
852
EmailShare
የኢህአዴግ ባለስልጣኖች ቦንጋ አካባቢ የነበረ የተፈጥሮ ጫካ ተቃዋሚ ድርጅቶች እየተንቀሳቀሱበት ነው በሚል ምክንያት እንዲቃጠል ማድረጋቸውን የትህዴን ድምጽ ዘገበ::
Zehabesha News
የትህዴን ምንጭ የዜና ምንጮቹን ጠእንደዘገበው በደቡብ ክልል ቦንጋ አካባቢ የሚገኝ ሰፊ የተፈጥሮ ጫካ በአካባቢው ህዝብ ለዘመናት ጠብቆት የኖረ ሃብት ሲሆን የገዢውን ስርአት በመቃወም እየታገሉ ያሉት ተቃዋሚዎች የሚንቀሳቀሱበት አካባቢ ነው ብለው ስጋት ላይ የወደቁት የስርአቱ ካድሬዎች እሳት ለኩሰው እንዲቃጠል ማድረጋቸውና ይህን እኩይ ተግባር የታዘበው የአካካባቢው ህዝብም በስርአቱ ላይ ጠንካራ ተቃውሞ እንዳስነሳ ለማወቅ ተችሏል።
የአካባቢው ህዝብ እየተቃዎመ በነበረበት ሰዓት እንደገለፀው በአፋችሁ ልማት አልሙ፤ ድህነት አጥፉ እያላችሁ በተግባር ግን መተኪያ የሌላቸውን የተፈጥሮ ሃብቶችን እያቃጠላችሁ ነው በማለት ሃይለኛ ተቃውሞ ማንሳታቸውን መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።
No comments:
Post a Comment