* ትናንት ቅዳሜ መጋቢት 19 ግብጽ ሻርማ ሸክ ተሰብስበው የነበሩት 22 የአረብ ሊግ ሀገራት መራሄ መንግስታት በ26 ኛው መደበኛ ስብሰባ
የየመንን ጉዳይ በሰፊው ተነጋግረውበታል
* መራሔ መንግስታቱ የሁቲ አማጽያን በኃይል ከያዘው ስልጣን ለማስወገድና ህጋዊውን የፕሬ አብድልረቡ መንግስት ወደ ቦታው ለመመለስ
ተስማምተዋል !
* የሳውዲው ንጉስ ሰልማን " ዘመቻው ግቡን እስኪመታ አያቆምም !" ሲሉ የግብጽ ፕሬ አል ሲሲ በበኩላቸው የጽንፈኝነትን መንሰራፋት በማውሳት
በአረብ ሀገራትን አደጋና ከኢራን ትንኮሳ ለመታደግ ጥምር የጦር የአረብ ሀገራት ሰራዊት እንደሚያስፈልግ በስብሰባው ላይ በአጽንኦት ተናግረዋል
* ጉባኤው በአረብ ጥምር የህብረት ጦሩን ጉዳይ ከመከረ በኋላ በስብሰባው መዝጊያ የአብ ሊግ ዋና ጸሃፊ ነቢል አል አረቢ ባሰሙት የአቋም መግለጫ
ከዚህ ቀደም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ያቀረቡት ረቂቅ ህግ ተጠንቶ በአጠቃላይ ጉዳይ በአንድ ወር ውስጥ ተገናኝተው በመምከር ታሪካዊ ያሉትን
የህብረት ጦሩ ለመጀመሪያ ጊዜ ለመመስረት እቅድ መያዙን አስታውቀዋል
* የኩዌትን አሚር ጨምሮ የተለያዩ አረብ ሀገራት ኢራን የአካባቢውን ሀገር ሰላም ለመንሳት በተዘዋዋሪ የምታሳየውን ተደጋጋሚ ፍላጎት
ተቃውመውታል
* ፖለቲካ ነውና ያልተጠበቀው ይሆናል ፣ የፍልስጥኤም መሪ ፕሬ መሀሙድ አባስ በአረብ ሊግ ስብሰባ የተገኙ ሲሆን ከኢራን ድጋፍ ያገኛል
የሚባለው የፍልስጥኤሙ ሽምቅ ተዋጊ ሃማስ የአረብ ሀገራቱን አቋም የሚደግፍ አስገራሚ የድጋፍ መግለጫ አውጥቷል
* የየመንን ህጋዊ መሪ ፕሬ አብድልረቡ መንሱር አልሃዲን መንግስት ወደ ስልጣን ለመመለስ በሳውዲ የሚመራውን ዘመቻ እንደሚደግፈው
ፍልስጥኤምን ነጻ ለማውጣት ጠመንጃ ያነሳው ሽምቅ ተዋጊው ሃማስ ዘመቻውን ደግፎ መግለጫ ማውጣቱ ብዙዎችን አስገርሟል
* ስድስቱ ኦማንን ሳይጨምር የባህረ ሰላጤ ሀገራትን ሳውዲ ፣ ኢምሬት ፣ ቃጣር ፣ ኩዌትና ባህሬንን ጨምሮ ዮርድያኖስ ፣ ግብጽ ፣ ሱዳን ፣ ሞሮኮ
በዘመቻው ተሳታፊ ሲሆኑ ፣ ቱርክ፣ ሞሮኮ ፣ አሜሪካ ፣ እንግሊዝ ፈረንሳይ እና ቤልጅየም ድጋፍ መስጠታቸው ይጠቀሳል በአንጻሩ ሶርያ ፣ ኢራን ፣
ራሽያና ቻይና ዘመቻውን አጥብቀው ተቃውመውታል
* ኢራን የሁቲ ሸማቂዎችን በማስታጠቅና በመደገፍ ከፍተኛ ሚና እንደተጫወተች የየመን ፕሬ አብድልረቡ መንሱርና የአረብ ሀገር መራሔ
መንግስታት ቢጠቁሙም ኢራን የሚቀርብባት ውንጀላ ሁሉ " መሰረተ ቢስ ውንጀላ ነው! " ስትል አስተባብላለች
የትዕንግርተኛው የመን " ድብደባውን አቁሙ! " ተማጽኖ ...
===================================
* የቀድሞው የየመን ፕሬ አሊ አብደላ ሳላህ ከ30 ዓመት በላይ የመንን ሲያስተዳድሩ አቀማጥለው የደገፏቸው ፣ የአረብ አብዮት መጥቶ ሀገር የመን
ስትታመስና ፕሬ አብደላ ሳላህ በአጥፍቶ ጠፊ ሲጎዱ አፈፍ አድርገው ህይወታቸውን የታደጉትንና ወደ ኋላም የመን በተቃውሞ ስትናጥና
ስልጣናቸው አልረጋ ሲል መውጫ መንገድ ያበጁላቸው በቅርብ ሳውዲዎች ፣ በርቀት የባህረ ሰላጤ ሀብታም አረብ ሀገራትና ምዕራባውያን ናቸው
* ዛሬ የቀድሞው ፕሬዚደንት ከቁርጥ ቀን ደጋፊያቸው ከሳውዲ ፣ ከአረብ ሀገራትና ከምዕራባውያን በተቃራኒ ጎራ መሰለፋቸው ይጠቀሳል ፣ የቀድሞ
ታዛዥ አጋራቸውና ስልጣናቸውን ሳይወዱ በግድ ያስረከቧቸውን የፕሬ አብድልረቡ መንበረ ስልጣን እንዳይረጋ እንደ ኢራን በድብቅም ባይሆን
በግላጭ ሁቲዎችን በመደገፍ የቀድሞው መሪና ልጃቸው አህመድ የመንን ለዚህ ውጥንቅጥ እንዳደረሷት ይጠቀሳል
* የቀድሞው የየመን ፕሬ አሊ አብደላ ሳላህ በ26 ኛው የአረብ ሊግ የመሪዎች ስብሰባ ለተቀመጡት መራሔ መንግስታት ሳውዲ መራሹ ዘመቻ ያቆም
ዘንድ " ችግሩ የተፈጠረው በፕሬ አብድልረቡ የአስተዳደር አቅም ማነስ ነው ፣ ድብደባውን አቁሙ ፣ መፍትሔው በድርድር እንጅ በጦርነት
አይደለም! " የሚል አንድምታ ያለው ትንግርተኛ ተማጽኖ በአንድ ታዋቂ የአረብኛ ቴሌቪዥን በኩል መልዕክት አስተላልፈዋል
* የቀድሞው ፕሬዚደንት የቆየውን የሳውዲና የሀገራቸውን መልካምና ጠንካራ ግንኙነት ፣ ከ1.7 ሚሊዮን በላይ የመናውያን በሳውዲ በተለያዩ
ስራዎች ተሰማርተው የመገኘታቸውን መልካም ጉርብትና በማውሳት ሳውዲ መራሹ ጦር በየመን ላይ የከፈተውን ዘመቻ ልጆቻችንና ሀገራችን
እያወደመ ነው ሲሉ ድብደባው በአስቸኳይ ያቆም ዘንድ ልዩ መልዕክትን ለሳውዲ መንግስት አስተላልፈዋል
* የቀድሞው የየመን ፕሬ አሊ አብደላ ሳላህ በዚሁ ንግግራቸው የመንን በድርድር የማረጋጋቱ ስራ ቅድሚያ ይሰጠው ሲሉ የየመን ወቅታዊ ችግር
በድርድር ከተፈታ በቀጣይ ምርጫ ቢደረግ እርሳቸውም ሆኑ የቤተሰብ አባሎቻቸው ወደ ስልጣን መንበር የመውጣት ፍላጎት እንደሌላቸው
በንግግራቸው አስታውቀዋል
* የቀድሞው የየመን ፕሬ አሊ አብደላ ሳላህ ልጆች መካከል የጦር መኮንኑ አህመድ በሶስተኛው ቀን የአየር ላይ ድብደባ እንደቆሰሉ አንዳንድ መገናኛ
ብዙሃን ጠቁመዋል ። የተረጋገጠ መረጃ ነው ማለት ግን አይቻልም። ይህ በእንዲህ እንዳለ በቀድሞው የየመን አስተዳደር በከፍተኛ የጦር ኃላፊነት
ያገለግሉ ከነበሩት ውስጥ የቀድሞው ፕሬዚደንት ልጅ አህመድ በሳውዲ የተመራው ጦር የዘመቻ ጥቃት ከመደረጉ አስቀድሞ የሁቲ አማጽያንን
ከስልጣን ለማስዎገድ እድሉ እንዲመቻችለት ጥያቄ አቅርቦ ተቀባይነት አለማግኘቱን አል አረቢያ ዘግቦታል
የሁቲዎቻ ዛቻና የዘመቻው መምሪያ መግለጫ
============================
* የሁቲ ከፍተኛ ባለስልጣን አብል ሙንኢም አል ቁረሽ የሳውዲን ጣልቃ ገብነት በዚህ ከቀጠለ ሳውዲ ልትቆጣ ጠር የማትችለው ጥቃት
እንሰነዝራለን ሲሉ ለኢራን አል ፋሪስ ዜና ወኪል በሰጡት መግለጫ ዝተዋል
* በሁቲዎች ዛቻና በዘመቻው ዙሪያ ትናንት መግለጫ የሰጡት በሳውዲ የተመራው የህብረት ጦር ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጀኔራል አህመድ አሲሪ ስለ
አራተኛው ቀን የአየር ድብደባ መግለጫ ሰጥተዋል
* ብርጋዴር ጀኔራል አህመድ አሲሪ በተለያዩ ከተሞች በዘመቻው መምሪያ በተጠኑ የሁቲ አማጽያን ወታደራዊ ኢላማዎች አልፎ ወደ ሳውዲ የመን
ድንበር የጀዛንና ነጅራን ዘልቀው ጥቃት ሊሰነዝሩ የነበሩ የሁቲ ቡድን አባላት እግር በእግር እያታሰሰ የመደምሰሱ ስኬታማ ስራ መስራቱን የዘመቻው
ቃል አቀባይ አስረድተዋል
* ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጀኔራል አህመድ አሲሪ በዚሁ መግለጫቸው በሳውዲ የተመራው የህብረት ጦር በሁቲ አማጽያን እጅ የነበረውን የብላስቲክሚሳየል ክምችት ballistic missile stockpile በአብዛኛው ማውደሙን አስታውቀዋል
* ከየመን ሰንአ የህብረቱ የአየር ኃይል ጦር የደቡብ ከተማዋ በዳሊያ ባደረገው ወታደራዊ ይዞታዎች ኢላማ ያደረገ ድብደባ የሁቲ አማጽያን ጸረ
አውሮፕላን በመተኮስ መልስ መስጠታቸውም ተጠቁሟል
* ወደ ሶስት መቶ የሚጠጉ የሳውዲ ፣ የምዕራባውያን ሀገር ዲፕሎማቶች እና የተባበሩት መንግስታት ሰራተኞችን በተለያየ ዘመቻ ሰንአ የመንን ለቀው
መውጣታቸው ታውቋል ። እስኪ ቸር ያሰማን
Tuesday, March 31, 2015
Hiber Radio: ግብጽ የአባይን ግድብ እንቅስቃሴ የሚቃኝ የስለላ ሳተላይት መግጠሟ ታወቀ.. ከ10 ሺ በላይ የቅማንት ማህበረሰብ ከቀያቸው እንዲለቁ ትዕዛዝ ተላለፈ… በካናዳ ለ5 ዓመት የጠፋው ኢትዮጵያዊ አስከሬኑ ከጣራው ስር ተገኘ.. የደብረታቦር ሕዝብ አገዛዙ ስልጣኑን እንዲለቅ በተቃውሞ ሰልፍ ጠየቀ… ኢትዮጵያ ጦሯን ከሶማሊያ ባይዳዎ ግዛት አወጣች…ኢትዮጵያውያን የእግረኛ ጦርነት ከመጀመሩ በፊት በየመን ላሉ ወገኖቻቸው ጠንክረው ድምፃቸውን እንዲያሰሙ ተጠየቁ… እና ሌሎችም
Hiber Radio: ግብጽ የአባይን ግድብ እንቅስቃሴ የሚቃኝ የስለላ ሳተላይት መግጠሟ ታወቀ.. ከ10 ሺ በላይ የቅማንት ማህበረሰብ ከቀያቸው እንዲለቁ ትዕዛዝ ተላለፈ… በካናዳ ለ5 ዓመት የጠፋው ኢትዮጵያዊ አስከሬኑ ከጣራው ስር ተገኘ.. የደብረታቦር ሕዝብ አገዛዙ ስልጣኑን እንዲለቅ በተቃውሞ ሰልፍ ጠየቀ… ኢትዮጵያ ጦሯን ከሶማሊያ ባይዳዎ ግዛት አወጣች…ኢትዮጵያውያን የእግረኛ ጦርነት ከመጀመሩ በፊት በየመን ላሉ ወገኖቻቸው ጠንክረው ድምፃቸውን እንዲያሰሙ ተጠየቁ… እና ሌሎችም

< …ዛሬ በደብረ ታቦር ሕዝቡ በተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ወጥቶ ስርኣቱ በቃን ፣ልቀቁን ውረዱ ብሏል…ሕዝቡ ሰልፉን እንዳይቀላቀል መንገድ ዘግተውበታል ። ከፍተና የፖሊስና የደህንነት ሀይል ነበር።..ምርጫው ነጻ ቢኖር ኖሮ ለብአዴን ድምጽ የሚሰጠው አይኖርም …> አቶ ሳሙኤል አበበ በደብረ ታቦር ሰማያዊ ፕርቲን ጨምሮ የዘጠኙ ፓርቲች ትብብር የጠራው ሰልፍ አስተባባሪና የሰማአዊ ዕጩ ተወዳዳሪ ስለሰልፉ ተጠይቆ ከተናገረው የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡ )
<…በየመን ያዩ ኢትዮጵያውያን ከወዲሁ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ከዚህ ሳውዲ የተባረሩትም በዚያው ነው የሚመጡት ከአገር ቤትም ወደ የመን የሚሄዱ ይኖራሉ በዚህ የጦርነት ወቅት ግን…>
ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ከጂዳ በሳውዲ የሚመራው ጦር በየመን አማጽያን ላይ የከፈተውን የአየር ጥቃት ተከትሎ በኢትዮጵያውያን ላይ ስለጋረጠው ስጋት ካደረግነው ቃለ መጠይቅ(ሙሉውን ያዳምጡት)
<…እዚህ በየመን ያለንበት ሁኔታ እጅግ አስጊ ነው። ስደተኛው በጥሩ መንገድ አይታይም ። የአየር ድብደባውን ተከትሎ የእግረኛ ጦርነት ከተጀመረ ሁኔታዎች አስቸጋሪ ይሆናሉ … አስከፊ ችግር ውስጥ ስንገባ ከመሰለፍ አሁኑኑ አስቀድሞ ሊጮህልን ይገባል…>
ጋዜጠኛ ግሩም ተ/ሀይማኖት በየመን ኢትዮጵያውያን ስላሉበት ሁኔታ ከህብር ተጠይቆ ከሰጠው ምላሽ(ሙሉውን አዳምጡት)
ኢትዮጵያ ግብፅና ሱዳን በህዳሴው ግድብ ላይ ያደረጉትን ስምምነት መሰረት ያደረገ የግብፅ መገናኛ ብዙሃን እይታ (ልዩ ዘገባ )
ባሻ ይገዙ < ሰይጣን በአገሩ! > (ልዩ ግጥም)
በቬጋስ የፍሪያስ የቀድሞ ታክሲ አሽከርካሪዎች የስራ ማቆም አድማ ያደረጉበትን ሁለተኛ ዓመት አስመልክቶ ውይይት
ሌሎችም
ዜናዎቻችን
– ግብፅ የአወዛጋቢውን ህዳሴ ግድብ እንቅስቃሴ የሚቃኝ ዘመናዊ የስለላ ሳተላይት መግጠሟ ታወቀ
– የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎችና የአገዛዙ ወታደሮች ፍጥጫ ውስጥ ገቡ
* ከ10 ሺህ በላይ የቅማንት ነዋሪዎች ከመኖሪያቸው በሁለት ሳምንታት ውስጥ ለቀው እንዲወጡ መመሪያ ተላለፈባቸው
– ኢትዮጵያ ጦሯን ከሶማሊያ ባይዳዎ ግዛት አወጣች
– የዘጠኙ ፓርቲዎች ትብብር በ15ከተሞች ካቀዱት ሰላማዊ ሰልፍ በጥቂት ከተሞች በከፍተኛ ጫና አካሄዱ
– በደብረ ታቦር በሰልፉ ላይ ህዝቡ አገዛዙ እንዲወርድ ጠየቀ
– ኬኒያ ህገወጥ ያለቻቸውን 65ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በገንዘብ ቀጣች
– በካናዳ ለ5 ዓመት የጠፋው ኢትዮጵያዊ አስከሬኑ ከጣራው ስር ተገኘ
– የየመን የእርስ በእርስ ጦርነት ወደ አካባቢ ጦርነት ማደጉ ስጋት ፈጠረ
– ሱዳን በየመን የተሰማሩ ጄቶቿ ጥቃት እንዳልደረሰባቸው ገለፀች
* ኤርትራ የየመን አማፅያን አላስተናገድኩም አለች
– በየመን የሚገኘው የአገዛዙ ኤምባሲ ዲፕሎማቶቹን ለማስወጣት እየተሯሯጠ ነው
* ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን በምዝገባ ስም እየሸነገለ ነው
– ኢትዮጵያውያን የእግረኛ ጦርነት ከመጀመሩ በፊት በየመን ላሉ ወገኖቻቸው ጠንክረው ድምፃቸውን እንዲያሰሙ ተጠየቁ
– በቬጋስ በፍ/ቤት ታግዶ የነበረው ሁበር በቅርቡ ወደ ገበያው እመለሳለሁ አለ
ሌሎችም ዜናዎች አሉ
የምርጫ ክርክር ሶስት- ግብርና እና ገጠር ልማት – ግርማ ሰይፉ ማሩ

“የ1997 የምርጫ ክርክር ይደገም ……”
ግርማ ሠይፉ ማሩ
girmaseifu32@yahoo.com; girmaseifu.blogspot.com
ተከራካሪዎች፤
አቶ ተፈራ ደርቤ እና ዶ/ር አብርሃም ተከስተ
አቶ ግርማይ አደራ እና ዐዐዐዐዐ
አቶ ትዕግሰቱ አወሉ እና አቶ ዮሃንስ አሰፋ
አቶ ግዑሽ ገብረሰላሴ እና ትዕግሰቱ ዱባለ
አቶ ጥላሁን እንዳሻው እና ሙላቱ ገመቹ
ግርማ ሠይፉ ማሩ
girmaseifu32@yahoo.com; girmaseifu.blogspot.com
ተከራካሪዎች፤
አቶ ተፈራ ደርቤ እና ዶ/ር አብርሃም ተከስተ
አቶ ግርማይ አደራ እና ዐዐዐዐዐ
አቶ ትዕግሰቱ አወሉ እና አቶ ዮሃንስ አሰፋ
አቶ ግዑሽ ገብረሰላሴ እና ትዕግሰቱ ዱባለ
አቶ ጥላሁን እንዳሻው እና ሙላቱ ገመቹ
በመጋቢት 18 እና 19 2007 ለግንቦት ምርጫ የተደረገው “የምረጡኝ ክርክር” የተጀመረው በአቶ ተፈራ ደርበው በተመራው የኢህአዴግ ቡድን በግንባሩ ውስጥ በከባድ ሚዛኑ ህወሃት ተወካዮ ዶክተር አብርሃም ተከሰተ በመታገዝ ነበር የተገኘው፡፡ ተከራካሪዎቹ በኢህአዴግ በተተኪ መስመር የሚገኙ ቢሆኑም እንደ ወትሮ ሁሉ ኢህአዴግ የሚያቀርበው አዲስ ሀሳብ ለሚቀጥለው የስልጣን ዘመን ሊያቀርብ አልቻለም፡፡ እነዚህ የኢህአዴግን ሹሞች ልብ አውልቅ የሆነውን በእውሸት የተሞላውን የቁጥር ጫወታ ይዘው ብቅ ያሉ ሲሆን በዚህ ደረጃ ሊሞግታቸው የሚችል፤ አንድም ተቃዋሚ ነኝ የሚል ለማየት አልቻልንም፡፡ ኢህአዴጎች ከታቃዋሚዎች በላቀ ደረጃ ጎላ ያደረጋቸው የለበሱት ሱፍና የተጫሙት ጫማ ማብቅረቅ ሲሆን ተቃዋሚዎች አሁንም ከጀርባቸው ያስቀመጧቸው አማካሪ ተብዬዎች ምንም ያለመፈየድ ሳይሆን እንቅልፍ ሲያንጎላጃቸው ማየት ኢህአዴግ በዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ምን ዓይነት ሰዎችን ወደፊት እያመጣ እና ወደፊትም እንደሚያመጣ አመላካች ነው፡፡ ከተቃዋሚ ጀርባ ለተቀመጡትም ሆነ በፊት መስመር ላሉት ደካማ ተቃዋሚዎች ተጠያቂው ኢህአዴግ እና የዘረጋው ስርዓት መሆኑን መዘንጋት የለብንም፡፡
ኢህአደግ ለቀጣይ አምስት ዓምት በስልጣን እንደሚቆይ ቢያውቅም ይህን በትህትና ለገጠሩ ህብረተሰብ ያስተላለፉት ዶክተር አብርሃም ተከሰተ እና ቆጣ ቆጣ ሲሉ የነበሩት አቶ ተፈራ ደርቤ ናቸው፡፡ ለዚህም እንደማስረጃ ያቀረቡልን
· 60 ሺ በላይ የገጠር ልማት ሰራተኞች እና የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች(በተቃዋሚዎች በትክክል ካድሬዎች ተብለው የተፈረጁት)፤
· ድህነትን በ1988 ከነበረበት 48 ከመቶ ወደ 24 ከመቶ ዝቅ ማድረጋቸው፤ (በመቶኛ ቀነሰ ቢባልም በቁጥር ግን በ1988 ከነበረው ጋር ተቀራራቢ ነው፡፡)
· መስኖ እና ሰፈራ በአርብቶ አደሩ አካባቢ ማስፋፋቱ፤
· 2.2 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በግል ባለሀብት እየለማ መሆኑ (ይህ መረጃ በቅርቡ እየተነገረ ቢሆንም ኢትዮጵያዊያን በዚህ መስክ የሚያደርጉት ተሳትፎ በግልፅ የሚታይ አይደለም)
· የመሰረተ ትምህርት እና ተግባር ተኮር የጎልማሶች ትምህርት መስፋፋቱ፤ ወዘተ ሲሆን
ኢህአደግ ለቀጣይ አምስት ዓምት በስልጣን እንደሚቆይ ቢያውቅም ይህን በትህትና ለገጠሩ ህብረተሰብ ያስተላለፉት ዶክተር አብርሃም ተከሰተ እና ቆጣ ቆጣ ሲሉ የነበሩት አቶ ተፈራ ደርቤ ናቸው፡፡ ለዚህም እንደማስረጃ ያቀረቡልን
· 60 ሺ በላይ የገጠር ልማት ሰራተኞች እና የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች(በተቃዋሚዎች በትክክል ካድሬዎች ተብለው የተፈረጁት)፤
· ድህነትን በ1988 ከነበረበት 48 ከመቶ ወደ 24 ከመቶ ዝቅ ማድረጋቸው፤ (በመቶኛ ቀነሰ ቢባልም በቁጥር ግን በ1988 ከነበረው ጋር ተቀራራቢ ነው፡፡)
· መስኖ እና ሰፈራ በአርብቶ አደሩ አካባቢ ማስፋፋቱ፤
· 2.2 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በግል ባለሀብት እየለማ መሆኑ (ይህ መረጃ በቅርቡ እየተነገረ ቢሆንም ኢትዮጵያዊያን በዚህ መስክ የሚያደርጉት ተሳትፎ በግልፅ የሚታይ አይደለም)
· የመሰረተ ትምህርት እና ተግባር ተኮር የጎልማሶች ትምህርት መስፋፋቱ፤ ወዘተ ሲሆን
በዚህ መነሻ አርሶ አደሩ ሀብት እያከባተ በመሆኑ ወደ ማንፋክቸሪንግ ዘርፍ እንሚገባ አሰረድተውናል፡፡ አህአዴጎች በዛሬው ክርክር የቀደሞ ሰርዓት መክስስ ዘዴያቸውን የገቱ ቢሆንም ተቃዋሚዎችን ማጣጣል በተለይ መድረክ ላይ ለመዝመት ተዘጋጅተው እንደመጡ አቀራረባቸው ያሳብቅ ነበር፡፡ አቶ ተፈራ ደርቤ በተደጋጋሚ ተቃዋሚዎች ከላይ የተዘረዘሩትን የኢህአዴግ ሰኬት በመቃወም መሬት ይሸጥ ይለወጥ በማለት አርሶ አደሩን በማፈናቀል ለጥቂት ባለሀብቶ የቆሙ መሆናቸውን ያረጋገጡበት ክርክር ነበር፡፡ አቶ ተፈራ ደርበው ከመድረክ ጋር ተከራከሩ ተብለው መመሪያ እንደተሰጣቸው በሚያሳብቅ ሁኔታ መድረክን መሬት ይሽጥ? ነው የምትሉት ወይስ ሌላ አማራጭ አላችሁ? እያሉ በተደጋጋሚ አንስተውታል፡፡ አቶ ጥላሁን እንሻውም እንዳሻቸው መልሰውላቸዋል፡፡
ከኢህአዴጉ ተወካይ ዶክተር አብርሃም ተከስተ ያነሱት ሀሳብ ግን ወደ 1997 ክርክር መልሶኛል፡፡ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ አቶ አዲሱ “ግብርና ሴክተር የእድገት ፍንጭ” እያሳየ ነው ሲሉ ለሰጡት አሰተያየት “ከ14 ዓመት በኋላ ፍንጭ እየታየ ነው አትበሉን” በሚል የሰጣቸውን ምላሽ አሰታውሶኛል፤ በ2007 ክርክር ዶክተር አብርሃም ተከስተ የግብርና ፖሊሲው “የስራ አጥ ቁጥርን የመቀነስ አዝማሚያ” እያሳየ ነው ብለውን ከ24 ዓመት በኋላ አዝማሚያ ላይ እንደሆኑ ነግረውናል፡፡ በእኔ እምነት የግብርና ዘርፉ ይህን ሁሉ ጉልበት ይዞ መቀመጥ አይጠበቅበትም፡፡ በግብርና ዘርፍ ያለው ትርፍ ጉልበት ሊቀበል የሚችል ግብርና ያልሆነ ዘርፍ መፍጠር ያልቻለው ኢህአዴግ ሊከሰስበት የሚገባው ዋና ነጥብ ነው፡፡ ይህን ለማድረግ ደግሞ 24 ዓመት ያልበቃው ኢህአዴግ ምን ሲሰራ ነበር ተብሎ አይጠየቅም፡፡ ብዙዎቹ ሚኒሰትሮች ከሁለተኛ ደረጃ፣ የመጀመሪያ ዲግሪ እንዲሁም ድህረ ምረቃ ትምህርት ሲከታተሉ እንደነበር ይታወቃል፡፡ አንድ አንዶች ለሶሰተኛ ዲግሪ የሚሆን ጊዜ ነበራቸው፡፡ አበበ ገላው እየገዙ ነው የሚለውን ወደጎን እንተወው ከተባለ ማለት ነው፡፡ ፕሮፌሰር መስፍን ያሉትም ማሰታወስ ያሰፈልጋል “እነዚህ ሰዎች ሀገር እየመሩ/እያሰተዳደሩ ሶሰተኛ ዲግሪ መያዛቸው ወይ ሰራቸውን እየሰሩ አይለም፣ ካልሆነም ትምህርቱ ቀሎዋል ማለት ነው” አሰተያየት ሰምቻለሁ፡፡ ቃል በቃል ባይሆንም፡፡
ለማነኛውም ኢህአዴግ መነሻ ሀሳቡንም፣ ማብራሪያውንም ማጠቃለያውን “በሚመጥነው” ደረጃ አቅርቦ ክርክሩን አጠናቆዋል፡፡ ከዚህ የጠነከረ ክርክር ቢያቀርብ ማን ከቁብ ሊቆጥርለት ነው፡፡ በእኔ ግምት ዶክተር አብርሃም ተከስተ በዚህ ክርክር ላይ ባልመጣው ሳይል የሚቀር አይመስለኝም፡፡ ጠንከር ያለ ቁጥርና ቁጥር ነክ ጥያቄዎች በተለይ ደግሞ የመዋቅራዊ ሽግግር ጥያቄዎች እና ማክሮ ኤኮኖሚክ ነክ የሆኑ ለምሳሌ በውጭ ምንዛሪ ግኝት፣ በግብርና ሴክተር የመሪነት ሚና ላይ ዝርዝር ሀሳቦች ለመመለስ በክርክሩ ላይ የተገኘ ይመስል ነበር፡፡ ዶክተር አብርሃም ተከስተ የክርክር ጊዜውን ለመግደል ዘና ብሎ ሲመልስ ላስተዋለ በእግር ኳስ ጫወታ እየመራ ያለ ቡድን ጎል ጠባቂ ጊዜ ሲያባክን የሚያሳየውን ባህሪ የሚያሰታውስ ነው፡፡
ለማነኛውም አቶ ተፈራ ደርቤ ያቀረቡት የመሬት ጉዳይ በህገ መንግሰት ውስጥ መግባቱ እና አሁን የሚከተሉት የመሬት ፖሊሲ መሰረቱ ኤኮኖሚያዊ ነው ብለው ቢዋሹም፣ ኢህአዴግ መሰረቴ ነው የሚለውን አርሶ አደር ለመቆጣጠር እንዲችል የተቀመጠ ፖለቲካዊ መሰረትነቱ መቼም ክዶት የማያወቅው ታውቆ ያደረ ጉዳይ መሆኑን የሚያስታውሳቸው አላገኙም፡፡ የዶክተር አብርሃም ተከሰተ ትህትና የተሞላበት የምረጡን ጥያቄም አማላይ ነበር፡፡
ኢህአዴግ በአቶ ግርማይ አደራ በሚባሉ ሰው የተወከለ ሲሆን በረዳትነት የተገኘውን ለማወቅ እድል አላገኘንም፡፡ አቶ ግርማይ ጊዜው አይበቃም ቢሉም ሲጀምሩ ቀስ ብለው ተዝናንተው ሲጨርሱም ሁለት ደቂቃ አሰቀርተው ሲያጣቃልሉም ለጊዜ አጠቃቀም ምንም ግድ ሳይሰጣቸው ነው፡፡ እውነቱን ለመናገር ከእኝ ግለሰብ ልይዝላቸው የቻልኩት ነጥብ መሬት ለኢትዮጵያን የዜግነት፣ የሀገር ባለቤትነት፣ የነፃነት መገለጫ ነው የሚሉት እና የማዳበሪያ ዕዳ ለመክፈል አዲስ አባባ ለልመና የሚመጡ አርሶ አደሮች መኖራቸውን ያስታወሱን መሆኑን ነው፡፡ አንድ የፖለቲካ ፓርቲ መሪ በፅሁፍ የያዘውን በቅጡ የማያነብ፣ በቂ አይደለም ብሎ ካለው ጊዜ ውስጥ በመግቢያና በመውጫ ሠዓት ማባከን ምን ግምት እንደሚያሰጥ ተከራካሪው ያሰቡበት አይመስለም፡፡ ለማነኛውም ኢህአዴግ አቻውን አግኝቶዋል ማለት ይቻላል፡፡ በቃ ኢህአዴግ የሚመጥነው እንደ አቶ ግርማይ አደራ ያሉ ፖለቲከኞች ናቸው፡፡ ምርጫቸው ነው እና ማክበር አለብን፡፡ አቶ ግርማይ አርማው ጋሻና ጦር የሆነ እድር ቢኖራቸው ችግር የለኝም ነገር ግን እርሳቸውም ሆነ የእርሳቸው ፓርቲ በሚሰጡት አመራር በማጠቃለያ እንደነገሩን በምግብ እህል ራሷን የቻለች ኢትዮጵጰያ ሊዚያውም ተርፎዋት ኤክስፖርት የምታደርግ ሀገር አይሰሩልንም፡፡ ለኢትዮጵያዊ የቀረበለት ከዝንጀሮ ቆንጆ መረጣ ነው፡፡
“ድንኩ አንድነት” እንደ ተለመደው በትዕግስቱ አወሉ የተወከለ ሲሆን በረዳትነት የተመደበለት ደግሞ አቶ ዮሐንስ አሰፋ ነው፡፡ አቶ ትዕግሰቱ በቴሌቪዥን በክርክር የሰንብት ክርክሩን አድርጎ ሄዶዋል፡፡ እኛም ተገላገልን፡፡ ባለፈው ድንኩ አንድነት የአንድነት ፓርቲ ውስጥ አባል ያልሆነ ሰው ለክርክር ቀረበ ብለን ትንሽ ተንጫጭተን ነበር፡፡ ዛሬ ደግሞ በረዳትነት የመጣው አቶ ዮሃንስ አሰፋው ለጫጫታ መነሻ የሚሆን አወዛጋቢ ግለሰብ ነው፡፡ ዮሐንስ በወረዳ 24 ውስጥ፣ ገዢውን ፓርቲ ወክሎ ወረዳውን ሲያምሰ የነበረ ነው፡፡ የሴራው ማጠንጠኛም አስራት አብርሃም ነበር፡፡ ፓርቲው አምኖበት በከፍተኛ ሃላፊነት ላይ ያስቀመጠውን ሰው የወያኔ ተላላኪ ነው እያለ ውንጀላ ሲያደርግ፣ በአስራት አብርሃም ደረጃ አሰተዋጽኦ የሚያደርግ ከየትም ቢመጣ ችግር እንደሌለብን አሰርደቼው ነበር፡፡ ለነገሩ ፓርቲውን ለመፍረስ ከሚያሴሩት ጋር በግልፅ እንደሚሰራ እያወቅን በዝምታ ያለፍነው የውስጥ አርበኛ ነው፡፡ አሁን ደግሞ በአሰራት አብርሃም ቦታ ወረዳ 24 ዕጩ ሆኖ የቀረበ ሲሆን ለትዕግሱቱ አወሉ ቡድን በቂ አማካሪ ሆኖ አግኝቼዋለሁ፡፡ ከዚህ የተሻለ ከትዕግሱቱ ጎን ማግኘት አጉል ነው የሚሆነው፡፡ ትዕግስቱም የልኩን አማካሪ ኢህአዴግም የሚመጥነውን ተቃዋሚ አግኝተዋል፡፡
ትዕግሰቱ የአንድነትን የፖሊሲ አማራጭም ሆነ ዝርዝር የኢህአዴግን የአፈፃፀም ክፍተት በተሟላ ይዞ ሊቀርብ እንደማይችል ማንም ያውቃል፡፡ በድፍረት ግን “የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ በአሰቸጋሪ ሁኔታም ቢሆን አንድነትን ምረጡ” የሚል ቃል እንዴት ሊወጣው እንደቻለ አልገባኝም፡፡ ከሁሉም ያስገረመኝ ደግሞ “ኢህአዴግ የመሬት ፖሊሲ የምቀይረው በመቃብሬ ላይ ነው” ይላል በሚል የሰጠው አስተያየት ነው፡፡ ኢህአዴግ ለስልጣኑ ዋልታና ማገር ያደረገውን የመሬት ፖሊሲ በመቃብሬ አለ የሚለው ትዕግሰቱ አወሉ እልህ ምላጭ ያስውጣል በሚል መፈክር ከራሱ ሌላ አንድ ሌላ ድምፅ ለማግኘት ያልቻለበትን አንድነት ፓርቲን ከምርጫ ቦርድ እና ከገዢው ፓርቲ ጋር እርሱ በሚያውቀው መስመር ተመሳጥሮ ድንክ ያደረገ ግለሰብ፣ ታንክና ባንክ ለማዘዝ የሚያሰችል ስልጣን የሚያስገኝን የመሬት ፖሊሲ በመቃብሬ ላይ ቢባል ምን እንደሚያስገርም አልገባኝም፡፡ ትዕግሰቱ አወሉ ታንክና ባንክ የሚያዝ መንግስት ቢሆን ብዬ ሳሰበው ዘገነነኝ፡፡
አቶ ትዕግሰቱ አወለ በክርክሮች ሁሉ ቀና ብሎ የቴሌቪዥን ካሜራ ለማየት ማፈሩ ተገቢ ሆኖ ባገኘውም የሚያፍር ከሆነ ለምን ቴሌቪዥን ላይ እንደሚመጣ ነው የማይገባኝ፡፡ አንድነት አማራጭ እንዳለው ሰንድ ማሳየት ይቻላል ያለው ትዕግሰቱ የአንድነትን ፕሮግራመ በቅጡ ማንበብና መዘጋጀት ሳይችል (የምርጫ ማኒፌስቶ እርሱ ሊያገኘው አይችልም፣ ቢሮ ዕቃ በጉልበት ሲዘርፍ በአባላት ጭንቅላት የሚገኝ እውቀት ግን በእርሱ እጅ አልገባም) የዛሬ አምስት ዓመት የተዘጋጀውን ሰትራቴጂክ ዕቅድ ላይ ለዚያውም በመግቢያ ላይ የተፃፈውን ሰለ ዜጎች ሰደት የሚያወራውን ክፍል ለግብርና ክርክር ይዞ ሲቀርብ፣ “የድንኩ አንድነት” ተወካይ መሪ አቶ ትዕግሰቱ ለመዘጋጀት ፈተና የሆነበት ምን ያህል የውስጥ ሰላም አጥቶ እንደሚገኝ የሚያሳይ ነው፡፡ አንድነት በየትም ቦታ ዜጎች ወደ ከተማ መምጣት ችግር ነው ብሎ አያውቅም፡፡ ይልቁንም ችግር ከሆነ እንደ ችግር የሚያየው ዜጎች ከመሬት ጋር ተጣብቀው በገጠር እንዲኖሩ መደረጋቸወ ነው፡፡
ሌላው ያስገረመኝ የጥርሶቹ ማለቅ ሲሆን (መለስ መላጣ ማለት ይቻላል፣ መንካት ግን አይቻልም ባለው መሰረት)፣ እንዴት ነው አሁን ያለው የገንዘብ ፍሰት ለዚህ የሚሆን እንጥፍጣፊ የለውም ወይ? የሚል ጥያቄ ጭሮብኛል፡፡ ከዚህ በፊት ጥርሳቸውን ያስተከሉ መሪዎች በፓርቲው ገንዘብ ነው እያለ እርሱ ሲያወራ ስለነበር ነው፡፡ ለማነኛውም “ሞያ በልብ ነው አንድነትን ምረጡ” ያለው ትዕግሰቱ በግሌ የወረዳ 8 ነዋሪ ከራሱ በስተቀር አንድም ድምፅ እንዳያገኝ በማድረግ እንዲያዋርደው በማክበር ጥሪ አቀርባለሁ፡፡ በሰፈሩ ያሉት እድሮችና የትዕግሱ የማሪያም ፅዋ ማህበርም ይህን እንዲያስተባብሩ እና ትዕግሰቱ ከራሱ በስተቀር አንድም ድምፅ እንዳያገኝ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህን የኢህአዴግ ኮካዎች ማህበራዊ ማግለል ወንጀል ነው ይሉታል፡፡ በትዕግስቱ ላይ ማህበራዊ ማግለል ወንጀል የሚሆንበት ህግ ካለ ለመማር ዝግጁ ነኝ፡፡ መቼም ትዕግሰቱን በመወከል ታዛቢ ይኖራል ብዬም አላምንም፡፡ በተጨማሪ የአንድነት ደጋፊዎችም ትዕግሰቱ ከራሱ ሌላ አንድም ሌላ ድምፅ እንዳያገኝ ጠንክረው መስራት ይኖርባቸኋል፡፡ ይህን ሳናደርግ ብንቀር ሌሎች ትዕግሰቱዎች ለዚህች ሀገር እየጋበዝን መሆኑን መዘንጋት የለብንም፡፡ አንድነት ዋንጫ የሚያነሳው ትዕግሰቱና የትዕግሰቱ ቡድን ድምፅ ሲያገኝ ሳይሆን እነርሱ ተገቢውን ውርደት ሲከናነቡ ነው፡፡
ኢድአን አቶ ግዑሽ ገ/ሥለሴ እና ትዕግስቱ ዱባለ በተባሉ አባላቱ ተወክሎ ነበር፡፡ በነገራችን ላይ አቶ ግዑሽ ገ/ሰላሴ በ2002 ምርጫ ወቅት መድረክ ሞቅ ያለ የምርጫ ስራ ላይ እያለ “ኢድአን ከምርጫ ወጥቶዋል” በሚል መድረክን ያመሱ ግለሰብ ናቸው፡፡ በምርጫ ወቅት የገዢው ፓርቲ ተቃዋሚዎችን የሚያዳክምበት መሳሪያ ናቸው፡፡ ከምርጫ በኋላ እዚህ ግባ በሚባል ፖለቲካ ውስጥ ጉልዕ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ አይታዩም፡፡ አቶ ግዑሽ ካቀረቡት ክርክር ነጥብ አድርጌ የያዝኩላቸው “ … እሰከ መገንጠል መብት የሰጠ መንግሰት፣ ለአርሶ አደሩ መሬትን እሰከ መሸጥ ለምን መስጠት ፈራ” የሚለው ነው፡፡ የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች መብት እሰከ መገንጠል ስለተሰጠ የተገነጠለ የለም በሚል የሚከራከረው ኢህአዴግ አርሶ አደሩ እሰከ መሸጥ የሚደርስ መብት ቢያገኝ በመሬቱ ተጠቃሚ ከሆነ አይሸጠውም የሚል መርዕ እንዴት ሊገባው አልቻለም የሚል ነው፡፡ ተዋዋሚዎች ትንሽ ከሚሏት የክርክር ደቂቃ ሁለት ደቂቃ ያገኘው የአቶ ግዑሽ ረዳት አቶ ትዕግሰቱ ዱባለ ያገኛትን ሁለት ደቂቃ በቅጡ የሚረባ ነገር ሳይናገር ላብ በላብ ሆኖ ወጥቶዋል፡፡ ከእንቅልፉ ድባብ ተቀስቅሶ በመናገሩ የተቸገረ ነው የሚመስለው፡፡ ኢህአዴግ የመጨሻውን ማጠቃለያ መስጠቱን ዘንግቶ ለኢህአዴግ ጥያቄም አቅርቧል፡፡ ለማነኛውም በማጭድ ምልክት ዘመናዊ የግብርና መሳሪያ በድጎማ ማቅረብ አማራጭ አድርጎ ያቀረበልን ኢድአን ከቁም ነገር የሚቆጠር አማራጭ ነው ብለን ልንወሰደው እንቸገራለን፡፡ እንኳን ሌሎች እንዲመርጧቸው ልንደግፋቸው አይደለም የራሳቸው “ከተመረጥን” የሚለው ድምፅ ለመመረጥ እንዳልተዘጋጁ የሚያሳጣ ነው፡፡
መድረክ ተወክሎ የገባው በአቶ ጥላሁን እንዳሻው እና በአቶ ሙላቱ ገመቹ በሚባሉ አባላት ሲሆን፡፡ ኢህአዴግም ቢሆን በዋነኝነት ሊከራከረው የገባው ከላይ እንደገለፅኩት ከመድረክ ጋር ብቻ እንደሆነ ያስታውቅ ነበር፡፡ መድረክ በመጀመሪያ ሰድስት ደቂቃ አንዱን ደቂቃ ጊዜው ትንሽ ነው በሚል ጉንጭ አልፋ ክርክር ጊዜ ያባከነ ሲሆን፤ በተጨማሪ መልስ በሌላቸው ህገመንግሰታዊ ድንጋጌዎችና ትርጉም ጊዜውን እንዳባከኑት ይሰማኛል፡፡ በእኔ ግምት በመሃል የተቆረጠ በሚመስል ሁኔታ አምሰት ደቂቃ የሚሞላ ሀሳብ አልሰማንም፡፡ ኢቲቪ ኢህአዴግን የመከላከል መብቱን ተጠቅሞ የቆረጠው ሃሳብ እንዳለ መገመት ይቻላል፡፡ መድረክ በቀጣዩ በነበረውን ዘጠኝ ደቂቃም ቢሆን ኢህአዴግ ላቀረበለት ጥያቄ መልስ በመስጠት፣ ለምሳሌ በሚል የአቶ ጥላሁን እንዳሻው ትውልድ አቅራቢያ ቦታዎች ላይ የሚገኙ የመሬት መፈናቀልና የመሰረተ ልማት እጥረትን በመዘርዘር ለክርክሩ የሚመጥን ነበር ለማለት የሚያስቸገር ሃሳብ ሲያቀርቡ ነበር፡፡ በ2002 አቶ ጥላሁን እንዳሻው በተመሳሳይ ርዕስ ተከራካሪ የነበሩ ሲሆን ይህን ልምድ ይዘው በተሻለ የመቅረብ እድሉ ቢኖራቸውም ሊጠቀሙበት አልቻሉም፡፡ ከመድረክ ክርክር ነጥብ የሚወሰድ ከሆነ በልማት ሰራተኛ ስም የተሰገሰጉት ካድሬዎች ጉዳይ ሲሆን ኢህአዴጎች ይህን ከሰራተኞቹ ጋር ለማጋጨት ሊጠቀሙበት የሞከሩ ቢሆንም በልማት ሰራተኛ ሰም በገጠር የሚንከራተቱት ሰራተኞች ይህን ተጨማሪ ያለፍላጎታቸው የሚሰጣቸው ሰራ እንደማይወዱት ለሚያውቅ የኢህአዴግ መንገድ የሚሳካ አይመስለኝም፡፡ በክርክሩ የመጨረሻ ተከራካሪ መሆን ያለውን ከፍተኛ የማጥቃት እድል በማያሰፈልግ ሁኔታ ከረዳታቸው ጋር የተካፈሉት አቶ ጥላሁን ረዳታቸውም ምንም አዲስ ነገር ሳይነግሩን ክርክሩም እንዲያበቃ አደርገውታል፡፡
በእኔ እምነት ኢህአዴግ አሁንም ቢሆን መንግሰት ሆኖ ያከናወናቸውን ስራዎች ይህን ማድረግ የማይችሉትን ተቃዋሚዎች መክሰሻ አድርጎ ለማቅረብ ሲሞክር ከመስማት የበለጠ አሳፋሪ ነገር የለም፡፡ ይህ ማለት ግን ተቃዋሚዎች በያዘው ስልጣን ሊያከናውን ያልቻለውን፣ በተለይ ደግሞ ባለፈው አምስት ዓመት በግብርና ዘርፍ አሳካዋለሁ ብሎ ያላሳካቸውን ነጥቦች አንሰተው ደካማ መሆኑን ማሳየት አይችሉም ማለት አይደለም፡፡ ኢህአዴግ አሁን የሚሞግተን የግብርና ፖሊሲና ስትራቴጂ፤
· ባለፉት 24 ዓመታት ይህችን ሀገር በምግብ እራሷን እንድትችል ባለማድረጉ የሚከሰሰበት ዋነኛ ነጥብ ነው፡፡ በሃያ አራት ዓመት አሁንም አዝማሚየ በሚባል ሁኔታ መሆናችን ተቀባይነት የለውም፤
· በኢትዮጵያ ሀገራችን በገጠር የሚኖረው ህዝብ ባለፉት 24 ዓመታት ከነበረበት 85 ከመቶ ወደ 83 በመቶ ብቻ ነው ዝቅ ሊል የቻለው፡፡ ይህ ደግሞ በአፍሪካ ደረጃ ከተሜነት 50 ከመቶ በላይ በደረሰበት ወቅት እጅግ አሳፋሪ ሲሆን፤ ይህን እንደ ነጥብ አንሰቶ የሚሞግት ያለመኖሩ ከዚያ ይልቅ የገጠሩ ህዝብ ወደ ከተማ እየፈለሰ ነው የሚል ቅሬታ የሚያሰሙ ተቃዋሚዎች መኖራቸው የሚያሳዝን ነው፤
· የከተሜነት ያለመስፋፋት፣ ዜጎች በገጠር ከመሬት ጋር ተጣብቀው እንዲኖሩ እያደረገ ያለው ደግሞ፤ ኢህአዴግ በውሸት ኤኮኖሚያዊ ምክንያት የሚለው ነገር ግን ፖለቲካው ምክንያት የሆነው መሬትን ህገመንግሰት ውስጥ መደንቀሩ ነው፤ ይህን ፖለቲካዊ የሆነ ጉዳይ ኤኮኖሚያዊ ነው ብለው ምንአልባት ከፓርቲው አቋም ውጭ የግብርና ሚኒሰትሩ ሃሳብ ሲሰነዝሩ የሚሞግታቸው አላገኙም፤
· ኢህአዴግ መሬት መሸጥ መለወጥ የሚለውን ሃሳብ ሲያነሳ መሬት የሚገዙ ጥቂት የሚላቸው ዜጎች መሬቱን የሚገዙት ምርት ለማምረትና ለማትረፍ በዚህም ሀገራችንን በምግብ እህል ራሰን ከመቻል አልፎ ኤክሰፖርት ለማድረግ መሆኑ ቀርቶ ለቀብራቸው መሬት የሚገዙ ያሰመስለዋል፡፡ መሬቱን ሸጦ የሚፈናቀል አርሶ አደር ደግሞ በሌሎች አገልግሎት ዘርፍ የማይገባ፣ ከመሬት ጋር ብቻ ተጣብቆ እንዲኖር የተፈረደበት ያሰመስልብናል፡፡
ባጠቃላይ በእኔ እምነት የ1997 የግብር እና የገጠር ልማት ስትራቴጂ ክርክር በድጋሚ ይቅረብልን ብዬ ማጠቃለል መርጫለሁ!!!
ባጠቃላይ በእኔ እምነት የ1997 የግብር እና የገጠር ልማት ስትራቴጂ ክርክር በድጋሚ ይቅረብልን ብዬ ማጠቃለል መርጫለሁ!!!
ቸር ይግጠመን!!!!!!!
/“የትግራይ ተወላጆች ታጥቀናል” ሲለኝ – ደነገጥኩ

