OPPOSITION PARTIES WEBSITES

ETHIO NEWS & VIEWS

RADIO & TV

Sunday, May 31, 2015

ግለሰቡ በትግራይ ክልል 6 ሰዎችን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውስጥ ገደለ

tigrai(ዘ-ሐበሻ) በትግራይ ክልል ከሚሰራበት ባንክ መስሪያ ቤት የተባረረው ግለሰብ በፊት ይሰራበት ባንክ ገብቶ 6 የባንኩን ሠራተኞች መግደሉ ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ አመለከተ:: በትናንትናው ዕለት ግንቦት 21 ቀን 2007 ዓ.ም በሰሜን ምዕራብ ትግራይ በምትገኘው ማይ ፀብሪ በተባለች ከተማ ይኸው ቀድሞ በዘበኝነት ባንኩን ያገለግል የነበረው ግለሰብ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ማይፀብሪ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅና የወንድ ዘበኛ ጨምሮ 6 የባንኩ ሰራተኞችን ሲገድል አንዲት የባንኩ ሴት ዘበኛም ማቁሰሉን የደረሰን መረጃ አመልክቷል:: እንደ ዜናው ከሆነ ይኸው ማንነቱ ያልታወቀ ግለሰብ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ቅርንጫፍ ለተወሰኑ ሰዓታት ተቆጣጥሮት ቆይቶ በመጨረሻም በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን ለዘ-ሐበሻ የመጣው መረጃ ጠቆሟል:: ሰዎቹን የገደለው ይኸው የቀድሞ የባንክ ሠራተኛ ለምን ከሥራው እንደተባረረ የደረሰን መረጃ የለም:: - 

በሀገራችን ኢትዮጵያ ስላለው ሁለንተናዊ ቀውስ በመወያየት ሁሉን አቀፍ የአማራጭ ኃይል የሚቋቋምበትን ሂደት ለመምከር ከጁላይ 2-3 በዋሽንግተን ዲሲ የሀገር አድን ጉባዔ በጋራ ይዘጋጃል -

shengoENTCየኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ፤ የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄና የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ኅብረት ጋር በተደረጉ ተከታታይ የሁለትዮሽ ውይይቶችና ስምምነቶች፡ ህዝባችን ላለፉት 24 ዓመታት ያለነፃነት በህወሓት የግፍ አገዛዝ ሥር ፍዳውን የሚያይበት ዋና ምክንያት፤ ሕዝብን መሠረት ያደረገና ብሄራዊ ጥቅምን ያስቀደመ፤ በአንድ ማዕከል የሚንቀሳቀስ ሁሉን አቀፍ የአማራጭ አካል በማቋቋም ሥርዓቱን ለማስወገድ አስፈላጊውን ትግል የማድረግ ቁርጠኝነቱ በተቃዋሚው ጎራ ያለመኖሩ ዋና ጉዳይ መሆኑን የጋራ ግንዛቤ ላይ ደርሰናል። ይህን አዙሪት በመስበርና ሁኔታዎችን በጋራ በማመቻቸት የአማራጭ ኃይሉ በአስቸኳይ እንዲቋቋም ስምምነት ላይ መድረሳችንንም በተከታታይ ባወጣናቸው የሁለትዮሽ መግለጫዎች ይፋ መሆናቸው የሚታወስ ነው።
ሥርዓቱ ባሳለፍነው ሳምንት ውጤቱ ምን ሊሆን እንደሚችል አስቀድሞ የታወቀውን የህወሓት/ኢህአዴግ የምርጫ ድራማ በማካሄድ፤ ሕዝብን ተስፋ በማስቆረጥና ግፉን አሜን ብሎ በመቀበል፤ ቀደም ሲል ሲያደረግ የነበረውን ሀገር የማፈራረስ ሂደትና የሕዝብን ስቃይ የሚያበዛ አገር በቀል የአፓርታይድ አገዛዝ ለቀጣይ አምስት አመታት ለማስቀጠል የሚያስችለውን ህጋዊ ሽፋን በማመቻቸት ላይ በሚገኝበት በዚህ ወሳኝ ወቅት፤ አገር አድን የምክክር ጉባዔ በማድረግ በሕዝብ ተቀባይነትና ታማኝነት ያለው ሁሉን አቀፍ የአማራጭ ኃይል በማቋቋም ትግሉን በተጠናከረ ሁኔታ መቀጠል ወቅታዊና አስቸኳይ ነው።
ከላይ በመግቢያው ላይ የተዘረዘሩት ድርጅቶች፤ ከተለያዩ አክቲቪስቶችና ታወቂ ግለሰቦች ጋር በመሆን ከጁላይ 2-3 የምክከር ጉባዔ በጋራ ያዘጋጃሉ። የጉባዔውን ውጤት ለማሳወቅ ሕዝባዊ ስብሰባም ይዘጋጃል። የመሰብሰቢያ ቦታ፤ ዝርዝር ፕሮግራሞችና ተያያዥ እንቅስቃሴዎችን በተከታታይ እንደምናሳወቅ ከወዲሁ መግለጽ እንወዳለን።
ስለዚህ፤ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ የፓለቲካ ድርጅቶችና የሲቪክ መኅበራት፣ የነገ ሀገር ተረካቢ የሆናችሁ ወጣቶች፤ በሀገራችን ነፃነት ሠላም እኩልነትና ፍትኅ ይሰፍን ዘንድ የምትተጉ የቴሌቪዥንና የሬዲዮ አዘጋጆች፣ የፓልቶክ ክፍሎች፣ ጋዜጠኞች፣ አክቲቪስቶች፣ ምሁራንና የሀገር ሽማግሌዎች፣ የእምነት አባቶች፤ እንዲሁም ለሀገር ደህንነት ተቆርቋሪ የሆናችሁ ዜጐች በሙሉ፤ የሚገነባው የተባበረ አማራጭ ኃይል ባለቤት እንደመሆናችሁ መጠን የሂደቱ ቀጥተኛ ተሳታፊ በመሆን፤ በሀገራችን ነፃነት እውን እንዲሆን በሚደረገው ወሳኝ ሕዝባዊ ትግል ውስጥ የበኩላችሁን አስተዋፅዖ ታበረክቱ ዘንድ፤ እንዲሁም በሕዝባዊ ስብሰባው ላይ ንቁ ተሳትፎ እንድታደርጉ አደራ እያልን በአክብሮት ሀገራዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
 
