
ቤተክርስቲያናችን ውስጥ የመከፋፈልና የማፍረስ እንቅስቃሴ ለማስቆም)የተጻፈ
ግልጽ ደብዳቤ በጋዜቤጠኛ አቶ አዲሱ አበበ መሪነት በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የተነገረው የሐሰት ወሬና ከቤተ ክርስቲያኗ
ውጭ የሚካሄዱ ስብሰባዎች)ጉዳይ በዓለም ሁሉ መነዛቱ የታወቀ ነው። ቤተ ክርስቲያናችን ግን ለዚህ
አፍራሽ ድርጊት አስተያየት ከመስጠት ተቆጥባ ቆይታለች። አሁን ግን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ
አስተያየቷን እንድትሰጥ ተገዳለች። ምክንያቱም ውሸት ሲደጋገም እውነት ይመስላል፣ ሰሚውንም
ያደናግራል።
እመሠክርላታልሁ ከሚሉ ላት ከኦርቶዶክስዊት ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ጋር፤ እውነትን ለመመሥከር
እፍጨረጨርለታለሁ ከሚሉለት ጋዜጠኝነት ጋር ሁኔታዎች ሲጋጭቦት እናያለን። እንዲሁም፤ ታማኝንትንና
ተቀባይነትን በሰፊው እንዲለግሦት ከሚማጸኑት ሕዝብዎና እውነት እንዲነገርባችው ከተዘረጉት ሕዝባዊ
መገናኛዎች ጋር መጋጨትዎንም እናስተውላለን። ስለዚህ የዚህ ግልጽ ደብዳቤ ዓላማ ከዚህ ተግባሮ
እንዲቆጠቡ ለማሳሰብና በእርሶ አንደበት የተነገሩትን ስሕተቶች የሰሙ ሁሉ የራሳቸውን ፍርድ እንዲስጡ
ለማስገንዘብ ነው።
በመጀመሪያ በእራስዎ ባህርይ ተገደን ይህችን ማሳሰቢያ ስንጽፍልዎ፤ ከእርስዎ እየመነጨ ሌላውን
የሚበክል ከእውነት የራቀ ቅስቀሳ ሲያካሄድና ሲነገር ቢቻል በቤተ ክርስቲያናችን እንዳይከሰት መጠንቀቅ፤
ከተከሰተም እንድናርመው ጥንታዊት ቤተ ክርስቲያናችን መመሪያ ሰጥታናለች። ሰለዚህ ክርስቶስ “ከእኔ ጋራ
የማይከማች ይበትነኛል” ማቴ 12፡30 ባለው ላይ ተመርኩዞ፤ ቅዱስ ጳውሎስ “መከፋፈል የሚያመጣውን
ሰው አንድ ጊዜ ምክረው ለሁለተኛ ጊዜ አስጠንቅቀው ከዚያ ካለፈ ከሱ ጋራ ምንም ነገር አይኑርህ ”(ቲቶ 3፡
10 )ብሏል። የቀኖናችን መጽሐፍም ራሱ እውነትን ክዶ ንጹህን ሰው ለማስካድና ሀሳብ ለማስቀየር ወደ
ራሱ ርካሽ አስተሳሰብ የማስለወጥ እኩይ ተግባር የሚፈጽመውን ሁሉ “የራሱ ክህደት የራሱ ክህደት ሳያንሰው
የባለአደራዎች ቦርድ ጽ/ቤት /OFFICE OF THE BOARD OF TRUSTEES
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን::
In the name of the Father, the Son, and the Holly Spirit, Amen
2
ባልንጀራውን ከሃይማኖቱ እስኪወጣ ድረስ ለመካድ ምክንያት ቢሆን ንስሐው ጽኑዕ ነው” (ፍትሐ ነገስት
