Tuesday, December 29, 2015

አዲስ አባባ ስለምን ታወዛግባለች? – በዘላለም ክብረት

aa

ሕሩይ ሚናስ አስደናቂ ሰው ነው፡፡ የገበሬ ልጅ፣ በአስራዎቹ መጨረሻ አዲስ አበባ የገባ፡፡ ከዛም የአብነት ተማሪ ሆነና ቅዳሴና ቅኔ ሞካከረ፡፡ እሱ አልሆን ሲለው ጎዳና ወጥቶ ጎዳና አዳሪ ሆነ፡፡ ቀጠለና የለማኝ መሪ (sighted guide) ሆነ፡፡ እሱም ሲያልፍ ‹ለምን አልማርም?› ብሎ ትምህርት ተማረና ዩንቨርሲቲ በገባ በዓመቱ ‹ማርክሲስት› ሆነ፡፡ ትምህርቱንም ለአቢዮቱ ሲባል ተወውና መፅሃፍ ነጋዴ ሆነ፡፡ ማርክሲስት ነጋዴ! ‹ከወገብ በላይ ታቦት፣ ከወገብ በታች ጣኦት› እንዲሉ የትናንት ቀዳሹ ሕሩይ ዛሬ ማርክስዚምን ወደደ፡፡ የሕሩይ ማርክሲዝም ከትናንት ማንነቱ እጅግ በተለየ መንገድ ወሰደው፣ የመፅሃፍ አርታኢነት፡፡ መፅሃፍ ሲያነብ፣ ሲተረጉም፣ ሲፅፍና የአርትኦ ስራ ሲሰራ ውሎ ጫት ይቅማል፤ በዛ ላይ አረቄም ይሞካክራል፡፡ በመጨረሻ አበደ፡፡ ከዛ በኋላ ያለው የሕይወቱ ምዕራፍ ብዙ ያሳዝናል፡፡

በኋላ ከአዕምሮ ሕመሙ ሲያገግም ግን የሚገርም ነገር አደረገ፡፡ ‹እብድ› እያለ ሲያደርጋቸው ነበሩትንና የሚያስታውሳቸውን ነገሮች ሁሉ በተርታ ፅፎ ‹እብዱ› በሚል ርዕስ መፅሃፍ አሳተመ፡፡ ይህ መፅሃፉ ለሕሩይ ከብዙ ስራዎቹ አንዱ ነው፡፡ ስለ አዲስ አበባ ለመፃፍ ከሕሩይ የተሻለ ምሳሌ ማግኝት ይከብዳል፡፡ እሱም ‹ወይ ዐዲስ ዓበባ› በሚል ርዕስ (እውነትን መሰረት ያደረገ) መፅሃፍ ፅፎ አዲስ አበባ ከሩቅ ሲያይዋት ምን እንደምትመስል ይተርካል፡፡ በሕሩይ የገጠር ሕይወት አይን አዲስ አበባ ገነት ነበረች፡፡ ሕሩይ እንዲያውም በመደነቅ ‹‹ለካ የዐዲስ ዓበባን ሰው ፎቶ እያነሱ ነው ወደ ገጠር ‹ምስለ መላዕክትና ሰማዕት› እያሉ የሚልኩልን›› በማለት እሱ ከሚያውቀው ገጠርና ሕዝቡ አንፃር አዲስ አበባ ገነት፣ ነዋሪዎቿም መልዓክት እንደሆኑ ይገልፃል፡፡ ገነት ሆና ከሩቅ የታየችው አዲስ አበባ ሲገባባት ጎዳና ላይ አስተኝታዋላች፣ ‹አቢዮተኛ› አድርጋዋለች፣ አሳብዳ አስለፍልፋዋለች … በስተርጅናውም ‹ከጋራ ኮንዶሚኒየም ቤቶቿ› በአንዱ ይኖር ዘንድ ፈቅዳለታለች፡፡ ሕሩይ አዲስ አባባን ከሩቅ አይቶ ጎምጅቶባታል፡፡ አዲስ አበባን ጉያዋ ስር ሆኖም ተሰቃይቶባታል፡፡ ዛሬ ደግሞ አዲስ አበባ ሕሩይን እንከባከብኻለሁ እያለችው ነው፡፡ ሕሩይ ሚናስ – ራሱን ‹አውግቸው ተረፈ› ብሎ የሰየመ ሰው፡፡

ይህ የሕሩይ ብቻ ታሪክ አይደለም፡፡ የብዙ ኢትዮጵያዊያንም እንጂ፡፡ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ አዲስ አበባን ከከተማም በላይ የስልጣኔ ምልክት አድርጎ ነው የሚቆጥራት፡፡ እንዲያውም ሌሎች ከተሞች የሚለሙት ከአዲስ አበባ የሚመጡ ነዋሪዎች እንዲዝናኑባቸው ሁሉ እስኪመስል ድረስ የሌሎች ከተሞችን ዕድገት ሁሉ ወሳኟ አዲስ አበባ እየሆነች ነው፡፡ ከአዲስ አበባ ውጭ ባሉ አካባቢዎች ‹የአዲስ አበባ እንግዶች መጥተዋል› ከተባለ ነገሩ ትልቅ ነው፡፡ አንዳንዴማ ‹እሷ እኮ አዲስ አበባ ቤት አላት› ሲባል ሁሉ ነው ሃብት የሚቆጠረው፡፡

አዲስ አበባ አንድ ከተማ ብቻ ነች ማለት ከባድ ነው፡፡ ከሀገሪቱ አጠቃላይ ሕዝብ 3.6 በመቶው ብቻ ቢሆንም አዲስ አበባ የሚኖረው ቀሪው የሀገሪቱ ሕዝብ ያለ አዲስ አበባ ምንድን ነው? እስኪባል ድረስ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ለተባለው ዓለም የስበት ማዕከል (center of gravity) ናት፡፡

1. “Addis Ababa: The 3rd most ‘Primate City’ on earth”

ጅኦግራፈሩ ማርክ ጀፈርሰን በጎርጎሮሳዊያን አቆጣጠር በ1939 አንድ የከተሞች እድገት ምጥጥን (balance) የሚገልፅ ሃሳብ ይዞ ብቅ አለ፡፡ የአውራ ከተማ (Primate City) ፅንሰ ሃሳብን፡፡ እንደ ጀፈርሰን አገላለፅ አንድ ከተማ በሀገሪቱ ውስጥ ካሉት ሌሎች ከተሞች መካከል በሕዝብ ቁጥር ትልቁ ሲሆንና የሕዝብ ቁጥሩም በሁለተኝነት ከሚከተለው ከተማ በእጥፍ ሲበልጥ ያ ከተማ ‹አውራ ከተማ› (Primate City) ይባላል፡፡ (በኋላ በጀርመናዊው ጅኦግራፈር ዋልተር ክራይስትለር የተፈጠረው የCentral Place Theory (CPT) በበኩሉ አውራነት የሚለካው አውራው ከተማ ከተከታዩ በሁለት ዕጥፍ ከበለጠ ነው በማለት ሌላ መከራከሪያ አቅርቧል)፡፡ ለማንኛውም ጀፈርሰን ይሄን የከተማ አውራነት መስፈርት (primacy rule) ካስቀመጠ ከአስር ዓመታት በኋላ በተለምዶ ‘Zipf’s law’ የሚባለውና በሳይንሳዊው አጠራር ‘Rank Size Rule’ እየተባለ የሚጠራው የምጥጥን (proportionality) ሂሳብ በአሜሪካዊው የስነ ቋንቋ ምሁር ጆርጅ ዚፒፍ ብቅ አለ፡፡ ዚፒፍ ምጥጥኑን ከቋንቋ ጋር አያይዞ ያቀረበው ቢሆንም በኋላ ወደሌሎች ጉዳዮችም አድጓል፡፡ በዚህም መሰረት እንደ ዚፒፍ ሎው የአንድ ሀገር የከተማ እድገት ጤነኛ ነው የሚባለው በአንድ ሀገር ውስጥ ካለው በሕዝብ ቁጥሩ ትልቁ ከተማ ቀጥሎ በሁለተኝነት የሚገኝው ሁለተኛው ከተማ በሕዝብ ትልቁ የሆነውን ከተማ ግማሽ ያክል ሕዝብ ያለው መሆን ይኖርበታል፡፡ ሶስተኛው ትልቅ ከተማ ደግሞ የትልቁን ከተማ ሲሶ ያህል ሕዝብ ሊኖርበት ይገባል፡፡ አራተኛው ትልቅ ከተማ ደግሞ የትልቁን ከተማ ሩብ ያህል ሕዝብ ሊኖርበት ይገባል… እያለ ምጥጥኑን ይቀጥላል፡፡

እንግዲህ ይሄን ህልዮታዊ መነሻ ይዘን፡፡ የአውራ ከተማ መኖር ምንን ያመላክታል የሚለውን ጉዳይ ስናይ ነው የሕልዮቶቹ መሰረት የሚገለፅልን፡፡ አንድ ሀገር አውራ ከተማ አላት ማለት አውራ የተባለው ከተማ የሀገሪቱ የትኩረት ነጥብ (national focal point) ነው ማለት ነው፡፡ ከዛም ባለፈ ያ ከተማ የሀገሪቱን ማሕበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች በዋነኛነት በያኝ (strong pull factor) ነው ማለት ነው፡፡ በሌላ አነጋገር ሀገሪቱ የንጉሳዊ ግርማ (King Effect) ሰለባ ነች ማለት ነው፡፡ ስለ ሀገሪቱ ማውራት ማለት ስለ አውራው ከተማ ማውራት ነው፡፡ በዚህም ምክንያት በመዓከሉ (center) እና በዳር ሀገሩ (periphery) መካከል የእኩልነት ሚዛን እጅግ ተዛብቷል (imbalance) እንደማለት ነው፡፡

1.1. ሁለተኛ ከተማ (Secondary City)

በሌላ በኩል ደግሞ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የአውራ ከተማን ፈተና ለመከላከልና ፍትሃዊ የከተማ እድገት እንዲኖር ሲባል የዓለም ባንክን ጨምሮ ብዙ ፖሊሲ አውጭዎች የሁለተኛ ከተማ (Secondary City) አማራጭን በማቅረብ ላይ ይገኛሉ፡፡ ይህም ማለት ከትልቁ ከተማ ባለፈ በሀገራት ውስጥ ከትልቁ ከተማ ብዙም ያልራቁ (አንዳንዶች ከ500,000 – 3,000,000 ነዋሪ ያለባቸው ከተሞች ሲሉ ሁለተኛ ከተማነትን ያብራራሉ) አማራጭ ከተሞችን መፍጠር ነው፡፡ ደቡብ ምስራቅ እስያ በዚህ በኩል በጣም የተሳካለት የዓለማችን ክፍል ነው፡፡

1.2. ኢትዮጵያስ?

የኢትዮጵያን ጉዳይ ስንመለከት ከላይ ከቀረቡት ሕልዮቶችና የፖሊሲ አውጭዎች ምክረ ሃሳብ እጅግ በተቃራኒው እናገኛታለን፡፡ የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ባለስልጣን በሃምሌ 2007 ባወጣው ሪፖርት መሰረት ኢትዮጵያ 973 ከተሞች እንዳሏት የገለፀ ሲሆን፤ ከሀገሪቱ አጠቃላይ ሕዝብም 19 በመቶ የሚሆነው (ይህ አሃዝ አከራካሪ ነው) በከተማ ውስጥ ይኖራል ይላል ሪፖርቱ፡፡ ምንም እንኳን ኢትዮጵያ 973 ከተሞች ቢኖሯትም ከአምስቱ የከተማ ነዋሪዎች መካከል አንዱ በአዲስ አበባ ከተማ ነው የሚኖረው፡፡ በሌላ አነጋገር በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ (አዲስ አበባን ሳይጨምር) ከአንድ መቶ ሺህ ሕዝብ በላይ ያላቸው አስራ ስድስት ከተሞች ያሉ ሲሆን፤ የአስራ ስድስቱ ከተሞች ሕዝብ ተደምሮ ከአዲስ አበባ ከተማ ሕዝብ ጋር እኩል ነው፡፡

የማርክ ጀፈርሰንን የአውራነት ሕግ (primacy rule) እዚህ ላይ አምጥተን ስንመለከት አዲስ አበባን ከአውራም አውራ ሆና እናገኛታለን፡፡ ይሄም የሚሆነው በአንድ ሀገር ውስጥ ያለው ትልቅ ከተማ (አዲስ አበባ) በሀገሪቱ ውስጥ ካለው ሁለተኛ ትልቅ ከተማ (በሃምሌው የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ባለስልጣን ሪፖርት መሰረት አዳማ ከተማ ናት ሁለተኛዋ ብዙ ሕዝብ የሚኖርባት ከተማ) በእጥፍ ከበለጠ አውራ ከተማ እንደሚባል ከላይ ያየን ሲሆን፣ በዚህ ስሌት መሰረትም አዲስ አበባ ከተከታዩ አዳማ ወደ አስራ አንድ እጥፍ እንደምትበልጥና ይሄም አዲስ አበባ ከታይላንዷ፣ ባንኮክና ከፔሩዋ ሊማ ቀጥላ በዓለም ላይ ሶስተኛዋአውራ ከተማ ሲያደርጋት በአፍሪካ ደግሞ አንደኛዋ ያደርጋታል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ይህ ግዝፈቷ የዚኮፍን የምጥጥን ሎው እንኳን መተግበር ማሰብም ከባድ ያደርገዋል፡፡ ይህ የተዛባ ምጥጥን አዲስ አበባ ከመመስረቷ ጀምሮ የተፈጠረ ነው ማለት ደግሞ ከባድ ነው፡፡ የአለፈውን የመቶ ዓመት እድገት እንኳን ብንመለከት በ1910 የአዲስ አበባ ከተማ ሕዝብ 65,000 የነበረ ሲሆን ይህ ቁጥርም በጊዜው ከሀረር ከተማ ሕዝብ ጋር እኩል ነበር፡፡ ከሃያ አምስት ዓመታት በኋላ 1935 የአዲስ አበባ ከተማ ሕዝብ 100,000 ሆነ፡፡ ከሌላ ሃያ አምስት ዓመታት በኋላ በ1961 የአዲስ አበባ ከተማ ሕዝብ 443,728 ደረሰ፡፡ አሁንም ከሌላ ሃያ አምስት ዓመታትም በኋላ በ1984 የአዲስ አበባ ከተማ ሕዝብ 1,423,111 ደረሰ፡፡ በመጨረሻም ከ35 ዓመታት በኋላ በ2015 የአዲስ አበባ ከተማ ሕዝብ ከእጥፍ በላይ ጨምሮ ዛሬ 3,194,000 ደርሷል፡፡ ከመቶ ዓመታት በፊት በጊዜው በሕዝብ ቁጥር ሁለተኛ ከነበረችው የሀረር ከተማ ጋር ተመጣጣኝ ቁጥር የነበረው የአዲስ አበባ ከተማ ሕዝብ ዛሬ በሁለተኝነት ከምትገኝው አዳማ ከተማ አስራ አንድ እጥፍ በልጣ በአውራ ከተማነት በሩቅ ተቀምጣለች፡፡

ስታንሊ ብሩን የተባሉ ፀሃፊ ‹‹የአውራ ከተማ መኖር በራሱ የሀገሪቱ እድገት ጤናማ እንዳልሆነና የተዛባ እንደሆነ ማሳያ ነው፡፡ ይሄም ማዕከሉ (center) ከዳሩ (periphery) አለመመጣጠናቸውን ያስገነዝበናል› ይላሉ፡፡ እንግዲህ የአሁኗ ኢትዮጵያን ፍትሃዊነት አዲስ አበባ በደንብ የምትገልፃት ይመስላል፡፡

አዲስ አበባ በታሪኳ ሶስት ጊዜ ከዋና ከተማነቷ የመቀየር እጣ ፋንታ ተጋርጦባት እንደምንም አልፋዋለች፡፡ የመጀመሪያው በአፄ ምኒልክ ዘመን በአካባቢዋ ያለው የማገዶ እንጨት በማለቁ ምክንያት ዋና ከተማው ወደ አዲስ ዓለም ለመቀየር በታሰበበት ወቅት ባህር ዛፍ ከአውስትራሊያ መጥቶ አዲስ አበባን ከመቀየር አድኗታል፡፡ ለሁለተኛ ጊዜ ጣሊያን አዲስ አበባን በተቆጣጠረበት ወቅት አዲስ አበባ ተራራማ ከተማ ላይ በመሆኗ ጣሊያኖቹ የራሳቸውን የቅኝ ግዛት ዋና ከተማ (colonial city) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ አካባቢ ለመመስረት ጥረት አድርገው በፋይናንስ እጥረት ምክንያት ሊተዉት ችለዋል፡፡ እንዲሁም አፄ ኃይለስላሴ የቀደመውን የተንቀሳቃሽ ዋና ከተማ (roving cities) ልምድ ለማስቀጠልና የራሳቸውን ዋና ከተማ ለማቋቋም በማሰብ ባህርዳርን ዋና ከተማቸው ለማድረግ አስበው እንደነበር ታሪክ ፀሃፊው በላይ ግደይ ‹አዲስ አበባ ያብባል ገና› ባሉት መፅሃፋቸው ላይ ይጠቁማሉ፡፡ ዛሬ አዲስ አበባ ዋና ከተማ ብቻ ሳትሆን ‹ሀገር› ናት፡፡ የበታቾቿን በሩቅ የምታይ ከተማ፡፡

