የሕወሓት መንግስት በርካታ ወጣቶችን ከአዲስ አበባ አፍሶ መውሰዱ ተዘገበ
(ዘ-ሐበሻ) በሰሜን እና በደቡብ በተከፈተበት ወታደራዊ ጥቃት ከፍተኛ መደናገጥ ውስጥ የገባው የሕወሓት መንግስት ከትናንት ማማሻውን ጀምሮ በአዲስ አበባ የተለያዩ ክፍለ ከተሞች ወጣቶችን ሲያፍስ መዋሉ ተዘገበ:: ዘገባዎች እንደሚጠቁሙት ከሆነ ከ4 ሺህ የማያንሱ የአዲስ አበባ ወጣቶች በትናንትናው እና በዛሬው ዕለት ታፍሰዋል:: አንዳንድ የዜና ምንጮች ለዘ-ሐበሻ እንደሚገልጹት ከሆነ የታፈሱት ወጣቶች በአብዛኛው ለውጥ ሊያመጡ ይችላሉ የተባሉት ናቸው:: በተለይም የአርበኞች ግንቦት 7ን ጥቃት ተከትሎ እነዚሁ ወጣቶች በአዲስ አበባ ከተማ ለለውጥ ሊነሱ ይችላሉ በሚል ስጋት ይህ አፈሳ እንደተካሄደ ይነገራል:: እነዚህ ወጣቶች መገናኛ አካባቢ የሚገኝ አንድ ትልቅ ስፍራ ውስጥ ታጉረው ከቆዩ በኋላ ወደ አልታወቀ ስፍራ በአውቶቡሶች ተጭነው መወሰዳቸውን የጠቆሙት የዜና ምንጮች ወደየት እንደተወሰዱ ለማረጋገጥ እንዳልቻሉ ገልጸዋል:: - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/45501#sthash.VWnOygQK.dpuf
No comments:
Post a Comment