Tuesday, June 30, 2015

ፖሊስና አቃቤ ህግ በኢህአዴግ ላይ ሰልፍ መውጣታቸውን ቀጥለዋል! – ጌታቸው ሺፈራው -

police brutalityአይ ኤስን ለመቃወም ከተጠራው ሰልፍ በኋላ ፖሊስና አቃቤ ህግ በየ ችሎቱ ኢህአዴግ ላይ ሰልፍ በመጥራት ስድብ እያዘነቡበት ነው፡፡ በሚያዝያ 14ቱ ሰልፍ ላይ በቦታው ያልነበሩት የሰማያዊ፣ የቀድሞው አንድነትና የቀድሞው መኢአድ አባላትና አመራሮች እንዲሁም ሌሎች ወጣቶችን ያስሩና እነዚህ ወጣቶች ያላሉትን ክስ ብለው ያቀርባሉ፡፡ ይህ ክስ ደግሞ ለእነሱ የሰልፍ መፈክር መሆኑ ነው፡፡ የስድብ ውርጅብኝ፡፡ በቃ ችሎት የቁጭት መውጫቸው ሆኗል ማለት ይቻላል!
ፖሊስና አቃቤ ህግ በየ ችሎቱ (ሰልፍ እንበለው) ከሚያሰሟቸው መፈክሮች መካከል፡-
• ኢህአዴግ ሌባ ነው!
• ጠንካራ እንጅ ጠንጋራ መሪ አንፈልግም
• ቴዎድሮስ ለህዝብ ሞተ፣ መለስ ደንግጦ ሞተ፣ ሀይለማሪያም በቁሙ ሞተ!
• እያዋረደን ያለው ወያኔ ነው!
• ወያኔ አሳረደን!
• ኢህአዴግ ቡሽቲ መንግስት ነው! (አሁን ይህም ክስ ላይ ይቀርባል! ዳንኤል ብርሃኔን መሰሉኝኮ)
• የወያኔ 24 አመት አገዛዝ ይበቃናል!
• የሀገር አበሳ የውጭ ሬሳ
• ኢህአዴግ….
• ኢህአዴግ….እና የመሳሰሉት ስድቦች (ማለቴ መፈክሮች) ይገኙበታል!
አንድ ጓደኛዬ በተደጋጋሚ ችሎት ላይ ተገኝቶ አቃቤ ህግና ፖሊስ ‹‹ጠንካራ እንጅ ጠንጋራ መሪ አንፈልግም!›› ብለዋል እያሉ መፈክር ሲያሰሙ ያዳምጥና ‹‹በዚህ መፈክር የተከሰስኩት እኔ ብሆን መከላከያ ምስክር የማደርጋቸው ጠንካራ መሪ አይደሉም የሚባሉትን ሰው ነበር፡፡ ችሎት ላይ አቅርቤ እሺ ጠንካራ ናቸው ወይንስ…. እላቸው ነበር›› ብሏል፡፡
ዛሬ እነ ቴዎድሮስ አስፋው ላይ ደግሞ ‹‹ቴዎድሮስ ለህዝብ ነው የሞተው፣ መለስ ደንግጦ ነው የሞተው፣ ኃይለማሪያም በቁሙ ነው የሞተው›› ብላችኋል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡ መርዶ እኮነው ስንሰማው የዋልነው፡፡ ለፖሊስና ለአቃቤ ህግ ደግሞ የብሶት መፈክር መሆኑ ነው! ሌላው ቀርቶ ‹‹ቴዎድሮስ ለህዝብ ነው የሞተው!›› የሚለውም የክስ መዝገብ ላይ መስፈሩ ያሳፍራል፡፡ ለማንኛውም በዚህ ክስ ላይም ያ ጓደኛዬ መቃወሚያ ቢጤ አቅርቧል፡፡
‹‹መለስ ደንግጦ አልሞተም ስትሉ፣ ኃይለማሪያም በቁሙ አልሞተም ስትሉ የሀኪም ማስረጃ አምጡ!›› እላቸው ነበር ብሏል! ያው የመለስን ገዳይ በቅርብ አላገኘውም ብሎ ይሆናል!
ጌታቸው ሺፈራው

” እንግሊዝ ግንቦት ሰባትን በሽብርተኝነት አልፈረጀችም፡፡ “ግሬግ ዶሪ፣ በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር -

ነገር ግን እንግሊዝ ግንቦት ሰባትን በሽብርተኝነት አልፈረጀችም፡፡ ግሬግ ዶሪ፣ በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር‹‹ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ያገኘነው መልዕክት የአውሮፓ ኅብረት ምርጫውን እንዲታዘብ ኢትዮጵያ ፍላጎት እንደሌላት ነው››
ግሬግ ዶሪ፣ በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር
አምባሳደር ግሬግ ዶሪ በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር ሲሆኑ፣ በተጨማሪም በጂቡቲ የእንግሊዝ አምባሳደር ናቸው፡፡ በአፍሪካ ኅብረትና በተመድ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ቋሚ ተወካይም ናቸው፡፡
ወደ ኢትዮጵያ ከመምጣታቸው በፊት በሃንጋሪ የእንግሊዝ አምባሳደር ሆነው አገልግለዋል፡፡ እ.ኤ.አ. ከ1989 እስከ 1992 ድረስ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ጉዳዮች አንደኛ ጸሐፊ በመሆንም በሃንጋሪ ታሪክ ብዙ እንቅስቃሴ የተደረገባቸውን ዓመታት በቅርበት ተከታትለዋል፡፡ እ.ኤ.አ. ከ1996 እስከ 2000 ድረስ በፓኪስታን፣ እ.ኤ.አ. ከ2000 ጀምሮ በሆንግ ኮንግ በተለያዩ የሥራ ኃላፊነቶች ያገለገሉት አምባሳደር ዶሪ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት እ.ኤ.አ. በ2011 ነው፡፡ አሥራት ስዩም በቅርቡ የተካሄደውን ጠቅላላ ምርጫ፣ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ መያዝና የእስር ሁኔታ፣ እንዲሁም የእንግሊዝ የንግድና ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎች በኢትዮጵያ ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ አምባሳደር ግሬግ ዶሪን አነጋግሯቸዋል፡፡
ሪፖርተር፡- በቅርቡ በኢትዮጵያ የተካሄደውንና ገዥው ፓርቲና አጋሮቹ የፓርላማውን ሁሉንም ወንበሮች ያሸነፉበትን ምርጫ እንዴት አዩት? ነፃ፣ ፍትሐዊና ተዓማኒ ነው ብለው ይገልጹታል?
አምባሳደር ግሬግ ዶሪ፡– በቅድሚያ ምርጫውን መታዘብ አለመቻላችን አሳዛኝ ነው፡፡ በምርጫ 97 እና በምርጫ 2002 ታዛቢ የነበረው የአውሮፓ ኅብረት ምርጫ 2007ን እንዲታዘብ አልተጋበዘም፡፡ የታዛቢ ልዑካን መላክ ከነበረብን ግብዣ ሊደርሰንና መንግሥት እንደሚተባበረን ማሳየት ነበረበት፡፡ መንግሥት የአውሮፓ ኅብረት ምርጫውን እንዳይታዘብ እንደሚፈልግ በግልጽ አሳይቷል፡፡ ባልተለመደ ሁኔታ ዲፕሎማቶችም ምርጫውን እንዳይታዘቡ ተከልክለዋል፡፡ ይሁንና የአፍሪካ ኅብረት የታዛቢዎች ልዑክ ውስጥ ዲፕሎማቶች እንዲካተቱ መደረጉን እናውቃለን፡፡ እኔ በግሌ በተለያዩ ቦታዎች ምርጫዎችን ታዝቤያለሁ፡፡ ከእነዚህም አንዱ በፓኪስታን ሩቅና ገጠራማ አካባቢ የተደረገው አንዱ ነው፡፡ አሁን ግን ባለመታዘባችን በምርጫው ምን እንደተከሰተ በቀጥታ መረጃው የለኝም፡፡ ውጤቱ በይፋ ሲገለጽ ጠብቀን አስተያየታችንን እንሰጣለን (ቃለ ምልልሱ ሲደረግ ውጤቱ በይፋ አልተገለጸም ነበር)፡፡ ከዚህ ውጪ ከምርጫው አስቀድሞ በነበረው የፖለቲካ ምኅዳር መጣበብ ላይ ግን ሥጋት ነበረን፡፡ አሁን ገዥው ፓርቲና አጋሮቹ መቶ በመቶ ፓርላማውን እንደሚቆጣጠሩ እየተሰማን ነው፡፡ በእኔ አስተያየት ይኼ ለዴሞክራሲ ጥሩ ነገር አይደለም፡፡ ይኼ እንደ ሰሜን ኮሪያ ባሉ አገሮች የሚከሰት ነገር ነው፡፡ በኢትዮጵያ ፓርላማ የተለያዩ አመለካከቶች ቢንሸራሸሩ ጥሩ ነበር፡፡
ይህ ማለት ግን በሥልጣን ላይ ያለው ፓርቲ ልማትን በተመለከተ እየሠራ ያለው ነገር መጥፎ ነው ማለት አይደለም፡፡ ልማት ላይ በአጠቃላይ ጥሩ ሥራ እየሠራ ነው፡፡ በዴሞክራሲ ግን ጤናማ የሚሆነው የተለያዩ አማራጭ ሐሳቦች ሲቀርቡ ነው፡፡ ባለፈው ፓርላማም ቢሆን ከ547 ወንበሮች ተቃዋሚዎች የተወከሉት በአንድ ግለሰብ ብቻ መሆኑ በቂ አይደለም፡፡ ወደፊት ፓርላማው ብዛት ያላቸውን የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ቢያቅፍ ኢትዮጵያ እያደገችና የዓለም አቀፍ ዴሞክራሲያዊ ማኅበረሰብ አባል ለመሆኗ ምልክት ይሆናል፡፡ በምርጫ ታዛቢ ስላልነበርን ስለተከሰቱ ግድፈቶች አስተያየት ለመስጠት አልችልም፡፡ ገዥው ፓርቲ መቶ በመቶ የፓርላማውን መቀመጫ የሚያሸንፍ ከሆነ፣ ድምፃቸውን ለተቃዋሚ ፓርቲዎች የሰጡ ዜጎች አገሪቱ እየሄደች ባለችበት አቅጣጫ ላይ የሚሰጡት አስተያየት ሊሰማ ይገባል፡፡ በርካታ ዜጎች ለተቃዋሚ ፓርቲዎች ድምፃቸውን እንደሰጡ አምናለሁ፡፡ ስለዚህ ድምፃቸው እስከ ከፍተኛ ውሳኔ ሰጪ አካላት ድረስ ሊሰማ ይገባል፡፡ ይኼ በአገሪቱ ዘላቂ መረጋጋት ለማምጣት ጠቃሚ ነው፡፡
ሪፖርተር፡- ይሁንና የኢትዮጵያ መንግሥት የሚለው የአውሮፓ ኅብረት የምርጫ ልዑክ እንዲልክ ግብዣ ያልላከው ኅብረቱ የገንዘብ እጥረት እንዳለበት በመግለጹ ነው፡፡ ይኼ ትክክል አይደለም?
አምባሳደር ግሬግ ዶሪ፡– በዚህ ዓመት በአፍሪካ ብቻ 17 ወይም 18 ምርጫዎች ተካሂደዋል፡፡ በትክክልም ሁሉንም ምርጫዎች ለመታዘብ የገንዘብ እጥረት አለብን፡፡ በኢትዮጵያ ግን ይህን ለመወሰን ግብዣ ስላልደረሰን ዕድሉንም አላገኘንም፡፡ እነዚህን ነገሮች ለማቀድ ጊዜ ያስፈልጋል፡፡ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ያገኘነው መልዕክት የአውሮፓ ኅብረት ምርጫውን እንዲታዘብ ኢትዮጵያ ፍላጎት እንደሌላት ነው፡፡ ለዚህም ነው ያለንን ሀብት ለሌሎች ምርጫዎች ለማዋል ያቀድነው፡፡ ስለዚህ ጉዳዩ መንግሥት በጣም አቅሎ በሚያምታታ ሁኔታ እንደገለጸው አይደለም፡፡ የተወሳሰበ ነው፡፡ ውሳኔያችን የተመሠረተው በገንዘብ እጥረት አልነበረም፡፡ ከምርጫ 97 እና ከምርጫ 2002 በኋላ የአውሮፓ ኅብረት ለኢትዮጵያ የተለያዩ የማሻሻያ ሐሳቦችን ሰጥቶ ነበር፡፡ መንግሥት በጠቅላላ ሐሳቦቹን ውድቅ አድርጓል፡፡ እርግጥ ነው ምርጫ ያካሄደው አገር ሐሳቦችህን የማይቀበል ሲሆን፣ ከሌሎች የአውሮፓ ኅብረትን መታዘብ ጠቃሚነት የተቀበሉ አገሮች ጋር ለመሥራት ማሰብ አይቀርም፡፡
ሪፖርተር፡- ተቃዋሚ ፓርቲዎች የምርጫውን ውጤት ለመቀየር ያደረጉትን አስተዋጽኦ እንዴት አዩት? የፖለቲካ ተንታኞች ከምርጫ 97 ጋር ሲነፃፀር ተቃዋሚ ፓርቲዎች የተከፋፈሉና ደካማ በመሆናቸው ለተገኘው ውጤት ተጠያቂ እንደሆኑ ይከራከራሉ፡፡ የእርስዎ አስተያየት እንዴት ነው? 
አምባሳደር ግሬግ ዶሪ፡- ይኼ በትክክልም የችግሩ አንድ አካል ነው፡፡ ሌላው ችግር የምርጫ ሥርዓቱ የሚከተለው የ‘አንደኛ አላፊ’ የምርጫ ሥርዓት ነው፡፡ እርግጥ ይህ ሥርዓት በእንግሊዝም ተግባራዊ የሚደረግ ነው፡፡ በዚህ ሥርዓት ለተቃዋሚዎች የተሰጡ በርካታ ድምፆች ወደ ፓርላማ መቀመጫ አይቀየሩም፡፡ የተመጣጣኝ ውክልና የምርጫ ሥርዓት ግን ይህን ያስችል ነበር፡፡ ነገር ግን እንደተባለው ተቃዋሚ ፓርቲዎች የተከፋፈሉ መሆናቸውንም ተመልክቻለሁ፡፡ ስለዚህ በቀጣይ ዓመታት ጉዳዩን እንደገና ሊመለከቱትና አብረው መሥራታቸው ውጤቱን የሚያሻሽለው ከሆነ ሊያስቡበት ይገባል፡፡ ፓርቲዎች በበዙ ቁጥር የመራጮችን ድምፅ ስለሚቀራመቱ የተሻለ ውጤት የማግኘት ዕድላቸውን ያጠባል፡፡
ሪፖርተር፡- ስለዚህ የ‘አንደኛ አላፊ’ የምርጫ ሥርዓት ለኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ ተስማሚ አይደለም እያሉ ነው?
አምባሳደር ግሬግ ዶሪ፡- የትኛው ሥርዓት ይሻላል የሚለውን የመወሰን ሥልጣን የአገሮቹ ነው፡፡ ሥርዓቱን እስከመረጥክ ድረስ አክብሮ መሥራትም ይጠበቅብሃል፡፡ አንድን ቡድን ተጠቃሚ ለማድረግ ሥርዓት መቀየር የለብህም፡፡ ይሁንና በአንድም ሆነ በሌላ የተለያዩ ሐሳቦች እንዲሰሙ ግን ዕድል መፍጠር ያስፈልጋል፡፡ ይህ ካልተፈጠረ ለአገር አለመረጋጋት ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያ ይኼን የምርጫ ሥርዓት ትቀበል ለማለት አልችልም፡፡ መንግሥት የተለያዩ ሐሳቦችንና አመለካከቶችን ለማስተናገድ መንገድ መፈለግ ግን አለበት፡፡
ሪፖርተር፡- ባለፈው ዓመት መንግሥትዎ ለደኅንነትና ለአስተዳደር መድቦት የነበረውን የገንዘብ ዕርዳታ ወደ ሌሎች ፕሮግራሞች አዘዋውሯል፡፡ የእንግሊዝ ዓለም አቀፍ የልማት ትብብር መሥሪያ ቤት እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ሂዩማን ራይትስ ዎች ኢትዮጵያ ላይ ባቀረበው ሪፖርትና በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ መታሰር ምክንያት እንደሆነ ይነገራል፡፡ ይህ ምን ያህል እውነት ነው?
አምባሳደር ግሬግ ዶሪ፡– የእንግሊዝ ዓለም አቀፍ የልማት ትብብር መሥሪያ ቤት ፕሮግራሞች የሚመሠረቱት ሰብዓዊ መብትን ጨምሮ ከአገሮቹ ጋር ባለን የሁለትዮሽ የአጋርነት ግንኙነት መርህ እንጂ፣ በግለሰብ ዲፕሎማሲያዊ ጉዳዮች ላይ አይደለም፡፡ ስለዚህ ከአቶ አንዳርጋቸው ጉዳይ ጋር የተገናኘ አይደለም፡፡ የእንግሊዝ መንግሥት ከመሠረታዊ አገልግሎቶች አቅርቦት ፕሮግራም በመውጣት ይበልጥ ኢኮኖሚያዊ ልማት ላይ ያተኮሩ እንቅስቃሴዎችን የመደገፍ የቆየ ሐሳብ ነበረው፡፡ ምክንያቱም ይኼ ዘለቄታዊ ለውጥ ለማምጣት ይበልጥ ዋጋ አለው፡፡ ውሳኔው ከዚህ ሐሳብ የመነጨ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ባለው የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች አፈጻጸም ላይ ያለን ሥጋት እዚህ ውሳኔ ላይ እንድንደርስ አንዱ ምክንያት ነው፡፡ ነገር ግን ውሳኔያችንን ያፋጠኑ ሌሎች በርካታ ምክንያቶችም ነበሩ፡፡
ሪፖርተር፡- አቶ አንዳርጋቸው የእንግሊዝ ዜጋ በመሆናቸው መንግሥትዎ ከኢትዮጵያ አቻው ጋር የግለሰቡን ዕጣ ፈንታ በተመለከተ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ሲያደርግ ነበር፡፡ አሁን አቶ አንዳርጋቸው በምን ሁኔታ ላይ ይገኛሉ?
አምባሳደር ግሬግ ዶሪ፡– በመጀመሪያ በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ ላይ ለመናገር በጣም የተገደብኩ መሆኔን ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡ ለአቶ አንዳርጋቸው ዲፕሎማሲያዊ ዕርዳታ እያደረግን ሲሆን፣ ከቤተሰባቸውም ጋር ቅርብ ግንኙነት አለን፡፡ በዲፕሎማሲያዊ ዕርዳታችን ላይ ስላሉ ዝርዝር ጉዳዮች አስተያየት መስጠት አልፈልግም፡፡ ምክንያቱም ለቤተሰቡ ያልተገለጸን ነገር ለሌላ አካል መናገር ስለማያስፈልግ ነው፡፡ አቶ አንዳርጋቸው ከተያዙ በኋላ ሦስት ጊዜ አይቻቸዋለሁ፡፡ ከዚህ ውጭ ምን ማለት እችላለሁ? በተገቢው ሁኔታ ስለመያዛቸው ለማረጋገጥ አልቻልንም፡፡ የዲፕሎማሲያዊ ጉብኝቱ ዋነኛ ዓላማም ይኼው ነው፡፡ ኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን የሚገዛውን የቪየና ዓለም አቀፍ ስምምነት ፈራሚ አይደለችም፡፡ ለምን እንዳልፈረመች ባይገባኝም አንድ ቀን ፈራሚ እንደምትሆን ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ይሁንና የዓለም አቀፍ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ቃል ኪዳን ፈራሚ በመሆኗ፣ የእስረኞች አያያዝን በተመለከተ ዓለም አቀፍ ደረጃ የማሟላት ግዴታ አለባት፡፡
ሪፖርተር፡- ነገር ግን አቶ አንዳርጋቸው የእንግሊዝ ዜጋ በመሆናቸው እንግሊዝ በእሳቸው አያያዝ ላይ ልዩ ፍላጎት የላትም?
አምባሳደር ግሬግ ዶሪ፡- አንድ የእንግሊዝ ዜጋ ውጭ አገር ሲታሰር ሥጋቶችና ልዩ ግዴታዎች አሉብን፡፡ የእንግሊዝ ሕዝብ እነዚህ ዜጎች በአግባቡና ዓለም አቀፍ መሥፈርቱን በጠበቀ መንገድ መያዛቸውን እንድናረጋግጥ ይጠብቃል፡፡ ከዚህ ውጪ በአጠቃላይ በሰብዓዊ መብት ላይ ሥጋት አለኝ፡፡ የሰብዓዊ መብት ምክር ቤትን ጨምሮ በተለያዩ ዓለም አቀፍ አካላት እንቅስቃሴ ላይ እንሳተፋለን፡፡ ስለዚህ በሌላ አገር ዜጎች የእስር አያያዝ ላይ ችግር ካለ እሱም ቢሆን ያሠጋናል፡፡ ሥጋቶቻችን የምንገልጸው መሠረታዊ መሥፈርቶች እንዳልተሟሉ ስናስብ ነው፡፡
ሪፖርተር፡- ለአቶ አንዳርጋቸው እነዚህ መሠረታዊ መሥፈርቶች እንደተሟሉላቸው መናገር ይቻላል? በተገቢው ሁኔታ እንክብካቤ እየተደረገላቸው ነው?
አምባሳደር ግሬግ ዶሪ፡- በዚህ ጉዳይ ላይ ለመናገር ገደብ ስላለብኝ አስተያየት ለመስጠት ፈቃደኛ አይደለሁም፡፡
ሪፖርተር፡- አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች እንግሊዝ ለዜጋዋ ያልታገለችው አቶ አንዳርጋቸው በነበራቸው የፖለቲካ ተሳትፎ የተነሳ አማራጭ ስላልነበራት ነው ይላሉ፡፡ የአቶ አንዳርጋቸው የፖለቲካ እንቅስቃሴ ምን ዓይነት ተፅዕኖ ፈጥሮባችኋል?
አምባሳደር ግሬግ ዶሪ፡- በአጠቃላይ አቶ አንዳርጋቸው በኢትዮጵያ ከመያዛቸው በፊት ምን እየሠሩ እንደነበር አስተያየት መስጠት አልፈልግም፡፡ ምክንያቱም ይኼ ጉዳይ ወደ ችሎት ሊያመራ ስለሚችል ነው፡፡ ነገር ግን ዲፕሎማሲያዊ ጉብኝት አቶ አንዳርጋቸው ይሠሩ ከነበረው ነገር ጋር ግንኙነት የለውም፡፡ ምንም አደረጉ ምንም ዲፕሎማሲያዊ አገልግሎት አይነፈጉም፡፡
ሪፖርተር፡- ስለዚህ ዜጎቻችሁ በከባድ የወንጀል ድርጊት የሽብር እንቅስቃሴዎችን ጨምሮ መጠርጠራቸው በአቀራረባችሁ ላይ ምንም ልዩነት አያመጣም እያሉኝ ነው?
አምባሳደር ግሬግ ዶሪ፡-ዜጋውን ከመጎብኘት፣ የጤና ሁኔታውን ከመከታተልና ለመኖር አስፈላጊ የሆኑ መሠረታዊ ፍላጎቶች መሟላታቸውን ከማረጋገጥ አኳያ ግለሰቡ የሠራው ሥራ ቅንጣት ልዩነት አያመጣም፡፡ ከዚያ በተረፈ በየትኛውም ሁኔታ የሞት ቅጣትን እንቃወማለን፡፡ የሞት ቅጣት ተግባራዊ የሚያደርጉ አገሮችን እንቃወማለን፡፡ የሞት ቅጣት ምንም ዓይነት ጥሩ የሆነ የሚያሳካው ዓላማ አለው ብለን አናምንም፡፡
ሪፖርተር፡- በቅርቡ አሜሪካ በኢትዮጵያ ፓርላማ በሽብርተኝነት የተፈረጁ ቡድኖችን እንደምትቃወም በአደባባይ ገልጻለች፡፡ ከእነዚህ አንዱ አቶ አንዳርጋቸው አባል የነበሩበት ግንቦት ሰባት ነው፡፡ በእነዚህ ድርጅቶች ላይ የእንግሊዝ አቋም ምንድን ነው?
አምባሳደር ግሬግ ዶሪ፡- አባባሉን በትክክል ስለማየቴ እርግጠኛ አይደለሁም….
ሪፖርተር፡- ይኼንን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትር ዊንዲ ሼርማን በቅርቡ ከሰጡት መግለጫ መረዳት ይቻላል ብዬ ነው…
አምባሳደር ግሬግ ዶሪ፡– ዊንዲ ሼርማን አሜሪካ ግንቦት ሰባትን አትደግፍም ነው ያሉት፡፡ ይኼን እኔም አረጋግጥልሃለሁ፡፡ ግንቦት ሰባትንም ሆነ መሰል ቡድኖችን እንግሊዝ አትደግፍም፡፡ ነገር ግን እንግሊዝ ግንቦት ሰባትን በሽብርተኝነት አልፈረጀችም፡፡ ምክንያቱም በእንግሊዝ ዓውድ አንድን ቡድን ሽብርተኛ ብሎ ለመፈረጅ የሚያስችል ማስረጃ አላየንም፡፡ ቢሆንም ሕጋዊ መንግሥትን ለመገርሰስ የሚሠራ ማንኛውንም ቡድን አንደግፍም፡፡ የዊንዲ ሼርማን መግለጫ በተለያዩ ሚዲያዎች በትክክል እንዳልተንፀባረቀ ግን እረዳለሁ፡፡ በትክክል ምን እንዳሉ አላውቅም፡፡ በጉዳዩ ላይ አሜሪካ ያላት ፖሊሲ ግን ከእንግሊዝ ፖሊሲ መሠረታዊ ልዩነት እንደሌለው ግን አምናለሁ፡፡
ሪፖርተር፡- የሁለትዮሽ ግንኙነትን በተመለከተ ባለፉት አራትና አምስት ዓመታት እንግሊዝ ለኢትዮጵያ በሰጠችው የዕርዳታ መጠን ተቀዳሚዋ አገር ነች፡፡ ነገር ግን ይኼ እያደጉ ያሉ እንደ ቻይናና ቱርክ ካሉ ኢኮኖሚዎች ጋር ሲነፃፀር በንግድና በኢንቨስትመንት ዘርፎች በሚደረግ ተሳትፎ የሚገለጽ አይደለም፡፡ ይህን ያላደረገችው ለምንድነው?
አምባሳደር ግሬግ ዶሪ፡– በመጀመርያ ደረጃ የልማት ድጋፍ የምናደርገው ሌሎቹ አገሮች እንደሚያደርጉት የእንግሊዝን ቢዝነስ ለማስፋፋት አይደለም፡፡ ዕርዳታውን በሚቀበሉ አገሮች የቢዝነስና ኢንቨስትመንት ከባቢ ሁኔታው በአጠቃላይ እንዲሻሻል ለማገዝ እንጥራለን፡፡ ይሁንና እኛ በምናደርገው ዕርዳታ የተነሳ የእንግሊዝ ድርጅቶች ከኢትዮጵያ መንግሥት የፕሮጀክት ኮንትራቶች እንዲያገኙ አናደርግም፡፡ እርግጥ አንዳንድ የእንግሊዝ ኩባንያዎች ከኢትዮጵያ ጋር ረዥም ጊዜ ያስቆጠረ ግንኙነት አላቸው፡፡ ከአምስትና ከስድስት ዓመት በፊት ግን እንግሊዝ በኢትዮጵያ የነበራት የኢንቨስትመንት መጠን አነስተኛ በመሆኑ ላይ እስማማለሁ፡፡ ከዚያ በኋላ ባሉት ዓመታት ግን በከፍተኛ መጠን ተሳትፎ እያደረጉ ነው፡፡ አሁን እንደ ዲያጆና ዩኒሊቨር ያሉ ኩባንያዎች የኢትዮጵያን ገበያ ተቀላቅለዋል፡፡ አስፈላጊው የሕግ ማዕቀፍ ከተጠናቀቀ በታዳሽ ኢነርጂ ላይ የመሥራት ፍላጎት ያላቸው በርካታ የእንግሊዝ ኩባንያዎች ገበያውን ይቀላቀላሉ፡፡
በነዳጅ ፍለጋና በማዕድን ማውጣት ዘርፎች ላይ ብዙ ካፒታል ፈሰስ ያደጉ የእንግሊዝ ኩባንያዎችም ለኢኮኖሚው ትልቅ አስተዋጽኦ የሚያደርግ ስኬት እንደሚያስመዘግቡ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ የጨርቃ ጨርቅ፣ የቡናና የምግብ ምርቶችን ከኢትዮጵያ የሚገዙ ታዋቂ የእንግሊዝ ኩባንያዎችም ይመጣሉ፡፡ ሌሎች ፍላጎት ያላቸው ኩባንያዎችም እንዲመጡ ለመሳብ እየጣርን ነው፡፡ እርግጥ እነዚህ ኩባንያዎች ኢትዮጵያን በአፅንኦት ማየትና አስቀድመው ገበያው ውስጥ የገቡ ኩባንያዎች እንዴት እየተስተናገዱ እንደሆነ ይገመግማሉ፡፡ አስቀድመው ገበያው ውስጥ የገቡ የእንግሊዝ ኩባንያዎች የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ብሩህ ተስፋ አለው ብለው ያምናሉ፡፡ የኢትዮጵያ ገበያ በዓለም ላይ ቀላል የሚባል እንዳልሆነ ቢገነዘቡም፣ በትዕግሥት በረዥም ጊዜ ለውጥ ለማምጣት ዝግጁ ናቸው፡፡ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የእንግሊዝ ኢንቨስትመንት ወደፊት እያደገ እንደሚመጣ ታያላችሁ፡፡
ሪፖርተር፡- የእንግሊዝ ኩባንያዎች እያደገ የመጣውን የአፍሪካ ገበያ እንዴት ያዩታል? በርካታ ተሳታፊዎች ስላሉ ይህ የአፍሪካ ገበያ ቀጣዩ የውድድር ቀጣና ይሆናል ብለው ይወስዱታል?
አምባሳደር ግሬግ ዶሪ፡- አዎ በዚያ ደረጃ መረዳት ይቻላል፡፡ በታሪክም ከታየ እንግሊዝ በአፍሪካ አኅጉር ቀዳሚ ኢንቨስተር ነች፡፡ አዳዲስ ኢንቨስትመንቶችን ከተመለከትን ግን ከአዳዲሶቹ ኢንቨስተሮች ከነ ቻይና፣ ቱርክና ህንድ ጋር ሲነፃፀር የእንግሊዝ ድርሻ በጣም አነስተኛ ነው፡፡ አፍሪካ የወደፊቱ የዕድገት ማዕከል ስለሚሆን ፍላጎት አለን፡፡ አንዳንዴ ከሌሎች አገሮች ጋር እንደምንወዳደር ይታየናል፡፡ በሌላ በኩል ግን ከሌሎች አገሮችና ከኩባንያዎቻቸው ጋር አብረን እንደምንሠራ እናስባለን፡፡ በኢትዮጵያ ግን ለውድድር አልደረስንም፡፡ በቂ ዕድሎች አሁንም አሉ፡፡ ከሌሎች አገሮች ኩባንያዎች ጋር በትብብር ለመሥራት እያሰብን ነው፡፡ ይኼ በኢትዮጵያ እንደሚሳካ አስባለሁ፡፡
ሪፖርተር፡- የሕግ ቁጥጥርን በተመለከተና በሌሎችም ጉዳዮች ለውጥና መሻሻል የሚያስፈልጋቸው የትኞቹ ናቸው ብላችሁ ታስባላችሁ?
አምባሳደር ግሬግ ዶሪ፡- የእንግሊዝ ኩባንያዎች ብቻ ሳይሆኑ ሌሎችም ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ኩባንያዎች ቢሮክራሲውን ለማለፍ ብዙ ጊዜ ያጠፋሉ፡፡ ይኼ ውድ ጊዜ ኢንቨስትመንቱን ለማሳደግ፣ የሥራ ዕድል ለማስፋትና የቴክኖሎጂ ሽግግርን ለማቀላጠፍ ጥቅም ቢውል መልካም ነበር፡፡ ኢኮኖሚው ጤነኛ እንዲሆን የሕግ ቁጥጥር መደረጉ ተገቢ መሆኑን እንረዳለን፡፡ ይኼ ቁጥጥር ሁሉም በቀላሉ የሚረዳው ግልጽ የሆነ ሥርዓት ለመፍጠር ይረዳል፡፡ ነገር ግን የቁጥጥር ሥርዓቱ በተቻለ መጠን ቀላል ቢሆን ይመረጣል፡፡ በእኔ አረዳድ የኢትዮጵያ የቁጥጥር ሥርዓት ከመጠን ያለፈ ነው፡፡ አንዳንድ ድንጋጌዎች መንግሥትንም፣ ኢንቨስትመንትንም ሆነ ሕዝቡን በአጠቃላይ የሚጠቅሙ አይደሉም፡፡ አንድ አካል እነዚህን ድንጋጌዎች በድጋሚ በማየት የትኞቹ ጠቃሚ እንደሆኑና የትኞቹ እንደማያስፈልጉ የመለየት ሥራ የሚያከናውን ይመስለኛል፡፡ አዳዲስ ድንጋጌዎች ሲወጡም በቢዝነስ ላይ የሚያደርሱት አሉታዊ ተፅዕኖ የግድ ግምት ውስጥ መግባት አለበት፡፡ በአሁኑ ወቅት በሥራ ላይ ያሉ አንዳንድ ደንቦች በቢዝነስ ዕድገት ላይ ጫና እየፈጠሩ ነው፡፡
ሪፖርተር፡- የቪዛና የጉዞ ደንቦች እዚህ ውስጥ ይካተታሉ? በቅርቡ በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ለመንግሥት ኃላፊዎች ቅሬታ ማቅረብዎ ተዘግቧል፡፡ 
አምባሳደር ግሬግ ዶሪ፡– የእንግሊዝ የቪዛ ሒደት በዓለም ላይ ቀላሉ እንዳልሆነ እረዳለሁ፡፡ ነገር ግን ግልጽነት ያለው መሆኑ የሚያስመሰግን ነው፡፡ በሒደቱ ላይ ለውጥ የምናደርግ ከሆነ ለውጡን አስቀድመን የምናስተዋውቅ ሲሆን፣ ሰዎችም ተረድተው በአዲሱ አሠራር እንዲስተናገዱ እናደርጋለን፡፡ ወደ እንግሊዝ ለመሄድ ቪዛ የሚጠይቁ በርካታ ሰዎች አሉ፡፡ ማመልከቻውን በትክክል የሞሉና ትክክለኛ መረጃ ያቀረቡ ሰዎች ይገኛሉ፡፡ ሌሎች በርካታ ሰዎች በተለያዩ ምክንያቶች እንግሊዝ ከሄዱ በኋላ ስለማይመለሱ ቪዛ የማያገኙ ሰዎችም አሉ፡፡ ሰነዶቻቸውን አጥፍተው ከተፈቀደው ጊዜ በላይ የሚቆዩ አሉ፡፡ ስለዚህ ቪዛ ከመስጠታችን በፊት ጠንካራ ቁጥጥር ማድረጋችን ፖለቲካዊ ተቀባይነት አለው፡፡ ከወራት በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ የተፈጠረው ነገር በድንገት የቪዛ ሒደቱ የሚያስወጣው ወጪ ከመጨመሩ ይጀምራል፡፡ ወጪው በመጨመሩ ላይ ይኼን ያህል ችግር የለብኝም፡፡
ነገር ግን አዳዲሶቹ ደንቦችና መመርያዎች ግልጽ ስላልነበሩ በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች የሚገኙ ዜጎቻችን በተለያዩ መንገዶች ነው የተረዷቸው፡፡ በድንገት ለቢዝነስ ሰዎች ይሰጥ የነበረው የሦስት ወራት ቪዛ ወደ አንድ ወር ቪዛ ተቀየረ፡፡ በተጨማሪ የቪዛ ማመልከቻው ቀን የቪዛ ቀን ተደርጎም ተወሰደ፡፡ በመሆኑም እዚህ በመጡ በቀናት ጊዜ ውስጥ መመለስ አለባቸው፡፡ የውጭ ኢንቨስትመንት ለመሳብ ለምትጥር አገር ይኼ ችግር ፈጣሪ ነው፡፡ በዚህ ላይ እንግሊዝ ዲፕሎማሲያዊ ፓስፖርት ለእያንዳንዱ ሰው የምትሰጥ አገር አይደለችም፡፡ ከፍተኛ ባለሥልጣኖቻችንና የፓርላማ አባሎቻችን ዲፕሎማሲያዊ ፓስፖርት የላቸውም፡፡ ስለዚህ ባለሥልጣኖቻችንም ለሥራ ሲመጡ በእነዚህ ግራ አጋቢ የቪዛ ደንቦች የተነሳ ችግር እየገጠማቸው ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ይኼ ችግር እንደሚቀረፍና ወደፊት ለቢዝነስ በተመቸ አኳኋን እንደሚስተካከል ቃል ገብተውልናል፡፡
ሪፖርተር፡- ምናልባትም በአፍሪካ አኅጉር የመጀመሪያው ኤምባሲ የሆነው የእንግሊዝ ኤምባሲ የቪዛ ማዕከሉን ወደ ደቡብ አፍሪካ አዛውሯል፡፡ የውሳኔው አመክዮ ምንድነው?
አምባሳደር ግሬግ ዶሪ፡– በከፊል ከወጪና ከደኅንነት ጋር በተያያዘ ምክንያት ነው፡፡ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የቪዛ ሒደቱን በየአገሮች ከማድረግ በማዕከል ለመሥራት ወስነናል፡፡ በአፍሪካ ፕሪቶሪያ ከተማ ብቻ ነው፡፡ በአዲስ አበባ በኢንተርኔት ማመልከቻ የሞሉ ሰዎች ፓስፖርት የሚሰጡበት ማዕከል አለን፡፡ ነገር ግን ፓስፖርቱ ፕሪቶሪያ ሄዶ መመለስ አለበት፡፡ በመደበኛው አሠራር ይኼ እስከ ሦስት ሳምንታት ሊወስድ ይችላል፡፡ ይኼ የአሠራር ለውጥ ከኢትዮጵያ ጋር የተገናኘ አይደለም፡፡ በመላው ዓለም አሠራራችንን በማዕከል ለማድረግ ስለወሰንን ብቻ ነው፡፡

በኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች የሚቀርቡት የፖለቲካ ክሶች ከጊዜ ወደ ጊዜ አስቂኝ እየሆነ ነው -

በኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች የሚቀርቡት የፖለቲካ ክሶች ከጊዜ ወደ ጊዜ አስቂኝ እየሆነ ነው።ከዚህ ቀደም በ1997 ምርጫ ወቅት በቅንጅት መሪዎች፣ በጋዜጠኞችና በሲቪክ ተቋማት መሪዎች ላይ የቀረበው ክስ ፣ 24 ሰአታት አስቂኝ ፊልም የሚል ስያሜ ተሰጥቶት ነበር። በፍርድ ቤቱ የነበረውን ሁኔታ ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና የቃሊቲው መንግስት በሚል ርእስ ዘርዝሮ ማቅረቡ ይታወቃል። በቅርቡ አይ ኤስ ኤስ የተባለው አሸባሪ ድርጅት በ30 ኢትዮጵያውያን ላይ የወሰደውን ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ ለማውገዝ መንግስት በጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ተፈጥሮ የነበረውን ተቃውሞ መርተዋል፣ በተቃውሞው ተሳትፈዋል እየተባሉ በእስር በሚሰቃዩ ወጣቶች ላይ የሚደርሰው ክስም እንዲሁ ፈገግ እያሰኘ ነገር ግን በዚያው ልክ እያሳዘነና አገራችን የገባችበትን የወርደት ደረጃ እያመላከተን ነው። ቴዎድሮስ አስፋው ፣ ያሬድ ደመቀና አንዋር ከድር በተባሉ ወጣቶች ላይ የቀረበው ክስ እንዲህ ይላል ” ተከሳሽ የሃሰት ወሬዎችን በማውራት ጥላቻና የፖለቲካ ሁከት ለመቀስቀስ በማሰብ በ14/08/07 ዓም ከጧቱ 12 ሰአት ሲሆን በአዲስ አበባ ክ ከተማ በ01/02/03 በአሸባሪዎች ጥቃት ምክንያት ተጠርቶ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ሰዎችን በመሰብሰብ ” መለስ የሞተው ደንግጦ ነው፣ ሃይለማርያም ደሳለኝ በቁሙ የሞተ ነው” የሚል ሃሰተኛ ወሬዎችን በማውራት ሁከት መቀስቀስ ወንጀል ተከሷል። 

Thursday, June 25, 2015

የፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የኢትዮጵያ የጉብኝት በሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ዘንድ ተቃውሞ አስነሳ -

የፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የኢትዮጵያ የጉብኝት በሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ዘንድ ተቃውሞ አስነሳበቀጣዩ ወር በኢትዮጵያ ጉብኝት የሚያደርጉት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ከተለያዩ አለም አቀፍ ተቋማት ተቃውሞ እንደገጠማቸው የእንግሊዙ ዘጋርዲያ ጋዜጣ የተለያዩ አካላትን ዋቢ በማድረግ ዛሬ ረቡእ ዘገበ።
አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ፕሬዚዳንቱ በሰብአዊ መብት ረገጣና አፈና የምትታወቅ ሃገርን ለመጎብኘት መወሰናቸው ተገቢ እንዳልሆነ በመግለጽ ላይ መሆናቸውንም ጋዜጣው አስነብቧል።
የፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ የኢትዮጵያ ጉብኝት ለሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች አስደንጋጭ ዜና ሆኗል ያለው የእንግሊዙ ዘ ጋርዲያን ጋዜጣ ተቋማቱ የኦባማ ጉብኝት ጨቋኝ ለሆነው የኢትዮጵያ መንግስት የተሳሳተ መልእክት ሊያስተላልፍ እንደሚችል ስጋት እንዳደረባቸው አመልክቷል።
የአሜሪካ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሬዚዳንቱ የምስራቅ አፍሪካ ጉብኝት በቀጠናው ስላለው የኢኮኖሚያዊ እንዲሁም የዲሞክራሲ ተቋማትና የደህንነት ሁኔታዎች እንዴት መጠናከር እንዳለበት ያለመ መሆኑን ገልጿል።
ይሁንና ፕሬዚዳንቱ በሰብአዊ መብት ረገጣዋ የቆየ ታሪክ ያላትን ኢትዮጵያ መጎብኘታቸው ተገቢ አለመሆኑን በርካታ ድርጅቶች በመግለጽ ላይ መሆናቸውን ከእንግሊዙ ጋዜጣ በተጨማሪ ሌሎች አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃንም ዘግበዋል።
የሂዉማን ራይትስ ዎች ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ኬኔት ሮስ አሜሪካ በከፍተኛ ባለስልጣናት ደረጃ በኢትዮጵያ ጉብኝት ማካሄዱዋ ተገቢ አለመሆኑን እና በተዘዋዋሪ እውቅና የመስጠት ድርጊት ተደርጎ እንደሚታይ ገልጸዋል።
ፍሪደም ሃውስ የተሰኘ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጀት በበኩሉ ኢትዮጵያ ሁሉንም የተቃዋሚ ድርጅቶች ከፖለቲካ ተሳትፎ ዉጭ አድርጋ ባለበት ወቅት ፕሬዚዳንቱ በሃገሪቱ ጉብኝት ማድረጋቸው ተገቢ አለመሆኑን አስታውቀዋል።
በጉዳዩ ዙሪያ ሰፊ ረፖርትን ያወጣው ግሎባል ቮይስ የተሰኘ አለም አቀፍ ድርጅት ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ሊጎበኟቸው ካቀዷቸው ሃገራት መካከል የኢትዮጵያው ጉብኝት ከፍተኛ ተቃውሞ ማስነሳቱን ገልጸዋል።
ተቃውሟቸውን በማቅረብ ላይ የሚገኙት የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ፕሬዚዳንቱ ከጉብኝታቸው እንዲታቀቡ ጥያቄ በማቅረብ ላይ መሆናቸውንም ግሎባል ቮይስ በሪፖርቱ አመልክቷል።
በቀጣዩ ወር የምስራቅ አፍሪካ ሃገራት ጉብኝታቸውን የሚያድርጉት ኦባማ በአዲስ አበባ ቆይታቸው ከአፍሪካ ህብረት እና ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚመክሩ ይጠበቃል።

«በሚቀጥሉት አስር ዓመታት ለውጥ ይመጣል፤ የኤርትራን ወደብ እንጠቀማለን» – አርከበ እቁባይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዩ አማካሪ -

