Tuesday, August 9, 2016

አባይ ማዶ ሕዝቡ ከከትግራይ ነፃ አውጪ ሠራዊት ጋር እየተጋደለ ነው * ባህርዳር የተኩስ ልውውጥ ይሰማል

Bilderesultat for ethiopia bahir dar(ዘ-ሐበሻ) በባህርዳር እና በጎንደር አሁንም ውጥረቱ እንዳየለና በተለይም በባህርዳር ከተማ የተኩስ ልውውጥ እንደሚሰማ ከስፍራው የደረሱን መረጃዎች አመለከቱ:: እንደመረጃዎቹ ገከጻ ከሆነ የአጋዚ ሰራዊት ሕዝቡን ለማሰስ ባደረገው ሙከራ የተነሳ ሕዝብ እየታከሰ ይገኛል::
በተለይ አባይ ማዶ በሚባለው አካባቢ ህዝቡ ወደ ባህርዳር ለመግባት ሲሞክር ከትግራይ ነጻ አውጪ ሰራዊት ጋር እንደታኮሰና ቁጥራቸው በይፋ ያልታወቀ ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል::
የሕወሓት ነፃ አውጪ ግምባር በተለይ በዛሬው ዕለት አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ከስልጣናቸው ካገደና ከማንኛውም የድርጅት ሥራ ውጭ ካደረገ በኋላ የሕዝቡ መነሳሳት እንደጨመረ ከስፍራው የሚደርሱን መረጃዎች ያመለከታሉ:: በተለይም የክልሉ ፖሊስም ከሕዝብ ጋር በመቆም ከትግራይ ነጻ አውጪ ወታደሮች ላይ ጥቃት እንደፈጸመም አንዳንድ መረጃዎች ተሰምተዋል::
በባህርዳር ምንም ዓይነት የንግድ ልውውጥ እንደሌለና በከተማዋ ያሉ ባጃጆችም ከአንዳንዶቹ በስትቀር በከተማዋ እንደማይታዩ ለዘ-ሀበሻ የመጣው ዜና ጠቁሟል::

No comments:

Post a Comment