Saturday, April 25, 2015

ከጩኸት ወደ ተግባር የሚነገድበት የስደት ማእበል ትውልድ ከየት መጣ? ለማቆም እንረባረብ። አክሎግ ቢራራ (ዶር) ከጩኸት ወደ ተግባር የሚነገድበት የስደት ማእበል ትውልድ ከየት መጣ? ለማቆም እንረባረብ። አክሎግ ቢራራ (ዶር)

ከጩኸት ወደ ተግባር  የሚነገድበት የስደት ማእበል ትውልድ ከየት መጣ? ለማቆም እንረባረብ።  አክሎግ ቢራራ (ዶር)እኛ ኢትዮጵያዊያን ከፋሽስቱ የጣሊያን ወረራ ወዲህ እንደዚህ ዓመት ተዋርደን አናውቅም። ውርደቱ ተከታታይና የማያቆም ለመሆኑ ምክንያቶቹ ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጭ ግንባርን (ህወሓት) ብሎ ከሚጠራው የጎሳዎች የበላይ ገዢ ፓርቲ ብቻ ሳይሆን እኛም ጭምር ነን። የሊቢያ ሽብርተኞች የኢትዮጵያን ወጣት ክርስቲያኖች፤ በኃይማኖታቸውና በማንነታቸው ለይተው “የእስልምና ኃይማኖት በእናንተ ኃይማኖት አማካይነት ደም ማፍሰስ ርካሽ አይደለም” (“Muslim blood that was shed under the hands of your religion is not cheap”) ብለው ወገኖቻችንን ሲያርዷቸውና በጥይት ሲገድሏቸው ያየ ኢትዮጵያዊና ማንም በሰው ህይወት ክቡርነት የሚያምን ግለሰብ ሁሉ ቪዲወውን አይቶ እንቅልፍ ለመተኛትና በሰላም ለመኖር አይችልም። ህሊናውን ለመመራመር ይገደዳል። ይኼ ብሄር፤ ብሄረሰብ ሳይለይ፤ በንፁህ ኢትዮጵያዊያን ላይ የደረሰው ግፍ በሌሎች ክርስቲያኖች፤ የእስልምናና ሌሎች ኃይማኖቶች ተከታዮች (አሜሪካኖች፤ እንግሊዞች፤ ጃፓኒሶች፤ ግብፆች፤ ጆርዳኒያኖችና ሌሎች) ላይም ደርሷል። ሽብርተኞቹ “በእስልምና ኃይማኖት ተከታዮች ላይ የደረሰው “ደም ማፍሰስ” ያሉት የኢትዮጵያ መንግሥት በሶማሌ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ገብነት መሆኑን ለመገመት ይቻላል። እኔ እስከማውቀው ድረስ የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች በኢትዮጵያ የሚኖሩ፤ ኢትዮጵያዊያን ወንድሞችና እህቶች የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮችን የገደለና ያረደ የለም። ታሪክ የመዘገበው ሃቅ አንድ ነው። ይኼውም የነብዩ ሞሃመድ ተከታዮች በሳውዲ አረቢያ ግፍ ሲደርስባቸው ተከታዮቹን የላከው ወደ ክርስቲያኗ ኢትዮጵያ መሆኑን ነው። ይኽች ሃገር የእስልምና ኃይማኖት ተከታዮችን አስተናግዳ፤ እነሱም ኢትዮጵያዊነታቸውን ተቀብለው፤ ኃይማኖታቸውን አስከብረው ከክርስትና ኃይማኖት ተከታዮች ጋር ተጎራብተው፤ ተጋብተውና ተከባብረው ለብዙ መቶ ዓመታት ኑረዋል፤ ወደፊትም ይኖራሉ። ታሪክ እንዲህ በሚል ያስተምረናል። “Islam was introduced to Ethiopia in 615 AD when the followers of Prophet Mohammed, including his wife sought refuge in Aksum. The king of Aksum welcomed them, respected their religion and offered them protection. They later settled in Negash, east of Tigray, which has become one of the most important places for the Islamic faith in Ethiopia. Prophet Mohammed ordered his followers not harm Ethiopians. Islam spread to the east of the country mainly the Harar region, which was established by Sultan Abu Beker Mohammed in 1520 and became the Holy City for the Muslims. Harar also became an important city for trade, famous for its Islamic architecture such as the City Walls and a centre of Muslim scholarship.” ባጭሩ፤ የኢትዮጵያ የክርስትናና የእስልምና ተከታዮች አንዱ ሌላውን በማይጎዳ መልክ፤ በሰላምና በመከባበር ለአንድ ሽህ አራት መቶ ዓመታት ኑረዋል። ወደፊትም አብረው፤ ተከባብረው ይኖራሉ የሚል ግምትና እምነት አለኝ። ስለሆነው፤ ሽብርተኞቹ በኢትዮጵያ የኃይማኖት ጦርነት እንዲነሳ ለማድረግ የሚሞክሩት ቅስቀሳ ለክርስቲያኑ ሆነ ለእስልምና ኃይማኖት ተከታዩ ኢትዮጵያዊ ይጎዳል። ተቀባይነት እንዳይኖረው መከላከል የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ያልተቆጠበ ጥረት መሆን አለበት እላለሁ። ገዢው ፓርቲ ኃይማኖትን ለፖለቲካ መሳሪያ መጠቀሙን ካላቆመ ይኼ የመቻችልና አብሮ የመኖር ታሪክ ይወድማል። ለኢትዮጵያ ጠላቶች መግቢያ ይሆናል። በኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ላይ የደረሰው ግፍ በእሥልምና ኃይማኖት ተከታዮችም ላይ እንደደረሰ የሚቆጠረው ለዚህ ነው። በተጨማሪ፤ በኢትዮጵያና በሌሎች ክርስትያኖች ላይ የሚደረገው ግድያ የዓለሙን ሕብረተሰብ አምቢተኛነት፤ ህብረትና ትግል ይጠይቃል። እምቢተኛነቱ ዓለም አቀፋዊ መሆን ይኖርበታል። የተባበሩት መንግሥታት፤ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት፤ የሰብአዊ መብቶች ድርጅቶች ወዘተ ከመንግሥታት ጋር ተባብረው የአይስልን፤ የአልካይዳን፤ የቦኮ ሃራምን፤ የአል ሸባብና ሌሎች ሽብርተኞችን ኢ-ሰብአዊ ግፍ መቋቋም አለባቸው። የኢትዮጵያ መንግሥት ያለምንም ማመንታት ከሌሎች ጋር አብሮና ተባብሮ ያልተቆጠበ ጥረት ማድረግ ይኖርበታል። ሁኖም፤ ፀረ-ሽብርተኛነት ዘመቻ ብቻውን ዘላቂ መፍትሄ ያመጣል የሚል ግምትና እምነት የለኝም። በሶማሊያ፤ በአፍጋኒስታን፤ በኢራክ፤ በየመን፤ በሶሪያና ሌሎች ሃገሮች ለሽብርተኛነት መንስኤ የሆኑትንና የሚሆኑትን--የሰብአዊ መብቶችና የነጻነት መገፈፍ፤ የፍትህ-ርትእ አለመኖር፤ የኃይማኖት መብት መታፈን፤ የስራ እድል በተፈለገው ደረጃ አለመስፋፋት፤ የእድገትና የገቢ መዛባት፤ ለሕዝብ ታዛዥ የሆነ መንግሥት አለመኖር፤ የጎሳዊና የኃይማኖት አድልዎ፤ የጉቦ፤ የሙስናና ከሃገር የሚሸሽ ሃብት ተቋማዊ መሆናቸው 2 ለሽብርተኛነትና ለስደት መጋቢ ሁነዋል። እነዚህ ስርዓት ወይንም አገዛዝ ወለድ የሆኑ ማነቆዎች ካልተወገዱ ሽብርተኛነትና ስደት ይቀጥላሉ። በአንድ ሃገር ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ ገብነት ይቀጥላል። አገዛዙ ራሱ የሚያመጣውን ችግር አልተረዳውም። የዚህ ሃተታ መሰረተ ሃሳብ ይኼ በሊብያ የደረሰው አሰቃቂና ወንጀለኛ ግፍ በተናጠል መታየት የለበትም የሚል ነው። በዚህ ዓመትና ባለፉት ሁለት ዓመታት ብቻ በኢትዮጵያዊያን---በአብዛኛው ወጣት ትውልድ--ላይ የደረሰው ኢ-ሰብአዊ ግፍ በምን ምክንያት ተከታታይ እንደሆነ ማጤን ግድ ይላል። በNovember, 2013 የሳውዲ አረቢያ መንግሥት 163,000 የቀንና የቤት ሰረታኞችን በጅምላ ከሃገሩ አስወጥቷል። በውጭ የሚገኘው ኢትዮጵያዊ ስደተኛ በመተባበር፤ በገፍ ወጥቶ ሰላማዊ ሰልፍ አድርጓል። የሳውዲ አረቢያና የኢትዮጵያ መንግሥታት ሃላፊነት እንዲወስዱ ለማድረግ ችሏል። ለዚህ የተቋቋመው አሁን Global Alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) ተብሎ የሚጠራው የሰብአዊ መብት ጠበቃ የሆነው ድርጅት ድምፅ በማሰማት ብቻ ሳይቆጠብ ኢትዮጵያዊያን ገንዘብ እንዲያዋጡ ዘመቻ አድርጎ በInternational Organization for Migration (IOM) በኩል የብዙ ሽህ ዶላር ድጋፍ ሰጥቷል። አሁንም ጠበቃነቱን ቀጥሏል። የየመን መንግሥትን ማስረጃ በመጠቀም IOM አንድ ሚሊየን ኢትዮጵያዊያን በየመን ብቻ እንደሚገኙ ተናግሯል። እነዚህ ወገኖቻችን ወደ የመን የሚሄዱበት ዋና ምክንያት በየመን የስራ እድል አለ በሚል ግምት አይደለም። የመንን እንደ ሊቢያ መሸጋገሪያ ለማድረግ ነው። እነዚህ ኢትዮጵያዊያን ከሃገር የሚወጡት ተበድረውም ሆነ ወላጆች፤ ዘመዶቻቸው ብዙ ሽህ ዶላር ወይንም ብር ለደላላዎች ከፍለው ነው። በወገኖቻቸው የሚደልሉና የሚነግዱ ከገዢው ፓርቲ ቁጥጥር ውጭ የሆኑ ግለሰቦችና ድርጅቶች መኖራቸውን የህወሓት/ኢህአዴግ መንግሥት ያምናል። የማያምነው ራሱና ከራሱ ጋር በጥቅም ተሳስረው በኢትዮጵያዊያን ህይወት የሚደልሉና የሚነግዱ መኖራቸውን ነው። የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር መስሪያ ቤት (UNHCR) ባለፈው ዓመት መጨረሻ ያወጣው ሰፊ ጥናትና ማስረጃ የኢትዮጵያ አዲስ ትውልድ የሚነገድበትና ብዙ መቶ ሚሊየን ዶላር የሚተረፍበት መሆኑን አሳይቶ ወደ ከፍተኛ አጣብቂኝ እንደገባ ያሳያል። የህወሓት/ኢህአዴግ መንግሥት እነዚህን የሰው ደላላዎች/ነጋዴዎች ፈቃድ የሚሰጥና ችግሩም ሲከሰት ፈቃዳቸውን የማይከለክል ቡድን ሁኗል። ልክ እንደ ሙስናው ማለት ነው። ፈቃዱን የሚሰጠው ራሱ ሁኖ ችግሩ ሲከሰት በሌሎች