ጥንቃቄ መውሰድ መጀመር ይኖርባቸዋል። እግዚኦ! ከስቃይ ላይ ሌላ ስቃይ ፈታኝና አስፈሪ ጊዜ እየመጣብን ነው። በየመን ደራሽ ላጡት ወገኖቻችን ደህንነት ተግተን መጸለያችንን አናቋርጥ!! በየመን የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ነቅታችሁ ራሳቸውን ጠብቁ አደራ። ቢቻል በሕብረት እና በአንድነት የምትኖሩበትንና የምትንቀሳቀሱበትን መንገድ አመቻቹ። በተለይ ደግሞ ለአደጋ ሊያጋልጡ ወደ ሚችሉ አስፈሪ ቦታዎች እንዲሁም ወደ ገጠራማ አካባቢዎች ከመንቀሳቀስ ታቀቡ። እናንተም ለጥንቃቄ ይጠቅማቸዋል የምትሉትን መልዕክት ሼር በምታደርጉበት ጊዜ አስቀምጡላቸው።

Saturday, April 25, 2015

በወይንሸት ሞላ ላይ የሀሰት የሰው ምስክር እንደቀረበባት ተሰማ በወይንሸት ሞላ ላይ የሀሰት የሰው ምስክር እንደቀረበባት ተሰማ

በወይንሸት ሞላ ላይ የሀሰት የሰው ምስክር እንደቀረበባት ተሰማመንግስት አይ ኤስ አይ ኤስ በኢትዮጵውያን ላይ የወሰደውን እርምጃ ለመቃወም በጠራው ሰልፍ ላይ ገና ሰልፉ ሳይጀመር ‹‹ለምርመራ እንፈልግሻለን›› ተብላ በደህንነቶች ከተያዘች በኋላ የታሰረችው ወይንሸት ሞላ ላይ ደህንነቶች ‹‹ሁከትና ብጥብጥ ስትፈጥር አይተናል፡፡›› ብለው እንዲመሰክሩ ሁለት የሀሰት የሰው ምስክሮች እንዳቀረቡባት ለማወቅ ተችሏል፡፡ ወይንሸት ከታሰረች ጀምሮ ደህንነቶች ሌሊት ሌሊት ከፍተኛ ምርመራ እንደሚያደርጉባትም ታውቋል፡፡
ወይንሸት ሞላ በትናንትናው ዕለት ፍርድ ቤት ቀርባ 6 ቀን የተቀጠረባት ሲሆን ደህንነቶች ያቀረቡባት የሀሰት የሰው ምስክሮች በሚቀጥረው ፍርድ ቤት ስለመቅረብ አለመቅረባቸው የታወቀ ነገር የለም፡፡
ነገረ ኢትዮጵያ

ኢህአዴግ የሞቱትን ወገኖች ክብር እያራከሰ ነው ሲል ሰማያዊ ወቀሰ ኢህአዴግ የሞቱትን ወገኖች ክብር እያራከሰ ነው ሲል ሰማያዊ ወቀሰ

ኢህአዴግ የሞቱትን ወገኖች ክብር እያራከሰ ነው ሲል ሰማያዊ ወቀሰነገረ ኢትዮጵያ /
• ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ ጉዳዩን በዝምታ አያልፈውም›› አቶ ዮናታን ተስፈዬ
ኢህአዴግ አይ ኤስ አይ ኤስን ለመቃወም በሚል በሚጠራቸው ሰልፎች ሰማያዊን በማውገዝ ላይ መጠመዱንና ይህንም ሰማያዊ ፓርቲ በዝምታ እንደማያልፈው የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት አቶ ዮናታን ተስፋዬ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡ ትናንት ሚያዝያ 15/2007 ዓ.ም በባህርዳር፣ ሆሳና እና ሌሎች የሀገሪቱ ከተሞች መንግስት በጠራው ሰልፍ ሰልፈኞቹ አይ ኤስን ሳይሆን ሰማያዊ ፓርቲን የሚያወግዙ መፈክሮችን ይዘው እንደወጡ የታወቀ ሲሆን አብዛኛዎቹ ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ ደም ከማፋሰስ ተግባሩ መቆጠብ አለበት›› የሚሉ መፍክሮችን ይዘው ወጥተዋል፡፡ 
ይህ የሆነው አዲስ አበባ ውስጥ መንግስት የጠራው ሰልፍ ላይ ሰልፈኞች መንግስት ለችግሩ አፋጣኝ ምልሽ አልወሰደም በሚል ተቃውሞ ካሰሙ በኋላ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ሚኒስትር አቶ ሬድዋን ሁሴን ገና ፖሊስ ምርመራውን ሳይጨርስ ተቃውሞውን ያሰማው ሰማያዊ ፓርቲ ነው ብለው ከወነጀሉ በኋላ ፓርቲያቸው የያዘው አቋም እንደሆነ ኃላፊው ገልጾአል፡፡ አቶ ዮናታን ይህን የኢህአዴግ አቋምም ‹‹እጅግ አሳፋሪና አፀያፊ ነው›› ብሎታል፡፡ የባህርዳርና የሆሳና ሰልፈኞች ሰማያዊ ፓርቲን ለማውገዝ በያዟቸው መፈክሮች ፊታቸውን እንደሸፈኑ የገለፀው አቶ ዮናታን ሰልፈኞቹ በኢህአዴግ ተገድደው እንጅ አምነውበት እንዳልወጡ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡
መንግስት ለችግሩ አፋጣኝ መፍትሄ መስጠት ሲያቅተው የሚነሱበትን ተቃውሞዎች ሰማያዊ ፓርቲና ድምጻችን ይሰማ የፈጠሯቸው አድርጎ መወንጀሉ ለስርዓቱም ሆነ ለሀገሪቱ አደጋ የሚፈጥር ነው ያለው አቶ ዮናታን ለአይ ኤስ አይ ኤስ ተብሎ የተጠራውን ሰልፍ ለራሱ የፕሮፖጋንዳ ፍጆታ ማዋሉ የሞቱትን ወገኖቻችን ክብር የሚያረክስ፣ ርካሽና ፀያፍ ፕሮፖጋዳ ነው ሲል ወቅሷል፡፡
ኢህአዴግ እንደ መንግስት መስራት ያለበትን ባለመስራቱ የሚነሱበትን ተቃውሞዎች ለመሸፈን እና አጀንዳ ለማስቀየስ ሲል በሰማያዊ ላይ እየፈጠራቸው ያሉትን ውንጀላዎች ፓርቲው በዝምታ እንደማያልፋቸውና ክስ እንደሚመሰርትም አቶ ዮናታን ገልጸዋል

በአርመኞች ላይ የተደረገው የዘር ማጥፋት ዕልቂትን እናስታውስ፣ – ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም በአርመኞች ላይ የተደረገው የዘር ማጥፋት ዕልቂትን እናስታውስ፣ – ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

በአርመኞች ላይ የተደረገው የዘር ማጥፋት ዕልቂትን እናስታውስ፣ – ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያምየጸሐፊው ማስታዋሻ፡ በአሁኑ ጊዜ ቱርክ እየተባለች በምትጠራው ሀገር ከ100 ዓመታት በፊት በዛሬው ሳምንት እ.ኤ.አ ሚያዝያ 24/1915 በአርሜኒያ ዜጎች ላይ የተፈጸመው የዘር ማጥፋት ፍጅት በዓለም አቀፍ ደረጃ ሲታወስ ይኖራል፡፡ ያ የዘር ፍጅት የኦቶማን ግዛት/Ottoman Empire ዋና መቀመጫ በነበረችው እና ኮንስታንቲኖፕል (እ.ኤ.አ በ1923 ኢስታንቡል ተብላ በተሰየመችው) ተብላ ትጠራ በነበረችው ከተማ ውስጥ በአርሜኒያ ምሁራን፣ የክርስትና ኃይማኖት እምነት ተከታዮች፣ የትምህርት ሰዎች፣ በጸሐፊዎች፣ በማህበረሰብ መሪዎች እና በሌሎች ታዋቂ በነበሩ የማህበረሰብ ስብስቦች ላይ ተጀመረ፡፡
ከአንድ ክፍለ ዘመን በላይ ኢትዮጵያን ሀገራቸው አድርገው ይኖሩ በነበሩ አርሜናውያን ላይ እ.ኤ.አ በ1915 የተፈጸመውን የዘር ማጥፋት ፍጅት ለማስታወስ በሚል ይህንን ትችት እየጻፍኩ ያለሁት ጥቂት አርሜናውያን ኢትዮጵያን ሀገራቸው አድርገው ሲኖሩ የቆዩ በመሆናቸው ምክንያት አይደለም፡፡ እንደዚሁም በወጣትነት ዘመኔ ኢትዮጵያዊ አርሜናውያን የትምህርት ቤት ጓደኞች የነበሩኝ በመሆኑ ምክንያት አይደለም ይህንን ትችት እየጻፍኩ ያለሁት፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በተማሪዎች እና አርሜናውያን፣ የኢትዮጵያ አርሜናውያን ወይም ደግሞ የአርሜናውያን ቅርስ በመኖሩ ምክንያት አይደለም፡፡