በሌላ በኩል እነ ዓለም ባንክ እያስተዋወቁት የሚገኝው የሁለተኛ ከተማ (Secondary City) ፅንሰ ሃሳብም በአሁኗ ኢትዮጵያ ቦታ የሌለው ጉዳይ ነው፡፡ በፖለቲካና የንግድ ማዕከልነት የአውራዋን አዲስ አበባን ሚዛን የሚገዳደር አይደለም፤ ተስፋ እንኳን ያለው ከተማ አለ ማለት በጣም ከባድ ነው፡፡ ይህ የአዲስ አበባ አውራነትም ከተማዋን በሀገሪቱ ውስጥ በነዋሪ ደረጃ የመሰረታዊ አገልግሎቶች በቀላሉ የሚገኝባት (the highest concentration of basic service facilities per population) ቀዳሚ ከተማ አድርጓታል፡፡ ይሄም ከተማዋን ‘privileged position’ ያሰጣት ከመሆኑም ሌላ፤ አዲስ አበባን እጅግ ግዙፍና የማይደረስባት አይነት ከተማ አድርጓታል፡፡

ከአዲስ አበባ ምስረታ ጋር ተያይዘው ከሚነገሩ አፈ ታሪኮች አንዱ፣ የአፄ ምኒልክ ሃይለ መለኮት አያት የሆኑት ንጉሰ ሸዋ ሳህለስላሴ በአንድ ወቅት ጉለሌ የሚገኝ አንድ ዛፍ ስር ቁጭ ብለው ‹እዚህ አካባቢ የልጅ ልጆቼ ትልቅ ከተማ ሲመሰርቱ ይታየኛል› ብለው ነበር ይላል፡፡ ሳህለስላሴ የዛሬዋን አዲስ አበባ ቢያዩ ‹እንዴ እኔ በራዕይ ያየሁት እኮ ሀገር አይደለም ከተማ ነው› ብለው መደናገራቸው የሚቀር አይመስለኝም፡፡

የፌደራል ሀገሮች ተሞክሮ እንደሚያሳየን ፌደራሊዝም ‹አውራ ከተማን› (Primate City) ያጠፋል፡፡ የደቡብ ምስራቅ ተሞክሮ እንደሚያሳየን ደግሞ ልማታዊ መንግስት በዛ ያሉ ሁለተኛ ከተሞችን (Secondary Cities) ይፈጥራል፡፡ አውራዋ አዲስ አበባ የአውራዎች አውራ እየሆነች እየሄደች ሲሆን፡፡ አውራ ብቻ ሳትሆን ሁለተኛ ከተማም (Secondary City) ራሷ አዲስ አበባ ነች፡፡ አዲስ አበባ ብቻዋን እንዲህ ገዝፋ የአውራም አውራ እስክትሆን ድረስ ፖሊሲ አውጭዎቹ የት ሂደው ነው ብሎ መጠየቅ እዚህ ጋር ተገቢ ነው፡፡ የአሁኗ አዲስ አበባ ሕጋዊ (Legal status) ምንድን ነው ብለንም መጠየቅ ተገቢ ነው፡፡

2. አዲስ አበባ ምንድን ናት?

ኢትዮጵያ የፌደራል ስርዓትን በሕገ መንግስት ደረጃ ከተቀበለች ሁለት አስርት ዓመታትን አስቆጥራለች፡፡ የኢትዮጵያ የፌደራል ስርዓትም በሕገ መንግስት ደረጃ ዘጠኝ ክልሎችንና አዲስ አበባን እንደ አንድ የፌደራል ከተማ አስተዳደር (ድሬ ዳዋ በሶማሌና በኦሮሚያ ክልሎች መካከል ያለው የይገባኛል ጥያቄ ‹ዘላቂ የሆነ ሕጋዊ መፍትሔ እስኪያገኝ› ለፌደራል መንግስቱ ተጠሪ በመሆን በአዋጅ ቁጥር 416/1996 የተቋቋመች የከተማ አስተዳደር ናት) በማድረግ ተቋቁሟል፡፡ በሕገ መንግስቱም ሆነ በኋላ ከተማዋን በሕግ ለማቋቋም በወጡት ቻርተሮች የከተማዋ ሕጋዊ ‹ስታተስ› (ከዋና ከተማነት ባለፈ) በግልፅ ባለመቀመጡም የከተማዋ ‹ስታተስ› ለተመሳሳይ ጥያቄ የተለያዩ መልሶችን እየሰጠ ቀጥሏል፡፡ ዓለም ላይ ባሉ የተለያዩ የፌደራል ስርዓቶች ዋና ከተማ ከዚህ በሚከተሉት ሶስት ጎራዎች በአንዱ ላይ ይመደባል፡፡ ራሱን የቻለ ክልል (City State)፣ በሕግ በፌደራል ቀጠናነት የተመደበ ከተማ (Federal District)፣ እና በአንድ ክልል ውስጥ የሚገኝ አንድ ከተማ (A City in A State)፡፡ ኢትዮጵያም በሕግ የፌደራል ስርዓትን ያቋቋመች ሀገር በመሆኗ ዋና ከተማዋ አዲስ አበባ በየትኛው ጎራ ትመደባለች ለሚለው ጥያቄ አንድ አይነት መልስ ማግኝት አስቸጋሪ ነው፡፡ ይህ አስቸጋሪ ሁኔታም ነው በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ክልል መካከል ያለው ውዝግብ እንዳይፈታ አይነተኛ አስተዋፅኦ እያደረገ ያለው፡፡ ከላይ ከተጠቀሱት ሶስቱ መደቦች አንፃር የአዲስ አበባን ‹ስታተስ መመልከት› ጉዳዩን በበለጠ እንድንረዳው ይረዳናልና እሱን እንመልከት፡፡ ለመሆኑ አዲስ አበባ ምንድን ናት?

2.1. ራሷን የቻለች ክልል (City State) ናት

የፌደራል ስርዓትን ተግባራዊ ያደረጉ ሀገሮች ከሚያጋጥሟቸው ፈተናዎች አንዱ ዋና ከተማን መምረጥና መሰየም ነው (የስዊዘርላንድ ሕገ መንግስት በሕገ መንግስት ደረጃ ዋና ከተማ ከመሰየም የተቆጠበውም በዚህ ውዝግብ ምክንያት ነው)፡፡ የፌደራል ስርኣት የመንግስት ስራን በማዕከሉ መንግስትና በክልሎች መካከል የሚከፍል በመሆኑ ዋና ከተማዋን የትኛው ክልል ላይ ማድረግ አለብን የሚለው ጥያቄ አወዛጋቢ ነው፡፡ እንደ ጀርመን እና ቤልጅየም ያሉ የፌደራል ሀገሮች ለዚህ መፍትሔ ብለው ያቀረቡት ሀሳብ ዋና ከተማውን ራሱን የክልል ማዕረግ በመስጠት ከፌደራሉም ሆነ ከክልል መንግስታት ነፃ ማውጣትን ነው፡፡ በመሆኑም በርሊን በአሁኑ ወቅት ከአስራ ስድስቱ የጀርመን ክልሎች አንዷና ዋና ከተማ ስትሆን የቤልጀሟ ብራሰልስም ከቤልጅየም ሶስት ክልሎች አንዷ በመሆን የተፎካካሪዎቹ ፍሌሚሽና ዋሎን ክልሎች አስታራቂ ሁና በመሃል ትገኛለች፡፡

ታዲያ አዲስ አበባ ከዚህ ሞዴል ጋር ምን አገናኛት? በርግጥ አሁን በስራ ላይ ያለው ሕገመንግስት ያቋቋመው ዘጠኝ ክልሎችን ብቻ ነው፡፡ አዲስ አበባ ደግሞ ከነዚህ ክልሎች ውጭ ናት፡፡ ነገር ግን አዲስ አበባን በዋና ከተማነት ያቋቋመው የሕገ መንግስቱ አንቀፅ 49ን በጥልቀት ስንመለከት በንዑስ አንቀፅ ሁለት ላይ አዲስ አበባን ራሷን በራሷ የማስተዳደር ሙሉ መብት ይሰጣታል፡፡ ይህ አንቀፅም በሽግግር መንግስቱ ወቅት በአዋጅ ቁጥር 07/1984 እንደ ራስ ገዝ አስተዳደር በመሆን የተቋቋመችውን አዲስ አበባን መንፈስ ያጠናክራል፡፡ ይሄንም ስንመለከት አዲስ አበባ በተግባር (de facto) ራሷን የቻለች ክልል ትመስላለች፡፡ በነገራችን ላይ አዲስ አበባ ራሷን ችላ በሕግ ደረጃ (de jure) ክልል እንድትሆን ከሽግግሩ ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ የሚጎተጉቱ አካላት ብዙ ናቸው፡፡

2.2. የፌደራል ቀጠና (Federal District) ናት

በሌላ በኩል የፌደራል ዋና ከተማን የመምረጥ ፈተና ለማለፍ በዛ ያሉት ፌደራል ሀገሮች ዋና ከተማዋን በፌደራል ቀጠናነት (Federal District) በሕግ በመከለል ተጠሪነቷን ሙሉ ለሙሉ ለፌደራል መንግስት የማድረግን አሰራር ይጠቀማሉ፡፡ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆኑት አሜሪካና ሕንድ ናቸው፡፡ አሜሪካ ከሜሪላንድና ከቨርጅኒያ ግዛቶች መሬት በመውሰድ ዋሽንግተን ዲሲን በዋና ከተማነት ሰይማ (ስፋቱ ከአስር ማይል መብለጥ የለበትም የሚል ገደብ በማስቀመጥ) ተጠሪነቷን ለኮንግረስ አድርጋለች፡፡ ሕንድም ዴልሂን ዋና ከተማና የፌደራል ቀጠና አድርጋ ተጠሪነቱን ለምክር ቤት አድርጋለች፡፡ ይህ አይነት የዋና ከተማ አደረጃጀት የራሱ የሆነ (በተለይም ከምርጫ፣ ግብር እና የክልሎች መብት አንፃር) ችግሮች ያሉበት ነው፡፡ ከታች ለማየት እንሞክራለን፡፡

አዲስ አበባን ስንመለከት የህገ መንግስቱ አንቀፅ 49 (3) እና (4) አዲስ አበባ ተጠሪነቷ ለፌደራሉ መንግስት መሆኑን በመግለፅ የአዲስ አበባ ቀጠና የፌደራል ቀጠና እንደሆነ በተዘዋዋሪ ያስረዳል፡፡ ይህ ብዙ ሰዎች የሚስማሙበት ሃሳብ ቢሆንም ተያያዥ ችግሮች ግን በየጊዜው መነሳቸው አልቀረም፡፡

2.3. በአንድ ክልል የምትገኝ አንድ ከተማ (A City in a State) ናት

ሌላው ከፌደራል ዋና ከተማ አመሰራረት ጋር ተያይዞ የሚቀርበው መፍትሔ ደግሞ ዋና ከተማዋን ከክልሎች (States) በአንዱ ከተማ ላይ ማድረግና ክልሎች ተገቢውን ጥቅም እንዲያገኙ ማድረግ የሚለው ነው፡፡ የዚህ መፍትሔ ምሳሌ ተደርጋ የምትቀርበው ካናዳ ነች፡፡ የካናዳዋ ዋና ከተማ ኦታዋ ከካናዳ ስድስት ክልሎች አንዷ በሆነችው ኦንታሪዎ ግዛት ውስጥ የምትገኝ ከተማ ነች፡፡ ኦንታሪዎም እንደ ዋና ከተማ መቀመጫ ክልልነቷ ከኦታዋ ማግኝት የሚገባት ጥቅም በሕግ የተደነገገና የፀና ነው፡፡ ይህ አካሔድ በሌሎች ክልሎች ዘንድ ቅሬታ ይፈጥራል የሚል ትችት ይቀርብበታል፡፡

የአዲስ አበባን ጉዳይ ከዚህ አንፃር ስንመለከተው ደግሞ ከላይ በጠቀስነው የሕገ መንግስቱ አንቀፅ 49 (5) ላይ ‹የኦሮሚያ ክልል […] አዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል መሃል ላይ የሚገኝ በመሆኑ […] ያለው ልዩ ጥቅም ይጠበቅለታል› ይላል፡፡ ይሄም ማለት በሌላ አነጋገር አዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የምትገኝ አንድ ከተማ ነች እንደማለት ነው፡፡

2.4. ቻርተርድ ከተማ (Chartered City) ናት

አዲስ አበባ ሶስቱንም የፌደራል ዋና ከተማ ባህሪ አዳለ በመያዝ በየትኛው ሕጋዊ ‹ሰታተስ› ላይ እንዳለች ግራ የምታጋባ ከተማ ነች፡፡ ከዚህ በባሰ ደግሞ ከተማዋ በራሴ ቻርተር የምትተዳደር ከተማ (Chartered City) ነኝ በማለት ራሷን በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ቻርተር 87/1989 አቋቁማለች (ቻርተሩ በ1995 በአዋጅ ቁጥር 311/1995 እና በአዋጅ ቁጥር 361/1995 ሙሉ ለሙሉ ተሸሽሏል፡፡ እንዲሁም በ1996 በአዋጅ ቁጥር 408/1996 በከፊል ተሻሽሏል)፡፡ ይህ በዋናነት በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች የከተማ ድህነትን ለመቀነስ እንደስትራቴጅ እየተወሰደ ያለ የአወቃቀር አይነት አዲስ አበባ ለምን እንደመረጠችው ብዙም ግልፅ ባይሆንም፤ በሁሉም ቻርተሮች ላይ ዋነኛ ዓላማው ‹የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ራሱን በራሱ የማስተዳደር ሙሉ ስልጣን እንዳለው […] በሕገ መንግስቱ በመደንገጉ› ምክንያት እንደሆነ ተገልፆ እናገኛለን፡፡ አዲስ አበባ ቻርተርድ ከተማ ነች ማለትም ከላይ 2.1 ላይ ለማመላከት የተሞከረውን የክልል ማዕረግ (status of state) የሚያጠናክር ሃሳብ ሆኖ የከተማዋን ስታተስ ለመወሰን ከላይ ያየናቸውን የዋና ከተማ ብያኔ ክርክር የበለጠ ያጦዘዋል፡፡

እንግዲህ አዲስ አበባ ራሷን የቻለች ክልል ናት፣ ተጠሪነቷ ለፌደራል መንግስቱ የሆነች የፌደራል ቀጠና ናት፣ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የምትገኝ አንድ ከተማ ናት እንዲሁም በራሷ የቆመች ቻርተርድ ከተማ ነች የሚሉ የራሳቸው አሳማኝ ምክንያት ያላቸው መከራከሪዎች ይቀርባሉ፡፡ ይህ ግልፅነት የጎደለው የከተማዋ ‹ስታተስም› አሁን ከተማዋን አስመልክቶ ለሚነሱ ውዝግቦች መነሻና መድረሻ ነው፡፡

3. ‹የአንተም ተው፣ አንችም ተይ ፌደራሊዝም› እና መዘዙ

[የኢትዮጵያ የሕገ መንግስት ኮሚሽን] ሰብሳቢ [አቶ ክፍሌ ወዳጆ] [የኮሚሽኑ] አባላት ተሳትፎና ኮሚሽን የሥራ ሒደት በተመለከተ አልፎ አልፎ አባላት በስብሰባ ላይ ያለመገኝት ሁኔታ በማሳየታቸው የስራ መጓተት እየተከሰተ መሆኑን፣ ከፓናሎች የሚጠበቁ ሪፖርቶች በተፈለገው ጊዜ ሊቀርቡ እንዳልቻሉና ይኸውም የፓናል አባላቶች በስብሰባ አለመገኘት ዋነኛው ምክንያት መሆኑን ገልፀው፣ ለመጪው ጊዜ በእያንዳንዱ ስብሰባ በሚነሱ ጉዳዮች ላይ በበቂ በመዘጋጀት ለውሳኔ የሚያበቃ ሰፈ ግንዛቤ በመጨበጥ መገኘት ከእያንዳንዱ አባል እንደሚጠበቅ አሳስበው፣ […] የአዲስ አበባን የመናገሻ ከተማነት ደረጃ (status) እና ወደፊት አከላለስ ሊኖራት የሚችለውን ቦታ አስመልክቶ በሚዘጋጀው የመወያያ ሰነድ (working paper) ውስጥ እንዴት ማስቀመጥ እንደሚቻል ውይይት ማድረግ እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል፡፡››

