ይድረስ ለክቡር ዶር ቴዎድሮስ አድሃኖም …
* ኢህአዴግን እንዴት እንምረጥ ?
* ኢህአዴግን እንዴት እንምረጥ ?
ትናንት በሁከት ፣ ዛሬ በመፈራረስ በሚመስል አደገኛ የለውጥ ሂደት ውስጥ ባለችው የመን የኢትዮጵያውያን የድረሱልኝ ድምጽ ከነኡኡታው ሰላም ይነሳል ። በደቡብ አፍሪካ በኢትዮጵያውያን ስደተኛ ወገኖቻችን ላይ ከኢራቅና ሶርያ አይ ኤስ አይ ኤስ ISIS ጽንፈኞች ባላነሰ ከፍ ሲል በሰብአዊው ዜጋ ፣ ዝቅ ሲል ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ በተለያዩ የውጭ ዜጎች ላይ የተጀመረው ጥቃት ሊያዩት ሊሰሙት ይከብዳል ። በሰላ ገጀራ ፣ ሰንጢ የሰው ፍጡር የመቆራረጥና ፣ በእሳት የማቃጠልን የአውሬ ተግባርን መመልከት ዘልቆ ልብን ይሰብራል ። ይህ ሁሉ ሲሆን ” መንግስት አለን !” ባዮች ኢትዮጵያውያን ፈጥኖ ደራሽ ቀርቶ ጉዳቱን አጥብቆ የተቃወመ መንግስት ባለማየታችን አዝነናል !

በማዲባ ምድር በደቡብ አፍሪካ በዜጎች ላይ እየተፈፀመ ያለውን አሰቃቂ ግፍ እንደ ዜጋ አሞኛል ። ድርጊቱን በአደባባይ የሚያወግዝልን መንግስት ማጣታችን አውጥቸ አውርጀ ለዜጎች መብት ማስጠበቅ ተግቶ የማላውቀው ኢህአዴግን ብመርጥ ሀገሬ ህዝቤ ምን እንደሚሆኑ ማሰቡ አልተሳነኝም ። …እናም መንግስትዎ የምመርጠው ደግሞ እንደ ዜጋ የስደተኛ መብታችን ስላስጠበቀልን እንጅ ግዑዙን መንገድ ስለሰራ ፣ ህንጻውን ስላቆመና ግድቡ ስለገደበልኝ መሆን አለበትን ? ስል ከራሴ የወጣ ፈታኝ ጥያቄ አንገላታኝ… እናም ትናንተም ሆነ ዛሬ ኢህአዴግ ለዜጎች መብት እስካልተጋ ድረስ እንዴት ኢህአዴግን እንምረጠው ? አልኩ ቢቸግረኝ …
የሆነው እና እየሆነ ያለው ቢያከፋኝና ፣ ቢያስጨንቅ ፣ ቢያስጠብበኝ ወቀሳ ቢጢ ልልክልዎ ነሸጠኝ … ! ብዕሩን በቀለም ነከሬና ወረቀቱን አቅርቤ የታወከው ውስጤ እርሙን ያወጣ ዘንድ እንደለመድኩት በማለዳ ወጌ ብሶቴን መተንፈሱን መረጥኩ … ንዴት ብስጭቴ አይሏልና ክብርዎን እንዳልነካ በመጠንቀቅ እራሴን አረጋግቸ ስሞታ ፣ ቅያሞቴን አሳምሬ በማውቀው የአረብ ሀገሩ ስደት በጨረፍታ ልጀምረው ፈቀድኩ … !
ከሁሉ በማስቀደም ከ20 ዓመታት ወዲህ ዘንድሮ ወግ ደርሶን ባለሙያ ወደ አካባቢው መላኩን ባልክድም ፣ ከዚህ ቀደም በአረብ ሃገራት በዜጎች መብት ጥበቃ የገጠመን የባለሙያ ተወካይና የመንግስት ትኩረት እጦት ፈተና ግን እንዲህ በአጭሩ የሚገለጽ አለመሆኑን ከጅመሩ አስረግጨ ልነግርዎ ደስ ይለኛል ! …ግን በአጭሩ ልሞክረው …

