Wednesday, May 6, 2015

ብፁዕ አቡነ አብርሃም የባሕር ዳር ከተማ ሀገረ ስብከትን እንዲመሩ ተመደቡ

ብፁዕ አቡነ አብርሃምብፁዕ አቡነ አብርሃምሐራ ዘተዋሕዶ
የምዕራብ ጎጃም – ፍኖተ ሰላም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም፣ የባሕር ዳር ከተማ ሀገረ ስብከትን ደርበው እንዲመሩ የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መደባቸው፡፡
ምልዓተ ጉባኤው ብፁዕነታቸውን የመደበው፣ የባሕር ዳር ከተማ የአዊ እና መተከል ዞኖች ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ሚያዝያ ፱ ቀን በድንገተኛ ሕመም ማረፋቸውን ተከትሎ ነው፡፡
ለብፁዕነታቸው መልካም የሥራ ዘመን እንመኝላቸዋለን፡፡

No comments:

Post a Comment