Thursday, March 19, 2015

አስደሳች ዜና ለኢትዮጵያውያኖች በሙሉ

የቀድሞ የኦነግ ሊቀመንበርና ለሺዎች ደም መፍሰስ ያልተጠየቁት አቶ ለንጮ ለታ፤ የአራዳ ስማቸው (ዮሃንስ) ከኦስሎ/ኖርዌይ ተነስተው ትናንት ምሽት አዲስ አበባ ገቡ። 
ጋሼ ለንጮ እ.ኤ.አ 1990/91 በመገንጠል ወረፋው ከኤርትራ ቀጥሎ እንደሆኑ በቀድሞ በጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ የተገባላቸው ቃል የእውነት መስሏቸው እ.ኤ.አ በ1993 ግማሽ ኢትዮጵያን ለማስገንጠል የነበራቸው ምኞት ቅዠት ብቻ ሆኖ የመገንጠል ጥያቄው ከጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ወደ ጥል በማምራቱ ኖርዌይ በስደት ከ22 አመታት በላይ መኖራቸው ይታወሳል። 
አስቡት!! ዛሬ እነ ሌንጮ ከኦሕዴድ ጋር ቁርጥ ሲበሉ የዲያስፖራ ኦነጎች አፈር ድሜ በሉ።

No comments:

Post a Comment