የእኛ እውነት የእናንተ ስህተት …
====================
====================
ክቡር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር …
እርስዎ የተኳቸው የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የአሁኑ የተከበሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ወደ ሳውዲ አረቢያ ለጉብኝት መጥተው የኮንትራት ስራ ኢትዮጵያውያንን ለመቀበል ሳውዲዎች ፍላጎት ማሳየታቸ ውን ለሳውዲ ታዋቂ ጋዜጦች መግለጫ ሰጥተው እንደ ሄዱ ያለምንም ቅድመ ዝግጅትና ጥናት የኮንትራት ስራውን ሲጀመር ከቀሩት ወገኖቸ ጋር በመሆን ህጋዊ የኮንትራት የሁለትዮሽ ውል ሳይደረግ ዜጎችን መላኩ አደጋ አለው በሚል የተቃውሞ ድምጻችን ስናሰማ የስምምነት ህጋዊ ውሉን መፈራረምና አማራጩ ቅድመ ዝግጅት ማድረግ ነው ብንልም ሰሚ አላገኘንም ። በአጭር ጊዜ ህጋዊ ውል በሌለው ስምምነት በኮንትራት ስራ ስም ዜጎች ይላኩ ጀመር ። ከጅምሩ እስከ አሁን ያለውን አሰቃቂ የእህቶቻችን የመከራ ዋይታ መስማት ጀመርን ። እርስዎ ወደ ስልጣን በመጡ ማግስት ያለምንም ጥናትና ቅድመ ዝግጅት የተጀመረውን በድርጊቱ ሁሉ ከታመሙት መካከል የምወዳት ሃገሬ እጓለማውታ ስደተኛ አንዱ እኔ ነኝ !

በደቡብ አፍሪካስ ለኢትዮጵያውያን የት አላችሁ?
==============================
ክቡር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶር ቴዎድሮስ…
==============================
ክቡር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶር ቴዎድሮስ…

ከአፖርታይድ የነጻነት እለህ አስጨራሽ ትግል በደ ገፍናት ፣ ለመሪዋ ለማንዴላ መሸሸጊያ ፣ ለታጋይ ፋኖዎቿ መጠጊያና ስንቅ ትጥቅ ያቀበለችው ሃገር ዜጎች በደቡብ አፍሪካ ዘረኛ ወሮበሎች ተደፍረናል ። በህግና በስርአት በምትመራ በምትባለው ስልጡን አፍሪካዊት ሀገር በደቡብ አፍሪካ ፣ በአለማችን የነጻነት ታጋይ በክቡር ኔልሰን ማን ዴላ ምድር ፣ ነጻነቷን ከወራሪ አስከብራ የኖረችው ሀገር የኢትዮጵያ ልጆች ግፍ ተፈጽሞብናል ። በዘር ጥላቻ የወገን ደም ረክሶ በሰላ ገጀራ አካላቸው ሲጎመድ ፣ ሲቃጠሉን ሲገደሉ እያያችሁ ዝምታን መምረጣችሁ እኔ በግል በመን ግስት ላይ ተስፋ እንድንቆርጥ አድርጎኛል ። አፋጣኝ የወ ገን አለኝታነትን አለማሳየታችሁ እኔን ብቻ ሳይሆን ሀገር ወዳዱን ደጋፊዎችዎን ሁሉ ማስቆጣቱን ማምሻውንበፌስ ቡክ በለቀ ቁት ብጣሽ መረጃ ስር የተጻፈውን የሰላ ሂስ ማንበቡ ብቻ በቂ ይመስለኛል ።
ክቡር ሚኒስትር ዶር ቴዎድሮስ በደቡብ አፍሪካ ዜጎ ቻችን ላይ አፋጣኝ እርምጃ አለመውሰዳችሁ በመስሪያ ቤትዎም ሆነ በመንግስት ተስፋ ያልቆረጥን የነበርንን ጥቂት ” ገለልተኛ ነን!” የምንል ወገኖችን ሞራል እንኳ አልጠበቃችሁትም ። ከእኛ አልፎ ድርጅትዎን ሲደግፉ ያው ግዑዙን መንገድ ፣ ህንጻውንና ግድቡን እያነሱ እየጣሉ “ተንፈላሰሳችሁበት ” የሚሉንን ዲሞክራሲና እድገቱን ከመጥቀስ ፈቀቅ የማይሉት ሳይቀር በስራችሁ አልተደሰቱም። የሚሰደደውን ህልቀ መሳፍርት ዜጋ ድህነት ፣ የኑሮ ውድነትና የአውራ ፖርቲ ፖለቲካ ትንኮሳ ምክንያት አስረግጠው ለማስረዳት በቂ ምክንያት የሚያጥራቸውን ከነፍሳቸው ጋር የታረቁ ደጋፊዎቻችሁን ተቀይመዋችኋል። እነሱን ለማጽናናት ሲባል ቢያንስ
” … የኢፌድሬ መንግስት ና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዜጎቹ የሚፈጸመውን አሰቃቂ በደል በመቃዎም የደቡብ አፍሪካን አንባሳደር በአስቸኳ ይ ጠርቶ አፋጣኝ እርምጃ እንዲዎስድ ማስጠንቀቂያ ሰጠ ! ይህ ካልሆነ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ግንኙነት እስከመቋረጥ የሚያደርስ እርምጃ እንደሚወስድ መንግስት ያወጣው መግለጫ አስታወቀ !”
ተብሎ በቴሌቪዥንና በራሳችሁ ራዲዮ መስማቱን ናፍ ቀነው የውሃ ሽታ ሆኖ ሳንሰማው ቀረን … እርስዎም ቢሆን መረጃው እንደ ደረሰዎ በትኩሱ በለመድነው ዘመነኛ መረ ጃ ቅበላዎ የረባ መረጃ ስላልሰጡን የለውጥ ተስፋ ያለን ሁሉ ምኞት ከንቱ መሆኑን አሳይቶ የማይጨበጠውን ተስፋ አጨናግፎታል !

