


በስልጣናቸው ተጠቅመው ህዝብን ረግጠውና አፍነው የሚገዙበት ያከተመበት ሰዓት ላይ ነን። ለነጻነት እውነትን መያዝ፣ ለነጻነት አንባ ገነኖችን ማስወገድ፣ ለነጻነት በኦሮሞ ህዝብ ስም ተደብቀው ኦሮሞን ከሌላው ህብረተሰብ ጋር ለማጣላት የሚጥሩትን ሰዓቱ ያለፈባቸው እና መቼም የማይሳካላቸው እንደሆነ በማሳወቅ ለኦሮሞ ተቆርቋሪ በመምሰል የኦሮሞን ጠላት የሆነውን ኦፒዲኦን የሚወገድበት ሰዓት መሆኑን ሁሉም ህዝብ አውቆ እና ነቅቶ በመንቀሳቀስ ላይ ነው።
የዶክተር መራራ እጅ ህዝቡን በአንድነት ያነሳሳ ያስተሳሰረ የነጻነት እጅ ነው። የመራራ እጅ ከእንግዲህ ወዲያ በወያኔ ኦፒዲኦ መገዛት፣ በአፋኞች መታፈን፣ በአሳሪዎች መታሰር አንፈልግም ያለ እጅ ነው። የመራራ እጅ ኦፒዲኦ ኢህአዲግ የተባለውን የኦሮሞ ማሊያ ለብሶ የኦሮምን ህዝብ ሲያስገድል ሲያስር ሲዘርፍ የነበረውን ያስደነገጠ ያስቆጣ የረበሸ እና ያተራመሰ እጅ ነው።
ህዝቤ ሆይ ተነስ!!! በሰሜን ብንሄድ የተጠላ መንግስት በደቡብ ብንሄድ የተወገዘ መንግስት በምስራቅ ብንሄድ የማይፈለግ መንግስት በምዕራብ ብንሄድ የተተፋ መንግስት ስለሆነ ህዝብን አፍኖ እና ረግጦ ለማስተዳደር በሚያደርገው እሩጫ በየትኛውም የኢትዮጵያ አካባቢ ተቀባይነት የሌለው የህዝብ ድጋፍም ሆነ ድምጽ የሌለው የተሸነፈ መንግስት ኢትዮጵያን እንዲመራት መፍቀድ የለብንም።
ወያኔ በማጭበርበር ስራ ህዝቡ መረጠኝ ለማስባል ከምርጫው በፊት የራሱን ፎርም አዘጋጅቶ ወደገጠሪቷ አካባቢ በመሄድ ኢህአዲግን ምረጡ በማለት የተናቀ እና የወረደ ተግባር እየሰራ ያለውን መንግስት ነኝ ባዩን በማጋለጥ ህዝብ የመረጠው እና ለእውነተኛ ዲሞክራሲያዊ ታጋዮች ወደ ስልጣን የሚመጡበት ግዜ እየደረሰ ስለሆነ በሁሉም አቅጣጫ ወያኔን አንቅሮ የተፋው ህዝብ እራሱን በተለያየ ስም ደብቆ መርዙን የሚረጨውን ኦፒዲኦ ብሎ ለኦሮሞ ተቆርቋሪ በመምሰል ብአዴን ብሎ ለአማራ ተቆርቋሪ በመምሰል ድህዴን ብሎ ለደቡብ ተቆርቋሪ በመምሰል ህዝብን የሚያጭበረብርበት እና የሚጨቁንበት ዘመን አብቅቷል።
የመራራ እጅ የኦፒዲኦ ኢህአዲግን የጭቆና ዘመንን ፍጻሜውን አብስራለች።
No comments:
Post a Comment