“የትግራይ ተወላጆች ታጥቀናል ሲለኝ – ደነገጥኩ” የሚል አስተያየት የሰጠው ኳስ አፍቃሪ ከጎልጉል የአዲስ አበባ ወኪል ጋር የተገናኘው አዲስ አበባ ስታዲየም ነበር። ጉዳዩ ለሚዲያ ግብዓት እንደሚውል ባይረዳም ገጠመኙን ለመናገር የተገደደው ስለ ምርጫ አንስተው ሲወያዩ ነው። ድንገት ተገናኝተው ቆሎ በመገባበዝ የጀመሩት ጨዋታ ዘጋቢውን ወደ 1997 ምርጫ ትዝታ ወረወረው። ተግባብተው አወጉና ተለያዩ። የትግራይ ተወላጆች ታጥቀናል!! ለምን? መርዝ ዘርቶ በጥይት ለማጨድ?
የስታዲየሙ ሰው የመኪና ማስጌጫ ለመግዛትና ለማስገጠም ሰባራ ባቡር እንደሄደ ይናገራል። እዛም እንደ ደረሰ የሚፈልገውን ገዝቶ እያስገጠመ ሳለ አንድ ጎረምሳ ቢጤ ይጠጋቸውና ወሬ ይጀምራል። ጎረምሳው የትግራይ ተወላጅ ነው። አንዳንድ ማስጌጫዎች የሚፈልግ ከሆነ እሱ ዘንድ በርካሽ እንደሚያገኝ እየነገረው ቃላት መለዋወጥ ጀመሩ። በዛው የተጀመረው ጨዋታ ስር እየሰደደ ሄደና ስለምርጫ ማውጋት ጀመሩ።
“ተቃዋሚዎች የትግራይ ህዝብን የመበቀል አጀንዳ እንጂ ሌላ ምንም ዓላማ የላቸውም። ያስጠሉኛል። ልማት አይወዱም። ከዚህ በላይ ምን እንዲደረግ ይፈልጋሉ? የትግራይ ህዝብ ነጻ አወጣቸው …” ወዘተ እንደ ሰውየው ገለጻ ጎረምሳው ብዙ ተናግሯል። በመሃሉ “አንተ ትፈራለህ እንዴ? እኔ ለምሳሌ ካንተ ጋር በፍቅር እያወራሁ ነው” ሲል ሰውየው በመካከል ጥያቄ አነሳበት። ጎረምሳው እየሳቀ ማብራሪያ ሲሰጥ ድንገት የ1997ቱን ምርጫ አነሳና ቤተሰቦቹና ታላላቅ የአገሩ ተወላጆች የነገሩትን አወሳ።
“ከ1997ቱ ምርጫ በኋላ ያልታጠቅነው ሁሉ ታጥቀናል” አለ። እሱ መሳሪያ እንዳለው ሰውየው ጠየቀው? “አዎ!! ምን ችግር አለው ጠይቀህ መውሰድ ትችላለህ” ሲል እንዴትና ከነማን መሳሪያ እንደሚወስድ ተናገረ። “መሳሪያው ምን ያደርግልሃል? ምን ልታደርግበት” ሰውየው እየሳቀ “አሁን እኔን ትገለኛለህ” ሲል ጠየቀው።
ጎረምሳው ብዙ ብዙ ተናገረ። ከተለያዩ በኋላ ሰውየው ድንጋጤ ውስጥ ስለወደቀ የሰማውን ለማሰላሰል አንድ ጥግ ይዞ ተቀመጠ። “ምን እየሆነ ነው?” ሲል አሰበ። የትግራይ ተወላጆችን ለይቶ ማስታጠቅ፣ ጠላት እንዳላቸው በስውር በማስተማር ማደራጀት፣ ከመደበኛ ስራቸው ውጪም ቢሆን ባልደረቦቻቸውን እንዲሰልሉና ተጠራጣሪ ሆነው እንዲኖሩ ማድረግ፣ በቀልን እያሰቡ ውለው በቀልን እያሰቡ እንዲተኙ ማድረግ፣ ከትልቅ እስከ ትንሽ ያሉት ሁሉ ቂምና በቀል እየጋቱ ሌሎች ህዝቦች ሁሉ የትግራይ ህዝብ ጠላትና ቀን ጠባቂ እንደሆኑ በመሳመን የጥይት ስንቅ ማስያዝ … ለምን? ለምን? እስከመቼ? እንዲህና እንዲያ እያሰበ ተምታቶበት እንደከረመ ለጎልጉል ዘጋቢው አወጋው።
በ1997 ቅድመ ምርጫ የመጨረሻ ሰላማዊ ሰልፍ ወቅት የቅንጅት ሱናሚ አዲስ አበባን የዋጣት ዕለት፣ ሱናሚው አዲስ አበባን አጥለቅልቆ ኢህአዴግን በተለይም ህወሃትን ጣር ውስጥ በከተተበት ወቅት ምንም ነገር ማድረግ ይቻል ነበር። ቤተ መንግስት ገብቶ ሁሉንም የጨዋታ ህጎች መደፍጠጥ ይቻል ነበር። የጎጥም ይሁን የጎሳ ችግር የበቀል አራራ ቢኖር ኖሮ ከዚያን ጊዜ በላይ አመቺ ወቅት አልነበረም። ባድሜ ስትወረር የተመመው የኢትዮጵያ ህዝብ፣ ደጀን የነበረው የኢትዮጵያ ህዝብ ጉዳዩ የትግራይና የተወላጆቿ ነው ብሎ አልተቀመጠም። ፈንጂ ላይ እየሮጠ፣ ፈንጂ ላይ “እናት አገር ወይም ሞት” በማለት እየደነሰ ያለቀው ይህ ትውልድ በእውነት ቂመኛ ነው? የዘጋቢው ጥያቄ ነው!!
በርግጥ የኢትዮጵያ ህዝብ ኢህአዴግ ላይ ቢያቄምስ ይፈረድበታል? ይኮነናል? ሃጢአት ተደርጎ ይወሰድበታል? በሰላም ከሚኖርበት ቀዬ የሚፈናቀል ህዝብ ቢያቄም ኩነኔ ነው? “ከክልላችን ውጣ” ተብሎ ደብዳቤ የተጻፈለት የ1ኛ ክፍል ተማሪ ቂም አርግዞ ቂምን ቢገላገላት ይወቀሳል? በዘሩ ምክንያት በደል የሚፈጸምነት ህዝብ ግፍ በዝቶበት “ቢያስታውከው” በተነፈሱ ቁጥር “አሸባሪ” እየተባሉ እስር ቤት የሚጣሉ ወገኖች በቂም ቢመረቅዙ እንዴት “ተው” ይባላሉ? የአገሪቱን ሃብት ውስን ሰዎችና ድርጅታቸው ሲቀራመቱት በገሃድ እየታየ ሰዎች እልህ ቢጋቡ፣ ጸሎት/ዱዓ ለማድረግና ቤተ እምነትን በነጻነት ማቆም ሲከለከል ዝም ማለት ይቻላል? ጥቂቶች ህንጻ እየገነቡ ሲንፈላሰሱ ቀልባቸው የሚቆጣባቸውን “ልክ አይደላችሁም” ማለት ማን ይቻለዋል? … ዘጋቢውና ሰውየው ካነሷቸው ጥያቄዎች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው።
ፕ/ር መስፍን ወልደ-ማርያም “የወያኔ የጥላቻ ፍሬ” በሚል ርዕስ የዛሬ ዓመት አካባቢ ባወጡት ጽሁፍ ላይ እንደጠቆሙት ግፍ ማብቂያ አለው፡- “ወያኔ ከሀያ ዓመታት በላይ አፍንጫ እየያዘ ያስከፈለውን የሚመልስበት ጊዜ እየተቃረበ ነው፤ ጥያቄው ወያኔ እንዲመልስ የሚገደደው እንዴት ነው? የሚል ነው፤ ጥላቻ ወደ ንዴት፣ ንዴት ወደ ቁጣ ተለውጦ ሲገነፍል ምጽዓት ደረሰ ማለት ነው፤ ሁሉም ሰው ራቁቱን ይሆናል፤ አንደአውሬ ከጥፍሩና ከጥርሱ በቀር ሌላ መሣሪያ አይኖረውም፤ ሰው ሁሉ በክፋት ወደ አውሬነት ይለወጣል፤ ጠመንጃና ቦምብ አያገለግሉም፤ ሕንጻው ምሽግ አይሆንም፤ መኪናው፣ ባቡሩ፣ ታንኩ ከቆመበት አይነቃነቅም፤ የትም አያደርስም፤ ጭፍራ ሁሉ በየራሱ ፍዳ ታንቆ እንኳን ለሌላ ሊተርፍ ለራሱም የማይበቃ ይሆናል፤ ለነገሩ ጌታና ሎሌም የለም፤ ሁሉም በአውሬ እኩልነት የተፋጠጠ ነው፤ ርኅራኄ ተሟጦ፣ መግል ያዘለ ልብ ፈርጦ፣ ውይይትና ክርክር አብቅቶ፣ ጥርሱን ያገጠጠና ጥፍሩን የሳለ መንጋ በደም የሚራጭበት ሁኔታ ነው።”
ስለዚህ አካሄድን በማሳመርና ሚዛን የጠበቀ አስተዳደር በማስፈን አገዛዝን ወደ ህዝባዊ መንግሥት በመቀየር ወግ ነው። ተስማምቶ መኖር እየተቻለ ወገን እየለዩ ማስታጠቅና ባምስትና በአስር ሰዎች የተመደበ የቀድሞ መከላከል፣ የቀድሞ ማጥቃት፣ ካልተቻለም የሚቻለውን አድርጎ የሚሆነውን ማየት በሚል እሳቤ መንጎድ የትኛውንም ወገን እንደማይጠቅም መረዳት ግድ ይላል። በተለያዩ ወቅቶች አስተያየት የሰጡ እንደሚሉት ህወሃት እንዲህ ካለው አጉል አካሄድ ራሱን በማረቅ ብቸኛ አማራጭ ወደ ሆነው እርቅ ፊቱን እንዲያዞር የሚመለከታቸው ሁሉ ሊያሳስቡት ይገባል።
ኢህአዴግ ዙሪያ ያሉ ድቃይ ድርጅቶችም በዚህ ጉዳይ ላይ በወጉ ሊመክሩና ከወዲሁ የሚበጀውን መንገድ በመከተል ቂምና ምሱን ለማክሰም መንቀሳቀስ እንደሚገባቸው ብዙዎች ይመክራሉ። ለህሊና ዋጋ በመስጠት የመርዝ እርሻን ማክሰም የጊዜው የከረመ ጥያቄ ነውና ሁሉም ልብ ሊሉት እንደሚገባ በተደጋጋሚ መዘገቡም አይዘነጋም። መርዝ እየዘሩ በጥይት አጭዶ ለመከመር መደራጀት ሌላውን ከሚያስፈራው ይልቅ የበደሉንና የቂሙን ቁስል ይበልጥ የሚያመረቅዝ ይሆናልና ህወሃት ልብ ሊገዛ እንደሚገባ የሚመክሩ ጥቂት አይደሉም። ህወሃት “ንፋስ ዘርቶ አውሎ ነፋስ አላጭድም” ማለት አይችልም – ቀን ጎዶሎ ነውና!
ፓትርያርኩ በሕግ አፍራሽነታቸው ጸኑ

በአ/አበባ ሀ/ስብከት ሥራ አስኪያጅ ምርጫ ከረዳት ሊቀ ጳጳሱ ጋራ እንዲግባቡ የተደረገው ጥረት አልተሳካም
- መመሪያቸው በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ኹለንተናዊ እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚኖረው ጠቅላይ ጽ/ቤቱ በዛሬው የቋሚ ሲኖዶሱ ስብሰባ ያቀረበውን ስጋት አጣጥለውታል
- በአ/አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች ምርጫ እና ሥያሜ የፓትርያርኩን የአካሔድ ስሕተት ከማረም አንጻር የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ውሳኔ እና መመሪያ እንደሚሰጥበት ይጠበቃል
በሥራ አስኪያጅ ምርጫ እና ሥያሜ አለመግባባቱ አጋጣሚ፣ ፓትርያርኩ፡-
- ረዳት ሊቀ ጳጳስ መርጦ ከማቅረብ ድርሻቸው በላይ በቅዱስ ሲኖዶሱ የሚወሰነው የመመደቡም ጉዳይ ከእርሳቸው ሓላፊነት ጋራ እንደሚያያዝ በመመሪያቸው ከመጥቀስ አልፎ፣ ‹‹እኔ[ሥራ አስኪያጅ] መድቤአለኹ፤ ሾሜአለኹ፤ የሚሠሩ ከኾነ ተስማምተው ይሥሩ›› በማለት የረዳት ሊቀ ጳጳሱን ሚና ፋይዳ ቢስ ማድረጋቸው፤
- በብፁዕ ዋና ጸሐፊው የሚመራው የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት፣ የቋሚ ሲኖዶሱንመነጋገርያ ርእሰ ጉዳይ አዘጋጅቶ ለውይይት የማቅረብ ተግባሩ መሠረት፣ በትላንትናው ዕለት በአድራሻ የተጻፈለት የረዳት ሊቀ ጳጳሱ ጥያቄ በአጀንዳነት ተይዞ እንዲታይ ሲጠይቅ፣ ጉዳዩን ለውይይት ዝግ ከማድረግ አልፎ ብፁዕ ዋና ጸሐፊውን በአሳዳሚነት መውቀሳቸው፤
እንደ ቅዱስ ፓትርያርክ መጠን፣ ሕጉን ተገንዝቦ እና ጠብቆ ለቤተ ክርስቲያን ከአድልዎ የጸዳ አጠቃላይ አባታዊ አመራር በመስጠት ረገድያለባቸውን የታማኝነት ውስንነትና የአማሳኝ አማካሪዎቻቸውን በተለይም በተደጋጋሚ ሲጋለጥ የቆየውን የልዩ ጸሐፊአቸውን ተንኰል እና ክፋት በገሃድ ያረጋገጠኾኖ አልፏል፡፡
Sunday, March 29, 2015
ኢትዮጵያዊቷ የISIS ሙሽራ እና “ጽንፈኛ” ሆነው የተገኙት አባቷ

