ዘንድሮ የመከፋፈሉ ሂደት ቀጠለ እና ዶ/ር ቴዎድሮስ ”የኦሮሞ ዲያስፖራ” የሚል ዝግጅት በፌስ ቡክ ገፃቸው ይዘው ብቅ አሉ።የዶ/ር ቴዎድሮስ መስርያቤት የኢትዮጵያ የሚል ስም ከያዘ በኃላ ዲያስፖራን በጎጥ የመከፋፈል ሥራ ላይ ለምን ይደክማል? አምናየመስርያቤታቸው ቃል አቀባይ ስሙ የኢትዮያ ይሁን እንጂ በኢቲቪ ቀርቦ ”የትግራይ ዲያስፖራ” በዓል እያዘጋጀ መሆኑን በኢቲቪ መግለጫ ሲሰጥ መስያቤቱ የኢትዮጵያ አይደለም እንዴ? ከ 2 ሚልዮን በላይ በውጭ የሚኖር ኢትዮጵያዊን አይመለከተውም እንዴ?ብለን እንዳፈርን ይሄው ሌላ ክረምት መጣ።ዶ/ር ቴዎድሮስ መስርያ ቤት የዲያስፖራ ፅ/ቤት ግን በጎጥ መከፋፈሉንቀጠለ።ዘንድሮ በሌላው ክረምት ላይ ዶ/ር ቴዎድሮስ በፌስ ቡክ ገፃቸው ላይ ስለ ኢትዮጵያ ያወራሉ ስንል ዲያስፖራውን መከፋፈል ቀጠሉ።”የኦሮምያ ዲያስፖራ” በዓል ላይ መሆናቸውን ነገሩን።
ሌሎቻችን እንዘጋጅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲያስፖራውን በጎጥ መከፋፈል ከሆነ ስራው ለምን ”የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ከፋፋይ ቢሮ” ብሎ እራሱን አያስተዋውቅም
የቤንሻንጉል ዲያስፖራ በዓል —–
የሐረር ዲያስፖራ በዓል—-
የወላይታ ዲያስፖራ ቢሮ ——
የከንባታ ዲያስፖራ ቢሮ ——–
የአፋር ዲያስፖራ ቢሮ ———
ጥያቄው ለምን ትከፋፍሉናላችሁ? ኦባማ ሉሲን የጎበኙት ከአንድ ግንድ የመጣን ነን ብለው ኢህአዴግ/ህወሃትን ”አንድነት 101” ኮርስ ለመስጠት መስሎኝ ነበር።አንድ ሰው ኦሮምኛ መናገሩ ወይንም ትግርኛ መናገሩ የእራሱን ባህል እና ቋንቋ ከማዳበር ባለፈ በመንግስት ደረጃ ህዝብን ለመከፋፈያ ይብሱንም ከሀገሩ ተሰዶ የሀገሩ ፍቅር ዘወትር በአዕምሮው ለሚመጣ ትውልድ ላይ በጎጥ ተከፋፍለህ መምጣት አለብህ ማለት ምን ማለት ነው?
ለመሆኑ በውጭ የተወለዱ ስለ ጎጥ የማያውቁ ኢትዮጵያውያን የጎጥ መታወቂያ ይዛችሁ ካልመጣችሁ ስትሏቸው እንዴት ይዘገንናል?

No comments:
Post a Comment