ይህ አደገኛ የቁልቁለት ጉዞ እንዲገታ በጋራ እንቁም!
የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (SHENGO)
የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት (ENTC)
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ህብረት (UEM-PMSG)
የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄ (EYNM)
 
ግንቦት 22፤ 2007 (May 30, 2015)

የጦማርያኑ እና የጋዜጠኞቹ የሃያ ዘጠነኛ የፍርድ ቤት ውሎ – ዞን9

zone9-bloggers6ከትላንትና ወዲያ በምሰክሮች እና ሲዲ ውዝግብ በይደር ተቀጥሮ የነበረው የነሶልያና ሽመልስ የክስ መዝግብ የፍርድ ቤት ውሎ ትላንትናም በተለያዬ ድራማዎች ታጅቦ ለግንቦት 25 እና ለሰኔ 8 ተቀጥሯል፡፡
የፍርድ ቤቱ ብይን
ፍርድ ቤቱ በ29ኛ ቀጠሮው ተጨማሪ ምስክሮችን ለመስማት እና ሲዲ ማስረጃዎች ላይ ብይን ለመስጠት የነበረ ሲሆን በዚህም መሰረት
1. የሲዲ ማስረጃ ተብለው አቃቤ ህግ በተደጋጋሚ የሚያነሳቸው ነገር ግን በስተመጨረሻ ከኮምፒውተር ላይ የሰነድ ማስረጃዎቸን ለመገልበጥ ብቻ የተጠቀምኩባቸው ናቸው ያላቸውን ሲዲዎች የኤግዚቢትም የሰነድም ማስረጃ ስላልሆኑ ሙሉ ለሙሉ አንዲሰረዙ ሲል ፍርድ ቤቱ ወስኗል፡፡ አቃቤ ህግ ከመጀመሪያው የማስረጃ መስማት ሂደት አንስቶ እስከ 28ተኛው ቀጠሮ ድረስ አንዴ ባለሞያዎች የሉም ሌላ ጊዜ የወንጀሉ ኤግዚቢት ናቸው ሲላቸው የከረሙትን ሲዲዎች በስተመጨረሻ ምንም አይነት የተለየ ይዘት ያላቸው ሲዲዎች የሉኝም ሲል አምኗል፡፡ እነዚህ ሲዲዎችን አስመልክቶ ብቻ ትንሽ የማይባሉ ቀጠሮዎች መሰጠታቸው ከዚያም በተጨማሪ የጦማርያኑ እና የጋዜጠኞቹ እነዲሁም የጠበቆች እና የፍርድ ቤቱ ጊዜ እና ጉልበት መባከኑ ይታወቃል፡፡
2. አቃቤ ህግ የጠየቀውን ተጨማሪ ምስክሮች ተፈልገው አንዲመጡ ጊዜ ይሰጠኝ ያለውን ጥያቄ አስመልክቶ ምስክሮቹ አሁንም የደረጃ ምስክሮች በመሆናቸው እቃ ሲፈተሽ አይተናል ከማለት ውጪ ስለማይመሰክሩ አቃቤ ህግም በተደጋጋሚ በፍርድ ቤቱ እድል ተሰጥቶት ምንም የተለየ ምስክር ሊያቀርብ ባለመቻሉ ተጨማሪ ምስክሮችን ለማቅረብ ተጨማሪ ቀጠሮ አይሰጠውም በማለት የምስክሮቹን ጉዳይ ፍርድ ቤቱ ዘግቶታል፡፡