አንቀጽ 20፡760 )በማለት አጠንክሮ አስጠንቅቋል።
ህግና ደንብ፤ ሥርዓትና የሰው ድምጽ በሚከበርበት ውቅያኖስ አቋርጠን ወደ አሜሪካ የመጣነው፤
በአገራችንና በህዝባችን እርስዎን በመሳሰሉ የጥፋት ወኪሎች ከሚያራመዷቸው መከፋፈል፣ ማጣላት፣
መለያየትና መተራመሱን ለመሸሽ ነበር። ቤተ ክርስቲያናችን የምትመራባቸውን ቅዱሳት መጻህፍትና ቀኖና
መነሻ በማድረግ መተዳደሪያ ደንብ ቀርጸን በመንግሥት ያስመዘገብነውም፤ እርስዎን የመሰሉ ሰዎች
አስመሳዮች መስለው በመግባት አሁን እያደረጉ ካሉት አደገኛ ፀረ ህብረትና ፀረ ሰላም ተግባራት ለመጠበቅና
ለመጠንቀቅ ነበር።
እርስዎ ግን ለሚናገሩት አሳሳች ንግግር ክብደት ሰጥተው፤ በህዝብ ታማኝነትንና ተቀባይነትን ለማግኘት
ጋዜጠኛና ኦርቶዶክስ ክርስቲያን በመሆኔ እያሉ ተቀጥረው በሚሰሩበት በቪኦኤ ራድዮና በአቢሲንያ ራድዮ
የሚናገሩት በግልዎ የወደዱትን ለመጥቀም፤ የጠሉትን ለመጉዳት ከጋዜጠኝነት ሥነ-ምግባር ውጭ
እንደሚጠቀሙበት በሩቅና በቅርብ ሆኖ ከሚሰማዎ ህዝብ ይልቅ፤ አሁን ያለንበት የኃላፊነት ቦታ ቀርበን
እንድንመለከተው በገጠመን እድል ማንነቶን በግልጽ እንድንረዳዎ አድርጎናል።
“በጋዜጠኛነት ሙያዬ ለእውነት በመቆም እፍጨረጨራለሁ” ስለሚሉት፤ ለቀጠረዎ ድርጅትና ለአድማጭዎ
ህዝብ ትዝብት በመተው፤ ተሰሚነትን ለማትረፍ የኦርቶዶክስ ክርስትናን ለእኩይ ተግባርዎ ለመጠቀም
ደጋግመው እየተናገሩ፤ ደጋግመው የሚፈጽሟቸው አሳዛኝ ተግባራት፤ የመንፈስና የሥነ ምግባር ቀውስ
ማድረሳቸውን በቅርብ ሆኖ ላልተረዳዎ፤ በሩቅ ሆኖም ድምጽዎን ብቻ ለሚሰማዎ ህዝባችን የማሳወቅ
ግዴታና ኃላፊነት አለብን።
በቤተ ክርስቲያናችን ስም ተጋርደው ከሚገቡበትና ከሚነካኩት ድርጅቶችና ግለሰቦች ጋራ ያደረጓቸውን
ግጭቶችና ቅራኔዎች ዝርዝር ለጊዜው እዚህ ላይ እናቁምና፤ ከስምንት ዓመታት በፊት የቤተ ክርስቲያናችንን
የህንጻ ግንባታ ባለ ሙያዎች በአቀረቡት ጥናት፤ የቤተ ክርስቲያኗ አባላት ባጸደቁት መሠረት የተጀመረውን
ሥራ ለማደናቀፍ አቅምዎ የፈቀደልዎትን ሁሉ አሳዛኝ ተንኮል ተግባራዊ ለማድረግ በቅርብም በሩቅም ላለው
ሁሉ ወገናችን ገልጸን ለማስረዳት የእርሰዎ አደገኛ ጸረ ሰላምና ጸረ ህዝብ እንቅስቃሴዎ አስገድዶናል።
የተጀመረው ሁለ ገብ የህንጻ ግንባታ ሥራ ለማከናወን ባንኩ ለማበደር የተስማማበትን ብድር እንዲያቆም
እርስዎና ጥቂት ግብር አበሮችዎ ያደረጋችሁትን ዘመቻ የጠላትነት ተግባር ነው ብለን ብንገምትም፤ የቤተ
3
