Friday, August 12, 2016

በፍራንክፈርት፣ በስቶክሆልም፣ በለንደን፣ በጄኔቫና በኦስሎ ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን የተላለፈ አስቸኳይ ጥሪ

Oromo amhara unityየሀገራችንን ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታና ወገኖቻችን እየከፈሉ ያሉትን ከፍተኛ መስዋዕትነት ለመደገፍ፣ ለማበረታታትና አጋርነታችን ለማሳየት ከአገር ውጭ በማንኛውም የአለም ክፍል የምንገኝ ኢትዮጵያውያን ከዚህ በታች የሚከተሉትን እንቅስቃሴዎች ለማድረግ ተዘጋጅተናል።

1ኛ: የሻማ ማብራት መርሐ ግብር
የፊታችን አርብ ኦገስት 12 ቀን 2016 ዓ/ም ኢትዮጵያውያን በብዛት በሚኖሩባቸው በዋና ዋና ከተሞች በህወሀት አጋዚ ጦር በጥይት ተደብድበው በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች ውድ ሕይወታቸውን ያጡትን ሰማዕታት ለመዘከር የሻማ ማብራት ፕሮግራም ማካሄድ፣
2ኛ: የፊታችን እሁድ ኦገስት ቀን 2016 ዓ/ም በሁሉም የእምነት ተቋማት ለነዚሁ ሰማዕታት ፀሎተ ፍትሃት ማድረግ፣
3ኛ: ከፊታችን አርብ ኦገስት 12 ቀን እስከሚቀጥለው አርብ ኦገስት 19 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ በዋና ዋና ከተሞች ጨፍጫፊውን የህወሃት ስርዓት ለመቃወምና የሰፊውንና የነፃነት ፈላጊውን የኢትዮጵያ ህዝብ እልህ አስጨራሽ ትግል ለመደገፍ እንዲሁም አጋርነታችን ለማሳየት ታላቅ ትዕይተ ህዝብ ማድረግ፣
4ኛ: ከህወሃት ወያኔ የዘረኛ አገዛዝ ለአንዴና ለመጨረሻ ለመገላገል አደባባይ ሲወጡ በአጋዚ ጦር በጥይት ተደብድበው መተኪያ የሌላት ህይወታቸውን መስዋዕት ላደረጉ ወገኖቻችን ቤተሰቦች መርጃ የሚሆን ገንዘብ የማሰባሰብ፣
5ኛ: በአጋዚ ስናይፐር፣ መትረየስና ክላሽ ተደብድበው በየሆስፒታሉና መኖሪያ ቤታቸው የተኙ ወነገኖቻችንን ለማሳከምና
6ኛ: በህወሃት ማጎሪያ ቤቶች በአማራ፣ በኦሮሚያና አዲስ አበባ ታስረው የሚገኙ ዜጎቻችንን በስንቅና በሞራል ልንደግፍባቸው የምንችልባቸውን መንገዶች ለመወያየት ከፊታችን አርብ ኦገስት 12 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ በተለያዪ የመወያያ መንገዶች ውይይት ለማድረግ ተዘጋጅተናል።
በዚህ መሰረት እስካሁን ሰላማዊ ሰልፍ ሊደረግባቸው የታቀዱ ከተሞች:
አርብ ኦገስት 12 ቀን 2016 ዓ/ም
በጀርመን ፍራንክፈርትና በስዊድን ስቶኮልም
ሰኞ ኦገስት 15 ቀን 2016 ዓ/ም
በእንግሊዝ ለንደን
ማክሰኞ ኦገስት 16 ቀን 2016 ዓ/ም
በስዊዘርላንድ ጄኔቫ
አርብ ኦገስት 19 ቀን 2016 ዓ/ም
በኖርዌይ ኦስሎ
ሲሆኑ በሌሎች የአለማችን ታላላቅ ከተሞችም ታላቅ ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፎችን ለማድረግ እንቅስቃሴዎች በመደረግ ላይ ናቸው።
ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን መርሃ ግብሮች ስኬታማ ለማድረግ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በሚኖርበት አካባቢ ተሳታፊ እንዲሆን ጥሪያችንን እናቀርባለን።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ

No comments:

Post a Comment