Monday, July 27, 2015

ሰበር ዜና – ኮማንደር ወልደሚካኤል ገ/እዝጊአብሄር እና ካሕሳይ ነጋሽ እርምጃ ተወሰደባቸው -

11223543_1134599499900891_4045522694507239238_nበትግራይ ምዕራባዊ ዞን ማይ-ሰገን በተባለው አካባቢ የሚገኙትን የኢህአዴግ የሰራዊት አባላት በግንቦት 7 አርበኞች ግንባር ሰራዊት በደረሰባቸው ድንገተኛ የማጥቃት እርምጃ ምክንያት ሙትና ቁስለኛ መሆናቸውን ተገለፀ። ባለፈው ቀናት በሑመራ አካባቢ ማይ ሰገን በተባለው ቦታ ላይ የግንቦት 7 አርበኞች ግንባር ሰራዊት በኢህአዴግ ሰራዊት ላይ ባደረሱት ድንገተኛ የማጥቃት እርምጃ ብዛት ያላቸው ታጣቂዎች ከጥቅም ውጭ ማድረጋቸውን የገለጸው መረጃው በውጊያው ከተገደሉት ታጣቂ አመራሮችም።…. ኮማንደር ወልደሚካኤል ገብረእዝጊአብሄር የሃይል አዛዥ የነበረ፤ ካሕሳይ ነጋሽ በባዕኸር የሚልሻ አዛዥ የነበረ፤ ለግዜው ስሙ ያልታወቀው የሻምበል ማእርግ ያለው በ24ኛ ክፍለጦር የሓይል አዛዥ የሆነውና ሌሎች የሚገኙባቸው እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል። እነዚህ የስርዓቱ ታጣቂዎች- በአካባቢው ሰላማዊ ህዝብ የተለያዩ ግፍ ሲፈፅሙ የቆዩ በመሆናቸው የተነሳ የግንቦት 7 አርበኞች ግንባር ሰራዊት በላያቸው ላይ እርምጃ መውሰዱን የተገኘው መረጃው አስረድቷል። 

No comments:

Post a Comment