ይህ ሐሳብ የተገለፀው የአሁኑን የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት ለማርቀቅ የተቋቋመው የሕገ መንግስት ኮሚሽን ሰብሳቢ በነበሩት አቶ ክፍሌ ወዳጆ ጳጉሜ 1- 1985 በኮሚሽኑ 39ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ነው፡፡ እንደ ሰብሳቢው ሐሳብ ከሆነ ሕገ መንግስትን ያህል ሰነድ ለማርቀቅ የተዋቀረው ኮሚሽን አባላት በኮሚሽኑ ስብሰባ ላይ አለመገኘታቸው አሳስቧቸውና የአዲስ አበባን ደረጃ (status) ገና ሳይወስኑ እስከ አሁን መቆየታቸው አሳስቧቸው ነው፡፡ ሰብሳቢው አቶ ክፍሌ ይሄን ቢሉም ይሄን ማስጠንቀቂያ በተናገሩበት እለት እንኳን ከ27 የኮሚሽኑ አባላት መካከል ስምንት የሚሆኑት አልተገኙም ነበር፡፡ አዲስ አበባን አስመልክቶ የቀረቡት ጉዳዮች በሕገ መንግስታዊው ጉባኤ የተወሰነ ውይይት ቢደረግበትም፣ በኮሚሽን ደረጃ ብዙም ውይይት እንዳልተደረገበት በጊዜው የኮሚሽኑ አባል የነበሩት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ይገልፃሉ፡፡ እንግዲህ ያ በቸልተኝነት የታለፈ ጉዳይ ነው አንዱ የዛሬው ችግር መነሻ፡፡ አዲስ አበባ የክልልም፣ የፌደራል ግዛትም እንዲሁም የአንድ ክልል ከተማ መልክ ይዛ ከሶስቱ አንዱን መሆን አለመቻሏ በጊዜው ሲሟገቱ የነበሩ ሁሉንም አካላት ለማስደሰት በሚል የታለፈ ጉዳይ ይመስላል፡፡

የተለያዩ ምሁራን አዲስ አበባን አስመልክቶ የተለያዩ ጥያቄዎችን እያነሱ ሕገ መንግስቱ መመለስ አለመቻሉን ሊያሳዩን ይሞክራሉ፡፡ መሰረታዊዎቹን ጥያቄዎች እዚህ ላይ ማንሳት ተገቢ ስለሚሆን አንስተን እንመልከታቸው፡፡

1. የአሜሪካ ዋና ከተማ የሆነችው ዋሽንግተን ዲሲ በተቋቋመችበት ወቅት መሬት ከሜሪላንድና ከቨርጅኒያ ስቴቶች ተቆርጦ ተሰጥቷት ነው የተቋቋመችው፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን ቨርጅኒያ መሬቴን መልሽልኝ በማለት መሬቷን በሕዝበ ውሳኔ መሬት የማስመለስ ሒደት (retrocession) መሰረት አስመልሳለች፡፡ ሜሪላንድም እስከ አሁን አልጠየቀችም እንጂ ብትጠይቅ ልታገኝ እንደምትችል የሕገ መንግስት ምሁራን ይገልፃሉ፡፡ አዲስ አበባ የምትገኝው በኦሮሚያ ክልል ውስጥ እንደሆነ ሕገ መንግስቱ በግልፅ ይደነግጋል፡፡ ታዲያ ኦሮሚያ ‹መሬቴን ራሴ አስተዳድራለሁ› ብትል በምን አግባብ ነው መልስ የሚሰጠው?

2. አሁንም እዛው ዋሽንግተን ዲሲ እንቆይና ባራክ ኦባማን ጨምሮ ብዙ የአሜሪካ ፖለቲከኞች ዋሽንግተን ዲሲ ራሷን የቻለች ሃምሳ አንደኛ የአሜሪካ ‹ስቴት› ብትሆን ፍላጎት እንዳላቸው (ከመራጭነት መብት አንፃር) ይገልፃሉ፡፡ ሐሳቡ ወደ ፊት ሊተገበር የሚችል ጉዳይ እንደሆነም ምሁራን እያስረዱ ይገኛሉ፡፡ አዲስ አበባ ራሴን ችዬ ክልል ልሁን ብትል በምን አግባብ ነው የሚስተናገደው ለሚለው ጥያቄ የራስን ክልል የመመስረት መብት የሚሰጠው የሕገ መንግስቱ አንቀፅ 47 (2) መብቱን የሚሰጠው ‹ለብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች› ሲሆን አዲስ አበባ በምን ጎራ ላይ እንደምታርፍ ምንም የተገለፀ ነገር የለም፡፡

3. አዲስ አበባ አሁን ባላት ቁመና ቻርተርድ ከተማ እንደሆነች ከላይ ለማየት ሞክረናል፡፡ ቻርተርድ ከተሞችን (Chartered Cities) ከሌሎች ከተሞች (General Law Cities) የሚለያቸው ዋነኛው ጉዳይ ደግሞ የፌደራልንም ሆነ የክልል መንግስታትን ጣልቃ ገብነትን የሚያስወግድ አሰራር መተግበራቸው ነው፡፡ ታዲያ አዲስ አበባ ቻርተርድ ከተማ እንደመሆኗ ‹የፌደራል መንግስቱን ጣልቃ ገብነት አልፈልግም› ብትል ሕገ መንግስቱ ምን መልስ ይሰጣል?

እነዚህን ሕልዮታዊ ጉዳዮች ያነሳነው የአሁኑ የኢትዮጵያ ፌደሬሽን በተግባር የሌለ ብቻ ሳይሆን በአወቃቀር ደረጃም የማይመልሳቸው መሰረታዊ ጥያቄዎች መኖራቸውን ለማመላከት ነው እንጂ፤ ‹ጠያቂም መላሽም› እንደሌለ መረዳት ከባድ ሆኖ አይደለም፡፡

አዲስ አበባም ፖለቲካዊ፣ ሕጋዊ እንዲሁም መዋቅራዊ ችግሮቿ ሰንገው በያዟት በዚህ ወቅት ነው ‹የአዲስ አበባና ዙሪያዋ ኦሮሚያ ልዩ ዞን [የተቀናጀ] የጋራ ልማት ፕላን› ተብሎ የተሰየመው የሃያ አምስት አመታት ዕቅድ ብቅ ያለው፡፡

4. ‹[የተቀናጀ] የጋራ ልማት ፕላን› እና አዲስ አበባ

ስድስተኛው የዓለም የከተሞች ፎረም በጣሊያን ኔፕልስ ከሴፕቴምበር 02 እስከ 07 – 2012 ነበር የተካሔደው፡፡ ፎረሙ በተባበሩት መንግስታት ከተቋቋመበት ከ2002 ጀምሮ ባሉት አስር ዓመታት ውስት ለስድስተኛ ጊዜ ስብሰባ ማድረጉ ነበር፡፡ ከመላው ዓለም ከመጡ የተለያዩ ሀገር ተወካዮች አማካኝነት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የተወያየ ሲሆን የፎረሙ ዋነኛ አጀንዳም ‹Urban Future› የሚል ሲሆን በዋናነትም አራት መሰረታዊ ጉዳዮችን እንደመወያያ ይዞ ተካሂዷል፡፡ ከነዚህ አራት የውይይት ርዕሶች መካከል ቀዳሚው ‹Urban Planning: Institutions and Regulations› የሚል ነበር፡፡ በውይይቶቹ መጨረሻ ‹የዓለም የከተሞች ማንፌስቶን› ጨምሮ የተለያዩ የውይይቱ ውጤቶች ይፋ የተደረጉ ሲሆን፤ ከነዚህ የውይይቱ ውጤቶች መካከልም የዓለም ከተሞች የተቀናጀ የልማት ዕቅድን (Integrated Development Plan – IDP) ተግባራዊ እንዲያደርጉ የሚመክረው (recommendation) ይገኝበታል፡፡ ይህ በተባበሩት መንግስታት ደረጃ የቀረበው በ2012 ቢሆንም ከዛ በፊት በ2007 ‘Leipzig Charter on Sustainable European Cities’ የአውሮፓ ሀገሮች ይሄን የተቀናጀ አካሄድ በከተሞቻቸው ተግባራዊ ማድረግ እንዳለባቸው ተስማምተው ነበር፡፡

ከዚህ ጊዜ ወዲህ አንዳንድ የአፍሪካ ሀገሮች የተቀናጀውን አካሄድ ተግባራዊ ሲያደርጉ ተስተውሏል፡፡ የደቡብ አፍሪካዋ ኬፕ ታውን (ከ2012 -2017) እና የኬኒያዋ ናይሮቢ (ከ2014 -2019) በዚህ ረገድ ተጠቃሾች ናቸው፡፡ ደቡብ አፍሪካ እንዲያውም በሃገሪቱ ላሉ ከተሞች አጠቃላይ የተቀናጀ የልማት ዕቅድን ተግባራዊ እንዲያደርጉ መመሪያ እስከማውጣት ደርሳለች፡፡

4.1. የተቀናጀ የልማት ዕቅድ (Integrated Development Plan – IDP) ምን ለማለት ነው?

አንድ አይነት እና ወጥ የሆነ መልስ ማግኝት ባይቻልም የተለያዩ ከተሞች ከሰጡት የተለያየ ትርጉም አንፃር ሁለት መሰረታዊ ነገሮችን ማግኘት እንችላለን፡፡ 1. ሁሉም መሰረተ ልማት ላይ የሚሰሩ አካላት (የትራንስፖርት፣ የመብራት፣ የቤቶች ወዘተ) ተቀናጅተው ለተመሳሳይ ግብ እንዲተጉ ማድረግና 2. እቅዱን ያወጣው አካል ከእቅዱ ባለቤት (የከተማው ነዋሪ) ጋር አሳታፊ (participatory) በሆነ መንገድ በየጊዜው በመወያየት ተቀናጅቶ የሚሰራበት አካሄድ ነው፡፡ እንደ ናይሮቢ ያሉ ከተሞች በተቀናጀ የልማት ዕቅዳቸው የመሰረተ ልማት አገልግሎት (በተለይም ትራንስፖርት) በዙሪያው ካሉ አካባቢዎች (surroundings) ጋርም ለማቀናጀት ሙከራ አድርገዋል፡፡

በዚህ ጊዜ አዲስ አበባም በ1996 አዘጋጅታው የነበረው የከተማ ልማት እቅድ (ማስተር ፕላን) የትግበራ ጊዜው እያለቀ ነበርና የራሷን አዲስ ዕቅድ ለማዘጋጀት ቢሮ ከፍታ እንቅስቃሴ የጀመረችበት ጊዜ ነበር፡፡ መጀመር ብቻም ሳይሆን ስድስተኛው የዓለም የከተሞች ፎረም በተካሔደበት በመስከረም 2005 ለእቅዱ የሚያስፈልገውን መረጃ ለቀማ እንዳጠናቀቀች ይፋ አድርጋ እቅዱንም በጥቂት ወራት ውስጥ አጠናቅቄ ይፋ አደርጋለሁ ብላ ነበር፡፡ እንደተባለው እቅዱ በጥቂት ወራት ውስጥ እንደተጠናቀቀ ውስጥ ለውስጥ የተነገረ ሲሆን የመጀመሪያውንም ተቃውሞ በግንቦት 2005 ከኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) በወጣ መግለጫ አስተናግዳ ከዛ በኋላ የሆነውና እየሆነ ያለው ጉዳይ ሁሉም የሚያውቀው ነው፡፡ እዚህ ላይ ትክክለኛውን አከራካሪ ጉዳይ ለመለየት እንችል ዘንድ የእቅዱን መሰረት እና ይዘት ማየት ተገቢ ጉዳይ ነው፡፡

4.2. ‹ኢንደስትሪያላይዜሽን› ዘመነኛው ካርድ

‹‹የህዝባችን ኑሮ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚደርሰው አገራችን በኢንዱስትሪ የበለፀገች አገር ስትሆን ነው፡፡ አገራችን በአለም አቀፋዊው ኢኮኖሚያዊ ትብብር ውስጥ የሚኖራት ድርሻና ከዚሁ የምታገኝው ጥቅም በከፍተኛ ደረጃ ሊያድግ የሚችለው በኢንዱስትሪ የበለፀገች ስትሆን ነው፡፡ በመሆኑም የኢኮኖሚ ልማት እንቅስቃሴያችን ግብ በኢንዱስትሪ የበለፀገች አገርን መፍጠር መሆን አለበት፡፡ ሌላው ቀርቶ የግብርናና የገጠር ልማት እንቅስቃሴያችን የመጨረሻው ግብ አገራችን በኢንዱስትሪ የበለፀገች እንድትሆን ማድረግ ነው፡፡››

ይህ ሀሳብ የተገለፀው በ1994 በወጣው የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጅ ላይ ነው፡፡ ስትራቴጂው የግሉን ባለሃብት የኢንደስትሪያላይዜሽኑ መሰረት ማድረግና ግብርናው ኢንደስትሪውን እንዲመራው ማስቻል (Agriculture Development Led Industrialization – ADLI ) መሰረታዊ ጉዳይ እንደሆነ አስቀምጦ ያልፋል፡፡ ከዚህ ስትራተጅ የተከተሉት የእድገትና እና ትራንስፎርሜሽን እቅዶችም ዓላማቸው ግብርና የሚመራውን የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ወደ ኢንደስትሪ መር ማሸጋገርን (transformation) ዓላማ አድረገው የተቀረፁ ናቸው፡፡ ቁጥሮች እንደሚነግሩን ግን ኢሕአዴግ በኢንደስትሪው መስክ አልተሳካለትም፡፡ ኢንደስትሪው ያለፉት 50 አመታትን ተመሳሳይ መንገድ ይዞ የሚያዘግም ነው፡፡ ኢንደስትሪውን ይመሩታል የተባሉት ግብርና እና የግል ባለሃብቱም ከፕሮፓጋንዳ ባለፈ ብዙም በአካባቢው አይታዩም፡፡

ኢንደስትሪው የትም እንዳልደረሰ እና ‹ትራንስፎርም› የሆነ ብዙም ነገር እንደሌለ የተረዳው ኢሕአዴግ በድንጋጤ (frustration) የደቡብ ምስራቅ እስያ ተሞክሮ የሆነውን መንግስት መር (statist) ኢንደስትሪያላይዜሽን ተግባራዊ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ ከአስራ አምስት ዓመታት በፊት ኢንደስትሪውን ይመራዋል የተባለው ገበያና የግል ባለሃብትም ከአመራርነት ወርደው ቦታቸውን ለመንግስት አስረክበው ይገኛሉ፡፡

እንግዲህ በዚህ የኢሕአዴግ የኢንደስትሪያላይዜሽን ድንጋጤ ወቅት ነው ‹የአዲስ አበባና ዙሪያዋ የኦሮሚያ ልዩ ዞን የጋራ [የተቀናጀ] የልማት ፕላንም› የመጣው፡፡ የፕላኑ ዋነኛ ግብ ‹ሀገሪቱ የሰነቀችውን የኢንደስትሪ ሽግግር ዕውን መሆን ወሳኝ አስተዋፅኦ የሚያደርግ የኢንዱስትሪ ልማት ማስተናገድ [የሚችል ክልል መፍጠር]› እንደሆነ በእቅዱ መግቢያ ላይ ተገልፆል፡፡ (ክልል የተባለው ምን እንደሆነ ወደታች የምናው ጉዳይ ነው)፡፡ በእቅዱ የተለያዩ ቦታዎች ላይ ‹‹ክልሉ የሀገሪቱን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በአጠቃላይ የዕቅዱ ዋና አካል የሆነውን የኢንደስትሪ ሽግግር በተለይም እውን በማድረግ ረገድ ወሳኝ ሚና መጫወት ይጠበቅበታል››፣ ‹‹ከግብርና ወደ ኢንደስትሪ የሚደረገውን ጥረት ማገዝ››፣ ‹‹በ2030 በምስራቅ አፍሪካ ተወዳደሪ የሆነና በኢኮኖሚ ውስጥ መሪ ሚና የሚጫወት ማዕከል መፍጠር››፣ ‹‹የከተማዋን እና የዙሪያ ኦሮሚያ አካባቢን በጋራ በአፍሪካ ቀንድ ቀዳሚ የኢንዱስትሪ ክልል ማድረግ›› ወዘተ የሚሉ የዕቅዱ ዋነኛ ትኩረት ‹ኢንደስትሪያላይዜሽን› እንደሆነ የሚያመላክቱ ጉዳዮችን እናያለን፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ኢሕአዴግ ስልጣን ከያዘ ወዲህ የአሁኑን ጨምሮ ለአዲስ አበባ ከተማ የተዘጋጁትን እቅዶች ስንመለከት ‹የዘመኑ መንፈስ› እንደሚመራቸው እናያለን፡፡ የመጀመሪያውና በ1986 የተዘጋጀው እቅድ ዋነኛ ትኩረቱ ‹ሰላማዊ ከተማ› መገንባት እንደነበር የተገለፀ ሲሆን፤ በ1996 የፀደቀው የከተማዋ የልማት እቅድ ደግሞ በጊዜው የኢሕአዴግ ዋነኛ ማጠንጠኛ የነበረውን ‹ኢንቨስትመንት› መሰረት ያደረገ ሲሆን በጊዜው የከተማዋን መሪ ፕላን ለማጽደቅ በከተማዋ አዲስ ነጋሪት ጋዜጣ ላይ በወጣው አዋጅ ቁጥር 17/1996 ላይም እንደተገለፀው ‹‹[…] ኢንቨስትመንትን በተሳለጠና ውጤታማ በሆነ መልኩ ለማካሔድ [ማስቻል]…›› እንደሆነ ተገልፆ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ‹የዘመኑ መንፈስ› ኢንደስትሪያላይዜሽን ነውና እቅዱ ዋነኛ ትኩረቱን ኢንደስትሪ ላይ ማድረጉ የሚጠበቅና የሚገርም ጉዳይ አይደለም፡፡ ነገር ግን ከተማዋ የምስራቅ አፍሪካ የኢንዱስትሪ ማዕከል ለመሆን ኢንደስትሪ የምትገነባበት በቂ ቦታ የላትምና አወዛጋቢውን መስፋፋት ለማድረግ ተነሳች ማለት እንችላለን፡፡ ይሄ እንዴት ሆነ?