ያመኻኛል። መንግሥት በዓመት ከሚሰጠው የመውጫ ፈቃድ፤ ከቀረጥ ወዘተ ምን ያክል ገቢ እንደሚያገኝ ግልፅ አያደርግም። የሰው ነጋዲዎች ምን ያህል ገቢ እንደሚያገኙ፤ እነማን እንደሆኑ፤ ከዓለም አቀፍ የሰው ደላላዎች ጋር እንዴት ያለ ቁርኝት እንዳላቸው ወዘተ አይታወቅም። የማይካደው ከፈለገ የህወሓት/ኢህአዴግ መንግሥት ግለሰቦቹ ከሃገር ሲወጡ ምን አይነት ችግር እንደሚገጥማቸው ለማወቅና አደጋውን ለማስረዳት ይችላል፤ አላደረገውም። ለንግድና ለገቢ ትኩረት የሚሰጥ አገዛዝ ጉዳቱ ይኼው ነው፤ ለሰው ክቡርነትና ህይወት የሚሰጠው ዋጋ ዝቅተኛ ነው። በሊቢያ እንደ በግ አንገታቸው ተቆርጦ፤ እንደ ተራ ነፍሰ ገዳይ በጥይት ተገድለው ያዩ ሁሉ--የተባበሩት መንግሥታት፤ ቫቲካን፤ የግብፅ፤ የአሜሪካና ሌሎች መንግሥታት--ወዲያውኑ ድርጊቱን አውግዘዋል። በግብፅ የኢትዮጵያ አምባሳደር “ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን እያጣራሁ ነው፤ አንዳንዶቹ በሽብርተኞች ሳይሆን በሰው ደላላዎች (Human Traffickers) የተገደሉ ይመስለኛል” ሲል ቀፈፈኝ፤ ዘገነነኝ። ምን አልባት ዲኤንኤ (DNA) ልይ ይል ይሆን የሚል ጥያቄ በዐእምሮየ ተቀረጸ። አገር ወዳዱ የግብጽ መንግሥት የሃገሩ ኮፕቲክ ክርስቲያኖች አንገት ሲታረድ ሳያመነታታ አፀፋውን ሽብርተኞች ባሉበት ቦምብ አድርጓል። የታረዱትና በጥይት ተደብድበው የሞቱት ኢትዮጵያዊያን “እኛ ኢትዮጵያዊያን እንደታረድን” እቆጥረዋለሁ። በእኔም፤ በሌሎቻችንም የተደረገ የማይረሳ ጥቃት ነው። የአምባሳደሩ ግምገማ መግባት ሃገርና ሁሉን ኢትዮጱያዊያን የሚያፈቅር መሆኑን አያሳይም። የሚያሳየው መለያየት የወከለው አገዛዝ የፖለቲካ ባህል መሆኑን ነው። የችግሩ ክብደት ምን ያህል ነው? ኢትዮጵያዊያን ለሃገሪቱ ህልውና በሚያሰጋ ደረጃ በገፍ ከሃገር መሰደድ ልምድ የሆነበት መንግሥት የህወሓት/ኢህአዴግ መንግሥት ነው። በየመን ብቻ አንድ ሚሊየን ስደተኞች ካሉ በዓለም ዙሪያ ምን ያህል ይሆኑ ይሆን የሚለውን ጥያቄ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ መጠየቅ አለበት። ጠይቆ ራሱን መመርመር አለበት። በሊቢያ በግፍ ከተገደሉት ወገኖቻችን በተጨማሪ፤ ባለፈው ሳምንት በመርከብ ወደ አውⶂፓ ይጓዙ ከነበሩት ወደ አንድ ሽህ ከሚጠጉት የሞቱ ሰዎች መካከል አራት መቶወቹ ኢትዮጵያዊያን ናቸው የሚል ዘገባ አለ፡፡ ሮይተር እንዳስታወቀው ከሆነ ሁለት መርከቦች ወይንም ጀልባዎች ሁለት መቶ አምሳ የኢትዮጵያ፤ የጋናና የሴኔጋል ተወላጆች ይዞ ሲጓዝ በሊቢያ ሚሊሽያ ተይዘዋል። ሚሊሺያው ሽብርተኛ ይሁን አይሁን፤ የት እንደሚወስዳቸውና ምን እንደሚያደርጋቸው አይታወቅም። ሁለተኛ 3 መርከብ ወይንም ጀልባ ለመከራ የተዳረጉትን ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያንን ብቻ ጭኖ ሲሄድ እንደተያዘ ተነግሯል፡፡ በሊቢያ ስንት ኢትዮጵያዊያን እንደሚገኙና በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ አናውቅም። የምናውቀው ለአደጋ መጋለጣቸውን ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት በህግ ከሃገር ከሚሰደዱት ውጭ ስንት ስደተኛ እንዳለ ማስረጃ የለውም። ስደቱ ማእበል መሆኑን እያመነ ነው። ኢትዮጵያዊያን የማይሰደዱበት የዓለም ክፍል የለም። በሌባኖን የሚኖሩ ወጣት ሴቶች በየቀኑ የሚደርስባቸው ግፍ ለህሊና ይቀፋል። አንዲት ወጣት ኢትዮጵያዊት ግፉ ሲበዛባት ከቀጣሪዎቿ አራተኛ ፎቅ ራሷን መንጥቃ ወድቃለች፤ ሁኔታዋ አይታወቅም። በተመሳሳይ፤ ሌላ ወጣት ሴት የቀን ሰራተኛ በጭንቀቷ የተነሳ ራሷን ገድላለች። በሌሎች የአረብ አገሮች የሚኖሩ ወጣት ሴቶች የሚደርስባቸው ግፍ ለሰራተኛ መብታቸው የቆመ መንግሥት እንደሌላቸው ያሳያል። በደሃዎቹ የአፍሪካ ሃገሮች፤ ማላዊና ዛምቢያ ብዙ መቶ ኢትዮጵያዊያን ታስረዋል። ኢትዮጵያዊያን በማላዊ ኃይቅ እንደሞቱ እናውቃለን። የአፄ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት ለጥቁር ደቡብ አፍሪካዊያን ስደተኞችና የነጻነት ተዋጊዎች ያላደረገው ነገር የለም። የትምኅርት እድል ሰጥቷል፤ ገንዘብና መጠለያ ሰጥቷል። ተዋጊዎችን አሰልጥኗል። የማያወላውል የፀረ- አፓርታይድ አቋም ይዞ የዲፕሎማቲክ ድጋፍ ሰጥቷል። በተመሳሳይ የደርግ መንግሥት ለፀረ- አፓርታይድ ትግል ከፍተኛ አስተዋፆ አድርጓል። የደቡብ አፍሪካ ጥቁር