Thursday, August 6, 2015

‹‹ ጊዜ የለም አዳራሹን ለቀህ ውጣ ›› – ሐና ሙሉጌታ

Eriteriaበአንዲት ጎደሎ ቀን ም/ፕሬዝደንቱን ጨምሮ አስራ አምስት የኤርትሪያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ለኤርትሪያ ይበጃታል ያሉትን አንድ ቀና ነገር አሰቡ፤ ሃሳባቸውም ፕሬዝደንት ኢሳይያስን ከስልጣናቸው በፈቃዳቸው እንዲለቅቁ አድርገው በምትካቸው ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር ሊቀላቅላቸው የሚችል ትንሽ ትምህርት ቀመስ የሆነ ሰው በስልጣን ላይ ማስቀመጥ የሚል ነበር ይህንንም እቅድ ውስጥ ውስጡን ሲያበስሉት ቆዩና በመግቢያዬ እንደገለፅኩት በአንዲት ጎደሎ ቀን በኮድ ስሟ ‹‹ 011 ›› በተባለች አዳራሽ ተሰብስበው ፕሬዝደንት ኢሳይያስን ይጠብቃሉ ሰዓቱ 21 ፡00 ሲል ፕሬዝደንቱ ወደ አዳራሹ ገቡ ገና መቀመጫቸው ወንበሩን ከመንካቱ ጥቂት ምስጢራዊ ሰዎች ብቻ የሚያውቋት ስልካቸው ተንጫረረች አነሷት የተደወለው ከሀገሪቱ የፀጥታ መስሪያ ቤት ከፍተኛ ባለስልጣን ከአብረሃ ካሳ ነበር ስልካቸውን ወደ ጆሮአቸው አስጠጉ ‹‹ ጊዜ የለም አዳራሹን ለቀህ ውጣ ›› የሚል መልእክት ሰሙ ፤ ፊታቸው አመድ መሰለ በቀስታ ዘወር ብለው በአዳራሹ የተሰበሰቡትን አስራ አምስት የኤርትሪያ ከፍተኛ ባለስልጣናትን በዓይናቸው ቃኟቸው ሠላሳ ዓይኖች አፍጥጠውባቸዋል፤ ሹልክ ብለው በመጡበት እግራቸው አዳራሹን ለቀው ወጡ ፡፡

እነዚያ ለኤርትሪያ ሲሉ ስንት መስዋዕትነት የከፈሉ አንቱ የተባሉ ባለስልጣናት እጅና እግራቸው በካቴና ተጠፍንገው ጨለማ ቤት ተወረወሩ ታዲያ ያኔ መፈንቅለ መንግሥት ሊያደርጉብህ ነው ብለው አስራ አምስት ፊደላትን ብቻ በፕሬዝደንቱ ጆሮ አሰምተው አስራ አምስቱን ባለስልጣናት ያስበሉ የፀጥታው መ/ቤት ሹም አብረሃ ካሳ ዛሬ የወያኔ ሰላይ ሆነው በውል የተረጋገጠ 1. አዲስ አባባ ላይ ባለ አስር ፎቅ ህንጻ ፣ 2. ጋምቤላ ሰፊ እርሻ ፣ 3. አፍዴራ የጨው ማምረቻ እንዲሁም 4. አዲስ አበባ ቦሌ መድኃኒዓለም ጀርባ ቋሚ ነዋሪነቱን ሱዳን ካደረገ ነቢል አልቁሙስ (አል-ኩሙስ) ከተባለ ግብፃዊ ጋር በሽርክና ዓለም አቀፍ አስጎብኚ ድርጅት በወንድማቸው ስም ከፍተው ቢዝነሱ ውስጥ ሲጨማለቁበት በምላሹም ወያኔዎች የኤርትሪያን ፣የግንቦት ሰባትን የአርበኞች ግንባርን መረጃዎች አንድ በአንድ ሲዘረግፉ ኖረው ተደርሶባቸው በተራቸው ጨለማ ቤት ተዘግቶባቸዋል በዚህ ሁኔታም የኤርትሪያ ፕሬዝደንት ኢሳይያስ አፈወርቂ የሚይዙት የሚጨብጡት አጥተዋል ዛሬ 8/5/2015 ነሐሴ 29 ቀን 2007 ዓ.ም ከግለሰቡ ጋር ቅርብ ግንኙነት ያላቸው ዘጠኝ ሰዎች በቁጥጥር ሥር ሲውሉ የግለሰቡ ዘመዶችም ተጠቃለው በየማጎሪያው ገብተዋል በመጨረሻም አቶ ኢሳይያስ እንዲህ ሲሉ ተደምጠዋል ‹‹ ግድ የለም እናንተ ሆዳችሁን አስፉ እኛ ደግሞ አዲኳላን እናሰፋለን ›› አዲኳላ ምን ይሆን ?

No comments:

Post a Comment