
በዘገባቸው ላይ እንደሰፈረው፥ . . . “ በዛሬው ዕለት ሚያዚያ 11 ቀን 2007 ዓመተ ምህረት የተለያዩ አለም ዓቀፍ ሚዲያዎች ባሰራጩት ዘገባ አይ ኤስ የተባለው አሸባሪ ቡድን ግድያ የፈፀመባቸው ስደተኞች ኢትዮጵያውያን እንደሆኑ ቢገልፁም“ . . . በማለት በመልካም ቃላት ቢያሸበራርቁትም በዓለም ላይ ያሉት ታዋቂ የዜና አጠናቃሪዎች ኢትዮጵያውያን እንደሆኑ እየተናገሩ እንኳን ይህንን ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው ስለ ፓስፖርት እና መታወቂያ በማውራት ኢትዮጵያዊነታቸው ላይ ጥርጣሬ እንዳለው እና ገና እያጣራው እንደሆነ መግለፁ ኢትዮጵያ መንግስት እንደሌላት ከሚያሳዩት ምልክቶች ቁጥር መመደብ የሚቻል አንገት አስደፊ እርምጃ ነው።
ይህ ልብን የሚያሳዝን የወያኔ ምልከታ ምን ያህል ለኢትዮጵያዊያን ደም መፍሰስ ልቡ እንደማይደነግጥ እና በደቡብ አፍሪቃም በየመንም አልፎም ተርፎ በአጭር ሰአታት ውስጥ በተጨባጭ ፊልም ተደግፎ የታየ ሆኖ ሳለ በተለያዩ የዜና ምንጮች ላይ የተዘገበውን የሊቢያውን አሰቃቂ ግድያ ገና እየተጣራ መሆኑ እጅግ አሳፋሪ እና ዜጋው ደራሽ እና መከታ እንደሌለው በተጨባጭ የሚያስረዳ ሁኔታ ነው ። በተጨማሪም በሊቢያ በስደት ያሉትን በፈቃደኝነት ወደ ሀገራቸው መመለስ የሚፈልጉ ቢገኙ ግብፅ ካለው ኤንባሲ ጋር ግንኙነት እንዲያደርጉ የሚል ሌላ ልብ አሳዛኝ ወሬ አውርቷል ። በእርግጥ ነገ ምን ሊገጥመው እንደሚችል የማያውቅ ስደተኛ በተንቀራፈፈ እና የተቀላጠፈ ስራ ሳይኖረው በሙስና እና በዘረኝነት ከተቀፈደደ ኤንባሲ ጋር በምን ፍጥነት እና ኢኮኖሚው ነው ስደተኛው ለመመለስ ካይሮ ካለ የወያኔ ኤምባሲ የሚያመለክተው? ዜጋ ከዚህስ ማጥ ማምለጥ የሚችልበትን ዘዴ እንደመንግስት ሊቀየስ የተገባው መፍትሔ በርግጥ ይህ መሆኑ ሀዘናችንን ድርብ አድርጎታል። የዚህ ሀዘን ተካፋይ ለሆንን ሁሉ የልብ መፅናናቱን እግዚአብሔር ያድርግልን።
ቢንያም ግዛው።
No comments:
Post a Comment