11541939_850345418354284_5434169820677150653_nአርከበ እቁባይ በየወሩ በሚታተመው “ዘመን መፅሄት” ይህን ተጠይቀው ነበር።
ዘመን፡- ግንቦት 20 ኤርትራንም ወደብም አሳጥቶናል የሚሉ ወገኖች አሉና ለእነዚህ ወገኖች ምላሽዎ ምንድን ነው?
ዶክተር አርከበ፡- ስለ ወደብ የሚያነሳ ነገር ግን ስለ ሕዝብ የማያነሳና የማያስብ ግለሰብ ወይም ቡድን ብቻ ነው ስለ መሬት የሚያነሳው። አገር ማለት ሕዝብ ነው። ስለሆነም ስለ ሕዝቦች በምናስብበት ጊዜ የኤርትራ ሕዝብ እንደ ሕዝብ ነው መወሰድ ያለበት። የኤርትራ ሕዝብ ምን ይፈልጋል? ለብዙ ዓመት በጦርነት ውስጥ የቆየ ሕዝብ ነው፤ ከ30 ዓመታት በላይ።
ከኢትዮጵያ መገንጠል እንፈልጋለን አሉ። ይሔንን በማየት ኢህአዴግ ጦርነቱ መራዘም የለበትም ብሎ ከድል በኋላ ዓመትም ሳይሞላው ሪፈረንደም እንዲካሔድ አደረገ። በዚያን ወቅት እንደ ኤርትራ ሕዝብ ተመሳሳይ ጥያቄ የነበራቸው ሕዝቦች ነበሩ፤ እንደ ዩጐዝላቪያ ያሉ።
እናም የዚያን ጊዜ የተደረገው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሪፈረንደሙን እንዲመራ ነበር። በዚህም 99 በመቶ የሚሆነው የኤርትራ ሕዝብ ነፃ ኤርትራን እንፈልጋለን አለ። ሕዝቡ ፍላጐቱን በድምፅ አረጋገጠ ማለት ነው። የሕዝቡ ፍላጐት ደግሞ መሟላት አለበት። ዴሞክራሲ ማለት ለሕዝብ መቆም ማለት ነው። ማነው የመጀመሪያ አገር ኤርትራን እንደ አገር የተቀበለው? የኢትዮጵያ መንግሥት ነበር። ያ ሆኖ ሰላም ማረጋገጥ ተችሏል።
ስለዚህ ያንን ያደረግነው ከሰላም፣ ከዴሞክራሲ፣ ከሕዝቦች መብት ማረጋገጥ አንፃር ነውና ይሔ መሆኑ ተገቢ ነው። ግን ዋናው ነጥብ ምንድንነው ወደብ ልማት ያመጣል ብለው የሚያስቡ ሰዎች ስለ ኢኮኖሚ ልማት ምንም የማይገባቸው ሰዎች ናቸው። በአካባቢያችን ሠፋፊ ወደብና የባህር ዳርቻ ያላቸው አገሮች እነማን ናቸው? አንዷ ሶማሊያ ናት። ሁለተኛዋ ማናት? ኤርትራ ናት። ሁለቱንም እንያቸው በጥፋት ሂደት ያሉ አገሮች ናቸው። ሶማሊያ ግን አሁን በተሻለ እንቅስቃሴና መረጋጋት ውስጥ ናት። ኢኮኖሚ ልማት በእነዚህ አገራት የለም።
ስለዚህ ልማትና ዕድገትን የሚያመጣው ወደብና የባህር ዳርቻ ነው የሚለው አስተሳሰብ ሕዝብን እንደ ሕዝብ ያለ ማየት አስተሳሰብ ምንጭ ነው። እኛ ወደብ መች ቸገረን፡፡ በጂቡቲና በበርበራ መጠቀም እንችላለን። የኤርትራም ሁኔታ መቀየሩ አይቀርም፡፡ አሁን ያለው ሁኔታ ለዘለዓለም ይኖራል ብለን አንገምትም። በእኔ ግምት በሚቀጥሉት አስር ዓመታት ውስጥ ለውጥ ይመጣል ባይ ነኝ። የኤርትራን ወደብ እንጠቀማለን። የኬንያን ወደብ መጠቀም እንችላለን። ከዚያ ወደ ኢትዮጵያ የሚገባ መስመር ለመገንባት ታቅዷል። የሱዳንንም እንጠቀማለን። ቢቻል ወደብ ቢኖረን ጥሩ ነበር ግን የሁሉም መቋጫና መፍትሔ እርሱ ነው ማለት አይደለም። የሚያመጣው መሠረታዊ ለውጥም የለም በእኔ እምነት።
በውጭ ጉዳይ ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ክርክር በሚዲያ ሳይ ነበር። ከተቃዋሚዎች አንዱ እንዴት ብለን ነው የኢትዮጵያን ውሃ ለጅቡቲ የምንሰጠው? የሚል ሃሳብ ነው ያነሳው። እነዚህ ሰዎች በእኔ ግምት ምን ዓይነት አስተሳሰብ እንዳላቸው አይገባኝም። ውሃ ልከን ገቢ ብናገኝ ምንድን ነው ችግሩ? የኤሌክትሪክ ኃይል ልከን ገቢ እንደምናገኘው ሁሉ ውሃም ልከን ገቢ ብናመጣ ጉዳት የለውም ጥቅም እንጂ፡፡ ውሃ መላክ ነዳጅ ከመላክስ ምን ልዩነት አለው? ምንም ልዩነት የለውም። እና የዚህ ሰው አስተሳሰብ ልማታዊ አስተሳሰብ ነው? ጅቡቲ ያለው ሕዝብ ውሃ እየፈለገ ውሃ የጠማውን ሰው ውሃ መከልከል ተገቢ ነው? በባህላችንስ ይሔ አለ? ስለዚህ የሚነሱ ነጥቦች በጣም አሳፋሪ ናቸው።
እና ተቃዋሚ ፓርቲዎች በዚህ ዙሪያ የእይታቸው አድማስ መለወጥ አለበት። ጊዜው ግን አልፏቸው ሔዷል። አጀንዳው ተቀይሯል። እያወሩ ያሉት ግን ከአስር ዓመት በፊት የነበረ አጀንዳ ነው። እና ችግሩ የአቋምና የአስተሳሰብ ችግር ነው።

የሕግ ስርዓቱ ጭቃ የሆነባት አገር (የአቶ ማሙሸት ጉዳይ) – ግርማ ካሳ

mamushetየፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ልጆች ተብለው ከሚቆጠሩት አንጋፋ ታጋይ መካከል አንዱ ናቸው። ለብዙ አመታት በአገዛዙ ታስረው ተሰቃይተዋል። ሆኖም አላፈገፈጉም። ጊዜያቸውና ሕይወታቸው ለአገራቸዉና ለሕዝባቸው የሰጡ ናቸዉና። የአንጋፋው የመኢአድ ሊቀመንበር ሆነው በከፍተኛ ድምጽ ይመረጣሉ። ሆኖም በአገሪቷ ጠንካራ ድርጅት እንዲኖር የማይፈልገው ሕወሃት፣ የግፍ በትሩን የሚመሩት ድርጅት፣ መኢአድ ላይ አሳረፈ። ምርጫ ቦርድን ተጠቅሞ ፣ የእኝህን ሰው አመራር አልቀበልም አለ። በአባላት ድጋፍ ለሌላቸው፣ መኢአድን ላቀጨጩ፣ ለአቶ አበባው መሐሪ የመኢአድ ሕጋዊነት ተሰጠ። የምርጫ ቦርድን ሕገወጥ ዉሳኔ ለማስቀልበስ የፍርድ ቤት ክርክር ዉስጥ ገቡ።አቶ አማረ ማሙሸት ይባላሉ።
አቶ አማረ በሚያዚያ 14 2007 በአዲስ አበባ ከተማ በተነሳውና ታሪካዊ ከፍተኛ ተቃውሞ ላይ፣ ወጣቶችን በማደራጀት በጥብጠሃል በሚል በቦሌ ክፍለ ከተማ አምቼ እሥር ቤት ይታሰራሉ። ከብዙ መንገላታት በኋላ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ። ወጣቶችን አደራጅተው በጥብጠዋል በተባለበት ቀን፣ ከምርጫ ቦርድ ጋር በሚደረግ ክርክር፣ ሌላ ፍርድ ቤት እንደነበሩ መረጃ ያቀርባሉ። አቃቢ ሕግ ኩም ብሎ፣ ክሴን አንስቻለሁ ይላል። ግንቦት 26 ቀን 22007 ዓ.ም ፣ የቦሌ ምድብ ችሎት ፍርድ ቤትም አቶ ማሙሸት እንዲለቀቁ ያዛል።
አቶ ማሙሸት መረጃ ስለነበራቸው ፖሊስ ክሱን ለማንሳት ተገደደ እንጂ፣ ሌሎች በሺህ የሚቆጠሩ ወገኖቻችንን ወያኔዎች እያሰሩ የሚያሰቃዩት ጥፋት ወይንም ወንጀል ሰርተው ሳይሆን በዉሸትና በፈጠራ እንደሆነ ይህ አንድ ትልቅ ማሳያ ነው።
አቶ ማሙሸት ፍርድ ቤቱን አመስግነው ወደ ቤታቸው ሊያቀኑ ሲሉ፣ ፖሊስ እንደገና አስሮ ይሄን ጊዜ ከማእከላዊ ቀጥሎ በቶርቸር ወደ ሚታወቀው የሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ይወስዳቸዋል። ስዬ አብርሃን ብርቱካን ሚደቅሳ ነጻ ስትለቀው፣ ከፍርድ ቤት ደጃፍ አንድ እርማጃ ሳይራመድ እንደገና ፖሊስ ይዞት እንዳሰረው ማለት ነው። ያኔ ስዬን የፈታችሁ ዳኛ ብርቱካን ሚደቅሳ ነበረች። አሁንም አቶ አማረ እንዲለቀቁ የወሰንነችዉም ዳኛ ብርቱካን ነው የምትባለው። ሴቶች ዳኛዎች ጀግኖች ናቸው እንበል !!! በመጽሀፍ ቅዱስ እንዳለችው ዲቦራ።
“ሚያዚያ 14 ቀን ሳይሆን ሚያዚያ 12 ቀን ነው ወጣቶችን አደራጅቶ ብጥበጣ የፈጠረ” የሚል ሌላ ክስ አቶ ማሙሸት ላይ ይመሰረትባቸዋል። ሰኔ 10 ቀን የአራዳ ችሎት ፍርድ ቤት፣ 5000 ብር ዋስትና ከፍለው ዉጭ ሆነው እንዲከራከሩ ትእዛዝ ይሰጣል። ዋስትና ተከፍሎ ወደ ቤታቸው ለመሄድ አቶ ማሙሸት ይዘጋጃሉ። ሆኖም ፖሊስ የፍርድ ቤት ትእዛዝ አልቀበልም ይላል።
በአገራች ፍርድ ቤቶች ያሉ ዳኞች፣ አብዛኞቹ ካድሬዎችና ለሙያቸው ሳይሆን ለሆዳቸው ያደሩ ፣ ፍርድ የሚያዛቡና የሚያጣምሙ መሆናቸው ይታወቃል። ሆኖም አልፎ አልፎ ደግሞ ትንሽም ቢሆን፣ ኢንቴግሪቲ ያላቸው ዳኞች ሲገኙ፣ ፖሊስ እንደፈለገ የዳኞችን ዉሳኔ የሚሽርበት ሁኔታ ነው ያለው። ያን ያህል የፍርድ ስርዓቱ ፍጹም ጭቃ የሆነባት አገር ናት ኢትዮጵያ።
ፖሊስ ይግባኝ ብሎ ሰኔ 15 ቀን፣ አቶ ማሙሸትን ፍርድ ቤት ያቀርባል። “ቢለቀቅ ፣ የአቃቢ ሕግ ምስክሮችን ያጠፋብናል። የተከሰሰበት ወንጀል ከባድና ውቅታዊ ነው” በሚል የዋስታና መብት አቶ ማሙሸት እንዲከለከሉ ይጠይቃል። ካድሬ ዳኛውም የፖሊስን ጥያቄ ያለምንም ማንገራገር ተቀብሎ፣ ፖሊስ ምርመራዉን እንዲጨርስ የ14 ቀናት ቀጠሮ ይሰጣል።
የአገሪቷ ሕግ መንግስት የዜጎችን የዋስትና መብት ያረጋግጣል። ግን ካድሬ ዳኞች ሕገ መንግስቱን አንብበው ሳይሆን ዉሳኔ የሚያስተላለፉት፣ በአቃቤ ሕግ በኩል ሕወሃቶች የሚልኩላቸውን የፖለቲካ ዉሳኔዎች ነው የሚያነቡት።
“የመጀመሪያውን ክስ ፍርድ ቤት በፃፈው ደብዳቤ ውድቅ ሆኗል፡፡ አሁን ደግሞ ዳኛዋ እንድለቀቅ ወስነዋል፡፡ ሆኖም ግን ፖሊስ እኔን መፍታት አልፈለገም፡፡ አሁንም ድረስ ታስሬ የምገኘው ባልዋልኩበት ነው፡፡ የታሰርኩት ባልሰራሁት ወንጀል ነው፡፡ እንግዲህ ቀጥሎ የሚመጣውን የምናየው ይሆናል፡፡ ምን እንደሚያደርጉ አላውቅም” ይላሉ አቶ ማሙሸት እየደረሰባቸው ስላለው ግፍፍ ሲናገሩ። እንደ ዜጋ ፍርድ ቤት መብታቸውን ሊያስጠብቅላቸው አልቻለም። እንደ ዜጋ ፍትህ ለማግኘት አልቻሉም። እነ ጌታቸው አሰፋ (የሕወሃት የደህንነት ሃላፊው) “ማሙሸት በወህኒ ይቆይ” የሚል ቀጭን ትእዛዝ ስለሰጠ ብቻ ፣ አቶ ማሙሸት በአሁኑ ጊዜ በወህኒ እየተሰቃዩ ይገኛሉ።
ዜጎች በአገራቸው በሰላም መኖር ካልቻሉ፤ በአገራቸው የሕግ ከለላ ካለገኙ፣ ጥቂቶች እንደፈለጉ ሕግ መንግስቱን ገልብጠው መንግስታዊ ሽብርና ዉንብድናን የሚፈጽሙ ከሆነ፣ እነርሱ ራሳቸው በጠራራ ጸሃይ ያፈረሱትን እና የናዱት፣ የረጋገጡትን ሕግ የመቀበልና የማክበር ግዴታ ሌሎች ሊኖራቸው አይችልም። አሁን ያለው የወያኔ ዘረኛ የናዚ ስርዓት የሕግ ጠላት እንጂ ፣ ሕግን አክባሪ አይደለም። ሕዝብን እያገለገ ሳይሆን፣ በሕዝብ ስም የሚገኝ እርዳታን እየመዘበረ፣ ጥቂት ፎቆችን ለይስሙላ እያሳየ ደጋፊዎችን ሃብታም እያደረገ፣ የኑሮ ዉድነቱን ከቁጥጥር ዉጭ ሆኖ አብዛኛውን ኢትዮጵያዊ በከፍተኛ ድህነት ዉስጥ የቀበረ፣ ዜጎችን እያሸበረ ያለ አሸባሪ ቡድን ነው።
dr3
(አቶ ማሙሸት በዋስትና እንዲለቀቁ የታዘዘበት ወረቀት ተያይዟል)
- See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/8081#sthash.vu1qYHbX.dpuf

Monday, June 22, 2015

የትግሬ-ወያኔ አመራር በቅርቡ ባደረገው ስብሰባ ዐማራን ፈጽሞ ሳያጠፋ እንቅልፍ እንደማይወስደው ዳግም አረጋገጠ! -

moresh-logoትናንት፣ ዛሬም ሆነ ነገ የትግራይ ሕዝብ ጠላት ዐማራው ስለሆነ፣» እያንዳንዱ ትግሬ ዐማራን በማጥፋት እንቅስቃሴ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆን፣ የወያኔ የአገር-ውስጥ እና የውጭ የስለላ ቡድኖች ከፍተኛ አመራሮች በጥናቶቻቸው እንዳሣዩ የታመኑ የሞረሽ-ወገኔ ምንጮቻችን አረጋገጡ። የመረጃ ምንጮቻችን እንደሚያስረዱት፣ አጥኚዎቹ ከሕወሓት ፖሊት ቢሮ በተሰጣቸው መመሪያ መሠረት የትግሬ-ወያኔን ዘረኛ አገዛዝ ያለፉትን የ፳፬(ሃያ አራት) ዓመታት ጉዞ መዝነው፣ ለሥልጣኑ አስጊው ማን እንደሆነ በመተንተን፣ ከ፪ሺህ፯ ዓ.ም. በኋላ የትግሬ-ወያኔ እንዴት መቀጠል እንዳለበት ዝርዝር ጥናት አቅርበዋል።
በትግሬ-ወያኔ የስለላ ተቋሞች ከፍተኛ አካሎች አማካይነት የተደረገው ይህ ዝርዝር ጥናት፣ «የመፍትሔ ኃሣብ ነው» ያለውን ለሕወሓት ፖሊት ቢሮ ማቅረቡን ምንጮቻችን ገልጸዋል። በስለላ ቡድኖቹ አንኳር የጥናት ውጤት መሠረት ወያኔ ገና «ሀ» ብሎ የትጥቅ ትግል ሲጀምር ከኢምፔሪያዝም በላይ እና በፊት «ዐማራ የትግራይ ሕዝብ ጠላት ነው» ብሎ መፈረጁ ትክክል እንዳልነበር፣ የትግሬ-ወያኔ ሥልጣን ከያዘ በኋላም ቀደም ሲል የፈጸመውን ስሕተት በማረም እና በማስተካከል ፋንታ በያዘው የቆየ የተሳሳተ ፍረጃ ገፍቶ በዐማራው ላይ ያደረሰው ጥፋት፣ እኒህ ሁሉ ተደማምረው ዐማራው «ትግሬ ጠላቴ ነው» ብሎ እንዲያስብ እና በነገዱ ዙሪያ እንዲሰባሰብ እንዳስገደደ ያመለክታል። ይህም ለተተኪው የትግራይ ትውልድ ቋሚ ጠላት የገዛ መሆኑ ተጠቅሷል። ከዚህ በተጨማሪም፣ ከሻዕቢያ ጋር የተገባው መቋጫ ያልተገኘለት ጦርነት የትግራይን ሕዝብ ከሥጋ ዘመዱ ከኤርትራ ሕዝብ ጋር ደም ያቃባ እና ቋሚ የደም ጠላት የገዛለት መሆኑ ተመልክቷል። በመሆኑም የትግራይ ሕዝብ ከላይ በኤርትራውያን፣ ከታች እና ከመሐል ደግሞ በዐማራው መካከል ሣንዲዊች ተደርጎ እንዲያዝ ያደረገ በመሆኑ፣ የወያኔ የ፳፬(ሃያ አራት) ዓመታት የሥልጣን ጉዞ ለመጭው የትግራይ ትውልድ ደም የገዛለት፣ የሥጋት ምንጮችን ያራባበት እንደሆነ የስለላ ቡድኖቹ የጥናት ውጤት አረጋግጧል።
የስለላ ቡድኖቹ ጥናት ለወደፊት የትግሬ-ወያኔ እንዴት በሥልጣን ላይ መቀጠል እንደሚችል የሚከተለውን ምክር መስጠቱ ታውቋል። ለጊዜው ወያኔ በሥልጣን ላይ በመሆኑ፣ ችግሩን ማስተዋል ቢሣነውም፣ የትግራይ ትውልድ በመጭዎቹ ዘመናት የሚታወቀው በሀገር ከሃዲነት፣ በኢትዮጵያ አፍራሽነት፣ ኢትዮጵያውያንን በጎሣ አቧድኖ በማጫረስ እና አገሪቱን ዝግ መሬት በማድረጉ እንደሚሆን ጥናቱ ያወሣል። ለወደፊቱም ወያኔ እንዴት መቀጠል እንዳለበት የሰጠው የመፍትሔ ኃሣብ፥ የተፈጸመውን ጥፋት በምንም መልኩ ወደኋላ ተመልሶ ማስተካከል ስለማይቻል፣ ማድረግ ያለበት በዝምታ ወደፊት መቀጠል መሆኑን፣ በአገሪቱ ውስጥ ካሉት ነገዶች ትግሬን የሚያሰጋው ሌላ ማንም ሳይሆን፣ ዐማራው መሆኑን፣ እና ይህ ነገድ በምንም ተዓምር የመደራጀት ዕድል እንዳያገኝ ወያኔ የሚቻለውን ሁሉ ማድረግ እንዳለበት ያስገነዝባል። ለዚህም ግብ ተግባራዊነት የተነደፉ ስልቶች፦
ሀ)      ዐማራዎች ከሁለት በላይ ሆነው እንዳይንቀሳቀሱ የተጠናከረ የስለላ እና የክትትል መረብ እንዲዘረጋ ማድረግ፤
ለ)      ወደውጪ አገር ለመሰደድ የሚፈልገውን ዐማራ በተለያዩ ስልቶች እንዲሰደድ ሁኔታዎችን በስውር በማመቻቸት ማሰደድ፤
ሐ)     በአገር ቤት ያለውን እና ለመሰደድ ፈቃደኛ ያልሆነውን ደግሞ አንገቱን ሳያቀና በልዩ ልዩ መንገዶች ማስወገድ፤
መ)     አንገታቸውን ያቀኑትን በተቀነባበረ መንገድ በሐሰት በመክሰስ በፍርድ ቤት የረጅም ጊዜ እስር በማስፈረድ ዕድሜያቸውን በእስር እንዲጨርሱ እና ተከታዮቻቸው ሞራላቸው እንዲላሽቅ ማድረግ፤
ሠ)      ድኃ ከዕለት ምግቡ በቀር ሌላ ነገር ማሰብ ስለማይችል፣ ዐማራውን በድኅነት ማጥ ውስጥ የሚከቱ ስልቶችን በመንደፍ ከሆዱ አልፎ ሌላ ነገር አንጋጦ እንዳያይ ማድረግ፤
(ረ)     ዐማራው በብዛት ተከማችቶ የሚገኝባቸውን ከተሞች እና መንደሮች በልዩ ልዩ የግንባታ ስበቦች በማፍረስ የዐማራውን የአብሮነት እና ማኅበራዊ ትሥሥር መበጣጠስ፤
(ሰ)     ሌሎች ነገዶች፣ በተለይ ኦሮሞዎቹ፣ ከዐማራው ጋር ምንም ዓይነት ቀና ግንኙነት እንዳይኖራቸው በሁለቱ ነገዶች መካከል ልዩነቶችን የሚያሰፉ የፕሮፓጋንዳ ሥልቶችን ቀይሶ መንቀሳቀስ፣ የሚሉ ይገኙበታል።
ለእነዚህም ስልቶች ተግባራዊነት፦
ሀ)      እያንዳንዱ ትግሬ በስለላ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆን ማድረግ፣
ለ)      የትግራይ ሕዝብ የትግሉ መሠረት እንደመሆኑ መጠን ከአሁኑ በተሻለ መንገድ የሁሉም ነገሮች ተጠቃሚ በማድረግ በሙሉ ኃይሉ ከሕወሓት ጎን እንዲሰለፍ ማድረግ፤
(ሐ)    ሕወሓት በሥልጣን ላይ ከሌለ የትግሬ ነገድ ዛሬ የጨበጠው የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ የበላይነት የማይቀጥል ከመሆኑም በላይ በወያኔ ተባባሪነት ተጠያቂ የሚሆነው ሕዝብ ጥቂት እንደማይሆን አውቆ ለሕወሓት ኅልውና የተለመደውን ትብብር ማድረግ እንዳለበት ያላሰለሰ ትምህርትና ቅስቀሳ መስጠት የማይታለፉ ተግባሮች መሆናቸውን የጥናት ቡድኑ መክሯል።
በቅርብ ሣምንታት ይህ አዲሱ የትግሬ-ወያኔ ዕቅድ በተግባር መተርጎም መጀመሩን የሚያመለክቱ ድርጊቶች ተበራክተዋል። ለአብነት ያህል ከሦሥት ቀናት በፊት ሰኔ ፰ ቀን ፪ሺህ፯ ዓ.ም. ሣሙኤል አወቀ የተባለውን እና ሰማያዊ ፓርቲን ወክሎ በምሥራቅ ጎጃም ዞን ለፓርላማ አባልነት የተወዳደረውን የ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ዓመት ወጣት በአሠቃቂ ሁኔታ ደብረማርቆስ ከተማ ውስጥ የገደሉት አንድ ምሣሌ ነው። ቀደም ብሎም በሚያዝያ እና በግንቦት ወራት አያሌ የዐማራ ተወላጆች ለግድያ፣ ለእሥር እና ለእንግልት መዳረጋቸው የአደባባይ ሚሥጢር ነው።
የትግሬ-ወያኔዎች እንዲህ ያስባሉ፣ ኃሣባቸውንም በተግባር ይተረጉማሉ። ዐማራውስ ራሱን ከፈፅሞ ጥፋት ለማዳን ምን ያስባል? መጥፋት ወይስ መክቶ ጥፋትን መከላከል? እንደሞረሽ ወገኔ አቋም «ጅብ ከሚበላህ፣ በልተኸው ተቀደስ» ነውና፤ ይህ አገርን እና ትውልድን አጥፊ የትግሬ-ወያኔ ናዚያዊ ቡድን አጥፍቶን ከመጥፋቱ በፊት እንቅስቃሴውን የሚያመክን የተግባር እርምጃ ይጠይቃል። ለዚህም ዐማራው ተደራጅቶ ራሱን እና አገሩን ከፈጽሞ ጥፋት ሊታደግ ይገባል ብለን እናምናለን። ይህ ጉዳይ «ቆይ እንመካከር፣ እንወያይ» የሚባልበት አይደለም። አፋጣኝ የተግባር እርምጃ ይጠይቃል።
ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደግ!

