OPPOSITION PARTIES WEBSITES

ETHIO NEWS & VIEWS

RADIO & TV

Saturday, August 13, 2016

የማንቂያ ደውል።- ዳዊት ዳባ

Bell-123909540w1በሀገራችን እየተካሄደ ያለው ህዝባዊ እንቢተኝነት የነፃነት የእኩልነት የፍትህና የኢኮኖሚ ጥያቄ መሆኑን ሁሉም የሚገነዘበው መሆኑ ቢታወቅም፤ ትግሉ የህዝባችንን ጥያቄ በመለሰ መልኩ እንዲጠናቀቅ ምን  ይጠበቃል የሚሉትን ከብዙዎቹ ጥቂቶቹን ለመዳሰስ እንሞክራለን።
የፖለቲካ ድርጅቶች፤- የህዝባችንን ጥያቄ በሀይልና በማሸበር ለማፈን የተለመደውን ተግባሩን ወያኔ ተያይዟል። ህዝብ እንደተፋው አሁንም ለመቀበል ዝግጁ አይደልም።  ድርጅቶች ወቅቱ የሚጠይቀውን ሀላፊነት ተገንዝባችሁ የህዝቡን ጥያቄ ግምት ውስጥ ያስገባና ለውጡን ሊሺከምና ሊያሻግረን የሚችል ብሎም ባለድርሻዎችን ሁሉ ያሳተፈ መፍትሄ እንደምትሰሩ ይጠበቃል።
ትግሉን የሚያንቀሳቅሱ ሀይላት፤- እስካሁን የሰራችሁት ስራ  የሚያመለክተው አንድ ታላቅ ነገር በዜጎች ዘንድ ለውጥ የሚታለም ብቻ ሳይሆን የሚታይ አልፎም የሚጨበጥ ማድረግ ችላችሗል።  አድካሚ የሆነው ስራና የበዛ ሀላፊነትን ለመሸከም መድፈራችሁ የአጥፊውን ወገን ያለፈበትና ያለቀለት ታክቲክ በማክሸፍ ደረጃ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል። አበው እንደሚሉት ለአንበሳ አይመትሩም ለብልህ አይመክሩም ቢሆንም ለለውጥ ፈላጊውም ሆነ ላገዛዙ አልፎም ለውጪ አገራት  ጥርት እንዲልና ዞሮ ዞሮ መዳረሻው ይህ ስለሆነም “የስርአት ለውጥ” የሚለውን የሚሰማ አድርጉት። አጨራረሱ በቅጡ ታስቦበታል ነው  ግምቱ።
ያሉን ጥቂት የመገናኛ ብዙሀን ትግሉን ያለወገንታዊነት በእኩልነት ሽፋን እየሰጣችሁ መሆኑን እርግጠኛ ሁኑ። የሚተላለፉ መልእክቶች ሆኑ ወቅታዊ ትንታኔዎች የተሳሳተ ድምዳሜ ላይ የሚያደርሱን  እንዳይሆኑ ጥንቃቄ ቢደረግም ጥሩ ነው። ሁላችንም እንደምንገነዘበው የተሳሳተ ድምዳሜ ፖለቲካዊ መፍትሄ የመስራቱን ሂደት አስቸጋሪ ያደርገዋል። በንኪያ ሰላምታ የህዝብ ትግል ይጎዳል። ጊዜው የሚሻው የሜዲያ ሽፋን አይነት ትግሉ እራሱ ነው። በመሬት ላይ የሚቀናጅበትን፤ ቀጣይ የሚሆንበትንና አዳዲስ የትግል ፈጠራዎች የሚያጭር ቢሆን ጠቃሚ ነው። መሳርያ የያዘውን የለውጡ አካል የሚሆንበትን ሂደት ማፍጠን ይቻላል። የሚሞተውንና የሚታሰረውን ሰው መቀነስ ይቻላል። ትግሉ ያልተጀመረባቸው ቦታዎች ማስጀመር ይቻላል…..ብዙ ብዙ።
ህዝባዊ ሀርነት ትግራይ፤- ህዝብ የችግሩን ምንጭ በትክክል ተገንዝቧል። “የወያኔ የበላይነት ይብቃ” ነው እያለ ያለው። አስተዳዳራዊ መዋቅሮች እየፈራረሱ ነው። አጋር ድርጅቶች በድርጅታዊ ነፃነትና እኩልነት ጥያቄ ማንቁረት ይዘዋል።  መሳርያ የያዘው እያጉረመረመ ነው። ቅሬታውን ተኩሶ እስኪገልፀው መጠበቅ ይቻላል። የሲቪል አስተዳደሩን አፍረሶ በወታደር አገዛዝ መተካት ለችግሩ መፍትሄ ተደርጓል። ኦሮሚያ ላይ ይህ ሆኗል። አማራ ክልልም በቀጣይ የሚጠበቅ ነው። ግን አልሰራም አይሰራምም። ይህ በአለማቀፍ ደረጃ የሚፈጥረው ተፅኖ እያያችሁ ነው። ትላልቆቹ ብሄረሰቦች የሚለውን እውነት የወለደው ይህው ነው።  በአጠቃላይ ቀላል የሆነ ማንቂያ ደውል ለናንተ መስቀመጥ የሚቻልበት ሁኔታ ያለ አይመስልም። ያም ሆኖ ጊዜው የሚሻውን ለየት ያለ የመፍትሄ ሀሳብን ይዞ መምጣትና መሞከር ይቻላል። መንግስታዊ ሽብር እየፈፀማችሁና ዜጎችን እየጨፈጨፋችሁ ለመዝለቅ መሞከሩ ግን የትም አያደርስም።
የወያኔ ሀርነት ትግራይ ደጋፊዎች፤- ከተለመደው ፋይዳ የሌለውን ደረቅ ክርክራችሁን አቁሙ። የህዘብ አሸናፊነት አይቀሬ ነውና አገዛዙ ያዋጣኛል ብሎ የገፋበትን  ሽብርና ጭፍጨፋ ላይ በማንኛውም መንገድ የሚገለፅ ድርሻ እያደረጋችሁ እንዳልሆነ ለራሳችሁ እርግጠኛ ሁኑ።  ሊሰሟችሁ የሚችሉ አይመስለንም።  ከቻሉ ከመንግስታዊ ሽብር እንዲታቀቡ መምከሩ ይጠቅማችሗል።  ይህ ባይሆን ግን ህዘብ በየትኛውም መሰዋትነት ድሉን ይጨብጣል። ኪሳርው በህዋዋትና በናንተ ኪሳራ ይወራረዳል።
ድል የህዝብ ነው።
ዳኮታ የጥናት ማእከል።
8/13/2016
dakotareserech2@yahoo.com

No comments:

Post a Comment