4.3. መሪ እቅድ (Master Plan) ወይስ አዲስ ክልል (New State)?

ሰኞ ግንቦት 18፣ 2000 በጊዜው የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ የነበሩት በአቶ መኩሪያ ሀይሌ እና ከአዲስ አበባ አስራ ሰባት እህት ከተሞች አንዷ በሆነችው የፈረንሳዩ፣ የሊዮን ከተማ ምክትል ከንቲባ Monsier Hubert Julien-Laferriere መካከል አንድ የትብብር ሰነድ ተፈረመ፡፡ የትብብር ሰነዱ በሁለቱ ከተሞች መካከል የተደረገው የአምስት ቀናት ውይይት ውጤት ነበር፡፡ ለውይይቱ የመነሻ ሃሳብ ያቀረበው የፌደራል የከተሞች ፕላን ኢንስቲትዩት በአዋጅ ቁጥር 450/1997 ከተሰጡት ስልጣኖች አንዱን በመጠቀም ሊዮን ከተማ አዲስ አበባን ልትረዳ የምትችልባቸው ሶስት አጀንዳዎችን አቀረበ፡፡ እነዚህም ሶስት አጀንዳዎች፡

1. የአዲስ አበባ ከተማን መሪ እቅድ (Master Plan) የመከለስ ስራ፣

2. በኦሮሚያ ክልል እና በአዲስ አበባ መካከል በጋራ ለመፍጠር ስለታሰበው ክልላዊ እቅድ (Regional Planning) እና፣

3. ስለ አዲስ አበባ ከተማ የውስጥ የልማት ስራ (Local Development Plan – LDP) ናቸው፡፡

በውይይቱ ማጠናቀቂያም በሶስቱ ጉዳዮች ላይ ስምምነት ላይ በመደረሱ የሁለቱ ከተሞች አቻ ባለስልጣናት የትብብር ሰነዱን ተስማምተው ፈረሙ፡፡ የመሪ እቅዱ እና የውስጥ የልማት ስራው ከዚህ በፊት የተለመዱ ጉዳዮች በመሆናቸው ብዙም ግርታን የሚፈጥሩ አልነበሩም፡፡ ነገር ግን በኦሮሚያና በአዲስ አበባ መካከል ሊፈጠር የታሰበው ክልላዊ የልማት እቅድ የተለመደ ስላልነበር አፈፃፀሙን ለማየት የሚያጓጓ ነበር፡፡ የዚህ ክልላዊ እቅድ መነሻ ግን አሁንም ወደኋላ ወደ 1996 ይወስደናል፡፡ በ1996 የወጣው የአዲስ ነጋሪቱ ‹የአዲስ አበባ ከተማ መሪ ፕላን አዘገጃጀትና አወጣጥ› አዋጅ ቁጥር 17/1996 በአንቀፅ 8 (2) ላይ ‹የአዲስ አበባ መዋቅራዊ ፕላን ከመዘጋጀቱ በፊት [ከኦሮሚያ ክልል ጋር] በፈቃደኝነት በጋራ ስምምነት ላይ የተመሰረተ የአዲስ አበባና አካባቢዎች ፕላን እንዲዘጋጅ አስተዳደሩ ሁኔታዎችን ያመቻቻል› በማለት ክልላዊ እቅድ መታቀድ ከጀመረ ቆየት ያለ ጊዜ እንዳስቆጠረ ያመላክተናል፡፡

አሁን መንግስት ያዘጋጀው የተቀናጀ የጋራ የልማት እቅድ ሰነድም (የዚህ ፅሁፍ ፀሃፊ እዚህ ላይ ያገኘው ሰነድ) እነዚህን የኋላ ታሪክ በመያዝ ክልላዊ እቅድን (Regional Planning) ከመሪ እቅድ (Master Plan) በመቀየጥ የተዘጋጀ ነው፡፡ ያለውን የፌደራል ስርዓት አይተን ትግበራው ምን ሊመስል ነው ብለን ማሰብ የሚከብደን አይነት እቅድም ነው፡፡ የእቅዱ ስያሜ እንኳን መሪ እቅድ (Master Plan) ሳይሆን ክልላዊ እቅድ (Regional Plan) ነው፡፡ ግቡም አዲስ አበባን በ 100 ኪሎ ሜትር ሬዲየስ የሚከብ ሰፊ ክልልን ማልማት ነው፡፡ 36 ከተሞችን እንደሚያካትትም ተጠቅሷል፡፡ ከአዲስ አበባ ሌላ በስም በእቅዱ ላይ ተጠቅሰው የምናገኛቸው ከተሞችም ዱከም፣ ገላን፣ ሰበታ፣ አዋሽ፣ ለገዳዲ፣ ለገጣፎ (ሁሉም በኦሮሚያ ክልል፣ የፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን ከተሞችን ማለት ነው) ናቸው፡፡ በልማት እቅዱ ውስጥ የተካተተው አካባቢም 85 በመቶው ገጠር እንዲሁም 15 በመቶው ደግሞ የከተማ አካባቢ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ እንዲሁም በአምስቱ ኦሮሚያ ክልል፣ የፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን አምስት ከተሞችን ውስጥ በ25 ዓመታት ውስጥ ከ30 ሺህ እስከ 40 ሺህ ነዋሪዎችን ማስፈርን በእቅድነት ይዟል፡፡ ይሄም ዓላማ ያደረገው ‹የክልሉን ነዋሪ ከአስከፊ ድህነት ማላቀቅ› ነው የሚል ሲሆን፤ እዚህ ላይ የየትኛውን ክልል ነዋሪ ማለታችን ተገቢ ነው፡፡

እነዚህን ጉዳዮች ስንመለከትም እቅዱ በዋናነት ክልላዊ እቅድ እንጂ የከተማ መሪ እቅድ እንዳልሆነ ለመረዳት ብዙም አያዳግተንም፡፡ ሰፊ የገጠር አካባቢን (85 በመቶው የእቅዱ አካባቢ) አካልሎ ግቡን ኢንደስትሪያላይዜሽን ማድረጉንም ስናይ ‹ግዙፏ አዲስ አበባ በተግባር ደረጃ (de facto) የራሷ የሆነ ክልል (አስረኛዋ የኢትዮጵያ ክልል) ለመመስረት ጥረት እያደረገች ነው እንዴ?› ብለን እንድንጠይቅ ያደርገናል፡፡ ከላይ የጠቀስነው አደናጋሪው በፌደራል ስርዓቱ ውስጥ የአዲስ አበባ ‹ስታተስ› ጉዳይም እዚህ ላይ መሰረታዊው የጥያቄ ነጥብ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡

4.4. ኦሮሚያ፣ አዲስ አበባ እና ‹እቅዱ›

ከላይ በተራ ቁጥር 3 ላይ ሕገ መንግስቱ በተረቀቀበት ወቅት የነበረው የአዲስ አበባን ‹ስታተስ› ግልፅ ያለማድረግ ችግርና አዲስ አበባ ከምትገኝበት ኦሮሚያ ክልል ጋር የሚኖራትን ግንኙነት ግልፅ ያለማድረግ ችግር ሕልዮታዊ ጥያቄዎችን ለማንሳት ሙከራ አድርገናል፡፡ እዚህ ላይ ደግሞ በተግባር እያጋጠሙ ያሉ ቸግሮችን በማንሳት የወደፊቱን ሁኔታ ለማየት እንሞክር፡፡

አብዛኛው የአዲስ አበባ ከተማና የኦሮሚያ ክልል ውዝግቦች የሚነሱት ከድንበርና ከሉዓላዊነት ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ ነው፡፡ አዲስ አበባ ያለ ቅጥ እየተስፋፋች ነው፣ የኦሮሞን ባህልና ቋንቋ እያጠፋች ነው፣ በሕገ መንግስቱ ለኦሮሚያ ክልል የተሰጣት ልዩ ጥቅም እስከ አሁን በሕግ ባለመወሰኑ ጉዳዩን አወሳስቦታል ወዘተ የሚሉ ትችቶች እየቀረቡ እስከ አሁን ቀጥሏል፡፡

4.4.1. ድንበር

የአዲስ አበባ ስፋት ባለፉት ሃምሳ አመታት ከእጥፍ በላይ አድጓል፡፡ በ1953 በሔክታር 21,800 የነበረው የአዲስ አበባ የቆዳ ስፋት በ1986 ወደ 53,014 ሔክታር ሰፍቶ፤ አሁን ያለውን የ54,000 ሔክታር ስፋት ደግሞ በ1996ቱን በከተማዋ መሪ ዕቅድ የተሰፈረላት ነው፡፡ በሀምሳ ዓመታት ውስጥ ከተማዋ በእጥፍ ያደገች ቢሆንም በአለፉት ሃያ ዓመታት ውስጥ ግን አሁን ካላት ስፋት ብዙም የተለየ ነገር አላሳየችም፡፡ የከተማዋ ከኦሮሚያ ጋር ያላት የድንበር ውዝግብ ዋነኛ መነሻ የሆነው የድንበሩ አለመካለል (demarcation ነው፡፡ በዚህም ምክንያት የተለያዩ ውዝግቦች በጊዜው እንደሚነሱ ይሰማል፡፡ ተሾመ ያሚ የተባሉ የሕግ ባለሙያም በጉዳዩ ላይ ባደረጉት ጥናት የኮልፌ-ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ከቡራዩ ከተማ አስተዳደር ጋር እንዲሁም የንፋስ ስልክ-ላፍቶ ክፍለ ከተማ ከሰበታ ከተማ አስተዳደር ጋር በቅርብ ጊዜያት ውስጥ የድንበር ይገባኛል ውዝግብ ውስጥ እንደገቡ ይገልፃሉ፡፡ እንዲሁም የገቢ ምንጭን አስመልክቶ የኦሮሚያ ክልል የማዕድን ኤጀንሲ ቢሮ ከአዲስ አበባ አቻው ጋር የተወዛገበባቸው አካባቢዎች እንዳሉ አያይዘው ይገልፃሉ፡፡ እነዚህን ችግሮች ግን መንግስት ሕጋዊ መፍትሔ ከመስጠት እና የሕግ አፈታቱን ከማሳደግ ይልቅ ተለመደውን ፖለቲካዊ መፍትሔ እየሰጠ ችግሩ አሁንም በዘላቂነት ያልተፈታ ጉዳይ እንደሆነ ቀጥሏል፡፡

አዲስ አበባ አሁን ካላት ቦታ ውጭ (54,000 ሔክታር ወይም 527 ኪሜ ስኩየር) መስፋት አትችልም ወይ? ለሚለው ጥያቄ ሕጋዊ መፍትሔ የሚሰጠን በ1996 የወጣው የአዲስ ነጋሪቱ ‹የአዲስ አበባ ከተማ መሪ ፕላን አዘገጃጀትና አወጣጥ› አዋጅ ቁጥር 17/1996 ሲሆን አዋጁም ‹‹[የአዲስ አበባ የ] መስፋፊያ አካባቢ [የሚባለው] በማስተር ኘላኑ የቦታ ደረጃ በአዲስ አበባ ከተማ ተከልሎ ባለ የአርሶ አደር ወረዳዎች ስር የሚገኝ የለማ እና ወደፊት የሚለማ መሬት የሚገኝበት አካባቢ ነው፡፡›› በማለት ከተማዋ አሁን ካላት ቦታ ውጭ እንደማትስፋፋ ይገልፃል፡፡ ከኦሮሚያ ክልል ጋር ያለው ግንኙነት አስመልክቶ በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር የመመስረቻ ቻርተር 87/1989ም ሆነ ይሄን ቻርተር ሙሉ ለሙሉ ያሻሻሉት አዋጅ ቁጥር 311/1995 እና በአዋጅ ቁጥር 361/1995 የድንበሩ ጉዳይ ‹ወደፊት በውይይት ይካለላል› ከማለት በስተቀር ያስቀመጡት ነገር የለም፡፡ በሌላ በኩል የአዲስ አበባ መለጠጥ ያሳሰበው እና ይሄም መገታት አለበት ብሎ ያሰበው የኦሮሚያ ክልል በ2000 የፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን በሚል አዲስ ዞን የአዲስ አበባ እና ኦሮሚያ ክልልን ግንኙነት ለማሳለጥ በሚል ሰበብ አቋቁሟል፡፡ አሁን የቀረበው ‹የልማት እቅድ› ደግሞ የልዩ ዞኑን ከተሞች ሙሉ ለሙሉ በማስገባት ሌላ አዲስ መካረር ፈጥሯል፡፡

4.4.2. ቋንቋ

የአሜሪካዋ ቨርጂኒያ ስቴት ለዋና ከታማዋ ዋሽንግተን ዲሲ የሰጠሁት መሬት ይመለስልኝ በማለት መሬቷን በ1846 አስመልሳለች፡፡ በሌላ በኩል አሁን ያለችውና መሬት ከሜሪላንድ ‹ስቴት› ወስዳ የቆመችው ዋሽንግተን ዲሲ ‹ራሷን የቻለች ክልል ትሁን የሚለውም› ሃሳብ ብዙም ተቃውሞ አይቀርብበትም፡፡ ለዚህም ለስላሳ ግንኙነት ዋነኛው መሰረትም የዋሽንግተን እና የዙሪያዋ ያለው የባህልና ቋንቋ መመሳሰል ነው፡፡

በተቃራኒው አዲስ አበባ የምትናገረው ቋንቋ በዙሪያዋ ካለው ቋንቋ የተለየ ነው፡፡ አዲስ አበባ አማርኛን ታወራለች ዙሪያዋ ደግሞ ኦሮምኛን ይናገራል፡፡ የቋንቋ ምሁሩ ፕሮፌሰር ባየ ይማም ‹አዲስ አበባ ለአማርኛ፣ አማርኛ ለአዲስ አበባ› ባሉት ፅሁፋቸው የአማርኛንና የአዲስ አበባን ግንኙነት ሲያስረዱ፡

ከአዲስ አበባ ከተማ ምሥረታ በኋላ የተለያየ ቋንቋ ተናጋሪ የሆኑ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በየምክንያቱ ወደ ከተማዋ በመግባት በጉርብትና አብረው መኖርና መሥራት ጀመሩ፡፡ ይህም ሁኔታ ሕዝቦችን ከተለያየ ቋንቋ ተናጋሪነት ወደ አንድ የጋራ ቋንቋ ተጠቃሚነት አሸጋገረ:: ልሳነ ዋህድ የነበረው ብሄረሰብ ልሳነ ክልዔ እየሆነ መጣ። አማርኛ ከመቼውም ጊዜ የበለጠ ከተመኛውን ሁሉ የሚያገናኝ የጋራ ቋንቋ ሆነ፡፡

አዲስ አበባና አማርኛ፣ ለርስበርሳቸው ብሎም ለመላው ኢትዮጵያ የለውጥ ተምሳሌት ናቸው፡፡ እያንዳንዱ ብሄረሰብ በቤቱም ሆነ በአደባባይ የሚናገረው የራሱን ቋንቋና አማርኛን ነው ለማለት ይቻላል፡፡ የአዲስ አበባ ሕዝብ ግን ከዚህ ይለያል፡፡ በአደባባይ ሁሉም የሚናረው አማርኛን ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ መርካቶ የሚሰማው ቋንቋ ሌላ ሳይሆን አማርኛ ነው፡፡ አዲስ አበባ የሕብረ-ብሔራዊነት ተምሳሌት እንደሆነች ሁሉ፣ አማርኛም የዚሁ መግለጫ ነው፡፡ ከሁሉም ይወስዳል፣ መልሶ ለሁሉም ያሰራጫል፡፡ ሁሉንም ያገናኛል፣ ከሁሉም ቃል ይወስዳል፣ ለሁሉም ቃል ይሰጣል፡፡

በማለት ይገልፃሉ፡፡ ፕሮፌሰሩ እንደሚሉት አዲስ አበባን ያለ አማርኛ ማሰብ በፍፁም የማይቻል ነው፡፡ በተቃራኒው ደግሞ በዙሪያዋ ያሉት የአዲስ አበባ ከባቢዎች ኦሮምኛ ተናጋሪዎች ናቸው፡፡ በመሆኑም ‹ይህች እንደ አንድ ከተማ ብቻ ሳይሆን እንደ ኢትዮጵያ ስልጣኔ ምልክት እየተደረገች የምትታይ ከተማ የምትናገረው ቋንቋ በዙሪያዋ ያለውን ኦሮምኛ ቋንቋ ያጨቁነዋል› የሚለው ሃሳብ የሚሰነዝሩ ሰዎች ብዙ ናቸው፡፡ አሁን ደግሞ ክልላዊ የልማት እቅድ ቀርቧል፡፡ እቅዱም ከቋንቋ ጋር በተገናኝ ያለውን ተቃውሞና ውዝግብ የበለጠ አክርሮታል፡፡

4.4.3. የገበሬ መሬት ለከተሜ?