መፈክር ብቻ ሳይሆን የአሜሪካንና እስራኤል ባንዲራ ሲቃጠል አቶ አባስ አጃቢ ናቸው። ልጃቸው ወደ ሶርያ ለመግባት በቱርክ በኩል ስታቋርጥ በካሜራ እይታ ውስጥ ከገባችና ሁኔታው በእንግሊዝ መንግስት በገሊ ከተነገረ በኋላ አቶ አባስ የእንግሊዝን ፖሊስ ተጠያቂ ማድረጋቸው ይታወሳል። በወቅቱ በብሪታኒያ ፖሊስ ማዕከል ስኮትላንድ ያርድ ቃለምልልስ ሲሰጡ ልጃቸው ስለአክራሪነት ፈጽሞ የምታውቅበት መንገድ ይፈጠራል ብለው እንደማያምኑ ሳግ እየተናነቃቸው ሲናገሩ ሰምተናል።
ነገር ግን አሁን ቀስቱ ወድሳቸው ዞሯል። ከ3 ዓመታት (2012) በፊት የዛሬን ጦስ ሳያስቡት እንግሊዝን ባስበረገገው የጽንፈኞች ሰልፍ ላይ ተዋናይ መሆናቸው በቀላሉ የማይታይ፣ ለልጃቸው የISIS ነፍሰ ገዳይ ለመሞሸር ድንበር ማቋረጧ በቀጥታ ተጠያቂ መሆናቸው አይቀሬ ነው። አሜሪካንም ሆነች እንግሊዝ ጉዳዩን በቀላሉ አያዩትም። ለዚህ ምክንያቴ አቶ አባስ:–
1. የአሜሪካኑን 911 እና የእንግሊዙን 7 July 2005 የሽብርተኞች ጥቃትን በአደባባይ የደገፈው ብሪታኒያዊው አካራሪ፣ አክቲቪስትና የሙስሊም ማህበረሰብ ጠበቃዎች ሊቀመንበር አንጀም ቾዳሪ የመራው ሰልፍ ላይ መገኘታቸው
2. በዛ ሰልፍ ላይ ከታደሙት መካከል Michael Adebowale የተባለ ወጣት ከዚያ የጽንፈኞች ሰልፍ አንድ ዓመት በኋላ የብሪታኒያን ወታደር Lee Rigbyን በደቡብ ምሥራቅ ለንደን በጠራራ ፀሐይ በመኪና ገጭቶ በስለት ወጋግቶ የገደለ መሆኑ ልጃቸውን ከማጣታቸው ጋር ተደማምሮ የአቶ አባስን ቀጣይ ሕይወት መሪር ያደርገዋል። ሆኖም ሰው የዘራውን ማጨዱ አይቀርም ቢባልም በልጃቸው ማንነት ላይ የነበራቸውን ሚና እርግጠኛ ሆኖ መናገር አዳጋች ነው።
ሆኔታው ግን ለጅምላ ፈራጆች ትልቅ ሲሳይ እንደሚሆን እርግጠኛ ነኝ። የኢትዮጵያ ሙስሊሞች እንቅስቃሴን በጎሪጥ ለሚያዩ ሰዎች፣ ህወሓት የሚሰራው ፕሮፓጋንዳ ለኀይማኖታቸው፣ ለብሔራቸው… በሚመች መልኩ በትሪ ጠረጴዛቸው ላይ ቁጭ ሲቀርብ ተስገብግበው ለሚሻሙ ሰዎች ለቁንጽል መረጃቸውና ድምዳሜያቸው ግዙፍ ርዕስ አግኝተዋል።
ድምጻችን ይሰማ በዚህ ውዥንብር ሳይደናገር ላለፉት 3 ዓመታት ያሳየንን ሰላማዊ እና ስልጡን ተቃውሞ እንደሚቀጥል ቅንጣት ታህል ጥርጥር የለኝም
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጡረታ የማራዝመው ሕግ አክብሬ ነው አለ

ፕሬዚዳንቱ ይህን ያስታወቁት መጋቢት 18 ቀን 2007 ዓ.ም. ዕለት በዩኒቨርሲቲው የሴኔት አዳራሽ ለተለያዩ የአገር ውስጥ ጋዜጠኞች አጠቃላይ የመማር ማስተማርና አስተዳደራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ በተሰጠ መግለጫ ላይ ነው፡፡
በዩኒቨርሲቲው በረዥም ዓመታት በመምህርነት ሲያገለግሉ የነበሩት ዶ/ር መረራ ጉዲና ‹‹የሥራ ውሌ በሕገወጥ መንገድ ተቋርጧል›› በማለት ዩኒቨርሲቲውን ለመክሰስ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡
በጉዳዩ ላይ የተጠየቁት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር አድማሱ ‹‹መንግሥት ያወጣው የጡረታ መመርያ አለ፡፡ አንድ የአካዳሚክ ሠራተኛ የሚተካው ሰው ከሌለና የጡረታ ዕድሜው ከደረሰ ጡረታውን ማራዘም ይችላል፤›› በማለት የዶ/ሩ ጥያቄ ሕጉን ያልተከተለ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ፕሬዚዳንቱ ‹‹የአንድ ሠራተኛ የጡረታ ዕድሜ ለማራዘም መሥሪያ ቤቱ ፍላጎት ማሳየት አለበት፤›› ያሉ ሲሆን፣ በተጨማሪም ‹‹ሠራተኛው ይጠቅመኛል ወይ፤ የሚሠራው ሥራ አለ ወይ ብሎ ገምግሞ ማስታወቂያ መውጣት አለበት፡፡ ይህ ሁሉ ደግሞ ሒደት አለው፤›› በማለት በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
ባለፈው ሳምንት ከሪፖርተር ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት ዶ/ር መረራ ጉዲና የትምህርት ክፍላቸው እሳቸውን ለማቆየት ፍላጎት እንዳለው ማሳወቁንና ለሁለት ተጨማሪ ዓመታት ኮንትራት መፈረማቸውን በድንገት ምክንያቱ ሳይገለጽላቸው የቅጥር ውላቸው መቋረጡ እንደተነገራቸው መግለጻቸው ይታወሳል፡፡ የሥራ ባልደረባቸውና የትምህርት ክፍሉ ኃላፊ የነበሩት ዶ/ር ካሳሁን ብርሃኑም በዚሁ ጉዳይ ደስተኛ ባለመሆናቸው ከኃላፊነታቸው በገዛ ፈቃዳቸው መልቀቃቸውንም መዘገባችን ይታወሳል፡፡
በተያያዘ ዜና ዩኒቨርሲቲው የተለያዩ የንግድ ተቋማትን ማቋቋሙን በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ተገልጿል፡፡ ‹‹የንግድ ተቋማትን በዚህ ዓመት አቋቁመናል ሥራ አስኪያጆችንም እንዲሁ መድበናል፡፡ እነዚህን የንግድ ተቋማት ስናቋቁም ሕጉ በሚፈቅደው መሠረት በአጠቃላይ ራሳቸውን ችለው ገቢ የማመንጨት ሥራ እንዲሠሩ ነው፤›› በማለት ፕሬዚዳንቱ አስረድተዋል፡፡ ገቢ እንዲያመነጩ ከተለዩት የዩኒቨርሲቲው ተቋሞች መካከል ደግሞ የዩኒቨርሲቲው ማተሚያ ቤት፣ ቡክ ሴንተር፣ ደብረዘይት የሚገኘው የእንስሳት ማደለቢያ ይገኙበታል፡፡
የአድዋ ዘማቾች – ዳንኤል ክብረት

ከዛሬ 119 ዓመት በፊት ጀግኖች አባቶቻችንና እናቶቻችን በዓለም ታሪክ ያልተለመደ አዲስ ታሪክ ለመሥራትና ኢትዮጵያ የምትባለውን ሀገር የማይደረስበት ከፍታ ላይ ለማስቀመጥ ሲሉ ከመላዋ ሀገሪቱ አንድ ሆነው ወጥተው፣ አንድ ሆነው ወደ አድዋ ዘምተው ነበር፡፡ ያኔ ብዙዎቹ የተጓዙት በእግራቸው ጋራ ሸንተረሩን፣ አረሁን ገደሉን እየተሻገሩ በፍጹም ኢትዮጵያዊ ወኔና ሀገራዊ ፍቅር ነበር፡፡ ያ አንድነትና የሀገር ፍቅር ስሜት ነበር ጀግኖች አባቶቻችንና እናቶቻችንን ሊደግሙት እንጂ ሊረሱት የማይገባ ታሪክ እንዲሠሩ ያደረጋቸው፡፡ትናንት(እሑድ መጋቢት 13 ቀን 2007 ዓም) በጨጨሆ የባሕል ምግብ አዳራሽ በተደረገ አንድ መርሐ ግብር ተጋብዤ ተገኝቼ ነበር፡፡ ‹ጉዞ አድዋ› ይባላል መርሐ ግብሩ፡፡
ይህንን የአድዋ መንፈስና ዝና፣ ክብርና ላቅ ያለ ኢትዮጵያዊነት ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ፤ አድዋ እንደ አንድ ተራ ሥነ ሥርዓት በምኒልክ አደባባይ የአበባ ጉንጉን ከማስቀመጥና ‹አስቦ ከመዋል› የዘለለ ትውልዳዊ ፋይዳ እንዲኖረው ለማድረግ፤ አድዋ እንደ ባለሞያ ጠጅ በየጊዜው ከጥንስሱ እየተቆነጠረ በየትውልዱ እንዲጠጣ ለማስቻል፤ እንደ ሰራፕታ ዱቄት በየዘመናቱ ቡኾ ውስጥ እንደ እርሾ እየተጨመረ እንዲበላ ለማብቃት፣ አድዋ ላይ የታየው የላቀ ኢትዮጵያዊነት አንደ ሜሮን ቅብዐት ከትውልድ ትውልድ ሳይቋረጥ እየፈላ የሁሉ ማጥመቂያ እንዲሆን የተነሡ ወጣቶች ያዘጋጁት መርሐ ግብር ነበር፡፡ እንደ አድዋ ዘማቾች ወኔ እንጂ ሌላ ሀብት የሌላቸው ወጣቶች፡፡
እነዚህ ወጣቶች አንድ አስደማሚ ተግባር ጀምረዋል፡፡ በየዓመቱ የአድዋ በዓል ከመከበሩ ቀደም ብለው ከአዲስ አበባ በመነሣት በእግራቸው ወደ አድዋ መዝመት፡፡ አባቶቻቸውና እናቶቻቸው በእግራቸው የተጓዙትን መንገድ እነርሱም በእግራቸው መከተል፡፡ የቀድሞ የአድዋ ዘማቾችን ስሜት እየተጋሩ፣ ታሪካቸውን እያጠኑ፣ በየደረሱበት ለሚያገኙት ሁሉ የአድዋን የላቀ ኢትዮጵያዊነት እየሰበኩ፣ የትውልድን ቃል ኪዳን ማደስ፡፡
ተጓዦቹ ከመልስ በኋላ
የዘንድሮ ተጓዦች ስድስት ናቸው፡፡ ከስድስቱ አንዷ ሴት ናት፡፡ ጽዮን ትባላለች፡፡ በጉዞው ስሟ ደግሞ እቴጌ ጣይቱ፡፡ ከአንድ ሺ ኪሎ ሜትር በላይ የሚሆነውን መንገድ በእግሯ አቆራርጣ እንደ እቴጌ ጣይቱ አድዋ ላይ ሰንደቋን ተክላለች፡፡ መድረኩ ላይ ወጥታ የእቴጌን ታሪክና የጉዞውን ትዝታ ስትተርክ የሆነ የሚንፎለፎል ትኩስ ወኔ ከውስጧ እየወጣ ይገርፈን ነበር፡፡ እናለቅሳለንም፣ እንገረማለንም፣ እናጨበጭባለንም፡፡ የማትነጥፍ ሀገር፡፡በድንኳን እያደሩ፣ ያገኙትን እየቀመሱ፣ ከአራዊት ጋር እየታገሉ፣ ከተራራና ገደል ጋር እየተገዳደሩ፣ እየወደቁ እየተነሡ፣ እየታመሙ እየተፈወሱ፣ እየደከሙ እየጀገኑ፣ እያዘገሙ እየፈጠኑ ከአንድ ሺ ኪሎ ሜትር በላይ የሚሆነውን መንገድ በእግር ማቆራረጥ፡፡ አድዋ ላይ ተጉዘው የታሪክ ማርሽ በዘወሩ ጀግኖች ስም ራሳቸው እየሰየሙ፣ የመንፈስ ወራሽታቸን ማረጋገጥ፡፡
ከጉዞ አስተባባሪዎች አንዱ የሆነው መሐመድ ስለ ጉዞው ዓላማና ሂደት ሲገልጥ እርሱ ራሱ ከዐፄ ምኒሊክ ሠራዊት ጋር የዘመተ ነበር የሚመስለው፡፡ መቼም መሐመድ ስለ ኢትዮጵያ ሲያወራ መስማት በባለሞያ ካህን የተከሸነ ቅዳሴ እንደመስማት ያለ ነው፡፡ ያወጣዋል፣ ይተርከዋል፣ ያውም ከዕንባና ከስሜት ጋራ፡፡
እነዚህ ወጣቶች የዛሬ ዓመት በ2008 ዓም አንድ ታላቅ ታሪክ ሊሠሩ አስበዋል፡፡ የአድዋ አንድ መቶ ሃያኛ ዓመት ሲከበር አንድ መቶ ሃያ ተጓዦችን ይዞ ወደ አድዋ በእግር ለመዝመት፡፡ ወጣቶች ናቸው፡፡ ግን ልባቸው ሸምግሏል፤ ብዙ ሊስቧቸው የሚችሉ ብልጭልጭ ነገሮች ነበሩ፤ ነገር ግን ሀገራዊውን ታሪክ መርጠዋል፡፡ ከሺ ኪሎ ሜትር በላይ የሚሆነውን መንገድ በእግር አቆራርጠው፣ የሀገራችንን ባንዴራ ከፍ አድርገው ፣ በየደረሱበት አድዋ ላይ የተገለጠውን ያንን ሁላችንንም የሚያኮራ ኢትዮጵያዊነት እየተረኩ በእግራቸው ሊጓዙ ተነሥተዋል፡፡
ጽዮን – እንደ እቴጌ ጣይቱ
የጉዞው አስተባባሪ ያሬድ ሹመቴ
እንደ እኔ እንደ እኔ አንድ ትውልድ ታሪኩን ሲያነሣ፣ በማንነቱ ሲኮራ፣ ታሪክም ለመሥራት ሲቆርጥ መደገፍ ይገባል እላለሁ፡፡ ወጣቶች ከሥነ ምግባር ሲወጡ፣ ማንነታቸውንና ታሪካቸው ሲረሱ፣ ለሀገራዊ ነገሮችም የእኔነት ስሜት ሲያጡ እንደምንወቅሰውና እንደምናዝነው ሁሉ፤ በሀገር ፍቅር ስሜት ሲነሡና ታሪካችንን ከፍ አድርገው በአዲሱ ትውልድ አዲስ መንፈስ ውስጥ ሊጽፉት ሲተጉም አብረናቸው መሥራት ይገባናል፡፡ ታሪካችንና ማንነታችን እንደማይዘነጋ ማረጋገጥ የምንችለው ተተኪው ትውልድ የእኔ ነው ብሎ በራሱ መንገድ ሊገልጠው ሲሞክር ካየን ብቻ ነው፡፡
እናግዛቸው፣ አብረናቸውም እንቁም፤ የቻልን የጉዟቸውን ወጭ እንጋራ፣ ያልቻልን በሚደርሱበት ቦታ ሽሮ ሠርተን ውኃ ቀድተን በማስተናገድ የጥንት አያቶቻችን የአድዋ ዘማቾችን የሸኙበትን ታሪክ እንድገመው፡፡ በሚደርሱባቸው ቦታዎች ያሉ ትምህርት ቤቶች ደግሞ ወጣቶቹ ከተጓዦቹ ጋር ስለ ታሪካቸው እንዲወያዩ መርሐ ግብር ያዘጋጁ፡፡ የእምነት ተቋማት ደግሞ በሚደርሱባቸው ቦታዎች በመቀበል ለታሪካችንና ማንነታችን ያለንን የከበሬታ ሥፍራ እናሳይ፡፡ በየቦታው የምንገኝ ኢትዮጵያውያንም በየደረሱበት ቦታ እየተቀበልን ባንዴራውን ከፍ አድርገን በማሻገር የታሪክ ተረካቢነታችን እናረጋግጥ፡፡ አንድ መቶ ሃያኛውን የአድዋ በዓል፣ በ2008 ዓም ከአበባ ማኖር በዘለለ በማይረሳ የወጣቶች ታሪካዊ ጉዞ እናክብረው፡፡
ጠቢብ አስቦ ይሠራል
ጎበዝ ደግሞ ከሚሠሩት ጋር ያብራል፡፡
የኢህአዴግ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በመጪው ሐገራዊ ምርጫ የሚወዳደሩት በቦሎሴ ሶሮ ሁለት ነው

አዲስ ትውልድ ፓርቲ ያቀረበው ዕጩ ደስታ ዳአ (አርቲስት)፣ የሰማያዊ ፓርቲው ዕጩ ቀኙ ሰባ (ተማሪ) እና የመድረክ እጩ የሆነው ተስፋዬ ኃይሌ (አርሶ አደር) ከጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር የሚወዳደሩ ናቸው፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ የሆኑት አቶ ተክለወልድ አጥናፉም በዚያ አካባቢ ባለ ሌላ የምርጫ አካባቢ በገዢው ፓርቲ እጩ ሆነው ቀርበዋል፡፡
ተቃዋሚ ፓርቲዎች በምርጫ ቅስቀሳ መልዕክታችን ላይ የቅድሚያ ምርመራ እየተደረገ ነው ሲሉ ከሰሱ