ሕዝብ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊያን ዜጎች የማይረሳ ውለታ አለበት። የኢትዮጵያ ወዳድ በነበረው ባለፈው በተወዳጁ ማንዴላ ሃገር ኢትዮጵያዊያን ተገድለዋል። ንብረታቸው ወድሟል። የሚዘገንነውና የማይረሳው ሁለት ኢትዮጵያዊ ወንድምቻችን በታጎሩበት ቤት ቤንዚን ተረጭቶ ተቃጠለው መሞታቸው ነው። የደቡብ አፍሪካ መንግሥትና ሕዝብ ሃላፊነት እንዳለበት አያከራክርም፤ ይኬ በቂ አይደለም። መፈታት ያለበት የችግሩ መንስኤ ነው (The Root cause of our shame and tragedy). ይኼ ግፍ ባለፉት መንግሥታት የማይታሰብ መሆኑን ብዙ ማስረጃዎች አሉ። ለምሳሌ፤ አገዛዙ በፈጠረው በደል ከደርግ መንግሥት አምልጠው ወደ ሱዳን፤ ኬንያና ዩጋንዳ በተሰደዱ ኢትዮጵያዊያን የሰብአዊ መብቶች ገፈፋ ሲደረግና በጅምላ ውጡ “ውጡ” የሚል ግፊት ሲደረግ ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማሪያም የተናገረው ትዝ ይለኛል። “እነዚህ ኢትዮጵያዊያን የጠሉትና የሚቃወሙት እኔንና እኔ የምመራውን መንግሥት ነው። እኔን ስለጠሉ ጠበቃና ሃገር የላቸውም ማለት አይደለም። በኢትዮጵያውዊነታቸው ማንም መንግሥት እንዲያሰቃያቸው አልፈቅድም። ይኼ ከሆነ የኢትዮጵያ መንግሥት አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል” ብሎ ነበር። ቁም ነገሩ አጼ ኃይለ ሥላሴን ሆነ መንግሥቱን መጥላት ወይንም መውደድ አይደለም። የማንም ኢትዮጵያዊ መብት ሲነካ ተቆርቋሪ የሆነ መንግሥት ድሙጹን የማሰማት ሃላፊነት አለበት ለማለት ነው። በደቡብ አፍሪካ የተካሄደው ግፍ ሲካሄድ ገዢው ፓርቲ፤ ሌሎች ሃገሮች እንዳደረጉት የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ሃላፊነት እንዲወስድ፤ ግድያው እንዲቆም፤ ኢትዮጵያዊያን በሰላም እስከኖሩ ድረስ ሰብአዊ መብታቸው እንዲከበር አልጠየቀም፤ አምባሳደሩን ልሳብ አላለም። ልክ በሳወዲ አረቢያ፤ በሌባኖን፤ በየመንና ሌሎች ሃገሮች እንዳደረገው “ከሩቅ ሁኖ ማየት” መመሪያው ሁኗል። በስልጣኑ ላይ ለሚነሳ ማንኛውም ትችትና የሕዝብ እምቢተኛነት የአፈና ፍጥነት የሚያሳየው አገዛዝ ለኢትዮጵያዊን ሰብአዊ መብቶች ደንታ እንደሌለው በተደጋጋሚ ታይቷል። “የሃገር አንበሳ፤ የውጭ እሬሳ” በሊቢያ የደረሰውን አሰቃቂ እልቂት በሚመለከት በገፍ ተሰልፎ ሃዘኑን፤ ምሬቱን፤ ቁጭቱን፤ ኢትዮጵያዊነቱን፤ ፍትህ ፈላጊነቱን ወዘተ በአዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ከተሞች ካስተጋባው ሰፊ ሕዝብ መካከል የአገዛዙን ሃላፊነትና ተጠሪነት በሚመለከት ድምፃቸውን በድፍረት እያሰሙ፤ “ወያኔ ሌባ፤ ሌባ፤ የአገር አንበሳ፤ የውጭ እሬሳ፤ መንግሥት የለም፤ የኢትዮጵያ መንግሥት የት ነው” ወዘተ እያሉ የጮሁበት ምክንያት አገር ወዳድ፤ መላውን ሕዝብ ወዳድና አስተናጋጅ የሆነ መንግሥትና አመራር እንደሌላቸው ስለሚያውቁ ነው። እኔን በተለይ የሳበኝና ይኼን ፅሁፍ ጠንካራ በሆነ መንገድ እንዳዘጋጅ ያበረታታኝ “የአገር አንበሳ፤ የውጭ እሬሳ” የሚለው መፈክር ነው። ህወሓት በበላይነት የሚያዘው አገዛዝ ብሄር፤ ብሄረሰብ፤ ጾታና ኃይማኖት ሳይለይ ሁሉኑም ኢትዮጵያዊያን ገርፏል፤ አድክሟል፤ አግልሏል፤ አዋርዷል፤ ሰብአዊ መብቶቹንና ክብሩን ገፏል። የኢትዮጵያን ግዛታዊ አንድነትና ሉዐላዊነት አውድሟል። የኢትዮጵያን ሕዝብ የተፈጥሮ ኃብት ለውጭ ወዳጆቹ ነግዷል። ተደጋጋሚ ጥቃት የሚደርስበት ሕዝብ የጥቃቱና የውርደቱ ምክንያት ምን እንደሆነ የማወቅ መብት ብቻ ሳይሆን ግዴታም አለበት። “እኔን አያገባኝም” ካለ ሲታረድ፤ ሲገደል፤ ሲዋረድ፤ ሲሰደብ፤ ሲሰደድ ይኖራል። ይኼ መልሶ ወደ ሂሳቡ ያመራኛል። ቁጥር ትርጉም አለው። ቁጥር የችግሩን መጠንና ክብደት ያመለክታል። 