ከአዲስ አበባ መስፋፋት ጋር ተያይዞ ሌላው እየቀረበ ያለው ጉዳይ አዲስ አበባ በሰፋች ቁጥር ገበሬዎችን እያፈናቀለች ቤት አልባ ታደርጋለች የሚለው ሲሆን፡፡ የተለያዩ ጥናቶችም ይሄን ያመላክታሉ፡፡ ፈየራ አብዲ የተባሉ አጥኝ አዲስ አበባ ከምስረታዋ ጀምሮ አሁን ያለችበትን ስፋት ለሜድረስ በዓመት በአማካኝ 400 ሔክታር ያህል ስትሰፋ ነበር ይላሉ፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ ግን ከተማዋ በሕግ አግባብ ልትሰፋ የምትችለው ከተማዋ በቻርተር ከተማነት በተቋቋመችበት አዋጅ ቁጥር 87/1989 ላይ የተገለፀውን ‹የአዲስ አበባ ከተማ የከተማውን ክልል እና በመስተዳደሩ ክልል ውስጥ የሚገኙትን ሃያ ሶስት የገጠር ቀበሌዎች ያጠቃልላል›› ተብሎ በተገለፀው አግባብ ወዳሉት ሃያ ሶስት የገጠር ቀበሌዎች ብቻ ነው ሊሆን የሚችለው፡፡ በኢፌዴሪ ሕገ መንግስት አንቀፅ 40 (4) ላይ ‹‹የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች መሬት በነፃ የማግኝትና ከመሬታቸው ያለመነቀል መብታቸው የተከበረ ነው፡፡›› ተብሎ የተከበረውን የገበሬዎችን መብት ይጥሳል የሚሉ ብዙ ወገኖች አሉ፡፡ ነገር ግን በዚሁ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 8 ላይ ‹‹መንግስት ለሕዝብ ጥቅም አስፈላጊ ሁኖ ሲያገኝው ተመጣጣኝ የካሣ ክፍያ በቅድሚያ በመክፈል […] [መሬቱን] ሊወስደው ይችላል›› ተብሎ በመደንገጉ ይህ የገበሬዎች መብት ገደብ ያለው ነው የሚለው ሃሳብም እዚህ ላይ መሰረታዊ ነገር ነው፡፡

ነገር ግን አሁን እየቀረበ ያለው ‹የተቀናጀ የጋራ እቅድ› ዓላማው ኢንደስትሪያላይዜሽን እንደሆነ ያስቀመጠ ሲሆን 1.1 ሚሊዮን ሔክታርን ያቀፈና 17 የሚሆኑ ወረዳዎችን የያዘ እንደሆነ ተገልፆል፡፡ ይሄም እጅግ ብዙ የገጠር ቀበሌዎችን እንደሚያካትት ግልፅ ነው፡፡ ኢንደስትሪያላይዜሽንን መሰረት ያደረገ እቅድ በዚህ ያህል ቦታ ሲታቀድ ገበሬዎችን በገፍ አያፈናቅልም ብሎ ማሰብ ራስን ከማሞኘት ባለፈ ፋይዳ ያለው ነገር አይደለም፡፡ መፈናቀሉንም ‹ለሕዝብ ጥቅም አስፈላጊ ሁኖ ስለተገን› ነው ብሎ ማሰብ የባሰ ሞኝነት ነው የሚሆነው፡፡

ሲጠቃለልም አዲስ አበባ በተሳሳተ የከተማ ልማት ፖሊሲ ሌሎች ከተሞች በሀገሪቱ ውስጥ የሉም እስኪባል ድረስ ያለልክ ገዝፋለች፡፡ በዚህም ምክንያት አዲስ አበባ ላይ የሚደረግ ማንኛውም እቅድ አካባቢያዊ እቅድ ከመሆን ይልቅ ሀገራዊ እቅድ ነው ማለት ይቻላል፡፡ በመሃሉና በዳር ሀገሩ መካከል ያለውን ልዩነት ለማጥበብ ከመስራት ይልቅ አሁንም በፖሊሲ ደረጃ የአዲስ አበባን ግዙፍነት በበለጠ የማስቀጠል አካሔድ ነው አሁን እየተካሔደ ያለው፡፡ ይህ አካሔድ ደግሞ በፌደራል ስርዓት ሊኖር የሚገባው ግልፅ የሆነ ድንበር እና ‹ስታተስ› ካለመኖሩ ጀምሮ የተነሳ ሲሆን፤ በተግባርም ችግሮችን በፖለቲካዊ ውሳኔ አድበስብሶ የማለፍ ውጤት ሲጠራቀም ቆይቶ አሁን ላይ የደረሰ ጉዳይ ነው፡፡ እንዲህ የገዘፈ እቅድን (ያውም ‹መሪ እቅድ› ይሆን ‹ክልላዊ እቅድ› በግልፅ ያልተቀመጠ እቅድ) ከአንድ ከተማ ጋር አያይዞ ማቅረብም ለጉልበተኛው የከተማ ገዥ ልሒቅ ተጨማሪ ሃይል በመስጠት ገበሬውን ከራሱ መሬት ወደ ጭሰኝነት የሚገፋ ነው የሚሆነው፡፡ ላልተሳካ ኢንደስትሪያላይዜሽን መሰረታዊ መፍትሔ ከመፈለግ ይልቅ የፌደራል ስርኣቱን በግዴለሽነት በመግፋትና በመሰለኝ ለማሳካት መሞከር ነገም ሌላ ችግር ነው የሚመዘው፡፡ ሕሩይ ሚናስን ከሩቅ ገነት ሁና በመግነጢሳዊ ሃይሏ ስባ ቤተኛ ያደረገችው አዲስ አበባስ እስከ መቼ ነው ሀገሪቱ በፖሊሲ ክሽፈት እየወደቀች ያለችውን የተለያየ ፈተና ለማለፍ መሳሪያ የምትሆነው? የፌደራል ስርዓቱስ እስከ መቼ ነው ሕጋዊነትን ሳይተዋወቅ የሚዘልቀው?

(በዘላለም ክብረት)

አንዳንድ ስህተቶች፣ አዲስ አይን ማውጣት፣ ወደ ውስጥ መመልከት ያሻል፤ – ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ -

oromo-students-protestበረታችንን ክፍቱን አናሳድርም፤ ያረባነውን፣ ያሰባነውን አውሬ ሊቀራመትብን፣ ሌባ ሊነዳብን ይችላል፡፡
Bedilu-Waqjira-DR
ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ
ምን ብናሳድጋቸው፣ ምን ብናሰባቸው እንሰሳት ናቸውና ለነዳቸው ይነዳሉ፤ ጥርሱን ካገጠጠ አውሬም ራሳቸውን ሊከላከሉ አይቻላቸውም፡፡ ሰው ግን እንደዚህ አይደለም፡፡ ራሱን ይከላከላል፤ ይጠብቃል፡፡ ሰው ለነዳው አይነዳም፤ የሰበከውን አይከተልም፡፡ በዚህም የተነሳ በበረታችን እንዳሉት ከብቶች፣ ላሳደግናቸው ልጆቻችን አንሰጋም፡፡ ልጆቻችንን ለመስረቅ ቀድሞ ህሊናቸውን፣ ማስተዋላቸውን መስረቅ ያስፈልጋል፡፡ ይህ ደግሞ ቀላል አይደለም፤ በስነምግባር ኮትኩተን ያሳደግናቸው ልጆቻችንን፣ ማንም በአፍታ ሰበካ ከጎጇችን ሊሰርቃቸው አይችልም፡፡ አስራ ስምንት አመት አብሮን የኖረ ልጃችንን የአፍታ ሰባኪ ካሸፈተብን፣ ድሮም አብሮን አልነበረም ማለት ነው፡፡ በስነምግባርና በእውቀት አንጸን አላሳደግነውም ማለት ነው፡፡ ከብብታችን ለመሽሎክ ‹‹ተከተለኝ›› በይ ጠሪ እየጠበቀ ነበር ማለት ነው፡፡ . . . እና ይህ ሲሆን ወላጅ ሰራቂውን፣ ወይም ልጁን መኮነን የለበትም፤ መጠየቅ ያለበት ራሱን ነው፡፡ ለአስራ ስምንት አመታት ያነጽኩት ግምብ እንዴት በአንድ ቀን ሰበካ ይናዳል? ወይስ ራሴ የገነባሁ መስሎኝ ሳፈርሰው ኖሬያለሁ? ወይስ መስሎኝ እንጂ ከቶም ያነጽኩት ግምብ አልነበረም? ምን ብንበድለው ነው ያሳደግነው ልጃችን ፊቱን ያዞረብን?. . . . ወዘተ. የመሳሰሉትን ጥያቄዎች መጠየቅ አለበት – ወላጅ፡፡ ከነዚህ ጥያቄዎች የሚገኘው መልስ እድሜው ገፍቶ ላላረጠ ወላጅ፣ ቀጣይ ልጁን እንዴት ማሳደግ እንዳለበት ትምህርት ይሆናል፡፡
.
ኢህአዴግም ማድረግ ያለበት እንዲሁ ነው፡፡ ለሀያ አምስት አመታት ያስተዳደረው ህዝብ (ወጣትም ይሁን ጎልማሳ) ለተቃውሞ አደባባይ ሲወጣ፣ መጠየቅ ያለበት ራሱን ነው፡፡ ለሀያ አምስት አመታት ያስተዳደረው ህዝብ፤ መንገድ ሰራሁለት፣ ትምህርት አስፋፋሁለት፣ ድህነቱን ቀነስኩለት የሚለው ህዝብ፤ በግዳጅ ለጦርነት ከመማገድ አዳንኩት፣ በጥቃቅንና አነስተኛ አደራጅቼ ስራ ፈጠርኩለት የሚለው ወጣት፣ መንገድ ዘግቶ፣ ድንጋይ ወርውሮ፣ ለተቃውሞ ሲወጣ፣‹‹በአሸባሪዎችና በጸረሰላም ሀይሎች ስብከት ተደልሎና ተወናድዶ ነው›› የሚል ምክንያት ማቅረብ ውሀ አያነሳም፡፡ እና ኢህአዴግ ራሱን መጠየቅ አለበት! ከጫንቃው ላይ ደርግን ያህል ግፈኛ መንግስት ያስወገድኩለት ህዝብ፣ ያስተማርኩትና ስራ የፈጠርኩለት ወጣት፣ በቀናት የሽብርተኞች ስብከት ተደልሎ ለጥፋት ሊነሳ ይችላል? ከቻለስ ስለምን በአሸባሪዎች ከንቱ ስብከት ተቃወመኝ? እኔ ሬዲና ቴሌቪዥን ይዤ፣ እየተሸሎከለኩ የሚሰብኩ ሀይሎች፣ እንደምን ተሰሚነት አግኝተው አመጽ ሊነሳ ቻለ? ከእኔ ልማታዊ- ተግባር የእነሱን ሽብራዊ ስብከት ስለምን ተቀበለ? ወይስ ስራ እየፈጠርኩለት፣ ድህነቱን እየቀነስኩለት አልነበረም? . . .ወዘተ. የመሳሰሉ በርካታ ጥያቄዎች ለራሱ ማቅረብ አለበት፡፡
.
ይህ ካልሆነና፣ ኢህአዴግ ችግር በተፈጠረ ቁጥር፣ ተቃውሞ በተነሳ ቁጥር፣ ‹‹አሸባሪዎችንና ‹‹ጸረልማት ሀይሎችን›› ተጠያቂ የሚያደርግ ከሆነ፣ችግሩን ከስሩ አልመረመረምና ዘላቂ መፍትሄ ሊያገኝ አይችልም፡፡ ይልቁንም እንዲህ ያለው ራስን ነጻ ማውጣትና ሌሎችን ተጠያቂ ማድረግ፣ እብሪትን ስለሚያጸና ሀይልን ወደመጠቀም ይገፋፋል፡፡ ሰሞኑን በኦሮምያ ክልል በተፈጠረው ችግር የደረሰው የሞት አደጋም ሰበቡ ይኸው ነው፡፡ ኢሕአዴግ እውነት ‹‹ተቃውሞው የተቀሰቀሰው ከህዝቡ ወገን ባልሆኑ ሀይሎች ነው›› ብሎ የሚያምን ከሆነ፣ የተወናበደው ተቃዋሚ ላይ፣ ተወናብዶ እንጂ የእኔ ነው የሚለው ተቃዋሚ ላይ መተኮስ የለበትም፡፡ እዚህ ላይ ኢህአዴግ በተቃውሞ የሚደርሰውን የሰላም መቃወስና የንብረት መውደም የመከላከል ሀላፊነት እንዳለበት አልዘነጋሁም፡፡ ግን በምንም መንገድ የሰው ህይወት መጥፋት የለበትም፡፡ በየሀገሩ ከተሞችን ያነደደ ተቃውሞ ያለምንም ህይወት መጥፋት ሲያልፍ አይተናል፡፡ የፈረሰው ድልድይና ህንጻ መልሶ ሲገነባም አይተናል፤ የሞተ ሰው ግን ተቃውሞው አልፎ ሰላም ሲወርድ፣ ከመቃብር ሲነሳ አልተመለከትንም፡፡
.
አብዛኛውን ጊዜ ኢህአዴግ በተቃውሞ ወቅት የሚደርሱ የሞት አደጋዎችን ምክንያታዊ ለማድረግ፣ በፖሊስ አባላት ላይ የተፈጸሙ ጥቃቶችን እንደመግፍኤ ያቀርባል፡፡ ይሁንእንጂ ይህ ተቀባይነት የሚኖረው፣ አማጺው በነፍስወከፍ ጠመንጃ ታጥቆ የወጣ እንደሁ ነው፤ ይህ ከሆነ ጉዳዩ ጦርነት ሆኗል ማለት ነውና ከፖሊስም በላይ የጦር ሰራዊት ሊገባበት ይችላል፡፡ ነገር ግን ተቃዋሚው ዱላና ድንጋይ ይዞ ቢወጣም እንኳን፣ በድንጋይና በዱላ ንብረት ቢያወድም፣ ፖሊስ ላይ ጥቃት ቢሰነዝር እንኳን፣ ጥይት ተኩሶ መግደል ተገቢ አይደለም፡፡ ፖሊስ ህዝብ ጠባቂ ነው፤ ህዝቡን የሚጠብቀው ደግሞ ከሌባና ከቀማኛ ብቻ ሳይሆን፣ ከህዝቡና ከራሱ ከፖሊሱ ጭምር ነው፡፡ ፖሊስ መኪና አቃጠልክ፣ መስታወት ሰበርክ ብሎ ህዝቡ ላይ የሚተኩስ ከሆነ፣ ህዝቡን ከራሱ ከህዝቡ አልጠበቀውም፡፡ ፖሊስ እኮ እኔን ከራሴም ሊጠብቀኝ ሀላፊነት አለበት፤ ለዚህ ነው እራሱን ሊያጠፋ የተዘጋጀን ሰው ፖሊስ መረጃ ካለው፣ ሊያስጥለው ሀላፊነት ያለበት፡፡ ፖሊስ በድንጋይ ፈነከትከኝ ብሎ፣ ህዝብ ላይ የሚተኩስ ከሆነም ከራሱ ከፖሊስ አልጠበቀውም፡፡ ፖሊስነት በማንኛውም ሁኔታ ህዝብን የማስቀደም ታላቅ ሀላፊነት ነው፡፡ ይህ ሲሆን፣ ፖሊሶቻችንን ስለኛ ስለሚከፍሉት መስዋእትነት እንወዳቸዋለን፡፡ የምንወዳቸው ከሆነ ደግሞ ስለኛም ደህንነት ቢሆንም እንኳን እንዲጎዱ አንፈልግምና እንሳሳላቸዋለን፤ እንጠብቃቸዋለን፡፡ . . . እናም በመጨረሻ በምንም ሁኔታ ውስጥ እንዳንጎዳ ይጠብቁናል፤ እኛም እንዲሁ አንጠብቃቸዋለን፡፡

Friday, December 4, 2015

በእሳት‬ በጋየው የጎንደሩ ግዙፍ ወህኒ ቤት ውስጥ በህወሓት ጦር የተጨፈጨፉት እስረኞች ማንነት በመታወቅ ላይ ነው

shimeles abuay(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ) ህዳር 21 2008 ዓ.ም በጎንደር ከተማ በሚገኘው ግዙፍ ወህኒ ከባድ የእሳት ቃጠሎ መነሳቱን ተከትሎ የህወሓት ሰራዊት በርካታ እስረኞችን በግፍ መጨፍጨፉና ዙሪያውን በእሩምታ ተኩስ አጥሮ ማህሉንም ዳሩንም እሳት በእሳት በማድረግ መሽሎኪያ ቀዳዳ በማሳጣት ብዙዎቹን ማጋየቱ ይታወቃል፡፡

በመሆኑም በግፈኛውና ፋሽስቱ የህወሓት አገዛዝ ሰራዊት ከተጨፈጨፉት እስረኞች መካከል የተወሰኑት ማንነታቸው ተለይቶ በየትውልድ ቀዬዎቻቸው በመቀበር ላይ ናቸው፡፡
አቶ አለቤ ኃይሌ የተባሉትና ከመታሰራቸው በፊት በጥበቃ ስራ ይተዳደሩት የነበሩት ሰው ትናንት በወገራ ወረዳ ጉንትር ቀበሌ አቦ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስርዓተ ቀብራቸው ተፈፅሟ፡፡ በተጨማሪም የዚሁ ወገራ ወረዳ ጉንትር ቀበሌ ነዋሪ የሆነው የ17 ዓመቱ ታዳጊ መላክ ችሎት በወህኒ ቤቱ ውስጥ በጥይት ተደብድቦ ከባድ ጉዳት ደርሶበት በህክምና ላይ ይገኛል፡፡
ከአርበኞች ግንቦት 7 ጋር ግንኙነት አላችሁ ተብለው በቅርቡ በህወሓት ደህንነቶችና የታጠቁ ቡድኖች ታፍነው ከደልጊ ወደ ጎንደር ከተወሰዱት ከ10 በላይ ሰዎች መካከል እስካሁን አቶ አሰፋ ገዳሙ የተባሉት አዛውንት መገደላቸው ተረጋግጧል፡፡ በአርማጭሆ የሽመለ ጋራ ቀበሌ አስተዳዳሪ የነበረው ነውጥ ብቃለ የተባለው ግለሰብም መገደሉ ጭምር ታውቋል፡፡
አድራሻቸውና የአባታቸው ስም ገና በመጣራት ላይ ከሚገኙት እጅግ በርካታ የተጨፈጨፉ እስረኞች መካከል ደግሞ ቀናው፣ እሸቴ፣ ጤናው፣ ማስረሻ፣ አዱኛ… የተባሉት ይገኙበታል፡፡
ሽመልስ አቡሃይ የተባለው እስረኛ ያልነበረ ሰላማዊ ወጣት ደግሞ ትናንትና በተነሳው ግርግር በግፍ ተገድሎ ዛሬ በጎንደር ደብረ ብርሃን ስላሴ ቤተክርስቲያን ተቀብሯል፡፡

Saturday, November 28, 2015

ከመጠምጠም መማር ይቅደም | መስፍን ወልደ ማርያም [ፕሮፌሰር]

mesfinኅዳር 2008 በፌስቡክ የምንሰባሰበው ለመወያየት፣ አንዱ ከሌላው እንዲማር፣ መረጃዎችን በነጻነት እንድንለዋወጥ፣ ይህንን ሁሉ በማድረግ ራሳችንን ለማሻሻል፣ የእኛ መሻሻል እየተራባና እየተባዛ የአገርና የሕዝብ መሻሻል እንዲሆን፣ ከተቻለንም ከአገራችንና ከሕዝባችን አልፈን የምንታይ የዓለም አካል እንድንሆን መስሎኝ ነበር፤ ሳየው በዚያ መንገድ ላይ ያለንና ፌስቡክን ለበጎ ዓላማ እየተጠቀምንበት ያለን አይመስለኝም፤ ስለዚህ ወይ መታረም፣ አለዚያም በፌስቢክ ጊዜ ማጥፋቱን መተው ምርጫ ሊሆንብን ነው፡፡ ምናልባት 99.99% በእኔ ሰፈር ያሉ የፌስቡክ ተሳታፊዎች ወደፌስቡክ የሚገቡት ለመናገር ነው፤ መናገር የህልውናቸው ምስክር ወይም ማረጋገጫ አድርገው የሚወስዱት ጥቂት አይደሉም፤ ካልተናገሩ የሌሉ ይመስላቸዋል፤ ዋናው ነገር መናገር ይሆንና የሚናገሩት ነገር ወይም ጉዳይ ሌላው ቀድሞ ከተናገረው ጋር የሚያያዝ (የሚቃወመው ወይም የሚደግፈው) ሳይሆን ፈጽሞ ወደተለየ ጉዳይ ውስጥ ገብቶ አዲስ ርእስ መክፈት የተለመደ ነው፤ የአብዛኛው ፍላጎት ማስተማር ወይም ማሳወቅ ነው፤ ማስተማር ወይም ማሳወቅ ቀላል ነው፤ መናገር የሚችል ወይም ፊደሉን አውቆ መጻፍ የሚችል ማስተማር ይችላል፡፡ የትምህርት ቤት ጓደኛዬ በጃንሆይ ዘመን ትልቅ ሚኒስትር ነበር፤ በደርግ ዘመን ለብዙ ዓመታት ታስሮ ሲወጣ ሥራ አልነበረውም፤ ችሎታውን ስለማውቅ በዩኒቨርሲቲ እንዲያስተምር አመቻቸሁለትና ማስተማር ጀመረ፤ ከጥቂት ወራት በኋላ ስንገናኝ ‹‹እኔ ማስተማር ቀላልና እረፍት የሞላበት ሥራ ይመስለኝ ነበር፤ ለካ አንቅልፍ የሚያሳጣ ነው! እዝናናለሁ ባልሁ ቁጥር አንድ ክፍል ሙሉ ተማሪዎች ተሰብስበው ዓይኖቻቸውን እያቁለጨለጩ ምን እንደማስተምራቸው ሲጠብቁ ይታዩኛል! እረፍት ይነሡኛል!›› አለኝ፤ ከአንድ ዓመት በኋላ ማስተማሩን ተወ፤ ኅሊና ላለው ሰው ማስተማር ቀልድ አይደለም፤ ያደክማል፤ ለማስተማር መማር ያስፈልጋል፤ ለማሳወቅ ማወቅ ያስፈልጋል፤ ከመማር ይልቅ ማስተማር፣ ለማወቅ ከመጣር ይልቅ ለማሳወቅ መጣር የሚቀልለው ሰው የእውቀት ሰው አይደለም፤ ሌላ ሥራ ቢመርጥ ይሻለዋል፡፡ ሳያውቁ ለማሳወቅ አደባባይ መውጣት ከችኮላ ወይም ከስንፍና፣ ከትዕቢት ወይም ከግዴለሽነት የሚመጣ ነገር ይመስለኛል፤ ውሎ አድሮ ይጎዳል እንጂ አይጠቅምም፤ በአደባባይ መናገር ወይም መጻፍ የመጨረሻው መጋለጥ ነው፤ በአደባባይ መናገርና መጻፍ በሕዝብ ፊት መጋለጥ መሆኑን ብዙ ሰዎች አያውቁም፤ በአንጻሩ ደግሞ ብዙ ሰዎች ይህንን መጋለጥ ፈርተውትና ሸሽተውት የሚርቁት አሉ፤ መጋለጥን ፈርተው ዓይኖቻቸውን ዘግተው፣ ጆሮዎቻቸውን ደፍነው፣ አፋቸውን ለምግብና ለመጠጥ በቀር የማይጠቀሙበት፣ ዝምታ ወርቅ ነው እያሉ ወርቅ የሚሸምቱበት ብዙ ናቸው፤ ከሕዝብ ጋር እየተጓዙ፣ በሕዝብ መሀል እየኖሩ የሕዝብ ጉዳይ (ፖሊቲካ) አይመለከተንም የሚሉ የማሰብ ችሎታቸውን ህልውና ይጠራጠሩ፤ የማሰብ ችሎታ ከሌለ የማወቅ አምሮት ወይም ምኞት የሚኖር አይመስለኝም፤ የማወቅ አምሮት በሌለበት የማሳወቅ አምሮት ጎልቶ ሲወጣና ሲደናበር ማየት በጣም የተለመደ እየሆነ ነው፤ ፌስቡክ የሚባለው መድረክ የመደናበሪያ መድረክ እየሆነ ነው፡፡ የማሰብ ችሎታው የሌላቸው ሰዎች ከሁለት አንዱን መንገድ በመምረጥ፣ ወይም በሁለቱም መንገዶች በመጠቀም ይሳተፋሉ፡– የማያውቁትን ለማሳወቅ በመሞከርና በዘለፋ! የማያውቁትን ለማሳወቅ መሞከርና ዘለፋ የባሕርይ ግንኙነት አላቸው፤ አሁን እዚያ ውስጥ አንገባም፤ በተለያዩ መስኮች፣ በተለያዩ ጉዳዮች፣ በተለያዩ የእውቀት ጥበቦች በሚያሰራጩት ፍንጥቅጣቂ በአእምሮና በመንፈስ ለመበልጸግ በመጣር ፈንታ በአጉል ትዕቢትና ፉክክር፣ በማይጠቅም ዘለፋና ማስፈራራት የፌስቡክን መድረክ ማበላሸትና ማርከስ ወደኋላ ይጎትተናል እንጂ ወደፊት አያራምደንም፡፡ መሠረታዊ የማሰብ መነሳችን ሳንገነዘብ የማሰብ ትርምስምስ ውስጥ እንገባና መውጣት ያቅተናል፤ ለምሳሌ በእውቀትና በእውነት መሀከል ያለውን ልዩነት ሳንገነዘብ እምነትን ስንሞግት የራሳችንንም ሆነ የሌላውን ጊዜ እናጠፋለን፤ እውቀትን በሙግት ለማጣራት ሲመጡብን ደግሞ ቶሎ ወደእምነት እንዞራለን፤ አጉል መሽከርከር ውስጥ እንገባለን፤ እንዲያው በሆነ ባልሆነው፣ ባወቅነውም ሆነ ባላወቅነው የመጣልንን ሁሉ መዘርገፍ አዋቂ አያሰኝም፤ ጎበዝ አያሰኝም፤ ብልህ አያሰኝም፤ ግን ባለጌ ያሰኛል፤ ባለጌ ነጻነትን አያውቅም፤ ለባለጌ ስድነት ነጻነት ይመስለዋል፤ ነጻነት ባለቤቱ ያጠረው ገደብ ወይም ወሰን አለው፡፡

ፕሮፓጋንዳው ስብዓዊነት ይኑረው!!! ሰው እየሞተ ነው!! ቁጥሩን ቤቱ ይቁጠረው!!! ግርማ ሰይፉ -

_girma_siefu - Satenaw Newsበሀገራችን ያለው ድርቅ ክብደት ከ1977ጋር የሚመሳሰል እንደሆነ የመንግሰት ሹም ከሸገር ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ምልልስ አረጋግጠዋል፡፡ ልዩነቱ ግን አሁን መንግሰት ይህን ለመቋቋም የሚያስችል አቅም አለን የሚልው ጉዳይ ነው፡፡ ይህ አቅም ግን መሬት ላይ ወርዶ ስናየ ወኔ ብቻ ይመስላል፡፡ ከፕሮፓጋንዳ ያለፈ የፈረንጆቹን ደጅ እንዳይጠኑ የሚያደርጋቸው አይደለም፡፡

“ደርግ” በ1977 የነበረፈውን ድርቅ ለዓለም ይፋ አድርጎ የነበረ ሲሆን የዚያን ጊዜ በነበረው ቀዝቃዛ ጦርነት መነሻ በሁለቱ ጎራ በሚደረገው ፍልሚያ ግዳይ የሚጣልብት ወቅት ነበር፡፡ ደርግ ለዓለም ህብረተሰብ ጥሪ ባቀረበበት ወቅት የሶሻሊስቱ ተከታይ በመሆኑ ይህ ጎራ ይህን ድጋፍ የሚያደርግበት አቅም የሌለው ሲሆን ይህን ለማድረግ አቅም ያላቸው ምዕራባዊያን ግን ውጤቱን በደንብ ሳናየው ድጋፍ ላለመስጠት መቁረጣቸው ለችግሩ ክብደት አንዱ እንደ ነበር ለመረዳት ሊቅ መሆን አያስፈልግም፡፡ በተጨማሪ ለ1997 ድርቅ ተገቢው ምላሽ በምዕራባዊያን እንዳይሰጥ በወቅቱ በትጥቅ ትግል ላይ የነበሩት በተለይ ህወሃት እና ሻቢያ የተጫወቱት ሚና ቀላል የማይባል ብቻ ሳይሆን አሁን ላይ ሆነን ስናየው ሰብዓዊነትን ለፖለቲካ ጥቅም እንዳዋሉት ፀሐይ የሞቀው ሀቅ ነው፡፡

አሁን ባለው ሁኔታ የኢህአዴግ መንግሰት ከምዕራባዊያኑ ጋር ያለው ቅርበት ከደርግ እንደሚሻል ስለሚታመን በተጨማሪ ህውሃትና ሻቢያ በዛን ጊዜ የሰሩትን ዓይነት ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት ለመስራት የሚችል ታጣቂ ሀይል ባለመኖሩ ችግሩን ለመቋቋም በተሻለ ሁኔታ ላይ ይገኛል፡፡ መንግሰት አቅሙ የከብቶቹን ህይወት ለመታደግ ለምን አልተጠቀመበትም? ካልቻለ ደግሞ ምዕራባዊያኑ ድጋፍ ለማድረግ ከፈለጉ አሁንስ ቢሆን ከብቶቹ ሳይሞቱ እንዲደርሱልን ለምን አልተደረገም? የሚለው ጥያቄ ለማንሳት አርብቶ አድር መሆን አይጠበቅብንም፡፡

ሁሉም የሚረዳው አንድ ሀገር በድርቅ መቼም ቢሆን ሊጋለጥ ይችላል፡፡ ይህ በዓለም ላይ ተደጋጋሚ ክስተት እንደሆነ ማንም ያውቃል፡፡ ድርቅ ሲኖር ግን ይህን ድርቅ የሌላ ሶሰተኛ ሀገር ድጋፍ ሳይጠየቅ ለመፍታት አቅም መፍጠር መቻል ነው፡፡ ኢትዮጵያ አሁን ባላት ስነ ምህዳር ከዚህ የተሻለ ማድረግ እና ለሌሎች መትረፍ ይገባት ነበር፡፡ ይህ ደግሞ አሰማት ሳይሆን ሊተገበር የሚችል የሀገር ሉዓላዊነት መገለጫ ነው ብሎ የሚያምን መንግሰት ያስፈልጋል፡፡ ኤክስፖርት የሚደረግ ታንክ ሰራን በፍፁም በዚህ ወቅት ሊያኮራን የሚችል ስ አይደለም፡፡ አሁን የምንረዳው መንግሰት ችግሩን ሪፖርት አድርጊያለሁ ማለትን እንደመውጫ ቀዳዳ እየተጠቀመበት መሆኑን ነው፡፡

