Tuesday, June 9, 2015

ይሄ ሕዝብ ነው እንግዲህ ወያኔን 100% መረጠ የሚሉን – የሚሊዮኖች ድምጽ

ይሄ ሕዝብ ነው እንግዲህ ወያኔን 100% መረጠ የሚሉን – የሚሊዮኖች ድምጽሕወሃት በደቡብ እና ሰሜን ጎንደር ዞን 100% አሸነፍኩ እያለ ነው። ተከዜ፣ አባይ፣ አንገረብ የመሳሰሉ ወንዞች የሚያልፉባት፣ በኢትዮጵያ ትልቁ ሃይቅ፣ ጣና የሚያዋስናት ጎንደር፣ በዉሃ እጥረት እየተመታች ነው። እንግዲህ በቂ የዉሃ አቅርቦት ያላገኘ ይህ ሕዝብ ነው፣ እልል እያለ ወያኔ/ኢሕአዴግን መረጠ የሚሉን።
አገዛዙ በኃይልና በጠመንጃ በጭካኔ የሚገዛ ዘረኛ አገዛዝ ነው ሲባል ያለ ምክንይታ አይደለም። ጎንደር (ደቡብና ሰሜን) በወያኔ ዘመን ምን ያህል ወደ ኋላ እንደቀረች፣ ፣ ምን ያህል እንደደተረሳች ለማየት የሚከተለዉን ፣ ሊንክ መመልከት ይቻላል።
የሕወሃት መንግስት ፍትህዊ በሆነ መልኩ ኢትዮጵያን እያስተዳደረ አይደለምም። አብዛኛው ሕዝብ በድህነትና በስቃይ ላይ ነው የሚገኝው። በአዲስ አበባ፣ በሕወሃት ባለስልጣናትና ጀሌዎቻቸው የሚሰሩ ፎቆችን በማሳየት አገር ተሻሻለች እያልኡ ቢደሰኩሩም አብዛኛው የአገራችን ሕዝብ ጠብታ ዉህ ለማግኘት ለሰዓታት የሚሰለፍበት ሁኔታ ነው ያለው።

No comments:

Post a Comment