
Tuesday, December 29, 2015
አንዳንድ ስህተቶች፣ አዲስ አይን ማውጣት፣ ወደ ውስጥ መመልከት ያሻል፤ – ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ -
በረታችንን ክፍቱን አናሳድርም፤ ያረባነውን፣ ያሰባነውን አውሬ ሊቀራመትብን፣ ሌባ ሊነዳብን ይችላል፡፡
ምን ብናሳድጋቸው፣ ምን ብናሰባቸው እንሰሳት ናቸውና ለነዳቸው ይነዳሉ፤ ጥርሱን ካገጠጠ አውሬም ራሳቸውን ሊከላከሉ አይቻላቸውም፡፡ ሰው ግን እንደዚህ አይደለም፡፡ ራሱን ይከላከላል፤ ይጠብቃል፡፡ ሰው ለነዳው አይነዳም፤ የሰበከውን አይከተልም፡፡ በዚህም የተነሳ በበረታችን እንዳሉት ከብቶች፣ ላሳደግናቸው ልጆቻችን አንሰጋም፡፡ ልጆቻችንን ለመስረቅ ቀድሞ ህሊናቸውን፣ ማስተዋላቸውን መስረቅ ያስፈልጋል፡፡ ይህ ደግሞ ቀላል አይደለም፤ በስነምግባር ኮትኩተን ያሳደግናቸው ልጆቻችንን፣ ማንም በአፍታ ሰበካ ከጎጇችን ሊሰርቃቸው አይችልም፡፡ አስራ ስምንት አመት አብሮን የኖረ ልጃችንን የአፍታ ሰባኪ ካሸፈተብን፣ ድሮም አብሮን አልነበረም ማለት ነው፡፡ በስነምግባርና በእውቀት አንጸን አላሳደግነውም ማለት ነው፡፡ ከብብታችን ለመሽሎክ ‹‹ተከተለኝ›› በይ ጠሪ እየጠበቀ ነበር ማለት ነው፡፡ . . . እና ይህ ሲሆን ወላጅ ሰራቂውን፣ ወይም ልጁን መኮነን የለበትም፤ መጠየቅ ያለበት ራሱን ነው፡፡ ለአስራ ስምንት አመታት ያነጽኩት ግምብ እንዴት በአንድ ቀን ሰበካ ይናዳል? ወይስ ራሴ የገነባሁ መስሎኝ ሳፈርሰው ኖሬያለሁ? ወይስ መስሎኝ እንጂ ከቶም ያነጽኩት ግምብ አልነበረም? ምን ብንበድለው ነው ያሳደግነው ልጃችን ፊቱን ያዞረብን?. . . . ወዘተ. የመሳሰሉትን ጥያቄዎች መጠየቅ አለበት – ወላጅ፡፡ ከነዚህ ጥያቄዎች የሚገኘው መልስ እድሜው ገፍቶ ላላረጠ ወላጅ፣ ቀጣይ ልጁን እንዴት ማሳደግ እንዳለበት ትምህርት ይሆናል፡፡
.
ኢህአዴግም ማድረግ ያለበት እንዲሁ ነው፡፡ ለሀያ አምስት አመታት ያስተዳደረው ህዝብ (ወጣትም ይሁን ጎልማሳ) ለተቃውሞ አደባባይ ሲወጣ፣ መጠየቅ ያለበት ራሱን ነው፡፡ ለሀያ አምስት አመታት ያስተዳደረው ህዝብ፤ መንገድ ሰራሁለት፣ ትምህርት አስፋፋሁለት፣ ድህነቱን ቀነስኩለት የሚለው ህዝብ፤ በግዳጅ ለጦርነት ከመማገድ አዳንኩት፣ በጥቃቅንና አነስተኛ አደራጅቼ ስራ ፈጠርኩለት የሚለው ወጣት፣ መንገድ ዘግቶ፣ ድንጋይ ወርውሮ፣ ለተቃውሞ ሲወጣ፣‹‹በአሸባሪዎችና በጸረሰላም ሀይሎች ስብከት ተደልሎና ተወናድዶ ነው›› የሚል ምክንያት ማቅረብ ውሀ አያነሳም፡፡ እና ኢህአዴግ ራሱን መጠየቅ አለበት! ከጫንቃው ላይ ደርግን ያህል ግፈኛ መንግስት ያስወገድኩለት ህዝብ፣ ያስተማርኩትና ስራ የፈጠርኩለት ወጣት፣ በቀናት የሽብርተኞች ስብከት ተደልሎ ለጥፋት ሊነሳ ይችላል? ከቻለስ ስለምን በአሸባሪዎች ከንቱ ስብከት ተቃወመኝ? እኔ ሬዲና ቴሌቪዥን ይዤ፣ እየተሸሎከለኩ የሚሰብኩ ሀይሎች፣ እንደምን ተሰሚነት አግኝተው አመጽ ሊነሳ ቻለ? ከእኔ ልማታዊ- ተግባር የእነሱን ሽብራዊ ስብከት ስለምን ተቀበለ? ወይስ ስራ እየፈጠርኩለት፣ ድህነቱን እየቀነስኩለት አልነበረም? . . .ወዘተ. የመሳሰሉ በርካታ ጥያቄዎች ለራሱ ማቅረብ አለበት፡፡
.
ይህ ካልሆነና፣ ኢህአዴግ ችግር በተፈጠረ ቁጥር፣ ተቃውሞ በተነሳ ቁጥር፣ ‹‹አሸባሪዎችንና ‹‹ጸረልማት ሀይሎችን›› ተጠያቂ የሚያደርግ ከሆነ፣ችግሩን ከስሩ አልመረመረምና ዘላቂ መፍትሄ ሊያገኝ አይችልም፡፡ ይልቁንም እንዲህ ያለው ራስን ነጻ ማውጣትና ሌሎችን ተጠያቂ ማድረግ፣ እብሪትን ስለሚያጸና ሀይልን ወደመጠቀም ይገፋፋል፡፡ ሰሞኑን በኦሮምያ ክልል በተፈጠረው ችግር የደረሰው የሞት አደጋም ሰበቡ ይኸው ነው፡፡ ኢሕአዴግ እውነት ‹‹ተቃውሞው የተቀሰቀሰው ከህዝቡ ወገን ባልሆኑ ሀይሎች ነው›› ብሎ የሚያምን ከሆነ፣ የተወናበደው ተቃዋሚ ላይ፣ ተወናብዶ እንጂ የእኔ ነው የሚለው ተቃዋሚ ላይ መተኮስ የለበትም፡፡ እዚህ ላይ ኢህአዴግ በተቃውሞ የሚደርሰውን የሰላም መቃወስና የንብረት መውደም የመከላከል ሀላፊነት እንዳለበት አልዘነጋሁም፡፡ ግን በምንም መንገድ የሰው ህይወት መጥፋት የለበትም፡፡ በየሀገሩ ከተሞችን ያነደደ ተቃውሞ ያለምንም ህይወት መጥፋት ሲያልፍ አይተናል፡፡ የፈረሰው ድልድይና ህንጻ መልሶ ሲገነባም አይተናል፤ የሞተ ሰው ግን ተቃውሞው አልፎ ሰላም ሲወርድ፣ ከመቃብር ሲነሳ አልተመለከትንም፡፡
.