ክርስቲያኗ ግንባታ እንዲቆም እንቅፋት ለመሆን የተቃጣ ተንኮል በመሆኑ፤ ይህንን ተንኮልዎንና መሠሪ
ተግባርዎን በቸልታ የምናልፈው ሆኖ አላገኘነውም።
በባለአደራዎች ቦርዱ አሠራርና በአዲሱ የሁለ ገብ ህንጻ ግንባታ ቅሬታ አለኝ በማለት፤ በአቢሲንያ
ሬድዮ ቀርበው በተደጋጋሚ ያስተላለፉትን ወቀሳና ተቃውሞ፤ ሲመችዎ በገሀድ ሳይመችዎ በስውር
ወረቀቶችን በማሰራጨት፤ ከቤተ ክርስቲያኗ ውጭ ስብሰባ በመጥራት ስለ ቤተ ክርስቲያናችን
በቅርብ ያልተከታተሉትን ሰዎች በማካተት ትክክለኛ ያልሆነ መረጃ ሲሰጡና ቅስቀሳ ሲካሂዱ፤
ቆይተዋል።
የባለ አደራዎች ቦርድም፤ ከቤተ ክርስቲያን አባላት ቅሬታ አለኝ የሚል ሲከሰት፤ በመመሪያ
ደንባችን መሰረት፤በግልና በቡድን ውይይት እንዲደረግ ባደረገው ጥረት፤ በቡድን በተገኛችሁበት
ስብሰባ ላይ በዕለቱ የቦርድ አባላት አባቶች ካህናት ሳይቀሩ ተገኝተው እርስዎና ተቆርቋሪ ነን የሚሉ
ሰዎች መጥታችሁ ችግራችሁን እንድትገልጹ ስትጠየቁ እርስዎና ሌላው ተባባሪዎ ግለሰብ የወከላችሁ
ብዙ ህዝብ እንዳለ በማስመሰል “ ብዙ ሕዝብ ነው የላከን ቁጥራችንም 25 ነው፤ የመጣነው
መልእክት ለማድረስ እንጅ ለመወያየት አይደለም” የሚል እምቢተኝነትን የተላበሰ ቃላት ወርውራችሁ
እንደሄዳችሁ የሚታወስ ነው።
በ December 7, 2014 በነበረው የቤተ ክርስቲያናችን የ2ኛው ዓመታዊ ጠቅላላ ስብሰባ ላይ ያካሄዱት
እውነትነት የሌለው ቅስቀሳ ስብሰባውን የማደናቀፍና የተንኮል ተቃውሞ ምን ያህል ስር የሰደደና ቤተ
ክርስቲያናችንንና አባላቱን ወደ አላወቀው እርስዎ ብቻ ወደሚያውቁት ጉድጓድ ለመክተት
እንደሚጣጣሩ ጥልቅና ስውር እቅድ በህሊናዎ እንዳለ አሳይቷል።
በስብሰባው ላይ ላሳዩት የሥነ ምግባር ግድፈትና ጥፋት ስብሰባውን ረግጠው በመውጣቶ፤ ከአስተዳደሩ
ቦርድ በቀረበልዎት ጥሪ መሠረት Janury 2, 2015 በአካል ተገኝተው መልስ ሲሰጡ፤ ግድፈቶን አምነው
ይቅርታ ቢጠይቁም፤ የበደሉት፣ የደፈሩትና የጣሱት አባቶቻችንን፣ ምልዓተ ጉባኤውንና መመሪያችንን
ሲሆን፤ እርሰዎ ግን ወጣቶችን ብቻ የበደሉ አስመስለው፤ “ወጣቶች ሲለምኑኝ በመውጣቴና ሊቀ
ማእምራን ዶር አማረ ካሣዬ ተቀመጥ ብለውኝ ስቀመጥ እንደገና ደግመው ተቀመጥ ሲሉኝ አያዬኝም
እንዴ ተቀምጨ በማለቴ ትክክል አልነበርኩም ለዚህም ይቅርታ እጠይቃለሁ” ማለትዎ የምናውቀው
የተለመደ የሽንገላ ባህርይዎ እንደሆነ ታዝበን መልሶን ተቀብለን። ቢያንስ ጉባኤውን በድያለሁ ይቅርታ
አድርጉልኝ ከማለት ይልቅ “ወጣቶች ሲለምኑኝ እምቢ በማለቴ ነው ጥፋቴ” ብለው በመሸፋፈንለማለፍ ያደረጉትንም ጥረት ከአንድ ክርስቲያን የማይጠበቅ ቅንነት የጎደለው አባባል መሆኑን ቦርዱ
