Tuesday, August 18, 2015

በቆሙበት የሚረግጡ ሰማያዊና መድረክ – ግርማ ካሳ

Bilderesultat for blue party ethiopiaBilderesultat for medrek party ethiopia“ፓርቲ አለኝ እያሉ አመታትን ከመቁጥር ግን ካአምባገነኖች ጋር ተጋፍጦ ፈርሶም ምስላቸዉን ማበላሸትና ጭምብላቸዉን ማስወለቅ ይሻላል፡፡አሁንም በህይወት ካሉት የጠፋን አንድነት ይፈራል ብሎኛል አንድ የዘመኑ ሰዉ….”
ይሄን የጻፊት አቶ ተክሌ በቀለ ናቸው። ትክክለኛ አባባል ነው ያስቀመጡት። አቶ ተክሌ የእዉነተኛው የአንድነት ፓርቲ ም/ሊቀመንበር ናቸው (ነበሩ ያላልኩት ወያኔ ሕጋዊነትን ቢወስድባቸው በአባላትና በደጋፊዎች ዘንድ አሁን እንደ መሪ ስለሚታዩ ነው) ።
እንደሚታወቀው ገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ በኃይልና በጉልበት የአንድነት ሕጋዊነት ነጥቆ የድርጅቱን ሰርተፊኬት ራሱ ላደራጃቸው የትግስቲ አወሉ ቡድን መስጠቱ ይታወቃል። ወያኔዎች ሌሎች ድርጅቶችን ለማፍረስ አልሞክሩም። በትራቸው ያነሱት አንድነት ላይ ብቻ ነው። አንድነት በርግጥ በአገሪቷ በሙሉ ከፍተኛ ጥንካሬ የነበረው ድርጅት ነው። ሌሎች ድርጅቶች በሙሉ በአንድ ላይ ቢጨፈለቁ አንድነት ፓርቲን አያክሉም ነበር የሚል እምነት ነው ያለኝ።
አቶ ተክሌ እንዳሉት በርግጥ ፓርቲ አለን እያሉ ዝም ብሎ ከማውራት ሥራ ሰርቶ አምባገነኖችን ማጋለጥ ይቻላል። አንድነት ያደረገው ያንን ነው። አንድነት ፣ የፖለቲካ እርምጃ የተወሰደበት፣ ሥራ ስለሰራ ነው። ለዚህም አንድነቶች እና የአንድነት ደጋፊዎች ሊኮሩበት የሚገባ ነገር ነው።
አንድነቶች ፓርቲያቸውን ቢነጠቁም፣ ከትግሉ አልሸሹም። አንድነት ማለት የምርጫ ቦርድ ወረቀት አይደለም። አንድነት ማለት አባላቱ ፣ደጋፊዎቹ፣ ህዝቡ ማለት ነው።
ሰማያዊዎች አንድነት የሚሊዮኖሽ ድምጽ እንቅስቃሴ ያደረግ የነበረ ጊዜ እንኳን የትግል አጋርነት ሊያሳዩ፣ ጭራሽ ችግር ፈጣሪዎች ነበሩ። የአቶ ይልቃል ፖለቲካ የአብሮ መስራት ፖለቲካ ሳይሆነ ሌሎችን የማሳነስና የመከፋፈል ፖለቲካ ነበር። መድረኮች፣ የሚሊዮኖች ድምጽ እንቅስቃሴ እኛን ሳያስፈቅድ ለምን አደረገ ብለው ፣ አንድነትን ከመድረክ ዉስጥ አግደዉት ነበር።
በምርጫ 2007 ግን፣ አንድነቶች፣ ድርጅታቸው ቢታገድም፣ ትግሉ የድርጅት ሳይሆን የአገር ጉዳይ ነው በሚል፣ ሰማያዊን፣ መድረክን በመደገፍ የትግሉ አካል ሆነው ሲንቀሳቀሱ ነበር።
በምርጫው ወቅት በተፌጠረው መቀራረብ ምክንያት፣ ሰማያዊን እና መድረክ በመደገፍ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ አንድነቶች፣ አዲስ ፓርቲ አናቋቁምም በሚል ሰማያዊ ፓርቲን ወይንም መድረክን ለመቀላቀል ሐሳብ ነበራቸው። ሆኖም እንዳሰቡትና እንደጠበቁት የሆነለቻው አይመስልም።