በመጪው ግንቦት 16 ቀን 2007 ዓ.ም. በሚደረገው ጠቅላላ ምርጫ ተሳታፊ የሆኑ ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ በምርጫ ቅስቀሳ መልዕክታቸው ላይ የቅድሚያ ምርመራ (ሳንሱር) እየተደረገ ነው ሲሉ ከሰሱ፡፡
ኢዴፓ ቅድመ ምርመራው ከተደገመ ራሴን ከምርጫ አገላለሁ ብሏል፡፡
የፖለቲካ ፓርቲዎቹ እስከ ግንቦት 13 ቀን 2007 ዓ.ም. በሚዘልቀው የምርጫ ቅስቀሳና ዘመቻ የጊዜ ሰሌዳ የተለያዩ መልዕክቶቻቸውን በተለያዩ የሚዲያ ተቋማት በማቅረብ ላይ ይገኛሉ፡፡ ይሁንና ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የሚዲያ ተቋማት ሕገ መንግሥታዊ ከለላውን በመጣስ የቅድመ ምርመራ በማድረግ መልዕክቶቻችንን አናስተላልፍም አሉን በማለት ፓርቲዎቹ ቅሬታ እያቀረቡ ነው፡፡ የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት በአንቀጽ 29(3) (ሀ) ላይ የቅድሚያ ምርመራ በማንኛውም መልኩ የተከለከለ እንደሆነ ይደነግጋል፡፡
የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) መጋቢት 18 ቀን 2007 ዓ.ም. ባወጣው የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መግለጫ ቅስቀሳዎቹ እንዳይተላለፉ በመደረጉ፣ በምርጫ ተሳትፎው ላይ ትልቅ ተግዳሮት እንደፈጠረበት ገልጿል፡፡
በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትና በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢብኮ) እንዳይተላለፍ የተከለከለው የቅስቀሳ ፕሮግራም ይዘት ሕግን የተፃረረ አለመሆኑንም አስምሮበታል፡፡ የሚዲያ ተቋማቱ ድርጊት ግን ሕግን የሚፃረርና በሕገ መንግሥቱ የተከለከለውን የቅድሚያ ምርመራ ያለመደረግ መብት የሚጥስ ሆኖ እንዳገኘው ፓርቲው አስገንዝቧል፡፡
‹‹በዘንድሮው ምርጫ የመወዳደሪያ ሜዳው ከመቼውም ጊዜ በበለጠ እየጠበበ መምጣቱን የሚያሳይ ተግባር ሆኖ አግኝተነዋል፤›› ሲል ያሰፈረው የኢዴፓ መግለጫ፣ መጋቢት 15 ቀን 2007 ዓ.ም. ለፋናና ለኢብኮ የላከው የቅስቀሳ መልዕክት እንዲስተካከል የቀረበው ጥያቄ አሳማኝ ምክንያት እንዳላካተተ አመልክቷል፡፡
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አክሲዮን ማኅበር እንዲሁም ኢብኮ ለኢዴፓ በጻፉት ደብዳቤ፣ ‹‹በአገሪቱ አሉ የሚባሉ ዴሞክራሲያዊ ተቋማት ሁሉ የኢሕአዴግ ሥልጣን መጠቀሚያና መጠበቂያ ብቻ እንዲሆኑ በማድረጉ፣ ተቋማቱ በገለልተኝነት እንዳይሠሩና ዓላማቸውን ለማሳካት የሚያስችል ነፃነት ብቻ ሳይሆን አቅምም እንዳይኖራቸው አድርጓል፤›› በማለት ኢዴፓ መልዕክት ለማስተላለፍ መሞከሩ ሕገ መንግሥቱን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ሥነ ምግባር አዋጅን፣ የምርጫ ሕጉን፣ የመገናኛ ብዙኃን ሕጉን፣ እንዲሁም የተቋማቸውን ኤዲቶሪያል ፖሊሲና ሌሎች ሕጎችን የሚጥስ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡ በተለይ በኢብኮ የምርጫ ዴስክ ሰብሳቢ በአቶ ሰለሞን ተስፋዬ መጋቢት 15 ቀን 2007 ዓ.ም. ተፈርሞ የወጣው የኢብኮ ደብዳቤ፣ ‹‹ይህ መልዕክት በሕገ መንግሥቱ የተቋቋሙ የዴሞክራሲ ተቋማትን ሁሉ ህልውና የሚክድና ተግባራቸውን የሚያንቋሽሽ፣ ሕዝቡ በተቋማቱ ላይ አመኔታ እንዲያጣ የሚያደርግ መልዕክት በመሆኑና ሕገ መንግሥቱን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ሥነ ምግባር ሕጉን አንቀጽ 29(1) እንዲሁም የድርጅታችንን ኤዲቶሪያል ፖሊሲ የሚፃረር ሆኖ አግኝተነዋል፤›› በማለት ገልጿል፡፡ የአዋጁ አንቀጽ 29(1) ማንኛውም ፖለቲካ ፓርቲ፣ የግል ዕጩ ተወዳዳሪ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቅንጅት፣ ግንባር፣ ጥምረት፣ ንቅናቄ፣ እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲ መሪ፣ ኃላፊ፣ ዕጩ፣ አባል፣ ወኪልና ተጠሪ የምርጫ ዘመቻውን ሰላም የሚያናጋ ወይም ግጭት የሚቆሰቁስ ወይም ስም የሚያጠፋ ወይም አመፅ የሚጋብዝ ወይም ሥጋት የሚፈጥር ንግግር ካደረገ የሥነ ምግባር ጥሰት እንደፈጸመ እንደሚቆጠር ይደነግጋል፡፡
ኢዴፓ በመግለጫው፣ ‹‹ለዴሞክራሲ ተቋማት ያለንን ተቆርቋሪነት ኢሕአዴግ በነፃነት እንዳይሠሩ እያደረጋቸው መሆኑን መግለጽና ተቋማቱ ለተቋቋሙለት ዓላማ ግብ መምታት ኢሕአዴግ እንቅፋት መሆኑን መግለጽን፣ እንዴት የተቋማቱን ስም ማጥፋት እንደሆነ ሊገባን አልቻለም፤›› ብሏል፡፡
ኢዴፓ ይህ የመብት ጥሰት የማይቆም ከሆነ ጉዳዩን በጥልቀት መርምሮ ከምርጫ ተሳትፎው ራሱን ሊያገል እንደሚችል አስጠንቅቋል፡፡ የኢዴፓ የጥናትና ምርምር ኃላፊ አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ፣ ‹‹ሐሳቦቻችንን በነፃነት ካልገለጽን ተሳትፎአችን የይስሙላ ስለሚሆን ድርጊቶቹ የሚቀጥሉ ከሆነ በምርጫው መሳተፋችን ከማጀብ ስለማይለይ ራሳችንን ከምርጫው ልናገል እንችላለን፤›› በማለት ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ አቶ ዋሲሁን ፋናና ኢብኮ አላስተናግድም ያሉት ጽሑፍ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ መስተናገዱ ከክልከላው ጀርባ የግለሰቦች ፍላጎት ይኖር ይሆን እንዴ ብለው እንዲጠራጠሩ እንዳደረጋቸውም አመልክተዋል፡፡ ጉዳያቸውን ለፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አቅርበው በችግሩ ላይ ስምምነት መፈጠሩን ግን እንደ ጥሩ ምልክት ወስደውታል፡፡
በተመሳሳይ ኢብኮንና ፋናን በቅድሚያ ምርመራ ከከሰሱት ተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል ሰማያዊና መድረክም ይገኛሉ፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ፣ እስካሁን ፓርቲው ስምንት የተለያዩ የምርጫ ቅስቀሳ መልዕክቶች እንደተሰረዘበት ገልጸዋል፡፡ ፓርቲያቸው ሕገ መንግሥቱ በግልጽ ባሰፈረው የቅድሚያ ምርመራ ክልከላ ላይ እንደማይደራደር ያስታወቁት አቶ ዮናታን እንደ ኢብኮ፣ አዲስ ቲቪና ኤፍ ኤም 96.3 ሬዲዮ ያሉ ተቋማት መልዕክቶቹን እንዲያስተካክሉ መጠየቃቸው ሕገወጥ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡ ይሁንና በጋዜጦች ላይ ግን የከፋ ችግር እስካሁን እንዳልገጠማቸው ገልጸዋል፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ መጋቢት 16 ቀን 2007 ዓ.ም. በኢብኮ እንዲተላለፍ የላከው የምርጫ ቅስቀሳ መልዕክት የጎሳ ፌዴራሊዝም ለግጭት መንስዔ ነው ማለቱ፣ አንዱን ብሔር ከሌላ ብሔር የሚያጋጭ ነው በሚል ውድቅ እንደተደረገበት መግለጹ ይታወሳል፡፡ በተመሳሳይ ‹‹የሕወሓት/ኢሕአዴግ ሥርዓት/መንግሥት›› የሚለውን አጠራር እንዲያስተካክል ጥያቄ እንደቀረበለት ገልጿል፡፡ ከዚህ አስቀድሞ ኢሕአዴግ ‹‹ፖሊስን፣ ሚዲያውን፣ መከላከያ ሠራዊቱንና ደኅንነቱን ሰማያዊና ሌሎች ፓርቲዎችን ለማጥፋት ሲጠቀምባቸው ቆይቷል››፣ ‹‹ምርጫ ቦርድ፣ ፍርድ ቤትና ሌሎችም ተቋማት ሕግ አክብረው አይሠሩም››፣ የሚሉትን ጨምሮ ሌሎች መልዕክቶች የአገሪቱን ሕጎች የሚፃረሩ በመሆኑ እንደማያስተናግድ ኢብኮ ለሰማያዊ በጻፈው ደብዳቤ ገልጾ ነበር፡፡ በተመሳሳይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መገናኛ ብዙኃን ኤጀንሲ የሰማያዊ ፓርቲ የቅስቀሳ መልዕክት ይዘቶች የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦችን ወደ አላስፈላጊ ግጭት ሊያመሩ የሚችሉና የሌላ ፓርቲን ስም የሚያጎድፉ በመሆናቸው፣ ለውጥ ካልተደረገ እንደማያስተናግድ ገልጾ ለሰማያዊ ፓርቲ ደብዳቤ ጽፏል፡፡
መድረክ በበኩሉ የተለያዩ የምርጫ ቅስቀሳ መልዕክቶቹ ላይ በተመሳሳይ የቅድሚያ ምርመራ እንደተደረገበት ይገልጻል፡፡ በተለይ ምርጫ ቦርድና የፍትሕ አካላት ነፃና ገለልተኛ አይደሉም በማለት ያቀረባቸው መልዕክቶች ውድቅ እንደተደረጉበት፣ የመድረክ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጥላሁን እንደሻው ገልጸዋል፡፡
ኢብኮ፣ ፋናና አዲስ ኤፍ ኤም እነዚህ ተቋማትና የመንግሥት ሚዲያን ነፃነት አስመልክቶ መድረክ ያቀረበው ትችት እንዲወጣ መጠየቃቸውን ጠቅሰዋል፡፡ መድረክ የፖለቲካ እስረኞች እንዳይኖሩ ያደርጋል በማለት ያቀረበው አማራጭም አሁን የፖለቲካ እስረኛ እንዳለ የሚያመለክት ስለሆነ አናስተናግድም እንደተባሉ አመልክተዋል፡፡ የኦሮሚያ መገናኛ ብዙኃንም ገዥው ፓርቲን ያለመረጃ እየተቻችሁ ነው በሚል መልዕክታቸውን ሳያስተላልፉ እንደቀሩ ገልጸዋል፡፡ ‹‹ሥርዓቱን አትንኩ የሚል አዝማሚያ ነው ያለው፡፡ ሥርዓቱ ላይ የሚነካ ነገር ከሌለ የእኛ ጥቅም ምንድነው?›› ሲሉም አቶ ጥላሁን ጠይቀዋል፡፡
ኢዴፓ፣ ሰማያዊና መድረክን ጨምሮ በቅድሚያ ምርመራ መገናኛ ብዙኃኑን የሚከሱ ፓርቲዎች ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አቤቱታቸውን ማቅረባቸውንና ቦርዱ ምላሽ እንዳልሰጠም ተችተዋል፡፡ የቦርዱ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደምሰው በንቲ፣ የኢዴፓን ቅሬታ ገና ያልተመለከቱት ቢሆንም በሰማያዊና በመድረክ ላይ በሕጉ መሠረት ማስተካከያ አድርጉ ማለት ቅድሚያ ምርመራ ተደረገ የሚያስብል እንዳልሆነ ገልጸዋል፡፡ ‹‹የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ባለሥልጣንና ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከፓርቲዎቹ ጋር ባደረጉት የጋራ ውይይት አሠራሮቹ ላይ ስምምነት ተደርጓል፡፡ የሁለቱ ፓርቲዎች ጉዳይ ከዚያ ያፈነገጠ ነው፡፡ መልዕክታችን ትክክል ስለሆነ ሕጉን አይፃረርም የሚል አቋም ወስደዋል፡፡ ነገር ግን የመገናኛ ብዙኃኑ ደግሞ ኃላፊነት አለባቸው፤›› ብለዋል፡፡
ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በፌስቡክ ይፋዊ ገጹ ላይ አንዳንድ ፓርቲዎች የተከለከሉ ይዘቶችን በምርጫ ቅስቀሳ እንደሚጠቀሙ የጠቀሰ ሲሆን፣ ከዚህም መካከል የምርጫ ቦርድን፣ የምርጫ አስፈጻሚዎችን፣ የፍርድ ቤቶችንና የፍትሕ አካላትን ገለልተኝነትና ነፃነት ማጣጣል፣ ብሔረሰብን ከብሔረሰብ የሚያጋጩ፣ አመፅ የሚቀሰቅሱ፣ ስም የሚያጠፉ እንደሚገኙበት ጠቅሷል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝም ከመንግሥት ሚዲያ ተቋማት ጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ቆይታ ጥቂት ፓርቲዎች ሕገወጥ የቅስቀሳ ይዘት ማምጣታቸውን ያቁሙ ብለዋል፡፡
ሪፖርተር ያነጋገራቸው ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የሕግ ባለሙያ ግን በሕገ መንግሥቱ የተቀመጠውን የቅድመ ምርመራ ክልከላን የሚፃረሩ ሕጎች መኖራቸውን ጠቅሰዋል፡፡ የሕጎቹ ሕገ መንግሥታዊነት ላይ ጥያቄ ሳያነሱ ሕገ መንግሥቱን ብቻ በመጥቀስ መከራከር፣ በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ የራሱ ችግሮች አሉት ብለዋል፡፡
መንግሥት ለምን ጩኸት ይወዳል? – ኤልያስ ገብሩ ጎዳና