አብዛኛውን ጊዜ ኢህአዴግ በተቃውሞ ወቅት የሚደርሱ የሞት አደጋዎችን ምክንያታዊ ለማድረግ፣ በፖሊስ አባላት ላይ የተፈጸሙ ጥቃቶችን እንደመግፍኤ ያቀርባል፡፡ ይሁንእንጂ ይህ ተቀባይነት የሚኖረው፣ አማጺው በነፍስወከፍ ጠመንጃ ታጥቆ የወጣ እንደሁ ነው፤ ይህ ከሆነ ጉዳዩ ጦርነት ሆኗል ማለት ነውና ከፖሊስም በላይ የጦር ሰራዊት ሊገባበት ይችላል፡፡ ነገር ግን ተቃዋሚው ዱላና ድንጋይ ይዞ ቢወጣም እንኳን፣ በድንጋይና በዱላ ንብረት ቢያወድም፣ ፖሊስ ላይ ጥቃት ቢሰነዝር እንኳን፣ ጥይት ተኩሶ መግደል ተገቢ አይደለም፡፡ ፖሊስ ህዝብ ጠባቂ ነው፤ ህዝቡን የሚጠብቀው ደግሞ ከሌባና ከቀማኛ ብቻ ሳይሆን፣ ከህዝቡና ከራሱ ከፖሊሱ ጭምር ነው፡፡ ፖሊስ መኪና አቃጠልክ፣ መስታወት ሰበርክ ብሎ ህዝቡ ላይ የሚተኩስ ከሆነ፣ ህዝቡን ከራሱ ከህዝቡ አልጠበቀውም፡፡ ፖሊስ እኮ እኔን ከራሴም ሊጠብቀኝ ሀላፊነት አለበት፤ ለዚህ ነው እራሱን ሊያጠፋ የተዘጋጀን ሰው ፖሊስ መረጃ ካለው፣ ሊያስጥለው ሀላፊነት ያለበት፡፡ ፖሊስ በድንጋይ ፈነከትከኝ ብሎ፣ ህዝብ ላይ የሚተኩስ ከሆነም ከራሱ ከፖሊስ አልጠበቀውም፡፡ ፖሊስነት በማንኛውም ሁኔታ ህዝብን የማስቀደም ታላቅ ሀላፊነት ነው፡፡ ይህ ሲሆን፣ ፖሊሶቻችንን ስለኛ ስለሚከፍሉት መስዋእትነት እንወዳቸዋለን፡፡ የምንወዳቸው ከሆነ ደግሞ ስለኛም ደህንነት ቢሆንም እንኳን እንዲጎዱ አንፈልግምና እንሳሳላቸዋለን፤ እንጠብቃቸዋለን፡፡ . . . እናም በመጨረሻ በምንም ሁኔታ ውስጥ እንዳንጎዳ ይጠብቁናል፤ እኛም እንዲሁ አንጠብቃቸዋለን፡፡
.
ኢህአዴግም ማድረግ ያለበት እንዲሁ ነው፡፡ ለሀያ አምስት አመታት ያስተዳደረው ህዝብ (ወጣትም ይሁን ጎልማሳ) ለተቃውሞ አደባባይ ሲወጣ፣ መጠየቅ ያለበት ራሱን ነው፡፡ ለሀያ አምስት አመታት ያስተዳደረው ህዝብ፤ መንገድ ሰራሁለት፣ ትምህርት አስፋፋሁለት፣ ድህነቱን ቀነስኩለት የሚለው ህዝብ፤ በግዳጅ ለጦርነት ከመማገድ አዳንኩት፣ በጥቃቅንና አነስተኛ አደራጅቼ ስራ ፈጠርኩለት የሚለው ወጣት፣ መንገድ ዘግቶ፣ ድንጋይ ወርውሮ፣ ለተቃውሞ ሲወጣ፣‹‹በአሸባሪዎችና በጸረሰላም ሀይሎች ስብከት ተደልሎና ተወናድዶ ነው›› የሚል ምክንያት ማቅረብ ውሀ አያነሳም፡፡ እና ኢህአዴግ ራሱን መጠየቅ አለበት! ከጫንቃው ላይ ደርግን ያህል ግፈኛ መንግስት ያስወገድኩለት ህዝብ፣ ያስተማርኩትና ስራ የፈጠርኩለት ወጣት፣ በቀናት የሽብርተኞች ስብከት ተደልሎ ለጥፋት ሊነሳ ይችላል? ከቻለስ ስለምን በአሸባሪዎች ከንቱ ስብከት ተቃወመኝ? እኔ ሬዲና ቴሌቪዥን ይዤ፣ እየተሸሎከለኩ የሚሰብኩ ሀይሎች፣ እንደምን ተሰሚነት አግኝተው አመጽ ሊነሳ ቻለ? ከእኔ ልማታዊ- ተግባር የእነሱን ሽብራዊ ስብከት ስለምን ተቀበለ? ወይስ ስራ እየፈጠርኩለት፣ ድህነቱን እየቀነስኩለት አልነበረም? . . .ወዘተ. የመሳሰሉ በርካታ ጥያቄዎች ለራሱ ማቅረብ አለበት፡፡
.
ይህ ካልሆነና፣ ኢህአዴግ ችግር በተፈጠረ ቁጥር፣ ተቃውሞ በተነሳ ቁጥር፣ ‹‹አሸባሪዎችንና ‹‹ጸረልማት ሀይሎችን›› ተጠያቂ የሚያደርግ ከሆነ፣ችግሩን ከስሩ አልመረመረምና ዘላቂ መፍትሄ ሊያገኝ አይችልም፡፡ ይልቁንም እንዲህ ያለው ራስን ነጻ ማውጣትና ሌሎችን ተጠያቂ ማድረግ፣ እብሪትን ስለሚያጸና ሀይልን ወደመጠቀም ይገፋፋል፡፡ ሰሞኑን በኦሮምያ ክልል በተፈጠረው ችግር የደረሰው የሞት አደጋም ሰበቡ ይኸው ነው፡፡ ኢሕአዴግ እውነት ‹‹ተቃውሞው የተቀሰቀሰው ከህዝቡ ወገን ባልሆኑ ሀይሎች ነው›› ብሎ የሚያምን ከሆነ፣ የተወናበደው ተቃዋሚ ላይ፣ ተወናብዶ እንጂ የእኔ ነው የሚለው ተቃዋሚ ላይ መተኮስ የለበትም፡፡ እዚህ ላይ ኢህአዴግ በተቃውሞ የሚደርሰውን የሰላም መቃወስና የንብረት መውደም የመከላከል ሀላፊነት እንዳለበት አልዘነጋሁም፡፡ ግን በምንም መንገድ የሰው ህይወት መጥፋት የለበትም፡፡ በየሀገሩ ከተሞችን ያነደደ ተቃውሞ ያለምንም ህይወት መጥፋት ሲያልፍ አይተናል፡፡ የፈረሰው ድልድይና ህንጻ መልሶ ሲገነባም አይተናል፤ የሞተ ሰው ግን ተቃውሞው አልፎ ሰላም ሲወርድ፣ ከመቃብር ሲነሳ አልተመለከትንም፡፡
.