የሰማያዊ ፓርቲ የአንድ ሰው ንብረት በመሆኑና ግትር ፖለቲካ በማራመዱ፣ ብዙ የአንድነት ኃይሎችን አቅፎ ማታገል አልቻለም። በአመራሩ ዘንድ ፍቃደኝነቱ ያለ አይመስልም። የተማሩ፣ የበሰሉ የአንድነት አመራሮች ሰማያዊን ከተቀላቀሉ እኛ ቦታችንን ልንለቅ እንችላለን የሚል ስጋት ሊቀመንበሩ ያደረበት ይመስላል። ሰማያዊ ሚስጥራዊ የሆነ፣ መሰረታዊ የሆነ የዲሞክራሲ አሰራር የሚጎድለው ድርጅት ነው። እጅግ በጣም የሚደነቁ፣ ጀግና ወጣቶችን አቅፏል። ሆኖም እነዚህ ወጣቶች በሳልና አስተዋይ መሪ አላገኙም። አሁን ያለው መሪ ያለ ምንም ተቀናቃኝ እንደገና የዉሸት ምርጫ ተደረጎ ተመረጥኩ ብሎ ራሱን በራሱ በመሾም ብቅ እንደሚል ብዙ መጠራጠር የለብንም። አቶ ኃይሉ ሻወል ከኢትዮጵያ ፖለቲካ ገለል ቢሉም በሌላ መልኩ ተመልሰው መጥተዋል። የአሁኑ የሰማያዊም መሪ ትንሹ ኃይሉ ሻወል መሆኑን በገሃድ እያሳየ ነው። እንደ ሰማያዊ ፓርቲ ዉስጣዊ ዲሞክራሲ የሌለው፣ የአንድ ሰው አምባገነንነት የሰፈነበት ድርጅት ደግሞ የትም አይደርስም።
ምናልባት እዚህ የምጽፈው ስህተት ሆኖ፣ የሰማያዊ ፓርቲ አዲስ አመራር ይዞ ብቅ ካለ ፣ ያደርገዉ እንጂ፣ ለጻፍኩት ነገር ይቅርታ እንደምጠየቅ ለመግለጽ እወዳለሁ። ግን የተረጋገጠ ነገር ነው። ከምርጫ 2007 ወያኔዎች አሸነፍን እንደሚሉ ተረጋግጦ እንደነበረው፣ አቶ ይልቃል ለሚቀጥሉት ሶስት አመታት ሰማያዊን የምመራው እኔ ነኝ ብሎ ይመጣል።
መድረክ በቅርቡ ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤ ብዙዎችን አሳዝኗል። ዉህደት የመፍጠሩን ነገር ሳይወስን፣ የጎሳ ድርጅቶች ስብስብ ብቻ ሆነ ለመቀጠል የወሰነ ይመስላል። በመድረክ ዉስጥ እንዳይቀጥሉም ለአንድነቶች በሩ የተዘጋባቸው ይመስላል።
አንድነቶች በመድረክ ሥር ለመቀጠል ከፈለጉ የኦፌኮ፣ ወይንም የአረና ወይንም የሲዳማ ንቅናቄ፣ ወይንም የደቡብ ድርጅት ወዘተረፈ አባል መሆን አለባቸው ማለት ነው። ለምሳሌ ኦሮሞ ያልሆነ፣ ትግሬ ያልሆነ ፣ የደቡብ ሰው ያልሆነ፣ ወይንም ኦሮሞ ትግሬ የደቡብ ሰው ሆኖ በዘሩ ሳይሆነ በኢትዮጵያዊነቱ መታገል የሚፈልግ ታጋይ እንዴት አደረጎ ነው የመድረክ አካል ሆኖ ሊሰራ የሚችለው ? ስለዚህ ለአብዛኛው የአንድነት የለዉጥ ሃይል በመድረክ ዉስጥ ሆኖ የመስራቱ ነገር ሙሉ ለሙሉ ተዘግቶበታል ማለት ይቻላል። መድረኮች ሌላውን ማቀፉ ሳይሆን ሌላው ማግለሉን የመረጡ ይመስላል።
ታዲያ የአንድነት የልውጥ ኃይሎች ፣ መቼም ዝም ብለው አይቀመጡም። ተደራጅተው መታገላቸው አይቀርም። እንዴት ነው የሚቀጥሉት ወደፊት የምናየው ይሆናል።

No comments:

Post a Comment