በአሁኑ ጊዜ የአርሜናውያንን የዘር ማጥፋት ዕልቂት የማስታውስበት እንዲህ የሚል ቀላል እና ግልጽ የሆነ የማሳመኛ አመክንዮ አለኝ፡ በዓለም ላይ በሀያኛው ክፍለ ዘመን እ.ኤ.አ ሚያዝያ 24/1915 ለመጀመሪያ ጊዜ በተፈጸመው የዘር ማጥፋት ዕልቂት እና ወደ 1.5 ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎች ላለቁበት ሰይጣናዊ ድርጊት የዓለም ህዝብ ቁጣ ቢኖር ኖሮ፣ እንዲሁም ይህንን ዕኩይ ድርጊት በአርሜናውያን ህዝቦች ላይ በፈጸሙት ጭራቆች ላይ ተጠያቂነት ቢኖር ኖሮ፣ የማያዳግም ህጋዊ እርምጃ ቢወሰድ ኖሮ እ.ኤ.አ ሚያዝያ 7/1994 ያ ጭራቃዊ ድርጊት በዚሁ ወር ከተፈጸመ ከ79 ዓመታት በኋላ ወደ 1 ሚሊዮን አካባቢ በሆኑ የሩዋንዳ ህዝቦች ላይ የዘር ማጥፋት ዕልቂት አይፈጸምም ነበር የሚል እምነት አለኝ፡፡
በአንደኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በአርሜናውያን ላይ በተፈጸመው የዘር ማጥፋት ዕልቂት የዓለም ህዝብ ቁጣውን ቢገልጽ ኖሮ፣ ያንን የመሰለ ጭራቃዊ ድርጊት በፈጸሙት ሰይጣኖች ላይ ተጠያቂነት ቢኖር ኖሮ የማያዳግም ህጋዊ እርምጃ ቢወሰድባቸው ኖሮ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት በሰው ልጆች ላይ ያንን የመሰለ አሰቃቂ ዕልቂት ይፈጸማል የሚል እምነት የለኝም፡፡ ሂትለር ያንን ዕኩይ ድርጊት በመመልከት በፖላንድ እና በሌሎች የምስራቅ አውሮፓ ሀገሮች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን ለመፍጀት የሚያስችለው አድርጎ በመቁጠር እንደ ጥሩ አጋጣሚ ተጠቅሞበታል፡፡ እ.ኤ.አ ሕዳር 24/1945 የለንደን ጊዜ/The Times of London የተባለው ጋዜጣ እ.ኤ.አ ሂትለር ነሀሴ 1939 ፖላንድን ከመውረሩ በፊት ያ እብሪተኛ አምባገነን ቆጥቋጭ የሆነ ንግግር አድርጎ እንደነበር ዘግቧል፡፡ ሂትለር እንዲህ በማለት አውጆ ነበር፣ “ጥንካሪያችን ያለው በእኛ ፍጥነት እና የጨካኝነት መጠን ነው…ደካማው የአውሮፓ ስልጣኔ ስለእኔ ስለሚያስበው ነገር ጉዳዬ አይደለም…ትዕዛዝ ሰጥቻለሁ፣ እናም አንድ ቃል በመሰንዘር ትችት አቀርባለሁ የሚል ማንም ቢሆን ይገደላል… ስለሆነም ለጊዜው የእኔን ገዳይ ኃይሎች ብቻ ወደ ምስራቅ በማዝመት ያለምንም ርህራሄ ወይም ደግሞ ሀዘኔታ ሁሉንም የፖላንድ ዘሮችና እናቋንቋውንም የሚናገሩ ሁሉንም ወንዶች፣ ሴቶች እና ልጆች እንዲገድሉ ልኪያቸዋለሁ፡፡በአሁኑም ጊዜአርሜናውያንን መፈጀት በመናገር ላይ ያለ ማን ነው?“ (አጽንኦ ተሰጥቷል፡፡)
የሂትለር ጥያቄ እንዲህ የሚል ቀላል መልስ አለው፡ ሁሉም በዓለም ዙሪያ በሚገኙ ጨዋ ሰዎች ላይ ኢሰባዊ የሆነ ድርጊት ሲፈጸምባቸው እና እ.ኤ.አ ከ1915-1923 በአርሜናውያን ህዝቦች ላይ ሲፈጸም የነበረው ዓይነት ሰይጣናዊ ድርጊት የሚቃወሙ ሁሉ በመናገር ላይ ይገኛሉ። ደግሞም ሰው ለሰው ልጅ ተኩላ ነው የሚለዉን መርህ የሚቃወሙም ስለ አርመኖች አልቂት ይናገራሉ;
የአርሜኒያ እና የኢትዮጵያ ታሪካዊ ትስስር፣
በኢትዮጵያ እና በአርሜኒያ መካከል የነበረው ግንኙነት ከክርስቶስ ልደት በኋላ የአክሱም ግዛት በኢትዮጵያ ከተመሰረተ ከመጀመሪያው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የነበረ ነው፡፡ ከ19ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ አካባቢ ጀምሮ በኦቶማን ግዛት ስቃይ እና መከራ ይደርስባቸው የነበሩ ጥቂት የአርሜኒያ ቡድኖች ሽሽት በማድረግ ወደ ኢትዮጵያ ገብተው ነበር፡፡ ጥቂት የታሪክ ባለሙያዎች እንደሚሉት እ.ኤ.አ በ1895 በኦቶማኖች ይፈጸም በነበረው ዕልቂት ምክንያት በኢትዮጵያ የነበሩት የአርሜኒያ ማህበረሰቦች ብዛት በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ መጥቶ እንደነበር ይገልጻሉ፡፡ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት የነበሩት ዮሐንስ 4ኛ በኦቶማን ገዥዎች እንግልት እና ስቃይ ይደርስባቸው የነበሩት አርሜናውያን ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት መኖር እንደሚችሉ ግብዣ ያቀርቡ ነበር፡፡ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት በአዲስ አበባ 50 አርመኖች ይኖሩ ነበር፡፡ አርመኖች፣ የወርቅ ማዕድን አንጥረኞች፣ ነጋዴዎች እና የስነህንጻ ባለሙያዎች እንደነበሩ ይነገርላቸዋል፡፡ እንደሚቀርቡ ዘገባዎች ከሆነ እ.ኤ.አ በ1905 የአርሜኒያ-ታታር (አዘርባዣ) ዕልቂትን ተከትሎ በርካታ አርመናውያን ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸው ይነገራል፡፡
እ.ኤ.አ በ1923 ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ስላሴ እየሩሳሌምን ጎበኙ፡፡ በእየሩሳሌም አርመኖች በሰፈሩባቸው አካባቢዎች በመንቀሳቀስ ላይ በነበሩበት ጊዜ 40 አባላትን ያካተተ የሙዚቃ ቡድን ሙዚቃዎችን በማቅረብ ላይ እንዳለ ተመለከቱ፡፡ እነዚህ የሙዚቃ ቡድኑ አባላት በዘር ማጥፋት ፍጅት ወላጆቻቸውን ያጡ እንደነበሩ ተገነዘቡ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ እነዚያ ወላጅ አልባ ልጆች ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ ችግር እንዳለባቸው በመገንዘብ የጡት ልጅ በማድረግ ለማሳደግ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ ፈቃዳቸውን ገለጹ፡፡ ለዚህም ከአርመኖች ጳጳስ ፈቃድ አገኙ እና ተመልሰው ወደ ኢትዮጵያ ይዘዋቸው መጡ፡፡ እነዚህ ወጣት ወንዶች በኋላ “አርባ ልጆች“ በመባል ይታወቁ ነበር፡፡ በጊዜ ሂደት የንጉሱ የሙዚቃ ተጫዋች ቡድን ሆኑ፡፡ የዚህ የሙዚቃ ቡድን መሪ የነበረው ኬቮርክ ናልባንዲያን ኢትዮጵያ ሆይ በሚለው የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት ኢትዮጵያ ደስ ይበልሽ በሚል የተፈሪ የሙዚቃ ማርሽ ላይ የሚሳተፈውን የአርሜኒያን ወጣት ቡድን በማንቀሳቀስ ረገድ ትልቅ ዕውቅና የተሰጠው ሰው ነበር፡፡ ያ የሙዚቃ ቡድን እ.