በደቡብ አፍሪካይቱ ደርባን ከተማ ካለፈው ሣምንት ማብቂያ ጀምሮ በውጭ ሀገር ዜጎች ላይ በደረሱ ጥቃቶች ቢያንስ አምስት ሰው መገደሉን የተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። ደርባን ውስጥ ለጥቃት የተጋለጡ ኢትዮጵያዊያን ሰልፍ /መጋቢት 30/2007 ዓ.ም – ደርባን ከተማ ማዘጋጃ ቤት ደጃፍ/ ትናንት፤ ማክሰኞ – ሚያዝያ 6 / 2007 ዓ.ም ደርባን ከተማ ጎዳናዎች ላይ ሁከት ተፈጥሯል። ኢትዮጵያዊያኑን ጨምሮ ደርባን ውስጥ የሚኖሩ አፍሪካዊያን በፍርሃት ቤታቸውን ዘግተው ተቀምጠዋል። ለዝርዝሩ የተያያዘውን ዘገባ ያዳምጡ፡፡
No comments:
Post a Comment