አብዛኛውን ጊዜ ኢህአዴግ በተቃውሞ ወቅት የሚደርሱ የሞት አደጋዎችን ምክንያታዊ ለማድረግ፣ በፖሊስ አባላት ላይ የተፈጸሙ ጥቃቶችን እንደመግፍኤ ያቀርባል፡፡ ይሁንእንጂ ይህ ተቀባይነት የሚኖረው፣ አማጺው በነፍስወከፍ ጠመንጃ ታጥቆ የወጣ እንደሁ ነው፤ ይህ ከሆነ ጉዳዩ ጦርነት ሆኗል ማለት ነውና ከፖሊስም በላይ የጦር ሰራዊት ሊገባበት ይችላል፡፡ ነገር ግን ተቃዋሚው ዱላና ድንጋይ ይዞ ቢወጣም እንኳን፣ በድንጋይና በዱላ ንብረት ቢያወድም፣ ፖሊስ ላይ ጥቃት ቢሰነዝር እንኳን፣ ጥይት ተኩሶ መግደል ተገቢ አይደለም፡፡ ፖሊስ ህዝብ ጠባቂ ነው፤ ህዝቡን የሚጠብቀው ደግሞ ከሌባና ከቀማኛ ብቻ ሳይሆን፣ ከህዝቡና ከራሱ ከፖሊሱ ጭምር ነው፡፡ ፖሊስ መኪና አቃጠልክ፣ መስታወት ሰበርክ ብሎ ህዝቡ ላይ የሚተኩስ ከሆነ፣ ህዝቡን ከራሱ ከህዝቡ አልጠበቀውም፡፡ ፖሊስ እኮ እኔን ከራሴም ሊጠብቀኝ ሀላፊነት አለበት፤ ለዚህ ነው እራሱን ሊያጠፋ የተዘጋጀን ሰው ፖሊስ መረጃ ካለው፣ ሊያስጥለው ሀላፊነት ያለበት፡፡ ፖሊስ በድንጋይ ፈነከትከኝ ብሎ፣ ህዝብ ላይ የሚተኩስ ከሆነም ከራሱ ከፖሊስ አልጠበቀውም፡፡ ፖሊስነት በማንኛውም ሁኔታ ህዝብን የማስቀደም ታላቅ ሀላፊነት ነው፡፡ ይህ ሲሆን፣ ፖሊሶቻችንን ስለኛ ስለሚከፍሉት መስዋእትነት እንወዳቸዋለን፡፡ የምንወዳቸው ከሆነ ደግሞ ስለኛም ደህንነት ቢሆንም እንኳን እንዲጎዱ አንፈልግምና እንሳሳላቸዋለን፤ እንጠብቃቸዋለን፡፡ . . . እናም በመጨረሻ በምንም ሁኔታ ውስጥ እንዳንጎዳ ይጠብቁናል፤ እኛም እንዲሁ አንጠብቃቸዋለን፡፡
Friday, December 4, 2015
በእሳት በጋየው የጎንደሩ ግዙፍ ወህኒ ቤት ውስጥ በህወሓት ጦር የተጨፈጨፉት እስረኞች ማንነት በመታወቅ ላይ ነው
(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ) ህዳር 21 2008 ዓ.ም በጎንደር ከተማ በሚገኘው ግዙፍ ወህኒ ከባድ የእሳት ቃጠሎ መነሳቱን ተከትሎ የህወሓት ሰራዊት በርካታ እስረኞችን በግፍ መጨፍጨፉና ዙሪያውን በእሩምታ ተኩስ አጥሮ ማህሉንም ዳሩንም እሳት በእሳት በማድረግ መሽሎኪያ ቀዳዳ በማሳጣት ብዙዎቹን ማጋየቱ ይታወቃል፡፡
በመሆኑም በግፈኛውና ፋሽስቱ የህወሓት አገዛዝ ሰራዊት ከተጨፈጨፉት እስረኞች መካከል የተወሰኑት ማንነታቸው ተለይቶ በየትውልድ ቀዬዎቻቸው በመቀበር ላይ ናቸው፡፡
አቶ አለቤ ኃይሌ የተባሉትና ከመታሰራቸው በፊት በጥበቃ ስራ ይተዳደሩት የነበሩት ሰው ትናንት በወገራ ወረዳ ጉንትር ቀበሌ አቦ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስርዓተ ቀብራቸው ተፈፅሟ፡፡ በተጨማሪም የዚሁ ወገራ ወረዳ ጉንትር ቀበሌ ነዋሪ የሆነው የ17 ዓመቱ ታዳጊ መላክ ችሎት በወህኒ ቤቱ ውስጥ በጥይት ተደብድቦ ከባድ ጉዳት ደርሶበት በህክምና ላይ ይገኛል፡፡
ከአርበኞች ግንቦት 7 ጋር ግንኙነት አላችሁ ተብለው በቅርቡ በህወሓት ደህንነቶችና የታጠቁ ቡድኖች ታፍነው ከደልጊ ወደ ጎንደር ከተወሰዱት ከ10 በላይ ሰዎች መካከል እስካሁን አቶ አሰፋ ገዳሙ የተባሉት አዛውንት መገደላቸው ተረጋግጧል፡፡ በአርማጭሆ የሽመለ ጋራ ቀበሌ አስተዳዳሪ የነበረው ነውጥ ብቃለ የተባለው ግለሰብም መገደሉ ጭምር ታውቋል፡፡
አድራሻቸውና የአባታቸው ስም ገና በመጣራት ላይ ከሚገኙት እጅግ በርካታ የተጨፈጨፉ እስረኞች መካከል ደግሞ ቀናው፣ እሸቴ፣ ጤናው፣ ማስረሻ፣ አዱኛ… የተባሉት ይገኙበታል፡፡
ሽመልስ አቡሃይ የተባለው እስረኛ ያልነበረ ሰላማዊ ወጣት ደግሞ ትናንትና በተነሳው ግርግር በግፍ ተገድሎ ዛሬ በጎንደር ደብረ ብርሃን ስላሴ ቤተክርስቲያን ተቀብሯል፡፡
Saturday, November 28, 2015
ከመጠምጠም መማር ይቅደም | መስፍን ወልደ ማርያም [ፕሮፌሰር]
ኅዳር 2008 በፌስቡክ የምንሰባሰበው ለመወያየት፣ አንዱ ከሌላው እንዲማር፣ መረጃዎችን በነጻነት እንድንለዋወጥ፣ ይህንን ሁሉ በማድረግ ራሳችንን ለማሻሻል፣ የእኛ መሻሻል እየተራባና እየተባዛ የአገርና የሕዝብ መሻሻል እንዲሆን፣ ከተቻለንም ከአገራችንና ከሕዝባችን አልፈን የምንታይ የዓለም አካል እንድንሆን መስሎኝ ነበር፤ ሳየው በዚያ መንገድ ላይ ያለንና ፌስቡክን ለበጎ ዓላማ እየተጠቀምንበት ያለን አይመስለኝም፤ ስለዚህ ወይ መታረም፣ አለዚያም በፌስቢክ ጊዜ ማጥፋቱን መተው ምርጫ ሊሆንብን ነው፡፡ ምናልባት 99.99% በእኔ ሰፈር ያሉ የፌስቡክ ተሳታፊዎች ወደፌስቡክ የሚገቡት ለመናገር ነው፤ መናገር የህልውናቸው ምስክር ወይም ማረጋገጫ አድርገው የሚወስዱት ጥቂት አይደሉም፤ ካልተናገሩ የሌሉ ይመስላቸዋል፤ ዋናው ነገር መናገር ይሆንና የሚናገሩት ነገር ወይም ጉዳይ ሌላው ቀድሞ ከተናገረው ጋር የሚያያዝ (የሚቃወመው ወይም የሚደግፈው) ሳይሆን ፈጽሞ ወደተለየ ጉዳይ ውስጥ ገብቶ አዲስ ርእስ መክፈት የተለመደ ነው፤ የአብዛኛው ፍላጎት ማስተማር ወይም ማሳወቅ ነው፤ ማስተማር ወይም ማሳወቅ ቀላል ነው፤ መናገር የሚችል ወይም ፊደሉን አውቆ መጻፍ የሚችል ማስተማር ይችላል፡፡ የትምህርት ቤት ጓደኛዬ በጃንሆይ ዘመን ትልቅ ሚኒስትር ነበር፤ በደርግ ዘመን ለብዙ ዓመታት ታስሮ ሲወጣ ሥራ አልነበረውም፤ ችሎታውን ስለማውቅ በዩኒቨርሲቲ እንዲያስተምር አመቻቸሁለትና ማስተማር ጀመረ፤ ከጥቂት ወራት በኋላ ስንገናኝ ‹‹እኔ ማስተማር ቀላልና እረፍት የሞላበት ሥራ ይመስለኝ ነበር፤ ለካ አንቅልፍ የሚያሳጣ ነው! እዝናናለሁ ባልሁ ቁጥር አንድ ክፍል ሙሉ ተማሪዎች ተሰብስበው ዓይኖቻቸውን እያቁለጨለጩ ምን እንደማስተምራቸው ሲጠብቁ ይታዩኛል! እረፍት ይነሡኛል!