4 ከላይ የጠቀስኩት የተባበሩት መንግሥታት ከፍተኛ የስደተኞች ኮሚሽን ባለፈው ዓመት ያወጣው የኢትዮጵያን ሰፊና ተከታታይ የሰው ኃይል ድለላና ንግድ (Human Trafficking) የሚመለከት ዘገባ እንዲህ ይላል። “ዛሬ ኢትዮጵያ ወደ ሃገሯ የሚገቡና ከሃገሯ የሚወጡ ሰዎች መተላለፊያና መነገሻ ሃገር ናት…” Ethiopia serves as a transit country for men, women and children who are subjected to forced labor, and sex trafficking.” መቀበል ያለብን አንድ ሃቅ አለ። ኢትዮጵያዊያን የሃያ አንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን “የሰራተኛ ባርነት” አካል ሁነናል። የሰው ንግድ ከሚያስፈራ ደረጃ ላይ ደርሷል። እንደኔ ያለው፤ ሃኪሙ፤ ፕሮፌሰሩ፤ መሃንዲሱ፤ የግል ኃብት ያለው ወዘተ የወገኖቸ ንግድ እኔን አይመለከተኝም እንደሚል አምናለሁ። አንዱ ችግራችን ክህደት ሁኗል። እኛን እስካልነካን፤ እኛ ደልቶን እስከኖርን፤ እኛ ኢትዮጱያ ደርሰን እስከመጣን ድረስ፤ እኛ ለጡሮታ ስንበቃ ኢትዮጵያ ሂደን እስከኖርን ድረን፤ እኛ በአውሮፕላን ተጭኖ የሚመጣ እንጀራ እስከበላን ድረስ ወዘተ ችግሩ እንደማይነካንና እንደማይመለከተን እናስተጋባለን። ስለዚህ፤ ችግሩ አገዛዙ የፈጠረው ብቻ አይደለም። እኛም ተባባሪና መጋቢ ሁነናል። ኢትዮጵያዊያን እየተነገደባቸው ነው ጥናቱ ኢትዮጵያዊያን በራሳቸው ሕዝብ ንግድ እያካሄዱ፤ በያመቱ ብዙ መቶ ሚሊየን ዶላር ትርፍ እንደሚያገኙ ያሳያል። በሚሰደዱት በኩል የሚደርሰውን ችግርና በደል እንዲህ ይለዋል። “Ethiopians transit through Djibouti, Egypt, Somalia, Sudan, or Yemen as they emigrate seeking work in the Middle East; some become stranded and exploited in these transit countries, and are subjected to detention, extortion, and severe abuses – some of which include forced labor and sex trafficking – while en route to their final destinations. Young women are subjected to domestic servitude throughout the Middle East, as well as in Sudan and South Sudan. Many Ethiopian women working in domestic service in the Middle East face severe abuses, including physical and sexual assault, denial of salary, sleep deprivation, withholding of passports, confinement, and even murder. Ethiopian women are sometimes exploited in the sex trade after migrating for labor purposes – particularly in brothels, mining camps, and near oil fields in Sudan and South Sudan – or after fleeing abusive employers in the Middle East. Low-skilled Ethiopian men and boys migrate to Saudi Arabia, the Gulf States, and other African nations, where some are subjected to forced labor.” መነሻ ኢትዮጵያ፤ መድረሻ የትም ዓለም ባጠቃላይ ሲታይ በገፍ ከሃገር የሚሰደደው ትውልድ በደርግ የመጨረሻ ዓመታትና በህወሓት/ኢህአዴግ መንግሥት የተወለደው ነው። ሰባ በመቶ የሚሆነውን የኢትዮጵያን ሕዝብ ይወክላል። የሚሰደዱባቸውን ሃገሮችና የሚደርስባቸውን አሰቃቂ ግፍ ከላይ አሳይቻለሁ። ኢትዮጵያዊያን በገፍ የሚወጡት በሁለት መንገዶች ነው---ዱሮ እንደሚባለው አንዱ “በቦሌ፤ ሌላው በባሌ.” በቦሌ የሚወጣው ፓስፖርትና ቪሳ አግኝቶ ለስራ ወይንም ለሌላ ይሰደዳል። ገዢው መንግሥት ከእያንዳንዱ ፓስፖርት ብዙ ገንዘብ ይሰበስባል፤ ንግድ ማለት ነው። ወጥቶ ገቢውን በውጭ ምንዛሬ ወደ ሃገር ይልካል። ሌላው ከላይ በተጠቀሱት ሃገሮች ለደላላና ለሰው ነጋዴ ገንዘብ ከፍሎ ይሰደዳል። አንዱ በማእረግ፤ ሌላው በአሰቃቂ ሁኔታ ይወጣል ማለት ነው። እኛ በቦሌ የወጣነው ስደተኞች ለኢትዮጵያ ያስከተልነውን አሰቃቂ ችግር በሚገባ አላሰብንበትም። እኛ ሃገራችን ለስራ እድል ብለን ለቀን ስንሰደድ ኢትዮጵያ ተቆርቋሪዎቿን እንደምታጣ አላሰብንበትም። ስደተኛው ብዙ አሉታዊ ሁኔታወችን ፈጥሯል። ተሰደን ባገኘነው ገንዘብ ቤት ስንሰራና ጡሮታ ስንወጣ፤ ገቢያችን አገር ቤት ከሚኖረው ተራ ሕዝብ ከፍተኛ ስለሆነ የመግዛት አቅማችን የሌላቸውን ወገኖቻችን እንደሚጎዳ አላሰብንበትም፤ ብናስብበትም ልክ እንደ ተራ ነገር እንቆጥረዋለን። ገዢው ፓርቲ ብቻ ሳይሆን ስደተኛው ለዋጋ ግሽበት ምክንያት ነው። የምንልከው የውጭ ምንዛሬ ለገዢው ፓርቲ የበላይነትና ባለፀጋነት መጋቢ እንደሆነ መገንዘብ አለብን። ገንዘባችን ለሰብ አዊ መብቶቻችን መገፈፊያ ይሆንል ማለት ነው። ገጠሬ ሆነ ከተሜ፤ በቦሌ ይውጣ በባሌ፤ ስደተኛው በውጭ ሃገር መኖርና መስራት ኑሮን እንደሚያሻሽል ስለሚያስተጋባ ሌላውም ወጣት ትውልድ ለመብቱ በመታገል ፋንታ፤ መሰደድን የገቢና የኑሮ ማሻሻያ መንገድ አድርጎ ተቀብሎታል። የሰው ነጋዴዎችና ገዢው መንግሥት ከሃገር መሰደድ ጥቅም እናንዳለው፤ ገቢና ኑሮ እንደሚያሻሽል ይናገራሉ (Marketing migration is part of the business). የማይቀበሉት፤ 5 የህወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ የስራ እድል መጥበብን ችግር የሚወጣው ወጣቱን ትውልድ በገፍ እንዲሰደድ የመውጫ ፈቃድ እንደ ምርት ማቅረቡን ነው። የቁጥሩን መጠን ስናይ ይኼ ታስቦበት የሚካሄድ ንግድ እንዴት አደገኛ እንደሆነ ለመገመት ይቻላል። ስራ አጥነትን በስደት እንወጣው የሚል ስልት። በቦሌ የሚጓዘውን ስደተኛ ስናይ፤ የአሜሪካ ዲቢ የተባለው የመግቢያ ፈቃድ ሁኔታውን አባብሶታል። ይኼ የማህበረሰብ ኃይል ስደትና ውድመት ለገዢው ፓርቲ ያስገኘው የፖሊቲካ፤ የኢኮኖሚና የፋይናንስ የበላይነት ጥቅም ግልጽ ነው። ሃገር በባዶ የሰው ኃይል ቤት ሊገነባ አይችልም። መለስ እንዳለው፤ አናሳው የህወሓት ቡድን “አይሁዶች የተጎናፀፉትን የኢኮኖሚ የበላይነት እኛም (ጥቂቶቹ ማለቱ ነው) ስኬታማ ማድረግ አለብን ያለው መርህ ተግባራዊ ሁኗል። የተማረው ስደተኛ እየጨመረ ሲሄድ በሃገር ውስጥ የሚኖረው ተወዳዳሪና ተቀናቃኝ እየቀነሰ ይሄዳል። “ላለው ይጨመርለታል” እንዲሉ ሌላው ተወዳዳሪ በስደት የሚኖር ሸማች መሆኑ ለገዢው ፓርቲ ከፍተኛ ስጦታ ሁኗል። ህወሓት የሚቆጣጠረው አገዛዝ ለስደት ያለው ያልተቆጠበ ትኩረትና ድጋፍ ከዚህ ታስቦበት ከተዘጋጀ የፖለቲካ፤ የኢኮኖሚ፤ የፋይናንስና የተፈጥሮ ኃብት የበላየት ጋር ተያይዟል። የችግሩ መጋቢ የሆነው ክፍል (ስደተኛው) አዛዡና አሽከርካሪው የሆነውን አገዛዝ ሲወቅስ ራሱንም መተቸት ይኖርበታል። ህወሓት/ኢህአዴግ የሚሰራውን ያውቃል። ሌላው የሚሰራውን አያውቅም፤ ገዢው ፓርቲ የሚጠቀምበት መሆኑን ይክዳል። የፓስፖርቱ ፋብሪካ የሰራተኛና የማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቲር የሚሰበስበው ዘገባ የሚያሳየው ፓስፖርት አውጥተው፤ ቪዛ አግኝተው ከኢትዮጵያ የሚወጡት ኢትዮጵያዊያን በአብዛኛው ወደ ምእራብ አገሮችና ስምምነት ወዳለበት የአረብ አገሮች ይሰደዳሉ። መስሪያ ቤቱ በቀን አንድ ሽህ አምስት መቶ ኢትዮጵያዊያን ከሃገር እንደሚወጡ አረጋግጧል። እነዚህ “በሕግ የሚወጡ” ይባላሉ። ሂሳቡ የሚሸፍነው ከሚወጣው ሰላሳ በመቶ የሚሆነውን ነው። አንባቢ እንዲገነዘበው ወይም እንድትገነዘበው የምፈልገው ሂሳቡን ነው። ፓስፖርት ተሰጥቶት በየቀኑ የሚወጣው ኢትዮጵያዊ ብዛት አንድ ሽህ አምስት መቶ ከሆነ፤ በዓመት 547,500 (ከግማሽ ሚሊየን በላይ) ይሰደዳል ማለት ነው። ከኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር ሩብ በላይ። ሚኒስትሩ በቀን ሰባ በመቶ የሚሆነው ከሕግ ውጭ በተከፈተው የስደት መንገድ የሚወጣ መሆኑን ገምቷል። ይኼን ሂሳብ ሳይ ለማመን ተቸግሬ ነበር። የተጻፈውን ደጋግሜ ሳይ ከቆየሁ በኋላ በየመን የተሰደዱት ኢትዮጵያዊያን ቁጥር ትዝ አለኝ፤ አንድ ሚሊየን በየመን ብቻ። ሰባ በመቶ የሚሆነው በሰው ነጋዴዎችና በሌላ መንገድ የሚወጣ ከሆነ በቀን 3,500 ይሰደዳል ማለት ነው። ሂሳቡን እዩትና ፍረዱ። “ህገ ወጥ” በሚባለው መንገድ በዓመት ከኢትዮጵያ የሚሰደደው ኢትዮጵያዊ ወጣት ትውልድ ብዛት 1 ,825, 000 (አንድ ሚሊየን ስምንት መቶ ሃያ አምስት ሽህ መሆኑ ነው። በሕግና ከሕግ ውጭ የሚሰደደው ማእበል ብዛት 2, 372, 500 (ሁለት ሚሊየን ሶስት መቶ ሰባ ሁለት ሽህ አምስት መቶ መሆኑ ነው)። የዓለም ባንክና የተባበሩት መንግሥታት የሰራተኛ ድርጅት ጥናቶች የሚያመለክቱት ኢትዮጵያ በዓመት ሁለት ሚሊየን አምስት መቶ ሽህ የስራ እድሎች ለወጣቶች መፍጠር አለባት የሚል ነው። ከላይ ያሳየሁት ግዙፍ የሆነ የስደተኛ ቁጥር የሚያሳየው፤ “አስደናቂው እድገትና” ለልማት ትኩረት የሚሰጠው “እድገታዊው” አገዛዝ የስራ እጥረትን ችግር የሚወጣው ስደትን በመቀበልና በማበረታታት ነው። አስደናቂና ፍትሃዊ እድገት ቢኖር በያመቱ የሚሰደደው ከሁለት ሚሊየን ሶስት መቶ ሽህ በላይ የሚሆእነው የሚሰደድ ወጣት ትውልድ የስራ እድል ይኖረው ነበር፤ በአንድ ፓርቲ የበላይነት የሚገዛው መንግሥት ወጣቱ ትውልድ የራሱን ስራ እንዲፈጥር ሁኔታዎችን ያመቻች ነበር። በገፍ የሚካሄደው ስደት ሌላ ጥቅም አለው። ወጣቱ ትውልድ ለመብቱ እንዳይቆም፤ ከሕዝብ ጋር ተጋርቶ አመፅ እንዳያካሂድ ይረዳል። ምናልባት ከላይ የቀረበው ሂሳብ ያስደነገጣቸው አንባቢዎች እንዴት ይኼ ይሆናል ይላሉ በሚል ግምት የወጣውን ዘገባ ከታች እንዳለ አቅርቤዋለሁ። “In October 2013, the Ethiopian government banned overseas labor recruitment. Preceding the ban, Ministry of Labor and Social Affairs (MOLSA) officials reported that up to 1,500 Ethiopians departed daily as part of the legal migration process. Officials estimated this likely represented only 30 to 40 percent of those migrating for work; the remaining 60 to 70 percent were smuggled with the facilitation of illegal brokers. Brokers serve as the primary recruiters in rural areas. Over 400 employment agencies were licensed to recruit Ethiopians for work abroad; however, government officials acknowledged many to be involved in both legal and illegal recruitment, leading to the government's ban on labor export. Following the ban, irregular labor migration through Sudan is believed to have increased. Eritreans residing in Ethiopia-based refugee camps, some of whom 6 voluntarily migrate out of the camps, and others who are lured or abducted from the camps, face situations of human trafficking in Sudan and Egypt's Sinai Peninsula” (UNHCR report, 2014). ኢትዮጵያ ብዙ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፤ የውጭ ሃገሮች የበጎ አድራጎት ተቋሞች፤ ኢንቬስተሮች፤ አማካሪዎች፤ ቱሪስቶች ወዘተ የሚኖሩባትና የሚጎበኟት ሃገር ሁናለች። ይኼ ራሱ ወንጀል ወይንም ችግር ሊሆን አይችልም። በሌላው ሃገር ይሆናል፤ መሆንም አለበት። ችግሩ አብሮ የሚመጣው የመጥፎ ልምድና ባህል ጓዝ ነው። ጥናቱ እንዲህ ይላል። “The central market in Addis Ababa (Merkato) is home to the largest collection of brothels in Africa, with girls as young as 8-years-old in prostitution in these establishments.” አስደናቂ እድገት አለ፤ እድሚያቸው ለትምኅርት የደረሱ ወጣት ሴቶች ይማራሉ ወዘተ በሚባልባት ሃገር የስምንት ዓመት እድሜ ያላቸው “ህጻናት” ሴቶች እንዴት ራሳቸውን ለመሸጥ ተገደዱ ብለን መጠየቅ ግድ ይላል። ሃገሪቱን በበላይነት የሚገዛው፤ ለጥቂት ሚሊየኔሮች ያላሰቡት ኃብት ያስረከበው፤ ጥቂት የጎሳ ነጋዴዎችንና “የወፍ ዘራሽ ባለፀጋዎችን” ያመረተው አገዛዝ ለእነዚህ ደሃ ወጣት ሴቶች ህይወት መሻሻል ሃላፊነት አለበት ወይንስ የለበትም? የሚለውን አስኳል ጥያቄ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በዜግነቱ ብቻ ሳይሆን በሰብእነቱ ማጤን አለበት። እኔ የምደመድመው ሃላፊነትና ተጠሪነቱ የማያከራክር በሚል ነው። የህወሓት/ኢህአዴግ ደጋፊዎች እንዲህ እንደሚሉ አስቀድሜ እገምታለሁ። መንግሥት የሰው ንግዱን አቁሟል ይላሉ፡፡ ወደ ሳውዲ አረቢያና ሌሎች የአረብ አገሮች መንግሥት የሚልከው የሰው ኃይል ቀነሰ ማለት ስደቱ ቀነሰ ማለት አይደለም። ከላይ ጥናቱ እንደሚያመለክተው በሁለቱ ሱዳኖችና በግብፅ፤ ሌላው ቀርቶ በሊቢያ የሚወጣው ስደተኛ መጠን አላቆመም፤ በኬንያ፤ በጅቡቲና በሶማልያ የሚወጣው ቀጥሏል። ገዢው ፓርቲ በዓመት ለሁለት ሚሊየን አምስት መቶ ሽህ ወጣቶች ስራ አልፈጠረም። የስደቱ መነሻ ስርዓቱ ስለሆነ፤ ስርዓቱ ካልተለወጠ ወይንም ራሱን