ቻይናንና ህንድን ያህል ታላላቅ አገራት የሚያዋስኗት አገር ሳር ቅጠሉ ‹‹በአምላክ ዙፋን ›› ተቀምጦ በሚመለክበት ቀጠና ….የእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ ዓለም ‹‹አላየሁም አልሰማሁም›› ብሎ አውቆ ተኝቷል !! የቢዮንሴ ማስነጠስ ሶስት ቀን ዜና የሚሆንባት አለም ላይ የኢስራኤል አንድ ወታደር መማረክ የጦር ጀቶች እና ሚሳኤል በሚያሰልፍበት ዘመን …. የበርማ ሙስሊሞች እጣ ፋንታ ከልጅ እስከአዋቂ እየደረሰባቸው ላለው ሰቆቃ ትንፍሽ ያለ ሚዲያ የለም ….ቢኖርም እንደው ዝም አሉ ላለመባል ላይ ላዩን ከአንገት በላይ ‹‹ዜና›› ብቻ ነበር !
ለምን ያለ የለም …. የቡዲህስት መነኩሴዎች እጅ ስለምን በሙስሊሞች ደም ጨቀየ …. ህግ ባለበት መንግስት አለ በሚባልበት አገር ስለምን እንዲህ ተደረገ …. መልስ የለም መልስም ቢኖር መልሱ ለተፈፀመው ግፍ መልስ ሊሆን አይበቃም ! የሆነው ሁሉ የጭካኔ ጥግ ነው … በየቀኑ ሰው በእሳት ይቃጠላል ህፃናት ተጨፍልቀው ይገደላሉ ….ሙስሊሞች ከቃያቸው ታፍሰው ይባረራሉ ….መሄጃ የላቸውምና ለቀናት ለሳምንታት በባህር ላይ እየተንሳፈፉ በርሃብ በበሽታ በእንግልት ያልቃሉ ! ዓለም ….‹‹የሰበዓዊ መብት ጉዳይ ›› የሚያስጨንቀው አለም ይሄን አፍንጫው ስር የሚፈፀም ሰቆቃ አላየሁም ሊል ተከናንቧል ….ይባስ የአረብ አገራት ዝምታ !

የቡድሂስት መነኮሳት ዓለም ዛሬም በጨዋነታቸው ሊዘክራቸው … ግራ ቀኝ የማይመለከቱ በራሳቸው ፅሞና ለሰው ልጆች ሁሉ ሰላምን የሚመኙ ‹‹መለአኮች›› ሊያደርጋቸው ይሻል …. አንድም ሰው በድፍረት ‹‹አሸባሪ›› ሊላቸው አልፈለገም ….ግን ሰውን በእምነቱ በማንነቱ ምክንያት ገድለዋል አጎሳቁለዋል አፈናቅለዋል ! አሁንም አለም በዝምታው አይዟችሁ እያላቸው ይሄንን ግፍ ቀጥለዋል ! ከአምሳ ሚሊየን ህዝብ በላይ በሚኖርባት አገር በርማ ይህ ሆነ ….አለምም አልሰማሁም ብሏል ! ከአካባቢው የሚወጡ ቪዲዮወች እና ፎቶወች ለማየት ይዘገንናሉ …. !!
ዓለም በግፍ ለሚገደሉ ሰዎች ሳይሆን ለገዳዮች ማንነት ወግና እንደምትጮህ የታየበት አጋጣሚ ነው ! የአለም ዝምታ ለነገ ትልቅ ጩኸት መሰነቅ ነው ! ‹‹ሰዎች በማንነታቸው በሚከተሉት እምነት መገፋት መጨቆን መገደልም የለባቸውም ›› ያለችን አለም የት አለች …. ሰቆቃ ወ በርማ ! ‹‹የጨዋዎቹ አሸባሪዎች ›› ግፍና በደል ከፍ ከፍ ብላለች ….ህፃናት ሴቶች እና አቅመ ደካሞች ደማቸው ትም እየፈሰሰ ነው …. ጩኸታቸውም ከዛ ምድር እየተመመ ነው ….ዓለም ግን ጀርባውን ሰጥቷቸዋል ….ፈጣሪ ይድረስላቸው !!
No comments:
Post a Comment