በሰፊው ተረድቶቷል።
ይሁን እንጅ የተቀበልነውን ይቅርታ መሰረት በማድረግ ቤተ ክርስቲያንም የሰላምና የይቅርታ ቤት
በመሆኗ ያለብዎትን ችግር ሰምተን በአባቶቻችን አማካይነት በሽምግልናና በመተራረም ችግሮችን
ለመፍታት ሁኔታዎችን በማመቻቸት ላይ እያለን፤ ይቅርታ የጠየቁበትን ስህተት ዘንግተው፤
የተነሱበትን የጥፋት ተልእኮዎን በመቀጠል ከአባሪዎቾ ጋር ፕሮግራም ይዛችሁ በ JANUARY 3,
2015, JANUARY 10, 2015 , JANUARY 17, 2015 እንዲሁም JANUARY 18,2015
በማከታተል በአቢሲንያ ራድዮ በቤተ ክርስቲያኗ ላይ የተለመደውን የመከፋፈል ዘመቻዎን
ቀጠሉበት።
ቀደም ብሎ SEPTEMBER 9, 2014 እራስዎ በሰበሰቡት ጉባኤ ላይ “ባንድ በኩል እውነት ተሸፍና
እንዳትቀር የምፍጨረጨር ጋዜጠኛ ነኝ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ለቤተ ክርስቲያኔ የቆምኩ ነኝ” እያሉ
ሲናገሩ፤ በስብሰባው ከተገኙት ታዳሚዎች መካከል “ከዚያ ቀደም የኀመረ ኖኅ ኪዳነ ምህረት ቤተ
ክርስቲያን ችግር ላይ በክርስትናህና በጋዜጠኝነትህ ተሸፋፍነህ ያልተወጣኸውን ታማኝነት አሁን
እንዴት ትታመናለህ?” የሚል ጥያቄ ባቀረቡልዎት ጊዜ ፤ ጥያቄውን በትክክልና በቀጥታ ከመመለስ
ይልቅ፤ ስም በመጥቀስ “የኀመረ ኖኅ ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን ችግር የፈጠሩት፤ በማርያም
አካባቢ ያሉ ሰዎች ናቸው” ብለው የመለሱት፤ ከተጠየቁበት ጉዳይ ጋራ የማይገናኝ መልስ
ከመስጠትዎም በላይ “ወጣቶች ሲለምኑኝ አለመቀበሌ ጥፋት ነው” ብለው ለማምለጥ ከሞከሩበት
ሽወዳ ጋር አንድ አድርጎታል:: ይህም ሽወዳዎ የማይታመነውና የማይጨበጠው ተለዋዋጭ ጠባይዎን
የሕሊና ወቀሳ የማይገስጸው አስመሳይ ባህሪዎን በገሀድ አሳይቷል።
ስለ ቤተ ክርስቲያናችን ሁለ ገብ የህንጻ ግንባታ እረስተውት ከሆነ፤ ለማስታወስ ያህል ቀደም ብሎ
ከስምንት ዓመታት በፊት ባለ ሙያዎች አጥንተው በአሰፈሩት እቅድ መሠረት የቤተ ክርስቲያኗ
አባላት ካጸደቁት በኋላ በአበዳሪ ባንኩ ምክርና ባለንበት ከተማ ህግ ተመሰረቶ፤ በጠቅላላ ጉባኤው
ተቀባይነት አግኝቶ፣ የመንፈሳዊ አገልግሎቱና የገንዘብ ምንጫችን እንዳይቋረጥ፣ ለብድሩ የምንከፍለው
ዕዳ ያለአንዳች እንቅፋት እንዲከናወን የተጀመረ መሆኑን፤ እንኳን ለእርስዎ ለቤተ ክርስቲያናችን