›› አለኝ፤ ከአንድ ዓመት በኋላ ማስተማሩን ተወ፤ ኅሊና ላለው ሰው ማስተማር ቀልድ አይደለም፤ ያደክማል፤ ለማስተማር መማር ያስፈልጋል፤ ለማሳወቅ ማወቅ ያስፈልጋል፤ ከመማር ይልቅ ማስተማር፣ ለማወቅ ከመጣር ይልቅ ለማሳወቅ መጣር የሚቀልለው ሰው የእውቀት ሰው አይደለም፤ ሌላ ሥራ ቢመርጥ ይሻለዋል፡፡ ሳያውቁ ለማሳወቅ አደባባይ መውጣት ከችኮላ ወይም ከስንፍና፣ ከትዕቢት ወይም ከግዴለሽነት የሚመጣ ነገር ይመስለኛል፤ ውሎ አድሮ ይጎዳል እንጂ አይጠቅምም፤ በአደባባይ መናገር ወይም መጻፍ የመጨረሻው መጋለጥ ነው፤ በአደባባይ መናገርና መጻፍ በሕዝብ ፊት መጋለጥ መሆኑን ብዙ ሰዎች አያውቁም፤ በአንጻሩ ደግሞ ብዙ ሰዎች ይህንን መጋለጥ ፈርተውትና ሸሽተውት የሚርቁት አሉ፤ መጋለጥን ፈርተው ዓይኖቻቸውን ዘግተው፣ ጆሮዎቻቸውን ደፍነው፣ አፋቸውን ለምግብና ለመጠጥ በቀር የማይጠቀሙበት፣ ዝምታ ወርቅ ነው እያሉ ወርቅ የሚሸምቱበት ብዙ ናቸው፤ ከሕዝብ ጋር እየተጓዙ፣ በሕዝብ መሀል እየኖሩ የሕዝብ ጉዳይ (ፖሊቲካ) አይመለከተንም የሚሉ የማሰብ ችሎታቸውን ህልውና ይጠራጠሩ፤ የማሰብ ችሎታ ከሌለ የማወቅ አምሮት ወይም ምኞት የሚኖር አይመስለኝም፤ የማወቅ አምሮት በሌለበት የማሳወቅ አምሮት ጎልቶ ሲወጣና ሲደናበር ማየት በጣም የተለመደ እየሆነ ነው፤ ፌስቡክ የሚባለው መድረክ የመደናበሪያ መድረክ እየሆነ ነው፡፡ የማሰብ ችሎታው የሌላቸው ሰዎች ከሁለት አንዱን መንገድ በመምረጥ፣ ወይም በሁለቱም መንገዶች በመጠቀም ይሳተፋሉ፡– የማያውቁትን ለማሳወቅ በመሞከርና በዘለፋ! የማያውቁትን ለማሳወቅ መሞከርና ዘለፋ የባሕርይ ግንኙነት አላቸው፤ አሁን እዚያ ውስጥ አንገባም፤ በተለያዩ መስኮች፣ በተለያዩ ጉዳዮች፣ በተለያዩ የእውቀት ጥበቦች በሚያሰራጩት ፍንጥቅጣቂ በአእምሮና በመንፈስ ለመበልጸግ በመጣር ፈንታ በአጉል ትዕቢትና ፉክክር፣ በማይጠቅም ዘለፋና ማስፈራራት የፌስቡክን መድረክ ማበላሸትና ማርከስ ወደኋላ ይጎትተናል እንጂ ወደፊት አያራምደንም፡፡ መሠረታዊ የማሰብ መነሳችን ሳንገነዘብ የማሰብ ትርምስምስ ውስጥ እንገባና መውጣት ያቅተናል፤ ለምሳሌ በእውቀትና በእውነት መሀከል ያለውን ልዩነት ሳንገነዘብ እምነትን ስንሞግት የራሳችንንም ሆነ የሌላውን ጊዜ እናጠፋለን፤ እውቀትን በሙግት ለማጣራት ሲመጡብን ደግሞ ቶሎ ወደእምነት እንዞራለን፤ አጉል መሽከርከር ውስጥ እንገባለን፤ እንዲያው በሆነ ባልሆነው፣ ባወቅነውም ሆነ ባላወቅነው የመጣልንን ሁሉ መዘርገፍ አዋቂ አያሰኝም፤ ጎበዝ አያሰኝም፤ ብልህ አያሰኝም፤ ግን ባለጌ ያሰኛል፤ ባለጌ ነጻነትን አያውቅም፤ ለባለጌ ስድነት ነጻነት ይመስለዋል፤ ነጻነት ባለቤቱ ያጠረው ገደብ ወይም ወሰን አለው፡፡ፕሮፓጋንዳው ስብዓዊነት ይኑረው!!! ሰው እየሞተ ነው!! ቁጥሩን ቤቱ ይቁጠረው!!! ግርማ ሰይፉ -
በሀገራችን ያለው ድርቅ ክብደት ከ1977ጋር የሚመሳሰል እንደሆነ የመንግሰት ሹም ከሸገር ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ምልልስ አረጋግጠዋል፡፡ ልዩነቱ ግን አሁን መንግሰት ይህን ለመቋቋም የሚያስችል አቅም አለን የሚልው ጉዳይ ነው፡፡ ይህ አቅም ግን መሬት ላይ ወርዶ ስናየ ወኔ ብቻ ይመስላል፡፡ ከፕሮፓጋንዳ ያለፈ የፈረንጆቹን ደጅ እንዳይጠኑ የሚያደርጋቸው አይደለም፡፡“ደርግ” በ1977 የነበረፈውን ድርቅ ለዓለም ይፋ አድርጎ የነበረ ሲሆን የዚያን ጊዜ በነበረው ቀዝቃዛ ጦርነት መነሻ በሁለቱ ጎራ በሚደረገው ፍልሚያ ግዳይ የሚጣልብት ወቅት ነበር፡፡ ደርግ ለዓለም ህብረተሰብ ጥሪ ባቀረበበት ወቅት የሶሻሊስቱ ተከታይ በመሆኑ ይህ ጎራ ይህን ድጋፍ የሚያደርግበት አቅም የሌለው ሲሆን ይህን ለማድረግ አቅም ያላቸው ምዕራባዊያን ግን ውጤቱን በደንብ ሳናየው ድጋፍ ላለመስጠት መቁረጣቸው ለችግሩ ክብደት አንዱ እንደ ነበር ለመረዳት ሊቅ መሆን አያስፈልግም፡፡ በተጨማሪ ለ1997 ድርቅ ተገቢው ምላሽ በምዕራባዊያን እንዳይሰጥ በወቅቱ በትጥቅ ትግል ላይ የነበሩት በተለይ ህወሃት እና ሻቢያ የተጫወቱት ሚና ቀላል የማይባል ብቻ ሳይሆን አሁን ላይ ሆነን ስናየው ሰብዓዊነትን ለፖለቲካ ጥቅም እንዳዋሉት ፀሐይ የሞቀው ሀቅ ነው፡፡
አሁን ባለው ሁኔታ የኢህአዴግ መንግሰት ከምዕራባዊያኑ ጋር ያለው ቅርበት ከደርግ እንደሚሻል ስለሚታመን በተጨማሪ ህውሃትና ሻቢያ በዛን ጊዜ የሰሩትን ዓይነት ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት ለመስራት የሚችል ታጣቂ ሀይል ባለመኖሩ ችግሩን ለመቋቋም በተሻለ ሁኔታ ላይ ይገኛል፡፡ መንግሰት አቅሙ የከብቶቹን ህይወት ለመታደግ ለምን አልተጠቀመበትም? ካልቻለ ደግሞ ምዕራባዊያኑ ድጋፍ ለማድረግ ከፈለጉ አሁንስ ቢሆን ከብቶቹ ሳይሞቱ እንዲደርሱልን ለምን አልተደረገም? የሚለው ጥያቄ ለማንሳት አርብቶ አድር መሆን አይጠበቅብንም፡፡
ሁሉም የሚረዳው አንድ ሀገር በድርቅ መቼም ቢሆን ሊጋለጥ ይችላል፡፡ ይህ በዓለም ላይ ተደጋጋሚ ክስተት እንደሆነ ማንም ያውቃል፡፡ ድርቅ ሲኖር ግን ይህን ድርቅ የሌላ ሶሰተኛ ሀገር ድጋፍ ሳይጠየቅ ለመፍታት አቅም መፍጠር መቻል ነው፡፡ ኢትዮጵያ አሁን ባላት ስነ ምህዳር ከዚህ የተሻለ ማድረግ እና ለሌሎች መትረፍ ይገባት ነበር፡፡ ይህ ደግሞ አሰማት ሳይሆን ሊተገበር የሚችል የሀገር ሉዓላዊነት መገለጫ ነው ብሎ የሚያምን መንግሰት ያስፈልጋል፡፡ ኤክስፖርት የሚደረግ ታንክ ሰራን በፍፁም በዚህ ወቅት ሊያኮራን የሚችል ስ አይደለም፡፡ አሁን የምንረዳው መንግሰት ችግሩን ሪፖርት አድርጊያለሁ ማለትን እንደመውጫ ቀዳዳ እየተጠቀመበት መሆኑን ነው፡፡
Thursday, November 5, 2015
ኢትዮጵያ የኢንተርኔት ነጻነት የሌለባት አገር ተብላለች – VOA
ጽዮን ግርማ / VOA
ፍሪደም ሃውስ (Freedom House) መቀመጫውን እዚህ ዋሽንግተን ዲሲ ያደረገና በመናገር ነጻነት ላይ የሚሠራ ዓለም አቀፍ ተቋም ነው፡፡ይህ ተቋም መንግሥታት ለሕዝቦቻቸው የሚሠጡትን የኢንተርኔት ነጻነት አጥንቶ እያንዳንዱ ሀገር ያለበትን ደረጃ ‹‹Freedom on the net 2015 ›› በሚል ርዕስ ስር ሪፖርት አውጥቷል፡፡ በዚህ ሪፖርት ሰንጠረዥ‹‹ኢትዮጵያ ከቻይና፣ከሦሪያ እና ከኢራቅ ቀጥሎ ምንም ዓይነት የኢንተርኔት ነጻነት የሌለባት አገር ተብላለች፡፡
ዋሽንግተን ዲሲ—
