Monday, July 20, 2015

ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ኤርትራ ገቡ፣የባለስልጣናት ፍጥጫ ተካሯል!

Birhanu-nega-photo-1024x577በ1997ቱ ሀገር አቀፍ ምርጫ ወቅት ቅንጅትን ወክለው ተወዳድረው በከፍተኛ ድምጽ አሸንፈው የአዲስ አበባ ከንቲባ እንዲሆኑ ተመርጠው የነበሩት ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ወያኔ የድምጽ ኮሮጆዎችን ገልብጦና ምርጫውን አጭበርብሮ ስልጣኑን በጉልበቱ ይዞ ለመቀጠል በመወሰኑ ምክንያት ከበርካታ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች እና የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች ጋር ለሁለት ዓመት ያህል በእስር ቤት እንዲቆዩ ተደርገዋል።Dr. Berhanu Nega Ginbot 7 Chairman
ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ከእስር ተፈተው ቀደም ሲል ይኖሩበት ወደነበረው አሜሪካን ሀገር ከተጓዙ በኋላ አፍታም ሳይቆዩ ነበር የሁለገብ ትግልን አስፈላጊነት መናገር የጀመሩት። ዶ/ር ብርሃኑ ወዲያውም አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጨምሮ ከሌሎች ሃሳባቸውን ከሚጋሩ ስመጥር ፖለቲከኞች እና የለውጥ አራማጅ ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን ግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄን መሰረቱ፣ በወቅቱ ዶ/ር ብርሃኑ የእርሳቸውን እና በግንቦት 7 ዙሪያ የተሰባሰቡ ጓዶቻቸውን ቁርጠኛነት ሲያስገነዝቡ “ዘረኛውን የወያኔ አምባገነን አገዛዝ ከህዝብ ጫንቃ ላይ ለማውረድ የማንፈነቅለው ድንጋይ አይኖርም” ነበር ያሉት።
11738072_899750846759450_731348357732726805_n
ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ ግንቦት 7 ጠንካራ የተዋጊ ሃይል ማቋቋም የቻለ ሲሆን ለጥቆም ቀደም ሲል ጀምሮ ወያኔን ማስወገድ የሚቻለው በሃይል ብቻ ነው በማለት መስዋዕትነት በመክፈል ላይ ከነበረው የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ጋር በመዋሃድ የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄን መፍጠር ተቻለ።
ዛሬ በወያኔ እጅ ወድቆ የሚገኘው በሳሉና ቆራጡ ታጋይ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እስካሁን ግንቦት 7 በተጓዘባቸው የስኬት ጎዳናዎች ሁሉ አሻራው እንዳለበት በቅርብ አብረውት ሲታገሉ የነበሩ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ይመሰክራሉ።
Birhanu-Nega-asmera-1024x574
በወጣት አርበኞች የተገነባውና እራሱን ለውጊያ ብቃት ሲያደራጅ የሰነበተው አርበኞች ግንቦት 7 በወያኔ ላይ ክንዱን ማሳረፍ በጀመረ ማግስት ነው እንግዲህ የንቅናቄው መሪ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እና ሌሎችም አመራሮች በአካል የትግሉን ጎራ ለመቀላቀል ወደ ሜዳ የወረዱት።
የዶ/ር ብርሃኑ ነጋንና የሌሎች አመራሮችን የትግሉን ጎራ በአካል መቀላቀል አስመልክቶ ንቅናቄው ባሰራጨው አጭር መልዕክት እንደገለጸው፣
“የተቀደሰ አላማን ያነገብን እርኩስ አላማን በሚያራምዱት ላይ ድልን እንቀናጃለን፣ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እና ሌሎችም የንቅናቄው አመራሮች የኢትዮጵያን ህዝብ ወደ ነጻነት፣ የፍትህ እና የዴሞክራሲ ጎዳና እንደሚመሩት ጥርጥር የለንም” ብሏል።
G7-Birhanu-negaBirhanu-nega-asmera-er-1024x574
አርበኞች ግንቦት 7 በወያኔ ላይ ጥቃት መሰንዘሩን ቀጥሎ ባለበት ሁኔታ የዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እና ሌሎችም የንቅናቄው አመራሮች በአካል ከአርበኞቹ ጎን መገኘት ከፍተኛ ሞራል እና መነቃቃትን ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል።

No comments:

Post a Comment