እንደ ከሸፍን እንዳንቀር ፣ ከኢትዮጵያ መንግስት የምንጠብቀው …በጥሞና ይስሙኝ !
==========================
==========================
ክቡር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር …
ክቡርነትዎም ሆኑ የሚመለከታችሁ እንዲህ እንደ ተዋረድን ፣ እንደ ከሸፍን እንዳንቀር ፣ በደቡብ አፍሪካ የተፈጸመብንን ግፍ የሚመለከት ከእርስዎና ከኢትዮጵያ መንግስት የምንጠብቀው ከብዙ በጥቂቱ ሃሳቤ የሚከተለው ነውና በጥሞና ስሙኝ !
ክቡርነትዎም ሆኑ የሚመለከታችሁ እንዲህ እንደ ተዋረድን ፣ እንደ ከሸፍን እንዳንቀር ፣ በደቡብ አፍሪካ የተፈጸመብንን ግፍ የሚመለከት ከእርስዎና ከኢትዮጵያ መንግስት የምንጠብቀው ከብዙ በጥቂቱ ሃሳቤ የሚከተለው ነውና በጥሞና ስሙኝ !
1ኛ / የኢትዮጵያ መንግስት በደቡብ አፍሪካ እየተፈጸመባቸው ላለው ግፍና በደል ለድርድር እንደማይቀርብ በማስገንዘብ ለአለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን በአደባባይ ከዚያም አልፎ ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ጠንከር ያለ መግለጫ መስጠት አለበት ።
2ኛ / ለነጻነት ትግሉ ከፍተኛ ተጋድሎ ያደረገችው ሃገር የኢትዮጵያ ዜጎች በደቡብ አፍሪካ የተፈጸመባ ቸውን ግፍ ህዝብን ያስከፋ ያስቆጣ ድርጊት መሆኑን በሀገር ቤት መገናኛ ብዙሃን ሳይቀር በግልጽ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፎች እንዲደረጉ መፍቀድ ።
3ኛ / ተቀማጭነታቸው አዲስ አበባ ያደረጉትን የደቡብ አፍሪካ ፣ የአፍሪካ ህብረት ፣ የተባበሩት መንግስታትን ከፍተኛ ኃላፊዎች በመጥራት በዜጎቻችን ላይ የተፈጸመው በደል የሁለቱን ሃገር ግንኙነት እስከ ማቋረጥ የሚደርስ እርምጃ እንደሚያስከትል ከበድ ማስጠንቀቂያ መስጠት ።
4ኛ / በህግና ስርአት በፕሬዝደንት ጃኮብ ዙማ ትተዳደራለች በምትባለው የደቡብ አፍሪካ መንግስት ግፍ በዜጎቻችን መፈጸሙን በአጽንኦት ለማስረዳት በጠቅላይ ሚኒስትሩም ሆነ በእርስዎ የሚመራ ቡድን በአስቸኳይ ወደ ደቡብ አፍሪካ ሊሄድ ይገባል ።
5ኛ / ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ የሚፈልጉ ዜጎች ለጉዳታቸውና ለተዘረፉት ንብረት ካሳ መጠየቅ ።
6ኛ / ወደ ሀገር መመለስ ለሚፈልጉ ተመላሽ ዜጎች አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ ፣ ወደ ሶስተኛ ሀገር መሔድ ለሚፈልጉ መብታቸውን ማክበር ይገባል ።
በደቡብ አፍሪካ ያላችሁ ዜጎች ብርታቱነን ይሰጣችሁ !
የሞቱትን ነፍስ ይማር ከማለት ባለፈ መሄድም ሆነ ክብራች ን መመለስ ባይቻልም ፣ ሀገርና መንግስት አለን ለማለት አፋጣኝ እርምጃ ከመንግስትዎና ከመስሪያ ቤትዎ እንጠብቃለን !
የሞቱትን ነፍስ ይማር ከማለት ባለፈ መሄድም ሆነ ክብራች ን መመለስ ባይቻልም ፣ ሀገርና መንግስት አለን ለማለት አፋጣኝ እርምጃ ከመንግስትዎና ከመስሪያ ቤትዎ እንጠብቃለን !
ሀገር ማለት ህዝቡ ነው !
ከሰላምታ ጋር !
አክባሪዎ
ነቢዩ ሲራክ
ሚያዝያ 9 ቀን 2007 ዓም
ሚያዝያ 9 ቀን 2007 ዓም
No comments:
Post a Comment