
የኤርትራ ወርቅ ማዕድን የአየር ጥቃት ደረሰበት
ከአንድ ቀን በፊት በኤርትራ እንደሚንቀሳቀስ ይፋ ያደረገ ኃይል፤ በዚሁ የወርቅ ማዕድን ላይ ጥቃት ማድረሱን ገልጾ፤ በትግርኛ የተጻፈ ወረቀት በከተማው ማሰራጨቱ ይታወሳል። በዚህ በራሪ ወረቀት ላይ ጥቃቱን የፈጸሙት የኤርትራን አስተዳደር በመቃወም መሆኑን ገልጾ ነበር። የአሁኑም ጥቃት ይህንኑ ተከትሎ የተሰነዘረ ይመስላል።
በአሁኑ ሰአት በማዕድን ማውጫው ላይ የደረሰው አደጋ ለህዝብ ይፋ አልሆነም። ነገር ግን በቃጠሎው ምክንያት ከርቀት የሚታየው ጭስ በሚስጥር የተያዘውን ጥቃት እያሳበቀ ነው።
ኤርትራ ከዚህ የማዕድን ማውጫ በአመት እስከ 400 ሚሊዮን ዶላር ታገኛለች። የዚህ ማዕድን ስፍራ መመታት፤ የአገሪቱን የኢኮኖሚ ኃይል በእጅጉ ይጎዳዋል። በሌላ በኩል ደግሞ በወያኔ የሚመራው መንግስት ጠብ አጫሪነት እንደዚሁ አነጋጋሪ ሆኗል። ጥቃቱን የሚደግፉ እና የሚቃወሙ በሁለት የተለያዩ ጎራ ሆነው፤ የሃሳብ ፍጭት በማድረግ ላይ ናቸው። በዚህ ሁሉ መሃል ግን የሚሻዕ ወርቅ ማዕድን ማውጫ ግቢ አሁንም በእሳተየነደደ ነው።
No comments:
Post a Comment