አባል ለሆኑና አባል ላልሆነው ሁኔታውን በቅርብ ለሚከታትል ግልጽ ነው። ሁለ ገብ የሕንጻ
ግንባታው ሂደት በሦስት ደረጃ በቅደም ተከተል እንደሚከናወን፤ አሁን የተጀመረው የመጀመሪያው ሁለገብ የሕንጻ ግንባታ ሂደት መሆኑን የእርስዎ ህሊና ቢክደውም፤ ጠቅላላው አባላት ግን የወሰኑት
ስለሆነ የእርስዎን የማደናቀፍ ጥረት የሚረዱት በመሆኑ ከግንዛቤ እንደማይከቱት የታወቀ ነው።
በዚህ ዓይነት ባህርይዎ የሚፈጽሙትን አስከፊ ተግባር አደገኛነቱን ማየት ቢሳንዎም፤ ህዝቡ
በድምጽ ብልጫ የወሰነውን ተግባራዊ ለማድረግ እንደ አንድ ልብ መካሪ አንደ አንድ ቃል ተናጋሪ
በመሆን፤ የአሜሪካ ህግ በሰጠን መብት ያስመዘገብነው መመሪያ ደንባችን በመከተል ይህን የመሰለ
ፈታኝና አፍራሽ ተግባር ለመቋቋም በጠቅላላው አባላት የተሰጠንን ኃላፊነት ሳንዘነጋ በገባነው ቃል
ኪዳን መሰረት ኃላፊነታችንን ለመወጣት አቅማችን የፈቀደለንን ሁሉ ለማድረግ ችላ እንደማንል
ጠንቅቀው ያውቃሉ። የዛሬን አያድርገውና የባለአደራዎች ቦርዱንና የመተዳደሪያ ደንቡን በማያጠራጥር
ሁኔታ ደግፈው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ መሆኖንዎትንም አባላት ጠንቅቀው ያውቃሉ። ስለዚህ
የባለአደራዎች ቦርድ የቤተ ክርስቲያኗን ህልውና የሚፈታተን አፍራሽ ድርጊት ሲከሰት አስተዳደራዊ
እርምጃ ባንወስድ በእግዚአብሔርም ዘንድ ያስጠይቀናል። ህሊናችንንም ይወቅሰናል። የመረጠን
ህዝብ የሰጠንን ኃላፊነት በአግባቡ አለመወጣትም ያስጠይቀናል።
በመሆኑም እኛ የርእሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ካህናት፣ አባላትና
ጠቅላላው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ እምነትና ሥርዓት የሚመሩት ምዕመናን በሙሉ
በእግዚአብሔር ቃል፣ በፍቅርና በእውነት የሚመሩ በመሆናቸው በመሐከላቸው እየገቡ የሚቃዡትንና
ለመከፋፈል የሚሞክሩትን ሐሰተኛ መልክተኞችን ለማስተናገድ ቦታ አይሰጡም። ቤተ
ክርስቲያናችንም በእግዚአብሔር ፈቃድ መገንባቷ የማይቀር ነው። ይልቁንስ እንደ እርስዎ ያሉ
በሐሰት ባህር ውስጥ ሰምጠው ለመውጣት ያቃታቸውን ለማዳን በፀሎታቸው ከጎናቸው በመቆም
እግዚአብሔር ይቅር እንዲላቸው ይማፀናሉ፡፡ አሁንም አቶ አዲሱ አበበ፣ ዛሬውኑ የያዙትን
ከእውነት የራቀ ከግል ፍላጎቶትና ከሐሰት የጥፋት ጎዳና ወጥተው፣ ወደ ልቦ ተመልሰው የኦርቶዶክስ
ተዋኅዶ ሃይማኖት በሚፈቅደው መንፈሳዊ መንገድ ሕይወትዎን እንዲመሩ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