ይሄም ብቻ አይደለም፣ ከተሰራው በላይ በማጋነን፣ የፕሮፖጋንዳ ሥራን በፈጆታነት ይጠቀማሉ፡፡ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ይሆናል ብዬ የማስበው ገዥው መንግሥት ኢህአዴግ ነው፡፡ መንግሥታችን ትልቅም ሆነ ትንሽ ሥራ ሲሳራ በግንነት መግለጽ አንዱ መለያው ማድረጉን ምርጫው ያደረገ ይመስላል፡፡
ከወራቶች በፊት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በጋዜጠኝነት የሙያ ዘርፍ ተመራቂ ተማሪዎች እኔን እና ጋዜጠኛ አናንያ ሶሪን ሀሳብን ከመግለጽ ነጻነት አኳያ እንግዳ አድርገው ከተማሪዎች ጋር በጥያቄ እና መልስ አወያይተውን ነበር፡፡ በዚህ ደስ የሚል ፕሮግራም ላይ ልማታዊ ጋዜጠኝነትን በተመለከተ በነበረው ገለጻ ላይ አናንያ የሚያስቅ ነገር ግን ቁም ነገር አዘል አስተያየቱን ሰንዝሮም ነበር፡፡ ‹‹ኢህአዴግ ለአባይ ግድብ ግንባታም ሆነ ሰፈር ውስጥ የቦኖ ውሃ እንዲወጣ አድርጎ ኅብረተሰቡን እኩል ድቤ ያስመታል›› ነበር ያለው አናንያ፡፡ ከዚህ ለመረዳት እንደሚቻለው ለትንሹም ሆነ ለትልቁ ‹‹ልማት›› ጩኸት ከመፈለጉም ባሻገር ውዳሴም መሻቱን ነው፡፡
ካነሳሁት ርዕሰ ጉዳይ ጋር በተያያዘ አንድ ምሳሌ ልጥቀስ፡-
ካነሳሁት ርዕሰ ጉዳይ ጋር በተያያዘ አንድ ምሳሌ ልጥቀስ፡-
ግንቦት 2 ቀን 2005 ዓ.ም አመሻሽ ላይ የፌዴራል የጸረ ሙስና እና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን ከብሔራዊ የመረጃ ደኅንነት ተቋም ጋር በመተባበር የፌዴራል ገቢዎች እና ጉምሩክ ባለሥልጣን መ/ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታ እና ምክትላቸው አቶ ገብረህዋድ ገ/ጊዮርጊስን ጨምሮ 13 ሰዎችን በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው መታሰር በአዲስ አበባ እና በሌሎችም የአገሪቱ ከተሞች ሰበር ዜና ሆኖ የመረጃ ቅብብሎሹ በፍጥነት ተዛምቶ ነበር፡፡ በተጨማሪም በሂደት ተጠርጥረው የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ50 በላይ ደረሱ፡፡
ይህንንም እስር ተንተርሶ ጠ/ሚ/ር ኃይለማርያም ደሳለኝ ትልቅ ሥራ እንደሰሩ ተደርጎ ‹‹በርቱ ተበራቱ፣ በዚሁ ቀጥሉበት፣ አሁን ሥራ መስራት ጀመሩ!›› ተብለው ሲመሰገኑ እና ሲወደሱ ነበር፡፡
ይህንንም እስር ተንተርሶ ጠ/ሚ/ር ኃይለማርያም ደሳለኝ ትልቅ ሥራ እንደሰሩ ተደርጎ ‹‹በርቱ ተበራቱ፣ በዚሁ ቀጥሉበት፣ አሁን ሥራ መስራት ጀመሩ!›› ተብለው ሲመሰገኑ እና ሲወደሱ ነበር፡፡
በዚያ ሰሞን በሀገሪቱ ላይ ትልቅ ተዓምር የተፈጠረ ይመስል፣ የመንግሥት እና የተወሰኑ የግሉ ሚዲያዎች ጉዳዩን ከልክ በላይ ዘገቡት፡፡ የኅብረተሰቡም ዋነኛ የመወያያ ርዕሰ ጉዳይ ይሄ ሆነ፡፡ ነገር ግን፣ ጉዳዩን በሰከነ መንገድ ማስተዋል ቢቻል ጉዳዩ ይን ያህል አስገራሚ አልነበረም፡፡ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የሥራ ኃላፊዎችና ታዋቂ ባለሃብቶች በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥራ መዋላቸውና መከሰሳቸው አይደለም፡፡ ከዚያ ቀደም የቀድሞ ጠ/ሚኒስትር ታምራት ላይኔ እና የመከለከያ ሚኒስትሩ አቶ ስዬ አብርሃም በመሰል ወንጀል ተጠርጥረው ከተከሰሱ በኋላ ተፈርዶባቸው ከእስር ወጥተዋል፡፡ ግን ሥርዓቱ ከእንደዚህ ዓይነት ተጠንተው በታቀዱ ክስተቶች ጩኸትን ይሻል፡፡ ለምን ለሚለው በጽሑፌ መደምደሚያ ላይ እመለስበታለሁ፡፡
የአባይ ግድብን የወሰድን እንደሆነም፣ መሰል ነገር እናስተውላለን፡፡ የአባይን መገደብ የደገፉት ብዙዎች እንዳሉ ሁሉ በምክንያታዊነት የፕሮጀክቱን ዓላማ የሚተቹ ወገኖችም መኖራቸው እሙን ነው፡፡ …የግድቡን ሥራ በቅንነት ካየነው፣ የዐባይ መገደብ አንድ ትልቅ ሀገራዊ የልማት ተግባር አድርጎ መውሰድ ይቻላል፡፡ ሆኖም በዐባይ ግድብ ስም ያለማቋረጥ እየተሰራ ያለው ፕሮፖጋንዳ ቀላል አይደለም፡፡ ስለፕሮጅክቱ ዝርዝር ነገር በመንግሥት ኃላፊዎች፣ በመንግሥት፣ በግሉና በውጭ ሀገራት ሚዲያዎች ለረዥም ጊዜ በተደጋጋሚ ተዘግቧል፡፡ በዚህ መሰረት፣ ሰፊው ሕዝብ ሥለግድቡ ጥሩ ግንዛቤ አግኝቷል ብሎ መውሰድ ይቻላል፡፡ ግን በሳምንት ለሰባት ቀናት እና 24 ሠዓታት ሙሉ በሚያስብል መልኩ ‹‹አባይ …አባይ›› ማለት ግድቡን ለፖለቲካ ፍጆታነት መጠቀም መሆኑን በግልጽ የሚያሳይ ነው፡፡
በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በኩል አባይ በሶስት ብር እንደሚገደብ አድርጎ የተለያዩ ማስታወቂያዎችን እስኪሰለቹ ድረስ ማቅረብም ጩኸትን መሻት አድርጌ እወስደዋለሁ፡፡ እንዲሁም ህዝብ ለግድቡ በግሉ ማድረግ ያለበትን ድጋፍ ከልቡ ፈቀዶ እንጂ በማስታወቂያ ጋጋታ ተሰላችቶ መሆን የለበትም፡፡
ሌላኛው ጩኸት የበዛበት ነገር፣ የህወሃት 40ኛ ዓመት ምስረታ በዓል ነው፡፡ ክብር ለሚገባቸው ታጋዮች ክብር መስጠት ተገቢ ሆኖ ሳላ፣ በዓሉን አስመልክቶ፣ ለረዥም ቀናት፣ እጅግ በተጋነነ መልኩ ጉዳዩን ማስጮህ አግባብ አይደለም፡፡ ለኦህዴድ 25ኛ ዓመት የምስረታ በዓልም ሌላ ግነት የበዛበት ጩኸት እየሰማን ነው፡፡
የርዕሰ ጉዳዬ ሀሳብ፣ ‹‹መንግሥት ለምን ጩኸት ይወዳል?›› የሚል ነው፡፡ በተለያዩ የልማት ሥራዎች እና መንግሥታዊ እርምጃች ውስጥ ጩኸትን መፈለግ እና መሻት ተገቢነት አለው ብዬ አላምንም፡፡ ለምን? ሥራውን በአግባቡ የሚሰራ መንግሥት ጩኸት አይፈልግም፤ አያሻውምም፡፡ ብዙ አያወራም፤ እንዲወራለትም አይፈልግም፡፡ ሥራው በራሱ ታሪካዊ ምስክሩ ነውና፡፡
ነገር ግን ኢህአዴግ የመንግሥት፣ የግሉን ሚዲያ የኅብረተሰቡን የሀሳብ በአቅጣጫ በተለያዩ ጊዜያት የማስቀየር የማስጮህ ልምድ አለው፡፡ በዚህ ረገድ የቀድሞ ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ማንሳት አስፈላጊ ነው፡፡ አቶ መለስ ወቅት እየጠበቁ የሚዲያውን እና የኅብረተሰቡን ሀሳብ ለተወሰኑ ጊዜያቶች በ‹‹አዳዲስ›› የተቀመሩ አጀንዳዎች (አነጋጋሪ ንግግሮችንና ቃላትን ይጨምራል) መስረቅ እና መጥለፍ የተካኑ ነበሩ ብል ያጋነንኩ አይለመስለኝም፡፡ ሚዲያው (አጠቃላይ ለማለት አይቻልም) እና ኅብረተሰቡ ‹‹አዲሱ››ን ርዕሰ ጉዳይ በመዘገብ፣ ትንታኔ በመስጠትና የመነጋገሪያ አጀንዳ እና ወሬ በማድረግ ለተወሰነ ጊዜ ሌላ ሐሳቡን በመጠኑ እንዲረሳ እና እንዲዘነጋ የቤት ሥራ ይሰጡት ነበር፡፡ ከዚያም ቀን እና ጊዜ ጠብቆ ሌሎች አጀንዳዎች እና የጩኸት ዜማዎች ይመጣሉ፡፡
በዚህ ቀመራዊ አካሄድ ሥርዓቱ ህዝብን ግራ እና ቀኝ እያወዛወዘ ‹‹ህዝብ የተሰጠን …ኮንትራት›› በሚል 24 ዓመታትን ሲገዛ ኖራል፡፡ ተጨማሪ ዓመታትንም ይፈልጋል፡፡ በዋነኝነት ጩኸት መውደዱም ለዚሁ ነው – ለሥልጣኑ!!!
Friday, March 27, 2015
ሁለተኛው የትዊተር ዘመቻ ከመጋቢት 21 ወደ ሚያዝያ 19 ተዛዋረ!!!

ለዘመቻው የምናደርገው ህዝባዊ ቅስቀሳ እና ዝግጅት እስከሚያዝያ 19 ባለበት እንደቀጠለ የሚቆይ ሲሆን ሰፊ የቅስቀሳ ጊዜ መኖሩም ዘመቻውን በተሻለ ስኬት ለመስራት ይበልጥ አመቺ እንደሚያደርገው የሚታመን በመሆኑ ሁላችንም የፌስቡክ ገጻችንን ፎቶ አሁን በተለጠፈው ፎቶ ዳግም በመቀየር በጀመርነው የቅስቀሳ ስራ ይበልጥ እንድንገፋበት አደራ እንላለን፤ ድልም ከአላህ እንጂ ከሌላ አይደለምና!
‹‹የህዝብ ወኪሎችን በነጻ ከማሰናበት ያነሰ ብይን አንቀበልም!››
ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!
ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!
“ጦር ሠራዊቱ ሕዝባዊ እምቢተኛነት ሲያይል የወያኔን መቃብር ይቆፍራል” – አርበኞች ግንቦት 7
የአርበኞች ግንቦት 7 ወቅታዊ መጽሐፍ
ጉዞአችን ወደ ነፃነት ነው!! መዳረሻችንም የነፃነት አደባባይ ብቻ ነው!!
ጉዞአችን ወደ ነፃነት ነው!! መዳረሻችንም የነፃነት አደባባይ ብቻ ነው!!
አለማችን አንባገነን ስታስተናግድ ወያኔ የመጀመሪያው አይደለም። ዘረኛንም እንዲሁ …….. እኛም ስለነፃነት ብለን ለትግል ሰንነሳ የመጀመሪያዎቹ አይደለንም …… አለማችን እንደየዘመኑና እንደ የወቅቱ አንባገነኖች ያለ የሌለ የመሳሪያና ወታደራዊ ሀይላቸውን በመጠቀም ህዝብን በፍርሀት አሸማቀውና ረግጠው ለመግዛት ሲውተረተሩ በተደጋጋሚ ታይተዋል። በዚያው ልክ ህዝባዊ ሀይልና መመከት ተስኗቸው ሲንኮታኮቱ በተደጋጋሚ የታየ ወደፊትም አናባገነኖች እስከተከሰቱ ድረስ በህዝባዊ ሀይል ተጠራርገው መቀመቅ ሲወርዱ መታየቱ አይቀሬ ነው ። ህዝብ የወደደውን አስተዳዳሪ እንጂ ረግጦ ሊገዛው የሚፈልገውና አንባገነን ተቀብሎ አያውቅም ፤ዛሬም አልተቀበለም ፤ ነገም አይቀበልም ። ይህን በሰው ልጆች ታሪክ ውስጥ በተደጋጋሚና በጉልህ የሚታይ ግዙፍ እውነት መቼም ተቀብለውና ከታሪክ ተምረው ስለማያውቁ አሳፋሪው ውድቀታቸው በተደጋጋሚ ሲታይ አለ።

ሀገራችን የአለማችን አካል እንደመሆኗ አንባገነኖች ተፈራርቀውባታል። አንባገነኖችም በህዝባዊ ሀይል ተጠራርገውባ ታል። ከደቡብ አፍሪካ ቀጥሎ ትልቅ ወታደራዊ ሀይል የነበረው የትናንቱ ደርግ እንደ እንቧይ ካብ ሲናድ ተመልክተናል። አንባገነኖችመናገር እንጂ መስማት የማ ችሉ፤ ማየት እንጂ ማስተዋል የተሳናቸው በመሆናቸው እነሆ ዛሬም የወያኔ ዘረኛው ቡድን ህዝባ ላነሳው የነፃነትና የፍትህ ጥያቄ ያለ የሌለውን ወታደራዊ ሀይል በጠራራ ጸሀይ በማሰለፍ መቼውንም ያልተቻለ ውን ህዝብን በሀይል አሸማቆ ለመግዛት መከራውን ሲያይ ይስተዋላል። ለዚህም ነው ….. ከሌላው የሀገራችን ክልሎች ከፍ ባለ ሁኔታ የህዝባዊ እንቢተኝነት እየታየ ባለበት ጎንደርና አካባቢው በሰራዊት ማጥለቅለቅ የተያያዘው።

ሀገራችን የአለማችን አካል እንደመሆኗ አንባገነኖች ተፈራርቀውባታል። አንባገነኖችም በህዝባዊ ሀይል ተጠራርገውባ ታል። ከደቡብ አፍሪካ ቀጥሎ ትልቅ ወታደራዊ ሀይል የነበረው የትናንቱ ደርግ እንደ እንቧይ ካብ ሲናድ ተመልክተናል። አንባገነኖችመናገር እንጂ መስማት የማ ችሉ፤ ማየት እንጂ ማስተዋል የተሳናቸው በመሆናቸው እነሆ ዛሬም የወያኔ ዘረኛው ቡድን ህዝባ ላነሳው የነፃነትና የፍትህ ጥያቄ ያለ የሌለውን ወታደራዊ ሀይል በጠራራ ጸሀይ በማሰለፍ መቼውንም ያልተቻለ ውን ህዝብን በሀይል አሸማቆ ለመግዛት መከራውን ሲያይ ይስተዋላል። ለዚህም ነው ….. ከሌላው የሀገራችን ክልሎች ከፍ ባለ ሁኔታ የህዝባዊ እንቢተኝነት እየታየ ባለበት ጎንደርና አካባቢው በሰራዊት ማጥለቅለቅ የተያያዘው።
ለሚነሱ ህዝባዊ ተቃውሞዎችና ህዝባዊ የመብት ጥያቄዎች የሚሰጡት ምላሾች እስር፤ አፈናና ግድያ ከሆነ ህዝባዊ እንቢተኝነትን ማስከተሉ አይቀሬ ነው። በእስር ፤በአፈናና በግድያ እንዲሁም በሰራዊት ሀይል ህዝብን በማሸማቀቅ በስልጣን መቆየት የሚቻል ቢሆን ደርግም ከቤተ-መንግስት ባልወጣ፤ ወያኔም ዛሬ ከቤተ-መንግስቱ ባልተንፈልለሰ ነበር። ይህ ደግሞ ሊያስተምር በተገባ ነበር።
እስከ ዛሬ የትኛውም አንባገነን ስርአት በሚተማመንበት የወታደራዊ ሀይል አማካይነት የመንኮታኮቻቸውን ሰአት በአንድ ሰኮንድ ማዘግየት የቻለ እንደሌለ ሁሉ ወያኔም ያለ የሌለውን ወታደራዊ ሀይል ሲያርመሰምስ ውሎ ቢያድር ውድ ቀቱን በአንድ ሰኮንድ ማዘግየት እንደማይችል በተለይ እንቢ ለነፃነቴ፤ እንቢ ለሀገሬ… ብለን ለትግል የተነሳን ሀይሎች በመረ ዳት፤ ይበልጡኑ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተቀጣጠለ ያለውን ህዝባዊ እንቢተኝነት ይበልጥ እያሰፋን የጀመርነውን የነፃነት ጉዞ ከነፃነታችን አደባባይ ለማድረስ ሌት ተቀን የመስራት ሀላፊነታችናና መወጣት ይገባናል።
በጎንደር የሚታየውን የአልገዛም ባይነት ትንቅንቅ በሌሎች ክልሎችም በማቀጣጠል፤ በደብረወርቅ የታየውን የመምህራን የስራ ማቆም አድማ ወደ ሌሎች አካባቢዎች በማስፋት፤ እንደ ድምፃችን ይሰማ ሁሉ ተቃውሞን ወደ እንቢተኝነት በማሸጋ ገር …… ወዘተ የነፃነታችንን ቀን ለማቅረብ መከፈል የሚገባውን መክፈል ይገባናል።
በደርግ ል የተነሳው እንቢተኝነት እያየለ ሲመጣ ያሰለፈው ሰራዊት ወያኔን አጅቦ የደርግን ቀብር እንደቆፈረለት ሁሉ ዛሬም በወያኔ ላይ እየተቀጣጠለ የሚገኘው ህዝባዊ እንቢተኝነት እየጠነከረ በመጣ ቁጥር የደረደረው ሰራዊት የወያኔን ቀብር ቆፋሪ ከመሆኑ እንደማኢመለስ ከቅርብ ጊዜ ታሪካችን በመማር ነፃነታችንን ለማስከበር የጀመርነውን የእንቢተኝነት ትግል በ መ ላው የሀገራችን ክፍሎች በማስፋትና በማቀጣጠል አይቀሬውን የወ ኔ ቀብር ለማቅረብ በአንድነት የነፃነት ጉዞውን እንቀ ላቀል። የጀመርነው የነፃነት ጉዞ መቆሚያው የነፃነታችን አደባባይ መሆኑን በተግባር ከምናሳይበት ወቅት ላይ እንገኛለንና በአንድነት እንነሳ!!!!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!!
በኦሮሚያ እና ሌሎች አካባቢዎች የመጠጥ ውሃ ችግር ት/ቤቶችን ከማዘጋት አልፎ ለስደት እየዳረገ ነው

