Friday, October 9, 2015

ዘራፊው ሕወሓት ቁልፍ ቦታዎችን በመያዝ ውሳኔ ሰጪ ያልሆኑ ወንበሮችን ለአሽከሮቹ አድሏል

አቶ ሬድዋን ሁሴን በሃሰት ሲምሉለት የነበረውን ወንበር አጥተዋል።…
☞ ሃይለማርያም ከኒውዮርክ መልስ ሁለት ቀን ከመኖሪያቸው እንዳይወጡ ከሰው እንዳይገናኙ ተደርገዋል።…
☞ ጥያቄ የሚያበዙት አቶ አለማየሁ ተገኑ እና አቶ ሶፊያን አህመድ ከአሽከርነት ቦታቸው ተነስተዋል።…
☞ ትግላችን ላይ በማተኮር ሕወሓትን ከነአሽከሮቹ ልናጠፋቸው ይገባል።
.
የሕወሓት አሻንጉሊት የሆነው ሃይለማርያም ደሳለኝ በትናንትናው እለት ባቀረበው የቸብ ቸብ ካቢኔ መሰረት ሕወሓት የጦር ሃይሉን የውጪ ጉዳዩን የደህንነቱን የኮሚኒኬሽን እና አስፈላጊ ቁልፍ ጉዳዮችን በመቆጣጠር ውሳኔ ሰጪ የማይባሉ ተራ ቦታዎችን ለአሽከሮቹ በማደል የተዋቀረ ሲሆን አለማየሁ ተገኑ እና ሶፍያን አህመድ ምን እንደዋጣቸው አይታወቅም። ከኒውዮርክ ስብሰባ መልስ ሁለት ቀን ከመኖሪያ ቤቱ እንዳይወጣ እና ከሰው እንዳይገናኝ የታገደው ሃይለማርያም ደሳለኝ ራሱን ፈልጎ አለማግኘቱ እና በአሽከርነት መኖሩን ቤተሰቦቹን እያበሳጨ መሆኑ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ይናገራሉ። ቁልፍ የሆኑ ስልጣኖቹን የተቆጣጠረው እና በዘመድ አዝማድ ተሞልቶ በከፍተኛ የሃገር እና ሕዝብ ሃብት ዘረፋ ላይ የተሰማራው ሕወሓት ባለፈው የኢሕአዲግ ስብሰባ ወቅት አንዳንድ አመራሮቹ ያነሱትን ጥያቄ ተከትሎ ከስልጣን እንደሚባረሩ ሲነገር ነበር።
.
የወያኔና አሽከሮቹ ሹመት እንደሚከተለው ነው:-
አቶ ደመቀ መኮንን – ም/ጠቅላይ ሚኒስትር እና የማህበራዊ ዘርፍ ክላስተር አስተባባሪ
ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል –በም/ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር
ወይዘሮ አስቴር ማሞ – በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የመልካም አስተዳደር ክላስተር አስተባባሪ እና የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስትር
አቶ ሲራጅ ፈጌሳ – የመከላከያ ሚኒስትር
ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም – የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
አቶ ካሳ ተክለብርሃን – የፌደራል ጉዳዮችና አርብቶ አደር አካባቢ ልማት ሚኒስትር
አቶ ጌታቸው አምባዬ – የፍትህ ሚኒስትር
አቶ አብዱላዚዝ መሀመድ – የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር
አቶ ተፈራ ደርበው – የእርሻ እና የተፈጥሮ ሀብት ልማት ሚኒስትር
አቶ ስለሺ ጌታሁን – የእንሰሳትና የዓሳ ሀብት ልማት ሚኒስትር
አቶ አህመድ አብተው – የኢንዱስትሪ ሚኒስትር
አቶ ያዕቆብ ያላ – የንግድ ሚኒስትር
አቶ አብይ አህመድ – የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር
አቶ ወርቅነህ ገበየሁ – የትራንስፖርት ሚኒስትር
አቶ መኩሪያ ሀይሌ – የከተማ ልማት እና ቤቶች ሚኒስትር
ዶክተር አምባቸው መኮንን – የኮንስትራክሽን ሚኒስትር
አቶ ሞቱማ መቃሳ – የውሃ፣ መስኖ እና ኤሌክትሪክ ሚኒስትር
አቶ ሽፈራው ሽጉጤ – የትምህርት ሚኒስትር
አቶ ቶሎሳ ሻጊ – የማዕድን፣ የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስትር
ዶክተር ከሰተብርሀን አድማሱ – የጤና ጥበቃ ሚኒስትር
አቶ አብዱልፈታህ አብዱላሂ – የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር
ኢንጂነር አይሻ መሀመድ – የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር
ወይዘሮ ዘነቡ ታደሰ -የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ሚኒስትር
ዶክተር ሽፈራው ተክለማርያም – የአካባቢ ደን ልማት እና የአየር ንብረት ለውጥ ሚኒስትር
አቶ ሬድዋን ሁሴን – የወጣቶች እና ስፖርት ሚኒስትር
ወይዘሮ ደሚቱ ሀምቢሳ – የመንግስት የልማት ድርጅቶች ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል።
አቶ በከር ሻሌ – የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬከተር
አቶ ጌታቸው ረዳ – የመንግስት ኮሙዩንኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሀላፊ ሚኒስትር
አቶ አስመላሽ ወልደስላሴ – የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር
ዶክተር ይናገር ደሴ – የብሄራዊ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር
.
ትግላችን ላይ በማተኮር ሕወሓትን ከነአሽከሮቹ ልናጠፋቸው ይገባል። በአንድነት በመቆም ሃገራችንን ከጅቦች እናድናለን!!
.
ምንሊክ ሳልሳዊ

የተቸካዮች ምክር ቤት – (በበውቀቱ ስዩም)

agenda_ethiopian_MPs1ትምርት በጨረስን ማግስት እኔና ፍቅር ይልቃል ፈረንሳይ ለጋስዮን ኣካባቢ በዘጠና ብር ቤት መሰል ነገር ተከራይተን እንኖር ነበር፡፡ በየሳምንቱ ቅዳሜ ወደ ቪድዮ ቤት ጎራ እንላለን ፤ እነኩማር በዜማቸው ወፍ ሲያረግፉ ፤ እነ ቫንዳም በጫማ ጥፍያቸው ጥርስ ሲያረግፉ በመመልከት ራሳችን ዘና ለማረግ እንሞክራለን፡፡ ፊልም ዛሬ እንዲህ ጥንቡን ሊጥል ያኔ በጣም ብርቅ ነበር፡፡ ፊልም ሰሪዎች እንኳ እኛ ፊልም ለማየት የምንከፍለውን ያክል መስዋእትነት የሚከፍሉ ኣይመስለኝም፡፡ ያኔ ፊልም ማየት የጫማና የግስላ ሲጃራ ድብልቅ ሽታ የመቻል ቁርጠኝነት ይጠይቃል ፡፡ እናም በጊዜው የሁለት ሰኣት ፊልም ኣይተን የሁለት ሳምንት ጉንፋን ተረክበን ለመውጣት እንገደድ ነበር፡፡

ኣሁን ሳስበው፤ ከፊልሙ በላይ የፈረንሳይ ልጆች በፊልሙ ላይ ተመስርተው የሚሰጡት ኣስተያየት ያዝናናኝ ነበር፡፡ ኣንድ ቀን በጣም እጅ እጅ የሚል ፊልም ስናይ “ፓርላማውን ቀይርልን ፓርላማውን ቀይርልን ”ብለው ቀወጡት፡፡ ኣሰልቺ ፊልሞች” ፓርላማ “ተብሎ እንደሚጠሩ ያወኩት ያኔ ነው፡፡ ባለቪድዮ ቤቱም ኣብላጫውን ድምጽ ኣይቶ ሌላ ፊልም እንዲቀየር ውሳኔ ኣስተለለፈ፡፡

የተወሰኑ የተቃዋሚ ድምጾች በሚሰሙበት ሰሞን እንዳሰልቺ ፊልም ይታይ የነበረው ፓርላማ ዛሬ ይሄ ኣይነቱ ኣጠራር እንኳ የሚበዛበት ይመስለኛል፡፡ እኔን የሚገርመኝ የተወካዮች ምክር-ቤት የሚለውን ስም እስካሁን ይዞ መቆየቱ ነው፡፡ የሚወከልም ሆነ የሚማከር በሌለበት ይሄን ስም መሸከም ኣይከብድም? እንዲያው ቤቱ ስሙ ከብዶት ኣለመፍረሱ ይገርማል፡፡

ያገራችን ፓርላማ ኋላቀር መሆኑን ብዙዎቻችን እናውቃለን፡፡ ግን ከመቶ ኣመት በፊት ከነበረው የምክክር ባህል ኣንጻር ሲወዳደር እንኳ እጅግ ኋላቀር መሆኑን ስንቶቻችን እናውቃለን??
“ብራናው ይገለጥ ተዘርግቶ በኣትሮኖሱ ላይ”::

1
በጅሮንድ ተክለሃዋርያት ተክለማርያም ባድዋ ጦርነት ዋዜማ ስለነበረው ምክር ያይን እማኝ ሆነው የተመለከቱትን ጽፈውልናል፡፡ልቀንጨበው፤
“ራስ(መኮንን)…መኳንንታቸውን ሰብስበው የጦር ምክር ተደረገ፡፡ ራስ ኣሉላም ምክሩ ላይ ነበሩ፡፡
ሌሊት ሲነጋጋ ሸለቆ ለሸለቆ ወርደን እግንቡ ስር ተጠግተን በመሰላል እየተንጠላጠልን ከምሽጉ ውስጥ ገብተን(ጠላትን) እንፍጀው መንገዱን የራስ ኣሉላ ሰዎች ይመሩናል ተባለና ተቆረጠ፡፡ ይህንን ምክር መኳንንቱም የጦር ኣለቆችም ባለሟሎቹም ወደዱት፡፡ ኣንድ ሰው ብቻ በማእረጉ ዝቅተኛ የሆነ(የደራሲው ወንድም ኣብዩ)እየተቃወመ ተናገረ፡፡