ባህርዳር ስራ አጥ ምሩቃን በህወሃት ደህንነቶች ታፍነው እየተወሰዱ ነው

protests-against-eprdf-in-bahir-dar-videoበባህርዳር ከተማ ትምህርታቸው ጨርሰው መንገድ ላይ ሲንቀሳቀሱ የተገኙት ወጣቶች ቦዞኔ እየተባሉ በጸጥታ አካላት ተገፈው ቤሻንጉል ወደሚገኘው የመንግስት እርሻ እንዲሰሩ መወሰዳቸው የተገኘው መረጃ አስታወቀ።
ምንጮቻችን ከቦታው እንደገለፁት በባህርዳር ከተማ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች ተመርቀው ስራ ያላገኙት ወጣቶች እለታዊ ንሮአቸውን ለመምራት ሲንቀሳቀሱ ስለተገኙ ብቻ በስርዓቱ ካድሬዎችና የፀጥታ ሃይሎች ቦዞኔ ተብለው እንዲያዙ ከተደረገ በኋላ ምንም ዓይነት የምግብና የህክምና አቅርቦት ወዳልተዘጋጀለትና ቤንሻንጉል ውስጥ ወደ ሚገኘው የመንግስት የጥጥ እርሻ ተወስደው በግድ እንዲሰሩ መደረጉን ተገለፀ።
እነዚህ በግድ ተገፈው የተወሰዱት ወጣቶች መጀመርያውኑ ወደ ቦታው ሲሄዱ ስላልተቀበሉትና የሰሩትን ያህል በቂ ዋጋ ስለማይከፈላቸው ተማርረው ከካምብ እየሸሹ ወደ ጎረቤት አገሮች እየጠፉ ለመሄድ ሲሞክሩ በተለያየ መንገድ አደጋ እየደረሰባቸውና ህይወታቸው እያጡ መሆነቸውን ለማወቅ ተችሏል።
መረጃው በማስከተል ከእርሻው ቦታ ጠፍተው ወደ ባህርዳር የተመለሱት አንዳንድ ግለሰዎች የመንግስት ንብረት ሰርቀው ነው የመጡት በሚል የሃሰት ውንጀላ ቢንያም ወርቁ፤ ፋንታሁን ይርሳው፤ ሙሉነህ ጥላሁን፤ ሙሉጌታ ታፈሰና ሌሎች ንፁሃን ወገኖች በፖሊሶች የታሰሩ መሆናቸው መረጃው አክሎ አስረድቷል።

ኢትዮጵያ ውስጥ ሁለት አይነት የብር ኖቶች እንደሚንቀሳቀሱ ታወቀ

unnamed (3)ኢትዮጵያ ውስጥ ሁለት አይነት የብር ኖቶች እንደሚንቀሳቀሱ ታወቀ፡፡ አትዮጵያ ውስጥ ባሉሁሉም ባንኮች ሳይቀር እየተዘዋወረ የሚገኘው ገንዘብ 2 አይነት መሆኑን ከብሄራዊ ባንክ አፈትልኮ የወጣው መረጃ ያሳያል ፡፡ #1ኛው አይነት የብር ኖት ብሄራዊ ባንክ በህጋዊ መንገድ በጨረታ የሚያሳትመው ሲሆን #2ተኛው አይነት የብር ኖት ደግሞ በ1997 ዓም ከቻይና ሃገር በሚስጥር በገባ 1 Sinocolor Solvent money printer በተባለ የብር ማተሚያ ማሽን በእነ #አዜብመስፍን እና አብሮአበሮቾ የሚታተም የባለ 50 እና ባለ 100 የብር ኖት ነው ፡፡ ይኽም የእነ አዜብ መስፍን የብር ኖት ከብሄራዊ ባንኩ የብር ኞት የጎላ ልዩነት የሌለው ቢሆንም በጣም ስስ በመሆኑ በገጠሩ ክፍል ተቀባይነት እንዳጣ ለማወቅ ተችሎል ፡፡ - 

Thursday, June 18, 2015

የአረናው አመራር አባል በ3 ሰዎች ታንቀው ተገደሉ

Tadese Aberhaዓምዶም ገብረስላሴ ከመቀሌ እንደዘገበው: ኣቶ ታደሰ ኣብርሃ የተባሉ የዓረና-መድረክ ኣባልና የምዕራባዊ ዞን የዓረና ኣመራር ኣባል ትናንት ማታ 09 / 10 / 2007 ዓ/ም በሶስት ሰወች ታንቀው ተገደሉ።
Tadese Aberhaኣቶ ታደሰ ኣብራሃ በቓፍታ ሑመራ ወረዳ ማይካድራ ቀበሌ ኑዋሪ ሲሆኑ በዘንድሮው ምርጫ ወቅት በቀበሌው ኣስተዳዳሪዎች፣ ካድሬዎች፣ የሚቀርቧቸው ሰዎች ከዓረና-መድረክ ኣባልነታቸው እንዲለቁ የተሸመገሉ፣ የተለመኑና በመጨረሻም ዛቻዎች ሲደርስባቸው እንደነበረ ይታወቃል።
ኣቶ ታደሰ ማታ 03:00 በ 3 ሰዎች ኣንገታቸው የታነቁ ሲሆን ሶስቱ ሰዎች ሙቷል ብለው የተዋቸው ቢሆኑም ሂወታቸው እስከ 09:15 ኣላለፈችም ነበር። ኣቶ ታደሰ ኣብራሃ የ48 ዕድሜ ጎልማሳ ነበሩ።
ኣደጋው 3 ሰዎች እንደፈፀሙባቸው፣ በኪሳቸውም 300 ብር የነበረ ቢሆንም ሰዎቹ ሊወስዱት እንዳልቻሉ ተናገረው ነበር።
የኣቶ ታደሰ ሬሳ በሑመራ ሆስፒታል ላለማስመርመር የማይካድራ ፖሊስ ትራፊክ በዓረና ኣባላት ላይ ከፍተኛ ጫና የፈጠሩ ሲሆን የተለያዩ የመንግስት ኣካላትም ምርመራው እንዳይካሄድ የተለያዩ ጫናዎች እንደፈጠሩ ኣባሎቻችን ከስፍራው ገልፀውልናል።
ሬሳው ወደ ሑመራ ወስዶ ለማስመርመር የሚጠቅም መኪና ለመከራይ ሲባል ኣባሎቻችን የተካራት ሞተር ሳይክ በፖሊስት ትራፊክ ተከልክላለች።
የኣቶ ታደሰ ኣብራሃ ቤት ኣካራይና ሌሎች ሰዎች ከኣደጋው በተያያዘ ጫና እየተፈጠረባቸው እንደሆነ ለማወቅ ተችለዋል።
የኣቶ ታደሰ ኣብራሃ ግድያ በሳምንት ውስጥ የወጣት ሳሙኤል ኣወቀን ጨምሮ ለሁለተኛ ግዜ በፖለቲከኞች ላይ የተፈፀመ ግድያ ሲሆን ከ2007 ዓ/ም በዓረና-መድረክ ኣባላት ለሁለተኛ ግዜ የተፈፀመ ግድያ ያደርገዋል።
ባለፈው ታህሳስ ወር የደቡባዊ ዞን የዓረና-መድረክ ኣስተባባሪና የማእከላይ ኮሚቴ ኣባል የነበረው ኣቶ ልጃለም ኻልኣዩ በኣዲስ ኣበባ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች መገደሉ ይታወቃል።
ይህ ተግባር በስፁም የሚወገዝና በሰላማዊ ትግል ላይ ሽብር የሚፈጥር ተግባር ነው።
በሰለማዊ መንገድ የሚታገሉ ፖለቲከኞች የሚፈፀም ግድያ ይቁም…!
መንግስት ነብሰገዳዮች ወደ ፍርድ ያቅርብ…!
ፈጣሪ ነብሳቸው ገነት ውስጥ ያኑርልን ኣሜን።
ነፃነታችን በእጃችን ነው።

ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ ጥልቅ የሐዘን መግለጫ!

ethiopia-blue-party-300x164አንድ በስልጣን ላይ የተቀመጠ አካል ተቀዳሚ ተግባር የዜጎችን ደህንነት መጠበቅ መሆኑን ጤነኛ አዕምሮ ያለው የሰው ልጅ የሚገነዘበው ጥሬ ሃቅ ነው፡፡ እንደ እርግማን ዛሬ በኢትዮጵያ የስልጣን እርካቡን የተቆጣጠረው ቡድን የሚገዛቸውን ዜጎች የሚያያቸው እንደጠላት እንጅ የመንግስትን ጥበቃ እንደሚፈልጉ፤ በጠላትነት የፈረጃቸው ዜጎች በከፈሉት ግብር ስልጣን ላይ መቆየት መቻሉን እንኳን ባለስልጣናቱ መረዳት ተስኗቸዋል፡፡
ሰኔ 8 ቀን 2007 ዓ.ም በደብረ ማርቆስ ከተማ እጅግ በሚሰቀጥጥ ጭካኔ እንደ እባብ ተቀጥቅጦ የተገደላው የሰማያዊ ፓርቲ ቆራጥ ታጋይ ሳሙኤል አወቀ የስርዓቱ አገልጋዩች ለዓመታት ሲያስፈራሩት፣ ሲደበድቡት፣ ሰርቶ የመኖር መብቱን ሲጋፉት፣ ያልተሳከ የመግደል ሙከራ በተደጋጋሚ ጊዜ ሲፈፅሙበት መቆየታቸውን የሚያረጋግጡ በርካታ ማስረጃዎች ተይዘዋል፡፡ ሳሙኤል ሕይወቱ አደጋ ላይ እንደሆነችና ጥበቃ እንዲያደርጉለት የጠየቃቸው የፀጥታና የፍትህ አካላት በተገላቢጦሽ ተጨማሪ ዛቻና ማስፈራሪያ ያደርሱበት እንደነበር አይዘነጋም፡፡ አንድ ወጣት በተወለደበት ምድር በሕይወት የቆየባቸውን ጊዚያት በስጋት እንዲኖር ከተፈፀመበት ግፍ በተጨማሪ በሕይወት የመኖር መብቱ በአረመኔዎች እጅ ስትነጠቅ የህዝብን ፀጥታና ደሕንነት እናስከብራለን የሚሉ አካላት በመሃል ከተማ እንኳን ደርሰው ለመታደግ አቅሙም ሆነ ፍላጎቱ አልነበራቸውም፡፡
ሳሙኤል በአሰቃቂ ሁኔታ ከመገደሉ በፊት በተለያዩ ጊዚያት ለሚመለካታቸው አካላትና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያስተላልፋቸው የነበሩ መልዕክቶች እንደተጠበቁ ሆነው በተለይ ግንቦት 25 2007 ዓ.ም በራሱ ገፅ በሆነው “የፌስ ቡክ” ማህበራዊ ሚዲያ ካስተላለፈው መልዕክት መረዳት እንደሚቻለው በተደራጀ ሁኔታ ሕይወቱ አደጋ ላይ እንደሆነች አስረግጦ ተናግሯል፡፡ ሆኖም የሚሰማውና የሚጠብቀው ምንም አካል እንዳልነበረ ይልቁንም ለመገደሉ ተባባሪ የሆኑ የመንግስት አካላት እንደነበሩ ስጋቱን በገለፀ በቀናት ውስጥ ሕይወቱ በአሰቃቂ ሁኔታ መቀጠፏ ጉልሕ ማስረጃ ነው፡፡
በሰላማዊ ትግል ፅኑዕ እምነት የነበረው ሳሙኤል አወቀ ይደርስበት የነበረውን ለቁጥርና ለዓይነት አታካች የሆነ በደል ተቋቁሞ፣ ትግሉን እንዲያቆም ወይም የሚወዳትን ሕይወቱን አሳልፎ የሰጠላትን ሐገሩን ለቆ እንዲሰደድ ይህ ካልሆነ ግን የእሱን ሕይወት ለማጥፋት እጅግ ቀላል መሆኑን የስርዓቱ ባለስልጣናት እና ካድሬዎች ደጋግመው ቢነግሩትም በጭቆና ስር ለሚማቅቀው የኢትዮጵያ ሕዝብ የገባውን ቃል ከማጠፍ ይልቅ ሕይወቱን ለመሰዋት እንደሚቀለው የገባውን ቃል በተግባር አስመስክሮ አልፏል፡፡ በማሰርና በመደብደብ አላማውን እንደማያስቀይሩት፤ ከገደሉት ግን ቀሪ ታጋዮች በተለይም የእድሜ አቻዎቹ የሆኑ የእርሱ ትውልድ የሚሰዋለትን ዓላማ ከግብ እንዲያደርሱ “ትግሌን አደራ!! አደራ!!” በማለት ተማፅኖ አስቀምጧል፡፡
እኛም እንላለን፡፡ አደራህ ከባድ ነው፡፡ ቃልህን እናከብራለን፡፡ አላማህንም እናሳካለን!!!!
ይህ ስርዓት በህግም በሞራልም ኢትዮጵያን የማስተዳደር ብቃት የለውም፡፡ ወንጀለኞች ለፍርድ ይቅረቡ እያልንም አናላዝንም፤ ወንጀለኞቹ የመንግስት አካላት ናቸውና፡፡ በወንድማችንና ገና በለጋ እድሜው በተቀጨው የትግል አጋራችን ላይ የተፈፀመውን ግፍ አይቶ እንዳላዬ ዝም ያለ መንግስት ከዚህ የተሻለ መልካም ነገር ያመጣል ብለን አንጠብቅም፡፡ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ግን መልዕክት አለን፡፡ እስከ መቼ በግፍ እንገደላለን?!! ሸፍጠኞችስ እስከ መቼ ይዘባበቱብናል?!! ትግል ለውጤት የሚበቃው በተወሰኑ ቡድኖች ወይም ግለሰቦች መፍጨርጨር ብቻ ባለመሆኑ የግፍ ስርዓት እንዲያበቃ ሁላችንም የሚገባንን የዜግነት ድርሻ እንድንወጣ ጥሪ እናቀርባለን፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ በአባላቱና በደጋፊዎቹ በአጠቃላይም የተለየ አስተሳሰብ ስላላቸው ብቻ በካድሬዎች የሚታሰሩ፣ የሚገረፉ፣ የሚሳደዱ፣ የሚዋረዱና የሚገደሉ ዜጎች ለከፈሉት መራራ ፅዋ ክብር ይሰጣል፡፡ መስዋዕትነታቸውም በከንቱ እንዳይሆን እሰከመጨረሻው ይታገላል፡፡
ሳሙኤል “ብታሰርም፣ ብገደልም ይህን ሁሉ የማደርገው ለሐገሬና ለነፃነቴ ነው” ያልከው ቃልህ ከመቃብር በላይ ነው!!!! ቃልህን እናከብራለን፡፡ አላማህንም እናሳካለን!!! ትግል ይቀጥላል . . .
ሰኔ 10 ቀን 2007 ዓ.ም
አዲስ አበባ

በሽብርተኝነት የተከሰሱ የአየር ኃይል አባላት ነገ ፍ/ቤት ይቀርባሉ

ethiopian_airforceበነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
ከግንቦት ሰባት ጋር ግንኙነት አላችሁ በሚል የሽብርተኝነት ክስ የቀረበባቸው ሰባት የአየር ኃይል አባላት ነገ ሰኔ 12/2007 ዓ.ም በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ይቀርባሉ፡፡
አቃቤ ህግ በሰኔ 7/2007 ዓ.ም ባቀረበባቸው ክስ ላይ እንደተመለከተው፣ ተከሳሾቹ የወንጀል ህጉ አንቀጽ 32(1)(ሀ)ን እና የጸረ-ሽብርተኝነት አዋጅ አንቀጽ 7(1) ስር የተመለከተውን በመተላለፍ በሽብተኝነት ተከስሰዋል፡፡ በክሱ የተመለከቱት ተከሳሾች የሚከተሉት ናቸው፣
1ኛ. መ/አ ማስረሻ ሰጤ……አድራሻ ድሬዳዋ
2ኛ. መ/አ ብሩክ አጥናዬ……. ›› ድሬዳዋ
3ኛ. መ/አ ዳንኤል ግርማ…… ›› ድሬዳዋ
4ኛ. ገዛኸኝ ድረስ………. ›› ድሬዳዋ
5ኛ. ተስፋዬ እሸቴ…….. ›› ምስራቅ ጎጃም
6ኛ. ሰይፉ ግርማ……. ›› አዲስ አበባ
7ኛ. የሻምበል አድማው…… ›› ምስራቅ ጎጃም፣ ናቸው፡፡
በአቃቤ ህግ ክስ ላይ እንደተመለከተው ተከሳሾች ‹‹….ህገ መንግስቱንና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል የማፈራረስ ዓላማ ይዘው ….በሽብር ድርጅት ውስጥ አባል በመሆንና በሽብር ድርጅት ተግባር ላይ ለመሳተፍ በማሰባቸው….›› የሽብርተኝነት ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡
ተከሳሾች ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ አየር ኃይል በመክዳት ግንቦት ሰባትን ለመቀላቀል ወደ ኤርትራ ሊያመሩ ሲሉ ባህር ዳር እና ጎንደር ላይ እንደተያዙ በክሳቸው ላይ የተመለከተ ሲሆን፣ በአጠቃላይ የሽብር ድርጅት አባል በመሆን፣ ተልዕኮ በመቀበል፣ አባላትን በመመልመል እና መረጃ በማቀበል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡
የአየር ኃይል አባላት ተከሳሾቹ በነገው ዕለት አቃቤ ህግ ባቀረበባቸው ክስ ላይ የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያ ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ተከሳሾች ለወራት ከቆዩበት ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ወጥተው በአሁኑ ወቅት ቂሊንጦ እስር ቤት እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Wednesday, June 17, 2015

የአቢሲኒያ ባንክ ሰራተኞች የተቃዋሚ ድርጅት ደጋፊ ናቸው ተብሎ በኢሕ አዴግ ባለስልጣናት ተፈረጀ -

bank of abissinyaየትህዴን ድምጽ እንደዘገበው ባህርዳር ከተማ ውስጥ የሚገኙ የአቢሲኒያ ባንክ ቅርጫፍ ሰራተኞች የተቃዋሚ ድርጅት ደጋፊዎች ናችሁ ተብሎው በኢህአዴግ ባለስልጣናት መነገራቸው ተገለጸ። ለዜና ምንጩ በደረሰው መረጃ መሰረት በባህር ዳር ከተማ የኢህአዴግ ባለስልጣን በሆነው በአዲሱ ለገሰ በተደረገው የስብሰባ መሪነት አብዛኛው የአቢሲያ ባንክ ሰራተኞች የተቃዋሚ ድርጅት ደጋፊዎች ናችሁ፤ ከመንግስት ጋር ያላችሁን ችግር በውይይት እንፋታው ብሎ በከፈተው ስብሰባ ላይ የባንኩ ሰራተኞች እኛን የቀጠረን ባንክ የግል ተቋም ነው። ስለዚህ ላንተ የምንሰጠው መልስ የለንም ብንናገርም የሚመጣ ለውጥ የለም በማለት ያለምንም ፍሬ ነገር ሳይግባቡ ከስብሰባው እንደተበተኑ ለማወቅ ተችሏል። በአሁኑ ሰዓት አብዛኛው የመንግስት ሰራተኛ ምንም ዓይነት ወንጀልና ጥፋት ሳይኖረው ስርዓቱ በውስጡ ካለው ያለመተማመንና መጠራጠር ሁኔታ በመነሳት ንፁሃን ዜጎችን እያንገላታና በቂ ማስረጃ ሳያገኝ እያሰቃያቸው እንደሚገኝ የተገኘው መረጃ ጨምሮ አስረድቷል። ለዘ-ሐበሻ በደረሰው መረጃ መሰረት ደግሞ አቢሲኒያ ባንክ የአማሮች ባንክ ተብሎ በሕወሓቶች ተፈርጇል:: ሕወሓቶች በአሁኑ ወቅት ወጋገን ባንክን እንደራሳቸው ባንክ የሚቆጥሩ ሲሆን አቢሲኒያ ባንክን ለማክሰም የአማሮች ባንክ በሚል ስያሜ እየሰጡ ሰዎችን እንደሚያሸማቅቁ ታውቋል:: 

በከፋ ዞን ቦንጋ ከተማ የዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ የምርጫ አደራጅ በድብደባ ሆስፒታል ገባ -

ቦንጋ ከተማበጊምቦ ገዋታና በቦንጋ የተራዘመው ምርጫ ባለፈው ሳምንት ከተጠናቀቀ በሁዋላ፣ የግል ተወዳዳሪው ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ የምርጫ ቀስቃሽና አደራጅ የሆነው ምትኩ ወልዴ ፣ ትናንት ከቀኑ 6 ሰአት ከ 30 ደቂቃ ላይ ፖሊሶች ከቤት አውጥተው የደበደቡት ሲሆን፣ ግለሰቡ በደረሰበት ከፍተኛ ድብደባ ቦንጋ ሆስታል ከገባ በሁዋላ፣ ወደ ጅማ ሪፈራል ሆስፒታል ተወስዷል።
ግለሰቡ የደረሰበት ድበደባ ከፍተኛ በመሆኑ ለህይወቱ አስጊ መሆኑን የዶ/ር አሸብር ደጋፊዎች ተናግረዋል። በዶ/ር አሸብር ቅስቀሳ ላይ ተሳትፈዋል የተባሉት ሁሉ እየታደኑ በመሆኑ ብዙዎች ከአካባቢው መሸሻቸውን ተናግረዋል።
ዶ/ር አሸብር በፓርላማ በነበራቸው ቆይታ ራሳቸውን የኢህአዴግ ደጋፊ እያደረጉ ሲናገሩ እንደበር ይታወቃል። ከምርጫው በፊት በአንድ ጋዜጣ ላይ ፣ የኢህአዴግ አባል ባይሆኑም ደጋፊ በመሆናቸው ኢህአዴግ የቦንጋን የምክር ቤት ቦታ ይልቀቅልኝ ብለው በይፋ ተናግረው ነበር።
ኢህአዴግ ያቀረባቸው እጩ አሸንፈዋል በመባላቸው ዶ/ር አሸበር በሚቀጥለው ፓርላማ አይገኙም። የዶ/ር አሸብር የምርጫ ታዛቢዎች የምርጫውን ውጤት አንቀበልም ማለታቸው ተሰምቷል። በሌላ በኩል ደግሞ በሰሜን ጎንደር በአዘዞ ከተማ መምህር ይትባረክ ጌታሁንና መምህር ሲሳይ ፣ አቶ ወርቁ በላይ የተባሉ የቀበሌ ሰራተኛና አቶ ፋንታሁን የሚባሉ የአገር ሽማግሌ ወጣቱን ለትግል እየቀሰቀሳችሁ ነው በሚል 5ኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው እንደሚገኙ የደረሰን መረጃ ያመለክቷል። ግለሰቦቹ የፓርቲ አባል ይሁኑ አይሁኑ ይታወቀ ነገር የለም።

አንድ የፌደራል ፖሊስ 3 ባልደረቦቹንና አንድ ቻይናዊ ገደለ

334_Ethiopia_12_10_31_Ethiopia_charges_29_Muslims_under_antiየትውልድ ቦታው አሶሳ አከባቢ የሆነ የፌዴራል ፖሊስ አባል ሌሎች ሶስት የፌዴራል ፖሊስ አባላትን እና አንድ ቻይናዊን በምዕራብ ሀረርጌ ሚኤሶ ወረዳ ልዩ ስሙ ቦርደዴ በተባለ ቦታ በጥይት ተኩሶ ከገደላቸዉ በሃላ መሰወሩን የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል:: የፌደራል ፖሊሶችና የኦሮምያ ፖሊስ ገዳዩን ለመያዝ በጭሮ፣ ሚኤሶ፣ በዴሳ፣ ገለምሶና አዋሽ ከተሞች ቤት ለቤት እየገቡ ፍተሻ በማካሄድ ላይ ናቸው። ፖሊሶቹ ለሰበተ-ሚኤሶ ባቡር ስራ ቻይናዎችን እንዲጠብቁ የተመደቡ ናቸው። ቻይናዊው ሰራተኛና ሶስቱ ፖሊሶች ህዝቡን በተለይም የቀን ሰራተኞችን ያለ ክፍያ የሚያሰሩ እንዲሁም ለባቡሩ ካሳ ያልተከፈለበት እርሻን አስገድደዉ መንገድ እንዲሰራ እንደሚያደርጉ ነዋሪዎች ይናገራሉ። ገዳዩ ፖሊስ ድርጊቱን ሲቃወም በመቆየቱ በአካባቢው ህዝብ ዘንድ ተወዳጅ መሆኑንና ያለመያዙም ሚስጢር ከህዝብ መጠለያ በማግኘቱ መሆኑን ነዋሪዎች ገልጸዋል። ድርጊቱ ከተፈጸመ በሁዋላ የባቡር ስራው መቆሙን ምንጮች ገልጸዋል። ኢሳት ቻይናውያን ሰራተኞች ስለሚፈጽሙት በደል ተደጋጋሚ አቤቱታዎች ሲደርሱት ቆይቷል። በጉዳዩ ዙሪያ የመንግስትን አስተያየት ለማካተት የተደረገው ጥረት አልተሳካም። የቻይናዊውን ግድያ በተመለከተም መንግስት እስካሁን የሰጠው ይፋዊ መግለጫ የለም። - 

Tuesday, June 16, 2015

የግፍ ሰለባ! – አርአያ ተስፋማሪያም

የግፍ ሰለባው ዶ/ር ተስፋዬ ብሩ እኚህ ናቸውአቶ ተስፋዬ ብሩ (ኋላ ዶ/ር) የደረሰባቸው ግፍና ስቃይ እጅግ አሳዛኝ ነው። ጉዳዩ እንዲህ ነው፤ ተስፋዬ የቴሌ ስራ አስኪያጅ ሆነው የተመደቡት በ1995ዓ.ም ነበር። አንድ በቴሌ የሚሰራ ኢንጂነር ወዳጄ በወቅቱ « ተስፋዬ ብሩ እውቀትና ብቃ…ት አለው። ግን አያሰሩትም» ያለኝን በኢትኦጵ ጋዜጣ በወቅቱ አስፍሬው ነበር። እርሳቸው ከመሾማቸው በፊት ቴሌን በአዜብ መስፍን “አዝማችነት” ኢያሱ በርሄን ጨምሮ 38 ግልሰቦች ለ7 አመት በደንብ አድርገው ገሽልጠውታል። በቁጥጥር ስር ቢውሉም ወዲያው አዜብ አስፈታቻቸው። የቴሌ አመራሮችም በቦሌ ተሸኙ። ድርጅቱን የተረከቡት ተስፋዬ ብሩ በአግባቡ ማስተዳደር ቀጠሉ። በ1998 ዓ.ም “ሪፖርተር” ጋዜጣ 20ኛ አመቱን ለማክበር ሲል ቴሌን የ250ሺህ ብር ስፖንሰር እንዲሆነው ይጠይቃል። ሃላፊውም “አይሆንም” ሲሉ ይመልሳሉ። አማረ አረጋዊ በተስፋዬ ብሩ ላይ አከታትሎ ዘመቻ ይከፍታል። በዛው አመት ከስልጣን ተነስተው የጠ/ሚ/ሩ አማካሪ ተደርገው ይሾማሉ። ከዚያም ወደ ውጭ ለትምህርት ይሄዳሉ። አማረ መፃፉን አላቆመም። ተስፋዬ ክስ ሲመሰረትባቸው ውጭ አገር ነበሩ። ትምህርታቸውን በማቋረጥ « እኔ የሰራሁት ወንጀል ስለሌ እሄዳለሁ» በማለት መጡ። ከቦሌ ተይዘው እስር ቤት ተወረወሩ። የሚገርመው ረቡዕ የወጣ ሪፖርተር ጋዜጣ በፊት ገፁ የተስፋዬን ፎቶ በማስፈር ሙሉ ሽፋን ሰጥቶ «ደስታውን» ገለፀ። በክሱ ላይ «ተስፋዬ ሳንቲም ሰርቀው ወሰዱ፣ ይህን ያክል ሃብት አፈሩ» የሚል ነገር በጭራሽ አልቀረበም። እነሆ ከ7 አመት ግፍና ስቃይ በኋላ ባለፈው ሳምንት ተፈቱ። እንደተስፋዬ ሁሉ የቀድሞ የፕራይቬታይዜሽን ስራ አስኪያጅ በሻህ አዝምቴ፣ የወንጂ ስኳር ብርሃኑ ጃጆ፣ አሰፋ አብርሃ፣ ኢ/ር ግዛቸው ተ/ማርያም፣ ጉልላት ጥላሁን ያለሃጢያታቸው በግፍ የተሰቃዩ ናቸው። (ስለነዚህ እመለስበታለሁ)…የሪፖርተሩ አማረ በሙስና ዙሪያ የፃፈው « ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ በሙስና ይጠየቁ» ሲል ስለ2 ቢሊዮን ያጋለጠበትና የግርማ ብሩ ይጠቀሳሉ። ከዛ ውጭ አባይ ፀሐዬ፣ ስብሃት ነጋ፣ አዜብና በረከት እንዲሁም የጄኔራሎችን ሙስና በተመለከተ አንስቶ አያውቅም። (የግፍ ሰለባው ዶ/ር ተስፋዬ ብሩ እኚህ ናቸው….) - 

እነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ የክስ መቃወሚያ አቀረቡ

እነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ የክስ መቃወሚያ አቀረቡበነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
መንግስት የኢትዮ-ኤርትራ ድንበርን ተሻግረው ኤርትራ የሚገኘውንና በተወካዮች ም/ቤት በሽበርተኝነት የተፈረጀውን የግንቦት ሰባት ወታደራዊ ክንፍ ሊቀላቀሉ ሲሉ በጸጥታ ኃይሎች ማይካድራ ላይ በቁጥጥር ስር አውያቸዋለሁ ያላቸው እነ ብርሃኑ ተክለያሬድ አቃቤ ህግ ባቀረበባቸው ክስ ላይ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያቸውን አስገቡ፡፡
ዛሬ ሰኔ 9/2007 ዓ.ም በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የቀረቡት በእነ ብርሃኑ ተክለያሬድ የክስ መዝገብ የተካተቱት አራት ተከሳሾች ማለትም፣ ብርሃኑ ተ/ያሬድ፣ እየሩሳሌም ተስፋው፣ ፍቅረማርያም አስማማውና ደሴ ካህሳይ በጋራ ያዘጋጁትን የክስ መቃወሚያ አስገብተዋል፡፡ አራቱ ተከሳሾች ጠበቃ ማቆም አንፈልግም በማለታቸው ያለጠበቃ የቀረቡ ሲሆን፣ ተከሳሾቹ በክስ መቃወሚያቸው ላይ ሁለት አብይት ነጥቦችን በመጥቀስ ክሱ ውድቅ ተደርጎ በነጻ እንዲሰናበቱ ጠይቀዋል፡፡
ተከሳሾቹ በክስ መቃወሚያቸው ላይ እንደጠቀሱት አቃቤ ህግ ያቀረበባቸው ክስ ከህገ መንግስቱ ጋር የሚጣረስና (ጸረ-ሽብር አዋጁ ከህገ መንግስቱ ጋር እንደሚጣረስ በመጥቀስ) በወ/መ/ሥ/ሥ/ህጉ መሰረት ያልቀረበ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ እንደ ህጉ ያልቀረበን ክስ ውድቅ በማድረግ በነጻ ያሰናብተን ብለዋል፡፡
ፍርድ ቤቱ በተከሳሾች የቀረበው አቤቱታ ላይ አቃቤ ህግ መልስ እንዲሰጥ በሚል ለሰኔ 19/2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ በሌላ በኩል አንደኛ ተከሳሽ ብርሃኑ ተ/ያሬድ በተደጋጋሚ በእስር ቤት በሚደርስበት በደል ላይ አቤቱታ ማሰማቱን ቀጥሏል፡፡ በዚህም ፍርድ ቤቱ አቶ ብርሃኑ አለኝ የሚለውን አቤቱታ በጽሑፍ እንዲያቀርብ አዝዞ የነበር ቢሆንም አቶ ብርሃኑ የማዘጋጀውን አቤቱታ ‹‹እንዴት ማረሚያ ቤቱን ትከሳለህ›› በሚል ጽሑፉን እየተነጠቀ እንደሆነ በመግለጽ አቤቱታውን በጽሑፍ ማቅረብ እንዳልቻለ አስረድቷል፡፡
ይህን የአቶ ብርሃኑን አቤቱታ በተመለከተ የማረሚያ ቤቱ ተወካይ ችሎት ፊት እንዲቀርቡ ተደርገው ‹‹ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ ያለውን አቤቱታ እንዲያቀርብ አዝዘናል፤ ስለዚህ እናንተ መልስ ካላችሁ መልሳችሁን እንቀበላለን፣ አሁን ግን ተከሳሹ የሚያዘጋጀውን አቤቱታ እንዲያቀርብ አድርጉ›› በማለት በፍርድ ቤቱ ተነግሯቸዋል፡፡ በመሆኑም አቶ ብርሃኑ በቀጣዩ ቀጠሮ በእስር ቤት አያያዝ ላይ ያለውን አቤቱታ በጽሑፍ ይዞ ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የዞን 9 ጦማርያንና ሦስቱ ጋዜጠኞች ለብይን ተቀጠሩ

zone9bloggers_januari28-Trial-Tadias-Magazine-coverበእነ ሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ ቀርቦባቸው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኙት የዞን ዘጠኝ ጦማርያን እና ሶስቱ ጋዜጠኞች የቀረበባቸውን ክስ መከላከል ያስፈልጋቸዋል ወይስ በነጻ ይሰናበቱ የሚለው ላይ ብይን ለመስጠት ለሐምሌ 13/2007 ዓ.ም ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡ ዛሬ ሰኔ 8/2007 ዓ.ም የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ልደታ ምድብ የቀረቡት ጦማርያኑና ጋዜጠኞቹ ጥቁር ለብሰው ችሎት ፊት ቀርበዋል፡፡ መዝገቡ ለዛሬ ተቀጥሮ የነበረው አቃቤ ህግ በአንደኛ ተከሳሽ ላይ የሲ.ዲ ዶክሜንተሪ ማስረጃ ማቅረቡን ተከትሎ ፍርድ ቤቱ በጽ/ቤት አይቶ ሲ.ዲው በግልጽ ችሎት ይታይ ወይስ በዝግ የሚለውን ብይን ለመስጠት ነበር፡፡ በዚህም ፍርድ ቤቱ ሲ.ዲው በችሎት መታየቱን ተገቢ ሆኖ ስላላገኘነው በሚል ዳኞች ብቻ ተመልከተውት በማስረጃነት እንዲያዝ ተደርጓል፡፡ ይህን ተከትሎ ተከሳሾች በብይኑ ላይ አለን ያሉትን አቤቱታ በጠበቆቻቸው አማካኝነት ያሰሙ ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱ ግን ብይን ባገኘ ጉዳይ ላይ አቤታቱውን ከመመዝገብ ውጭ ለውጥ እንደማይኖረው ገልጹዋል፡፡ በመሆኑም ፍርድ ቤቱ ሐምሌ 13/2007 ዓ.ም ተከሳሾች አቃቤ ህግ ያቀረበባቸውን ክስ ይከላከሉ ወይስ በነጻ ይሰናበቱ በሚለው ጉዳይ ላይ ብይን ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ 

ወጣት ሳሙኤል አወቀ ተገደለ – ነገረ ኢትዮጵያ

ከሳሙኤል አወቀ ዓለም - የሰማያዊ ፓርቲ የደብረ ማርቆስ የሕዝብ ተወካዮች እጩ ተወዳዳሪይህ የምታዩት የሰማያዊ ፓርቲ የምስራቅ ጎጃም ዞን ፀኃፊና በ2007 ዓ.ም ምርጫ የፓርቲው ዕጩ ተወዳዳሪ የነበረው ወጣት ሳሙኤል ፤ትናንት ሰኔ 8/2007 ዓ.ም ምሽት ላይ ወደ ቤቱ እየገባ በነበረበት ወቅት በሁለት ግለሰቦች ከፍተኛ ድብዳባ ከተፈፀመበት በኋላ ሆስፒታል ውስጥ ነፍሱ ማለፏን እየሰማን ነው።
ይህች አጭር ጽሁፍ ደግሞ ሳሙኤል ከመገደሉ በፊት በፌስቡክ ገጹ ያሰፈራት ነች ፦
“…ውድ የደብረማርቆስ ከተማ ኗሪዎች ፤ ሰማያዊ ፓርቲን የመረጣችሁ ከ25’0000 በላይ መራጮች(ኮረጆውን) እርሱት እና በተጨማሪም በ31 ዩኒቨርስቲ የምትገኙ ከ14,000 በላይ ሰማያዊ ፓርቲን የመረጣችሁ ሌሎች ደጋፊዎች እና የኢሕአዴግ አባላትም የማያፍረው ብአዴን / ኢሕአዴግ ድምፅ መቀማቱ ሳያንስ በ21/08/2007 ዓም አፍነው ደብድበው ከሞት መትረፌ ቆጭቷቸው እሰር ቤት ለ…መወርወር ያለመከሰስ መብቴን እንኳን ተዳፍረው የሀሰት ክሰ እየፈጠሩ ነው!!!” በስልኬ እደተደወለም ያለፍላጎቴ ደሕንነት እያስገደደኝ ይገኛል!!!!! ተገደልሁም ታሠርሁም ፤ ታፈንኩም ነፃነት አይቀርም እና ለማሰረጃነት የደሕንነቶችን ስም፤ ፎቶግራፍ ፤ እና አድራሻ እንዲሁም በሐሠት ምሰክርነት እና ከሳሽነት የተደራጁ አካላት እና ዋና ተወካዮች የደብረማርቆስ ከተማ 04 ቀበሌ አመራሮች እና ፖሊስ ለታሪክ አሰመዘግባለሁ ማንኛውም የምከፍለው ዋጋ ለሀገሬ እና ለነፃነት ነው ከታሠርሁም ሕሊናዬ አይታሰርም ከገደሉኝም ትግሌን አደራ በተለይ የኔ ትውልድ አደራ !!!!” አገራችን የወያኔ ዘረኞች ብቻ መፈንጫ መሆን የለባትም ትግላችን የነፃነት ጉዟችን ጎርባጣ መድረሻችን ነፃነት ታሪካችን ዘላለማዊ ነው!!!!”(ከሳሙኤል አወቀ ዓለም – የሰማያዊ ፓርቲ የደብረ ማርቆስ የሕዝብ ተወካዮች እጩ ተወዳዳሪ)

Monday, June 15, 2015

የሕወሓት መንግስት የግንቦት 20ን በዓል በ20 ሰው በድብቅ በሚኒሶታ አከበረ

Girma biru(ዘ-ሐበሻ) የሕወሓት መንግስት የሚኒሶታን ሕዝብ እንደ ጦር ነው የሚፈራው – ለዛም ነው ሕዝባዊ ስብሰባና በዓል ሲያደርግ በድብቅ የሚያደርገው:: ከዚህ ቀደም በአደባባይ ፖስተር ለጥፎ ስብሰባ ሲጠራ ሕዝቡ ስብሰባው ከመጀመሩ በፊት በማወኩ ስብሰባው ሳይካሄድ ቀርቷል:: ትናንት June 13 በሚኒሶታ የሕወሓት መንግስት የግንቦት 20ን በዓል ለማክበር በሚኒሶታ በድብቅ ስብሰባ ጠርቶ ነበር:: በሚኒሶታ 5ለ1 በሚል ጥርነፋ የተደራጁ የሕወሓት መንግስት ደጋፊዎች ያሉ ሲሆን እነዚህ ሰዎች የየራሳቸውን ኮኔክሽን ቢጠሩም በስብሰባው ላይ ከ20 የበለጠ ሰው ሳይገኝ ቀርቷል:: በረመዳ ሆቴል በተደረገው በዚሁ በከሰረው የግንቦት 20 በዓል ላይ የሕወሓቱ ተላላኪና ከደንበል ሲቲ ሴንተር ጋር በተያያዘ በሙስና የሚታሙት አቶ ግርማ ብሩ የመጡ ቢሆንም በኪሳራ ወደመጡበት ተመልሰዋል:: ከአቶ ግርማ ብሩ የቀረቡ ምንጮች ባገኘነው መረጃ መሠረት በስብሰባው ላይ ከ20 ሰው በታች መገኘቱ በጣም ከመበሳጨታቸው የተነሳ በድብቅ የተጠሩት ሰዎች ሁሉ ባለመገኘታቸው “ምን አድርገናቸው ነው?” የሚል ጥያቄ ማንሳታቸውን ነው:: የሕወሓት መንግስት በዓል የሆነው የግንቦት 20 በዓል በሚኒሶታ በባዶ አዳራሽ መካሄዱ ለሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ትልቅ ድል ነው:: - 

Hiber Radio: በሰሜን ጎንደር በታጣቂዎች በተወሰደው እርምጃ አምስት ንጹሃን ሲገደሉ ስድስት መቁሰላቸው ተነገረ፣ በእንግሊዝ ሁለት የጥበቃ ሰራተኞች ትገል ነበር ተብሎ ኢትዮጵያዊው ከሰባት ዓመት በላይ ተፈረደበት፣የአፍሪካ ህብረት የጦር ቃል አቀባይ በአልሸባብና በኢትዮጵያ ወታደሮቹ መካከል የደፈጣ ውጊያ መኖሩን ማመኑ፣ ደቡብ አፍሪካዊው በስጦታ ያገኘው ብልት ለእጮኛው ተርፎ ማስረገዙ መዘገቡ፣ በሆንግ ኮንግ የሚገኘው ቆንስላ በህግ ወጥ ንግድ መሰማራቱ መጋለጡ የሚሉና ሌሎችም አሉን -

Habitamuአቶ ወረታው ዋሴ የሰማያዊ ፓርቲ የፋይናንስ ጉዳይ ሀላፊ በድህረ ምርጫ የተቃዋሚዎች ዝምታን አስመልክቶ ጠይቀናቸው ከሰጡት ምላሽ የተወሰደ  (ሙሉውን ያዳምጡ) <…በቀጥታ አይከል ከተማ ከላይ አርማጭሆ የመጡ ሶስት ወጣቶች ሻይ ቤት ተቀምጠው እያለ ታጣቂዎቹና ፖሊሶች በአንድነት መጥተው ወጣቶቹ ላይ ጥቃት ሲፈጽሙ ሰው ግልብጥ ብሎ አትነኳቸውም ልጆቻችንን አለ በዚህ ጊዜ ወደ ሕዝቡ ተኮሰው አምስት ገለው ስድስት ቆስለዋል..እንዴት ሰላማዊ ሰው ላይ በመሳሪያ ጭፍጨፋ ይደረጋል?..> በሰሜን ጎንደር የተፈጸመውን ግድያ አስመልክቶቃለ መጠይቅ (ሙሉውን ያዳምጡ) <…ሁበር ኤክስ ለቬጋስ አያዋጣም የሚያዋጣው ብላኩ ነው እሱ እንዲፈቀድ መታገል ጥሩ ነው ካልሆነ የቲፕ ነገር የግድ በስብሰባ መነሳት አለበት…> አሌክስ አበራ ከሳን ፍራሲስኮ ስለ ሁበር የግል ልምዱን መሰረት አድርጎ ከሰጠው ማብራሪያ  (ውይይቱን ያዳምጡት) ከኒዮርኩን እስር ቤት ያመለጡት መጨረሻ ያለመታወቅ የፈጠረው ጭንቀት እና ያልተሳካው በመቶዎች የሚቆጠሩ ፖሊሶች አሰሳ( ልዩ ዘገባ) በውጭ የሚኖረው ነጻነት ናፋቂ ኢትዮጵያዊ በጭብጨባ ተገቢውን ትኩረት አግኝቷል? (ምልከታ) ሌሎችም ዜናዎቻችን የአፍሪካ ህብረት የጦር ቃል አቀባይ አልሸባብ ከኢትዮጵያ ወታደሮች ጋር መዋጋቱን አመነ ኢትዮጵያዊው በእንግሊዝ ሁለት የጥበቃ ሰራተኞችን በጠርሙስ ልትገድል ነበር በሚል ከሰባት ዓመት በላይ እስር ተፈረደበት በሆንግ ሆንግ የኢትዮጵያን ቆንስላ የሚመሩት ባለስልጣን በህገ ወጥ የዝሆን ጥርስ ዝውውር እንዳሉበት ተዘገበ በሰሜን ጎንደር የአገዛዙ ታጣቂዎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ ተኩሰው አምስት ሲገድሉ ስድስት ማቁሰላቸው ታወቀ የደቡብ አፍሪካው ፍርድ ቤት በአልበሽር ላይ ያስተላለፈው ውሳኔ አለመከበር ቅሬታ ፈጠረ  የሰው ብልት በበስጦታ ያገኘው ደቡብ አፍሪካዊ ከእጮኛው ልጅ ማግኘቱ ተዘገበ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የይስሙላውን ምርጫ የመቶ በመቶ አሸነፍኩ ማለቱ  አገዛዙ የማጭበርበር አቅም ማጣቱን ያሳያል ብሏል የኢትዮጵያው ዋሊያ የሌሴቶን ቡድን 2 ለ1 አሸነፈ የሱዳኑ ፕሬዝዳንትን የደቡብ አፍሪካ ባለስልጣናት የፍርድ ቤት ውሳኔ በመጣስ ከአገር እንዲወጡ መፍቀዳቸው ተዘገበ  ሌሎችም ዜናዎች አሉ (ህብርን ከዘሐበሻ፣አፍሮ አዲስ ድህረ ገጾችእና በሌሎችም ያዳምጡ።  በተጨማሪ  በማንኛውም ቀን በስልክ ለማዳመጥ 2139924347 ይደውሉ)ነ Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢውሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8  ሰዓት በ1340 ኤ.ኤም  የአየር ሞገድ ያዳምጡ። በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው። 

‹‹ለህዝባዊ እምቢተኝነት ሁኔታዎች ተመቻችተዋል›› – የእስክንድር ነጋ መልዕክት ከቃሊቲ እስር ቤት

‹‹ለህዝባዊ እምቢተኝነት ሁኔታዎች ተመቻችተዋል››
የእስክንድር ነጋ መልዕክት ከቃሊቲ እስር ቤት
21017_723668881092106_8730743743929156513_nበሰላማዊ ትግል ውስጥ ሁለት አብይት የትግል ስልቶች አሉ፡፡ አንደኛው ገለልተኛ የዴሞክራሲ ተቋማትና ህግጋት ባሉበት ነባራዊ ሁኔታ የሚደረግ ህዝብን ያሳተፈ ምርጫ ነው፡፡ ምርጫ ሲባል ዝም ተብሎ ለማስመሰልና የአምባገነኖችን የስልጣን እድሜ ለማራዘሚያነት የሚደረገውን አይጨምርም፡፡ ምርጫ ሲባል ዓለም አቀፍ መመዘኛዎች ያሉት ነው፤ መመዘኛዎችን ባሟላ መልኩ የሚደረግ ምርጫ፣ ምርጫ ሊባል ይችላል፡፡
አምባገነን ስርዓቶች ምርጫ ሲያደርጉ አስተውለናል፤ ግን የይስሙላ ነው፡፡ ግብጽ በሙባረክ ጊዜ ምርጫ ታደርግ ነበር፡፡ ብዙ አምባገነኖች ምርጫ አደረግን ይላሉ፡፡ ኢህአዴግም ምርጫ አደረግሁ ይላል፡፡ በእነዚህ ስርዓቶች የተደረጉት ምርጫዎች ግን ዴሞክራሲያዊ ሆነው አላየናቸውም፡፡ በዚህ ምክንያት ምርጫን እንደ ሰላማዊ የትግል ስልት አማራጭ አድርገው ይመለከቱ የነበሩ ዴሞክራሲያዊ ኃይላት ፊታቸውን ወደ ሌላኛው ስልት እንዲያዞሩ ይገደዳሉ፤ እሱም ህዝባዊ እምቢተኝነት ነው፡፡ በግብጽ የሆነው ይኸው ነው፡፡

አንድ ነገር ማስተዋል አለብን…የምርጫ ስልት ተዘጋ ማለት ሰላማዊ ትግል አበቃለት ማለት አይደለም፡፡ ይልቁንስ ወደሌላኛው ምዕራፍ ተሸጋገረ ማለት እንጂ፡፡ ምርጫ ሲያበቃለት ህዝባዊ እምቢተኝነት አማራጭ ይሆናል፡፡ አሁን በኢትዮጵያ ሁኔታዎች ለህዝባዊ እምቢተኝነት ተመቻችተዋል፡፡ አሁን ህዝቡ በምርጫ ላይ ያለውን አሰራር አስረጅ ሳያስፈልገው ራሱ አይቶታል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በኋላ አማራጩ ህዝባዊ እምቢተኝነት እንደሆነ መገንዘብ ግድ ይለናል፡፡ ህዝባዊ እምቢተኝነት ህጋዊና ሰላማዊ የትግል ስልት መሆኑን ዓለም ይገነዘባል፡፡

በዚህ ወቅት ስለህዝባዊ እምቢተኝነት የሚሰሩ አካላት ካሉ መንገዳቸው ልክ ነው፤ ሊገፉበትም የሚገባ ነው፡፡ በእርግጥ ህዝባዊ እምቢተኝነት ላይ በቅድሚያ መግባባት ላይ መድረስ ያለባቸው አካላት አሉ፣ ዋነኛዎቹ ‹አክቲቪስቶች› ናቸው፡፡ አክቲቪስቶች መግባባት ላይ ደርሰው ህዝቡን የማነቃነቅ ስራቸውን በጋራ ቢያከናውኑ አንድነቱን ያጠናከረ እንቅስቃሴ መተግበር ይቻላል፡፡

እስካሁን በተገለጸው የ2007 ‹‹ሀገራዊ ምርጫ›› (በትምህርተ ጥቅስ አስገባልኝ) ውጤት እጅግ ደስተኛ ነኝ፡፡ አዎ፣ የተለያየ ፍላጎትና ጥቅም ያላቸው ኢትዮጵያውያን በሙሉ ተስማምተው አንድ ፓርቲ መረጡ ቢባል ለሰሚውም ቀልድ ነው፡፡ ይህ ተፈጥሯዊ ያልሆነ ውጤት ነው፡፡ ይህ የሚያሳየው ኢህአዴግ ለማጭበርበር እንኳ አቅም እንዳጠረው ነው፡፡ ለዚህም ነው በውጤቱ ደስ የተሰኘሁት፡፡ ውጤቱ በግልጽ የሚነግረን ከዚህ በኋላ ለሚመጣው ህዝባዊ እምቢተኝነት ዋናው ገፊ ምክንያት ኢህአዴግና የኢህአዴግ ስርዓት መሆኑን ነው፡፡ እናም ህዝባዊ እምቢተኝነት በኢትዮጵያ ‹ጀስቲፋይድ› ነው፡፡

በእርግጥም አሁን ያለው የኢህአዴግ ስርዓት ለራሳቸው ለኢህአዴግ አባላት እንኳ አሳፋሪ እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ የማስመሰል ካባው እንኳ አላስፈለገውም፤ ሁሉንም ነገር ከርችሞታል፡፡ እናም ቀጣዩ ትግል የነጻነት ትግል ነው፡፡ ይህን የነጻነት ትግል ዳር የሚያደርሰው ማሳረጊያ ደግሞ ህዝባዊ እምቢተኝነት እንደሆነ አምናለሁ፡፡ ህዝባዊ እምቢተኝነት ኢህአዴግ ራሱ መርጦ ለህዝቡ የተወው እንደሆነ መረዳት አለብን፡፡ የታፈነ ህዝብ ሲነሳ ማዕበል ነው፣ አምባገነኖችን ይጠራርጋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው አፈና ህዝባዊ እምቢተኝነት አይቀሬነቱን በግላጭ ያረጋግጣል፡፡

አልሸባብ 30 የኢትዮጵያ ወታደሮችን መግደሉንና ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን ማውደሙን ገለፀ -

Dead_AMISOM_Forces (1)ሚዮ በተባለ መንደር የሚኖሩ ነዋሪዎች በሁለቱ ሃይሎች መካከል ከፍተኛ ጦርነት መካሄዱንና ከባድ የጦር መሳሪያዎች ሲተኮሱ መስማታቸውን ተናግረዋል።አልሸባብ አገኘሁት ያለውን ድል በተመለከተ ከኢትዮጵያ መንግስት በኩል የተበባለ ነገር የለም። ነዋሪዎችን ዋቢ በማድረግ ሆርሲድ ሚዲያ እንደዘገበው ደግሞ የአልሸባብ ተዋጊዎች የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን የጫኑ ወታደሮችን አድፍጠው በመጠበቅ ጥቃት ፈጽመዋል።ለ12 ሰአታት ያክል የቆየ በከባድ መሳሪያዎች የታጀበ ጦርነት መካሄዱን ነዋሪዎች ገልጸዋል። አልሸባብ በጥቃቱ 30 ወታደሮችን መግደሉንና ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን ማውደሙን ገልጿል። ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የአካባቢው ባለስልጣን የኢትዮጵያ ወታደሮች ተጨማሪ ሃይል እንደሚጣላቸው ጥያቄ ማቅረባቸውን ጋዜጣው ዘግቧል። ሞቃዲሾን ከደቡቡ ክፍል ጋር በሚያገናኘው መንገድ ላይ ተደጋጋሚ የደፈጣ ጥቃት ይፈጸማል። ሚያዚያ ላይ 6 የአፍሪካ ህብረት ተዋጊዎች በተመሳሳይ መንገድ ተገድለዋል። የኢትዮጵያ ጦር ወታ ገባ በማለት በሶማሊያ ከ7 አመታት በላይ አስቆጥሯል። ካለፈው አመት ጀምሮ በአፍሪካ ህብረት ስር ሆኖ በባይዶዋ አካባቢ ጥበቃ እያደረገ ነው። 

የአንድነቱ አብርሃም ልጃለም በረሃ ወርዶ የብረት ትግሉን ተቀላቅሏል – ከዳዊት ሰለሞን -

የአንድነቱ አብርሃም ልጃለም የቀድሞው አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ከዓመት በፊት ጠቅላላ ጉባኤውን በአዲስ አበባ ሲያከናውን ከየክልሉ የመጡ ተሳታፊዎችን የማግኘትና በክለላቸው ስለሚያደርጓቸው እንቅስቃሰዎች፣ስለሚደርስባቸው እስራት፣ወከባ፣ድብደባና ስለሚፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እንዲያካፍሉን የፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ ባልደረቦች እንወተውታቸው ነበር፡፡
የአንድነቱ አብርሃም ልጃለም
የአንድነቱ አብርሃም ልጃለም
አብርሃም ልጃለም ከጎንደር አካባቢ ወደ አዲስ አበባ ለጠቅላላ ጉባኤው የራሳቸውን የትራንስፖርት ወጪ ችለው ከመጡ የክልሉ የአንድነት አመራሮች አንዱ ነው፡፡ጎንደሮች አዲስ ሲመጡ ባዶ እጃቸውን አልመጡም፡፡ገበሬውን ወላጅ አባቷን በመኖሪያ ቤቱ በጥይት ደብድበው ከገደሉት በኋላ በተኛችበት የመደብ አልጋ በተተኮሰባት ጥይት የቀኝ እጇን ለመቆረጥ የበቃችን የስምንት ዓመት ታዳጊ ወጪዋን ሸፍነው አምጥተዋት ነበር፡፡
አብርሃም ልጃለምና ጓደኞቹ በክልላቸው ስለሚፈጸም የመብት ጥሰት የሚያወሩት በቃል አይደለም፡፡ስለሚያወሩት ነገር በሙሉ መረጃዎች አጠናቅረው ዶሴ አዘጋጅተው ሌላው ቀርቶ ኢህአዴግ አካባቢውን ከተቆጣጠረበት ግዜ አንስቶ ጠቅላላ ጉባኤው እስከተደረገበት ወቅት ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ የተገደሉ ሰዎችን ስም ዝርዝር እስከ አያታቸው መዝግበው ይዘዋል፡፡
የ2007 ምርጫ ለኢህአዴግ በክልላቸው የመጨረሻ እንደሚሆን በድፍረት የሚናገሩት እነ አብርሃም ምርጫው ከመድረስ አስቀድሞ ምርጫ ቦርድ የተባለ መራጭ አንድነትን ለትዕግስቱ መስጠቱን ተከትሎ ህልማቸው ተዘረፈ፡፡አፍታም ሳይቆይ የአብርሃም አካባቢ የአንድነት አባላት በገዢው ፓርቲ ፖሊሶች ታስረው ማዕከላዊ ተወሰዱ፡፡
አብርሃምና ከአፈናው የተረፉት የአርማጭሆ ልጆች ተማከሩ፡፡ከአሁን በኋላ ምን ቀረን የሚለው ጥያቄ የምክራቸው ማጠንጠኛ ነበር፡፡ፓርቲያቸው ፈርሷል፣ሰላማዊ ትግልን የቆረቡበት ያህል ጸንተው ያጸኗቸው ጓዶቻቸው ‹‹ሽብርተኛ››ተሰኝተው ደብዛቸው እንዲጠፋ ተደርጓል፡፡እናማ ቀሪዎቹን የወሰዱ እግሮች እያንዳንዳቸው ደጃፍ ከመድረሳቸው አስቀድሞ ቀደሟቸው፡፡
አብርሃምን በምስሉ እንደምትመለከቱት በረሃ ወርዶ ከሐሳቡ ውጪ የነበረውን መንገድ ተቀላቅሏል፡፡ከ15 የማያንሱ የጎንደር አካባቢ የቀድሞ የአንድነት አባላትም ዛሬ በአብርሃም መንደር ይገኛሉ፡፡

Wednesday, June 10, 2015

ከእዚህ በላይ ያለው ፎቶ በአንድ ወቅት ጠላት የነበሩ ሀገሮች መሪዎች ፕሬዝዳንት ኦባማ እና የጀርመን ቻንስለር አንግሌ መራክልከሶስት ቀናት በፊት በቡድን 7 ስብሰባ ወቅት በእረፍት ሰዓት ሲነጋገሩ ያሳያል። -

 ከእዚህ በላይ ያለው ፎቶ በአንድ ወቅት ጠላት የነበሩ ሀገሮች መሪዎች ፕሬዝዳንት ኦባማ እና  የጀርመን ቻንስለር አንግሌ መራክልከሶስት ቀናት በፊት በቡድን 7 ስብሰባ ወቅት በእረፍት ሰዓት  ሲነጋገሩ ያሳያል።የጣልያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ማተዎ ረንዚ ( Matteo Renzi) በሶስት ቀናት ልዩነት ውስጥ ብዙ ሥራ እንደሚሰሩ አስመሰከሩ።በሩስያ ላይ እቀባ ካደረጉት ከቡድን ሰባት አባላት ጋር ስብሰባ ተቀምጠው ሩስያ ስትታማ እና ምናልባትም ሲያሟት ከርመው  ዛሬ ዘወር ብለው የሩስያውን ፕሬዝዳንት ፑቲንን  በሀገራቸው እያስተናገዱ ነው።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፑቲን ጋር በጋራ በጣልያኗ ከተማ ሚላኖ በሰጡት መግለጫ ”ሩስያ ለዓለም ጠቃሚ ሀገር መሆኗን እና ሽብርተኝነትን ጨምሮ ብዙ የጋራ አጀንዳ ከአውሮፓ ጋር ያላት መሆኑን”ሲያብራሩ ፑቲን እራሳቸውን ወደላይ እና ወደታች እያደረጉ አድንቀውላቸዋል።ይህ ጣልያን ነው።ጣልያን እጥፍ ሲል እንደ ሮማ መንገዶች ነው።ለነገሩ በሩስያ ላይ የተደረገው እቀባ ለአውሮፓ ብዙም እንዳልተመቸው በብርቱ ይታመናል። - 

የስርዓቱን ብልግና ለመድነው – ጌታቸው ሺፈራው

ነገረ ኢትዮጵያ - የሰማያዊ ፓርቲ አባላትአሁን አሁንማ ዜና የሚሆን ነገር ጠፍቷል፡፡ መታሰር ተለምዷል፡፡ መደብደብ ተለምዷል፡፡ የሀሰት ምስክርነት ተለምዷል፡፡ ከአሁን ቀደም ‹‹ጉድ ነው!›› ያሰኙ የነበሩ ህገ-ወጥነቶች አሁን የቀን ተቀን ተግባር ሆነው ወደ ጎን እያየን እየተውናቸው ነው፡፡ በአጠቃለይ የስርዓት ነውር፣ ብልግና፣ ስርዓት አልበኝነትን ለዜናም የሚበቁ አልሆኑም፡፡ በአንድ ወቅት ‹‹እንትና ጠያቂ ተከለከለች፣ እንትና ምግብ እንዳይገባለት ተደረገ›› ተብሎ ዜና ይሰራ ነበር፡፡ እንደ ትልቅ የስርዓቱ ብልግና እና ነውርም ተደርጎ ይታይ ነበር፡፡ እንዲያውም ይህ አይነት በደል የሚፈፀምባቸው በፀረ ሽብር ህጉ ተከሰው የሚታሰሩ ኢትዮጵያውያን ብቻ ነበሩ፡፡ አሁን በሰልፍና በሌሎች ሰበቦች የሚታሰሩ ኢትዮጵያውያን ላይ ይህ በደል እየተደጋገመ ወደ ተራ አሰራርነት (የስርዓቱ ህግና ደንብ) ተቀይሯል፡፡ ነውር ቢሆንም እኛ ግን ለምደነዋል፡፡
ዛሬ በጠዋት ተነስተን ከኢ/ር ይልቃል ጌትነት ጋር ቃሊቲና ቂሊንጦ የሚገኙ እስረኞችን ለመጠየቅ አቀናን፡፡ መጀመሪያ ወደ ቃሊቲ ስንሄድ ኢ/ር ይልቃል ቃሊቲ የታሰሩትን የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ጠያቂዎች ስም ዝርዝር ላይ ስሙ እንዳለ በማወቅ ነበር፡፡ ህገ መንግስቱ እስረኞች በዘመዶቻቸው፣ በህግ አማካሪዎቻቸው፣ በሀኪሞቻቸው፣ በጓደኞቻቸው የመጠየቅ መብት እንዳላቸው ቢደነግግም እስረኞቹ ግን ‹‹የሚጠይቃችሁን የጥቂት ሰዎች ስም ዝርዝር አስቀምጡ›› ተብለው ተገደዋል፡፡ ‹‹አይ! መብታችን ነው፡፡ ማንም ሊጠይቀን ይገባል!›› ያሉት ደግሞ ከእነአካቴው እንዳይጠየቁ ተደርገዋል፡፡ እኛ ይህንንም ስለለመድነው እስረኛ ለመጠየቅ ‹‹የጠያቂ ስም ዝርዝር ላይ ተመዝግበሃል?›› መባባል አዲስ አይደለም፡፡ ይህ ማጎሪያ ቤቶቹ ህገ መንግስቱን በአፍ ጢሙ ገልብጠው ያወጡት ‹‹ህገ አራዊት››› ነውር ቢሆንም እኛ ግን ለምደነዋል፡፡
የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶች የሚጠየቁት ከ6፡00 – 6፡30 ባለው ጊዜ ነው፡፡ በ24 ሰዓት ውስጥ ለ30 ደቂቃ ማለት ነው፡፡ ይህም ቢሆን ማረሚያ ቤቱ ያወጣው ሌላኛው ነውር ነው፡፡ ያም ሆኖ በ30 ደቂቃ ውስጥ ለመጠየቅ እንዲያውም እንዳይዘጋብን ተጣድፈን እንሄዳለን፡፡ ለዛምው እድሉን ያገኘ ‹‹ዛሬ እኮ ገባሁ!›› እያለ እንደ እድል ማውራት ሁሉ ተጀምሯል፡፡ ለ30 ደቂቃ ያህል እነ ወይንሸትን ለመጠየቅ እየተጠባበቅን ባለንበት ወቅት አንዱ መዝጋቢ እኛ የተቀመጥንበት አካባቢ ሆኖ መመዝገብ ጀመረ፡፡ ሁለት ታሳሪ ለመጠየቅ የጓጉ የሚመስሉ ወጣቶች ለመመዝገብ ቀርበዋል፡፡
‹‹ማንን ነው የምትጠይቀው?
‹‹አቡበክር አህመድን!››
‹‹ምኑ ነህ?››
‹‹ጓደኛው!›› መዝጋቢው ትንሽ ተጨነቀና ሌላ ነውሩን የሚያስቀጥልበት ጥያቄ ጠየቀ፡፡
‹‹ከአሁን ቀደም ገብተህ ታውቃልህ?››
‹‹አዎ! በቀደም ዕለት ገብቻለሁ!›› የገባበት ቀን ሩቅ ቢሆን ኖሮ ከዛ በኋላ የወጣ ህግ እንዳለ በመግለጽ እንዳይጠይቅ ለመከልከል ይመስላል፡፡ ግን ነውር ተለምዶ የለ?! ‹‹ጓደኛው ነኝ›› ብሎት ወደ ሌላ ጥያቄ አልፎ ያነሳው ጥያቄ ለመከልከል የሚያስችል ባለመሆኑ ወደ ኋላ ተመልሶ ‹‹ጓደኛ መጠየቅ አይችልም፡፡ ለመጠየቅ ዘመድ መሆን አለብህ፡፡ አባት፣ እናት፣ወንድም..››
‹‹እንዴ! በቀደምኮ ጠይቄዋለሁ!››
‹‹አይቻልም! ከላይ የመጣ ትዕዛዝ ነው!››
በእርግጥ እናት፣ አባት፣ ወንድም መሆኑን ይህን ነውር አያስቀረውም፡፡ ምክንያቱም ቂሊንጦ ታስረው የሚገኙት እነ ብርሃኑ ተክለያሬድ፣ እነ ናትናኤል ያለም ዘውድ ‹‹ማንም ሊጠይቀን ይገባል፡፡ ህገ መንግስታዊ መብታችን ነው፡፡›› በማለታቸው በቤተሰቦቻቸውም ጭምር እንዳይጠየቁ ተደርገዋል፡፡ አቡበክርን ለመጠየቅ ወደ ቃሊቲ የሄዱት ወጣቶችም ዘመድ ቢሆኑ የሆነ ምክንያት ተመዞላቸው መመለሳቸው አይቀርም ነበር፡፡ ምክንያቱም ከዛ ቤት ነውር ተለምዷል፡፡ እኛም ለምደንላቸዋል፡፡
በዚህ እየተገረምኩ እያለ አንድ እነ ወይንሸትን ለመጠየቅ እንደመጣን የገባው ወጣት ወደመዝጋቢዋ ጠቆመን፡፡ ኢ/ር ይልቃል መታወቂያውን አሳይቶ ወይንሸት ሞላን እንደሚጠይቅ ለመዝጋቢዋ ነገራት፡፡ ወይንሸት ሞላ ያስመዘገበቻቸው ጠያቂዎች ስም ዝርዝር ተፈለገ፡፡ የኢ/ር ይልቃልን ጨምሮ ወይንሸትን የሚጠይቁ ሰዎች ስም ዝርዝር ይታያል፡፡ የኢ/ር ይልቃል ስም የመጀመሪያ ተራ ቁጥር ላይ ነው፡፡ ግን በኮምፒውተር የተፃፈው የስም ዝርዝር ላይ የኢ/ር ይልቃል ስም መሃል ለመሃል አንድ ጊዜ በእስክርቢቶ ተሰርዟል፡፡ ምን አልባት የኢ/ር ይልቃልን ስም መጀመሪያ ላይ ያየው የህወሓት/ኢህአዴግ ካድሬ በንዴት የሰረዘው ይመስለኛል፡፡ መዝጋቢዋ የሆነ ደስ ያላት ትመስላለች፡፡ ‹‹ተሰርዟል!›› አለች፡፡ ህግ ጠቅሳ መከራከር የምትችል ያህል በልበ ሙሉነት ነው የምትናገረው፡፡ በኮምፒውተር የተፃፈ ስም ዝርዝር ላይ በእስክርቢቶ ሰርዘው አትገባም ከሚሉ ሌላ የኢ/ር ይልቃል ስም የሌለበት ስም ዝርዝር ቢያስቀምጡ የጠያቂዎች ስም ዝርዝር ላይ የለህም ማለት ይችሉ ነበር፡፡ ግን ደግሞ ያ ነውራቸውን ሊቀንሰው ሆነ፡፡ ነገሩ ለማንስ ተጨንቀው? ምንስ ይመጣባቸዋልና?
በአንድ ወቅት ነገረ ኢትዮጵያ የህግ ባለሙያውን ተማም አባቡልጉን ይህን ለ30 ደቂቃ ብቻ መጠየቅ እና ጠያቂን መከልከልን በሚመለከት ጥያቄ አቅርባለት ነበር፡፡ ተማም እንደሚለው ይህ አሰራር ከህገ መንግስቱም፣ ከሞራልም፣ ከኢትዮጵያዊ ባህልም የሚቃረን ነውር ነው፡፡ እሱስ ብልግናም ነው ይለዋል፡፡ ተማም ‹‹በ21ኛው ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያን በምታክል ትልቅ አገር እንዲህ አይነት ነገር መከሰቱ በእውነቱ ነውር ነው፡፡….እንዲያውም ለእኔ ይህ ብልግና ይመስለኛል፡፡›› ይላል፡፡
አንድ ሰው የሚታሰረው ከጥፋቱ ይታረም ዘንድ ለማስተማር ነው፡፡ ነገር ግን አሁን የሚፈፀመው በደልና ግፍ ስርዓቱ ሲያስር ከዛም በላይ ዓላማ እንዳለው የሚያሳይ ነው፡፡ ተማምም ‹‹ሰውን ካሰርከው በኋላ የግል ጉዳይ የለህም፡፡ …. የግል ካልሆነ ደግሞ በግለሰብ የሚፈጸም በቀል አይኖረውም፡፡ ምክንያቱም የግል ጉዳይ አይደለም! …የግል የሚሆነው ሰዎች ህግን ለተወሰነ ሰው አድርገው ስለሚወስዱት ነው፡፡›› ይላል፡፡
እውነት ነው! መጀመሪያ ነገር እነ እስክንድር፣ አንዱዓለም፣ ወይንሸት፣ አበበ ቀስቶ፣ ተመስገን ደሳለኝ፣ በፍቃዱ ኃይሉ፣ የሽዋስ አሰፋ ….. የታሰሩት አጥፍተው መታረም ስለሚያስፈልጋቸው አይደለም፡፡ መታረም ላቃተው ስርዓት የራስ ምታት ስለሆኑበት እንጅ፡፡ እንደ በደል ከተቆጠረ የእነዚህ ሰዎች በደል በህጋዊ መንገድ ህገ ወጥ ስራ የሚሰራውን ስርዓት በመቃወማቸው ነው፡፡ ህግ ደግሞ የስርዓቱ ቁንጮ ሰዎች የግል ንብረትና ማጥቂያ መሳሪያ ሆኗል፡፡ ለህዝብና ለሀገር ዋስትና ከሚሆን ህገ መንግስት ይልቅ የራሳቸው፣ የግላቸው ‹‹ህገ አራዊት›› ነግሷል፡፡ ይህ ህገ አራዊት ደግሞ ለበቃል እንጅ ለፍትህ ቦታ የለውም፡፡ መብቱን የጠየቀ መልሱ በቀል ነው፡፡ ስርዓቱን በህጋዊ መንገድ የጠየቀ መልሱ በቀል ነው፡፡ ምግብ እንዳይገባለት መከልከል፣ ጠያቂ እንዳይገባለት ማድረግ፣ ማሰቀየት፣ መስለብ፣ …..ስቀይ፣ ነውር….፡፡ እኛም ቢበዛ፣ ቢደጋገም…ይህንን ነውር፣
የስርዓት አልበኛውን ስርዓት ብልግና ለመድነው፡፡

ምርጫም ቅርጫም መሆን ያልቻለው የ2007ዓ.ም. አምስተኛው ዙር ግርግር ትዕይንቱ! – ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው -

በአህጉራችን አፍሪካ ዲሞክራሲያዊ ፍትሐዊ ተአማኒና ነጻ ምርጫዎች እየተኪያሔዱ መንግሥታት የመቀያየሩ ሒደት ከጀመረ 20 ዓመታት አለፉ፡፡ ለዘመናዊ ሥልጣኔና ዲሞክራሲ (በይነ ሕዝብ) ባይተዋር በመሆኗ በዚህም ምክንያት ድሀ በመሆኗ “ጨለማዋ አህጉር” በመባል በምትታወቀዋ አህጉራችን ዛሬ ላይ በትክክለኛና ተአማኒ በሆነ መንገድ ነጻና ፍትሐዊ ምርጫ በተደጋጋሚ በማኪያሔድ ወደ 10 የሚደርሱ የአፍሪካ ሀገራት አዳዲስ መንግሥታት ተመሥርተው ዲሞክራሲያዊ (በይነ ሕዝባዊ) በሆነ የመንግሥት ሥርዓት እየተዳደሩ ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህ ሀገራት የሚበዙቱ ከሰሀራ በታች ያሉ ሀገራት ናቸው፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያ በብዙ ነገር ለአፍሪካ ሀገራት ዓርአያ እንደመሆኗና የረጅም ጊዜ ሥልጣኔ ባለቤት እንደመሆኗ ዲሞክራሲያዊ (በይነ ሕዝባዊ) ምርጫ አድርጋ ዲሞክራሲያዊ (በይነ ሕዝባዊ) መንግሥት በመመሥረት በዚህ ረገድም ለሌሎቹ የአፍሪካ ሀገራት ምሳሌ አርዓያ መሆን ባለመቻሏና የራሳቸው ሥልጣኔ ባልነበራቸው በቅኝ ግዛት በደቀቁት ሀገራት በመቀደሟ የማያዝን የማይቆጭ የማይቃጠል የማይንገበገብ በይነ ሕዝባዊ መንግሥት በሀገራችን እንዲመሠረት የድርሻውን የማይፍጨረጨር ሕዝቧን የሚጨቁን ሀገሪቱን የሚበዘብዘው ዘገዛዝ ተባባሪና አጋር ዜጋ ካለ በተለይም ደግሞ “የተማርኩ ነኝ” የሚል ከሆነ የተሟላ ጤና ላይ እንዳልሆነና ለዚህች ሀገርና ሕዝቧ ጠላት እንደሆነ እርግጠኛ መሆን ይኖርበታል ተምሬያለሁ ብሎም ሊያስብ ፈጽሞ አይገባም፡፡
andnet-blue-mergeበዘመነ ወያኔ ለ5 ዙር ያህል ምርጫ መሰል ግርግር ተደርጓል፡፡ ይሁን እንጅ እነዚህ ግርግሮች አንዳቸውም ምርጫ አልነበሩም፡፡ በዘመነ ወያኔ ምርጫ ተደርጎ አያውቅም፡፡ በእርግጥ የ3ኛው ዙር ማለትም 1997ዓ.ምሕረቱ ብሔራዊ ምርጫ እስከ ምርጫው ማግስት የነበረው ሁኔታ አንጻራዊ በሆነ መልኩ በጣም ጥሩ የሚባል ነበር፡፡ እሱም ቢሆን ግን ከምርጫው ማግስት በኋላ ከሆነው ነገር መረዳት እንደምንችለው ከምርጫው ማግስት በፊት የነበረው ሁኔታ እንደዛ ሊሆን የቻለበት ምክንያት ወያኔ በሕዝብ ምርጫ ለሚመሠረት መንግሥት ቦታውን ለመልቀቅ ፈቃደኛ ስለነበረ ወይም ይለው እንደነበረው ሁሉ ነጻ ፍትሐዊና ተአማኒ የሆነ እንከን የለሽ ምርጫ አድርጎ ለታሪኩ ጥሩ ስም ለመተው ስለወሰነ፣ ለዲሞክራሲ (ለመይነ ሕዝብ) ታማኝነቱን ለማረጋገጥ ሲል ያደረገው አልነበረም፡፡ ነገር ግን ከዚያ ምርጫ በፊት ሥልጣን ከያዘ ጊዜ ጀምሮ ጠንካራ ተቃዋሚ ወይም ተወዳዳሪ ፓርቲ አይደለም እንደ የመምህራን ማኅበርን፣ የሠራተኛ ማኅበራትን፣ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበርን የመሳሰሉትን ሲቪክ (ሕዝባዊ) ማኅበራትን ሁሉ ሳይቀር አንባገነናዊና ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ እየበተነና እያስወገደ ጠንካራ ሲቪክ (ሕዝባዊ) ማሕበራት እንኳን እንዳይፈጠሩና ተፈጥረውም ለጠንካራ የፖለቲካ ፓርቲዎች መፈጠር ምክንያትና ዓርአያ እንዳይሆኑ ሲሠራው በነበረው ጥቃት ሸር አሻጥር ጫና ጥቃት ውክቢያና ስውር ደባ ሊፎካከረው የሚችል ጠንካራ የፖለቲካ ፓርቲ እንደሌለና እንደማይኖርም በመተማመኑ በዓለማቀፉ ማኅበረሰብ ፊት ጉራውን ለመንፋትና ዲሞክራሲያዊ (በይነ ሕዝባዊ) ለመባል ሲል የዚያን ምርጫ በር ከፍቶት ነበር፡፡
ይህችን ቁማር የተረዷት ምሁራን “ምርጫው እንከን የለሽ ይሆናል” ተብሎ ከታወጀ ከምርጫው ጥቂት ወራት አካባቢ ሲቀር ጀምረው ልዩ አጋጣሚውን ለመጠቀም በመወሰን እነ ዶ/ር ብርሃኑ እነ ፕሮፌሰር መስፍንና ሌሎች አጋሮቻቸው ተፋጥነው ቀስተ ደመናን መሠረቱና አስቀድመው ከነበሩ ሌሎች ፓርቲዎች ጋር በመቀናጀት “ቅንጅት” የተባለን ጉደኛ ፓርቲ ፈጥረው ወደ ምርጫው ገቡ፡፡
election-2015-ethiopiaበወቅቱ ወያኔ አስቀድሞ “መጥታቹህ ታዘቡልኝ እንከን የለሽ ምርጫ አደርጋለሁ!” ሲል አውጆ ለምዕራባዊያኑ በገባው ቃል መሠረት ከምዕራባዊያኑ ከየአቅጣጫው የሚለቀቅለትን የውዳሴ ዜማ በተመስጦ በማዳመጥ ተጠምዶ ስለነበር ምርጫው ሊደረግ በጣት የሚቆጠሩ ቀናት እስኪቀር ድረስ ወያኔ የቅንጅትን መቅሰፍትነትና “ጠንካራ ፓርቲ አላደለንም” የሚለውን የምጸት ጸሎቱን አምላክ ሰምቶለት እንዲያውም እሱ ከፈለገውና ሊቋቋመው ከሚችለው በላይ ጠንካራ ፓርቲ በድንገት እንደሰጠው በቅጡ አልተረዳም ነበር፡፡ በተረዳ ጊዜም ቢሆን የምርጫው ቀን በጣት የሚቆጠሩ ቀናት ብቻ የቀሩት ከመሆኑና ታዘቡልኝ ተብለው ተጠርተው የመጡት ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች ተገኝተው እየሆነ ያለውን ሁሉ እየታዘቡ ከመሆናቸው አንጻር የሚያደርገው ጠፍቶት በመንተፍረቱ ምርጫውን በነጻነት መምረጥ እንዲቻል አድርጎ ነበር፡፡ ምንም እንኳን ካድሬዎቹ ከምርጫው ቀን በፊት በየቦታው እጅግ ከመጨነቃቸው የተነሣ አንዳንድ ችግሮችን መፍጠራቸው የቀረ ባይሆንም ቅሉ፡፡
በምርጫው ማግስት ግን ወያኔ የማስመሰሉን ጨዋታው የወለደውን ውጤት መቀበል ፈጽሞ የሚቻል ስላልሆነበት “ጨዋታ ፍርስርስ” የሚልበት ሰዓት ያ ሰዓት እንደሆነ በመረዳቱ የኢትዮጵያን ሕዝብ ድምፅ በማስወገድ ምርጫውን ወደ ቅርጫ በመለወጥ አብዛኛውን ለራሱ በመውሰድ ይሄንን ያህል ወንበር ይበቃቹሀል ብሎ ለተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በኮታ አከፋፍሎ ሰጠ፡፡ በዚህ አንባገነናዊ ወንጀሉም ሕዝብ ተቆጣ፡፡ ወያኔም በጭካኔ ያደረገውን ሁሉ አድርጎ ዕድሜውን እስከአሁን ድረስ ሊያራዝም ቻለ፡፡ ከዚያ በኋላ ባሉ ሁለት “ምርጫዎች” ግን “የምርጫ 97ዓ.ም. ዓይነት ቅብጠት ሁለተኛ አይለመደኝም” ብሎ ከምርጫ 97ዓ.ም. በፊት ወደ ነበረው አቋሙ በመመለስ “ዲሞክራሲ፣ ፍትሐዊ ነጻ ተአማኒ ምርጫ ብሎ ነገር አይገባኝም ታግየ ነው የመጣሁ ሥልጣን የሚፈልግ አካል ካለ ታግሎ ይምጣ!” የሚል ጠንካራና የማይደራደርበት አቋም በመያዝ ይሄው እንደምታዩት “ምርጫ” የሚል የአንድ ሰሞን የቀልድ ጨዋታ በማዘጋጀት ግርግር እየፈጠረ ያሳልፋል፡፡
ይሄንን 5ኛ ዙር ብሔራዊ የቀልድ ግርግር ምርጫ እንዳንለው የሚከለክሉን ምክንያቶች ወይም ምርጫው ነጻ ፍትሐዊ ተአማኒና ዲሞክራሲያዊ (በይነ ሕዝባዊ) አልነበረም እንድንል የሚያደርጉን ጉዳዮች ምን ምን ናቸው?
ቅድመ “ምርጫ” በነበረው “የምርጫ” ሒደት
  1. የምርጫ ቦርድ አባላት በግልጽ በሚታይ መልኩ ገለልተኛ አለመሆናቸውና ከወያኔ ታጋዮች ባልተናነሰ ለወያኔ ህልውና ዋጋ ለመክፈል የተዘጋጁ በመሆናቸው፡፡
  2. የምርጫ ካርድ ዕደላው “አንድ ካርድ ለአንድ መራጭ” ከሚለው ትክክለኛ አሠራር ወጥቶ የአገዛዙ ደጋፊዎች መሆናቸው ለሚታወቁት ግለሰቦች ከሠላሳ በላይ ካርዶች ለእያንዳንዳቸው የታደለበት መሆኑና ይሄንን በተመለከተም ተወዳዳሪ ፓርቲዎች በመረጃ በተደገፈ ላቀረቡት ክስ ገለልነኛ ነኝ በሚለው የምርጫ ቦርድ ምንም ዓይነት የማስተካከያም ሆነ ሊወስድ የሚገባውን እርምጃ ባለመውሰዱ፡፡ የተቀረው ካርድ ደግሞ የኢትዮጵያ ሕዝብ በምርጫው አመኔታ ያለው ለማስመሰልና ፍላጎቱ ስላለውም ከ1997ቱ በላይ መራጭ ተገኘ ለማሰኘት ዜጎች ያለፍላጎታቸው ቤት ለቤት እየተጎተጎቱ ከመንገድ እየተጎተቱ መታወቂያ የለኝም ላለው ሳይቀር በግዳጅ እንዲወስዱ በመደረጉ፡፡
  3. አገዛዙ ተወዳዳሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ከመሀላቸው ያሉ አባላቶቻቸውን የቻለውን በጥቅም በመደለል ያልቻለውን በማስፈራራት ፓርቲያቸውን እንዲከዱና በፓርቲያቸው ላይ እንዲሸፍጡ ለእሱ እንዲያድሩ በማድረግ አሻጥር በመፈጸም ከሕዝብ ጋር ረዘም ያለ ትውውቅ ያላቸውን ፓርቲዎች መኢአድንና አንድነትን እንደ ቅንጅት ሁሉ እንዲፈርሱ በማድረግ ሕዝቡ “ጠንካራ ተፎካካሪ ፓርቲ የለም” የሚል ቀቢጸ ተስፋ ውስጥ እንዲወድቅ የተደረገበት በመሆኑ፡፡
  4. በተለይም የሰማያዊ ፓርቲ ተወዳዳሪዎችን የምርጫ ቦርድ ተብየው ቅጥረኛነቱን ለማሳየት ለአገዛዙ ታማኝነቱን ለማረጋገጥ ወይም የአገዛዙን ትዕዛዝ በመቀበል ምንም ዓይነት ሕጋዊ ተቀባይነት በሌለው ምክንያት ከግማሽ በላይ ተወዳዳሪዎቻቸውን ከተወዳዳሪነት የሰረዘበት በመሆኑ፡፡ ፍርድ ቤት ከሰው የመወዳደር መብት እንዳላቸው ሲረጋገጥም ይህ ቅጥረኛ የምርጫ ቦርድ ተብየ ጥቂቶቹን ብቻ በመቀበል ዐይን ባወጣ ሁኔታ ሕግ የማይገዛው ከሕግ በላይ መሆኑን በግልጽ በማሳየት ፍርድ ቤቱ መብታቸውን ያረጋገጠላቸው ቢሆንም የተቀሩትን አልቀበልም ብሎ ከውድድር ውጪ በማድረጉ፡፡
  5. የዜጎችን ሰብአዊና ሕገ መንግሥታዊ የመምረጥ መመረጥ መብትን በመንፈግና በመጻረር በአንድ ምርጫ ጣቢያ ከ12 በላይ ተወዳዳሪ መወዳደር አይቻልም የሚል ገዳቢ ሕግ በማውጣትና ቦታውን እሱ በፈጠራቸው የውሸት ተወዳዳሪ ፓርቲዎች እንዲያዝ እንዲሞላ በማድረግ ለትክክለኛና ሕዝብ ለሚፈልጋቸው የተወዳዳሪ ፓርቲዎች ተመራጮች ቦታ እንዲያጡና ከውድድር ውጪ እንዲሆኑ የተደረገ በመሆኑ፡፡
  6. የፖለቲካ ፓርቲዎች የፖለቲካ አቅዶቻቸውንና ፖሊሲ (መመሪያዎቻቸውን) ለሕዝብ ሊያስተዋውቁ ሊገልጹ የሚችሉባቸውን የገጽ ለገጽ መድረኮችንና የብዙኃን መገናኛ ዕድሎችን ኢሕገመንግሥታዊና ሕገ ወጥ በሆኑ ምክንያቶች እንዳያገኙ የተደረጉበት በመሆኑ፡፡ እንደ ሕገ መንግሥታቸው ቢሆን ኖሮ ምርጫ ሲመጣ ብቻ ሳይሆን ከምርጫ ወቅት ውጪም በማንኛውም ጊዜ የፖለቲካ ፓርቲዎች አቅድ ፖሊሲዎቻቸውን (መመሪያዎቻቸውን) በመንግሥት (በሕዝብ) የብዙኃን መገናኛዎች ለሕዝብ የማስተዋወቅ መብት ነበራቸው፡፡ እየሆነ ያለው ግን የዚህ ተቃራኒና እንኳን ከምርጫ ወቅት ውጪ በምርጫ ወቅት እንኳን ዕድሉን ሊያገኙ አልቻሉም፡፡
  7. የተወዳዳሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች አባላትና ደጋፊዎቻቸው ላይ እስራትና እንግልት በሰፊው የተፈጸመበት በመሆኑ፡፡
  8. አገዛዙ በሕዝቡ ላይ በፈጸመው ከባድ ጫናና ባሳደረው የፍርሐት መንፈስ ለተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚታዘብ የምርጫ ታዛቢ ፍጹም በመታጣቱ እሽ ያሉትንም በማስፈራራት እንዲሸሹ በመደረጋቸው ተወዳዳሪ ፓርቲዎች በየምርጫ ጣቢያዎች የየራሳቸውን ታዛቢዎች ወክለው እንዳያስቀምጡ የተደረገበትና በሚበዛው የምርጫ ጣቢያዎች ያለ ታዛቢ ለመወዳደር የተገደዱበት ሁኔታ እንዲፈጠር በመደረጉ፡፡
  9. በምረጡኝ የቅስቀሳ ወቅት የተቃዋሚ ወይም ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ይቀሰቅሱባቸው የነበሩ ተሸከርካሪዎች በአገዛዙ የጸጥታ አካላትና ደጋፊዎች በመሠባበራቸው በቀስቃሽ አባላቶቻቸውም ላይ ለአካል ጉዳት የዳረገ ጥቃት በመፈጸሙ፡፡ ተወዳዳሪ ፓርቲዎች ይሄንን የአገዛዙን የውንብድና ተግባር ገለልተኛ ነኝ እያለ ለሚያሾፈው የምርጫ ቦርድ ሲያመለክቱም ገለልተኛ ነኝ ባዩ የምርጫ ቦርድ ተብየው የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ባለማድረጉ፡፡ በተሰጠው ሥልጣንም ጥቃቱን የፈጸሙትን አካላት በሕግ እንዲጠየቁ ባለማድረጉ፡፡ የሚገርመኝ ነገር ይህ የምርጫ ቦርድ ተብየ ገለልተኛ አለመሆኑ እንዳይታወቅ ሲል ለማስመሰል ያህል እንኳ እንዲህ ዓይነት የውንብድና ጥቃቶች በመላ ሀገሪቱ በአገዛዙ አካላት ሲፈጸምና ተጠቂዎቹ ተወዳዳሪ ፓርቲዎች ኡኡ ሲሉ የአገዛዙን ጥቃት አድራሾችን አካላት ለአንዲት ጊዜም እንኳ ቢሆን ሊወቅስ ተጠያቂ እንደሆኑም ሊያስጠነቅቅ በፍጹም አለመፈለጉና አለመቻሉ ነው፡፡ በአንጻሩ ግን በተወዳዳሪ ፓርቲዎች ላይ ግን እንኳን ሊያደርጓቸው ገና ያላሰቧቸውን ነገሮች እየቀበጣጠረ ተጠያቂ እንደሚያደርጋቸው ሲዝት ሲያስፈራራ ነበር የከረመው፡፡ የአገዛዙ ባለሥልጣን አቶ ሬድዋን ሑሴን እነኝህን ጥቃቶች በተመለከተ የቪ.ኦ.ኤ የእንግሊዝኛው አገልግሎት ክፍል ጋዜጠኛ ጠይቃው ሲመልስ “የተፈጸሙት ጥቃቶች የተፈጸሙ ቢሆኑም ጥቃት አድራሾቹ በራሳቸው ተነሣሽነት ያደረጉት እንጅ ከላይ ወደታች በወረደ ትዕዛዝ በተማከለ አሠራር የተፈጸሙ አይደሉም” ሲል ነበር የመለሰው፡፡ በተማከለና ከላይ ወደ ታች በወረደ ትዕዛዝ ለመፈጸማቸውማ ማስረጃው ጥቃቱን የፈጸሙት አካላትና ግለሰቦች ተጠያቂ አለመሆናቸው ሕግ ፊት አለመቅረባቸው ነው፡፡
  10. በምርጫው ዕለት ዋዜማ ድምፅ የሚሰጥበት ወይም የመምረጫው ወረቀት ለግለሰቦች ታድሎ ምልክት እንዲያደርጉ እየተደረገ በማግስቱ ያንኑ እንዲያስገቡ በመደረጉ፡፡ አስቀድሞም የምርጫ ቦርድ ተብየው ይህ የድምፅ መስጫ ወረቀት ለዚህ የውንብድና ተግባር እንዲመች ለማድረግ የድምፅ መስጫ ወረቀቶቹን ተከታታይ የመለያ ቁጥር እንዳይኖርባቸው አድርጎ ማተሙ የመሳሰሉት ናቸው፡፡
በምርጫው ዕለት በነበረው ሒደት
  1. የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ታዛቢ ባገኙባቸው ጥቂት የምርጫ ጣቢያዎች ያስመዘገቧቸው ታዛቢዎች አብዛኞቹ በየተመደቡበት የምርጫ ጣቢያዎች ተገኝተው እንዳይታዘቡ በመደረጋቸው፡፡
  2. የምርጫ ኮሮጆዎች ከሰዓቱ በፊት ተከፍተውና የድምፅ መስጫ ወረቀቶች በብዛት ተከቶባቸው በመገኘቱ፡፡
  3. መራጮች በተደጋጋሚ እንዲመርጡ በመደረጉ፡፡ የቀበሌዎቹ ወይም የምርጫ ጣቢያዎቹ ነዋሪዎች ያልሆኑ ሰዎች በተሽከርካሪዎች እየተጫኑ መጥተው እንዲመርጡ መደረጉ፡፡
  4. ታጣቂዎች በየምርጫ ጣቢያው አቅራቢ በመሆን በሕዝቡ ላይ የፍርሐት ድባብ እንዲፈጥሩ በመደረጉ፡፡
  5. ምርጫው እየተደረገ ባለበት ሰዓትም ቢሆን ለመታዘብ የቻሉ የተወዳዳሪ ፓርቲዎችን ታዛቢዎች በጥቅም በመደለልና እንዳይናገሩ በማስፈራራት በአገዛዙ አካላት የምርጫ ኮሮጆዎችን የመሙላት ድርጊቶች ሲፈጸሙ በመታየታቸው፡፡
  6. ሕዝቡ የሰጠው ትክክለኛው የሕዝብ ድምፅ የተመለከተበት የድምፅ መስጫ ወረቀቶች ተቃጥለውና ሽንት ቤቶች ተጥለው መገኘታቸው፡፡
  7. ቀደም ሲል የተጠቀሱትን ማጭበርበሮች መፈጸም ባልተቻለባቸው የምርጫ ጣቢያዎች ምርጫው ከተጠናቀቀበት ሰዓት በኋላ የጸጥታ ኃይሎች ኮሮጆ አናዘርፍም አናስነካም ባሉ ጽኑአንና ታማኝ የተወዳዳሪ ፓርቲዎች ታዛቢዎችና ደጋፊዎች ላይ ግድያን ጨምሮ አሰቃቂ ድብደባ እስራትና እንግልት የተፈጸመ በመሆኑ ወዘተረፈ፡፡
ከምርጫው ዕለት በኋላ በነበረው ሒደት
  1. የምርጫ ቦርድ ተብየው ከላይ በተጠቀሱት እንከኖች በተሞላ ሒደት የተፈጸመን የሐሰተኛ ምርጫ ውጤት ተቃዋሚዎች በየጊዜው እያቀረቧቸው ለመጧቸው ቅሬታና አቤቱታዎች ለአንድም ጊዜ እንኳ አግባብነት ያለው ሕጋዊ ምላሽ ለመስጠት ፈጽሞ ሳይፈልግ ክሶቹንም ለማጣራት ሳይሞክርና ሳይፈልግ በምርጫው ማግስት ምርጫው ከምንጊዜውን በበለጠ መልኩ ፍትሐዊ ተአማኒና ሰላማዊ ሆኖ ተጠናቋል ብሎ በማወጁ፡፡
  2. ይሄንን ሙሉ ለሙሉ የተጭበረበረን ውጤትም የምርጫ ቦርድ ተብየው ውጤት እገልጻለሁ ብሎ ካስታወቀበት ቀን 3 ቀናት አስቀድሞ የግንቦት 20 በዓላቸውን ለማድመቅ ሲባል በዋዜማው እረቡ ለት በ19 የ105ቱን ውጤት ለተንኮሉ ከፍሎ በማስቀለት ወያኔና አጋሮቹ ሙሉ ለሙሉ አሸናፊዎች መሆናቸውን በማወጁ፡፡