ፍሪደም ሃውስ(Freedom House) የተሰኘው ተቋም “Freedom on the net 2015” የተሰኘው ይህ ሪፖርት በዛሬው ዕለት በቀረበበት ወቅት፤ሪፖርቱን ያዘጋጁት ባለሞያዎች፣የዩኒቨርስቲ መምሕራንንና ተመራማሪዎች፣የጎግል መስሪያ ቤት ባለሞያ፣ከመናገር እና ከመጻፍ ነጻነት ጋር የሚሠሩ ተቋማት ተወካዮች በአጠቃላይ ከሰብዓዊ መብት ጋር የሚሠሩ ግለሰቦችና የድርጅት ተወካዮች ተገኝተው ሪፖርቱን አዳምጠዋል፡፡ ተወያይተዋል፡፡
ማንኛውም ሰው የኢንተርኔት የመረጃ መረብን ተጠቅሞ ያለምንም ቅድመ ምርመራ እና ችግር ሐሳቡን በነጻነት የማስተላለፍ መብት እንዳለው የሚጠቅሰው ይህ ሪፖርት በአሁኑ ወቅት ግን መንግሥታት የሕዝቦቻቸውን የኢንተርኔት ነጻነት እያፈኑ፣አገልግሎቱንም እየዘጉ ከዛ ባለፈ ደግሞ እያሠሩ እንደሚገኙ ይጠቅሳል፡፡
voa amharic
አገራት ለሕዝቦቻቸው የሚሰጡትን ነጻነት በሦስት ቀለማት ከፍሎ ያስቀመጠው የሪፖርቱ አንድ አካል የኾነው አንድ ሠንጠረዥ ኢትዮጵያ ከቻይና፣ከሦሪያ እና ከኢራቅ ቀጥሎ “የባሰ አፈና” ባለባቸው አገራት ዝርዝር ውስጥ ያስቀምጣታል፡፡ በሌላኛው የሪፖርቱ ክፍል ደግሞ “ኢትዮጵያ የኢንተርኔትም ኾነ የመናገርና መጻፍ ነጻነት ያለባት አገር አይደለችም” ይላታል፡፡

Friday, October 9, 2015
ዘራፊው ሕወሓት ቁልፍ ቦታዎችን በመያዝ ውሳኔ ሰጪ ያልሆኑ ወንበሮችን ለአሽከሮቹ አድሏል
☞ ሃይለማርያም ከኒውዮርክ መልስ ሁለት ቀን ከመኖሪያቸው እንዳይወጡ ከሰው እንዳይገናኙ ተደርገዋል።…
☞ ጥያቄ የሚያበዙት አቶ አለማየሁ ተገኑ እና አቶ ሶፊያን አህመድ ከአሽከርነት ቦታቸው ተነስተዋል።…
☞ ትግላችን ላይ በማተኮር ሕወሓትን ከነአሽከሮቹ ልናጠፋቸው ይገባል።
.
የሕወሓት አሻንጉሊት የሆነው ሃይለማርያም ደሳለኝ በትናንትናው እለት ባቀረበው የቸብ ቸብ ካቢኔ መሰረት ሕወሓት የጦር ሃይሉን የውጪ ጉዳዩን የደህንነቱን የኮሚኒኬሽን እና አስፈላጊ ቁልፍ ጉዳዮችን በመቆጣጠር ውሳኔ ሰጪ የማይባሉ ተራ ቦታዎችን ለአሽከሮቹ በማደል የተዋቀረ ሲሆን አለማየሁ ተገኑ እና ሶፍያን አህመድ ምን እንደዋጣቸው አይታወቅም። ከኒውዮርክ ስብሰባ መልስ ሁለት ቀን ከመኖሪያ ቤቱ እንዳይወጣ እና ከሰው እንዳይገናኝ የታገደው ሃይለማርያም ደሳለኝ ራሱን ፈልጎ አለማግኘቱ እና በአሽከርነት መኖሩን ቤተሰቦቹን እያበሳጨ መሆኑ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ይናገራሉ። ቁልፍ የሆኑ ስልጣኖቹን የተቆጣጠረው እና በዘመድ አዝማድ ተሞልቶ በከፍተኛ የሃገር እና ሕዝብ ሃብት ዘረፋ ላይ የተሰማራው ሕወሓት ባለፈው የኢሕአዲግ ስብሰባ ወቅት አንዳንድ አመራሮቹ ያነሱትን ጥያቄ ተከትሎ ከስልጣን እንደሚባረሩ ሲነገር ነበር።
.
የወያኔና አሽከሮቹ ሹመት እንደሚከተለው ነው:-
አቶ ደመቀ መኮንን – ም/ጠቅላይ ሚኒስትር እና የማህበራዊ ዘርፍ ክላስተር አስተባባሪ
ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል –በም/ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር
ወይዘሮ አስቴር ማሞ – በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የመልካም አስተዳደር ክላስተር አስተባባሪ እና የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስትር
አቶ ሲራጅ ፈጌሳ – የመከላከያ ሚኒስትር
ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም – የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
አቶ ካሳ ተክለብርሃን – የፌደራል ጉዳዮችና አርብቶ አደር አካባቢ ልማት ሚኒስትር
አቶ ጌታቸው አምባዬ – የፍትህ ሚኒስትር
አቶ አብዱላዚዝ መሀመድ – የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር
አቶ ተፈራ ደርበው – የእርሻ እና የተፈጥሮ ሀብት ልማት ሚኒስትር
አቶ ስለሺ ጌታሁን – የእንሰሳትና የዓሳ ሀብት ልማት ሚኒስትር
አቶ አህመድ አብተው – የኢንዱስትሪ ሚኒስትር
አቶ ያዕቆብ ያላ – የንግድ ሚኒስትር
አቶ አብይ አህመድ – የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር
አቶ ወርቅነህ ገበየሁ – የትራንስፖርት ሚኒስትር
አቶ መኩሪያ ሀይሌ – የከተማ ልማት እና ቤቶች ሚኒስትር
ዶክተር አምባቸው መኮንን – የኮንስትራክሽን ሚኒስትር
አቶ ሞቱማ መቃሳ – የውሃ፣ መስኖ እና ኤሌክትሪክ ሚኒስትር
አቶ ሽፈራው ሽጉጤ – የትምህርት ሚኒስትር
አቶ ቶሎሳ ሻጊ – የማዕድን፣ የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስትር
ዶክተር ከሰተብርሀን አድማሱ – የጤና ጥበቃ ሚኒስትር
አቶ አብዱልፈታህ አብዱላሂ – የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር
ኢንጂነር አይሻ መሀመድ – የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር
ወይዘሮ ዘነቡ ታደሰ -የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ሚኒስትር
ዶክተር ሽፈራው ተክለማርያም – የአካባቢ ደን ልማት እና የአየር ንብረት ለውጥ ሚኒስትር
አቶ ሬድዋን ሁሴን – የወጣቶች እና ስፖርት ሚኒስትር
ወይዘሮ ደሚቱ ሀምቢሳ – የመንግስት የልማት ድርጅቶች ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል።
አቶ በከር ሻሌ – የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬከተር
አቶ ጌታቸው ረዳ – የመንግስት ኮሙዩንኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሀላፊ ሚኒስትር
አቶ አስመላሽ ወልደስላሴ – የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር
ዶክተር ይናገር ደሴ – የብሄራዊ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር
.
ትግላችን ላይ በማተኮር ሕወሓትን ከነአሽከሮቹ ልናጠፋቸው ይገባል። በአንድነት በመቆም ሃገራችንን ከጅቦች እናድናለን!!
.