ይህ ምክር ትልቅ ጉዳት ያመጣል ሰራዊታችንም በከንቱ ያልቃል ይልቅስ ታግሰን ቀንና ሌሊት ዘብ እየጠበቅን ውሃ ከምሽጉ ውጭ መቅዳት እንዳይችል እናድርግ …”ብሎ ተናገረ፡፡
ቀኛዝማች በሻህ ያብዩን ነገር ክፍኛ ነቀፉት…”ኣንተ ወረቀት ሲጻፍ ትመክራለህ ፡፡ፈርተህ እንደሆነ እሰፈር ዋል ፡፡ እኛ በሾተል እየቀነጠስን እንደኣይጥ እንፈጀዋለን ኣሉ….“

…ኣብዩ ከምንም ኣልቆጠራቸውም ፡፡ በትእግስት መለሰላቸው፡፡”ሰራዊታችን በከንቱ እንዲያልቅ በመደረጉ ኣዝናለሁ፡፡ እናንተ ስትሞቱ እኔ የቀረሁ እንደሁ ያን ጊዜ ፈሪ ተብየ እሰደባለሁ፡፡ “ይህ ተናገረና ወጣ፡፡”
(ኦቶባዮግራፊ፤ ገጽ 60)
የምክሩ ውሳኔ ምንም ይሁን ሰዎች በትልልቅ ኣገራዊ ጉዳዮች ላይ ተሰብስበው ይሟገቱ እንደነበር እንረዳለን ፡፡ በምክሩ ላይ የተለያየ ማእረግ ያላቸው ብቻ ሳይሆን የተለያየ ኣመለካከት ያላቸው ሰዎች ተሳትፈዋል፡፡ በምክክሩ ኣብላጫውን ውሳኔ መቃወም ብቻ ሳይሆን ስብሰባ ረግጦ መውጣትም ይታወቅ ነበር ማለት ነው(ይህን ተናገረና ወጣ“ ተብሎ የተጻፈለትን ኣብዩን ኣስታውሱ )

2
ፕላውደን የተባለ የንግሊዝ ተጓዥ፤ በዘመነ መሳፍንት ማብቂያ በጉድሩ(ወለጋ)የተመለከተውን የሪፐብሊክ ኣስተዳደር እያደነቀ ሲጽፍ እንዲህ ብሏል፡፡
•”ከሌሎች ጎሳዎች ጋር ስለሚኖረው ጉዳይ የሚወሰነው በጉባኤ ነው፡፡ ባደባባዩ ጉባኤ ለመታደም የሚፈልግ ሰው ሁሉ ክብ ሰርቶ ጦሩን ተደግፎ ከብቦ ቆሞ ይመለከታል፡ ፡ ሽማግሌዎች በሚያስደንቅ መንገድ ተራቸውን እየጠበቁ በሰላምና በጦርነት ዙርያ ይከራከራሉ።“
በራስ መኮንን የሸማ ድንኳን ውስጥ እና በጉድሩ መስክ ላይ የታየው ክርክርና ሙግት ፤ በዛሬው ፓርላማ ውስጥ ይታያል?ያለፈውን ስርኣት የመናፈቅ መብት በህገ መንግስቱ ይካተትልንማ!

ዲሞክራሲ ሂደት ነው ይባልልኛል፡፡ ሊሆን ይችላል፡፡ ባገሬ ግን እንኳን ሲሄድ ሲንፏቀቅ ኣይታየኝም፡ ፡ የሚሄድ ቢሆን ኖሮ ከቀደምቶቻችን ውጥን ላይ ተነስቶ ዛሬ ትልቅ ደረጃ ደርሶ እናየው ነበር፡፡ የሚታየኝ ወንበር ላይ ተቸክሎ በድሃ እንባ የተቦካ እንጀራ የሚበላ ሰው ብቻ ነው፡፡ የተወሰኑ ሰዎች ሳይወጡ ሳይወርዱ ቀኝ እጃቸውን ብቻ እያወጡ እያወረዱ እንጀራ የሚበሉበት ቤት፤ “ የተወካዮች ምክር” ቤት መባሉ ያስቃል፡፡ ምናልባት” የተቸካዮች ምክር ቤት “ የሚለው ስም ይመጥነው ይሆን?