ካልቀየረ (ራሱን የሚለውጥ አይመስለኝም) ችግሩ ይቀጥላል፤ እንዲያውም ይባባሳል። ጩኸቱና ለቅሶው አይበቃም የምልበትን ምክንያት አሳይቻለሁ። በሊቢያ አንገታቸው የታረደውን፤ በጥይት የተገደሉትን፤ በደቡብ አፍሪካና ሌሎች ሃገሮች የሞቱትን፤ በስደት ላይ ያሉትን ወዘተ ስናንሰላስል አፋኙንና አግላዩን አገዛዝ መርሳት የለብንም። የማን ልጅ ይማራል፤ የማን ልጅ ይሰደዳል? ከተራው የትግራይ ወይንም ሌላ ድሃ ኢትዮጵያዊ ገበሬ ልጆች እድገትና የወደፊት እድል ህይወት አንጻር ሲታይ ስርዓቱ ቀጭ፤ አፋኝ፤ አግላይና አድካሚ ነው ለማለት ያስደፍራል። ማን ተጠቃሚ ሆነ? የህወሓት የበላይ ባለስልጣናቶችና ወዳጆቻቸው ልጆች ናቸው። ህወሓት የወደፊት መሪዎችን፤ ሃብታሞችን መስርቷል። “ይድረስ ለኢሃዴግ አመራር አባላት፤ ልጆቻችሁ ቻይና ምን እየሰሩ ነው?” በማለት ተመስገን ደሳለኝ “እናንተ የግንባሩ አባላትና ደጋፊዎች! ለመሆኑ አብዛኞቹ የፓርቲያችሁ አመራሮች ምን እያሰቡ እንደሆነ ቀርቶ ምን እያደረጉ እንደሆነ ታውቃላችሁ? ለምሳሌ ስዮም መስፍን፤ ስብሓት ነጋ፤ አባይ ጸሓዪ፤ ክንፈ ገ/መድህን (በህይወት የሌሉ)፤ አርከበ እቁባይ፤ በረከት ሰምኦን፤ አዲሱ ለገሰ…ልጆቻቸው የት ናቸው?.....ካላወቃችሁ እኔ ልንገራችሁ፤ እነዚህ የባለስልጣኖች ልጆች የ12ኛ ክፍል ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ፤ የዩኒቨርስቲ ትምህርታቸውን ከቅርብ አመታት ወዲህ “ወዳጅ” በሆነቻቸው ቻይና ይከታተሉ ዘንድ ተልከዋል….” ድሃው የትግራይና የሌላው ኢትዮጵያ ገበሬ ወይንም መካከለኛ መድብ የለት ጉርስ ለማግኘት ይቸገራል። የዶሮ ዋጋ እስከ አራት መቶ ብር ከደረሰ ስደትና ውርደት የማይቀር ነው። የፖለቲካ ስልጣን ይዘው ከፍተኛ ኃብት ያካበቱት ባለስልጣናት ልጆች የሚወጡት በቦሌ ነው። ለስደት ሳይሆን ለከፍተኛ ትምኅርት ወይንም ለስራ ነው። በባሌ የሚሰደደው ድሃና የድሃ ልጅ ወዶ ሳይሆን ገዢው ፓርቲ የስራ እድል ለመፍጠር ስላልቻለና ለወጣቱ ትውልድ ትኩረት ስላልሰጠ ነው። የማን ልጅ ይማራል፤ የማን ልጅ ይሰደዳል፤ የማን ልጅ ወደፊት ይገዛል፤ የማን ልጅ አንገቱ ተቆርጦ ወይንም በጀልባ ተገልብጦ ወይንም በጦርነት መስክ ተሰዶ ይሞታል? ብለን ስንጠይቅ፤ እኛስ ምን እያደረግን ነው የሚለውን መሳት የለብንም። ራሳችንን ካላስከበርን ማንም አያከብረንም። ወገኖቻችን ካልተከበሩ እኛም አንከበርም። የገዢው ፓርቲ የበላዮች ለልጆቻቸው ምርጥ እድል የከፈቱላቸው “ፈላጭ ቆራጭነታቸውን” ተጠቅመው፤ ማንም ሊጠይቀን አይችልም ብለው ነው። የስርአቱ አድሏዊ፤ በደላዊ፤ ዘራፊያዊ መሆን በዚህም ተከስቷል። የእነዚህ ምርጥ ወጣቶች በድሃው የኢትዮጵያ ሕዝብ ወጭ በህወሓት ወዳጅ ሃገር፤ ቻይና ብዙ ሽህ ዶላር እየተከፈለ መማር ስናይ፤ የእነሱ መማር ለምስኪኑና በየቦታው ለተሰደደው የትግራይ፤ የጋምቤላ፤ የአፋር፤ የኦሮምያ፤ የሶማሌ፤ የጉራጌ፤ የአማራ ወዘተ ድሃ ገበሬ ልጅ፤ በየወሩ ለሚሰደደድው አምስት ሽህ ወጣት፤ እንደ ተራ ሸቀጥ በእየቀኑ ወደ ሳውዲ አረቢያ ለሚሄዱት እህቶቻችን ምን ፋይዳ አለው? የለውም። የሚደጉመው የወደፊት ገዢዎችን መሆኑን ለመጠራጠር አይቻልም። የህወሓት አገዛዝ፤ በተለይ ለድሃው የሚዘገንን የሚሆነው ለዚህም ጭምር ነው። 7 በአጠቃላይ፤ በሊቢያ አንገታቸው እንደ በግ የታረዱትን፤ በጥይት የሞቱትንና ሌሎችን ስናስብ ትኩረቱ ለዚህ ያበቃቸው የአገዛዝ ስርዓት ምን እንደሆነ ማጤን ይኖርብናል። ወጣቱ ትውልድ ተምሮ ለስደት መዳረግ የለበትም። ገዢውን ፓርቲ መተቸት ብቻ በቂ አይደለም። በተመሳሳይ የተሰደደው ግዙፍ ኢትዮጵያዊ ምን አስተዋጾ ሊያደርግ ይችላል? የሚለው ጥያቄ አግባብ አለው። በድርጊቱ ከተቆጣን ለአንዲት ኢትዮጵያና ለመላው ሕዝቧ ነጻነት፤ እውነተኛ እኩልነትና ዲሞክራሳዊ አገዛዝ አብረን፤ ተባብረን የምንቆምበት ወቅት አሁን ካልሆነ መቸ እንደሚሆን ለማሰብ እቸገራለሁ። የውጭ ጠላቶቻችንና የውስጥ ገዢዎቻችን በአንድ ድምጽ የሚሰሩ መሆናቸውን በተደጋጋሚ አይተናል። በጥቃቅን ልዩነቶች ላይ ማተኮሩን እንተወው፤ አስጠቅቶናል፤ አሳፍሮናል፤ አድክሞናል። በገፍ ለሚሰደደውና ለሚዋረደው ብዙ ሚሊየን ወጣት ትውልድ እንደምናስብ አምናለሁ። እምነት፤ ጩኸት፤ ፀሎት አስፈላጊ ቢሆኑም አንገት ቆራጭ ሽብርተኞችን አይከላከሉም። አፋኝ፤ አግላይና ራሱን አገልጋይ የሆነ የመንግሥት ስርዓትን አይለውጡም። ሁለቱንም አብሮና ተባብሮ ለመለወጥ ይቻላል የሚል እመነት አለኝ።

No comments:

Post a Comment