ምንሊክ ሳልሳዊ
የተቸካዮች ምክር ቤት – (በበውቀቱ ስዩም)
ትምርት በጨረስን ማግስት እኔና ፍቅር ይልቃል ፈረንሳይ ለጋስዮን ኣካባቢ በዘጠና ብር ቤት መሰል ነገር ተከራይተን እንኖር ነበር፡፡ በየሳምንቱ ቅዳሜ ወደ ቪድዮ ቤት ጎራ እንላለን ፤ እነኩማር በዜማቸው ወፍ ሲያረግፉ ፤ እነ ቫንዳም በጫማ ጥፍያቸው ጥርስ ሲያረግፉ በመመልከት ራሳችን ዘና ለማረግ እንሞክራለን፡፡ ፊልም ዛሬ እንዲህ ጥንቡን ሊጥል ያኔ በጣም ብርቅ ነበር፡፡ ፊልም ሰሪዎች እንኳ እኛ ፊልም ለማየት የምንከፍለውን ያክል መስዋእትነት የሚከፍሉ ኣይመስለኝም፡፡ ያኔ ፊልም ማየት የጫማና የግስላ ሲጃራ ድብልቅ ሽታ የመቻል ቁርጠኝነት ይጠይቃል ፡፡ እናም በጊዜው የሁለት ሰኣት ፊልም ኣይተን የሁለት ሳምንት ጉንፋን ተረክበን ለመውጣት እንገደድ ነበር፡፡ኣሁን ሳስበው፤ ከፊልሙ በላይ የፈረንሳይ ልጆች በፊልሙ ላይ ተመስርተው የሚሰጡት ኣስተያየት ያዝናናኝ ነበር፡፡ ኣንድ ቀን በጣም እጅ እጅ የሚል ፊልም ስናይ “ፓርላማውን ቀይርልን ፓርላማውን ቀይርልን ”ብለው ቀወጡት፡፡ ኣሰልቺ ፊልሞች” ፓርላማ “ተብሎ እንደሚጠሩ ያወኩት ያኔ ነው፡፡ ባለቪድዮ ቤቱም ኣብላጫውን ድምጽ ኣይቶ ሌላ ፊልም እንዲቀየር ውሳኔ ኣስተለለፈ፡፡
የተወሰኑ የተቃዋሚ ድምጾች በሚሰሙበት ሰሞን እንዳሰልቺ ፊልም ይታይ የነበረው ፓርላማ ዛሬ ይሄ ኣይነቱ ኣጠራር እንኳ የሚበዛበት ይመስለኛል፡፡ እኔን የሚገርመኝ የተወካዮች ምክር-ቤት የሚለውን ስም እስካሁን ይዞ መቆየቱ ነው፡፡ የሚወከልም ሆነ የሚማከር በሌለበት ይሄን ስም መሸከም ኣይከብድም? እንዲያው ቤቱ ስሙ ከብዶት ኣለመፍረሱ ይገርማል፡፡
ያገራችን ፓርላማ ኋላቀር መሆኑን ብዙዎቻችን እናውቃለን፡፡ ግን ከመቶ ኣመት በፊት ከነበረው የምክክር ባህል ኣንጻር ሲወዳደር እንኳ እጅግ ኋላቀር መሆኑን ስንቶቻችን እናውቃለን??
“ብራናው ይገለጥ ተዘርግቶ በኣትሮኖሱ ላይ”::
1
በጅሮንድ ተክለሃዋርያት ተክለማርያም ባድዋ ጦርነት ዋዜማ ስለነበረው ምክር ያይን እማኝ ሆነው የተመለከቱትን ጽፈውልናል፡፡ልቀንጨበው፤
“ራስ(መኮንን)…መኳንንታቸውን ሰብስበው የጦር ምክር ተደረገ፡፡ ራስ ኣሉላም ምክሩ ላይ ነበሩ፡፡
ሌሊት ሲነጋጋ ሸለቆ ለሸለቆ ወርደን እግንቡ ስር ተጠግተን በመሰላል እየተንጠላጠልን ከምሽጉ ውስጥ ገብተን(ጠላትን) እንፍጀው መንገዱን የራስ ኣሉላ ሰዎች ይመሩናል ተባለና ተቆረጠ፡፡ ይህንን ምክር መኳንንቱም የጦር ኣለቆችም ባለሟሎቹም ወደዱት፡፡ ኣንድ ሰው ብቻ በማእረጉ ዝቅተኛ የሆነ(የደራሲው ወንድም ኣብዩ)እየተቃወመ ተናገረ፡፡
ይህ ምክር ትልቅ ጉዳት ያመጣል ሰራዊታችንም በከንቱ ያልቃል ይልቅስ ታግሰን ቀንና ሌሊት ዘብ እየጠበቅን ውሃ ከምሽጉ ውጭ መቅዳት እንዳይችል እናድርግ …”ብሎ ተናገረ፡፡
ቀኛዝማች በሻህ ያብዩን ነገር ክፍኛ ነቀፉት…”ኣንተ ወረቀት ሲጻፍ ትመክራለህ ፡፡ፈርተህ እንደሆነ እሰፈር ዋል ፡፡ እኛ በሾተል እየቀነጠስን እንደኣይጥ እንፈጀዋለን ኣሉ….“
…ኣብዩ ከምንም ኣልቆጠራቸውም ፡፡ በትእግስት መለሰላቸው፡፡”ሰራዊታችን በከንቱ እንዲያልቅ በመደረጉ ኣዝናለሁ፡፡ እናንተ ስትሞቱ እኔ የቀረሁ እንደሁ ያን ጊዜ ፈሪ ተብየ እሰደባለሁ፡፡ “ይህ ተናገረና ወጣ፡፡”
(ኦቶባዮግራፊ፤ ገጽ 60)
የምክሩ ውሳኔ ምንም ይሁን ሰዎች በትልልቅ ኣገራዊ ጉዳዮች ላይ ተሰብስበው ይሟገቱ እንደነበር እንረዳለን ፡፡ በምክሩ ላይ የተለያየ ማእረግ ያላቸው ብቻ ሳይሆን የተለያየ ኣመለካከት ያላቸው ሰዎች ተሳትፈዋል፡፡ በምክክሩ ኣብላጫውን ውሳኔ መቃወም ብቻ ሳይሆን ስብሰባ ረግጦ መውጣትም ይታወቅ ነበር ማለት ነው(ይህን ተናገረና ወጣ“ ተብሎ የተጻፈለትን ኣብዩን ኣስታውሱ )
2
ፕላውደን የተባለ የንግሊዝ ተጓዥ፤ በዘመነ መሳፍንት ማብቂያ በጉድሩ(ወለጋ)የተመለከተውን የሪፐብሊክ ኣስተዳደር እያደነቀ ሲጽፍ እንዲህ ብሏል፡፡
•”ከሌሎች ጎሳዎች ጋር ስለሚኖረው ጉዳይ የሚወሰነው በጉባኤ ነው፡፡ ባደባባዩ ጉባኤ ለመታደም የሚፈልግ ሰው ሁሉ ክብ ሰርቶ ጦሩን ተደግፎ ከብቦ ቆሞ ይመለከታል፡ ፡ ሽማግሌዎች በሚያስደንቅ መንገድ ተራቸውን እየጠበቁ በሰላምና በጦርነት ዙርያ ይከራከራሉ።“
በራስ መኮንን የሸማ ድንኳን ውስጥ እና በጉድሩ መስክ ላይ የታየው ክርክርና ሙግት ፤ በዛሬው ፓርላማ ውስጥ ይታያል?ያለፈውን ስርኣት የመናፈቅ መብት በህገ መንግስቱ ይካተትልንማ!
ዲሞክራሲ ሂደት ነው ይባልልኛል፡፡ ሊሆን ይችላል፡፡ ባገሬ ግን እንኳን ሲሄድ ሲንፏቀቅ ኣይታየኝም፡ ፡ የሚሄድ ቢሆን ኖሮ ከቀደምቶቻችን ውጥን ላይ ተነስቶ ዛሬ ትልቅ ደረጃ ደርሶ እናየው ነበር፡፡ የሚታየኝ ወንበር ላይ ተቸክሎ በድሃ እንባ የተቦካ እንጀራ የሚበላ ሰው ብቻ ነው፡፡ የተወሰኑ ሰዎች ሳይወጡ ሳይወርዱ ቀኝ እጃቸውን ብቻ እያወጡ እያወረዱ እንጀራ የሚበሉበት ቤት፤ “ የተወካዮች ምክር” ቤት መባሉ ያስቃል፡፡ ምናልባት” የተቸካዮች ምክር ቤት “ የሚለው ስም ይመጥነው ይሆን?