ኤ.አ ሕዳር 2/1930 አጼ ኃይለ ስላሴ የዘውድ ንግስ በዓላቸውን ሲያከብሩ ተዘጋጅቶ የቀረበ ነበር፡፡ ያ ብሄራዊ የሙገሳ ሙዚቃ እ.ኤ.አ በ1974 ወታደራዊው አምባገነን መንግስት ስልጣን እስከሚይዝ ድረስ ያገለግል ነበር፡፡ (የዚያን የሙዚቃቡድን የመሳሪያ ቅንብር ሙዚቃ ለማዳመጥ እዚህ  ይጫኑ፡፡) የአርመኖች የመጀመሪያው ቡድን እና ልጆቻቸው ውጤታማ፣ ስኬታማ እና በኢትዮጵያ በልዩ ልዩ የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊ እና ባህላዊ ተግባራት ላይ በታማኝ ዜግነት ተሰማርተው ያገለግሉ ነበር፡፡
በታሪክ የኢትዮጵያ እና የአርመን ክስርትና እምነት ተከታዮች በዓለም ላይ 2ኛው የክርስትና እምነት ቤተክርስቲያን የምስራቅ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አካል ናቸው፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ከብዙ መቶ ዓመታት በፊት በአርመኖች እና በኢትዮጵያውያን መካከል የትምህርት ግንኙነትን በመፍጠር የእውቀት የልውውጥ መድረክ ተከፍቶ ነበር፡፡ “በአርሜኒያ የፊደላት ዕድገት ላይ የኢትዮጵያ ተጽዕኖ“ በሚል ርዕስ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ መጽሔት (ቮል. 1፣ ቁጥር 1) ተዘጋጅቶ በቀረበ መጽሔት ላይ አየለ በከሬ እንዲህ በማለት የክርከር ጭብጣቸውን ያቀርባሉ፣ “የሁለቱን ሀገሮች የጽሁፍ ስርዓት በምንመረምርበት ጊዜ ልዩ የሆነ ምሁራዊ እና ባህላዊ ጥናቶችን ይገልጻል፡፡“
በርካታ የኢትዮጵያ አርመኖች እ.ኤ.አ በ1974 የደርግ ወታደራዊ አምባገነን መንግስት ስልጣን በተቆናጠጠበት ጊዜ ንብረቶቻቸውን በመውረስ ከሀገር እንዲባረሩ ተደርገዋል፡፡ አብዛኞቹ ወደ ዩኤስ አሜሪካ እና ወደ ካናዳ ሄደዋል፡፡
ስለአርሜኒያ የዘር ማጥፋት ፍጅት ውዝግብ እና ስለማይካደው እውነታ፣
እ.ኤ.አ ከ1915-1923 ባሉት ዓመታት ውስጥ በኦቶማን መንግስት በአርመኖች ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሞ ነበርን?
እ.ኤ.አ ከ1915-1923 ድረስ ባሉት ዓመታት መካከል በኦቶማን ቱርክ ስር በነበሩት አርመኖች ላይ ምንድን ነገር ነበር የተደረገው?
እ.ኤ.አ በ1915 በአንደኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ የኦቶማን ግዛት መፈረካከስ በሚጀምርበት ጊዜ የቱርክ አመራሮች በምስራቁ ግዛት የሚገኘው አናሳው የአርመን የክርስቲያን ህዝብ ከራሽያ ጋር በመቀላቀል እነርሱን ሊወጋቸው እንደሚችል ቱርኮች ስሌታቸውን ሰርተው ነበር፡፡ የቱርክ ባለስልጣኖች አስቀድሞ ለማጥቃት ዝግጅት በማድረግ አርመኖችን ማጋዝ እና መጠነ ሰፊ የሆነ ግድያን ጨምሮ ስልታዊ የሆነ የማሰቃየት ድርጊት እንዲፈጸምባቸው ትዕዛዝ ሰጡ፡፡ በኦቶማን ቱርኮች ወታደሮች እና ፖሊሶች አማካይነት ወደ በረሀዎች ፈጥኖ በመድረስ፣ በረሀብ በማሰቃየት እና ግድያን በመፈጸም ወደ 1.5 ሚሊዮን የሚን የአርመን የጎሳ ዝርያ ያላቸው ዜጎች ያለቁ መሆኑ ይገመታል፡፡ ሌሎች ግማሽ ሚሊዮን የሚሆኑት ዜጎች ደግሞ በራሽያ፣ በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ እና ሌሎች የአርሜኒያ ዲያስፖራን በመመስረት ስደተኛ እንዲሆኑ ተደርገዋል፡፡ እ.ኤ.አ በ1915 በቱርክ ውስጥ የነበረው የአርመን ህዝብ በኦቶማን መንግስት ላይ ወይም ደግሞ ሩሲያን ደግፎ በማመጽ በቱርክ እና በአጋሯ በጀርመን ላይ አምጾ ስለመነሳቱ በዋቢነት ሊቀርብ የሚችል ታሪካዊ ማስረጃ የለም፡፡
የቱርክ መንግስት ለዘመናት ያህል በቱርክ ውስጥ የሚገኙ አርመኖች የዘር ፍጅት ዕልቂት ወይም ደግሞ የዕልቂት ዘመቻ ሰለባ መቸውንም ጊዜ አልነበሩም በማለት ሙልጭ ያለ ክህደት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ እንደ የቱርክ መንግስት ዘገባ ወደ 1.5 ሚሊዮን የሚሆኑት አርመናውያን ያለቁት ከሩሲያ ጎን ተሰልፈው ሲያደርጉት በነበረው አጭር ውጊያ ወይም ደግሞ በአንደኛው የዓለም ጦርነት አሰቃቂ ዕልቂት አማካይነት ነው ይላል፡፡ የቱርክ መንግስት እንደማንኛውም ጦርነት ሁሉ ጥቂት የሰብአዊ መብት ድፍጠጣዎች ተካሂደው እንደነበር አምኖ ሆኖም ግን በዘር ማጥፋት ዘመቻ አማካይነት ምንም ዓይነት የአርመን ሰው እንዳልተገደለ ሙልጭ አድርጎ የክህደት ቃል ሰጥቷል፡፡
የቱርክ መንግስት ክህደት በእውነታ ላይ እና የሕግ ጭብጥን መሰረት ባደረገ መልኩ የተዘጋጀ አይደለም፡፡ በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪክ የቱርክ አምባሳደር የሆኑት እንደ ናቢ ሴንሶይ አባባል ከሆነ የጅምላ መቃብሮች እና በገፍ በአንድ ላይ ተቀብረው የተገኙት ታሪካዊ የአርመኖች የሰው ቅሬተ አጽሞች ሁኔታ በቀላሉ “የጦርነትን አሰቃቂነት” የሚያመላክት ማስረጃ እንጅ አርመኖች በቱርኮች ለመፈጀታቸው የሚያመላክት ምንም ዓይነት ነገር የለም ብለዋል፡፡ ሴንሶይ እ.ኤ.