Thursday, July 23, 2015

ሰበር መረጃ – ከውስጥ ታጋይ አርበኞች የተላከ መረጃ

ginbot 7“ሰሞኑን ከተው የከረሙት የ ህወዓት ባለስልጣናት የተስማሙበት እና ለፓርላማ ውይይት እንዲቀርብ የደረሱበት ውሳኔ:
አገሪቷ የተቃጣባትን ጥቃት ለመከላከል እራስን የመከላከል ካውንተር ኦፌንሲቭ እርምጃ መውሰድ አለብን፥፥ ይህ እርምጃ የ አለም አቀፍ ስምምነቶችን ከግንዛቤ ያስገባ እና ወዳጅ አገሮቻችን ለምናደርገው እራስን የመከላከል እርምጃ ድጋፋቸው እንዳይለየን በ አገራችን እና ህዝባችን ሰላም ላይ ያነጣጠረ የስጋት ድባብ ማየሉን በመረጃ አስደግፈን ለ አለም የጸጥታው ምክርቤት ፥ ለኢጋድ እና መሰል ድርጅቶች እና አጋር አገሮች ደብዳቤ ሰርኩሌት በማድረግ ህጋዊነታችንን ማረጋገጥ አለብን፥፥
ይህ የምናደርገው ሁለገብ ካወንተር ኦፌንሲቭ ለ አንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ሰላማችንን እና ልማታችንን የሚያደናቅፉ የጥፋት ሃይሎች ላይ የማያዳግም እርምጃ እንወስዳለን፥፥ ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት ለህዝባችን እና ለ አለም ህዝብ በተለይ ደግሞ ለ ወዳጅ አገሮች ይህ ጦርነት ወደን ሳይሆን ተገደን የምንገባበት መሆኑን ከፈተኛ የሆነ የፕሮፓጋንዳ እና የዲፕሎማሲ ስራወችን መስራት ይጠበቅብናል፥፥ የተቃጣብን ትንኮሳ በተለይ በ አሁኑ ወቅት አገራችን በ አልሻባብ እስላማዊ አክራሪ ቡድን ላይ የተቃጣብንን ዳግም ትንኮሳ በመመከት ላይ እያለን መሆኑ የ አለም ህዝብ እንዲገነዘብልን መስራት አለብን፥፥
ይህን ወቅታዊ ችግራችንን አይተው ለመጠቀም ያሰፈሰፉ አሸባሪወችን ለመከላከል በምናደርገው ሁለገብ እራስን የመከላልከል እርምጃ በተለይ የሱዳን ህዝብና መንግስት ከጎናችን እንዲቆም ጥሪ ማቅረብ አለብን፥፥ ደህንነት እና መከላከያ በጋራ በመሆን አስቸኳይ ካወንተር ኦፌንሲቭ ኮምፕረኽንሲቭ እቅድ መንደፍ እንዳለባቸው በማሳሰብ ይህንን የሚመራ ጊዜያዊ ቡድን ተመርጧል፥፥”

No comments:

Post a Comment