Thursday, August 11, 2016

እሁድ በደብረብርሃን ይደረጋል የተባለው ሰልፍ ያስፈራው የሕወሓት መንግስት ዛሬ የባጃጅ ሹፌሮችን ሰብስቦ ሲያስፈራራ ዋለ

የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ከስብሰባው ያነሱት ፎቶ(ዘ-ሐበሻ) የፊታችን እሁድ በደብረብርሃን ከተማ ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀው ሰላማዊ ሰልፍ ያስፈራው የትግራይ ነፃ አውጪ መንግስት ዛሬ የደብረብርሃን የባጃጅ ሹፌሮችን ስብሰባ ጠርቶ ‘በ እሁዱ ሰልፍ ላይ እንዳትሳተፉ; በእሁዱ ሰልፍ ላይ የሚገኝ የባጃጅ ሹፌር ፈቃዱን ይነጠቃል” እያሉ ሲያስፈራሩት እንደዋሉና ተሰብሳቢው ግን ፊቱን እንዳዞረባቸው የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ከስፍራው በፎቶ ግራፍ አስደግፈው በላኩት መረጃ ጠቁመዋል::
ዛሬ በደብረብርሃን ከተማ ምንም ዓይነት የባጃጅ ትራንስፖርት አልነበረም ያሉት እነዚሁ የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች በወልቃይት ጉዳይ ጥያቄ እንዳታነሱ; በጎንደርና በባህር ዳር የተደረገውን የህዝብ ተቃውሞም እንዳትደግፉ; ያንን የሚደግፉ ጸረ ልማቶች ናቸው የሚሉ ማስፈራሪያዎች ከመድረኩ ተሰምቷል::
የባጃጅ ሹፌሮቹ በጎንደርና ባህርዳር ሕዝብ ያነሳውን ጥያቄ አውግዙ ሲባሉ እምቢ ቢሉም የሕወሃት መንግስት ግን “በደብረብርሃን ያሉ የባጃጅ ሹፌሮች በጎንደና ባህርዳር የተደረገውን የሕዝብ ተቃውሞ አወገዙ” የሚል ዜና ከመስራት እንደማይቆጠብ ታዛቢዎች ይናገራሉ::
በደብረብርሃን ወጣቶችን ሳይቀር ቤት ለቤት እሁድ ሰልፍ እንዳትወጡ እያሉ እያስፈራሩ ነው ያሉት ዘጋቢዎቻችን አብዛኛው ሕዝብ ግን እሁድ ሰልፍ ከመውጣት የሚያግደን ምንም የለም የሚል አቋም እንደያዘ ለመረዳት ተችሏል::

No comments:

Post a Comment