  3. ሕዝቡ መብቱን ለአገዛዙ አሳልፎ የሰጠ በመሆኑ ያለ ፍላጎቱና ያለ ምርጫው የሥራ ዋስትናንና የመሳሰሉትን መሠረታዊና የዜግነት መብት ጥቅሞቹን በግፍ ላለማጣት ሲል ተገዶ ጠርናፊም ተጠርናፊም ሆኖ በ5 ለ1 አደረጃጀት የተጠረነፈው የኢትዮጵያ ሕዝብ አገዛዙ “ምንም ዓይነት ፖለቲካዊ ዓላማና ተልእኮ የለውም” የሚለውን ይሄንን አደረጃጀት በመጠቀም ሕዝቡ የተዘረፈበትን ድምፅ የተፈጸመበትን ውንብድና የመቃወም መብቱን በመጠቀም መብቱንና የሰጠውን ድምፅ ለማስከበር እንቅስቃሴ እንዳያደርግ በከፍተኛ ደረጃ እየወተወተው እየዘበዘበው ከፍተኛ ጫና እያደረገበት በመሆኑ ወዘተረፈ፡፡
እውነት ለመናገር የዘንድሮውም “ምርጫ” ተጭበርብሮ ውጤቱ እንዲህ በመሆኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ እጅግ ነው ያዘነው፡፡ ሕዝቡ ወያኔን ላለመምረጡ እንዴት እርግጠኛ ልትሆን ቻልክ? የሚል ጥያቄ ሊነሣ ይችል ይሆናል፡፡ ይሄንን ለማወቅ የግድ የድምፅ መስጫ ወረቀቶችን አገላብጨ ማየት አይጠበቅብኝም፡፡ የሕዝብ ምርጫ ምን እንደነበር ለማወቅ የሚረዱ ሌሎች መንገዶች አሉ፡፡ ሕዝብ የሚባለው ከሰማይ የተሰቀለ የሆነ አካል ማለት አይደለም፡፡ ሕዝብ የሚባለው እኔ አንተ አንቺ እሱ እሷ የየመንደሩ ወይም የየሰፈሩ ሰዎች ማለት ነው፡፡ የእነዚህ የየሰፈሩ ወይም የየመንደሩ ሰዎች ፍላጎትና ምርጫ ምን እንደነበር ደግሞ እዚያው እየሰፈሩ እየመንደሩ የሆድ የሆዳችንን ስንጫወት ስናወጋ በሚገባ እናውቀዋለን፡፡ ከዚህ ባሻገር የሕዝቡ ምርጫ ምን እንደነበር ለመረዳት ይረዳቹህ ከሆነ አንድ ጉዳይ ልጥቀስላቹህ፡፡ እንዳልኳቹህ ይሄንን ጉዳይ የምጠቅስላቹህ የሕዝቡ ምርጫ ምን እንደነበር እንድትረዱ ብቻ እንጅ ለሌላ ዓላማ እንዳልሆነ ግን አስቀድሜ ማስጠንቀቅ እወዳለሁ፡፡ ይሄንን ያየችውን ነገር ያጫወተችኝ የሰፈሬ ልጅ ናት፡፡
ነገርየው ምን መሰላቹህ? ረቡእ ለት ነው ማለትም ምርጫው በተደረገ 3ኛው ቀን ጠዋት፡፡ ይህች የሰፈሬ ልጅ ረቡእ ለት ጠዋት በሀይገር (መለስተኛ የከተማ አውቶቡስ) ወደ ሥራዋ ስትሔድ እንደ እሷ ሁሉ ወደ ጉዳይዋ ለመሔድ የተሳፈረች ሌላ የሰፈር ሰው ነበረች፡፡ ይህች የሰፈር ሰው ግጥም አድርጋ የትግሬ ሹርባ ተሠርታ ነበር፡፡ ሌላው ተሳፋሪ በግልምጫ ሲያነሣ ሲጥላት ይቆይና አንደኛው ምክንያት ፈልጎ በድንገት ይዘልፋታል፡፡ ወዲያውንም በዚያ ሀይገር ውስጥ ያለ ሰው ሁሉ ሊባል በሚችል ደረጃ እየተቀባበለ ያበሻቅጣት ጀመር፡፡ አንዱን ብጠቅስ “ቆይ! ጠብቂ! በደረቁ እንላጭሻለን! ሩቅ መስሎሽ ነው? አሁን በቅርቡ ጠብቂ….” ይህች ልጅ ያም ያም እየተቀባበለ ሲወርድባት በፍርሐት ተውጣ እየተንቀጠቀጠች “ኧረ እባካቹህ እኔ ትግሬ አይደለሁም፡፡ እኔ ወሎየ ነኝ ዝም ብየ ነው ይሄን ሹርባ የተሠራሁት!” ብላ ትናገራለች፡፡ ልጅቱ በእርግጥም ትግሬ አልነበረችም፡፡ ይህች ልጅ ከሥራዋ እንደተመለሰች ወዲያውኑ ነበር ሹርባዋን የፈታችው፡፡ የዚህ ዓይነት ተመሳሳይ ድርጊቶች በየቦታው አይጠፉም፡፡ እነዚህ ጉዳዮች የሚያመለክቱን ብዙ ነገር አለ፡፡ ከብዙው ነገሮች አንዱ ከላይ የገለጽኩላቹህን የሕዝቡ ምርጫ ማን እንደነበርና የልቡን ትርታ ነው፡፡ በዚያ ሚዲባስ (መካከለኛ ተሸከርካሪ) ውስጥ የነበሩ ሰዎች “የእነ እከሌ ደጋፊዎች የሆናቹህ ብቻ!” ተብለው የተጫኑ ተሳፋሪዎች ባለመሆናቸው በሚገባ የሕዝቡን ሥሜት ይወክላሉ፡፡ እናም የሕዝቡ ስሜት ፍላጎት ምርጫ ይሄው ነው፡፡ ይህ ባይሆን ኖሮ በምንም ተአምር ቢሆን አገዛዙ መቶ በመቶ አሸነፍኩ ሕዝቡ ወዶና ፈቅዶ መረጠኝ በሚልበት አዲስ አበባ ከተማ አገዛዙ መሠረቴና መከታየ ነው ለሚለውና ለሱም እንደቆመ ለሚናገርለት ብሔረሰብ እንዲህ ዓይነት ጥላቻ ሊገልጽ አይችልም፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለያየ ጊዜ በተደረጉት 5 ዙር ምርጫዎች ለአንድም ጊዜ እንኳን ቢሆን ወያኔን መርጦ አያውቅም፡፡ ወያኔ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያለውን ጥላቻና በየጊዜው የሚወስደውን የተለያየ ዓይነት የበቀል እርምጃዎች ባያቹህ ጊዜ በተደረጉት ምርጫዎች ሁሉ ወያኔ አሸንፎ እንደማያውቅ ታረጋግጣላቹህ፡፡ ወያኔ በጥላቻ ታንቆ የቀረው በኢትዮጵያ ሕዝብ እምነት ያጣውና በጎጠኛነት አስተሳሰብ ታስሮ የቀረው በዚህ ምክንያት ነው፡፡ ወያኔ በሕዝብ ድምፅ ሥልጣን የያዘ ቢሆን ኖሮ ለሥልጣን ላበቃው ሕዝብ ከፍተኛ አክብሮት ይኖረው ነበር፡፡ የምናየው ማን አለብኝነት ንቀትና እረገጣ ፈጽሞ ባላየነው ነበር፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝብ ምንም እንኳ በጣታቸው የሚፈርሙ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ ጄኔራሎች፣ የሚንስትሮች ተቆጣጣሪ አለቆች ከታጎሩበት ከወያኔ የማይሻል በሕዝብ ተቀባይነትን ያገኘ የፖለቲካ ፓርቲ በሀገራችን ባይኖርም ቅሉ የተወዳዳሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች ብቃት ሳያሳስበው ሁሌም እነሱን የሚመርጥበት ምክንያት ለምን እንደሆነ ታውቃላቹህ? አንዱ ወያኔ ለዚህች ሀገር ጠንቅ እንደሆነ ጠንቅቆ ስለሚያው ሲሆን ሌላው ደግሞ ብቻ አንድ ጊዜ የመንግሥት ሥልጣን እንደ ደርግና እንደ ወያኔ ባለ ትጥቅ ባለ አፈሙዝ በሆነ አካል ሳይሆን ትጥቅ አፈሙዝ ባልያዘ ከራሱ ከሕዝቡ የወጡ ሲቪል ወይም ሕዝባዊ የሆኑ በሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች የመንግሥት ሥልጣን ቢያዝ ትጥቅ አፈሙዝ ያልያዙ እንደመሆናቸው መጠን እንደ ደርግና እንደ ወያኔ ፈላጭ ቆራጭ፣ አንጋገነን፣ ጨቋኝ የመሆን ዕድል ስለማይኖራቸው ሰብአዊ ዲሞክራሲያዊ (በይነ ሕዝባዊ) የመንግሥት አሥተዳደር ይኖረናል የሥልጣን ባለቤቱም እኔው እራሴ እሆናለሁ የሚል የጸና እምነት ስላለው ነበር ሳይሰለች ሳይታክት በተደጋጋሚ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን የሚመርጠው፡፡ እንዳለመታደል ሆኖ ግን የሚሰጠው ድምፅ ዋጋ አግኝቶለት ምኞቱ ሠምሮ እስከ አሁን ድረስም ሕዝባዊ መንግሥት ሊመሠረት አልቻለም፡፡ ወያኔ እስካለ ጊዜ ድረስም ይህ ምኞቱና መሻቱ እውን ሊሆን አይችልም፡፡ ምክንያቱም ይህ እንዳይሆን የሚያደርጉ ብዙ ነገሮች አሉና፡፡ ወያኔ ሥልጣን ስለጣመው ብቻ አይደለም ሥልጣን ማስረከብ የማይፈልገው፡፡ ነገር ግን ከዚህ ቀደምም በተደጋጋሚ እንደነገርኳቹህ ወያኔ ከሀገር ክህደት ጀምሮ እስከ በንጹሐን ደም መጨማለቅ ድረስ ያልፈጸመው የወንጀል የግፍ ዓይነት ስለሌለና ሥልጣን ባስረከቡ ማግስትም በእነዚህ በፈጸሟቸው ግፎችና ወንጀሎች ምክንያት እየታነቁ ለፍርድ እንደሚቀርቡ ጠንቅቀው ስለሚያውቁት በምንም ተአምር ለመቸውም ቢሆን ወያኔዎች “አዎ ተሸንፈናል” ብለው መሸነፋቸውን አምነው የሕዝብን ድምፅ አክብረው ሥልጣን አያስረክቡም፡፡
ቀጣዩ የተቃዋሚ የተወዳዳሪ ፓርቲዎች እርምጃ ምን ሊሆን ይገባል?
እንግዲህ በዘመነ ወያኔ ሰላማዊ ትግል ማድረግና ውጤትም ማምጣት ፈጽሞ እንደማይቻል ከአንዴም 5 ጊዜ ሁሉ በተደጋጋሚ የታየ ሀቅ ነው፡፡ ወያኔ ምርጫን እያዘጋጀ ሁሌም አሸነፍኩ እያለ ሥልጣንን ይዞ የሚቀጥለው ያለ ምርጫ ልግዛ ቢል “የለየለት አንባገነን” የሚባል ስም ስለሚያሰጠውና ይሄንንም መባል ስለማይፈልግ እንጅ በምርጫ ስሚያምን አይደለም፡፡ በምን ምክንያት እንደሆነ ባላውቅም ተቃዋሚ ፓርቲዎች ይሄንን ሀቅ ሊገነዘቡ አልቻሉም፡፡ ቢያንስ ከ97ቱ ምርጫ በኋላ ሊነቁ ይገባ ነበር፡፡ ወያኔ ሁሌም በሚያዘጋጀው የውሸት ምርጫ እየተሳተፉ ለወያኔ “የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት አለ” ልፈፋው (ፕሮፖጋንዳው) መጠቀሚያ መሆንን እንደ አንድ ቁምነገር ቆጥረው ይሄው እንደምናየው ጊዜያቸውን በከንቱ ያቃጥላሉ፣ ወያኔ በሕዝብ ላይ እየቀለደ እያሾፈ እንዳሻው እየሆነ እንዲኖር ዕድል እንዲያገኝ ያደርጋሉ፡፡ “ሞኝን እባብ ሁለት ጊዜ ይነድፈዋል፤ የመጀመሪያውን ተንከርፍፎ ሲሔድ ሳያየው ሁለተኛውን ይሄው እዚህ ቦታ ነው ነድፎኝ እዚህ ውስጥ የገባው ብሎ ሲያሳይ” ይባላል፡፡ አንድ ሌላ አባባልም አለ “ትናንት ያነቀፈህ ድንጋይ ዛሬም ካነቀፈህ ድንጋዩ አንተ ነህ” የሚል፡፡
አማራጭ ስለሌለ እንጅ ከሰላማዊ የትግል አማራጭ ሌላ የትግል አማራጭ ተመራጭ ሆኖም አልነበረም ወገኖቻችን የትጥቅ ትግልን የመረጡት፡፡ ከሰላማዊ የትግል አማራጭ ውጭ ሌላ አማራጭ አስፈላጊ አይደለም የሚሉ ፓርቲዎችም ሆኑ ግለሰቦች የኔ ቢጤ ፈሪ ስለሆኑ እንጅ የሚሉትን ነገር ስለሚያምኑበትና ለዚህ የሰላማዊ ትግል እራሳቸውን የሰጡ ስለሆኑ አይደለም፡፡ የዚህ ማረጋገጫውም በሰላማዊ ትግል የሕዝብን መብትና ፍላጎት ማረጋገጥ ማስከበር ከሚቻልባቸው መንገዶች አንዱ የሆነው በሕዝብ ምርጫ ሥልጣን መረካከብ የመንግሥት ለውጥ መከወን በወያኔ አገዛዝ የማይታሰብ መሆኑን ካረጋገጡ ዘንዳ ሌሎች የሕዝብን መብትና ፍላጎት ማረጋገጥ ማስከበር የሚቻልባቸውን የሰላማዊ ትግል አማራጮችን ተጠቅመው የሕዝብን መብትና ፍላጎት ለማረጋገጥ ለማስከበር አለመሞከራቸው አለመቻላቸውና ለዚህም ቁርጠኛ አለመሆናቸው ነው፡፡ እነዚህ ከምርጫ ሌላ አንድን አንባገነናዊ አገዛዝ ማንበርከክና ማስወገድ የሚቻልባቸው የሰላማዊ ትግል እርምጃዎች ከሥራ ማቆም አድማ ጀምሮ እስከ መታቀብ (boycott) ድረስ በርካቶች ናቸው፡፡ እነኝህ “ያለ ሰላማዊ የትግል አማራጭ!” ባይ ወገኖቻችን እነዚህን የሰላማዊ ትግል እርምጃዎችን አድርጎ የሕዝብን መብትና ፍላጎት ማረጋገጥ ማስከበር የሚቻልበት ምንም ዓይነት ምቹ ሁኔታ በዚህች ሀገር እንደሌለና አገዛዙ አስቀድሞ እነኝህን እርምጃዎች በመውሰድ ስኬት ላይ መድረስ እንዳይቻል ወደዚያ የሚወስዱ መንገዶችን ሁሉ በመዝጋት ሕዝብን በማነቃነቅ እነኝህን እርምጃዎች መውሰድ እንዳይቻል እንዳደረገ እነኝህ ወገኖቻችን አያውቁም ለማለት እጅግ ይቸግረኛል፡፡ አይ! ዕድሉ አለ እነኝህን የሰላማዊ ትግል አማራጭ እርምጃዎችን በመውሰድ የሕዝብን መብትና ፍላጎት ማረጋገጥ ማስከበር እንችላለን ካሉም እነሆ! ይሄው ሰዓቱ አሁን ነውና አድርጉትና እንያቹሃ! ይሄንን ማድረግ ሳትችሉ ግን በሌለ ምኅዳር ላይ “ሰላማዊ ትግል” እያላቹህ ብታላዝኑ እራሳቹህን ለትዝብት ከመዳረግ ሀገሪቱን የከፋ ችግር ላይ እንድትወድቅ ምቹ ሁሌታን ከመፍጠር ውጪ ለሀገራችን ፖለቲካ (እምነተ አስተዳደር) ዕድገትና መሻሻል የምታበረክቱት የምትፈይዱት አንዳችም ነገር እንደሌለ ልታውቁት ልትረዱት ይገባል፡፡ አሁን በትጥቅ ትግል ላይ ያሉ ወገኖቻችን የጠቀስኳቸው የሰላማዊ ትግል እርምጃዎች በ97ቱ ምርጫ አገዛዙ የምርጫውን ውጤት በቀለበሰበት ወቅት ሞክረውት ዛሬም ድረስ ባሉ ወያኔ እስካለ ጊዜ ድረስም ወደፊትም በሚኖሩ በተለያዩ ምክንያቶች ተሞክሮ እንዳልተሳካ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡ ስንት ጊዜ እባቡ ሲነድፋቸው ወይም እንቅፋቱ ሲያነቅፋቸው ነው የሚነቁት የሚገባቸው?
እዚህ ላይ “እሽ የትጥቅ ትግልስ እናድርግ ብንል የት ልናደርግ እንችላለን? ወያኔ ይሄንን አውቆ አስቀድሞ የሀገራችንን ሉዓላዊ መሬትና ሌሎች ብሔራዊ ጥቅሞቿን ሁሉ አሳልፎ እየሰጠ ጎረቤት ሀገራትን ሁሉ በወዳጅነት ይዟቸዋል፡፡ ያለው ብቸኛ መንደርደሪያ መተላለፊያ (corridor) ባሕረ ምድር (ኤርትራ) ብቻ ናት ሸአቢያ ደግሞ የባሰ ጠላት እንጅ የተሻለ አይደለምና እንዴት ብለን ሸአቢያን አምነን እዚያ የትጥቅ ትግል ልናደርግ እንችላለን?” የሚል ጥያቄ መነሣቱ አይቀርም፡፡ ሁለት ሦስት የፌስ ቡክ (የመጽሐፈ ገጽ) ጓደኞቸ ሰሞኑን ይሄ ጥርጣሬ ስላላቸው በፍጹም የማይታሰብ ነው ብለው ሐሳባቸውን በመጽሐፈ ገጻቸው ላይ እስከ መጻፍ ደርሰው ነበር፡፡ ለአንደኛው ወንድሜ ይሄንን ብየ መለስኩለት፡፡
“ወንድሜ… ያልከው ሁሉ እውነት ነው አንድም ስሕተት የለበትም እንዲያውም ኢሳይያስ ማለት ይሔ ብቻ አይደለም ከጠቀስካቸው የከፉ ብዙ ጉዶችም ይኖራሉ፡፡ ማየት ያለብን ነገር ቢኖር እኛ ወደ ሸአቢያ የምንሔደው አማራጮች ስለሌሉንና ብቸኛው አማራጭ እሱ ብቻ በመሆኑ እንጅ ወደን ፈልገን መርጠን አለመሆኑን ነው፡፡ “ዘመኑን እንዋጅ” የሚል አማርኛ ተጠቅሜ እንደነበር ታስታውሳለህ? እኛ ኢትዮጵያዊያን የማንነት የደም ነገር ሆኖብን ውስለታ ማስመሰል አንችልበትም፡፡ ያለፉት መንግሥታቶቻችን ከባዕዳን ጋር ሀገር ለሀገር ግንኙነትን ሲፈጥሩ ፍጹም ቅንና ገር ልብ ይዘው ነበር የሚቀርቡት፡፡ የፈጠርነውን ወዳጅነታችንንም ለዘለዓለም እንደሚኖር አድርገን እናስብ ነበር፡፡ በዚያ በኩል ያለው አስተሳሰብ ግን ዘላቂ ጥቅምን እንጅ ዘላቂ ወዳጅነትን መሠረት ያደረገ አልነበረም፡፡ ይሄንን መረዳት ባለመቻላችን ብዙ ጊዜ እየተከዳን ለጉዳት ተዳርገናል፡፡ አሁንም በዚህ የቆየና የዘመኑን አስተሳሰብ ግንዛቤ ውስጥ ያላስገባ ቀጥተኛ አስተሳሰብ የኢትዮጵያን ሕዝብ ለመከራ ዳርጓል፡፡ በነፍስ ሊጠቅመን ይችል ይሆናል ይጠቅማልም፡፡ በሥጋ ግን የምታየውን ያህል እየጎዳን ለመከራ ዳርጎን ይገኛል፡፡ አማራጭ ከሌለና መቀመቅ እየወረደች ያለች ሀገራችንን እየጠፋ ያለ ሕዝባችንን ማዳን መታደግ ካለብን እዚህ ሆነንም ወያኔ በግልጽም በስውርም በሚፈጽመው የማጥፋት ዘዴ ለመጥፋት ቀናችንን መጠበቅ ካልሆነ በቀር በሚፈጽምብን ጥቃት ከሞት የማንተርፍ ከሆነ ያለውን አማራጭ የግድ መጠቀም አመንታች ሊሆን በፍጹም አይገባም፡፡ እዚህም ሆነን እጣችን ሞት ከሆነ እዚህ ሆነን አንዳች ነገር ማድረግ የምንችልበት አማራጭ ከሌለ አንድና ሁለት ብቻ ሳይሆን በገፍ ወደዚያው ብንገባ የኃይል ሚዛኑ በእርግጠኝነት ነገሮችን መለወጡና የተቀስካቸውን ሥጋቶች ማስቀረቱ አይቀርም፡፡ ኢሳይያስ “ቅዱስ” በሉኝ ካለ ብፁዕ የሚል ጨምረን በመስጠት፣ “ሸአቢያ ሽህ ዓመት ይኑር!” በሉ ቢለን “ለዘለዓለም ይኑር” እያልን ለጊዜው በመወስለትና በመርከስ በማስመሰል ዛሬን ማለፍና ነገን ማግኘት የግድ ይኖርብናል፡፡ ይሔ አማራጭ የለውም፡፡ የዓለም ፖለቲካ እየተዘወረ ያለው በእንደዚህ ዓይነት የቅጥፈት ቅኝት ነው፡፡ ሸአቢያና ወያኔ ለዚህ የደረሱት በዚህ እኩይ ክህሎታቸው ነው፡፡ በደንብ መቅጠፍ ማስመሰል የቻለበት ያሸንፋል ያሰበውን ያሳካል፡፡ ቅንነት እውነተኛነት ሐቀኝነት አሁን ላይ አዋጭ አይደለም ድሮ ቀርቷል፡፡ የየዋሀን አምላክ እንዳይረዳንም ኃጢአታችን በየት በኩል ያቅርበው? ጸሎታችን ከጣሪያ በላይ የማያልፍ ሆነ፡፡ እንግዲህ ምን ይደረግ የዋህነት ቅንነት እውነተኛነት ቀጥተኝነት ካስበላ እያዘንን እስከ ነጻነት ቀን ድረስ ከልባችን የውስጠኛው ክፍል ዘግተንበት ቅጥፈትን ማስመሰልን በመካን እኩዮችን ክፉዎችን ሸረኞችን ጠንቀኞችን አስመሳዮችን ሸረኞችን በመብለጥ እራሳችንን ማዳን ይኖርብናል” ነበር ያልኩት፡፡
እናም ለእናንተም እላቹሀለሁ ያለን አማራጭ አንድና አንድ ብቻ ነው የትጥቅ ትግሉን ተቀላቅሎ ወያኔን በተመኘው እሳት አንጨርጭሮ አሳርሮ በማጥፋት ሀገርንና ሕዝብን ነጻ ማውጣት፡፡ ወያኔን ስናጠፋ ሀገርንና ሕዝብን ከወያኔ አገዛዝ ብቻ እንዳይመስላቹህ ነጻ የምናወጣ፡፡ ነገር ግን ወያኔ ቅጥርኛ ሆኖ ከሚያገለግላቸው የዚህች ሀገርና ሕዝቧ ጠላት ከሆኑት ጠላቶቻችን ሁሉም እንጅ፡፡
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው