Thursday, April 2, 2015

ጥንታውያን የብራና መጻሕፍት እንደ ሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ ጽ/ቤት – ዳንኤል ክብረት

CIMG4002በግእዝ የተጻፉ ጥንታውያን መዛግብት ከተጻፉበት ዓላማ በተጨማሪ ሌሎችንም አገልግሎቶች ሲሰጡ ኖረዋል፡፡ አብዛኞቹ የተጻፉት ለሃይማኖት ማስተማሪያነትና ለታሪክ መመዝገቢያነት ቢሆንም በየዘመናቱ የተፈጠሩትን ማኅበራዊ ክስተቶች ተከትለው ሌሎችንም አገልግሎቶች ሰጥተዋል፡፡
በዚህ ጥናታዊ ጽሑፍ አንደኛውን እንመለከታለን፡፡ ጥንታውያን የብራና መጻሕፍት እንደ ሰነዶች  ምዝገባና ማረጋገጫ ጽ/ቤት ሆነው ሲያገለግሉ የኖሩበትን አሠራር፡፡
በጥንታውያን የግእዝ የብራና  ጽሑፎች  ላይ ከሃይማኖታዊና ታሪካዊ ይዘቶች በተጨማሪ በመጻሕፍቱ መጀመሪያና መጨረሻ በሚኖሩ ባዶ የብራና ቅጠሎች፣ በኅዳጎች፣ በራስጌና  በግርጌ ክፍት ቦታዎች ላይ ውሎችን፣ ቃል ኪዳኖችንና ስጦታዎችን ሲመዘግቡ ኖረዋል፡፡ እነዚህ ምዝገባዎች በተዋዋዮቹ፣ በገዥዎቹና ሻጮቹ፣  በስጦታ ሰጭዎቹ ወዘተ መካከል የሚኖሩትን ስምምነቶች በማስፈር እንደ ሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ ጽ/ቤት እየሆኑ ማገልገላቸውን ያሳዩናል፡፡
( ጥናታዊ ጽሑፉን ቀጥሎ ካለው የፒዲኤፍ ፋይል ይመልከቱ)   [ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ] pdf

No comments:

Post a Comment