Thursday, May 21, 2015

የመራራ እጆች ኦፒዲኦ-ኢህአዲግን ጭንቀት እና ድንጋጤ ውስጥ ከተዋል

11149372_1592182241052973_1641463425734244573_nዶክተር መራራ ጉዲና በምርጫ ለመሳተፍ መድረክን( ኦፌኮ) ወክለው የምረጡኝ ቅስቀሳ በማርደግ በተዘዋወረበት የኦሮሚያ ክልሎች ሁሉ በጣም ሰፊ ቁጥር ያለው ተከታይ በማግኘቱ ወያኔ ድንጋጤ ውስጥ ከተውታል።
abadula_gemedaየምርጫ ግዜ እየተቃረበ መጥቷል። ከምርጫው በፊት ኢህአዲግ ምርጫውን እንዳሸነፈ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል። በየትኛው መስፈርት አልያም ህግ እንደሆነ ባይታወቅም የአሸናፊውን ቦታ ለገዚው ፓርቲ ሰጥቷል። ምርጫው ሳይጀመር የአሸናፊነትን ብስራት የሚያበስር በአለማችን ብርቅዬ አገር ኢትዮጵያ መሆኗ ይገርማል። ለነገሩ ምን ይገርማል? ህግ አውጪው እራሱ ህግ ተርጓሚ እራሱ ህግ አስፈጻሚ እራሱ በወያኔ ቁጥጥር ስር ያደረገ መንግስት ይህንን ከማድረግ ወደኋላ የማይሉ የደናቁርት ስብስብ መሆኑ የታወቀ ነው።
11011695_1592182851052912_2244778226499121642_nዶክተር መራራ ጉዲና አምቦን፣ ሻሸመኔን የመሳሰሉት የኦሮሚያ ክልል እየተዘዋወረ ኦፒዲኦ ኢህአዲግን የሚያስተዳድረውን ህዝብ ዲሞክራሲ የተጠማውን ህዝብ ሰላምን የተራበ ህዝብ ነጻነትን የሚፈልግ ህዝብ አብሮ መኖርን የናፈቀን ህዝብ በመረጠው መተዳደርንና መመራትን የጓጓውን ህዝብ እጁን ከፍ አድርጎ ለነጻነቱ፣ ለመብቱ፣ ለህይወቱ፣ ለእናቱ፣ ለሚስቱ፣ ለልጁ፣ ላገሩ በቆራጥነት በአንድ ላይ እንዲቆም መንገዱን እየጠቆመ ያለውን መራራ ጉዲናን ህዝቡ በነቂስ በመውጣት ይሄ እጅ የስራ እጅ ነው። ይሄ እጅ ጨቋኞችን የሚጥል እጅ ነው። ይሄ እጅ ዲሞክራሲን የሚያመጣ እጅ ነው። ይሄ እጅ አንባ ገነኖችን የሚያንበረክክ እጅ ነው። ይሄ እጅ ስለነጻነቱ የተነሳ እጅ ነው። ይሄ እጅ በኦሮሞ ህዝብ ስም የሚነግደውን ኦፒዲኦን አሳፍሮ የሚያጠፋ እና የሚፈጅ እጅ ነው ብሎ ለውጥን ለማምጣት የወያኔን ስርአት ያበቃለት እንደሆነ እና በህዝብ ዘንድ ምንም ድጋፍም ሆነ ተቀባይነት የለለው ያበቃለት አገዛዝ መሆኑን የመጣበት ሰዓት ነው።
በስልጣናቸው ተጠቅመው ህዝብን ረግጠውና አፍነው የሚገዙበት ያከተመበት ሰዓት ላይ ነን። ለነጻነት እውነትን መያዝ፣ ለነጻነት አንባ ገነኖችን ማስወገድ፣ ለነጻነት በኦሮሞ ህዝብ ስም ተደብቀው ኦሮሞን ከሌላው ህብረተሰብ ጋር ለማጣላት የሚጥሩትን ሰዓቱ ያለፈባቸው እና መቼም የማይሳካላቸው እንደሆነ በማሳወቅ ለኦሮሞ ተቆርቋሪ በመምሰል የኦሮሞን ጠላት የሆነውን ኦፒዲኦን የሚወገድበት ሰዓት መሆኑን ሁሉም ህዝብ አውቆ እና ነቅቶ በመንቀሳቀስ ላይ ነው።
የዶክተር መራራ እጅ ህዝቡን በአንድነት ያነሳሳ ያስተሳሰረ የነጻነት እጅ ነው። የመራራ እጅ ከእንግዲህ ወዲያ በወያኔ ኦፒዲኦ መገዛት፣ በአፋኞች መታፈን፣ በአሳሪዎች መታሰር አንፈልግም ያለ እጅ ነው። የመራራ እጅ ኦፒዲኦ ኢህአዲግ የተባለውን የኦሮሞ ማሊያ ለብሶ የኦሮምን ህዝብ ሲያስገድል ሲያስር ሲዘርፍ የነበረውን ያስደነገጠ ያስቆጣ የረበሸ እና ያተራመሰ  እጅ ነው።
ህዝቤ ሆይ ተነስ!!! በሰሜን ብንሄድ የተጠላ መንግስት በደቡብ ብንሄድ የተወገዘ  መንግስት በምስራቅ ብንሄድ የማይፈለግ መንግስት በምዕራብ ብንሄድ የተተፋ መንግስት ስለሆነ ህዝብን አፍኖ እና ረግጦ ለማስተዳደር በሚያደርገው እሩጫ በየትኛውም የኢትዮጵያ አካባቢ ተቀባይነት የሌለው የህዝብ ድጋፍም ሆነ ድምጽ የሌለው የተሸነፈ መንግስት ኢትዮጵያን እንዲመራት መፍቀድ የለብንም።
ወያኔ በማጭበርበር ስራ ህዝቡ መረጠኝ ለማስባል ከምርጫው በፊት የራሱን ፎርም አዘጋጅቶ  ወደገጠሪቷ አካባቢ በመሄድ ኢህአዲግን ምረጡ በማለት የተናቀ  እና የወረደ ተግባር እየሰራ ያለውን መንግስት ነኝ ባዩን በማጋለጥ ህዝብ የመረጠው እና ለእውነተኛ ዲሞክራሲያዊ ታጋዮች ወደ ስልጣን የሚመጡበት ግዜ እየደረሰ ስለሆነ በሁሉም አቅጣጫ ወያኔን አንቅሮ የተፋው ህዝብ እራሱን በተለያየ ስም ደብቆ መርዙን የሚረጨውን ኦፒዲኦ ብሎ ለኦሮሞ ተቆርቋሪ በመምሰል ብአዴን ብሎ ለአማራ ተቆርቋሪ በመምሰል ድህዴን ብሎ ለደቡብ ተቆርቋሪ በመምሰል ህዝብን የሚያጭበረብርበት እና የሚጨቁንበት ዘመን አብቅቷል።
የመራራ እጅ የኦፒዲኦ ኢህአዲግን የጭቆና ዘመንን ፍጻሜውን አብስራለች።

No comments:

Post a Comment