Wednesday, April 20, 2016

የጋመቤላው ጭፍጨፋ፣ ምሥጢሩ ምንድን ነው? (ፕ/ር መስፍን ወልደማሪያም)

13043ይህ የመጀመሪያው አይደለም፤ የበፊቱም ሆነ የአሁኑ ጭፍጨፋ ያነጣጠረው አኑዋኮች ላይ ይመስላል፤ የፊቱ በእኛው አገዛዝ የተፈጸመ እንደነበረ ተረጋግጧል፤ የዛሬዎቹ ገዳዮች ደግሞ ሌሎች ናቸው፤ ደቡብ ሱዳን? ወሮ-በሎች? የሃይማኖት ነው ወይስ የጎሣ ጥቃት? ወይስ ሰሞኑን ከሚታየው አዲስ የትግራይ ካርታ ጋር የተያያዘ ነው? በተለያዩ አገሮች ኢትዮጵያውያን መገደላቸውን መስማት ከጀመርን ቆይተናል፤ በሜዲቴራንያን ባሕርና በቀይ ባሕር ኢትዮጵያውያን መስመጣቸውን መስማት ከጀመርን ቆየን፤ ዛሬም እየሰማን ነው፤ የጋምቤላውን ጭፍጨፋ በጣም ልዩ የሚያደርገው ሰዎቹ በገዛ አገራቸው፣ በገዛ ቤታቸው ውስጥ፣ በገዛ መሬታቸው ላይ መሆኑ ነው፤ ወይስ አገሩ፣ ማለት ጋምቤላ፣ የኢትዮጵያ አካል መሆኑ ቀርቷል? ሰዎቹ ኢትዮጵያውያን ባይሆኑም የደረሰባቸው ግፍ ኢሰብአዊ ነው፤ እስቲ የሚያውቅ ሰው ያብራራልን፡፡

No comments:

Post a Comment