Thursday, May 21, 2015

አረና ቅስቀሣውን አቋረጠ፤ በአባሎቹ ላይ ጥቃት መፈፀሙን አስታወቀ

DBED33B8-D8E6-4018-9CE8-8589E7956DD0_w640_r1_s_cx0_cy8_cw0ተቃዋሚው አረና ትግራይ “በአባሎቼ ላይ ተፈፅሟል” ባለው ድብደባና ለምርጫ ቅስቀሣ ሥራ በተከራያት መለስተኛ አውቶቡስ ላይ በደረሰው ጉዳት ምክንያት በመላው የትግራይ ክልል የጀመረውን የምረጡኝ ቅስቀሣ ዛሬ ማቋረጡን ይፋ አድርጓል። ተቃዋሚው አረና ትግራይ “በአባሎቼ ላይ ተፈፅሟል” ባለው ድብደባና ለምርጫ ቅስቀሣ ሥራ በተከራያት መለስተኛ አውቶቡስ ላይ በደረሰው ጉዳት ምክንያት በመላው የትግራይ ክልል የጀመረውን የምረጡኝ ቅስቀሣ ዛሬ ማቋረጡን ይፋ አድርጓል። ዘጋቢያችን ግርማይ ገብሩ የተሽከርካሪዋ የኋላ መስትዋትና መብራት መሰባበሩን በሥፍራው በአካል ተገኝቶ ተመልክቷል።
ድብደባ ተፈፀመብን ከሚሉ ሰዎች መካከል ደግሞ ከአፅቢ ከተማ የመጡት አቶ ሄድሮም ኃይለሥላሴ እራሣቸው ላይ በመፈንከታቸው መቀሌ ውስጥ ሕክምና ማግኘታቸው ተገልጿል፡፡ አረና “የህወሓት ካድሬዎች ያደራጇቸው ወጣቶች አድርሰውታል” ያለውን ጥቃት አስመልክቶ የክልሉ የፀጥታና የአስተዳደር ኃላፊ አቶ ሓዱሽ ዘነበ ተጠይቀው “ተፈጽሟል የተባለውን ጥቃት ለማጣራት መርማሪዎቻችንን ወደ አካባቢው ልከናል፤” ብለዋል፡፡  ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል
ያዳምጡ፡፡

No comments:

Post a Comment