Thursday, October 1, 2015

ከአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ (ሞላ አስገዶምን አስመልክቶ) -

ginbot-7በኢትዮጵያ የቅርብ ጊዜ የፖለቲካ ትግል ታሪክ ውስጥ ባጠቃላይና በተለይ ደግሞ ህወሓት/ኢህአዴግ የፖለቲካ ስልጣኑን በተቆጣጠረባቸው ባለፉት ሁለት አስርት አመታት ውስጥ ህወሓት/ኢህአዴግን እንቃወማለን በሚለው ወገን ገንነው የመጡ ሁለት አፍራሽና ኋላቀር የፖለቲካ አዝማሚያዎች (trends ) አሉ። ከነኝህ ውስጥ አንደኛው ራስን በፖለቲካ አመለካከት ዙሪያ ከማሰባሰብ ይልቅ በጎጥና በዘውግ ደረጃ የመመልከትና ሀገራዊ ፖለቲካን በደም ቆጠራ የመመንዘር አባዜ ነው። ሁለተኛውና ከዚሁ ያልተናነሰው ችግር የፖለቲካ ድርጅት በመሰረታዊ ያመለካከት መርሆች ዙሪያ ሰፋ ያለ የማህበረሰብ ክፍልን የማሰባሰቢያ ድንኳን መሆኑ ቀርቶ፤ በስራ ሳይሆን ድንገተኛ አጋጣሚን በመጠበቅ ትርፍ ለማጋበስ በሚቋምጡ ሰነፍ “ነጋዴዎች“ የተቋቋሙ ሩቅ የማይሄዱ የንግድ ድርጅቶች ይመስልበ ተግባር ምንም የማይፈይዱ ”የፖለቲካ ድርጅቶች“ እንደ አሸን የመፍላታቸው ፈሊጥ ነው። እነኝህ ሁለቱም አዝማሚያዎች የህወሓት/ኢህአዴግን ህይወት ከማራዘም አልፈዉ ማህበረሰቡን ወደሚመኘው እውነተኛ የዴሞክራሲያዊ ስርዓት አንድ ጋት እንኳን ፈቀቅ አላደረጉትም። ይልቁንም ዴሞክራሲን የሚናፍቁ ታጋዮች ተሰባስበውና ተጠናክረው ስርዓቱን ከመግፋት ይልቅ በግለሰብ ደረጃ ወይንም በትናንሽ ቡድኖች በመሰባሰብ የሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች በስርዓቱ በቀላሉ እየተመቱ ብዙ ታጋዮች ለሞት፤ ለስቃይና ለእስር ተዳርገዋል። አሁንም እየተዳረጉ ነው።


የዚህ አይነት የትግል አካሄድ ሩቅ እንደማያስኬድ የኢትዮጵያ ህዝብ ከተገነዘበው ቆይቷል። ይህ አካሄድ እንዲቀየርና የፖለቲካ ሀይሎች ተሰባስበው ይህንን በስልጣን ላይ ከሚገባው በላይ የቆየና አገሪቱን ለውርደት የዳረገ የጥቂት ዘራፊዎች ቡድን ከጫንቃው ላይ እንዲያነሱለት ሲማጠን ቆይቷል።ምንም እንኳን በመሪዎች ድክመት የሚመኘውን ዳር መድረስ ባይችልም ባጭር ጊዜ ልምዱ በትንሹም ቢሆን የተባበረ ትግል ሊያስገኝ የሚችለውን ጥቅም በመጠኑም ቢሆን አይቶታል።
ይህ የህዝብ ፍላጎት መኖር ግን በራሱ ይህንን የተባበረ ሰፊ ማህበራዊ እንቅስቃሴ መፍጠርን ቀላል ያደርገዋል ማለት አይደለም። በብዙ ስራ፤ በብዙ ድካምና ያላሰለሰ ጥረት የሚፈጠር እልህ አስጨራሽ ሂደት ነው። ባንድ በኩል እንዲህ አይነት ሰፊ የህዝብ እንቅስቃሴ በስልጣኑ ለመቆየት የሚፈጥርበትን ችግር የሚረዳው በስልጣን ላይ ያለው የዘራፊዎች ቡድን ይህን እንቅስቃሴ ከወዲሁ ለማምከን ያለ የሌለ የገንዘብ፤ የስለላና የተንኮል ሀይሉን ይጠቀማል። በተቃዋሚ ድርጅቶች ውስጥ ሰርጎ በመግባትና ደካማ ሀይሎችን በገንዘብ በመግዛት ወይንም በማስፈራራት እንዲህ አይነት ትብብሮች እንዳይፈጠሩ ከውስጥ ለመቦርቦር ተግቶ ይሰራል። በሌላ በኩል ደግሞ የትም የማያደርሳቸውን “የራሳቸውን ድርጅት” የሙጢኝ ብለው ለትልቅና አገራዊ አላማ እራሳቸውን ላለማስገዛት የቆረጡ ደካማ “የድርጅት መሪዎች” እንዲህ አይነቱን የጋራ እንቅስቃሴ በራሳቸው ግብዝነትና ስግብግብነት ምክንያት ብቻ ሊያሰናክሉት መሞከራቸው አይቀርም።


