Friday, May 22, 2015

10 ዕጩዎች ከምርጫው ራሳቸውን ለማግለል ለምርጫ ቦርድ ደብዳቤ ብናስገባም ማስጠንቀቂያ ተሰጠን ይላሉ -

Awelበምርጫ ቦርድ ፖለቲካዊ ውሳኔ የአንድነት ፓርቲን ሰርተፊኬትና ማህተም ያገኙት አቶ ትዕግስቱ አወሉና ተከታዩቻቸው በመካከላቸው በተነሳ ልዩነት ምክንያት በምርጫው በዕጩነት ከቀረቡ ሰዎች መካከል 10ሩ ከምርጫው ራሳቸውን ለማግለል መወሰናቸውን በመጥቀስ ደብዳቤ ለምርጫ ቦርድ ቢያስገቡም ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ደብዳቤያቸውን እንዲስቡና በምርጫው እንዲሳተፉ እንደተነገራቸው ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ የመረጃ ምንጭ ተናግሯል ፡፡ እንደ ምንጩ አቶ ትዕግስቱ ሐሰተኛ የስም ዝርዝር በማዘጋጀት ለምርጫ ቦርድ የብሄራዊ ምክር ቤት አባላቶች አሉን ማለታቸውን በመቃወማቸውና የተጠቀሱትን አባላት አይተዋቸውም ሆነ የብሄራዊ ምክር ቤት ስብሰባ ተደርጎ ባለማወቁ የተነሳ ተቃውሞ ቢያቀርቡም ሰሚ ባለማግኘታቸው ከምርጫው ራሳቸውን ለማግለል በመወሰን ለምርጫ ቦርድ ደብዳቤ አስገብተዋል ፡፡ ለምርጫ ቦርድ ያስገቡትን ደብዳቤ በግልባጭ ለአቶ ትዕግስቱ ማድረሳቸውን ተከትሎ አቶ ትዕግስቱ በተወሰኑት ላይ እገዳ ማስተላለፋቸውን ጨምሮ ገልጧል፡፡ከምርጫ ቦርድ ምላሽ በምንጠብቅበት ወቅት በግል ስልካችን ተደውሎ የማናውቃቸው ሰዎች ‹፣ከምርጫው ራሳችሁን ብታገሉ ዋጋችሁን ታገኛላችሁ››በመባላቸው ያለ ውዴታቸው ለመወዳደር መወሰናቸውን ይናገራል፡፡ በጫና የሚወዳደሩት ዕጩዎች ለምርጫው ምንም አይነት እንቅስቃሴ ያላደረጉ ሲሆን ‹‹ስለ ፈራን ለይስሙላ እንወዳደራለን››ማለታቸውን ምንጩ አክሎ አውስቷል፡፡ በተያያዘ ዜና ወረዳ 4 ለፓርላማ የሚወዳደረው ደረጄ ጣሰው የተባለው ግለሰብ በፌስ ቡክ ገጹ በማይታወቁ ሰዎች ተወሰደች በማለት ምስሏን ጭምር በመለጠፍ የተናገረላት የካፌ አስተናጋጇ ኤዶን እቤቷ መሆኗን የመረጃው ምንጭ በአግራሞት ተናግሯል፡፡ 

No comments:

Post a Comment