Thursday, November 5, 2015

ኢትዮጵያ የኢንተርኔት ነጻነት የሌለባት አገር ተብላለች – VOA

voa amharicጽዮን ግርማ / VOA

ፍሪደም ሃውስ (Freedom House) መቀመጫውን እዚህ ዋሽንግተን ዲሲ ያደረገና በመናገር ነጻነት ላይ የሚሠራ ዓለም አቀፍ ተቋም ነው፡፡ይህ ተቋም መንግሥታት ለሕዝቦቻቸው የሚሠጡትን የኢንተርኔት ነጻነት አጥንቶ እያንዳንዱ ሀገር ያለበትን ደረጃ ‹‹Freedom on the net 2015 ›› በሚል ርዕስ ስር ሪፖርት አውጥቷል፡፡ በዚህ ሪፖርት ሰንጠረዥ‹‹ኢትዮጵያ ከቻይና፣ከሦሪያ እና ከኢራቅ ቀጥሎ ምንም ዓይነት የኢንተርኔት ነጻነት የሌለባት አገር ተብላለች፡፡

ዋሽንግተን ዲሲ—
ፍሪደም ሃውስ(Freedom House) የተሰኘው ተቋም “Freedom on the net 2015” የተሰኘው ይህ ሪፖርት በዛሬው ዕለት በቀረበበት ወቅት፤ሪፖርቱን ያዘጋጁት ባለሞያዎች፣የዩኒቨርስቲ መምሕራንንና ተመራማሪዎች፣የጎግል መስሪያ ቤት ባለሞያ፣ከመናገር እና ከመጻፍ ነጻነት ጋር የሚሠሩ ተቋማት ተወካዮች በአጠቃላይ ከሰብዓዊ መብት ጋር የሚሠሩ ግለሰቦችና የድርጅት ተወካዮች ተገኝተው ሪፖርቱን አዳምጠዋል፡፡ ተወያይተዋል፡፡

ማንኛውም ሰው የኢንተርኔት የመረጃ መረብን ተጠቅሞ ያለምንም ቅድመ ምርመራ እና ችግር ሐሳቡን በነጻነት የማስተላለፍ መብት እንዳለው የሚጠቅሰው ይህ ሪፖርት በአሁኑ ወቅት ግን መንግሥታት የሕዝቦቻቸውን የኢንተርኔት ነጻነት እያፈኑ፣አገልግሎቱንም እየዘጉ ከዛ ባለፈ ደግሞ እያሠሩ እንደሚገኙ ይጠቅሳል፡፡
voa amharic
አገራት ለሕዝቦቻቸው የሚሰጡትን ነጻነት በሦስት ቀለማት ከፍሎ ያስቀመጠው የሪፖርቱ አንድ አካል የኾነው አንድ ሠንጠረዥ ኢትዮጵያ ከቻይና፣ከሦሪያ እና ከኢራቅ ቀጥሎ “የባሰ አፈና” ባለባቸው አገራት ዝርዝር ውስጥ ያስቀምጣታል፡፡ በሌላኛው የሪፖርቱ ክፍል ደግሞ “ኢትዮጵያ የኢንተርኔትም ኾነ የመናገርና መጻፍ ነጻነት ያለባት አገር አይደለችም” ይላታል፡፡voa amharic

Friday, October 9, 2015

ዘራፊው ሕወሓት ቁልፍ ቦታዎችን በመያዝ ውሳኔ ሰጪ ያልሆኑ ወንበሮችን ለአሽከሮቹ አድሏል

አቶ ሬድዋን ሁሴን በሃሰት ሲምሉለት የነበረውን ወንበር አጥተዋል።…
☞ ሃይለማርያም ከኒውዮርክ መልስ ሁለት ቀን ከመኖሪያቸው እንዳይወጡ ከሰው እንዳይገናኙ ተደርገዋል።…
☞ ጥያቄ የሚያበዙት አቶ አለማየሁ ተገኑ እና አቶ ሶፊያን አህመድ ከአሽከርነት ቦታቸው ተነስተዋል።…
☞ ትግላችን ላይ በማተኮር ሕወሓትን ከነአሽከሮቹ ልናጠፋቸው ይገባል።
.
የሕወሓት አሻንጉሊት የሆነው ሃይለማርያም ደሳለኝ በትናንትናው እለት ባቀረበው የቸብ ቸብ ካቢኔ መሰረት ሕወሓት የጦር ሃይሉን የውጪ ጉዳዩን የደህንነቱን የኮሚኒኬሽን እና አስፈላጊ ቁልፍ ጉዳዮችን በመቆጣጠር ውሳኔ ሰጪ የማይባሉ ተራ ቦታዎችን ለአሽከሮቹ በማደል የተዋቀረ ሲሆን አለማየሁ ተገኑ እና ሶፍያን አህመድ ምን እንደዋጣቸው አይታወቅም። ከኒውዮርክ ስብሰባ መልስ ሁለት ቀን ከመኖሪያ ቤቱ እንዳይወጣ እና ከሰው እንዳይገናኝ የታገደው ሃይለማርያም ደሳለኝ ራሱን ፈልጎ አለማግኘቱ እና በአሽከርነት መኖሩን ቤተሰቦቹን እያበሳጨ መሆኑ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ይናገራሉ። ቁልፍ የሆኑ ስልጣኖቹን የተቆጣጠረው እና በዘመድ አዝማድ ተሞልቶ በከፍተኛ የሃገር እና ሕዝብ ሃብት ዘረፋ ላይ የተሰማራው ሕወሓት ባለፈው የኢሕአዲግ ስብሰባ ወቅት አንዳንድ አመራሮቹ ያነሱትን ጥያቄ ተከትሎ ከስልጣን እንደሚባረሩ ሲነገር ነበር።
.
የወያኔና አሽከሮቹ ሹመት እንደሚከተለው ነው:-
አቶ ደመቀ መኮንን – ም/ጠቅላይ ሚኒስትር እና የማህበራዊ ዘርፍ ክላስተር አስተባባሪ
ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል –በም/ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር
ወይዘሮ አስቴር ማሞ – በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የመልካም አስተዳደር ክላስተር አስተባባሪ እና የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስትር
አቶ ሲራጅ ፈጌሳ – የመከላከያ ሚኒስትር
ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም – የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
አቶ ካሳ ተክለብርሃን – የፌደራል ጉዳዮችና አርብቶ አደር አካባቢ ልማት ሚኒስትር
አቶ ጌታቸው አምባዬ – የፍትህ ሚኒስትር
አቶ አብዱላዚዝ መሀመድ – የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር
አቶ ተፈራ ደርበው – የእርሻ እና የተፈጥሮ ሀብት ልማት ሚኒስትር
አቶ ስለሺ ጌታሁን – የእንሰሳትና የዓሳ ሀብት ልማት ሚኒስትር
አቶ አህመድ አብተው – የኢንዱስትሪ ሚኒስትር
አቶ ያዕቆብ ያላ – የንግድ ሚኒስትር
አቶ አብይ አህመድ – የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር
አቶ ወርቅነህ ገበየሁ – የትራንስፖርት ሚኒስትር
አቶ መኩሪያ ሀይሌ – የከተማ ልማት እና ቤቶች ሚኒስትር
ዶክተር አምባቸው መኮንን – የኮንስትራክሽን ሚኒስትር
አቶ ሞቱማ መቃሳ – የውሃ፣ መስኖ እና ኤሌክትሪክ ሚኒስትር
አቶ ሽፈራው ሽጉጤ – የትምህርት ሚኒስትር
አቶ ቶሎሳ ሻጊ – የማዕድን፣ የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስትር
ዶክተር ከሰተብርሀን አድማሱ – የጤና ጥበቃ ሚኒስትር
አቶ አብዱልፈታህ አብዱላሂ – የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር
ኢንጂነር አይሻ መሀመድ – የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር
ወይዘሮ ዘነቡ ታደሰ -የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ሚኒስትር
ዶክተር ሽፈራው ተክለማርያም – የአካባቢ ደን ልማት እና የአየር ንብረት ለውጥ ሚኒስትር
አቶ ሬድዋን ሁሴን – የወጣቶች እና ስፖርት ሚኒስትር
ወይዘሮ ደሚቱ ሀምቢሳ – የመንግስት የልማት ድርጅቶች ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል።
አቶ በከር ሻሌ – የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬከተር
አቶ ጌታቸው ረዳ – የመንግስት ኮሙዩንኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሀላፊ ሚኒስትር
አቶ አስመላሽ ወልደስላሴ – የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር
ዶክተር ይናገር ደሴ – የብሄራዊ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር
.
ትግላችን ላይ በማተኮር ሕወሓትን ከነአሽከሮቹ ልናጠፋቸው ይገባል። በአንድነት በመቆም ሃገራችንን ከጅቦች እናድናለን!!
.
ምንሊክ ሳልሳዊ

የተቸካዮች ምክር ቤት – (በበውቀቱ ስዩም)

agenda_ethiopian_MPs1ትምርት በጨረስን ማግስት እኔና ፍቅር ይልቃል ፈረንሳይ ለጋስዮን ኣካባቢ በዘጠና ብር ቤት መሰል ነገር ተከራይተን እንኖር ነበር፡፡ በየሳምንቱ ቅዳሜ ወደ ቪድዮ ቤት ጎራ እንላለን ፤ እነኩማር በዜማቸው ወፍ ሲያረግፉ ፤ እነ ቫንዳም በጫማ ጥፍያቸው ጥርስ ሲያረግፉ በመመልከት ራሳችን ዘና ለማረግ እንሞክራለን፡፡ ፊልም ዛሬ እንዲህ ጥንቡን ሊጥል ያኔ በጣም ብርቅ ነበር፡፡ ፊልም ሰሪዎች እንኳ እኛ ፊልም ለማየት የምንከፍለውን ያክል መስዋእትነት የሚከፍሉ ኣይመስለኝም፡፡ ያኔ ፊልም ማየት የጫማና የግስላ ሲጃራ ድብልቅ ሽታ የመቻል ቁርጠኝነት ይጠይቃል ፡፡ እናም በጊዜው የሁለት ሰኣት ፊልም ኣይተን የሁለት ሳምንት ጉንፋን ተረክበን ለመውጣት እንገደድ ነበር፡፡

ኣሁን ሳስበው፤ ከፊልሙ በላይ የፈረንሳይ ልጆች በፊልሙ ላይ ተመስርተው የሚሰጡት ኣስተያየት ያዝናናኝ ነበር፡፡ ኣንድ ቀን በጣም እጅ እጅ የሚል ፊልም ስናይ “ፓርላማውን ቀይርልን ፓርላማውን ቀይርልን ”ብለው ቀወጡት፡፡ ኣሰልቺ ፊልሞች” ፓርላማ “ተብሎ እንደሚጠሩ ያወኩት ያኔ ነው፡፡ ባለቪድዮ ቤቱም ኣብላጫውን ድምጽ ኣይቶ ሌላ ፊልም እንዲቀየር ውሳኔ ኣስተለለፈ፡፡

የተወሰኑ የተቃዋሚ ድምጾች በሚሰሙበት ሰሞን እንዳሰልቺ ፊልም ይታይ የነበረው ፓርላማ ዛሬ ይሄ ኣይነቱ ኣጠራር እንኳ የሚበዛበት ይመስለኛል፡፡ እኔን የሚገርመኝ የተወካዮች ምክር-ቤት የሚለውን ስም እስካሁን ይዞ መቆየቱ ነው፡፡ የሚወከልም ሆነ የሚማከር በሌለበት ይሄን ስም መሸከም ኣይከብድም? እንዲያው ቤቱ ስሙ ከብዶት ኣለመፍረሱ ይገርማል፡፡

ያገራችን ፓርላማ ኋላቀር መሆኑን ብዙዎቻችን እናውቃለን፡፡ ግን ከመቶ ኣመት በፊት ከነበረው የምክክር ባህል ኣንጻር ሲወዳደር እንኳ እጅግ ኋላቀር መሆኑን ስንቶቻችን እናውቃለን??
“ብራናው ይገለጥ ተዘርግቶ በኣትሮኖሱ ላይ”::

1
በጅሮንድ ተክለሃዋርያት ተክለማርያም ባድዋ ጦርነት ዋዜማ ስለነበረው ምክር ያይን እማኝ ሆነው የተመለከቱትን ጽፈውልናል፡፡ልቀንጨበው፤
“ራስ(መኮንን)…መኳንንታቸውን ሰብስበው የጦር ምክር ተደረገ፡፡ ራስ ኣሉላም ምክሩ ላይ ነበሩ፡፡
ሌሊት ሲነጋጋ ሸለቆ ለሸለቆ ወርደን እግንቡ ስር ተጠግተን በመሰላል እየተንጠላጠልን ከምሽጉ ውስጥ ገብተን(ጠላትን) እንፍጀው መንገዱን የራስ ኣሉላ ሰዎች ይመሩናል ተባለና ተቆረጠ፡፡ ይህንን ምክር መኳንንቱም የጦር ኣለቆችም ባለሟሎቹም ወደዱት፡፡ ኣንድ ሰው ብቻ በማእረጉ ዝቅተኛ የሆነ(የደራሲው ወንድም ኣብዩ)እየተቃወመ ተናገረ፡፡

ይህ ምክር ትልቅ ጉዳት ያመጣል ሰራዊታችንም በከንቱ ያልቃል ይልቅስ ታግሰን ቀንና ሌሊት ዘብ እየጠበቅን ውሃ ከምሽጉ ውጭ መቅዳት እንዳይችል እናድርግ …”ብሎ ተናገረ፡፡
ቀኛዝማች በሻህ ያብዩን ነገር ክፍኛ ነቀፉት…”ኣንተ ወረቀት ሲጻፍ ትመክራለህ ፡፡ፈርተህ እንደሆነ እሰፈር ዋል ፡፡ እኛ በሾተል እየቀነጠስን እንደኣይጥ እንፈጀዋለን ኣሉ….“

…ኣብዩ ከምንም ኣልቆጠራቸውም ፡፡ በትእግስት መለሰላቸው፡፡”ሰራዊታችን በከንቱ እንዲያልቅ በመደረጉ ኣዝናለሁ፡፡ እናንተ ስትሞቱ እኔ የቀረሁ እንደሁ ያን ጊዜ ፈሪ ተብየ እሰደባለሁ፡፡ “ይህ ተናገረና ወጣ፡፡”
(ኦቶባዮግራፊ፤ ገጽ 60)
የምክሩ ውሳኔ ምንም ይሁን ሰዎች በትልልቅ ኣገራዊ ጉዳዮች ላይ ተሰብስበው ይሟገቱ እንደነበር እንረዳለን ፡፡ በምክሩ ላይ የተለያየ ማእረግ ያላቸው ብቻ ሳይሆን የተለያየ ኣመለካከት ያላቸው ሰዎች ተሳትፈዋል፡፡ በምክክሩ ኣብላጫውን ውሳኔ መቃወም ብቻ ሳይሆን ስብሰባ ረግጦ መውጣትም ይታወቅ ነበር ማለት ነው(ይህን ተናገረና ወጣ“ ተብሎ የተጻፈለትን ኣብዩን ኣስታውሱ )

2
ፕላውደን የተባለ የንግሊዝ ተጓዥ፤ በዘመነ መሳፍንት ማብቂያ በጉድሩ(ወለጋ)የተመለከተውን የሪፐብሊክ ኣስተዳደር እያደነቀ ሲጽፍ እንዲህ ብሏል፡፡
•”ከሌሎች ጎሳዎች ጋር ስለሚኖረው ጉዳይ የሚወሰነው በጉባኤ ነው፡፡ ባደባባዩ ጉባኤ ለመታደም የሚፈልግ ሰው ሁሉ ክብ ሰርቶ ጦሩን ተደግፎ ከብቦ ቆሞ ይመለከታል፡ ፡ ሽማግሌዎች በሚያስደንቅ መንገድ ተራቸውን እየጠበቁ በሰላምና በጦርነት ዙርያ ይከራከራሉ።“
በራስ መኮንን የሸማ ድንኳን ውስጥ እና በጉድሩ መስክ ላይ የታየው ክርክርና ሙግት ፤ በዛሬው ፓርላማ ውስጥ ይታያል?ያለፈውን ስርኣት የመናፈቅ መብት በህገ መንግስቱ ይካተትልንማ!

ዲሞክራሲ ሂደት ነው ይባልልኛል፡፡ ሊሆን ይችላል፡፡ ባገሬ ግን እንኳን ሲሄድ ሲንፏቀቅ ኣይታየኝም፡ ፡ የሚሄድ ቢሆን ኖሮ ከቀደምቶቻችን ውጥን ላይ ተነስቶ ዛሬ ትልቅ ደረጃ ደርሶ እናየው ነበር፡፡ የሚታየኝ ወንበር ላይ ተቸክሎ በድሃ እንባ የተቦካ እንጀራ የሚበላ ሰው ብቻ ነው፡፡ የተወሰኑ ሰዎች ሳይወጡ ሳይወርዱ ቀኝ እጃቸውን ብቻ እያወጡ እያወረዱ እንጀራ የሚበሉበት ቤት፤ “ የተወካዮች ምክር” ቤት መባሉ ያስቃል፡፡ ምናልባት” የተቸካዮች ምክር ቤት “ የሚለው ስም ይመጥነው ይሆን?

Thursday, October 1, 2015

ከአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ (ሞላ አስገዶምን አስመልክቶ) -

ginbot-7በኢትዮጵያ የቅርብ ጊዜ የፖለቲካ ትግል ታሪክ ውስጥ ባጠቃላይና በተለይ ደግሞ ህወሓት/ኢህአዴግ የፖለቲካ ስልጣኑን በተቆጣጠረባቸው ባለፉት ሁለት አስርት አመታት ውስጥ ህወሓት/ኢህአዴግን እንቃወማለን በሚለው ወገን ገንነው የመጡ ሁለት አፍራሽና ኋላቀር የፖለቲካ አዝማሚያዎች (trends ) አሉ። ከነኝህ ውስጥ አንደኛው ራስን በፖለቲካ አመለካከት ዙሪያ ከማሰባሰብ ይልቅ በጎጥና በዘውግ ደረጃ የመመልከትና ሀገራዊ ፖለቲካን በደም ቆጠራ የመመንዘር አባዜ ነው። ሁለተኛውና ከዚሁ ያልተናነሰው ችግር የፖለቲካ ድርጅት በመሰረታዊ ያመለካከት መርሆች ዙሪያ ሰፋ ያለ የማህበረሰብ ክፍልን የማሰባሰቢያ ድንኳን መሆኑ ቀርቶ፤ በስራ ሳይሆን ድንገተኛ አጋጣሚን በመጠበቅ ትርፍ ለማጋበስ በሚቋምጡ ሰነፍ “ነጋዴዎች“ የተቋቋሙ ሩቅ የማይሄዱ የንግድ ድርጅቶች ይመስልበ ተግባር ምንም የማይፈይዱ ”የፖለቲካ ድርጅቶች“ እንደ አሸን የመፍላታቸው ፈሊጥ ነው። እነኝህ ሁለቱም አዝማሚያዎች የህወሓት/ኢህአዴግን ህይወት ከማራዘም አልፈዉ ማህበረሰቡን ወደሚመኘው እውነተኛ የዴሞክራሲያዊ ስርዓት አንድ ጋት እንኳን ፈቀቅ አላደረጉትም። ይልቁንም ዴሞክራሲን የሚናፍቁ ታጋዮች ተሰባስበውና ተጠናክረው ስርዓቱን ከመግፋት ይልቅ በግለሰብ ደረጃ ወይንም በትናንሽ ቡድኖች በመሰባሰብ የሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች በስርዓቱ በቀላሉ እየተመቱ ብዙ ታጋዮች ለሞት፤ ለስቃይና ለእስር ተዳርገዋል። አሁንም እየተዳረጉ ነው።


የዚህ አይነት የትግል አካሄድ ሩቅ እንደማያስኬድ የኢትዮጵያ ህዝብ ከተገነዘበው ቆይቷል። ይህ አካሄድ እንዲቀየርና የፖለቲካ ሀይሎች ተሰባስበው ይህንን በስልጣን ላይ ከሚገባው በላይ የቆየና አገሪቱን ለውርደት የዳረገ የጥቂት ዘራፊዎች ቡድን ከጫንቃው ላይ እንዲያነሱለት ሲማጠን ቆይቷል።ምንም እንኳን በመሪዎች ድክመት የሚመኘውን ዳር መድረስ ባይችልም ባጭር ጊዜ ልምዱ በትንሹም ቢሆን የተባበረ ትግል ሊያስገኝ የሚችለውን ጥቅም በመጠኑም ቢሆን አይቶታል።
ይህ የህዝብ ፍላጎት መኖር ግን በራሱ ይህንን የተባበረ ሰፊ ማህበራዊ እንቅስቃሴ መፍጠርን ቀላል ያደርገዋል ማለት አይደለም። በብዙ ስራ፤ በብዙ ድካምና ያላሰለሰ ጥረት የሚፈጠር እልህ አስጨራሽ ሂደት ነው። ባንድ በኩል እንዲህ አይነት ሰፊ የህዝብ እንቅስቃሴ በስልጣኑ ለመቆየት የሚፈጥርበትን ችግር የሚረዳው በስልጣን ላይ ያለው የዘራፊዎች ቡድን ይህን እንቅስቃሴ ከወዲሁ ለማምከን ያለ የሌለ የገንዘብ፤ የስለላና የተንኮል ሀይሉን ይጠቀማል። በተቃዋሚ ድርጅቶች ውስጥ ሰርጎ በመግባትና ደካማ ሀይሎችን በገንዘብ በመግዛት ወይንም በማስፈራራት እንዲህ አይነት ትብብሮች እንዳይፈጠሩ ከውስጥ ለመቦርቦር ተግቶ ይሰራል። በሌላ በኩል ደግሞ የትም የማያደርሳቸውን “የራሳቸውን ድርጅት” የሙጢኝ ብለው ለትልቅና አገራዊ አላማ እራሳቸውን ላለማስገዛት የቆረጡ ደካማ “የድርጅት መሪዎች” እንዲህ አይነቱን የጋራ እንቅስቃሴ በራሳቸው ግብዝነትና ስግብግብነት ምክንያት ብቻ ሊያሰናክሉት መሞከራቸው አይቀርም።


ይህ ግን ጊዜው ያለፈበት አዝማሚያ ነውና የሚሳካ ሙከራ አይሆንም። የተናጠል ትግል ሂደት ማብቂያው ጊዜ ተቃርቧል። የኢትዮጵያ ህዝብም ሆነ ለእውነተኛ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ የሚታገሉ ኃይሎች እንዲህ አይነቱን ፋይዳ ቢስ ሂደት የመቀበል ትዕግስታቸው ተሟጧል። በቅርብ ጊዜ የሞላ አስገዶምን መክዳት በማስመልከት የትህዴን አመራር ባወጣው መግለጫ“ኢትዮጵያን እውነተኛ ዴሞክራሲያዊት ሀገር ለማድረግ ከሁሉም ኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ጋር አብሮ መስራት የድርጅታችን መሰረታዊ መርሆ ነው” እንዳለው ይህ መሰረታዊ መርሆ በሀገራችን የጸረ ህወሓት/ኢህአዴግ ትግል የበላይነት ይዞ እየመጣ ያለ እጅግ አስፈላጊና ለድሉም ወሳኝ የሆነ የጊዜው የፖለቲካ አዝማሚያ ነው። አርበኞች ግንቦት 7 ይህን መሰረታዊ መርሆ ከምር ወስዶ የሚንቀሳቀስ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ነው።


ይህአዲስ የፖለቲካ አዝማሚያ ምቾት የማይሰጣቸው የፖለቲካ ኃይሎች መኖራቸው የሚጠበቅ ነው። የህወሓት/ኢህአዴግ የስለላ ድርጅት ከሰሞኑ ሞላ አስገዶምን በማስመልከት ባወጣው መግለጫ በግልጽ እንዳስቀመጠው ኢትዮጵያውያን የዴሞክራሲ ኃይሎች ተሰባስበው እንዳይታገሉና ስርዓቱን እንዳይፈታተኑ የማያደርገው ጥረት የለም። በዚህ በህወሓት/ኢህአዴግ መሰሪ እንቅስቃሴ ደግሞ በቀላሉ መጠቀሚያ የሚሆኑት በጋራ የሚደረግ ትግል በግለሰብ ደረጃ ያሳጣናል ብለው የሚፈሩት “የግል ጎጆና” ጥቅም የሚያስጨነቃቸው ደካማ የፖለቲካ መሪዎች ነን ባዮችን ነው። ባንጻሩ በየድርጅቶቹ ውስጥ በሚገኙት ብዙሀኑ ሩቅ አሳቢ መሪዎች ጥረትና በተለይም ደግሞ ይህን ትግል ለአላማ እንጂ ለሌላ ምንም አይነት የግል ጥቅም ያልተቀላቀሉና በትግሉ ሂደትም ትልቁን ሚና በሚጫወቱት ብዙሀን ታጋዮች አልበገር ባይነት እንዲህ አይነት ደካማ መሪዎች ተከታይ በማጣት ሲዳከሙና በሚያደርጉት እንቅስቃሴ በድርጅታቸው ውስጥ የሚነሳባቸውን ተቃውሞ መቋቋም ባለመቻላቸው በቀላሉ እየተፍሸለሸሉ ከመራገፍ በስተቀር በድርጅቶቹ ላይ ከባድ ጉዳት ሳያደርሱ ይከስማሉ።


በህወሓት/ኢህአዴግ “የስለላ ድርጅት አቀናባሪነት” በሞላ አስገዶም መሪነት ከሰሞኑ የተሞከረው የማፍረስ ንቅናቄ ከሽፎ ወደ ተስፋ መቁረጥ የክህደት እንቅስቃሴ የተቀየረው የሰሞኑ ሙከራም የዚህ አጠቃላይ ሂደት አካል ነው። በዚህ የከሸፈ ሙከራ ውስጥ እጅግ የሚገርመውና የትህዴንን ብዙሀን አመራሮች ብስለት፤ የድርጅቱን መዋቅራዊና ድርጅታዊ ጥንካሬ፤ እንዲሁም ብዙሀኑ ታጋይ ለጋራ ትግል ያለውን ቆራጥ አቋም ያስመሰከረው፤ ይህንን የማፍረስ ሙከራ የመራውና ሳያሳካለት በመጨረሻም በጣም ጥቂት ተከታዮቹን ብቻ ይዞ የከዳው ለረጅም ጊዜ የድርጅቱ ሊቀመንበር የነበረው ሞላ አስገዶም መሆኑ ነው። እንዲህ አይነት የመክዳት ሂደት ባጭር ጊዜ በማህበረሰባችን ላይ የሚፈጥረውን አስጨናቂ ስሜት የምንረዳው ቢሆንም ከዚያ በላይ ልንረዳው የሚገባው ግን በእንዲህ አይነት ከፍተኛ ያመራር ቦታ የነበረ ሰው ሙከራ አለመሳካት በእርግጥም የሀገራችን ፖለቲካ እየበሰለ፤ ከግለሰብ አመራሮች ተጽእኖ እየተላቀቀ፤ አዲስ የተባብሮ መታገል አቅጣጫን እያበሰረ እየሄደ መሆኑንና በትናንሽ ሰዎች መግተርተር ይህ ሂደት የማይቀለበስ መሆኑን የሚያመለክት የረጅም ጊዜ ግኝት መሆኑን ነው።


አርበኞች ግንቦት 7 በዚህ አጋጣሚ ለትህዴን ብዙሀን አመራርና ለሰፊው ታጋይ በመርህ ላይ ለተመሰረተው አቋማቸውና መርሃቸውን ለማስጠበቅ ለሚያደርጉት ቆራጥ ትግል ያለውን ጓዳዊ አክብሮት ይገልጻል። በመግለጫቸው ላይ በግልጽ ያስቀመጡት መርሆአቸው የኛም መርሆ መሆኑን ስንገልጽላቸው በታላቅ ኩራት ነው። ድርጅታቸውን እያጸዱ የተመሰረቱበትን መርሆ ጠብቀው ለመጓዝ ባሳዩት ቁርጠኝነትና ወደፊትም በሚያደርጉት ትግል ምንጊዜም ከጎናቸው መሆናችንንና ጓዳዊ ድጋፋችን ምንጊዜም እንደማይለያቸው በዚህ አጋጣሚ ደግመን ልናረጋግጥላቸው እንወዳለን። በመግለጫቸው ላይ እንዳሉትም ይህ ትግል ኢትዮጵያን ዴሞክራሲያዊ ሳያደርግ የማይቆምና እንዲያውም ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና ለኢትዮጵያ ህዝብም በየጊዜው በሚፈጠሩ እንቅፋቶች ላይ ሳያተኩር ትግሉን በሙሉ ልብ እንዲደግፍ ያደረጉት ጥሪ የኛም ጥሪ ነው።


አንድነት ኃይል ነው!!!
አርበኞች ግንቦት 7: ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ

ህወሃት ጦርነት ጀመረ፣ ቁስለኞች ታይተዋል

pow-and-medic-3_xlargeበነጻ አውጪ ስም አገር እየገዛ ያለውን የትግራይ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃትን) ለመውጋት ብረት ያነሳው ሌላ የትግራይ ነጻ አውጪ ሃይል /ትህዴን ወይም በትግሪኛ ዴምህት/ መሪ የነበረው “ተጋዳላይ” ሞላ አስገዶም ህወሃትን ከተቀላቀለ ጥቂት ቀናት በኋላ ጦርነት መጀመሩ ተሰማ። የህወሃት ወኪል ሃይለማርያም ደሳለኝ ውጊያው የሚጀመረው የህዝብ ፈቃድ ተጠይቆ እንደሚሆን ተናግረው ነበር።

የጎልጉል መረጃ አቀባዮች ከአዲስ አበባ እንደገለጹት ጦር ኃይሎች ሆስፒታል ቁስለኞች እየገቡ መሆኑንን እማኞች ነግረዋቸዋል። ጦርነቱ በየትኛው መንደርና ወረዳ እንደተጀመረ ለይተው ያላስረዱት የዜናው ባለቤቶች፣ ውጊያ እየተካሄደ ያለው ኤርትራ ምድር ላይ እንደሆነ ግን አልሸሸጉም።

አንድ የሆስፒታል ሰራተኛ ዘመድ ደውሎላቸው “ቁሰለኞች አሉ ሥራ በዝቶብኛል” ማለታቸውን የጎልጉል መረጃ ሰጪዎች ከአዲሰ አበባ ገልጸዋል። ባለፈው ሳምንት በሁመራ አቅጣጫ የከባድ መሳሪያ ተኩስና ድብደባ መሰማቱን የተለያዩ ድረገጾች ዘግበው ነበር። ይህ ሁሉ ከመሆኑ በፊት ሻእቢያ “ህወሃት ሊወረኝ ነው” ሲል ክስ ማሰማቱ አይዘነጋም።

ኦምሃጀር በሚባለው ስፍራ የከረረ ውጊያ እየተካሄደ መሆኑን እንደሰሙ የገለጹ በውጊያው የትኛው ወገን ድል እንደተቀዳጀ ለጊዜው መናገር እንደማይቻል አመልክተዋል። ውጊያው ጠርዙን አስፍቶ እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል።

ከህወሃት በኩል ውጊያው ከሻዕቢያ ጋር እንደሆነ ቢገለጽም ከሌላ ወገን “ህወሃትን የወጋሁት እኔ ነኝ” ባይ ይህ ዜና እስከታተመ ድረስ አልተሰማም። የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ህወሃትን በነፍጥ አንበረክካለሁ በማለት ማወጁና አመራሮቹም ወደ ውጊያው አውድ ማምራታቸው ይታወቃል። ህወሃት ኤርትራን በአራት አቅጣጫ የመውጋት እቅድ እንዳለው ጎልጉል መዘገቡ የሚታወስ ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በርካታ የሰራዊቱ አባላት ከሰራዊቱ እየሸሹና እየተሰወሩ መሆናቸው ህወሃትን እንዳሳሰበው፣ ጦሩ የመዋጋት ፍላጎት ያጣል የሚል ሥጋት እንዳለ የሚጠቁሙ ክፍሎች “የአሁኑ የውጊያ አቅጣጫ በዚህ መልኩ እንዲሆን መደረጉ ይህንኑ ለመፈተንም ጭምር ነው” ብለዋል።

በሌላ ዜና በሶማሌ ያለው ሰራዊት የመመለስ ጥያቄ ማንሳቱና ሁለት ጄኔራሎች ጦሩን ለማወያየት ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ስፍራው አቅንተው እንደነበር ለማወቅ ተችሏል። ጦሩ መስዋዕትነት እየከፈለ በተደጋጋሚ የተቆጣጠረውን ቦታ እንዲለቅ ትዕዛዝ ሲቀበል መቆየቱ ሌላው የቅሬታው መነሻ ሲሆን በሶማሌ ያለው የሰላም አስከባሪ ሃይል ይህንኑ ነቅፎ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል። በህወሃት የሚመሩት የኢህአዴግ ባለስልጣናት በሶማሌ ስለተገደሉት ወገኖች መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆናቸው፣ ተቃዋሚ ፓርቲዎችም ይህንን አክርረው አለመጠየቃቸው፣ ላለፉት አምስት ዓመታት 99.6 በመቶ ህወሃት የነገሰበት ማኅበርም (ፓርላማ) ለይስሙላ እንኳን ጥያቄ አቅርቦ እንደማያውቅ በርካቶች የሚተቹበት አገራዊ ጉዳይ ነው።