ይህ ግን ጊዜው ያለፈበት አዝማሚያ ነውና የሚሳካ ሙከራ አይሆንም። የተናጠል ትግል ሂደት ማብቂያው ጊዜ ተቃርቧል። የኢትዮጵያ ህዝብም ሆነ ለእውነተኛ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ የሚታገሉ ኃይሎች እንዲህ አይነቱን ፋይዳ ቢስ ሂደት የመቀበል ትዕግስታቸው ተሟጧል። በቅርብ ጊዜ የሞላ አስገዶምን መክዳት በማስመልከት የትህዴን አመራር ባወጣው መግለጫ“ኢትዮጵያን እውነተኛ ዴሞክራሲያዊት ሀገር ለማድረግ ከሁሉም ኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ጋር አብሮ መስራት የድርጅታችን መሰረታዊ መርሆ ነው” እንዳለው ይህ መሰረታዊ መርሆ በሀገራችን የጸረ ህወሓት/ኢህአዴግ ትግል የበላይነት ይዞ እየመጣ ያለ እጅግ አስፈላጊና ለድሉም ወሳኝ የሆነ የጊዜው የፖለቲካ አዝማሚያ ነው። አርበኞች ግንቦት 7 ይህን መሰረታዊ መርሆ ከምር ወስዶ የሚንቀሳቀስ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ነው።


ይህአዲስ የፖለቲካ አዝማሚያ ምቾት የማይሰጣቸው የፖለቲካ ኃይሎች መኖራቸው የሚጠበቅ ነው። የህወሓት/ኢህአዴግ የስለላ ድርጅት ከሰሞኑ ሞላ አስገዶምን በማስመልከት ባወጣው መግለጫ በግልጽ እንዳስቀመጠው ኢትዮጵያውያን የዴሞክራሲ ኃይሎች ተሰባስበው እንዳይታገሉና ስርዓቱን እንዳይፈታተኑ የማያደርገው ጥረት የለም። በዚህ በህወሓት/ኢህአዴግ መሰሪ እንቅስቃሴ ደግሞ በቀላሉ መጠቀሚያ የሚሆኑት በጋራ የሚደረግ ትግል በግለሰብ ደረጃ ያሳጣናል ብለው የሚፈሩት “የግል ጎጆና” ጥቅም የሚያስጨነቃቸው ደካማ የፖለቲካ መሪዎች ነን ባዮችን ነው። ባንጻሩ በየድርጅቶቹ ውስጥ በሚገኙት ብዙሀኑ ሩቅ አሳቢ መሪዎች ጥረትና በተለይም ደግሞ ይህን ትግል ለአላማ እንጂ ለሌላ ምንም አይነት የግል ጥቅም ያልተቀላቀሉና በትግሉ ሂደትም ትልቁን ሚና በሚጫወቱት ብዙሀን ታጋዮች አልበገር ባይነት እንዲህ አይነት ደካማ መሪዎች ተከታይ በማጣት ሲዳከሙና በሚያደርጉት እንቅስቃሴ በድርጅታቸው ውስጥ የሚነሳባቸውን ተቃውሞ መቋቋም ባለመቻላቸው በቀላሉ እየተፍሸለሸሉ ከመራገፍ በስተቀር በድርጅቶቹ ላይ ከባድ ጉዳት ሳያደርሱ ይከስማሉ።


በህወሓት/ኢህአዴግ “የስለላ ድርጅት አቀናባሪነት” በሞላ አስገዶም መሪነት ከሰሞኑ የተሞከረው የማፍረስ ንቅናቄ ከሽፎ ወደ ተስፋ መቁረጥ የክህደት እንቅስቃሴ የተቀየረው የሰሞኑ ሙከራም የዚህ አጠቃላይ ሂደት አካል ነው። በዚህ የከሸፈ ሙከራ ውስጥ እጅግ የሚገርመውና የትህዴንን ብዙሀን አመራሮች ብስለት፤ የድርጅቱን መዋቅራዊና ድርጅታዊ ጥንካሬ፤ እንዲሁም ብዙሀኑ ታጋይ ለጋራ ትግል ያለውን ቆራጥ አቋም ያስመሰከረው፤ ይህንን የማፍረስ ሙከራ የመራውና ሳያሳካለት በመጨረሻም በጣም ጥቂት ተከታዮቹን ብቻ ይዞ የከዳው ለረጅም ጊዜ የድርጅቱ ሊቀመንበር የነበረው ሞላ አስገዶም መሆኑ ነው። እንዲህ አይነት የመክዳት ሂደት ባጭር ጊዜ በማህበረሰባችን ላይ የሚፈጥረውን አስጨናቂ ስሜት የምንረዳው ቢሆንም ከዚያ በላይ ልንረዳው የሚገባው ግን በእንዲህ አይነት ከፍተኛ ያመራር ቦታ የነበረ ሰው ሙከራ አለመሳካት በእርግጥም የሀገራችን ፖለቲካ እየበሰለ፤ ከግለሰብ አመራሮች ተጽእኖ እየተላቀቀ፤ አዲስ የተባብሮ መታገል አቅጣጫን እያበሰረ እየሄደ መሆኑንና በትናንሽ ሰዎች መግተርተር ይህ ሂደት የማይቀለበስ መሆኑን የሚያመለክት የረጅም ጊዜ ግኝት መሆኑን ነው።


አርበኞች ግንቦት 7 በዚህ አጋጣሚ ለትህዴን ብዙሀን አመራርና ለሰፊው ታጋይ በመርህ ላይ ለተመሰረተው አቋማቸውና መርሃቸውን ለማስጠበቅ ለሚያደርጉት ቆራጥ ትግል ያለውን ጓዳዊ አክብሮት ይገልጻል። በመግለጫቸው ላይ በግልጽ ያስቀመጡት መርሆአቸው የኛም መርሆ መሆኑን ስንገልጽላቸው በታላቅ ኩራት ነው። ድርጅታቸውን እያጸዱ የተመሰረቱበትን መርሆ ጠብቀው ለመጓዝ ባሳዩት ቁርጠኝነትና ወደፊትም በሚያደርጉት ትግል ምንጊዜም ከጎናቸው መሆናችንንና ጓዳዊ ድጋፋችን ምንጊዜም እንደማይለያቸው በዚህ አጋጣሚ ደግመን ልናረጋግጥላቸው እንወዳለን። በመግለጫቸው ላይ እንዳሉትም ይህ ትግል ኢትዮጵያን ዴሞክራሲያዊ ሳያደርግ የማይቆምና እንዲያውም ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና ለኢትዮጵያ ህዝብም በየጊዜው በሚፈጠሩ እንቅፋቶች ላይ ሳያተኩር ትግሉን በሙሉ ልብ እንዲደግፍ ያደረጉት ጥሪ የኛም ጥሪ ነው።


አንድነት ኃይል ነው!!!
አርበኞች ግንቦት 7: ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ

ህወሃት ጦርነት ጀመረ፣ ቁስለኞች ታይተዋል

pow-and-medic-3_xlargeበነጻ አውጪ ስም አገር እየገዛ ያለውን የትግራይ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃትን) ለመውጋት ብረት ያነሳው ሌላ የትግራይ ነጻ አውጪ ሃይል /ትህዴን ወይም በትግሪኛ ዴምህት/ መሪ የነበረው “ተጋዳላይ” ሞላ አስገዶም ህወሃትን ከተቀላቀለ ጥቂት ቀናት በኋላ ጦርነት መጀመሩ ተሰማ። የህወሃት ወኪል ሃይለማርያም ደሳለኝ ውጊያው የሚጀመረው የህዝብ ፈቃድ ተጠይቆ እንደሚሆን ተናግረው ነበር።

የጎልጉል መረጃ አቀባዮች ከአዲስ አበባ እንደገለጹት ጦር ኃይሎች ሆስፒታል ቁስለኞች እየገቡ መሆኑንን እማኞች ነግረዋቸዋል። ጦርነቱ በየትኛው መንደርና ወረዳ እንደተጀመረ ለይተው ያላስረዱት የዜናው ባለቤቶች፣ ውጊያ እየተካሄደ ያለው ኤርትራ ምድር ላይ እንደሆነ ግን አልሸሸጉም።

አንድ የሆስፒታል ሰራተኛ ዘመድ ደውሎላቸው “ቁሰለኞች አሉ ሥራ በዝቶብኛል” ማለታቸውን የጎልጉል መረጃ ሰጪዎች ከአዲሰ አበባ ገልጸዋል። ባለፈው ሳምንት በሁመራ አቅጣጫ የከባድ መሳሪያ ተኩስና ድብደባ መሰማቱን የተለያዩ ድረገጾች ዘግበው ነበር። ይህ ሁሉ ከመሆኑ በፊት ሻእቢያ “ህወሃት ሊወረኝ ነው” ሲል ክስ ማሰማቱ አይዘነጋም።

ኦምሃጀር በሚባለው ስፍራ የከረረ ውጊያ እየተካሄደ መሆኑን እንደሰሙ የገለጹ በውጊያው የትኛው ወገን ድል እንደተቀዳጀ ለጊዜው መናገር እንደማይቻል አመልክተዋል። ውጊያው ጠርዙን አስፍቶ እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል።

