
ይህ ለምን አስፈለገ? ለሚለው ጥያቄዬም፣ ከመለስ ሞት ወዲህ ላደረባቸው የበታችነት ስሜትና ፍርሃት፣ አማራጭ አድርገው የወሰዱት ወያኔን እንደ ድርጅት ማጠናከር ፣ ከድርጅቱ ተባረው የነበሩትን መመለስ ፣ ትግሬዎችን በሁሉም መንግስታዊ ድርጅቶች የበላይነታቸውን ማረጋገጥና፣ በአይን አውጣነት በስፋት ትግሬዎችን እንዲቀጥሩ ማድረግ ፣ የተያዘው ስልት ይሄ መሆኑን አጫወተኝ ። ከተባረሩት መሃል ለመመለስ በሚደረገው ጥረትም፣ ለምሳሌ የትግራይ ፕሬዚደንት የአቶ አባይ ወልዱ ታላቅ ወንድም የሆኑት አምባሳደር አውአሎም አባይ፣ በአቶ መለስ ዘመን የተባረሩ ቢሆንም፣ በቅርቡ የመንግስት ቪላ እንዲሰጣቸው ተደርጓል ።
የሚያሳዝነው በቪላው ውስጥ ላለፉት 20 አመታት ነዋሪ የነበሩት አንድ የቀድሞ ረዳት ሚኒስትር በ3 ቀናት ውስጥ ቤቱን ለቀው እንዲወጡ ተደርጓል አለኝ ። ይሄ ሁሉ ሲሆን ብአዴኖች ምን እያደረጋችሁ ነው ስለው፣ እኛማ የአማራ ክልልን መሬት ለመንጠቅ የሚጋፉንን የትግራይ ክልል ወራሪዎች ስንከራከርና የህዝቡን ቁጣ ለማብረድ ላይ ታች ስንል፣ እነርሱ ፌዴራል መንግስቱን ትግራዋይ የማድረግ ስራቸውን እያፋጠኑ ነው አለኝ ። ከወልቃይት ሌላ ምን መሬት ፈለጉ? ብዬ ስጠይቅ፣ “ወልቃይት ትላለህ ጠገዴን አልፈው ሳንጃ እኮ ደርሰዋል ። ችግሩ በጣም ስለተባባሰ፣ ሃይለማርያም ደሳለኝ ራሱ መጥቶ ካድሬዎችን ሰብስቦ እስከማናገር ደርሷል
No comments:
Post a Comment