ከግብርና ሚኒስቴር የወጣ አዲስ መረጃ እንደሚያሳየው፣ በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች የተከሰተው የመጠጥ ውሃ ችግር ሕዝብን ለከፍተኛ ችግር ከመዳረጉም አልፎ የመማር ማስተማር ስራ በማደናቀፍ ትምህርት ቤቶችን እስከማዘጋት ደርሷል።የመጠጥ ውሃ ችግር ከገጠማቸው የኦሮሚያ አካባቢዎች መካከል በአርሲ ዞን በጎሎልቻ፣ መርቲ፣ .ዝዋይ፣ ዱግዳ፣ ሴሩና ደጁ ወረዳዎች፣ በምዕራብ አርሲ ዞን በሻላ ሲራሮና ሻሸመኔ ወረዳዎች፣ በምስራቅ ሐረርጌ ዞን በሚደጋ፣ ቁምቢያ መዩ ወረዳዎች፣ በምስራቅ
ሸዋ ዞን በቦሰት ወረዳ እና በጉጂ ዞን በሊበንና ሰባቦሩ ወረዳዎች አስከፊ የተባለ የመጠጥ ውሃ ችግር ማጋጠሙን ሚኒስቴሩ አጋልጦአል፡፡
የመጠጥ ውሃ ችግሩ በተለይ በአርሲ ዞን በዝዋይ ዱግዳና በሴሩ ወረዳዎች፣ በጉጂ ዞን በሊበን ወረዳ ት/ቤቶችን እስከማዘጋት የደረሰ ችግር መከሰቱ ተረጋግጦአል፡፡ በእነዚህ አካባቢዎች የተከሰተውን የመጠጥ ውሃ ችግር ለመቅረፍ ሚኒስቴሩ ከአጋር ድርጅቶች
ባገኘው ድጋፍ ውሃ በቦቴ የማደል ስራ እያከናወነ መሆኑ ታውቋል፡፡
የመጠጥ ውሃ ችግሩ በተለይ በአርሲ ዞን በዝዋይ ዱግዳና በሴሩ ወረዳዎች፣ በጉጂ ዞን በሊበን ወረዳ ት/ቤቶችን እስከማዘጋት የደረሰ ችግር መከሰቱ ተረጋግጦአል፡፡ በእነዚህ አካባቢዎች የተከሰተውን የመጠጥ ውሃ ችግር ለመቅረፍ ሚኒስቴሩ ከአጋር ድርጅቶች
ባገኘው ድጋፍ ውሃ በቦቴ የማደል ስራ እያከናወነ መሆኑ ታውቋል፡፡
በቦረና ዞን አንዳንድ ወረዳዎች ማለትም በአሬሮ፣ ድሬ፣ ዲሎ፣ ዳስ የእንስሳት መዳከምና ሞት መከሰት የጀመረ ሲሆን በአርሲና ምዕ/ሐረርጌ ዞኖች የእንስሳቱ አቋም እየተዳከመ መሆኑ፣ የእንስሳት እንቅስቃሴም ተጀምሮ በምዕ/ሐረርጌ ዞን ከቡርቃ ዲምቱና ሃዊ
ጉዲና ወደ ዱንገታና ዋቤ ወንዝ፣ በቦረና ዞን ከተልተሌ ወደ ገራንና ኮንሶ፤ ከድሬ፤ ሚዮና ሞያሌ ወደ ኬንያ (አዋሳኝ ቦታዎች) በመንቀሳቀስ ላይ መሆናቸው በሪፖርቱ ተመልክቷል።
ጉዲና ወደ ዱንገታና ዋቤ ወንዝ፣ በቦረና ዞን ከተልተሌ ወደ ገራንና ኮንሶ፤ ከድሬ፤ ሚዮና ሞያሌ ወደ ኬንያ (አዋሳኝ ቦታዎች) በመንቀሳቀስ ላይ መሆናቸው በሪፖርቱ ተመልክቷል።
የኦሮሚያ ክልል ገዥ ፓርቲ ኦህዴድ/ኢህአዴግ እንዲህ ዓይነቱን የህዝብ ችግር ሳይፈታ ለክብረበአል በመቶ ሚሊየን ብሮችን ሲያፈስ መታየቱ አሳዛኝ መሆኑን ዘጋቢያችን ያነጋገርናቸው የኦሮሞ ተወላጆች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
በአማራ ክልል ደግሞ በሰ/ሸዋ ዞን በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ፣ በሰ/ጎንደር ዞን በምስራቅ በለሳ ወረዳ በእያንዳንዳቸው 3 ቀበሌዎች የውሃ እጥረት፣ በዋግኸምራ ዞን በሳህላ፣ ዝቋላና ሰቆጣ ወረዳዎች፣ በሰ/ወሎ ዞን በላስታና ቡግና ወረዳዎች፣ በደ/ወሎ ዞን በመቅደላ
ወረዳ በ4 ቀበሌዎች፣ በኦሮሚያ ዞን በአ/ፉርሲ ወረዳና በምስ/ጎጃም ዞን ቆላማ አካባቢዎች የውሃ እጥረት ተከስቷል።
በሀረሪ ክልል በ5 ቀበሌዎችና በድሬዳዋ አስተዳደር ቆላማ ቀበሌዎችም ተመሳሳይ ችግር ተከስቷል። ችግሮችን ለመቅረፍ ውሃ በቦቴ ለማደል ሙከራ መደረጉም በሪፖርቱ ተጠቅሷል።
ወረዳ በ4 ቀበሌዎች፣ በኦሮሚያ ዞን በአ/ፉርሲ ወረዳና በምስ/ጎጃም ዞን ቆላማ አካባቢዎች የውሃ እጥረት ተከስቷል።
በሀረሪ ክልል በ5 ቀበሌዎችና በድሬዳዋ አስተዳደር ቆላማ ቀበሌዎችም ተመሳሳይ ችግር ተከስቷል። ችግሮችን ለመቅረፍ ውሃ በቦቴ ለማደል ሙከራ መደረጉም በሪፖርቱ ተጠቅሷል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድን እንሻረክህ የሚሉ አየር መንገዶች መበርከታቸው ተዘገበ…

አሁን ላይ ከናይጄሪያ መንግስት በኩል ለግዙፍ ባለኢኮኖሚ አፍሪካዊቷ ሀገር የእቃ ጫኝ አየር መንገድ በማቋቋም በኩል እንዲሳተፍ ጥሪ እንደቀረበለት የተነገረው አየር መንገዱ በሌሎች ሶስት የአፍሪካ ሀገራት ውስጥም ተመሳሳይ እንቅስቃሴ ለመጀመር በሚያስችል መንገድ ላይ ንግግሮች መጀመራቸውን የወሬ ምንጩ የአየር መንገዱን ዋና ስራ አስኪያጅ ጠቅሶ ዘግቧል፡፡
ብሉምበርግ ዋና ስራ አስኪያጁን አቶ ተወልደ ገብረማሪያምን ጠቅሶ እንደዘገበው ከሆነ በሌሎች አየር መንገዶች ውስጥ ገብቶ የመሳተፍ ተደጋጋሚ ጥያቄዎች አየር መንገዱ እንደቀረቡለትና ይህንን በሚመለከትም ተቋሙ የቢዝነስ ጥናቶችን በማካሄድ ላይ እንዳለ ተናግሯል፡፡
የኢትዮጵ አየር መንገድ በሰውም ሆነ በእቃ መጫን መጓጓዣ አገልግሎቶቹ ከአፍሪካ እጅግ ጠንካራ አየር መንገድ እንደሆነ ያስነበበው ዘገባው ለነዚህ በሽርክና የእንስራ ጥያቄዎች መቅረብም ዋነኛ ምክንያት ይሄው መሆኑን ነው የሚተነትነው
የአምስት ዓመት የፍትሕ አፈጻጸም በአንድ ሳምንት ሊገመገም ነው

‹‹ፍትሕና ሁለንተናዊ ዕድገት›› በሚል መሪ ቃል በሚከበረው የፍትሕ ሳምንት፣ በአምስት ዓመቱ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የፍትሕ አፈጻጸም ምን ይመስል እንደነበር፣ ከኅብረተሰቡ አንፃር ምን ውጤት እንደተመዘገበና ያልተፈጸሙ ተግባራት ምን ምን እንደሆኑ ግምገማ እንደሚደረግባቸው፣ የፍትሕ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ልዑል ካህሳይ ገልጸዋል፡፡
ሚኒስትር ዴኤታው እንዳብራሩት፣ ለአምስተኛ ጊዜ የሚከበረው የፍትሕ ሳምንት ለሰላም፣ ለቀልጣፋና ፍትሐዊ ለሆነ ልማት መረጋገጥ፣ ሥር የሰደደ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲገነባና የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ጉልህ ድርሻ ይኖረዋል፡፡
ለበዓሉ መከበር ዋናው ምክንያት ከ2002 ዓ.ም. በኋላ አጠቃላይ የፍትሕ ሥርዓቱ የተሟላ የለውጥ ትግበራ የተጀመረበት ጊዜ መሆኑና የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ የአምስት ዓመት ፕሮግራምም እየተጠናቀቀ በመሆኑ፣ የበዓሉ ዋና ተዋናይ የሆኑት ተቋማት፣ ተቀናጅተው ሲሠሩ የከረሙትን አፈጻጸም የሚገመገምበትና ውጤቱና ድክመቱ የሚለይበት መሆኑን አቶ ልዑል ተናግረዋል፡፡
የለውጥ ሒደት የፍትሕ አካላቱ ለብቻቸው በተናጠል የሚያካሂዱት ሒደትና እንቅስቃሴ አለመሆኑን የገለጹት ሚኒስትር ዴኤታው፣ ከኅብረተሰቡ ጋር በመሆን የሠራውንና አገልግሎቱንም ሕዝቡ እንዴት እያገኘ እንደሆነ ሐሳቡን የሚገልጽበት መድረክ መፍጠሪያም መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ኅብረተሰቡ የራሱ ድርሻ ምን እንደሆነ ለይቶ የሚያውቅበትና የፍትሕ አካላቱን ከመደገፍ አንፃር የበኩሉን ሚና እንዲጫወት ለማስቻል በዓሉ ወሳኝ መሆኑንም አክለዋል፡፡ ከኅብረተሰቡ ግብዓትና ትችትም መቀበል ጠቃሚ በመሆኑ፣ በዓሉ አገራዊ ባህሪ ይዞ በፌዴራል ብቻ ሳይሆን በክልልም እንደሚካሄድ አቶ ልዑል አስታውቀዋል፡፡
በበዓሉ ላይ የፓናል ውይይቶች እንደሚካሄዱ፣ ኤግዚቢሽን መኖሩን፣ ጥሩና ምርጥ ተሞክሮዎች እንደሚቀርቡ፣ የእግር ጉዞ እንደሚደረግ፣ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትና በርካታ ሕዝብ የሚሳተፍበት የፍትሕ ሳምንት እንደሚሆንም ሚኒስትር ዴኤታው አመልክተዋል፡፡
የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩ በደህንነቶች ከለቅሶ ቤት ተባረሩ
የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር እሁድ መጋቢት 20/2007 ዓ.ም ለሚያደርገው ሰልፍ የሰማያዊ ፓርቲ ቲሸርትን ለብሰው ቅስቀሳ ላይ የነበሩት አቶ ተስፋየ ኃይሌ ከቅስቀሳ መልስ የፓርቲያቸው አባል የሆነው ግለሰብ የቀብር ሥነ ስርዓት ላይ መተገኙበት ወቅት ከካድሬዎች ከፍተኛ ወከባ እንደደረሰባቸውና በኋላም እንዲወጡ መደረጉን ገልጸዋል፡፡
ሆኖም ‹‹ካድሬዎች ከለቅሶው ካባረሩኝ በኋላ ህዝቡ ምን አገባችሁ፣ ለቅሶ መድረስ መብቱ ነው፡፡ ብሎ እንደገና እንድመለስ አድርጓል፡፡›› ሲሉ አቶ ተስፋየ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
Source-ነገረ ኢትዮጵያ
ፓትርያርኩ በሕግ አፍራሽነታቸው ጸኑ

በአ/አበባ ሀ/ስብከት ሥራ አስኪያጅ ምርጫ ከረዳት ሊቀ ጳጳሱ ጋራ እንዲግባቡ የተደረገው ጥረት አልተሳካም
- መመሪያቸው በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ኹለንተናዊ እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚኖረው ጠቅላይ ጽ/ቤቱ በዛሬው የቋሚ ሲኖዶሱ ስብሰባ ያቀረበውን ስጋት አጣጥለውታል
- በአ/አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች ምርጫ እና ሥያሜ የፓትርያርኩን የአካሔድ ስሕተት ከማረም አንጻር የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ውሳኔ እና መመሪያ እንደሚሰጥበት ይጠበቃል
በሥራ አስኪያጅ ምርጫ እና ሥያሜ አለመግባባቱ አጋጣሚ፣ ፓትርያርኩ፡-
- ረዳት ሊቀ ጳጳስ መርጦ ከማቅረብ ድርሻቸው በላይ በቅዱስ ሲኖዶሱ የሚወሰነው የመመደቡም ጉዳይ ከእርሳቸው ሓላፊነት ጋራ እንደሚያያዝ በመመሪያቸው ከመጥቀስ አልፎ፣ ‹‹እኔ[ሥራ አስኪያጅ] መድቤአለኹ፤ ሾሜአለኹ፤ የሚሠሩ ከኾነ ተስማምተው ይሥሩ›› በማለት የረዳት ሊቀ ጳጳሱን ሚና ፋይዳ ቢስ ማድረጋቸው፤
- በብፁዕ ዋና ጸሐፊው የሚመራው የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት፣ የቋሚ ሲኖዶሱንመነጋገርያ ርእሰ ጉዳይ አዘጋጅቶ ለውይይት የማቅረብ ተግባሩ መሠረት፣ በትላንትናው ዕለት በአድራሻ የተጻፈለት የረዳት ሊቀ ጳጳሱ ጥያቄ በአጀንዳነት ተይዞ እንዲታይ ሲጠይቅ፣ ጉዳዩን ለውይይት ዝግ ከማድረግ አልፎ ብፁዕ ዋና ጸሐፊውን በአሳዳሚነት መውቀሳቸው፤
እንደ ቅዱስ ፓትርያርክ መጠን፣ ሕጉን ተገንዝቦ እና ጠብቆ ለቤተ ክርስቲያን ከአድልዎ የጸዳ አጠቃላይ አባታዊ አመራር በመስጠት ረገድያለባቸውን የታማኝነት ውስንነትና የአማሳኝ አማካሪዎቻቸውን በተለይም በተደጋጋሚ ሲጋለጥ የቆየውን የልዩ ጸሐፊአቸውን ተንኰል እና ክፋት በገሃድ ያረጋገጠኾኖ አልፏል፡፡
የግብፅ እና የኢትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች ተወዛገቡ

በግምት ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ገደማ የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ እና የግብጹ ፕሬዚደንት አብዱልፈታህ አልሲሲ በተገኙበት የሁለቱ ሀገራት የንግድ ማህበረሰብ አባላት ባሰተፈው ስብሰባ ላይ ለመዘገብ የሄዱ የኢትዮጽያ ጋዜጠኞች በግብጽ የጸጥታ ኃይሎች ገብተው እንዳይዘግቡ የተከለከሉ ሲሆን የኢትዮጽያ የጸጥታ ኃይሎች በተቃራኒው ጋዜጠኞቹ ገብተው እንዲዘግቡ በመወሰናቸው ለጥቂት ደቂቃዎች አለመግባባትና ግርግር ተፈጥሯል፡፡
ሆኖም ጋዜጠኞቹ እንዲገቡ በመፈቀዱ አለመግባባቱ ረግቧል፡፡
በዚህ ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያ እና ግብፅ የንግድ ግንኙነት በየዓመቱ ለውጥ እያመጣ ቢሆንም አመታዊ የንግድ ልውውጡ መድረስ ይገባል ተብሎ ከተገመተው የአምስት ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር አንፃር ሲታይ ግን ዝቅተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተገምግሟል።
በኢትዮጵያ ለሚሰማሩ የግብፅ ባለሃብቶች ተገቢውን ድጋፍ እንደሚያገኙ ነው ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በውይይቱ ላይ ማረጋገጫ ሰጥተዋል፡፡
በውይይቱ ላይ የግብፅ ፕሬዝዳን አብዱልፋታህ አል ሲሲ ሃገራቱ በዲፕሎማሲ መስክ እያሳዩት ያለውን ግንኙነት በኢኮኖሚ መስክም እንዲጠናከር ግብፅ ፍላጎቷ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)