በዋሽንግተን ዲሲ ማንደሪን ኦሪየንታል ሆቴል ድንገት የተገኙት የወያኔው መንግስት መከላከያ ሚኒስተር ጄነራል ሳሞራ የኑስ በኢትዮጵያዊያኑ ከፍተኛ ተቃውሞ ደርሶባቸው ውርደትን መከናነባቸውን ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ አመለከተ:: በአንድ ለሊት አዳር 12 ሺህ 700 ብር በሚከፈልበት በማንደሪን ኦሪየንታል ሆቴል ያረፉት ጀነራል ሳሞራ የኑስ ከዋሽንግተን ዲሲ ግብረሃይል ወጣቶች ጋር ፍጥጫ ገጥመው ከፍተኛ የሆነ ግብግብ ተፈጥሯል:: አካባቢው በዲሲ ፖሊሶች የታጠረ ሲሆን ሳሞራም ካረፈበት ከዚህ ሆቴል ሊወጣ እንዳልቻለ የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ጠቁመዋል:: ኢትዮጵያውያኑ “ኢትዮጵያውያንን የሚያሰቃይ ወንጀለኛ ለፍርድ ይቅረብ” በሚል ሳሞራ ላይ ተቃውሟቸውን በማሰማት ላይ ናቸው:: በሽንግተን ዲሲ መጥተው በኢትዮጵያውያኑ ውርደትን ከተናነቡ የወያኔ ተላላኪ ባለስልጣናት ውስጥ ስብሃት ነጋ; ሬድዋን ሁሴን; ሶፊያን አህመድና ሌሎችም ይገኙበታል:: ግብግቡ አሁንም የቀጠለ ሲሆን የደረስንበትን መረጃ እናሳውቃችኋለን:: Wednesday, May 13, 2015
ሳሞራ የኑስ በዋሽንግተን ዲሲ እጅግ ተዋረዱ * ተቃውሞው ቀጥሏል
በዋሽንግተን ዲሲ ማንደሪን ኦሪየንታል ሆቴል ድንገት የተገኙት የወያኔው መንግስት መከላከያ ሚኒስተር ጄነራል ሳሞራ የኑስ በኢትዮጵያዊያኑ ከፍተኛ ተቃውሞ ደርሶባቸው ውርደትን መከናነባቸውን ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ አመለከተ:: በአንድ ለሊት አዳር 12 ሺህ 700 ብር በሚከፈልበት በማንደሪን ኦሪየንታል ሆቴል ያረፉት ጀነራል ሳሞራ የኑስ ከዋሽንግተን ዲሲ ግብረሃይል ወጣቶች ጋር ፍጥጫ ገጥመው ከፍተኛ የሆነ ግብግብ ተፈጥሯል:: አካባቢው በዲሲ ፖሊሶች የታጠረ ሲሆን ሳሞራም ካረፈበት ከዚህ ሆቴል ሊወጣ እንዳልቻለ የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ጠቁመዋል:: ኢትዮጵያውያኑ “ኢትዮጵያውያንን የሚያሰቃይ ወንጀለኛ ለፍርድ ይቅረብ” በሚል ሳሞራ ላይ ተቃውሟቸውን በማሰማት ላይ ናቸው:: በሽንግተን ዲሲ መጥተው በኢትዮጵያውያኑ ውርደትን ከተናነቡ የወያኔ ተላላኪ ባለስልጣናት ውስጥ ስብሃት ነጋ; ሬድዋን ሁሴን; ሶፊያን አህመድና ሌሎችም ይገኙበታል:: ግብግቡ አሁንም የቀጠለ ሲሆን የደረስንበትን መረጃ እናሳውቃችኋለን::
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment