OPPOSITION PARTIES WEBSITES

ETHIO NEWS & VIEWS

RADIO & TV

Friday, August 26, 2016

በጎጃም ጅጋ ከተማ በተቀሰቀሰ አመጽ ከሕዝቡ 4 ከትግራይ ነጻ አውጪ ሰራዊት 3 ወታደሮች ተገደሉ

Jiga gojam(ዘ-ሐበሻ) በጎጃም ክፍለ ሃገር ጅጋ ከተማ ውስጥ የሃይማኖት አባቶች ሕዝቡን ለመገዘትና በመንግስት ላይ ያለውን የ እኩልነት ጥያቄ እንዲያቆሙ ለመጠየቅ የጠሩት ስብሰባ ወደ አመጽ ተሸጋግሮ በአሁኑ ወቅት ከተማዋ በክፍተኛ ተቃውሞ እየተናጠች መሆኑን ለዘ-ሐበሻ ከስፍራው የደረሱ መረጃዎች አመለከቱ::
ከፍኖተ ሰላም ከተማ በስተምስራቅ 10 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው ጅጋ ከተማ ሕዝቡ ባነሳው ተቃውሞ የትግራይ ነጻ አውጪ ወታደሮች በተኮስቱት ጥይት 4 ሰዎች መገደላቸውን ተከትሎ ሕዝብ በወሰደው እርምጃ 3 ወታደሮች መሞታቸውም የአይን እማኞች ገልጸዋል::
የአካባቢው ሕዝብ ወደ ሕዝብ ሲተኩስ ወደነበረ አንድ ፖሊስ መኖሪያ ቤት በመሄድም ንብረቱን አደባባይ በመዘርገፍ እንዳቃጠሉበት የተነገረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ሕዝብ ጎማዎችን በማቃጠል ከፍተኛውን ተቃውሞ እያደረገ መሆኑ ተሰምቷል:: በተለይም የስር ዓቱ ደጋፊዎች ንብረት ነው የተባለ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስም በድንጋይ ተወግሮ መስታወቱ ከጥቅም ውጭ መሆኑ በፎቶ ጭምር የተለቀቀው መረጃ አሳይቷል::

ቋሪት በሕዝብ ቁጥጥር ስር ዋለች  በወልቃይት የአማርኛ ሙዚቃ አትሰሙም በሚል ግጭት ተፈጠረ * በበርከታ የጎጃም ከተሞች የዐማራ ተጋድሎ ተፋፍሟል (የዛሬው የትግል ውሎ ዝርዝር ዘገባ)

bure1በበርከታ የጎጃም ከተሞች የዐማራ ተጋድሎ ተፋፍሟል፤ ራሳቸውንም ከወያኔ አገዛዝ ነጻ አድርገዋል
• 40 የዐማራና ኦሮሞ የጸረ ሙስና ኮሚሽን አቃቢ ሕግ ባለሙያዎች ከሥራ ተባረሩ
 በቡሬ ከተማ ከሠላሳ ሺህ በላይ ዐማራ ለተጋድሎ ወጥቷል፤ የኦሮሚያ ኢንተ. ባንክን ሕዝቡ ጥበቃ አድርጎለታል
 በጅጋ የተጋድሎ ሰልፉ ሦስተኛ ቀኑን ይዟል
 ቋሪት ወረዳ ሙሉ በሙሉ በሕዝብ ቁጥጥር ሥር ሆኗል
 ማንኩሳ፣ ፍኖተ ሰላምና ጉንደወይን ሌሎች የዐማራ ተጋድሎ የተካሄደባቸው ከተሞች ናቸው
 በጎንደር ብዙ የዐማራ ልዩ ኃይል ፖሊስ አባሎች ከሥራ ታግደዋል
 በደብረ ታቦር የሥራ ማቆም አድማ ሊጀመር ነው
 በወልቃይት የአማርኛ ሙዚቃ አትሰሙም በሚል ግጭት ተፈጠረ
ከሙሉቀን ተስፋው
ቡሬ፤ በሬ ዛሬ የዐማራ ተጋድሎ ከተካሔደባቸው ከተሞች ዋነኛዋ ናት፡፡ ከጠዋቱ ሦስት ሰአት አካባቢ የጀመረው የዐማራ ተጋድሎ እስከ ምሽት 12 ሰአት ድረስ ቆይቷል፡፡ የተጋድሎ ሰልፉ ማዶ በሚባለው የከተማው ክፍል የተጀመረ ሲሆን ከሰላሳ ሺህ በላይ የሚሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎች ተጋድሏቸው ሲያሰሙ ውለዋል፡፡ ወልቃይት ዐማራ ነው፤ ኮ/ል ደመቀ እና የወልቃይት ጠገዴ የዐማራ ማንነት ጥያቄ አቅራቢ ኮሜቴዎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ይፈቱ፤ መሬታችን ይመለስ፤ 25 ዓመት ታስረናል አሁን ግን በቃን፤ ዐማራነት ወንጅል አይደለም፣ ወያኔ ሌባ ነው፤ ብአዴን እኛን አይወክልም… የሚሉ መፈክሮች ገልተው ሲሰሙ ውለዋል፡፡ የወያኔ ደጋፊ የሆኑ ድርጅቶችና ግለሰቦች ንብረት ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ ትንሳኤ ሆቴል (ባለቤቱ ዐማራ ሲያስገድል የኖረ ሕወሓት ነው)፣ ቀበሌ 01 ጽ/ቤት፣ አብቁተ፣ የዓባይና የንግድ ባንኮች መጠነኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ የኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክን ሊያወድሙ የሚፈልጉ ተላላኪዎችን ወጣቱ ዐማራ አክሽፎታል፡፡ ኦሮሞ ወገኖቻችን ላይ የሚደርሰው ግፍ መቆም አለበት ሲሉም የዐማራ ሕዝብ አጋርነቱን አሳይቷል፡፡
በሰው ሕይወት ላይ የደረሰ አደጋ መኖሩን በተመለከተ ላቀረብነው ጥያቄ የዐይን ምስክር ሲናገሩ ‹‹እኔ በዐይኔ አንድ ለእረፍት የመጣ የዩንቨርሲቲ ተማሪ አጋዚ ሲገድለው አይቻለሁ፤ ሦስት ዐማሮችም በጥይት ተመተው ሆስፒታል ገብተዋል፤ በሕይወት ስለመኖር አለመኖራቸው ያወቁት ነገር የለም›› ብለዋል አንድ እማኝ በስልክ እንዳረጋገጡልን፡፡ የአጋዚ ወታደሮች ያቆሰሏቸው ሰዎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ በቡሬ ከተማ መግቢያና መውጫ በሮች ሙሉ በሙሉ በወጣቱ ተዘግተዋል፡፡Bure

ጅጋ፤ የጅጋ ዐማሮች ዛሬ ለሦስተኛ ቀን የዐማራ ተጋድሎ አድርገዋል፡፡ የጅጋ ከተማ ሕዝብ ከነሃሴ 18 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ በየቀኑ ወደ አደባባይ እየወጣ ተጋድሎውን እያደረገ ነው፡፡ በጅጋ እስካሁን አንዲት እህታችን ተሰውታለች፡፡ ከተማዋንና አጠቃላይ ወረዳውን ዐማሮች ራሳቸው የተቆጣጠሩ ሲሆን ዛሬ ላይ የሃይማኖት አባቶች ወጣቱን ለመሰብሰብ ሞክረው ነበር፡፡ የዐማራው ወጣትም ከእንግዲህ በኋላ የዐማራ የመኖር መብት ሳይረጋገጥ ተጋድሎው እንደማይቆም እንቅጩን በአንድ ድምጽ ተናግረው ስብሰባው ያለስምምነት መበተኑን ከቦታው በስልክ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ በጅጋ ለተከታታይ ሦስት ቀናት ምንም ዓይነት የንግድ እንቅስቃሴም የለም፡፡ ሁሉም ዐማራ የተጋድሎ ጥያቄውን እያስተጋባ ነው፡፡ በስልክ ያነጋገርናቸው ወጣቶች ‹‹ከእንግዲህ በኋላ ዐማራነት ወንጅል ሆኖ የምንኖርበት ምንም ምክንያት የለም፤ የአባቶቻችን የአርበኝነት ታሪክ በዚህ ትውልድ ይደገማል›› ሲሉ በጎበዝ አለቃዎች ጭምር መመራት መጀመራቸውን ተናግረዋል፡፡
ቋሪት፤ በቋት ወረዳ ገነት አቦ ከተማ ትናንት ነሃሴ 19 ቀን 2008 ዓ.ም. የተጀመረው የዐማራ ተጋድሎ አድማሱን አስፍቶ የወረዳዋ ከተማ ገበዘ ማርያምም በሕዝብ ቁጥጥር ሥር ሆናለች፡፡ ገነት አቦ ከተማ ትናንት ከቀኑ ከ9፡00 እስከ 12፡00 የነበረውን የዐማራ ተጋድሎ ለማደናቀፍ ከወረዳው የወያኔ ተላላኪዎች የተውጣጡ የፖሊስና የሚንሻ አባላት ወደ ገነት አቦ ተላኩ፡፡ የገነት አቦ ዐማሮችም በአንድ ድምጽ ‹‹በመጣችሁበት መኪና አሁኑ ተመለሱ፤ አይ ካላችሁ ሕይወታችሁን ጠልታችኋል ማለት ነው›› አላቸው፡፡ ከመኪና ሳይወርዱ ተመለሱ፡፡ የከተማዋ ነዋሪዎች ለዛሬ ጠዋት ቀጠሩ፡፡ በቃላቸው መሠረት ከጠዋቱ 12፡00 ጀምሮ የተጋድሎ ሰልፉ ተካሄደ፡፡ የገበዘ ማርያም ከተማ ዐማሮችም ተጨመሩ፡፡ የከተማ ፖሊሶች ዝም አሉ፡፡ ከዞን የመጣ ሁለት መኪና የፌደራል ፖሊስም የቋሪትን ዐማራ መጋፈጥ አልቻለም፡፡ የፌደራል ፖሊሶች ልብሳቸውን ቀይረው ተደብቀው ዋሉ፡፡ ነፍጠኛው ዐማራ ጥይቱን ሲቆላው ዋለ፡፡ ለዚህማ ቋሪትን ማን ብሎት፡፡ በቋሪት ነገም የዐማራ ተጋድሎ ይቀጥላል፡፡
ማንኩሳ፤ በማንኩሳ የተጀመረው የዐማራ ተጋድሎ ለሁለተኛ ቀን መቀጠሉን ሰምተናል፡፡ በማንኩሳ ትናንት የተካሔደው የዐማራ ተጋድሎ መጠነኛ ቢሆንም ዛሬ ግን ወደ አደባባይ ያልወጣ የከተመዋ ነዋሪ አልነበረም ነው የተባለው፡፡ በማንኩሳ ዝርዝር ጉዳዮችን በስልክ መቆራረጥ ምክንያት ማግኘት አልቻልንም፡፡

ፍኖተ ሰላም፤ በፍኖተ ሰላም ከተማ የዐማራ ተጋድሎ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል፡፡ ትናንት የአንድ ዐማራ ወጣት ነፍስ ያጠፈው ቅጥረኛ ምንሻ ቤት መቃጠሉንም ሰምተናል፡፡ የፌደራልና የአጋዚ ጦር በፍኖተ ሰላም ከተማ ከመጠን በላይ መግባቱን ሰምተናል፡፡ ዛሬ ይህ ሪፖርት እስከተሠራበት ሰዐት ድረስ መንገዶች ሁሉ ዝግ መሆናቸውን ሰምተናል፡፡
ጉንደወይን፤ በእነሴዎች አገር ጉንደወይን ትናንት ነሃሴ 19 ቀን 2008 ዓ.ም. ታላቅ የዐማራ ተጋድሎ ሰልፍ ተካሒዷል፡፡ የጎንቻ ሲሦ እነሴ ወረዳ ዐማሮች ትናንት ባካሔዱት ተጋድሎ የትግራይ የበላይነት ይብቃ፣ የማንነት ጥያቄያችን መልስ ይሰጥ፣ ዐማራነት ወንጀል አይደለም፣ የወንድሞቻችን ደም መፍሰስ መቆም አለበት… የሚሉ መፈክሮች መሰማታቸውን ዛሬ ከጉንደ ወይን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ በተያያዘም ነሃሴ 18 ቀን 2008 ዓ.ም. በብቸና አንድ የአገዛዙ መሣሪያ የሆነ ሰው ተገድሎ መገኘቱንም ሰምተናል፡፡
ደብረ ታቦር፤ በደብረ ታቦር ከተማ ከነሃሴ 22 ቀን ጀምሮ ለሦስት ቀን የሚቆይ የቤት ውስጥ አድማ እንደሚደረግ መርሃ ግብሩ ያሳያል፡፡ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች እንዳትወጡ የሚሉ ማስታዎቂያዎች ተለጥፈዋል፡፡ ይህን ተላልፎ በሚገኝ ሰው ላይም የዐማራውን ተጋድሎ እንደመተላለፍ ስለሚቆጠር ከህዝብ ጋር እንደተጣላ ይቆጠራል ተብሏል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ ቅጥረኛ ካቢኒዎች ነጋዴዎችን ሱቆቻቸውን እንዳይዘጉ ያስጠነቀቀ ሲሆን የቤት ውስጥ ተጋድሎው አስተባባሪዎች ማንኛውንም ተቋም የሚከፍት ሰው ከወያኔዎቸ ጋር እንዳበረ ስለሚቆጠር የሚያስከፍለው ዋጋ የከፋ ነው ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
ጎንደር፤ ጎንደር የቤት ውስጥ አድማው ለሦስተኛ ቀን ቀጥሏል፡፡ የቤት ውስጥ አድማው እስከ እሁድ ይደርሳል ተብሏል፡፡ ኮሎኔል ደመቀን የመውሰድ እቅዱ መክሸፉን የሰማን ሲሆን ትናንት ምዕራብ አርማጭሆ አብደራፊ አካባቢ አንድ ዐማራ የተሰዋ ሲሆን ሁለት የወያኔ ቅጥረኛ ፖሊሶች ዛሬ መገደላቸውን ሰምተናል፡፡
የጎንደር ከተማ ልዩ ኃይል ፖሊስ ምክትል አዛዥ መልካሙ የሽዋስ ጋርም ብዛት ያላቸው የፖሊስ አባላት በወያኔ ትእዛዝ መቀነሳቸውን ሰምተናል፡፡ የተቀነሱት የዐማራ ልዩ ኃይል ፖሊስ አባላት በሕዝብ ላይ ባለመተኮሳቸው ነው የተባለ ሲሆን ሁሉም የዐማራ ፖሊሶች በዐማራው ሕዝብ ላይ እንደማይተኩሱ ቃል ገብተዋል ሲሉ ምንጮቻችን ነግረውናል፡፡
አዲረመጥ፤ በወልቃይት ከተማ አዲረመጥ ትናንት ነሃሴ 19 ቀን 2008 ዓ.ም. የወልቃይት ዐማሮች የፋሲል ደመወዝን ‹‹ዐማራ ነኝ›› አዲስ ሙዚቃ ከፍተው ሲያዳምጡ የትግራይ ልዩ ኃይል ፖሊስ ‹‹አማርኛ ሙዚቃ ማዳመጥ አትችሉም›› በማለቱ በተፈጠረ ግጭት ከስድስት በላይ የሚሆኑ ፖሊሶች በከፍተኛ ሁኔታ ቆስለው አምልጠዋል፡፡ አንድ የወልቃይት ዐማራ በጥይት የተመታ ሲሆን ለሕይወቱ አስጊ እንዳልሆነ ከቦታው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አዲስ አበባ፤ 40 የዐማራና ኦሮሞ ተወላጅ የጸረ ሙስና ኮሚሽን አቃቢ ሕግ ባለሙያዎች ከሥራ ተባረሩ፡፡ ከአዲስ አበባ የጸረ ሙስና ኮሚሽን ዋና መሥሪያ ቤት ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው በሙስና ወንጀል የተዘፈቁ የትግራይ ተወላጆችን መዝገብ ክስ የያዙ 40 የዐማራና ኦሮሞ የአቃቢ ሕግ ባለሙያዎች ከሥራ ተባረዋል፡፡ የተባረሩት የአቃቢ ሕግ ባለሙያዎች በሥራቸው የተመሰከረላቸውና አንቱ የተባሉ የሕግ ባለሙያዎች ናቸው ተብሏል፡፡ ሆኖም የያዙት የሙስና ክስ መዝገብ የትግራይ ተወላጅ ሙሰኞችን በመሆኑ ሕወሓትን በከፍተኛ ሁኔታ ያዳክማል በሚል የዐማራና የኦሮሞ የሕግ ባለሙያዎቹ ከሥራ ገበታቸው ለመጨረሻ ጊዜ ተባረዋል፡፡ ወያኔ ከዚህ በፊትም እንደ ዳኛ ግዛቸው ምትኩ ያሉ ጠንካራ የዐማራ የሕግ ባለሙያዎችን የማባረር ልምድ መኖሩን ያስታውሷል፡፡
የዐማራ ሕዝብ ተጋድሎ ያሸንፋል::
ይህ ሁሉ የመጨረሻው መጀመሪያ ነው!!

በማጀቴ፣ በፍኖተ ሰላም፣ በቋሪት፣ በጎንደርና በወሎ የአማራው ህዝብ የዛሬ የትግል ውሎ አጫጭር ዘገባዎች

ፍኖተ ሰላምከመሳፍንት ባዘዘው
ኮለኔል ደመቀ ዘውዱን ከጎንደር እስር ቤት አፍኖ የመውሰዱ የህወሓት ሙከራ በእስር ቤቱ ፖሊሶች፣ በእስረኞች እና በጎንደር ህዝብ ነቅቶ ጥበቃ ሳይሳካ ቀርቷል ። በተለይ የጎንደር ማረሚያ ቤት ታራሚዎች በታላቅ ቁጣ ነበር ለድርጊቱ ምላሽ የሰጡት ። ድርጊታቸው የተነቃባቸው የህወሓት ፖሊሶች “እኛ የመጣነው ደሞዝ ለመክፈል ነው” በማለት ለማረሚያ ቤቱ ፖሊሶች መልስ ሲሰጡ ነበር ። የማረሚያ ቤቱ ፖሊሶች “ደሞዝ ከዚህ አይከፈልም ” በማለት አካባቢውን ለቀው እንዲሄዱ አስገድደዋቸዋል ። ህዝቡም በብዛት ወደ አካባቢው በመሄድ ለኮሎኔል ደመቀ ያለውን አጋርነት አሳይቷል። የታጠቁ አማሮች አሁንም ድረስ አካባቢዉን በቅርብ ርቀት በጥንቃቄ እዬጠበቁ ነው ተብሏል ።ጎንደር ዛሬ ሌላ በቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማ አድርጋ ውላለች ። አድማው ነገም ይቀጥላል ተብሏል።
የአማራ ተጋድሎ ዛሬ ጎጃም ዳሞት ፍኖተሰላም ላይ ሲንቦገቦግ ውሏል ። ቋሪት ላይ ህዝቡ ከህወሓት መንግስት እራሱን ነፃ አውጥቷል ተብሏል። የፍኖተሰላሙ የአማራ ተጋድሎ ጠንካራ እና አማራዊ አይበገሬነት የታዬበት ነው። አካባቢው በአሁኑ ሰአት በሕወሓት ጦር ተከቦ እንደሚገኝ ከስፍራው የቤተ አማራ ምንጮች ገልፀውልንል።
አለፋ ጣቁሳ እና ደንቢያ እስከ አሁንም ድረስ መንግሥት አልባ ቀጠናዎች እንደሆኑ ነው። የህወሓት ካብኔ አባላት አካባቢውን ለቀው ከወጡ ሳምንታት ተቆጥሯል ። ህዝቡ ራሱን በራሱ እያስተዳደረ ይገኛል።
ሸዋ ማጀቴ አካባቢ አሁንም አማራዊ ተጋድሎው እንደቀጠለ ነው። የሸዋ አማራ በተደጋጋሚ የወልቃይት አማራነት ጥያቄ በቀጥታ እንደሚመለከተው ጮክ ብሎ እየተናገረ ነው።
ወሎ በተለያዩ ቦታዎች የአማራ ልጆችን አፍኖ የመውሰድ ህወሃታዊ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።ትልልቅ ከተሞች የወታደራዊ ቀጠና እስኪመስሉ ድረስ በሕወሓት ጦር ተወረዋል። ያ መስመር የህወሓት ትልቅ የደም ስር ስለሆነ ከፍተኛ የሆነ ወታደራዊ ጥበቃ እዬተደረገለት ነው። ይህን ሁሉ አፈና ተቋቁሞ የወሎ አማራ አሁንም ቢሆን አማራዊ ተጋድሎውን አላቆመም ። በተለያዩ መንገዶች ተቃውሞውን እያሰማ ነው። ከወሎ ምድር ተቆርሶ የተወሰደው የራያ የቆቦ አማራዊ ክፍል ቁጭት ከመቸውም ጊዜ በበለጠ በህዝቡ ዘንድ የጋለበት ሰአት አሁን ነው ተብሏል።
በተያያዘ ዜና አዲስ አበባ ውስጥ ንዋሪ የሆኑ የህወሓት አባላት እና ደጋፊዎች ከፍተኛ የሆነ የሞራል ቀውስ ውስጥ እንደገቡ ምንጮቻችን ገልፀውልናል ። ህዝቡ በማንኛውም ሰአት ግልብጥ ብሎ ወጥቶ በእነሱ ላይ ርምጃ ሊወስድ ይችላል በሚል ፍራቻ የተነሳ የሰቀቀን ኑሮ እዬኖሩ እንዳለ ተገልጿል ። ይህን ፍራቻ መቋቋም ካቃታቸው የህወሓት ልጆች በተለያዩ የትግራይ ከተማዎች ግዜያዊ መጠለያ ካምፕ እዬተዘጋጀላቸው መሆኑን ለመረዳት ችለናል። እስከ አሁን ከጎንደር እና ከባህርዳር ብዛት ያላቸው የህወሓት የቁርጥ ቀን ልጆች ወደ ትግራይ ሄደዋል።

የአትሌት ፈይሳ ሌሊሳ እናት “መንግስት ያለውን አላምንም… ልጄ እዚያው ይቀመጥልኝ አሉ”

feysa lelisa mom በአሁኑ ወቅት ጎግል ላይ ገብተው ኢትዮጵያ የሚል ቃል ቢጽፉ ከ100 በላይ ዜናዎችን በቅድሚያ የምታገኙት ስለአትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ነው:: ከ500 በላይ የኦሮሞ ተማሪዎች እና ከ200 በላይ አማሮች በዚህ በሰሞኑ የሕዝብ ተቃውሞ በሕወሓት መራሹ መንግስት ሲገደሉ ያላገኝነውን የዓለም አቀፍ ሚድያ መድረክ በአንድ ፈይሳ ሌሊሳ ተቃውሞ የዓለማችንን ታላላቅ ሚዲያዎችን ትኩረት አግኝተናል:: መለስ ዜናዊ ሲሞት ዜናውን ለ15 ሰከንድ የዘገበው የአሜሪካው ሲኤን ኤን ሳይቀር ለፈይሳ ሌሊሳ ተቃውሞና ያን አስታኮ ስለኢትዮጵያ ያለውን ግድያና የሰብአዊ መብት ረገጣ በሰፊው ዘግቧል::
የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ አትሌት ፈይሳ ወደ ሃገሩ እንዲመለስ; ከተመለሰ በኋላም ስላደረገው ተቃውሞ ምንም የሚደርስበት ነገር የለም ማለታቸውን ተከትሎ ሬውተርስ የጀግናውን አትሌት ፈይሳ እናት የሆኑትን ወ/ሮ ብሪቱን አነጋግሯቸው ነበር::
ወይዘሮ ብሪቱ መንግስት ልጃቸውን ምንም አላደርገውም ወደሃገሩ ይግባ ያለውን ለሮይተርስ ምላሽ ሲሰጡ <ይሄ ነገር እናንተስ እውነት ይመስላችኋል?… እዛው ይቀመጥልኝ!> ሲሉ ተናግረዋል::

ፍኖተሰላም፣ ጅጋ፣ ማንኩሳ፣ ቡሬና ግንደወይን ሕዝብ ከትግራይ ነጻ አውጪ ሰራዊት ጋር እየተዋደቀ ነው | ሞጣና ቢቸና ተወጥረዋል

(ዘ-ሐበሻ) በጎጃም ፍኖተ ሰላም ከተማ የተጀመረው ሕዝባዊ ተቃውሞ ዛሬም በመቀጠል ከተማዋ በተኩስ እሩምታ ስትታመስ መዋሏን ምንጮች ዘገቡ:: እንደምንጮች ዘገባ ዛሬ አንድ የትግራይ ነጻ አውጪ ሰራዊት ተላላኪ ታጣቂ በቀበሌ 03 አንድን ሰላማዊ ወጣት ገድሎ ሌሎችን ሲያቆስል በአጸፋው ሕዝብ የዚህን ታጣቂ መኖሪያ ቤት እንዳነደደው ተዘግቧል::
Zehabesha-News.jpg
ለፍኖተ ሰላም ከተማ ቅርብ በሆነችው ጅጋ ከተማም በተደረገ ተቃውሞ አንድ ወጣት በትግራይ ነጻ አውጪ ሰራዊት መገደሉ ሲሰማ ከተማው በተቃውሞ ሲናጥ ውሏል:: ፍኖተሰላምን ተሻግሮ በቡሬ ከተማ እና በግንደወይን የአማራው ተቃውሞ አይሎ ሲውል አካባቢውን የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት ወታደሮች ከበውታል:: ሆኖም ግን ሕዝቡ ምንም ሳይፈራ ተቃውሞውን በማሰማት ላይ ነው:: እንደምንጮች ገለጻ ሠራዊቱ ወደ ሕዝቡ የተኮሰ ሲሆን ምን ያህል ሰው እንደተጎዳ ለማወቅ አልተቻለም::
ይህ በጎጃም የተነሳው ተቃውሞ በማንኩሳ ከተማም እየደረገ ሲሆን የትግራይ ነጻ አውጪ ሰራዊት አንድ ሰላማዊ ሰው መግደሉና በርካቶችን ማቁሰሉን የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ:: ይህ የአማራው ተቃውሞ በሞጣና ቢቸና ከተምችም ይዛመታል በሚል ከተሞቹ በከፍተኛ ጥበቃ ስር ሲሆኑ አካባቢው ውጥረት መንገሱም ታውቋል::
በሌላ በኩል ኮለኔል ደመቀ ዘውዱን ከጎንደር ማረሚያ ቤት ለመውሰድ የመጣው የትግራይ ነጻ አውጪ ሰራዊት በማረሚያ ቤት ፖሊሶች አንሰጣችሁም በመባላቸው ወደ መጡበት እየተመለሱ መሆኑ ተሰምቷል:: እንደ መረጃው ከሆነ ትናንት ኮለኔል ደመቀ ዘውዱ አንሰጥም በሚል በተነሳ ግጭት ከተማዋ ለሊቱን ሙሉ በተኩስ ስትናጥ አድራለች:: በመላው ጎንደር አሁንም ውጥረቱ እንዳለ ሲሆን ሕዝብ አንገዛም ባይነቱን እንደቀጠለ ነው::

Wednesday, August 24, 2016

የአዲስ አበባው ተቃውሞ መስተጓጎል ምን ይነግረናል?

Bilderesultat for addis ababaበአዲስ አበባ ይካሄዳል ተብሎ የነበረው የተቃውሞ ስልፍ ሳይካሄድ ቀርቷል። ለሰልፉ አለመካሄድ ዋና ምክንያት የመንግስት ማስፈራሪያና ተቃዋሚዎች ላይ ማናቸውም እርምጃ ለመውሰድ መዛቱ ነበር። የአዲስ አበባው ስልፍ አለመሳካት በሀገሪቱ የተነሳውን ተቃውሞ ያዳክመው ይሆን አርጋው አሽኔ ዘገባ አለው-እዚህ ያድምጡትየተቃውሞ ሰልፉ አለመሳካት ለገዥው ፓርቲ የልብ ልብ የሚሰጥና የእስካሁኑ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሊያሳድር ይችላል ሲሉ ለዋዜማ አስተያየታቸውን የሰጡ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች ተናግረዋል።
ምንም እንኳን የሰልፉ መቅረት ለገዥው ፓርቲ የፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ጥሩ አጋጣሚ ቢመስልም በሀገሪቱ ያለውን ተቃውሞ በመሰረታዊነት ሊቀይረው የሚችል አይደለም። ከህዝባዊ አመፁ ባሻገር ገዥው ፓርቲ ሊጠገን የማይችል ውስጣዊ የመሰንጠቅ አደጋ አንዣቦበታል።
ከሳምንት በፊት በማህበራዊ ድረ ገፃች ቀጠሮ የተጠራበት የአ.አን የተቃውሞ ሰልፍ በባለቤትነት የጠራ የፓለቲካ ፓርቲ ያለመኖሩ በመንግስት ከተነገረው ማስፈራሪያና ዛቻ በተጨማሪ የተቃውሞ ሰልፉ ለመቅረቱ ምክንያት መሆኑንም ፓለቲከኞቹ ገልፀዋል።

Tuesday, August 23, 2016

Hiber Radio: በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የለውጥ አብዮት ትውልድ አቀፍ ነው ተባለ – ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩ ስለ አዲስ አበባ ሁኔታ ይናገራል – የኦባንግ ሜቶና አብርሃ በላይ ቃለምልልስን ይዘናል

habtamu05
የህብር ሬዲዮ ነሐሴ 15 ቀን 2008 ፕሮግራም
< ... ዛሬ አዲስ አበባን የጦርነት ቀጠና ያስመሰላት የሕወሃት አገዛዝ ያልተረዳው ይሄ የተጀመረ ወታደር ማንጋጋት የትኛውንም አምባገነን ከውድቀት አላዳነም...ታላቅ ነኝ ያለው ሳዳም አትግደሉኝ እያለ ፉካ ውስጥ ተወሽቆ ነው የተገኘው። ግብጽ ሙባረክ ያ ጠንካራ አምባገነን ተንኮታኩቷል ።ሕዝብ ሲተባበር አምባገነኖች ቦታ የላቸውም ።የኢትዮጵያ ሁኔታም ከዚህ የተለየ ሊሆን አይችልም...ሕወሓት ሮጦ ትግራይ ሕዝብ ቀሚስ ውስጥ ለመደበቅ መሞከሩን መረዳት ያስፈልጋል ... > ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ዛሬ በአዲስ አበባ ስለታሰበው ተቃውሞና በከተማው ስለፈሰሰው ሰራዊት ከህብር ሬዲዮ ተጠይቆ ከሰጠው ምላሽ የተወሰደ (ቀሪውን ያዳምጡት)
<...እነዚህ ቀድሞም ሲቃወሙ የነበሩ ናቸው ።ያደረጉት ትልቅ ነው ቀሪዎቹ የትግራይ ምሁራን የወያኔን ጭፍጨፋ ለምን አይቃወሙም?...> አቶ ኦባንግ ሜቶ ከጋዜጠኛ አብርሃ በላይ ጋር በጋራ ለህብር ሬዲዮ ከሰጡት ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ክፍል አንድ አድምጡት)
<... ሕወሓት ከበረሃ ጀምሮ የትግራይ ኮሚኒቲ በሚል በዲያስፖራ ያደራጃቸው ራሳቸውን ነጥለው የቆሙ የጥቅም ተካፋዮች ናቸው...ጥረታችን በአስር ሺዎች የሆኑ የስርኣቱ ጥቅመኞች ላይ ሳይሆን እየተረገጠ ያለው የትግራይ ሕዝብ ከቀሪ ወገኖቹ ጎን ቆሞ ጸረ ኢትዮጵያ የሆነውን ሕወሓትን እንዲታገል ነው በዚያው መጠን ግን በጭፍን ጥላቻ በተዘዋዋሪ ለሕወሓት መሳሪያ የሚሆኑ ጥቂት ዘረኞችም ከዚህ ድርጊት መጠንቀቅ አለባቸው ።እየጠቀሙ ያሉት ሕወሓትን ነው ...> ጋዜጠኛ አብርሃ በላይ ከአቶ ኦባንግ ሜቶ ጋር በጋራ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ክፍል አንድ ያድምጡት)
ኢትዮጵያዊው አርቲስት እና የታክሲ ሹፌር በአሜሪካ ሎስ አንጀለስ ውስጥ የተፈጸመበት አሳዛኝ ግድያ እና የቅርብ ጎደኞቹ እይታ/ልዩ ጥንቅር/
<...ተቃውሞው እንዳይቀዘቅዝ በየቦታው ያሉ ዋና አጀንዳዎች እየታዩ መቅረብና በጋራ ማስተባበር ያስፈልጋል..> አክቲቪስት ገረሱ ቱፋ(ካለፈው የቀጠለ ውይይት-ክፍል ሁለት) <...ተቃውሞው የታሰበለትን ዓላማ እንዳይስትና ተፈላጊውን ለውጥ እንዲያመጣ መታገል ተቃዋሚዎች በጋራ መስራት አለባቸው...> አክቲቪስት መስፍን አማን(ካለፈው የቀጠለ ያድምጡት) ሌሌችም
ዜናዎቻችን
ኢትዮጵያዊው የማራቶን ጀግና በኦሎምፒክ መድረክ በአገር ቤት የሚፈጸመውን ግፍ መቃወሙ ታላቅ ብሔራዊ ጀግና አሰኘው
አሜሪካዊው ከፍተኛ ዲፕሎማት በኦሮሚያና በአማራ ክልል የተነሳው ተቃውሞ ለኢትዮጵያው አገዛዝ ብርቱ ፈተና መሆኑን ገለጹ
አትሌት ፈይሳ ለሊሳ አገዛዙ ወገኖቼን እየጨፈጨፈ ነው ሲል ገለጸ
አገር ቤት ቢገባ ሊገደል ወይ ሊታሰር እንደሚችል ና ጥገኝነት እንደሚጠይቅ አስታወቀ
የትግራይ ሕዝብ በስሙ ወገኖቹን በሚገለውን ስርዓት ላይ እንዲነሳ ተጠየቀ
በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የለውጥ አብዮት ትውልድ አቀፍ ነው ተባለ
አቶ ኦባንግ የትግራይ ልሂቃን ለሕዝቡ የሚአስቡ ከሆነ ከቀረው ወገናቸው ጎን የሚሰለፉበት ወሳኝ ወቅት መሆኑን ገለጹ
በተቃውሞ የሚታወቁት የእነ ዶ/ር አረጋዊ መግለጫ ብቻ በቂ አለመሆኑን አስታወቁ
በብራዚሉ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያኖችን አንገት ያስደፋው አትሌት በቶኪዮ ኦሎምፒክ እንገናኝ አለ
አትሌት አልማዝ አያናና ገንዘቤ ዲባባ ስለቀረበባቸው ክስ ምላሽ ሰጡ
በሚኒሶታ የሚገኘው ደብረ ሰላም መድሓኒዓለም ቤተ ክርስቲያን በአገር ቤት እየተፈጸመ ያለውን ግድያ አውግዞ መግለጫ አወጣ
ሌሎችም

Saturday, August 13, 2016

የማንቂያ ደውል።- ዳዊት ዳባ

Bell-123909540w1በሀገራችን እየተካሄደ ያለው ህዝባዊ እንቢተኝነት የነፃነት የእኩልነት የፍትህና የኢኮኖሚ ጥያቄ መሆኑን ሁሉም የሚገነዘበው መሆኑ ቢታወቅም፤ ትግሉ የህዝባችንን ጥያቄ በመለሰ መልኩ እንዲጠናቀቅ ምን  ይጠበቃል የሚሉትን ከብዙዎቹ ጥቂቶቹን ለመዳሰስ እንሞክራለን።
የፖለቲካ ድርጅቶች፤- የህዝባችንን ጥያቄ በሀይልና በማሸበር ለማፈን የተለመደውን ተግባሩን ወያኔ ተያይዟል። ህዝብ እንደተፋው አሁንም ለመቀበል ዝግጁ አይደልም።  ድርጅቶች ወቅቱ የሚጠይቀውን ሀላፊነት ተገንዝባችሁ የህዝቡን ጥያቄ ግምት ውስጥ ያስገባና ለውጡን ሊሺከምና ሊያሻግረን የሚችል ብሎም ባለድርሻዎችን ሁሉ ያሳተፈ መፍትሄ እንደምትሰሩ ይጠበቃል።
ትግሉን የሚያንቀሳቅሱ ሀይላት፤- እስካሁን የሰራችሁት ስራ  የሚያመለክተው አንድ ታላቅ ነገር በዜጎች ዘንድ ለውጥ የሚታለም ብቻ ሳይሆን የሚታይ አልፎም የሚጨበጥ ማድረግ ችላችሗል።  አድካሚ የሆነው ስራና የበዛ ሀላፊነትን ለመሸከም መድፈራችሁ የአጥፊውን ወገን ያለፈበትና ያለቀለት ታክቲክ በማክሸፍ ደረጃ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል። አበው እንደሚሉት ለአንበሳ አይመትሩም ለብልህ አይመክሩም ቢሆንም ለለውጥ ፈላጊውም ሆነ ላገዛዙ አልፎም ለውጪ አገራት  ጥርት እንዲልና ዞሮ ዞሮ መዳረሻው ይህ ስለሆነም “የስርአት ለውጥ” የሚለውን የሚሰማ አድርጉት። አጨራረሱ በቅጡ ታስቦበታል ነው  ግምቱ።
ያሉን ጥቂት የመገናኛ ብዙሀን ትግሉን ያለወገንታዊነት በእኩልነት ሽፋን እየሰጣችሁ መሆኑን እርግጠኛ ሁኑ። የሚተላለፉ መልእክቶች ሆኑ ወቅታዊ ትንታኔዎች የተሳሳተ ድምዳሜ ላይ የሚያደርሱን  እንዳይሆኑ ጥንቃቄ ቢደረግም ጥሩ ነው። ሁላችንም እንደምንገነዘበው የተሳሳተ ድምዳሜ ፖለቲካዊ መፍትሄ የመስራቱን ሂደት አስቸጋሪ ያደርገዋል። በንኪያ ሰላምታ የህዝብ ትግል ይጎዳል። ጊዜው የሚሻው የሜዲያ ሽፋን አይነት ትግሉ እራሱ ነው። በመሬት ላይ የሚቀናጅበትን፤ ቀጣይ የሚሆንበትንና አዳዲስ የትግል ፈጠራዎች የሚያጭር ቢሆን ጠቃሚ ነው። መሳርያ የያዘውን የለውጡ አካል የሚሆንበትን ሂደት ማፍጠን ይቻላል። የሚሞተውንና የሚታሰረውን ሰው መቀነስ ይቻላል። ትግሉ ያልተጀመረባቸው ቦታዎች ማስጀመር ይቻላል…..ብዙ ብዙ።
ህዝባዊ ሀርነት ትግራይ፤- ህዝብ የችግሩን ምንጭ በትክክል ተገንዝቧል። “የወያኔ የበላይነት ይብቃ” ነው እያለ ያለው። አስተዳዳራዊ መዋቅሮች እየፈራረሱ ነው። አጋር ድርጅቶች በድርጅታዊ ነፃነትና እኩልነት ጥያቄ ማንቁረት ይዘዋል።  መሳርያ የያዘው እያጉረመረመ ነው። ቅሬታውን ተኩሶ እስኪገልፀው መጠበቅ ይቻላል። የሲቪል አስተዳደሩን አፍረሶ በወታደር አገዛዝ መተካት ለችግሩ መፍትሄ ተደርጓል። ኦሮሚያ ላይ ይህ ሆኗል። አማራ ክልልም በቀጣይ የሚጠበቅ ነው። ግን አልሰራም አይሰራምም። ይህ በአለማቀፍ ደረጃ የሚፈጥረው ተፅኖ እያያችሁ ነው። ትላልቆቹ ብሄረሰቦች የሚለውን እውነት የወለደው ይህው ነው።  በአጠቃላይ ቀላል የሆነ ማንቂያ ደውል ለናንተ መስቀመጥ የሚቻልበት ሁኔታ ያለ አይመስልም። ያም ሆኖ ጊዜው የሚሻውን ለየት ያለ የመፍትሄ ሀሳብን ይዞ መምጣትና መሞከር ይቻላል። መንግስታዊ ሽብር እየፈፀማችሁና ዜጎችን እየጨፈጨፋችሁ ለመዝለቅ መሞከሩ ግን የትም አያደርስም።
የወያኔ ሀርነት ትግራይ ደጋፊዎች፤- ከተለመደው ፋይዳ የሌለውን ደረቅ ክርክራችሁን አቁሙ። የህዘብ አሸናፊነት አይቀሬ ነውና አገዛዙ ያዋጣኛል ብሎ የገፋበትን  ሽብርና ጭፍጨፋ ላይ በማንኛውም መንገድ የሚገለፅ ድርሻ እያደረጋችሁ እንዳልሆነ ለራሳችሁ እርግጠኛ ሁኑ።  ሊሰሟችሁ የሚችሉ አይመስለንም።  ከቻሉ ከመንግስታዊ ሽብር እንዲታቀቡ መምከሩ ይጠቅማችሗል።  ይህ ባይሆን ግን ህዘብ በየትኛውም መሰዋትነት ድሉን ይጨብጣል። ኪሳርው በህዋዋትና በናንተ ኪሳራ ይወራረዳል።
ድል የህዝብ ነው።
ዳኮታ የጥናት ማእከል።
8/13/2016
dakotareserech2@yahoo.com

ተይ አንቺ ውሻ!!! በዮሴፍ ሙሉጌታ ባባ (ዶ/ር)

Woyane Generals -- satenawጭብጥን በጭብጥ መመከት የማይፈልጉ አንድ አንድ ሰዎች፣ ብዕርን እንደ ጦር ይፈራሉ። በእርግጥ ሰውዬው እንዳለ ‹‹ብዕር የወጋዉን ቁስለኛዶክተር አያድነዉም!›› ከማንኛውም የጦር መሣሪያ በላይ እሳት የሚተፋ ብዕር የሚፈራ ለዝህ ይመስለኛል። በሀገራችን ኢትዮጵያ ‹‹ፍደል ቆጠርኩ›› የሚል ጥሩንባ ነፊ፣ ለተነሳው ሐሳብ/‹‹ክርክር›› ምክንያት ማቅረብ ስያቅተው፣ ተቃራኒውን/ሌላውን ወገን ለማሸማቀቅ፣ የስድብ ውርጅብኝ ማጦዝ ይጀምራል። እንድህ ዓይነቱ ሕፀፅ ‹‹አህያውን ፈርቶ ዳውላውን›› (Argumentum ad Hominem) ይባላል!! በሥነ-አመክንዮ፣ ሐሳብን በሐሳብ መመከት ማለት፣ ‹‹አንድ በቂ ምክንያት ከሃምሳ ሰበቦች የተሻለ ነዉ!›› የሚለውን አባባል በትክክል መረዳት ማለት ነው።
በሕዝብ ስም የራሳቸውን ኑሮ አደላድሎ መኖር የሚፈልጉ ሰዎች፣ ማንኛውንም ‹‹ነገር›› ከነባራዊ እውነት (Objective Truth) አንፃር ለመረዳትና ለማብራራት አይፈልጉም። ያላቸው ብቸኛ አማራጭ፣ በተለያዩ ድኅረ-ገጾች ላይ ቅዱሱን ነገር ፍጹም እርኩስ፣ እርከሱን ደግሞ ፍጹም ቅዱስ አድርጎ ማቅረብ ነው። ይህንን ስያደርጉ ትክክለኛ ስማቸውን ይቀይራሉ። በዝህ የተነሳ፣ አብዛኛው ሰው የሚደርስበትን ትችትና ስድብ በመፍራት፣ እውኔታውን ለመጻፍ አይደፍርም። በተለይ፣ አድናቆትንና ክብርን አብዝቶ የሚሹ ምሁራንና ጻሐፍዎች፣ ከሌላ ወገን የሚሰነዘርባቸውን ሂስ/ማስፈራሪያ/ስድብ መቋቋም ይሳናቸዋል።
አንድ ጸሐፍ/ተመራማር አንዱን ወገን ላመስደሰት፣ ሌላውን ደግሞ ለማስከፋት እስከጻፈ ድረስ፣ መቼም ቢሆን ቡከን መሆኑ የማይቀር ነገር ነው። የምርምር ዓለም እስከገባኝ ድረስ፣ የአንድ ጸሐፍ/ተመራማር ዋና ተልዕኮ መሆን ያለበት አንድን ወገን በጅምላ ማዋረድ (ማስከፋት)፣ ሌላውን ወገን ደግሞ ማወደስ (ማስደሰት) ሳይሆን፣ በሰከነ መንፈስ እውነቱን ጽፎ ማኅበረሰቡን/ግለሰቡን ማስተማር፣ መገጸጽና ማስረዳት ብቻ ነው።
ይሁን እንጂ፣ ሌላውን ወገን ላለማስቀየም በሚል ሰበብ፣ የማያምኑበትን ነገር እንደ ወረደ ተቀብለው ጽፈው የሚያስተምሩ ሰዎች አሉ። ይህ ደግሞ ቡከንነትና በጣም አሳፋር ድርጊት ነው። ኢትዮጵያዊው ፈላስፋ ስብሃት ገብረ-እግዚብሄር ለተስፋዬ ገ/አብ የለገሰውን ምክር መቼም ቢሆን መርሳት የለብንም፤ “ሰዎች ሲያደንቁህ አትኩራራ! ሲያጥለሉህ ደግሞ አትደንግጥ። የምረግሙህም የሚያደንቁህም በብዛት ይፈጠራሉ። መልስ እንዳትሰጥ። ይህን እርሳዉና ሌላ መፅሐፍ ጀምር።”
‹‹የሰው ልጅ ህሊና ትንሹ እግዚአብሔር ነው!›› ከተባለ፣ አንድ ግለሰብ ትክክለኛውን ነገር ጽፎ ማስተማር እንጅ፣ የለሎችን ዛቻ/ስድብ ፈርቶ እውነቱን መደበቅ የለበትም። በዓሉ ግርማ እንድህ ይላል፤ ‹‹ድፍረት የሌላት ብዕር ወረቀት ባታበላሽ ይመረጣል፣ ከአድርባይ ብዕር ባዶ ወረቀት ብዙ ይናገራል።›› እንድህ ዓይነቱ ድፍረት ግን ንብረትና ልጆች ላፈሩት ግለሰቦችም ሆነ ‹‹ከአስር ድግሪ አንድ ግሮሰሪ›› ቢሎ ለሚፈላሰፉ አድርባዮች ላይዋጥላቸው ይችላል። ይሁን እንጅ፣ ገንዘብና ህሊና የተሰማሙበት ጊዜ አልነበረም፤ አይኖርምም። ስለዝህ፣ የሰው ልጅ ለእውነት የመኖርና የመሞት ግዴታ አለበት።
ፍልስፍና በተፈጥሮው የአዞ-ቆዳ አለው! ‹‹ዳንሰኛውን ከዳንሱ ነጥሎ ማዬት የማይችሉ ሰዎች›› የሚሰነዝሩትን ማንኛውም ዓይነት አፍራሽ ትችት (ስድብ፣ ማስፈራሪያ፣ ዛቻ…ወዘተ) የማስተናገድ አቅም አለው።  በሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ፣ ስፍር-ቁጥር የሌላቸው ጥያቄዎች ይከሰታሉ። ለእነኝህ ጥያቄዎች እንዳስፈላግነቱ ጊዜያዊና ዘላቂ መፍትሔዎችን ማፈላለግ፣ የፍልስፍና ተፈጥሯዊ (ሳይንሳዊ አላልኩም!) ግዴታ ነው። ይህንን ተልዕኮ በማሳካት ሂዴት ውስጥ፣ ከሌላ ወገን ለሚሰነዘርበት ማንኛውም ዓይነት አፍራሽ ትችቶች እጅ መስጠት የፍልስፍና ተፈጥሮአዊ ባህርይ አይደለም። በሰው ልጅ ታሪክ ውሰጥ፣ ፍልስፍና ፈላስፎችን እየቀበረ፣ ራሱ ግን ሕያው ሆኖ የሚኖርበት ዋና ምክንያት ይሄው ነው። ለምሳሌ፣ በሀገራችን ኢትዮጵያ፣ የሰውሻዊያንን ፈተና ማለፍ የሚቻለው፣ በእውቀት ደረጃ ሳይሆን፣ በጥበብ (በፍልስፍና) ብቻ ስንመራ መሆኑን ለአንድ አፍታም ቢሆን መዘንጋት የለብንም።  ለመሆኑ ሰውሻዊያን ማን ናቸው?
ሰውሻዊያን ሰው ያላሰበውን የሚያሳስቡ ሰዎች ናቸው!! ሰውሻውያን የተባሉበት ዋና ምክንያት ደግሞ፣ ድርጊታቸውና አካሄዳቸው ሉሉ ከሚትባል የአፄ ኃይሌ ሥላሴ ውሻ ጋር በጣም ስለምመሳሰል ነው። ዶ/ር መረራ ጉዲና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ምስቅልቅ ጉዞና የሕይወቴ ትዝታዎች በተሰኘ መጻፉ ውስጥ ሰለዝች ጉደኛ ውሻ እንድ ሲል አስፍሮ ነበር፡-
‹‹በአፄ ኃይለ ሥላሴ ላይ ተንኮል የሚያስብባቸዉን ሰው ፊቱን አይታ የምትናገር ውሻ አንደነበራቸው፣የውሻዋ ፊት በጣም ከተቆጣ እጅ ሊነሳ የሄደው ባለስልጣን እንዲገደል ወይም እንዲታሰር፣ መጠነኛ ቁጣ ከሆነ ደግሞ፣ ስልጣኑ እንደምቀነስበት፣ አንድ ቀን በጣም ቀልደኛ ነው የሚባለዉ የአፄ ኃይለ ሥላሴ በለስልጣን፣ አቶ ይልማ ዴሬሳ የሚባለው (ይህ ሰው አነጄነራል መንግስቱ ኖዋይ የአፄ ኃይለ ሥላሴን በለሥልጣን ሰብስቦ የጨረሱ ግዜ፣ አቴጌ ታማለች ብለው ሲጠሩት እኔ ኢኮኖምስት ነኝ እንጅ ሀኪም አይደለሁም ብሎ ዲኖዋል ይባላል) አፄውን እጅ ሊነሱ ሲሄዱ፤ ውሻው ያዙኝ ልቀቁኝ ትላለች አሉ። የውሻዋን ጨወታ በትክክል የሚያውቁ አቶ ይልማም ‹ተይ አንቺ ውሻ ሰዉ ያላሰበውን፣ አተሳስቢ› አሉዋት ይባላል።››
   በሀገራችን ኢትዮጵያ፣ አንድ ተመራማሪ/ጸሐፍ ትምክህተኝነትንና ጠባቢነትን አስወግዶ፣ በንፁህ ህሊና ከሱ የሚጠበቀውን ተልዕኮ በሚወጣበት ጊዜ፣ የሉሉን መንቃራ አመል የተላበሱ ሰዎች ሆን ብሎ ችግር ይፈጥራሉ።  ሰውሻዊያንና ሉሉ የአንድ ሣንትም ሁለት ገጽታ ናቸው ያልኩበት ምክንያት ለዝህ ነው። ‹‹ተው ወንድም-አለም ሰው ያላሰበዉን፣ አታሳስብ!›› ማለት ግን ጠቢብነት ነው። ፈጣሪ ከሰውሻዊያን ፍልስፍናዊ ወጥመድ ይሰውረን እያለኩኝ፣ በማረፊያ በቀለ ግጥም የዛሬ መጣጥፌን ላሳርግ!

እንደ ተንጣለለ―አንደ ውብ ከተማ
ባንድ ጎንህ ብርሃን―በሌላው ጨለማ
ግማሽን ገልጠህ―ግማሽህን ግጠም
ልክ እንደ ጨረቃ―ተደበቅ ግድየለም
ይበቃኛል በርግጥ―ግማሽህን ማየት
ግማሽ በመሆኑ―ሰው የመሆን እዉነት

በክፍል 13 ‹‹የዶ/ር መረራና በእውቀቱ መንገድ!›› እንመለከታለን
ቸር እንሰንብት!!!  

በደ/ማርቆስ ከ1000 በላይ ዐማሮች ታስረዋል፤ ነገም የተጋድሎ ሰልፍ ይኖራል • በከሚሴ መሣሪያ እየተነጠቀ ነው • በአርማጭሆ ከፍተኛ መጠን ያለው ጦር ገብቷል

deremarkosዐማራ እንዴት ዋለ? ነሃሴ 7 ቀን 2008 ዓ/ም
• በከሚሴ መሣሪያ እየተነጠቀ ነው
• በአርማጭሆ ከፍተኛ መጠን ያለው ጦር ገብቷል
• በወልዲያ፣ ደሴ፣ ኮምቦልቻ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ሞጣ፣ ፍኖተ ሰላም፣ ደብረ ብርሃንና ሌሎች ከተሞች ነገ የተጋድሎ ሰልፍ ይጠበቃል
• የሚታሰሩ ዐማሮች ቁጥር ጨምሯል፣ ገበሬዎች ወደ ከተማ እንዳይገቡ እየታገዱ ነው

ደብረ ማርቆስ፤ በደብረ ማርቆስ ከተማ በርካታ የአጋዚ ወታደሮች ከተማዋን ወረዋት ቢዉሉም ሞትን የማይፈሩት የበላይ ዘለቀ ልጆች ለተጋድሎ ሰልፍ ወጥተዋል፡፡ ከጠዋቱ 4፡30 አካባቢ የተጀመረው የተጋድሎ ሰልፍ እስከ 8፡00 እንደቆየ ለማወቅ ችለናል፡፡ ከከተማዋ ሦስት የተለያዩ አቅጣጫዎች የነበረውን ሰልፍ ለመበተን ጥረት ተደርጓል፡፡ በሰልፉ ሁለት ዐማሮች የተሰው ሲሆን ቁጥሩ ወደ አራትም ሊያሻቅብ እንደሚችል ተገልጧል፡፡

በደብረ ማርቆስ ከተማ ከሕዝብ ጎን ተሰልፏል የተባለ አንድ የዐማራ ፖሊስም በአጋዚ ጦር መገደሉን ከቦታው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ በደብረ ማርቆስ በአጋዚ የተገደሉት ዐማሮች በድብደባ እንደሆነ ነው መረጃ ያቀበሉን ሰዎች የገለጹት፡፡ በጥይት በርካታ ሰዎች ቆስለዋል፡፡ ይህን ተከትሎ ከሰአት በኋላ ከሁለት መቶ በላይ የሚሆኑ የማርቆስ ወጣቶች በቀበሌ 03 አስተዳደር ጽ/ቤት መታሰራቸው ታውቆ ነበር፡፡ ከመሸ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው በከተማዋ የታሰሩ ሰዎች ብዛት ከ1000 እንደሚበልጥና የፖሊስ ጣቢያዎችና የቀበሌ ጽ/ቤቶች ሁሉ በመጥበቡ ምክንያት ሲኒማ አዳራሽ ተዘግተዋል ተብሏል፡፡

በደብረ ማርቆስ ነገም የተጋድሎ ሰልፍ እንደሚኖር የሚጠበቅ ሲሆን ዛሬ ከተሰሙት መፈክሮች ‹‹እንኳን ለወልቃይት ለባድመስ ታግለን አይደል!›› የሚለው የማኅበራዊ ሚዲያውን ተቆጣጥሮ ውሏል፡፡
ከሚሴ፤ በከሚሴ ያሉ ዐማሮች መሣሪያቸውን እየተገፈፉ እንደሆነ በጠዋት ነው መረጃው የደረሰን፡፡ የተጋድሎ ሰልፉን ያስተባብራሉ የሚባሉትን ወጣቶች እንደታሰሩም ለማወቅ ችለናል፡፡

አብደራፊ/አብራጂራ፤ ወደ ምዕራብ አርማጭሆ አብደራፊና አብራጂራ ከተሞች ከሦስት አቅጣጫዎች የመከላከያ ሠራዊት ከነሙሉ ትጥቁ ሲገባ መሰንበቱን ለማወቅ ችለናል፡፡ በሶረቃ በኩል የገባው የመከላከያ ሠራዊትና ትጥቅ 8 ኦራል እና 5 ዘመናዊ ታንኮች ሲሆን በመተማና በኹመራ በኩል የገባው የጦር መጠን ከዚህ የዘለለ ነው ተብሏል፡፡ ለምን ዓላማና እንዴት እንደገባ ለጠየቅናቸው ጥያቄ ‹‹በቄስና በመነኩሴ እያስገዘቱ ለይቅርታ ነው የመጣነው ቢሉም አሁን ላይ ግን ዐማሮችን ማደን ይዘዋል›› ሲሉ ገለጸዋል፡፡

አጠቃላይ፤ በወልድያ፣ ደሴና ኮምቦልቻ፣ ደብረ ብርሃን፣ ደጀን፣ ሞጣ፣ ብቸና፣ ፍኖተ ሰላም ከተሞች ወጣቶች በብዛት እየታሰሩ እንደሆነ ነው መረጃዎች የሚደርሱን፡፡ በወልድያ የሰሜን ወሎ የብአዴን ኃላፊ አቶ አበባው ሲሳይና የቅጥረኛ ካቢኔዎቹ በርካታ ወጣቶችን ፒያሳና አዳጎ በሚባሉ ሰፈሮች እንዳሳሰሩ ለማወቅ ችለናል፡፡ በግል ቢዚነስ የሚንቀሳቀሱ ብሎም የመንግሥት ሠራተኛ የሆኑ ሰዎች ሁሉ ይገኙበታል፡፡ በደሴና በኮምቦልቻ ከተማዎች ለነገ ሠልፍ ይኖራል በሚል የፈሰሰው የአጋዚ ጦር መጠን ብዛት አለው ተብሏል፡፡

በደሴ ከተማ በቀን ሥራና በሊስትሮነት የተሠማሩ ልጆችን ፖሊሶች በመዞር እያስፈረሙና እየመዘገቡ ነገ ሰልፉ ላይ ብትገኙ ወዮላችሁ ስማችሁን መዝግበናል እያሉ ውለዋል፡፡ በኮምቦልቻ ከተማ ደግሞ የቀን ሠራተኞችንና የኔ ቢጤዎችን እስከ ቅዳሜ ድረስ ሠርታችሁ ከተማ መገኘት የለባችሁም፤ ቦርከና ወንዝ ልብስ ስታጥቡ ዋሉ ተብለዋል፡፡

በምስራቅ ጎጃሟ የብቸና ከተማ ዛሬ ማንኛውም ዓይነት የንግድ እንቅስቃሴ ባንክን ጨምሮ ዝግ ሆኖ ውሏል፡፡ ከገጠር ወደ ከተማ የሚመጡ አርሶ አደሮች እንዳይገቡም ተከልክለዋል፡፡ የዐማራን ሕዝብ ለመግደል የተመደቡት የአጋዚ ጦር አባላት የሚመገቡት በከተመዋ ከሚገኘው ‹‹ጽጌረዳ ሆቴል›› እንደሆነ ነው የተነገረን፡፡ በሞጣ፣ በደጀን፣ በዕድውኃ፣ በፍኖተ ሰላም ከገጠር የሚመጡ ገበሬዎች እንዳይገቡ መከልከላቸው ተሰምቷል፡፡
ከመንዝ ላሎ እና ማማ ምድር ወደ ደብረ ብርሃን የሚመጡ ገበሬዎች ላይ ከፍተኛ ፍተሻና ወከባ እንዳለም ለማወቅ ችለናል፡፡
ይህ ሁሉ የመጨረሻው መጀመሪያ ነው::

ሕወሓት ለፕሮፓጋንዳው እንዲጠቅመው የትግራይ ተወላጆችን ከጎንደር በአውሮፕላን ማስወጣቱን ቀጥሎበታል

tigraiየትግTigrai2ራይ ሕዝብ ተነጥሎ በጎንደር ጥቃት እንደደረሰበት ለማስመሰልና ፕሮፓጋንዳ ለመሥራት እንዲመቸው በጎንደር የሚገኙ የትግራይ ተወላጅ ነጋዴዎችንና የተመረጡ ነዋሪዎችን በአውሮፕላን ማስወጣቱን ቀጥሎበታል::
ሕወሓት በትግርኛ የሚያስተላልፋቸው መርዘኛ መልዕክቶቹ “አማራው ትግሬን ለማጥፋት ተነስቷል” የሚል ሲሆን አንዳንድ የትግራይ ተወላጆችም በዚህ መርዘኛ ፕሮፓጋንዳ እየተታለሉ መሆኑ በግልጽ እየታየ ነው:: በተለይ በጎንደርም ሆነ በባህርዳር ዛሬም በደብረማርቆስ የወጣው ሰላማዊ ሰልፈኛ በትግራይ ነጻ አውጪ ሠራዊት ጥይት ሰለባ እየሆነ ሕዝቡ የሚናገረው “ጠላታችን ሕወሓት እንጂ የትግራይ ሕዝብ አይደለም” ቢልም ሕወሓት ግን ሆን ተብሎ የአማራው ሕዝብ የትግራይ ሕዝብን ሊያጠፋ ተነስቷል የሚል ፕሮፓጋዳ ሥራዎች ውስጥ መጠመዱ በይፋ ታይቷል::
በጎንደር ተቃውሞ ንብረታቸው በብዛት የወደመባቸው ለሕወሓት መንግስት ተላላኪ የሆኑ አማሮች ቢሆንም ሕወሓት ግን በትግርኛ ለትግራይ ሕዝብ የሚያስተላልፈው መረጃ የትግራይ ተወላጆች ንብረት ብቻ እንደወደመ ነው:: በዚህም መሰረት ሕዝብን ከሕዝብ ለማቃቃር ተግቶ የሚሰራው ሕወሓት ከጎንደር ትግራዮችን በአውሮፕላን እያስወጣ ፎቶዎችንም በሶሻል ሚድያዎች በመልቀቅ ለትግራይ ሕዝብ ቆሚያለው የሚል ፕሮፓጋንዳውን እየነዛ ነው::
በጎንደር ሰላማዊ ሰልፈኛው ማንኛውም ለ ስር ዓቱ እስካላቃጠረና ሕዝብን እስካላስጠቃ በሰላም መኖር ይችላል የሚል ጠንካራ መልዕት መስተላለፉ አይዘነጋም::

Friday, August 12, 2016

ቅኝ ተገዥነቱን ያወቀ ሕዝብ በከፊል ነፃ ነው! – ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት

ሐሙስ ነሐሴ ፭ ቀን ፪ሺህ፰  ዓ.ም.              ቅፅ ፬ ፣ ቁጥር ፳፩
Moresh-901.jpgየኢትዮጵያ ሕዝብ በትግሬ ወያኔ ቅኝ ተገዥ ከሆነ ድፍን 25 ዓመት ሆነው። በእነዚህ ረጅም ዓመታት፣ የተማሩትም ሆነ ያልተማሩት ዜጎች፣ በቅኝ ተገዥነት መያዛቸውን ያወቁትም ሆነ ለማወቅ የጣሩት በጣም ጥቂቶች ናቸው። እነዚህ በቅኝ ተገዥነት ተይዘናል ያሉት የጥቂቶቹ ድምፅ፣ በብዙኃኑ፣ ከሁሉም በላይ በጎሣ ፖለቲከኞቹ ድምፅ ተውጦ፣ ወያኔ፣ ያላንዳች ሀግ ባይ፣ ሩብ ምዕተ ዓመታት  የአገሪቱን ብሔራዊ ጥቅምና ሉዓላዊነት በእጅጉ የጎዱ ሥራዎችን እንዲሠራ ሠፊ ዕድል ሰጠው። በመሆኑም የኢትዮጵያዊነት አያያዥ ማገርና ወራጅ፣ መሠረትና ጭምጭም የነበሩትን፣ የኢትዮጵያዊነት ዕሴቶቻችን ከሥራቸው ነቀላቸው። ሕዝቡን በነገድ ከፋፍሎ እሣትና ጭድ አደረጋቸው። የኢትዮጵያ ነገዶች ሙጫ በመሆን ከሌሎች ነገዶችና ጎሣዎች ጋር ሰምና ፈትል ሆኖ፣ ኢትዮጵያዊነትን ሲገነባ የኖረውን የዐማራ ነገድ፣ በዘር ጠላትነት ፈርጆ፣ የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል ፈጸመበት። አምስት ሚሊዮን ዐማራ ከምድረ ኢትዮጵያ እንዲጠፋ ተደረገ። በወለጋ፣ በኢሉባቡር፣ በከፋ፣ በሐረርጌ፣ በጎጃምና በጎንደር ይኖሩ የነበሩትን ዐማሮች በግፍ ሀብት ንብረታቸውን ነጥቀው ለርሃብ፣ ለድህነትና ለአገር አልባነት አሳልፎ ሰጣቸው። ይህ ዓለም በዝምታ እየተመለከተው ያለው የዘር ጥቃት፣ ዛሬ የጥቃቱ ሰለባ የሆኑት ዐማሮች የቅኝ አገዛዙን ሰንሰለት በጣጥሰው፣ ፍፁም ነፃ የሆነ ዐማራዊ ማንነታቸውን አረጋግጠው፣ የኢትዮጵያን ትንሣዔ ለማብሰር ከአፋኙ የወያኔ የስለላና የአፈና መዋቅር ኃይል ጋር የሞት ሽረት ትግል እያደረጉ ይገኛሉ።
የዐማራው ነገድ ዛሬ በትግሬ ወያኔ ቅኝ ተገዥ መሆኑን ከማወቅ አልፎ፣ ለነፃነቱ ቆርጦ የሕይዎት መስዋዕትነት እየከፈለ ነው። በዚህ የሞት ሽረት ትግል ውስጥ፣ እስካሁን በጎንደር ከተማ፣ አዘዞ፣ ቆላድባ፣ አርማጭሆ፣ ጠገዴ፣ ጠለምት፣ ወልቃይት፣ ጋይንት፣ ደብረታቦር፣ ባሕር ዳር ወዘተርፈ ቁጥራቸው ገና በውል ያላወቅናቸው አያሌ ወንድምና እህቶቻችን ባልሞ ተኳሾች የጥይት አረር ወድቀዋል። በርካቶቹ በወያኔ እስር ቤቶች የመከራን ጽዋ እየተቀበሉ ነው። ዐማራውን ለዚህ ግፍ ያበቁት በወያኔ የመከላከያ፣ የፖሊስና የፀጥታ ሠራቶች የተቀጠሩ ብቻ ሳይሆኑ፣ ከሕዝቡ ጋር የሚኖሩት በየኮንዶሚኒየሙ በሰፈራነት የተሰገሰጉት ትግሬዎች መሆናቸውን ስንገነዘብ፣ «ለካ እስከ ዛሬ በጉርብትናም ሆነ በጋብቻ ከእነዚህ ሰዎች ጋር የፈጠርነው ግንኙነት፣ እኛን ለማጥቂያ ውስጣችንን ገልጠው እንዲያዩን ሁኔታዎችን ያመቻቸ ነው፤» ብለን እንድናስብ አስገድደውናል።
ባሕር ዳር እና ጎንደር በጥይት ለተቀጠፉት ሰዎች ገዳዮቹና አስገዳዮቹ በከተሞቹ ነዋሪ የሆኑት የወያኔ የውስጥ አርበኛ ትግሬዎች መሆናቸውን በተጨባጭ አረጋግጠናል። ይህም «ወያኔን እና ትግሬን ለዩ» ለሚሉ የዋሕ ፖለቲከኞችና የሰብአዊ መብት ጠበቆች ነን ለሚሉ ሁሉ የሚያራምዱት ሀሳብ መሠረት የሌለው መሆኑን አሳይቷል። ሕዝብን በሙሉ የክፋት ሥራ ተጠያቂ ማድረግ ተገቢ አይደለም የሚባለው፣ ሕዝቡ የጥፋት ተባባሪ አይደለም ከሚል መነሻ ሳይሆን፣ ሕዝብን በሕዝብነቱ መወንጀልም ሆነ ለጥፋቱ ተጠያቂ ማድረግ ለችግሮቹ ዘላቂ መፍትሔ አያስገኝም ከሚል መነሻ እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል። ዛሬ የትግራይ ሕዝብ በወያኔ አገዛዝ ተጠቃሚ መሆኑ ጥያቄ ውስጥ የሚገባ አይደለም። ሌላውን ቁሣዊና ለወዲፊቷ ትግራይ ልማትና ዕድገት የተሠሩትን መጠነ ሠፊ ሥራዎች ትተን፣ በአገዛዙ ባለሥልጣኖች እንደ ዐማራውና ኦሮሞው አይጠረጠሩም፣ አይፈተሹም፣ በሥራቸው የመረጃ ታኮ አይለጠፍባቸውም፣ የመሥራትና የመንቀሳቀስ መብታቸው የተገደበ አይደለም፤ የፈለጉትን  ሠርተውና ተናግረው በሰላም ተኝተው ያድራሉ። ይህ ጥቅም አይደለም የሚል ካለ፣ ይህን መብት ያጡት የዐማራ ልጆች ጥቅሙ ከቁሣዊ አልፎ የኅልውና እና የነፃነት ዋጋ ያለው መሆኑን እየከፈሉት ባለው የደምና የሕይዎት ዋጋ ሊማር ይገባዋል።
ከሁሉም በላይ፣ የትግራይ ሕዝብ፣ ልጆቹ የሁሉም ነገር አድራጊና ፈጣሪዎች መሆናቸውን ስለሚያውቅ፣ በልጆቹ ድርጊት ይመካል። ከመመካትም አልፎ እየኮራ ሌሎችን ሲያዋርድ እያየን ነው። ይህም ለአጉል ትዕቢት ዳርጎት ሌሎችን «ሽንታም፣ ፈሪ» በማለት  በየምርመራ ጣቢያውና በየፓልቶክ ክፍሉ የምንሰማው የዕለት ተዕለት ስድባቸው ነው። ይህ ድርጊት የሌሎችን ነገድ ልጆች አዕምሮ አያነቁርም፣ ደም አያፈላም፣ አያስቆጭም የሚል ካለ «ግሞ ሲሉህ፣ ጥንቦ በለው» ተብሎ ያላደገ የማንነት መገለጫ ዕሴት የሌለው፣ የተዋራጅ ሕዝብ ባህል ብቻ ነው። በመሆኑ፣ ከ25 ዓመታት ትዕግሥትና የአብሮነት ፍላጎት በመነጨ፣ ዐማራው ወያኔ የጣለበትን ዕዳ፣ ያሸከመውን የመከራ ቀንበር ተሸክሞ መቆየቱ ግልጽ ነው።
የዐማራው ሕዝብ ዛሬ ግን ከመከራ አልፎ፣ ማንነቱን በመነጠቁ «አሻፈረኝ፣ መከራው በዛብኝ፣ ሸክሙ ከምችለው በላይ ሆነብኝ፣ ግፉ ከአናት በላይ ወጣ፣» ብሎ ማንነቱን ለማስከበርና ነፃነቱን ሙሉ በሙሉ ለማስመለስ ከአፋኙ የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ ሠራዊት ፊት ለፊት በባዶ እጁ እየተጋፈጠ ይገኛል። ይህም ዐማራው በቅኝ ቅዛት መያዙን ከማወቅ አልፎ፣ ለነፃነቱ ቁርጠኛ ውሣኔ ላይ የደረሰ መሆኑን ያሳያል። ካልቆረጡ ከግብ አይደረስምና! በዚህ ረገድ የቁርጠኝነቱን ጉዞ፤ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ በከፈተው የጀግንነት ድርጊት፣ ለዐማራው ወጣት አርአያነቱን አሳይቷል። ዐማራው ማንነቱን አስጠብቆ የኢትዮጵያ ትንሣዔ አብሳሪ የሚሆነውም በዚህ መንገድ ብቻ መሆኑን የትግሬ-ወያኔ ባሕሪ አስተምሮናል። ስለዚህ ትግሉ፣ መስዋዕትነትን ቀንሶ፣ ባጭር ጊዜ ውስጥ የድሉ ባለቤት የሚሆንበትን መንገድ መከተል ብልኅነት ብቻ ሳይሆን፣ አዋቂነትም ነው።
ለዚህም የሚረዳው፣ በየቀበሌውና ወረዳው የጎበዝ አለቆችን በመምረጥ የተደራጁ ቡድኖችን መፍጠር ሲቻለው ነው። በየደረጃው የተመረጡ የጎበዝ አለቆች በተመሳሳይ መልክ ከሚደራጁ አቻዎቻቸው ጋር ተያያዥና ተጋጋዥ የሆኑ ሥራዎችን ለመሥራት ሁኔታዎች በፈቀዱት መጠን የግንኙነት ሰንሰለት መፍጠር እጅግ አስፈላጊና ጠቃሚም ነው። ይህ ግንኙነት በአስተማማኝ ሁኔታ ከተመሠረተ በኋላ፣ የወያኔን የስለላና የአፈና መዋቅር ኃይል ለማሳሳት፣ የገንዘብ አቅሙን ለማዳከም፣ በተለያዩ ቦታዎች የሕዝባዊ እንቢተኝነቱ እንቅስቃሴን፥ ሰልፍና የመሳሰሉን፣ ማካሄድ። ለትግሬ-ወያኔ አፋኝ ኃይል፣ የኃይል ምንጭ፣ የሥንቅና የትጥቅ አቅርቦት ክምችት ያለባቸውን ቦታዎች በማጥናት ድንገተኛ ወረራ በማድረግ የሕዝብ ማድረግ የግድ ይላል። ይህ ሁሉ ሲሆን፣ አመራሩ ከውስጥ ከሕዝቡ መሀል ያሉ፣ የንቅናቄው ተሳታፊዎች አምነው የመረጧቸውን እንጂ፣ ከርቀት «መንፈስ ነን» የሚሉ የአየር በአየር የፖለቲካ ሰዎች ነን ከሚሉት ጋር እንቅስቃሴው እንዳይያያዝ ጥንቃቄ መደረግ አለበት። «የአህያ ባል ከጅብ አያድንም» እና በዚህ ረገድ ብርቱ ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ ነው። ወያኔ እንኳን ሰበብ አገኝቶ፣ ራሱ ወንጀል ፈብርኮ፣ ሰዎችን ማሰር መግደሉ ይታወቃልና፣ ከውጭ ሆነው የሚፎክሩ ድርጅቶች፣ ለሕዝቡ መመቻ፣ መረጃ እየሰጡ ናቸውና በወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ ባለቤቱ ዐማራው ራሱ እንጂ፣ ሌሎች አለመሆናቸውን በግልጽ ሊያውቁት ይገባል።
በመሆኑም የወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ የመላው ዐማራ ጥያቄ በመሆኑ፣ የጎንደር፣ የጎጃም፣ የወሎ፣ የሸዋ፣ የሐረርጌ፣ የአዲስ አበባ፣ የወለጋ፣ የአርሲ፣ የከፋ፣ የጋሞጎፋ፣ የሲዳሞ፣ የባሌ እንዲሁም በዓለም ላይ በስደት የሚኖረው ዐማራ የትግሉ አካል እንዲሆን፣ የንቅናቄው አስኳል የሆነው የወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ አስተባባሪ ኮሚቴ የመሪነቱን ቦታ በመያዝ፣ ሕዝቡን መድረስ ይጠበቅበታል። ከሁሉም በላይ የእንቅስቃሴው ባለቤቶች «እኛ ነን፣ እኔ ነኝ» ለሚሉ ወገኖች አቅማቸውንና ቁርጣቸውን እንዲያውቁ፣ የንቅናቄውን ዕለታዊና ሳምንታዊ ዘገባዎች ለዓለም ማኅበረሰብ የሚሰማ፣ ሕዝቡ የሚፈልገውን ርዳታ ተቀብሎ በትግሉ ውስጥ ላሉት አመራሮች ማስረክብ የሚችል ታማኝ ግለሰብ ወይም ቡድን ካለ እርሱን፣ ከሌለ በፍጥነት ተሰይሞ፣ ሕዝቡ እንዲያውቀው ቢደረግ ውንዥንብሩን ያጠራዋል፤ የሰከነ ሥራም ለመሥራት ያስችላል ብለን እናምናለን።
ሌለው፣ ንቅናቄው ሊመራባቸው የሚገቡ ቋሚ መፈክሮች ያሹታል። መፍክሮቹን ማንም እንደፈለገ እንዳይለጥጣቸው ከወልቃይት ጠገዴና ከዐማራ ማንነት ጋር የተያያዙ፣ ይህንም ባጭሩ መልዕክት የሚያስተላልፉ ሊዘጋጁ ይገባል እንላለን። ይህ ሲሆን ጎንደር ላይ የተቀጣጠለው የዐማራ የማንነት ጥያቄ፣ ቅኝ ገዥውን ቡድን ድባቅ መትቶ፣ ዐማራው ማንነቱናና ኅልውናውን አስጠብቆ፣ የኢትዮጵያን ነፃነት ዕውን ለማድረግ የበኩሉን አስተዋፅዖ ያደርጋል ብለን እናምናለን። በዛሬዪቱ ኢትዮጵያ የዕውቀትም ሆነ የሀብት ባለቤቶች እነርሱ መሆናቸው ስለሚታወቅ፣ በዚህ ነፃነት ከማንም ይልቅ ተጠቃሚዎቹ ትግሬዎች ይሆናሉ። ስለዚህ በነገይቱ ኢትዮጵያ ትግሬዎች ያላቸውን ዕውቀትና ሀብት በሥራ ላይ አውለው በነፃነት ለመጠቀም፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከወያኔ ነፃ መውጣቱ ፍቱን አብነት ነው። ለዚህም ከጠፊው የወያኔ ቡድን ጋር ሳይሆን፣ ከዘላለማዊው የኢትዮጵያ ሕዝብ እና ከታሪክ ጋር መቆም ይጠበቅባችኋል።
ወያኔ ለትግሬም ሆነ ለኢትዮጵያ አጥፊ እንጂ፣ አልሚ አይደለም። የትግራይ ተወላጆች፣ በጊዜአዊ ሥልጣንና ጥቅም ተገብዛችሁ ሊሆን ይችላል፤ ይህ ግን ዘላቂ አይደለም። ከዘላቂ ጥቅም፣ ክብር፣ ማንነትና ከሠፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር እንድትቆሙ ጥሪያችን እናቀርባለን።

ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!
የዐማራነት ማንነት በትግላችን ያብባል!
ዐማራነት ነፃነትና ዕኩልነት ነው!                                        
ዐማራነት ፍትሕና ኢትዮጵያያዊነት፣ ጀግንነትና መስዋዕትነት ነው!

በፍራንክፈርት፣ በስቶክሆልም፣ በለንደን፣ በጄኔቫና በኦስሎ ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን የተላለፈ አስቸኳይ ጥሪ

Oromo amhara unityየሀገራችንን ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታና ወገኖቻችን እየከፈሉ ያሉትን ከፍተኛ መስዋዕትነት ለመደገፍ፣ ለማበረታታትና አጋርነታችን ለማሳየት ከአገር ውጭ በማንኛውም የአለም ክፍል የምንገኝ ኢትዮጵያውያን ከዚህ በታች የሚከተሉትን እንቅስቃሴዎች ለማድረግ ተዘጋጅተናል።

1ኛ: የሻማ ማብራት መርሐ ግብር
የፊታችን አርብ ኦገስት 12 ቀን 2016 ዓ/ም ኢትዮጵያውያን በብዛት በሚኖሩባቸው በዋና ዋና ከተሞች በህወሀት አጋዚ ጦር በጥይት ተደብድበው በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች ውድ ሕይወታቸውን ያጡትን ሰማዕታት ለመዘከር የሻማ ማብራት ፕሮግራም ማካሄድ፣
2ኛ: የፊታችን እሁድ ኦገስት ቀን 2016 ዓ/ም በሁሉም የእምነት ተቋማት ለነዚሁ ሰማዕታት ፀሎተ ፍትሃት ማድረግ፣
3ኛ: ከፊታችን አርብ ኦገስት 12 ቀን እስከሚቀጥለው አርብ ኦገስት 19 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ በዋና ዋና ከተሞች ጨፍጫፊውን የህወሃት ስርዓት ለመቃወምና የሰፊውንና የነፃነት ፈላጊውን የኢትዮጵያ ህዝብ እልህ አስጨራሽ ትግል ለመደገፍ እንዲሁም አጋርነታችን ለማሳየት ታላቅ ትዕይተ ህዝብ ማድረግ፣
4ኛ: ከህወሃት ወያኔ የዘረኛ አገዛዝ ለአንዴና ለመጨረሻ ለመገላገል አደባባይ ሲወጡ በአጋዚ ጦር በጥይት ተደብድበው መተኪያ የሌላት ህይወታቸውን መስዋዕት ላደረጉ ወገኖቻችን ቤተሰቦች መርጃ የሚሆን ገንዘብ የማሰባሰብ፣
5ኛ: በአጋዚ ስናይፐር፣ መትረየስና ክላሽ ተደብድበው በየሆስፒታሉና መኖሪያ ቤታቸው የተኙ ወነገኖቻችንን ለማሳከምና
6ኛ: በህወሃት ማጎሪያ ቤቶች በአማራ፣ በኦሮሚያና አዲስ አበባ ታስረው የሚገኙ ዜጎቻችንን በስንቅና በሞራል ልንደግፍባቸው የምንችልባቸውን መንገዶች ለመወያየት ከፊታችን አርብ ኦገስት 12 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ በተለያዪ የመወያያ መንገዶች ውይይት ለማድረግ ተዘጋጅተናል።
በዚህ መሰረት እስካሁን ሰላማዊ ሰልፍ ሊደረግባቸው የታቀዱ ከተሞች:
አርብ ኦገስት 12 ቀን 2016 ዓ/ም
በጀርመን ፍራንክፈርትና በስዊድን ስቶኮልም
ሰኞ ኦገስት 15 ቀን 2016 ዓ/ም
በእንግሊዝ ለንደን
ማክሰኞ ኦገስት 16 ቀን 2016 ዓ/ም
በስዊዘርላንድ ጄኔቫ
አርብ ኦገስት 19 ቀን 2016 ዓ/ም
በኖርዌይ ኦስሎ
ሲሆኑ በሌሎች የአለማችን ታላላቅ ከተሞችም ታላቅ ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፎችን ለማድረግ እንቅስቃሴዎች በመደረግ ላይ ናቸው።
ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን መርሃ ግብሮች ስኬታማ ለማድረግ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በሚኖርበት አካባቢ ተሳታፊ እንዲሆን ጥሪያችንን እናቀርባለን።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ

Thursday, August 11, 2016

የጉራጌ ወጣቶች ለእሁድ ነሐሴ 15 በወልቂጤ እና ቡታጅራ ከተሞች ተቃውሞ ጠሩ

Bilderesultat for gurage ethiopia region“ለእሁድ ነሐሴ 15 የቡታጅራ እና ወልቂጤ ከተማ ነዋሪዎች ተዘጋጁ” ይላል ለዘ-ሐበሻ የደረሰውና በጉራጌ ከተሞች እየተበነ ያለው ወረቀት:: “ላለፉት 25 ዓመታት በስልጣን ላይ ያለው የትግራይ መንግስት ቤተጉራጌን በማፈራረስና የጉራጌ ነጋዴን ከገበያ በማውጣት ያደረሰው በደል የተሰማችሁ ሁሉ እንዲሁም በኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች ወንድም እና እህቶቻችሁ መገደል ያንገበግባችሁ እሁድ ነሐሴ 15 በወልቂጤና ቡታጅራ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ ለመውጣት ተዘጋጁ” ይላል የተበተነው ወረቀት::

መንግስት በጉራጌ ማህበረሰብ ላይ የሚያደርሰውን በደል እና በሃገሪቱ ውስጥ እንደ እኩል ዜጋ ሳይቆጠር ከንግድ እንዲወጣ መደረጉ ያንገበገባቸው የጉራጌ ወጣቶች እሁድ ነሐሴ 15, 2016 በሚያድርጉት ተቃውሞ ላይ የተለያዩ ሃገራዊ መፈክሮችን ይዘው ይወጣሉ ተብሎ ይጠበቃል::
በአዲስ አበባ በተለምዶ መርካቶ በሚባለው አካባቢ ድሮ የጉራጌ ነጋዴዎች ይበዙ የነበሩ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ግን ዙሩ ተገልብጦ የንግድ እድሉ በጠቅላላ ለትግራይ ተወላጆች ተሰጥቶ ጉራጌ ከመርካቶ ወጥቷል:: ቤተጉራጌም ሕወሓት በሚመራው መንግስት እንዲዳከም መደረጉ ይታወሳል::

እሁድ በደብረብርሃን ይደረጋል የተባለው ሰልፍ ያስፈራው የሕወሓት መንግስት ዛሬ የባጃጅ ሹፌሮችን ሰብስቦ ሲያስፈራራ ዋለ

የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ከስብሰባው ያነሱት ፎቶ(ዘ-ሐበሻ) የፊታችን እሁድ በደብረብርሃን ከተማ ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀው ሰላማዊ ሰልፍ ያስፈራው የትግራይ ነፃ አውጪ መንግስት ዛሬ የደብረብርሃን የባጃጅ ሹፌሮችን ስብሰባ ጠርቶ ‘በ እሁዱ ሰልፍ ላይ እንዳትሳተፉ; በእሁዱ ሰልፍ ላይ የሚገኝ የባጃጅ ሹፌር ፈቃዱን ይነጠቃል” እያሉ ሲያስፈራሩት እንደዋሉና ተሰብሳቢው ግን ፊቱን እንዳዞረባቸው የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ከስፍራው በፎቶ ግራፍ አስደግፈው በላኩት መረጃ ጠቁመዋል::
ዛሬ በደብረብርሃን ከተማ ምንም ዓይነት የባጃጅ ትራንስፖርት አልነበረም ያሉት እነዚሁ የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች በወልቃይት ጉዳይ ጥያቄ እንዳታነሱ; በጎንደርና በባህር ዳር የተደረገውን የህዝብ ተቃውሞም እንዳትደግፉ; ያንን የሚደግፉ ጸረ ልማቶች ናቸው የሚሉ ማስፈራሪያዎች ከመድረኩ ተሰምቷል::
የባጃጅ ሹፌሮቹ በጎንደርና ባህርዳር ሕዝብ ያነሳውን ጥያቄ አውግዙ ሲባሉ እምቢ ቢሉም የሕወሃት መንግስት ግን “በደብረብርሃን ያሉ የባጃጅ ሹፌሮች በጎንደና ባህርዳር የተደረገውን የሕዝብ ተቃውሞ አወገዙ” የሚል ዜና ከመስራት እንደማይቆጠብ ታዛቢዎች ይናገራሉ::
በደብረብርሃን ወጣቶችን ሳይቀር ቤት ለቤት እሁድ ሰልፍ እንዳትወጡ እያሉ እያስፈራሩ ነው ያሉት ዘጋቢዎቻችን አብዛኛው ሕዝብ ግን እሁድ ሰልፍ ከመውጣት የሚያግደን ምንም የለም የሚል አቋም እንደያዘ ለመረዳት ተችሏል::