OPPOSITION PARTIES WEBSITES
▼
ETHIO NEWS & VIEWS
▼
RADIO & TV
▼
የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ አባላትና ደጋፊ በኖርዌይ ከተሞች ተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ
በመላው አለም የተከበረውን የወዝ አደሮችን ቀን ምክንያት በማድረግ በኖርዌይ ከተሞች በተለይም በኦስሎ በበርገንና በስታቫንገር የሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል
በዚህ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ባዘጋጀው ሰልፍ ላይ በአሁኗ ሰዓት በስደት ላይ ያሉ ወገኖቻችን በደቡብ አፍሪካ በየመንና በሊብያ የደረሰባቸውን ግፍና ጭካኔ በማውገዝ መፈክሮች ያሰሙ ሲሆን በወያኔ መንግስት በግፍ ታስረው በየወይኒ ቤቱ የሚገኙት የሕሊና እስረኞች ይፈቱ ዘንድ ጠይቀዋል በማያያዝም የኖርዌይ መንግስት ለአንባገነኑ የወያኔ መንግስት የሚያደርገውን ድጋፍ ያጤነው ዘንድ እንዲሁም የኖርዌይ ህብረተሰብ የሚከፍለው ታክስ ለጨኝቋ አገዛዞች እንዳይውል ይቆጣጠሩ ዘንድ በራሪ ወረቀቶችን በመስጠት አሳስበዋል።
No comments:
Post a Comment