ከህወሃት በኩል ውጊያው ከሻዕቢያ ጋር እንደሆነ ቢገለጽም ከሌላ ወገን “ህወሃትን የወጋሁት እኔ ነኝ” ባይ ይህ ዜና እስከታተመ ድረስ አልተሰማም። የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ህወሃትን በነፍጥ አንበረክካለሁ በማለት ማወጁና አመራሮቹም ወደ ውጊያው አውድ ማምራታቸው ይታወቃል። ህወሃት ኤርትራን በአራት አቅጣጫ የመውጋት እቅድ እንዳለው ጎልጉል መዘገቡ የሚታወስ ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በርካታ የሰራዊቱ አባላት ከሰራዊቱ እየሸሹና እየተሰወሩ መሆናቸው ህወሃትን እንዳሳሰበው፣ ጦሩ የመዋጋት ፍላጎት ያጣል የሚል ሥጋት እንዳለ የሚጠቁሙ ክፍሎች “የአሁኑ የውጊያ አቅጣጫ በዚህ መልኩ እንዲሆን መደረጉ ይህንኑ ለመፈተንም ጭምር ነው” ብለዋል።

በሌላ ዜና በሶማሌ ያለው ሰራዊት የመመለስ ጥያቄ ማንሳቱና ሁለት ጄኔራሎች ጦሩን ለማወያየት ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ስፍራው አቅንተው እንደነበር ለማወቅ ተችሏል። ጦሩ መስዋዕትነት እየከፈለ በተደጋጋሚ የተቆጣጠረውን ቦታ እንዲለቅ ትዕዛዝ ሲቀበል መቆየቱ ሌላው የቅሬታው መነሻ ሲሆን በሶማሌ ያለው የሰላም አስከባሪ ሃይል ይህንኑ ነቅፎ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል። በህወሃት የሚመሩት የኢህአዴግ ባለስልጣናት በሶማሌ ስለተገደሉት ወገኖች መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆናቸው፣ ተቃዋሚ ፓርቲዎችም ይህንን አክርረው አለመጠየቃቸው፣ ላለፉት አምስት ዓመታት 99.6 በመቶ ህወሃት የነገሰበት ማኅበርም (ፓርላማ) ለይስሙላ እንኳን ጥያቄ አቅርቦ እንደማያውቅ በርካቶች የሚተቹበት አገራዊ ጉዳይ ነው።

የአመቱ ምርጥ ባለጌ ሰው! (በጌታቸው ረዳ)

hqdefault (1)መስከረም 1/2008 ዐ.ም አዲስ አመት የኢትዮጵያ ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ “የአመቱ ባለጌ ሰው” አፈላልጎ በብልግናው የመረጠው “የአመቱ ባለጌ ሰው” ባሕርዳር የሚኖረው ፎቶግራፉ ከላይ የሚታዬው “አለምነህ መኮንን” /ን ነው። አለምነህ መኮንን በጎሳው “አማራ” ነው። ወያኔ “አማራ ክልል” ብሎ ጸረ አማራ አጀንዳው ለማራመድ እንዲመቸው ባለ ሁለቱ ሕበረ ቀለም (ቢጫና ቀይ) ባንዴራውን በቅጅ አዘጋጅቶ፤ እንደ ግኡዝ ዕጭቃ አድቦልቡሎ ወያኔ ከሰራቸው፤ ስብእናቸውን አውልቆ ጠርቦ በምስሉ የቀረጻቸው፤ እራሳቸወን የማይመስሉ፤ ትንንሽ ሕሊና ያላቸውን ሰዎችን ትግራይ ሜዳ ውስጥ የሕሊና አጠባ አድርጎ ተሸክሞአቸው አማራውን ሕብረተሰብ እንዲዘልፉለት ጎጃም ክ/ሐገር ባሕርዳር ውስጥ ከሾማቸው የወያኔ ብአዴን አማራዎች መካካል አለምነህ መኮንን ነው።
አለምነህ መኮንን ከነ ደመቀ እና ከነ ወንድወሰን የመሳሰሉ አማራዎች ሆኖ የወያኔ አሽከር ሆኖው ወያኔ ሲሞት ከወያኔ ጋር ለመሞት ከተዘጋጁ የአማራን ሕብረተሰብ ከሚያሰድቡና ከሚሳደቡት ማፈሪያዎቹ አንዱ ነው። ወያኔ እንደ አፓርታይድ በቋንቋ ክልሎ ካዘጋጃቸው አማራ ብሎ ከሚጠራቸው “ክፍለ አፓርታይድ” አካባቢዎች አንዱ ከሆነው “የአማራ ክልል” ምክትል ፕረዚዳንት እና የብአዴን ጽ/ቤት ሓለፊ ነው። አለቆቹ አማራን ስለዘለፈላቸው አሜሪካ ድረስ ልከው ሰሞኑን ካንሳስ ሲቲ አየር ማረፊያ ጣቢያ እንደታዬ ዜናዎች እየዘገቡ ነው።
ይህ ሰው አባቱን እናቱን ዘመዶቹን በጠቅላላ አማራውን ሕብረተሰብ
“ስንፋጭ” ትምክህት የተጠናወተው፡፤ትምክሕትነቱን ያልተወው፤ በባዶ እግሩ እየሄደ መርዝ ንግግር የሚናገር፤ ከሌሎች ሕዝቦች ጋር ተግባብቶ መኖር የማይችል፤ የሸተተው እግሩ እንዳይሸት ከጫማው ስር ‘የባሕር ዛፍ ቅጠል ያደረግበታል”፤ /ዚስ ኢዝ ቴክኖሎጂ!………ባዶ እግሩ እየሄደ የሚናገረው ንግግር ግን መርዝ ነው። ልሃጩን ማራገፍ አለበት! ይኼ ላሃጭ ሳይራገፍ በጋራ መኖር አይቻልም። ማንኛወም ሙትቻ ፓርቲ ሁሉ መነሻው አማራ ክልል ነው። ይላል። ምክንያቱንም ሲገልጽ “ትምክህተኝነትን አንደ ምግብ ስለሚመገበው ነው። ያንን ምግብም እየተመገበ ያቅራራል።” እያለ ተሰብሳቢ ካድሬዎቹን ሳቅ በሳቅ እያደረገ በሕዝብ ክብር ሲያላግጥ በድምፁ የተቀዳ ዋልጌ ግለሰብ ነው።
ይህ ወላጆቹን እና ሕዝብን የሚሰድብ ስድ ግለሰብ፤ “አማራው ይህ ሰንፋጭ ትምክሕቱ በቤንሻንጉል እና በተቀሩት አካባቢዎች ለመሰደድ ምክንያት ሆኖታል።ሲል ተሳድቧል። ያውም እዛው በአማራዎች አገር ፤ አማራዎች በሚኖሩበት በባሕርዳር ከተማ! ወይ ዘመን! አያሰማን ጉድ የለ!
ከትንሽም ትንሽ ሰው መሆኑን የሚያሳይ “ይቅርታ ከመጠየቅ ይልቅ፤ የተቀዳው ድምፅ ይፋ ሲሆን ‘የሚመልሰው በማጣቱ ተደናግጦ ለካድሬዎቹ ጋዜጠኞቹን ሰብስቦ (አፋጥጠው ከነማስረጃው ሊወጥሩት አንደማይችሉ ስላወቀ)፤ ይህ እኔ አልተናገርኩም፤ የቴክኖሎጂ “የቆርጦ ቀጥል ስራ ነው” ሲል ንግግሩ ከሚያሳውቅበት ድንጋጤ ጋር ወዲያ ወዲህ ሲረግጥና ሲዘላብድ ተደምጧል። አለቆቹና ካድሬ ጸሐፊዎቹ በወያኔ ድረገፆች ላይ (አውራምባ ድረገጽ፤ትግራይ ኦን ላይን፤አይጋ… ላይ የተጻፈውን ተመልከቱት)፤ እሱን ለመከላከል ሲሉ ያልፈነቀሉት የሽፋን ጥረት አልነበረም። ሆኖም አገር ውስጥ የሚገኘው ‘ዩዲጀ’ የተባለው ፓርቲ የፔትሽን /የፌርማ የማሰባሰብን ስራ በመስራት ከሥራው እንዲባረር ቢጥርም፤ “ክቡር መሪያችን ከሞታቸው በፊት….” እያለ ጌታውን መለስ ዜናዊን ሲያሞካሽ ያደመጡት ጌቶቹ ከሥራው ሊያግዱት አልፈለጉም እና እዛው ሆኖ አማራውን ሕዝብ መዝለፉን እንዲቀጥል አድርገዋል። ሆኖም የባሕር ዳር ሕዝብ በነቂስ በመውጣት “ከባዶ ጭንቅላት፤ ባዶ እግር ይሻላል!” የሚል መፈከር ይዘው አዳባባይ ወጥተው፤ “ስድ አደግ”፤ “ሙጀሊያም አፍ” እና “የወያኔ መጸዳጃ የሚል ቅጥያ ስም ተሰጥቶታል።
ይህ ስድ አደግ’ ሙጀሊያም፤ጉርፉጥ አፍ (ግረፉጥ ማለት ትግርኛ ነው፤ ባለጌ ያልታረመ ፤ ማለት ነው” አማራውን ሕዝብ የዘለፈበትን ስድ አንደበቱን ለማድመጥ የሚከተለውን የአውዲዮ አድራሻ ይጫኑ። የአመቱ ባለጌ ሰው እንዴት እንደመረጥኩት መረጃው እራሱ ይናገራል። አመሰግናለሁ፤ ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ብሎግ አዘጋጅ)፤ በዚህ ሦሰት ቀን የሚወጣ ሌላ ዝግጅት ስላለ፤ እሱንም እንዳያመልጣችሁ ይሁን። “የአመቱ ባለጌ ሰው” ሲናገር በአንደበቱ ይኼውና አድምጡ። ኢትዮጵያ እንደዚህ አይነት የሕሊና ድኩማን ተሸክማ ትገኛለች።