Thursday, October 1, 2015
ከአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ (ሞላ አስገዶምን አስመልክቶ) -
በኢትዮጵያ የቅርብ ጊዜ የፖለቲካ ትግል ታሪክ ውስጥ ባጠቃላይና በተለይ ደግሞ ህወሓት/ኢህአዴግ የፖለቲካ ስልጣኑን በተቆጣጠረባቸው ባለፉት ሁለት አስርት አመታት ውስጥ ህወሓት/ኢህአዴግን እንቃወማለን በሚለው ወገን ገንነው የመጡ ሁለት አፍራሽና ኋላቀር የፖለቲካ አዝማሚያዎች (trends ) አሉ። ከነኝህ ውስጥ አንደኛው ራስን በፖለቲካ አመለካከት ዙሪያ ከማሰባሰብ ይልቅ በጎጥና በዘውግ ደረጃ የመመልከትና ሀገራዊ ፖለቲካን በደም ቆጠራ የመመንዘር አባዜ ነው። ሁለተኛውና ከዚሁ ያልተናነሰው ችግር የፖለቲካ ድርጅት በመሰረታዊ ያመለካከት መርሆች ዙሪያ ሰፋ ያለ የማህበረሰብ ክፍልን የማሰባሰቢያ ድንኳን መሆኑ ቀርቶ፤ በስራ ሳይሆን ድንገተኛ አጋጣሚን በመጠበቅ ትርፍ ለማጋበስ በሚቋምጡ ሰነፍ “ነጋዴዎች“ የተቋቋሙ ሩቅ የማይሄዱ የንግድ ድርጅቶች ይመስልበ ተግባር ምንም የማይፈይዱ ”የፖለቲካ ድርጅቶች“ እንደ አሸን የመፍላታቸው ፈሊጥ ነው። እነኝህ ሁለቱም አዝማሚያዎች የህወሓት/ኢህአዴግን ህይወት ከማራዘም አልፈዉ ማህበረሰቡን ወደሚመኘው እውነተኛ የዴሞክራሲያዊ ስርዓት አንድ ጋት እንኳን ፈቀቅ አላደረጉትም። ይልቁንም ዴሞክራሲን የሚናፍቁ ታጋዮች ተሰባስበውና ተጠናክረው ስርዓቱን ከመግፋት ይልቅ በግለሰብ ደረጃ ወይንም በትናንሽ ቡድኖች በመሰባሰብ የሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች በስርዓቱ በቀላሉ እየተመቱ ብዙ ታጋዮች ለሞት፤ ለስቃይና ለእስር ተዳርገዋል። አሁንም እየተዳረጉ ነው።
የዚህ አይነት የትግል አካሄድ ሩቅ እንደማያስኬድ የኢትዮጵያ ህዝብ ከተገነዘበው ቆይቷል። ይህ አካሄድ እንዲቀየርና የፖለቲካ ሀይሎች ተሰባስበው ይህንን በስልጣን ላይ ከሚገባው በላይ የቆየና አገሪቱን ለውርደት የዳረገ የጥቂት ዘራፊዎች ቡድን ከጫንቃው ላይ እንዲያነሱለት ሲማጠን ቆይቷል።ምንም እንኳን በመሪዎች ድክመት የሚመኘውን ዳር መድረስ ባይችልም ባጭር ጊዜ ልምዱ በትንሹም ቢሆን የተባበረ ትግል ሊያስገኝ የሚችለውን ጥቅም በመጠኑም ቢሆን አይቶታል።
ይህ የህዝብ ፍላጎት መኖር ግን በራሱ ይህንን የተባበረ ሰፊ ማህበራዊ እንቅስቃሴ መፍጠርን ቀላል ያደርገዋል ማለት አይደለም። በብዙ ስራ፤ በብዙ ድካምና ያላሰለሰ ጥረት የሚፈጠር እልህ አስጨራሽ ሂደት ነው። ባንድ በኩል እንዲህ አይነት ሰፊ የህዝብ እንቅስቃሴ በስልጣኑ ለመቆየት የሚፈጥርበትን ችግር የሚረዳው በስልጣን ላይ ያለው የዘራፊዎች ቡድን ይህን እንቅስቃሴ ከወዲሁ ለማምከን ያለ የሌለ የገንዘብ፤ የስለላና የተንኮል ሀይሉን ይጠቀማል። በተቃዋሚ ድርጅቶች ውስጥ ሰርጎ በመግባትና ደካማ ሀይሎችን በገንዘብ በመግዛት ወይንም በማስፈራራት እንዲህ አይነት ትብብሮች እንዳይፈጠሩ ከውስጥ ለመቦርቦር ተግቶ ይሰራል። በሌላ በኩል ደግሞ የትም የማያደርሳቸውን “የራሳቸውን ድርጅት” የሙጢኝ ብለው ለትልቅና አገራዊ አላማ እራሳቸውን ላለማስገዛት የቆረጡ ደካማ “የድርጅት መሪዎች” እንዲህ አይነቱን የጋራ እንቅስቃሴ በራሳቸው ግብዝነትና ስግብግብነት ምክንያት ብቻ ሊያሰናክሉት መሞከራቸው አይቀርም።
ይህ ግን ጊዜው ያለፈበት አዝማሚያ ነውና የሚሳካ ሙከራ አይሆንም። የተናጠል ትግል ሂደት ማብቂያው ጊዜ ተቃርቧል። የኢትዮጵያ ህዝብም ሆነ ለእውነተኛ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ የሚታገሉ ኃይሎች እንዲህ አይነቱን ፋይዳ ቢስ ሂደት የመቀበል ትዕግስታቸው ተሟጧል። በቅርብ ጊዜ የሞላ አስገዶምን መክዳት በማስመልከት የትህዴን አመራር ባወጣው መግለጫ“ኢትዮጵያን እውነተኛ ዴሞክራሲያዊት ሀገር ለማድረግ ከሁሉም ኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ጋር አብሮ መስራት የድርጅታችን መሰረታዊ መርሆ ነው” እንዳለው ይህ መሰረታዊ መርሆ በሀገራችን የጸረ ህወሓት/ኢህአዴግ ትግል የበላይነት ይዞ እየመጣ ያለ እጅግ አስፈላጊና ለድሉም ወሳኝ የሆነ የጊዜው የፖለቲካ አዝማሚያ ነው። አርበኞች ግንቦት 7 ይህን መሰረታዊ መርሆ ከምር ወስዶ የሚንቀሳቀስ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ነው።
ይህአዲስ የፖለቲካ አዝማሚያ ምቾት የማይሰጣቸው የፖለቲካ ኃይሎች መኖራቸው የሚጠበቅ ነው። የህወሓት/ኢህአዴግ የስለላ ድርጅት ከሰሞኑ ሞላ አስገዶምን በማስመልከት ባወጣው መግለጫ በግልጽ እንዳስቀመጠው ኢትዮጵያውያን የዴሞክራሲ ኃይሎች ተሰባስበው እንዳይታገሉና ስርዓቱን እንዳይፈታተኑ የማያደርገው ጥረት የለም። በዚህ በህወሓት/ኢህአዴግ መሰሪ እንቅስቃሴ ደግሞ በቀላሉ መጠቀሚያ የሚሆኑት በጋራ የሚደረግ ትግል በግለሰብ ደረጃ ያሳጣናል ብለው የሚፈሩት “የግል ጎጆና” ጥቅም የሚያስጨነቃቸው ደካማ የፖለቲካ መሪዎች ነን ባዮችን ነው። ባንጻሩ በየድርጅቶቹ ውስጥ በሚገኙት ብዙሀኑ ሩቅ አሳቢ መሪዎች ጥረትና በተለይም ደግሞ ይህን ትግል ለአላማ እንጂ ለሌላ ምንም አይነት የግል ጥቅም ያልተቀላቀሉና በትግሉ ሂደትም ትልቁን ሚና በሚጫወቱት ብዙሀን ታጋዮች አልበገር ባይነት እንዲህ አይነት ደካማ መሪዎች ተከታይ በማጣት ሲዳከሙና በሚያደርጉት እንቅስቃሴ በድርጅታቸው ውስጥ የሚነሳባቸውን ተቃውሞ መቋቋም ባለመቻላቸው በቀላሉ እየተፍሸለሸሉ ከመራገፍ በስተቀር በድርጅቶቹ ላይ ከባድ ጉዳት ሳያደርሱ ይከስማሉ።
በህወሓት/ኢህአዴግ “የስለላ ድርጅት አቀናባሪነት” በሞላ አስገዶም መሪነት ከሰሞኑ የተሞከረው የማፍረስ ንቅናቄ ከሽፎ ወደ ተስፋ መቁረጥ የክህደት እንቅስቃሴ የተቀየረው የሰሞኑ ሙከራም የዚህ አጠቃላይ ሂደት አካል ነው። በዚህ የከሸፈ ሙከራ ውስጥ እጅግ የሚገርመውና የትህዴንን ብዙሀን አመራሮች ብስለት፤ የድርጅቱን መዋቅራዊና ድርጅታዊ ጥንካሬ፤ እንዲሁም ብዙሀኑ ታጋይ ለጋራ ትግል ያለውን ቆራጥ አቋም ያስመሰከረው፤ ይህንን የማፍረስ ሙከራ የመራውና ሳያሳካለት በመጨረሻም በጣም ጥቂት ተከታዮቹን ብቻ ይዞ የከዳው ለረጅም ጊዜ የድርጅቱ ሊቀመንበር የነበረው ሞላ አስገዶም መሆኑ ነው። እንዲህ አይነት የመክዳት ሂደት ባጭር ጊዜ በማህበረሰባችን ላይ የሚፈጥረውን አስጨናቂ ስሜት የምንረዳው ቢሆንም ከዚያ በላይ ልንረዳው የሚገባው ግን በእንዲህ አይነት ከፍተኛ ያመራር ቦታ የነበረ ሰው ሙከራ አለመሳካት በእርግጥም የሀገራችን ፖለቲካ እየበሰለ፤ ከግለሰብ አመራሮች ተጽእኖ እየተላቀቀ፤ አዲስ የተባብሮ መታገል አቅጣጫን እያበሰረ እየሄደ መሆኑንና በትናንሽ ሰዎች መግተርተር ይህ ሂደት የማይቀለበስ መሆኑን የሚያመለክት የረጅም ጊዜ ግኝት መሆኑን ነው።
አርበኞች ግንቦት 7 በዚህ አጋጣሚ ለትህዴን ብዙሀን አመራርና ለሰፊው ታጋይ በመርህ ላይ ለተመሰረተው አቋማቸውና መርሃቸውን ለማስጠበቅ ለሚያደርጉት ቆራጥ ትግል ያለውን ጓዳዊ አክብሮት ይገልጻል። በመግለጫቸው ላይ በግልጽ ያስቀመጡት መርሆአቸው የኛም መርሆ መሆኑን ስንገልጽላቸው በታላቅ ኩራት ነው። ድርጅታቸውን እያጸዱ የተመሰረቱበትን መርሆ ጠብቀው ለመጓዝ ባሳዩት ቁርጠኝነትና ወደፊትም በሚያደርጉት ትግል ምንጊዜም ከጎናቸው መሆናችንንና ጓዳዊ ድጋፋችን ምንጊዜም እንደማይለያቸው በዚህ አጋጣሚ ደግመን ልናረጋግጥላቸው እንወዳለን። በመግለጫቸው ላይ እንዳሉትም ይህ ትግል ኢትዮጵያን ዴሞክራሲያዊ ሳያደርግ የማይቆምና እንዲያውም ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና ለኢትዮጵያ ህዝብም በየጊዜው በሚፈጠሩ እንቅፋቶች ላይ ሳያተኩር ትግሉን በሙሉ ልብ እንዲደግፍ ያደረጉት ጥሪ የኛም ጥሪ ነው።
አንድነት ኃይል ነው!!!
አርበኞች ግንቦት 7: ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ
ህወሃት ጦርነት ጀመረ፣ ቁስለኞች ታይተዋል
በነጻ አውጪ ስም አገር እየገዛ ያለውን የትግራይ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃትን) ለመውጋት ብረት ያነሳው ሌላ የትግራይ ነጻ አውጪ ሃይል /ትህዴን ወይም በትግሪኛ ዴምህት/ መሪ የነበረው “ተጋዳላይ” ሞላ አስገዶም ህወሃትን ከተቀላቀለ ጥቂት ቀናት በኋላ ጦርነት መጀመሩ ተሰማ። የህወሃት ወኪል ሃይለማርያም ደሳለኝ ውጊያው የሚጀመረው የህዝብ ፈቃድ ተጠይቆ እንደሚሆን ተናግረው ነበር።
የጎልጉል መረጃ አቀባዮች ከአዲስ አበባ እንደገለጹት ጦር ኃይሎች ሆስፒታል ቁስለኞች እየገቡ መሆኑንን እማኞች ነግረዋቸዋል። ጦርነቱ በየትኛው መንደርና ወረዳ እንደተጀመረ ለይተው ያላስረዱት የዜናው ባለቤቶች፣ ውጊያ እየተካሄደ ያለው ኤርትራ ምድር ላይ እንደሆነ ግን አልሸሸጉም።
አንድ የሆስፒታል ሰራተኛ ዘመድ ደውሎላቸው “ቁሰለኞች አሉ ሥራ በዝቶብኛል” ማለታቸውን የጎልጉል መረጃ ሰጪዎች ከአዲሰ አበባ ገልጸዋል። ባለፈው ሳምንት በሁመራ አቅጣጫ የከባድ መሳሪያ ተኩስና ድብደባ መሰማቱን የተለያዩ ድረገጾች ዘግበው ነበር። ይህ ሁሉ ከመሆኑ በፊት ሻእቢያ “ህወሃት ሊወረኝ ነው” ሲል ክስ ማሰማቱ አይዘነጋም።
ኦምሃጀር በሚባለው ስፍራ የከረረ ውጊያ እየተካሄደ መሆኑን እንደሰሙ የገለጹ በውጊያው የትኛው ወገን ድል እንደተቀዳጀ ለጊዜው መናገር እንደማይቻል አመልክተዋል። ውጊያው ጠርዙን አስፍቶ እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል።
ከህወሃት በኩል ውጊያው ከሻዕቢያ ጋር እንደሆነ ቢገለጽም ከሌላ ወገን “ህወሃትን የወጋሁት እኔ ነኝ” ባይ ይህ ዜና እስከታተመ ድረስ አልተሰማም። የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ህወሃትን በነፍጥ አንበረክካለሁ በማለት ማወጁና አመራሮቹም ወደ ውጊያው አውድ ማምራታቸው ይታወቃል። ህወሃት ኤርትራን በአራት አቅጣጫ የመውጋት እቅድ እንዳለው ጎልጉል መዘገቡ የሚታወስ ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በርካታ የሰራዊቱ አባላት ከሰራዊቱ እየሸሹና እየተሰወሩ መሆናቸው ህወሃትን እንዳሳሰበው፣ ጦሩ የመዋጋት ፍላጎት ያጣል የሚል ሥጋት እንዳለ የሚጠቁሙ ክፍሎች “የአሁኑ የውጊያ አቅጣጫ በዚህ መልኩ እንዲሆን መደረጉ ይህንኑ ለመፈተንም ጭምር ነው” ብለዋል።
በሌላ ዜና በሶማሌ ያለው ሰራዊት የመመለስ ጥያቄ ማንሳቱና ሁለት ጄኔራሎች ጦሩን ለማወያየት ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ስፍራው አቅንተው እንደነበር ለማወቅ ተችሏል። ጦሩ መስዋዕትነት እየከፈለ በተደጋጋሚ የተቆጣጠረውን ቦታ እንዲለቅ ትዕዛዝ ሲቀበል መቆየቱ ሌላው የቅሬታው መነሻ ሲሆን በሶማሌ ያለው የሰላም አስከባሪ ሃይል ይህንኑ ነቅፎ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል። በህወሃት የሚመሩት የኢህአዴግ ባለስልጣናት በሶማሌ ስለተገደሉት ወገኖች መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆናቸው፣ ተቃዋሚ ፓርቲዎችም ይህንን አክርረው አለመጠየቃቸው፣ ላለፉት አምስት ዓመታት 99.6 በመቶ ህወሃት የነገሰበት ማኅበርም (ፓርላማ) ለይስሙላ እንኳን ጥያቄ አቅርቦ እንደማያውቅ በርካቶች የሚተቹበት አገራዊ ጉዳይ ነው።
Subscribe to:
Posts (Atom)