ቀደም ብለንም ለመመሪያችንና ለጠቅላላው ጉባኤ ድምጽ ተገዥ እንዲሆኑ ምክር አዘል
ማስጠንቀቂያ ልከንልዎት ነበር። ነገር ግን እርሶ ከጀመሩት አፍራሽ እንቅስቃሴ እንደማይመለሱ
MARCH 7/2015 በአቢሲኒያ ሬዲዮ ባደረጉት ከእውነት የራቀ ቅስቀሳዎ ለመረዳት ችለናል።
በመሆኑም በመተዳደሪያ ደንባችን መሠረት ከቤተ ክርስቲያናችን አባልነት ለማስወገድ እንሆ ተገደናል።
በዚሁ ሬዲዮ ባደረጉት ንግግርዎ ማስመሰል በሚችለው አንደበትዎ ቤተ ክርስቲያኗ ህልውናዋን
ለማስጠበቅ፣ አንድነቷን ለማጽናት የወሰደችውን አስተዳደራዊ እርምጃ ለማጣጣል ከኢትዮጵያ አገራች አስተዳደራዊ ሥርዓት ጋር በማነጻጸር የሰው ልጅ ሰብአዊ መብቶች ከማይከበሩባት፣ የመናገር፣ የመጻፍ፣
የመሰብሰብና ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መሠረታዊ መብቶች የተከለከሉባት አገራችንን ሲያወድሱ
ይደመጣሉ። ይህ ሙከራዎ መሠረታዊ የሰብአዊ መብቶቻቸው እንዲከበሩ በመጠየቃቸው በየእስር
ቤቱ እየተሰቃዩና እየተጋዙ ባሉት ወገኖቻችን ላይ ሲያፌዙ፣ ከአንድ ሁኔታውን በቅርብ ከሚከታተል
ጋዜጠኛ መስማት ምን ያህል ሊያሳዝንና ሊጎዳ እንደሚችል ፍርዱን ለአድማጮቾ እንተወዋለን::
በመጨረሻም እስከዛሬ ድረስ አታካሮ ውስጥ ላለመግባት፣ ኃላፊነት ስለሚሰማንና የቤተ ክርስቲያንም
ባህሪ ስለአልሆነ ለእርሶ አጸፋውን ከመመለስ ተቆጥበን ነበር። አሁን ግን ይህችን ግልጽ ደብዳቤ
ለአንዴና ለመጨረሻ ለመጻፍ የተገደድነው፦
1. “ውሸት ሲደጋገም እውነት ይሆናል።” የሚለውን ቢሂል መሣሪያ አድርገው
እንደሚቀሳቀሱት ሁሉ የእርስዎም የሐሰት ቅስቀሳዎ ሲደጋገም እውነት እየመሰለ ስለሄደ
በቤተ ክርስቲያኗ ያለውን እውነት ግልጽ ለማድረግ፤
2. በተለይ በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ሳይወዱ ለሚተራመሱት በስደት አገር ላሉት
አብያተ ክርስቲያናት ትምህርት ሊሰጥ ይችላል ብለን በማሰብ፤
3. በሩቅም በቅርብም ጉዳዩን ሰምተው ግራ ለተጋቡ ወገኖቻችን ማብራሪያ ለመስጠት፣
4. ቤተክርስቲያናችን በዚህ ችግር ላይ መሆኗን በመስማትና አይቶ በመጨነቅ ላይ ላለት
ወገኖቻችን ሁሉ መጽናኛና መልስ ትሆናለች ብለን በማሰብ ያወጣነው መሆኑን
ወገኖቻችን እንዲገነዘቡልን በትህትና እንጠይቃለን።
ወሰብሐት ለእግዚአብሔር
የርእሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን
የባለአደራዎች ቦርድ
No comments:
Post a Comment