አ ከ1915 ጀምሮ ከፍተኛ መጠን ያለው የአርመን ህዝብ የማለቁ ሁኔታ ማጋዝ በሚደረግበት ጊዜ እና ወደ ማጋዝ በሚሄድበት ጊዜ እንደሆነ በመግለጽ እንዲህ ብለው ነበር፣ “በአርመኖች ላይ የተቀነባበር ግድያ አልነበረም፣ ሆኖም ግን በአንደኛው የዓለም ጦርነት ምክያንት በርካታ ሰዎች ያለቁ የመሆናቸውን እውነታ ጨምሮ አሰቃቂ ነገሮች ተፈጽመዋል፡፡“ የሴንሶይ የዘር ማጥፋት ዕልቂት አልተፈጸመም ዓይነት የህግ ጭብጥ ክርክር በተሳሳተ ማዕዘን ላይ የተቀመጠ ጉዳይ ነው፡፡ ለሴንሶይ በአርመኖች ላይ የተፈጸመው መጠነ ሰፊ ዕልቂት ወይም ደግሞ ግድያ በእራሱ የዘር ማጥፋት ዕልቂት መሆኑን አያረጋግጥም፣ ይልቁንም ይኸ የሚያሳዬው ጉዳይ ቢኖር ከፍተኛ ብዛት ያለው ሰው ማለቁን ነው፡፡ ሴንሶይ እንዲህ በማለት የክርክር ጭብጣቸውን አቅርበዋል፣ “ዋናው ቁም ነገር ሙከራው ነው፡፡ ግድያው ሌላ ጉዳይ ነው፡፡ በሁለቱም ወገኖች በኩል የተፈጸመ ነገር ነው፡፡ ሆኖም ግን የዘር ማጥፋት ፍጅት ይዞ ከሆነ ይኸ ሌላ ጉዳይ ነው፡፡ ይኸ የሕግ ቃለ ነው እናም አንዲሁ በቀላሉ ጥቅም ላይ የሚውል ነገር አይደለም፡፡ የአርመንን ህዝብ በአጠቃላይ ወይም ደግሞ በተናጠል የመውረር ዓላማ የለም፡፡“ በሴንሶይ የክርክር ጭብጥ ላይ ድብቅ ሆኖ የሚታየው ነገር እ.ኤ.አ በ1915 በዓለም አቀፍ ሕግ መሰረት የዘር ማጥፋ ወንጀል አልነበረም፣ እናም እንደ ሕግ ቱርክ የምትባል ሀገር ምንም ዓይነት የዘር ማጥፋት ወንጀል አልፈጸመችም የሚል ሆኖ ይገኛል፡፡
ራፌል ለምኪን ዘር ማጥፋት የሚለውን ቃል ለመግለጽ በአይሁዶች እና በሌሎች ላይ በናዚ የተፈጸመ ስልታዊ የሆነ የጅምላ ግድያ በማለት ያያይዙታል፡፡ ለዘመናት የቱርክ መንግስት እ.ኤ.አ ከ1915-1923 ባሉት ዓመታት ውስጥ በአርመኖች ላይ የተካሄደውን ዘር ማጥፋት የሚለውን ቃል በጥቅም ላይ ላለማዋል ሽንጡን ገትሮ በመከላከል ላይ ይገኛል፡፡ በዚያን ጊዜ የተፈጸመውን ነገር ለመግለጽ ዘር ማጥፋት ከሚለው ቃል በስተቀር ማንኛውንም ነገር ይቀበላሉ፡፡ ዘር ማጥፋት የሚለው ቃል እ.ኤ.አ በ1948 በዘር ማጥፋት የተባበሩት መንግስታት በጸደቀው ሰነድ ላይ ተካትቶ ይገኛል፡፡
በአሁኑ ጊዜ ባሉ ዓለም አቀፍ የሕግ መስፈርቶች የዘር ማጥፋት የሚለው ቃል ለመፈጸም ባቀዱ፣ ባቀነባበሩ፣ ትዕዛዝ በሰጡ፣ በተገበሩ፣ ወይም ደግሞ እገዛ ላደረጉ እና በእቅድ፣ ዝግጅት ወይም ደግሞ በአፈጻጸም ጊዜ ሆን ተብሎ ሙሉ ለሙሉ ወይም ደግሞ በከፊል ለማጥፋት እንዲሁም በብሄራዊ፣ በጎሳ፣ በዘር፣ ወይም ደግሞ በኃይማኖት፣ በቡድን፣ ወዘተ በመደራጀት የሚሰፋ ቃል ይሆናል፡፡ በእርግጥ ሴንሶይ በሕግ ትንታኒያቸው ላይ ስህተት ሰርተዋል፡፡ በአጠቃላይ በሕጉ ላይ ስለሚናገሩት የዕቅድ ድርጊት ሆን ተብሎ አንድን ቡድን በጎሳ፣ በዘር፣ ወይም ደግሞ በሌላ ምክንያት ለማጥቃት ወይም ደግሞ ትንበያ ለመስጠት እና መጥፎ ነገር በማድረግ ለመውረር ዘር ማጥፋት የሚለውን ቃል በትክክል ይገልጻል፡፡ ለምሳሌ ያህል በአንድ በተሰበሰበ ህዝብ ላይ ጥይት በመተኮስ ወይም ደግሞ አንድ ሰው ያለበት በት ዉስጥ ተኩስ ከፍቶ የሰው ነፍስ ቢጠፋ ግድያ አልተፈጸመም ማለት አይቻልም። 9 ሺ አርመናውያንን ለመግደል የማዘዣ ወረቀት አልወጣም ስለዚህ በ9 ሺሺ አርመናውያንን የተገደሉና ወደ ወንዝ በጅምላ የተጣሉት የዘር ጥፋት አይደለም ማለት አይቻልም። በእርግጥ ያ ድርጊት መተግበሩን ለመተንበይ አስፈላጊነት የለውም ምክንያቱም የኦቶማን መንግስት አናሳ የሆኑትን የአርሜናውያንን ህዝቦች የክርስትና እምነት ተከታዮች በተገኘው ማንኛውም አጋጣሚ ሁሉ በማስወገድ የጎሳ እና የኃይማኖት ማጽዳት ሲያካሂድ እንደነበር ሊያረጋግጡ የሚችሉ በርካታ የሰነድ እና የቃል ምስክርነት ማስረጃዎች ነበሩ፡፡
ማስተባበያ ሊቀርብባቸው የማይችሉት የአርመናውያን የዘር ማጥፋት ፍጅቶች ምንድን ናቸው?
እ.ኤ.አ ከ1915-1923 ባሉት ጊዚያት ውስጥ በቱርክ ውስጥ በነበሩት አርሜናውያን ላይ በእርግጠኝነት ምን እንደተደረገ ለመወሰን ማንም ሰው ቢሆን የሰነድ ማስረጃዎችን ነጻ በሆነ መልኩ መሰብሰብ እና ታሪካዊ እውነታዎችን መመርመር አለበት፡፡ ተመዝግቦ የሚገኘው የዘር ማጥፋት ፍጅት ድርጊቱ እጅግ ግዙፍ የሆነ ማስረጃ የሚገኝበት ነው፡፡ እ.ኤ.አ ነሀሴ 4/1915 የኒዮርክ ታይምስ መጽሔት እንዲህ የሚል ዘገባ አውጥቶ ነበር፣ “9 ሺ አርመናውያን እንዲያልቁ ተደርገው ወደ ቲሪስ ወንዝ እንዲጣሉ ተደርገዋል፣“ በጥይት ተደብድበው ወደ ወንዙ ተጥለዋል፡፡ እንደዚሁም ደግሞ እ.ኤ.አ ነሀሴ 18/1915 የኒዮርክ ታይምስ መጽሔት እንዲህ የሚል ዘገባ አውጥቶ ነበር፣ ”አርሜናውያን ከምድረ ገጽ እንዲጠፉ ወደ በረሀ ይላካሉ፣ ቱርኮችሁሉንም ህዝብለመጨረስ ባዘጋጁት ዕቅድ ላይክስ ቀርቦባቸዋል፡፡“ (አጽንኦ ተጨምሯል፡፡) ከዚህም በተጨማሪ እ.ኤ.አ ነሀሴ 20/1915 የኒዮርክ ታይምስ መጽሔት እንዲህ የሚል ዘገባ አውጥቶ ነበር፣ “በአንድ መንደር 1000 ወንዶች፣ ሴቶች እና ልጆች ከእንጨት በተሰራ ቤት ውስጥ እንዲቆለፍባቸው ተደርጎ ቤቱን በእሳት እንዲቃጠል በማድረግ እንዲያልቁ ተደርገዋል፡፡“ እ.ኤ.አ ነሀሴ 27/1915 የኒዮርክ ታይምስ መጽሔት እንዲህ የሚል ዘገባ አስነብቦ ነበር፣ ”ቱርኮች የአርሜናውያንን ከተማ በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡“ እንደዚሁም ደግሞ የኒዮርክ ታይምስ መጽሔት እ.ኤ.አ መስከረም 24/1915 የዩኤስ አሜሪካ የመንግስት መምሪያ በአርሜናውያን ውስጥ በነበሩት የኮንሱላር ኃላፊዎች አማካይነት በትንሿ ኢስያ ባገኙት በቂ እና ዝርዝር መረጃ መሰረት የአርሜኒያ የክርስትና እምነት ተከታዮች በቱርክ እና በኩርዶች ይፈጸሙባቸው የነበሩትን የፍርሀት፣ የእልቂት እና ተስፋ የመቁረጥ የጭካኔ አያያዞች ትረካዎችን ያቀርቡ እንደነበር ግልጽ አድርጓል፡፡ እነዚህ ዘገባዎች ሁሉ ለህዝብ ይፋ አልተደረጉም ነበር፡፡ የቀረቡት ሁሉም ዘገባዎች በአርሜኒያውያን ላይ በተለይም ደግሞ 90 በመቶ አርሜኒያውያን በሆኑት በግሪጎሪያን ቤተክርስቲያን ላይ የጦርነት ፍጅት ይፈጽሙ እንደነበር በግልጽ ያመላክታሉ፡፡ የቱርክ መንግስት ገና ከመጀመሪያው አርሜኒያውያንን ያግዝ ነበር፣ ሆኖም ግን በጊዜ ሂደት በዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሄንሪ ሞርገንዛው ከተሾሙ በኋላ የኦቶማን መንግስት የካቶሊክን እና የፕሮቴስታንት ኃይማኖት እምነት ተከታዮችን እንዳያካትት ትዕዛዙ እንደገና እንዲሻሻል ማጋገጫ ሰጠ፡፡ (አጽንኦ ተጨምሯል፡፡)
እ.ኤ.አ በ1915 ብቻ በአርሜናውያን የዘር ማጥፋት ዕልቂት ላይ በኒዮርክ ታይምስ መጽሔት ከ194 በላይ ዘገባዎች ቀርበዋል!
የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት የአርሜናውያንን የዘር ማጥፋት ፍጅት ሙሉ በሙሉ ተገንዝቦት ነበር፣ ሆኖም ግን ለጉዳዩ ምንም ዓይነት ትኩረት ሳይሰጥ ጆሮ ዳባ ልበስ በማለት ዝም ብሎ ይመለከት ነበር፡፡ የዩናናይትድ ስቴትስ አሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ሄንሪ ሞርገዛው እንዲህ በማለት ጽፈው ነበር፡
ሁሉም የሰው ልጅ ዘር ታሪኮች እንደዚህ ያለ በሰው ልጆች ላይ የተፈጸመ አስፈሪ ክስተትን አስተናግደው አያውቁም፡፡ እነዚህ እ.ኤ.አ በ1915 በአርሜናውያን ዝርያ ላይ በመፈጸም ላይ ያሉት እልቂቶች እና ስቃዮች ባለፉት ጊዚያት በምድር ላይ ከተፈጸሙት እልቂቶች እና ስቃዮች ጋር ሲነጻጸሩ ምንም ያህል ውኃ የሚቋጥሩ ሆነው አይገኙምየቱርክ ባለስልጣኖች እንደዚህ ያሉትን የማጋዝ ትዕዛዞችሲሰጡ ለሁሉም የሰው ዘር የሞትማረጋገጫዋስትና ነበር የሰጡት፣ እንደዚሁም ደግሞ ይህንን ጉዳይ አሳምረው ያውቁት ነበር እናም ከእኔ ጋር በሚያደርጓቸው ንግግሮች ሁሉ እውነታውን ለመደበቅ የተለዬ ሙከራ ሲያደርጉ አይታዩም ነበር፡፡ (አጽንኦ ተጨምሯል፡፡)
በአርሜናውያን የዘር ማጥፋት ፍጅት ላይ ሊካድ በማይችል እውነታ ላይ ክህደት መፈጸም፣
ቱርክ በአርሜናውያን የዘር ማጥፋት ፍጅት ላይ ጠንካራ የሆነ አወዛጋቢ ሁኔታ ብታቀርብም እንኳ የድርጊቱ የመፈጸም እውነታ በበርካታ ሀገሮች ማለትም ካናዳን፣ ጀርመንን፣ ግሪክን፣ ጣሊያንን፣ ፖላንድን፣ ሩሲያን፣ ስዊድንን፣ ስዊዘርላንድን እና የሮማን ጳጳስ ጨምሮ በሁሉም ዘንድ በሚገባ ይታወቃል፡፡ በደርዘን የሚቆጠሩ ሌሎች አህጉራዊ መንግስታትም (አህጉራዊ ፓርላሜንቶች በተለይም ሀገሮች) እንደዚሁም አርመኖች ታላቁ እልቂት እያሉ ይጠሩት የነበረውን የዘር ማጥፋት ፍጅት በሚገባ ያውቁት ነበር፡፡ በዩናይትድ ስቴትስ ከ50ዎቹ ግዛቶች 43ቶቹ በአርሜናውያን ላይ ለተፈጸመው የዘር ማጥፋት ፍጅት እውቅና በመስጠት እያንዳንዱ ግዛት አዋጅ አውጥቷል፡፡ እ.ኤ.አ 2010 የዩኤስ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ ቃል አቀባይ እ.ኤ.አ በ1915 የተፈጸመውን እልቂት የዘር ማጥፋት ድርጊት የሚል እውቅና ሰጥቶታል፡፡
እ.ኤ.አ ጥር 19/2008 የዩናይትድ ስቴትስ ሴናተር እና ዕጩ ፕሬዚዳንት የነበሩት ባራክ ኦባማ በሰጡት መግለጫ እንዲህ ብለው ነበር፣
እንደ ዩናይትድ ስቴትስ የምክር አባልነቴ/ሴናተርነቴ ከአርሜኒያ አሜሪካን ማህበረሰብ ጎን በመቆም ለአርሜናውያን የዘር ማጥፋት ፍጅት እውቅና እንድትሰጥ ለቱርክ ጥሪዬን አቀርባለሁ…እንደ ምክር ቤት አባል የአርሚኒያን የዘር ማጥፋት የውሳኔ መግለጫ (H.Res.106) ማለፍ እንዲችል እንደምደግፍ እና እንደፕሬዚዳንት ለአርሚኒያ የዘር ማጥፋት ዕልቂት ዕውቅና እሰጣለሁ፡፡ (አጽንኦ ተጨምሯል፡፡)
የባራክ ኦባማ ሌሎች ተቆጥረው የማያልቁ የተሰበሩ ቃል ኪዳኖች፣
ባለፉት አስርት ዓመታት የቱርክ መንግስት በአርሜኒያ ምንም ዓይነት የዘር ማጥፋት ፍጅት እንዳልተካሄደ ለማሳመን ማቋረጫ የሌለው የህዝብ ግንኙነት ስራዎችን እና የፕሮፓጋንዳ ዘመቻዎችን ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡ በእራሱ ህዝብ ላይ በሀገር ውስጥ የተሳካለት ይመስላል፡፡ በቅርቡ የኢኮኖሚክስ እና የውጭ ፖሊሲ ጥናት ማዕከል/Center for Economics and Foreign Policy Studies የተባለ የኢስታንቡል የጥናት ድርጅት ባጠናው ጥናት መሰረት 9 በመቶ የቱርክ ህዝብ የቱርክ መንግስት ያደረገው የሰብአዊ መብት ድፍጠጣ የዘር ማጥፋት ወንጀል መሆኑን አምኖ ድርጊቱን የፈጸመባቸውን ሀገር ህዝቦች ይቅርታ እንዲጠይቃቸው አሳስቧል፡፡
የቱርክ መንግስት በአርመን ህዝቦች ላይ የዘር ማጥፋት ድርጊት እንዳልፈጸመ ለመካድ እያደረጋቸው ያሉት ዓለም አቀፍ የህዝብ ግንኙነት ጥረቶች ከፍተኛ ቢሆኑም በአብዛኛው ስኬታማ አልሆኑም፡፡
ሁሉንም የማታለል ዘዴዎች ሁሉ ሞክረዋል፡፡ እ.ኤ.አ በ2007 እንደወጣው ዘገባ ከሆነ ቱርክ ለዲኤልኤ ፓይፐር/DLA Piper 1.2 ሚሊዮን ዶላር ለዓመቱ የከፈለ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ 750,000 ለሊቪንግስተን ቡድን/Livingston Group ለአርሜኒያ የዘር ማጥፋት ፍጅት እውቅና እንዳይሰጥ ለሚወተውቱ እና በአሸናፊነት ለመውጣት በሚል ክፍያ ተፈጽሟል፡፡ በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ምክር ቤት/ ኮንግረስ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ሰነድ እንዳይጸድቅ ዲኤልኤ ፓይፐር/DLA Piper የተባለው ወትዋች አሸናፊ ለመሆን ሲጫወት የነበረውን ሚና በርካታ ኢትዮጵያውያን ያስታውሳሉ፡፡ (እ.ኤ.አ በ2007 ዲኤልኤ ፓይፐር/DLA Piper የተባለውን ወትዋች ለመሞገት አዘጋጅቸው የነበረውን ባለ16 ገጽ ደብዳቤ ለማንበብእዚህ  ይጫኑ፡፡ የአርሜናውያን ብሔራዊ ኮሚቴ ዳይሬክተር የነበሩት አራም ሀምፓሪያን ቱርክ ለገጽታ ግንባታዋ ጎጂ መሆኑን ብታውቅም እንኳ የቱርክን የወንጀለኛ መቅጫ አንቀጽ 301 ዲኤልኤ ፓይፐር/DLA Piper ከቱርክ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ በመውሰድ በክርክሩ ጉዳዮች ላይ ለመከላከል እና የኮንትራክት ስምምነቱን ለማሸነፍ ባደረጉት ጥረት በተለዬ መልኩ ከታላቅ ችግር ላይ ወድቀው ነበር፡፡ ከአርሜኒያ ዴሞክራሲያዊ ባህል ውጭ የሆነው ይኸ መስፈርት ቱርክነትን ለመዘለፍ የተደረገው ንግግር እና ወንጀል ነው በማለት የመናገር ነጻነትን ለመጨቆን ከቱርክ መንግስት ጥረቶች ጋር ሙሉ በሙሉ የሚስማማ ሆኗል፡፡
የቱርክ መንግስት ስለአርሜኒያ የዘር ማጥፋት ፍጅት በድፍረት በሚናገረው ላይ ሁሉ ሀሰት እና ጎጅ የሆነ ነገር በመናገር፣ በማስቸገር፣ እና ማንንም ጥላሸት በመቀባት ምንም ዓይነት ያባከነው ጥረት የለም፡፡ ባለፈው ሳምንት ፖፕ ፍራንሲስ እ.ኤ.አ በ1915 በአርሜናውያን ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ በ20ኛው ክፍለ ዘመን የተፈጸመ የዘር ማጥፋት ፍጅት ወንጀል በማለት ጠርተውታል፡፡ በመቀጠልም እንዲህ ብለዋል፣ “ጭራቃዊነትን መደበቅ ወይም ደግሞ መካድ በቁስል ላይ ምንም ዓይነት ፋሻ ሳያስሩ ደሙ ያለምንም የመከላከል ጥረት እንዲሁ እንዲፈስ መፍቀድ ማለት ነው፡፡“ ፖፕ ኦቶማን ቱርኮች ኃላፊነት በጎደለው መልኩ 1.5 ሚሊዮን የሚሆኑትን አርሜናውያንን የመፍጀታቸውን ጉዳይ የዓለም ህዝብ መርሳት የለበትም በማለት ጩኸታቸውን በማሰማት ላይ ይገኛል፡፡
የፖፕ ፍራንሴ መግለጫ የቱርክን መንግስት ሙሉ በሙሉ ከቁጥጥር ውጭ አደረገው…የቱርክ ጠቅላይ ሚኒስትር አህመት ዳቩቶግሉ በፖፕ ፍራንሲስ ላይ የጭቃ ጅራፋቸውን በማጮህ እንዲህ በማለት ጥላሸት መቀባት ጀመሩ፡፡ “ህገወጥ የሆነ ጭራቃዊነት ከፊት ለፊታችን ቆሞ ይታያል…እናም በአሁኑ ጊዜ ፖፕ እና እነዚህ ሸፍጦች ተቀላቅለውታል…በታሪክ ሀገራችን እንድትዘለፍ አንፈቅድም፣ ቱርክ በታሪካዊ ንትርክ ውስጥ ተገድዳ እንድትገባ በፍጹም አንፈቅድም፡፡“ አምባሳደራቸውን ከቫቲካን እንደገና ጠሯቸው፡፡
የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት ሜቭሉት ካቩሶግሉ ንቀትን የሚያሳዩ ባለስልጣን ናቸው፡፡ እንዲህ ብለው ነበር፣ “ከማንኛውም ዓይነት የህግ ወይም ደግሞ ታሪካዊ እውነታ ያፈነገጠውን የፖፕን መግለጫ ለመቀበል አይቻልም…የኃይማኖት ባለስልጣኖች መሰረተቢስ የሆነ ውንጀላን በማራመድ የበቀል እና የጥላቻ መቀፍቀፊያ ቦታዎች አይደሉም፡፡“
የአውሮፓ ጉዳዮች የቱርክ ሚኒስትር የሆኑት ቮልካን ቦዝኪር ከስነምግበር ውጭ በሆነ መልኩ እና ባልተረጋጋ የስነ ልቦና መንፈስ እንዲህ ብለው ነበር፣ “ፖፕ ፍራንሲስ አርጀንቲናዊ ነው…አርጀንቲና የተባለችው ሀገር የአይሁዳችን ዕልቂት ፈጻሚ የናዚ አሰቃዮችን ግልጽ በሆነ መልኩ ለፍትህ እንዲቀርቡ በበላይነት የመራች ሀገር ናት…በአርጀንቲና ያሉ የአርመን ዲያስፖራዎች የመገናኛ ብዙሀንን እና የንግድ ስርዓቱን ተቆጣጥረውታል፡፡“ እንዴት ያለ እንቆቅልሽ የሆነ አስገራሚ ነገር ነው! ቦዝኪር ከአይሁዶች እልቂት ጋር ተመሳሳይ ነው የሚሉትን ሰዎች በመለየት እና ጥላሸት በመቀባት ፈጣን ነበሩ፣ ሆኖም ግን የአርመናውያንን የዘር ማጥፋት ፍጅት የሚያነሱትን ሰዎች ከፍተኛ በሆነ መልኩ ይተቿቸዋል፡፡ ቦዝኪር ምናልባትም እንዲህ የሚለውን የቆዬ አባባል አልሰሙትም ይሆናል፣ “አመልካች ጣትህን በሰዎች ላይ ስትቀስር ሌሎቹ ሶስቱ ጣቶችህ ወደ አንተ እንዲያመለክቱ አስተውል“
የቱርክ ፕሬዚዳንት የሆኑት ርሴፕ ቲ. ኢርዶጋን የጥቃቱ ሰለባዎችን በማውገዝ የአርሜኒያውያንን የዘር ማጥፋት ፍጅት ጨዋታ ተጫውተዋል፡፡ በመሰረታዊ ነገር የዓለም ህዝብ ስለአርሚኒያውያን የዘር ማጥፋት ፍጅት ምን እንደሚያስብ ደንታ ሳይሰጡ ተናግረዋል፡፡ በአንዱ ጆሮ ገብቶ በሌላኛው ይወጣል በማለት እንዲህ ብለው ነበር፣ “የአርሜናውያን ዲያስፖራ እ.ኤ.አ በ1915 ምዕተ ዓመቱ ከመጠናቀቁ በፊት አስቀድሞ ቀደም ሲል ተካሄደ በተባለው የዘር ማጥፋት ፍጅት በዓለም አቀፍ ዘመቻ በቱርክ ላይ የጥላቻ መንፈስ እንዲሰርጽ ጥረት እያደረገ ነው…ሀገራችን ባለፉት ከ100 እስከ 150 ዓመታት ውስጥ ምን እንዳደረገች አርሜናውያን እየሄዱበት ካለው በበለጠ አስቸጋሪ በሆኑ ነገሮች ላይ አልፈናል፡፡“ ከዚህም በተጨማሪ እንዲህ ብለው ነበር፣ “በአሁኑ ጊዜ የቱርክ ዜግነት ያላቸው ወይም ደግሞ የሌላቸው 100,000 አርሜናውያን ዜጎች በሀገሬ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ በእነዚህ ዜጎች ላይ እነርሱን ሊጎዱ የሚችሉ የተለያዩ የአያያዝ ድርጊቶች ተፈጽመውባቸዋልን?…“ በሀገሪቱ ውስጥ ከሚገኙ በሁሉም ዓይነት ዕድሎች ላይ ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡ እነዚህን ሰዎች ልናስወጣቸው እንችል ነበር፣ ሆኖም ግን በፍጹም አናደርገውም፡፡ እነዚህ ዜጎች በእኛ ሀገር እንግዶቻችን ናቸው…ምንም ዓይነት ውሳኔ ቢሰጡ በአንድ ጆሯችን ሰምተን በሌላው ጆሯችን እናስወጣለን…ለቱርክ ሬፐብሊክ እንደዚህ ያለ ኃጢያትን እና ወንጀልን የያዘ ነገር አንፈጽምም›፡፡
የኢርዶጋን ሊታመኑ የማይችሉ ድፍረት የተሞላበት የተዛባ ኢአመክንዮአዊ ድርጊት በቸልታ የሚታይ ጉዳይ አይደለም፡፡ ኢርዶጋን እ.ኤ.አ በ2015 በአርሜኒያ ዜጎች ላይ ከሀገር የማባረር እና የዘር ማጥፋት ፍጅት ያልፈጸምን መሆኑ የተረጋገጠ ስለሆነ እደዚሁም ደግሞ እ.ኤ.አ በ1915 በአርሜናውያን ህዝቦች ላይ ምንም ዓይነት የዘር ማጠፋት ድርገት ላለመፈጸማችን እንደማስረጅ ይቆጠራል የሚል ዓይነት የማሳመኛ ጭብጥ በማቅረብ ሲውተረተሩ ይታያል! በእርግጥ እ.ኤአ በ1915 በሀገራቸው ቱርክ ይኖሩ የነበሩት 2 ሚሊዮን ወይም ከዚያ በላይ የነበሩ የአርሜኒያ ህዝቦች በምን ዓይነት መንገድ እንደዚህ ተቀንሰው እ.ኤ.አ በ2015 100,000 እንግዳ ህዝቦች በሀገራቸው ላይ እንዳሉ ግልጽ ሊያደርጉልን አልሞከሩም፡፡
በአማራጩ ደግሞ የቱርክ መንግስት በአርሜናውያን ህዝቦች ላይ የዘር ማጥፋት ፍጅት የፈጸመ መሆኑን የሚናገሩትን ሰዎች ስም ጥላሸት በመቀባት እና በመዘለፍ ምንም ዓይነት የዘር ማጥፋት ፍጅት እንዳልተፈጸመ ማረጋገጫ ሊይደርግ ይሞክራል! ሆኖም ግን ፖፕ ፍራንሲስ አካፋን አካፋ በማለት 2ኛው የሮማ ካቶሊክ ጳጳስ ናቸው፡፡ እ.ኤ.አ በ2001 ፖፕ ጆን ፓውል 2ኛ በተመሳሳይ መልኩ በተረጋጋ መልኩ “የዘ-ቃል/G-word“ ሳይጠቀሙ እንዲህ ብለው ነበር፣ “የሮማ ካቶሊኮች በአርሜናውያን ህዝቦች ላይ ተደርጎ በነበረው አጠቃላይ የማጥፋት ድርጊት የኃይል እርምጃ ምክንያት በጣም አስደንጋጭ ሀዘን ተጋልጠው ነበር፡፡“ ፓፓው በጸሎታቸው እንዲህ የሚል ተማጽዕኖ አቅርበው ነበር፣ “አዳምጡኝ፣ ኦ ጌታዬ ከዚሀ ቦታ ለተነሳው ሀዘን፣ ከጥልቁ መቃብር ጥሪ ለተደረገለት ሙት፣ እንደ አቤል ደም የሌሎች ንጹሀን ሰዎች ለቅሶ፣ ምንም ባለማድረጋቸው ምክንያት ራሄል ለልጆቿ እንዳለቀሰችው ሁሉ አይተህ ምህረቱን አውርድልኝ፡፡“
የአርሜኒያውያን የዘር ማጥፋት ፍጅት በዓለም የኃይማኖት መሪዎች እና በፖለቲከኞች ብቻ እውቅና የሚያገኝ አይደለም ሆኖም ግን ያ እኩይ እና ዘግናኝ ድርጊት በታዋቂ ዓለም አቀፍ ምሁራን፣ በምርምር ሰዎች እና በታሪክ ምሁራን ጭምር እንጅ፡፡ እ.ኤ.አ በ1997 የዓለም አቀፍ የዘር ማጥፋት ፍጅት ምሁራን ማህበር (አዘማፍምማ)/International Association of Genocide Scholars (IAGS) በኦቶማን እልቂት የተፈጸመባቸውን አርሜናውያን በአንድ ድምጽ የዘር ማጥፋት ፍጅት በማለት ዕውቅና የሰጠ መሆኑን በአንድ ድምጽ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ አዘማፍምማ እ.ኤ.አ በ1915 በቱርክ ውስጥ ከአንድ ሚሊዮን በላይ በሚሆኑ አርሜናውያን ላይ ለተፈጸመው የጅምላ እልቂት የተባበሩት መንግስታት የዘር ማጥፋት መከላከል እና ቅጣት/United Nations Convention on the Prevention and Punishment of Genocide የተስማማበትን የጅምላ ዕልቂት አረጋግቷል፡፡
ቱርክ ብዙ ተቃውሞዎችን ታቀርባለች፣ በአርሜኒያ የዘር ማጥፋት ጉዳዮች ላይ ያለኝ አስተያየት፣
ሸክስፒር በአንዲት መንደር ውስጥ እንዲህ የሚል ጽሑፍ ጽፈዋል፣ “ወይዘሮዋ በርካታ ነገሮችን ትቃወማለች፣ ለእኔ እንዲህ ይመስለኛል፡፡“ በአርሚኒያን ላይ ምንም ዓይነት የዘር ማጥፋት ፍጅት እንዳልተፈጸመ እና በዘር ማጥፋት ፍጅቱ ጉዳይ ላይ በምትሰጠው አመክኖያዊነት የሌለው ተከላካይነት የቱርክ መቋጫ የሌለው እና ኃይለኛ ተቃውሞ በተቃራኒው ለዓለም ህዝብ የዘር ማጥፋት ፍጅት የተፈጸመ መሆኑን ያመላክታል፡፡ ሸክስፒር እንዲህ በማለት ጽፈዋል፣ “ኦ፣ ሌላ ስም ቢሰጠውም ጽጌረዳ እያልን የምንጠራው አበባ በሌላ ስም ቢጠራም ያው ጥሩ ጥሩ መሽተቱን አይለውጥም፣ በስሙ ውስጥ ምን አለ?“ ሆኖም ግን የዘር ማጥፋት ፍጅትበሌላ በማናቸውምስም ቢጠራ ያው በከፍተኛ ደረጃ መጠንባቱን አይተውም!
እውነት ለመናገር የዘር ማጥፋት ፍጅቱን የካደችው ቱርክ ብቻ አይደለችም፡፡ ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ የሩዋንዳን የዘር ማጥፋት ፍጅት በመካዷ ከፍተኛ ለሆነ የሞራል ዝቅጠት ኪሳራ ተዳርጋለች፡፡ እ.ኤ.አ በ1994 የክሊንተን አስተዳደር በሩዋንዳ የተፈጸመውን የዘር ማጥፋት ፍጅት ሆን ብሎ ጆሮዳባ ልበስ ብሎ ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ የፕሬዚዳንት ኦባማ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ የሆኑት ሱሳን ራይስ በሩዋንዳ ለተፈጸመው የዘር ማጥፋት እልቂት ቸልተኛ በመሆን ለድርጊቱ መፈጸም እውቅና ባለመስጠት እና ተገቢ የሆነ እርምጃ ባለመውሰድ ይከራከሩ ነበር ምክንያቱም ለእርሳቸው ለምክር ቤታዊ ምርጫ በእራሳቸው የፖለቲካ ፓርቲ ላይ አሉታዊ የሆነ ተጽዕኖ ያሳድር ስለነበር ነው፡፡ ራይስ በበከተ የሞራል ስብዕና እና በምን አገባኝነት መንፈስ በመሞላት አንዲህ የሚል መግለጫ ሰጥው ነበር፣ “ዘር ማጥፋት የሚለውን ቃል የምንጠቀም ከሆነ እና ከዚህ ጋር በተያያዘ መልኩ በሩዋንዳ ምንም ነገር ማድረግ የማንችል ከሆነ በህዳር በሚደረገው የምክርቤታዊ ምርጫ ምን ዓይነት ውጤት ሊከተል ይችላል?“ (በክሊንተን አስተዳደር ክህደት የተፈጸመበትን የሩዋንዳን የዘር ማጥፋት እልቂት ያዘጋጀሁትን ሙሉ ትችት እዚህ ጋ በመጫን ያንብቡ፡፡)
የሩዋንዳን ህዝብ የመጭፍጨፉ ድርጊት እ.ኤ.አ ሚያዝያ 7/1994 ተጀምሮ እስከ ሀምሌ ድረስ ቀጠለ፡፡ ሚያዝያ 23 የኒዮርክ ታይምስ መጽሔት ዋና ዓርታኢ እንዲህ የሚል መግለጫ አወጣ፣ “በሩዋንዳ የሚካሄደውን የዘር ማጥፋት ፍጅት የመሰለ አስቀያሚ ነገር ምን አለ? ህዝቦች ከመኪኖች እና ከአውቶብሶች እየተጎተቱ እንዲወርዱ እየተደረገ የማንነት መለያ ወረቀቶቻቸውን እንዲያሳዩ እየታዘዙ የሌላ ጎሳ አባል መሆናቸው ከተረጋገጠ ወዲያውኑ በዚያው ቦታ ላይ ይገደሉ ነበር፡፡ “
በሺዎች የሚቆጠሩ ሬሳዎች በአንድ ላይ እንደበረዶ ቁልል ተከመሩ፡፡ እናም 1700 የተባበሩት መንግስታት የሰላም አስከባሪ ኃይሎች በዚያች ሀገር የነበሩ ቢሆንም ቅሉ ግድያው በተጠናከረ መልኩ ቀጠለ፡፡ ፕሬዚዳንት ክሊንተን በኋላ ላይ እንዲህ በማለት አዘኑ፣ “ቀደም ብለን ብንደርስላቸው ኖሮ በዚያ ዕልቂት ከሞቱት ቢያንስ የአንድ ሶስተኛውን ህዝብ ህይወት ማትረፍ እንችል ነበር…በእኔ ላይ የሚያስጨንቅ ስሜትን ፈጥሯል፡፡“ ከዚያ የዘር ማጥፋት ድርጊት ቢያንስ 300,000ን ከእልቂት ማትረፍ እንችል ነበር!
እውነት እና ዕርቅ፡ ከአርሜኒያ የዘር ማጥፋት እልቂት ትምህርት መውሰድ እና ዓለም አቀፍ በጥፋተኝነትያለመጠየቅ እና የዘርማጥፋት ባህልን ማቆም፣
የአርሜኒያ የዘር ማጥፋት ፍጅት ለበርካታ አርሜናውያን የማይድን የአዕምሮ ቁስል ሆኗል፡፡ ያ አስከፊ የነበረው የዘር ማጥፋት ፍጅት ትውስታ ከአንድ ትውልድ ወደ ሌላ ትውልድ በመሸጋገር ላይ ይገኛል፡፡ ለ100 ዓመታት ያህል ተክዶ እና ጸጥ ተብሎ የቆዬውን ያንን አሰቃቂ የዘር ማጥፋት ፍጅት የማቆሚያ ጊዜው አሁን ነው፡፡
ኔልሰን ማንዴላ ለዓለም ህዝብ ያስተማሩት ታላቅ ትምህርት የዕውነት እና እርቅን ከፍተኛ ጠቃሚነት ነበር፡፡ ቱርኮች ይፋ በሆነ መልኩ በአርመናውያን ላይ የፈጸሙትን የዘር ማጥፋት ወንጀል አምነው እስካልተቀበሉ ድረስ በአርመን እና በቱርክ ህዝቦች መካከል ትርጉም ያለው ዕርቅ ሊኖር አይችልም፡፡ እውነት ብቻ በአርሜናውያን ትውልድ የመረቀዘውን የትውልድ ነብስ የህሊናን ቁስል ያድናል፡፡
ማንዴላ በአፓርታይድ የጥላቻ እና የዘረኝነት ስርዓት የቆሰለውን ቁስል በማስተማር እና ይቅርታ በማድረግ የህሊናን ቁስል መፈወስ እንደሚቻላል አሰተምረዋል፡፡ ይቅርታ የማድረግ ሂደት በመጀመሪያ ደረጃ የዕኩይ ድርጊት አራማጆች በዜጎች ላይ የፈጸሟቸውን እልቂቶች ተገንዝበው ያለምንም ማመንታት እውቅና መስጠት እንዳለባቸው እምነት አለኝ፡፡
ማንዴላ የዕውነት እና ዕርቅ ኮሚሽን ዘገባን በተቀበሉበት ጊዜ እንዲህ ብለው ነበር፣ “ዛሬ ከዚህ ቀደም በደቡብ አፍሪካ ረኃብ መጨረሻ የዘራናቸውን ጥቂት ምርቶች በመሰብሰብ ላይ እንገኛለን፡፡ እናም ይህንን አዝመራ በበዓሉ አከባበር ላይ እና በሀዘናችን ላይ ሆነው በመከታተል ህይወታችንን ለማስቀጠል፣ እንደማህበረሰብ ህልውናን ለማስጠበቅ እና የእኛ ትውልድ እንዲያውቁት ለማድረግ እንዲሁም በመጨረሻ ወደማይቀረው ዓለም ለዘላለም እስከምንሄድ ድረስ ለእኛ ህልውና ቀጣይነት እንደገና መዝራት እንዳለብን፣ በተደጋጋሚ እና በቀጣይነት መዝራት እንዳለብን መገንዘብ እና ሁለቱን ቀላል ቃላት ማለትም “እንደገና በፍጹም” የሚሉትቃላት ተግተባራዊ እስከሚሆኑ ድረስ የማምረት ትግሉ ይቀጥላል!“
የዕውነት እና የዕርቅ ሌላው ተቃራኒው ነገር ደግሞ የታሪክ እስረኛ መሆን እና የበለጠ የዘር ማጥፋት ፍጅት በመፈጸም በዓለም አቀፍ ደረጃ በጥፋተኝነት ተጠያቂ ያለመሆን እና ክህደት እንዲፈጸም ማድረግ የሚለው ነው፡፡
የዘር ማጥፋት ፍጅትን ያለመቀበል እና መካድ ለሌላ የዘር ማጥፋት ፍጅት ግብዣ የመጥራት ያህል ነው፡፡ ቱርክ በአርሜናውያን ላይ የፈጸመችውን የዘር ማጥፋት ፍጅት ምንም ሳትሆን ማድረግ እንደምትችል የሚፈቀድላት ከሆነ ሌላ ማንኛውም ሀገር ተመሳሳዩን ነገር ይፈጽማል፡፡ በእርግጥ ያ ዕልቂት ያለማንም ተቀናቃኝነት ተፈጽሟል፡፡ እ.ኤ.አ በ2007 ኦማር አልባሽር ከቱርክ እልቂት ትምህርት በመውሰድ የእርሱ መንግስት ምንም ዓይነት የዘር ማጥፋት ፍጅት ወይም ደግሞ ዘር መፍጀትን ያለምንም ስጋት በዳርፉር ላይ ፈጸመ፡፡ ባሽር በዳርፉር ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ፍጅት እንዳልተፈጸመ ሲናገር እና የዩናይት ስቴት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኮሊን ፓውልም ተራ ፈጠራ ነው ብለው የባሽርን ክህደት አጣጥለውታል፡፡
ባሽር ዩኤስ አሜሪካ ዘር ማጥፋት የሚለውን ቃል በመውሰድ ሁለት ዋና ዋና ዓላማዎችን ለማሳካት ነው የጠቀሙበት ብለዋል፡፡ እነርሱም፡ 1ኛ) የዳርፉርን የተፈጥሮ ዘይት እና ጋዝ በመቆጣር ለእራሳቸው ጥቅም ለማዋል እና 2ኛ) ዳርፉርን ከሱዳን ነጥሎ ለማስወጣት ነበር፡፡
በሰሩት ጥፋት ያለመጠየቅ እና ክህደት የመፈጸም ባህል መቆም አለበት፡፡ ቱርኮች እና የዓለም ህዝብ በአርሜናውያን ላይ የተፈጸመውን የዘር ማፋት ድርጊት ማመን እና እውቅና መስጠት አለባቸው፡፡
የአርሜናውያን የዘር ማጥፋት ፍጅት እውነታ ቱርኮችን ነጻ ሊያወጣቸው ይችላል፣ እናም የአርመናውያንንቁስል ይሽራል፡፡
በመጨረሻው ጊዜ ወደማይቀረው ዓለም ሄደን ስናርፍ የእኛ ልጆች እውቀትን በመያዝ እንዲህ በሚሉትቀላል ቃላት ይገዛሉ፡እንደገና ፍጹም!
ኔልሰን ማንዴላ
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!