አንደኛ ተከሳሽ ሶልያና ሽመልስን የተመለከተ ማስረጃ
አቃቤ ህግ እስካሁን ምንም ሳይል የቆየባት አንደኛ ተከሳሽ ሶልያና ሽመልስን በተመለከተ በትናንትናው የፍርድ ቤት ውሎ ማጠቃለያ ላይ አንድ ዶክሜንተሪ የያዘ ሲ.ዲ በማስረጃነት ማቅረቡን ገልጾ ፍርድ ቤቱ እንዲመለከተው ማመልከቱ ይታወሳል፡፡ ይህን የሲ.ዲ ማስረጃ በተመለከተ በ29ኛው ችሎት ቀጠሮ ብይን የተሰጠ ሲሆን፣ በብይኑ መሰረትም ትላንትና ከሰዓት በኋላ አቃቤ ህግ ሲ.ዲውን በጽ/ቤት በኩል እንዲያስገባ ታዝዟል፡፡ ፍርድ ቤቱ ጨምሮ እንደገለጸው በአንደኛ ተከሳሽ ላይ የቀረበውን ዶክሜንተሪ በቢሮ ዳኞቹ እንዲመለከቱት ከተደረገ በኋላ ሲ.ዲው ሌሎችን ተከሳሾች ይመለከታል ወይስ አይመለከትም የሚለውን አይቶ ብይን የሚሰጥ ይሆናል፤ ብይኑን ለመስጠትም ለሰኔ 8/2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ በተጨማሪም ሲ.ዲው የያዘው ዶክሜንተሪ በግልጽ ቢታይ የሚያስከትለው ጉዳት አለ ወይስ የለም የሚለውንም ፍርድ ቤቱ ብይን እንደሚሰጥበት ይጠበቃል፡፡ አቃቤ ህግ በቀደመው ችሎት አንደኛ ተከሳሽ አመጽ ስታነሳሳ የሚያሳይ ዶክመንተሪ ሲዲ አለኝ ማለቱ ይታወሳል፡፡
አቃቤ ሀግ ጠበቆች ላይ ያቀረበው አቤቱታ
አቃቤ ህግ በዚሁ ችሎት ጠበቆች የፍርድ ቤቱን ውሎ አስመልክቶ የሚሰጡትን አስተያየት የአንድ ወገን አስተያት ከመሆኑም በላይ የፍርድ ሂደቱን ተጽእኖ ሊያመጣ ይችላል የሚል በቤቱታ አቅርቧል፡፡
ጠበቃ አምሃ መኮንን በበኩላቸው አቃቤ ሀግ እዚህ አንድ ተከራካሪ ወገን አንጂ የሂደቱ አዛዥ አለመሆኑን በተጨማሪም ግድፈት ካለ የተጣሰውን ህግ ግድፈት በጽሁፍ አቤቱታ ማቅረብ አንደሚችል ከዚያ ውጪ ግን በግልጽ የተሰየመውን ችሎት ከአገር ቤት እስከአለም አቀፍ ሚዲያዎች በዝርዝር አንደሚዘግቡትና የጠበቃው አስተያየትም ከዚህ የተለየ አንዳልሆነ ገልጸዋል፡፡
ፍርድ ቤቱ በበኩሉ ‹‹የተሰጠው አስተያየት አቃቤ ህግ በሰጠው ቃል መሰረት ተፈጽሞ ከሆነ ስህተት ስለሆነ ሊስተካከል ይገባል›› በሚል ማሳሰቢያ ብቻ አልፎታል፡፡
በፍርድ ቤትም ውስጥ የታፈነው የተከሳሾቹ ድምጽ
ብይኑ መሰማት ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በተደጋጋሚ ጥያቄ ለመጠየቅ ሲጠይቁ የነበሩት ተከሳሾች በፍርድ ቤቱ እድል አልተጣቸውም ፡፡ በተለይም የአቶ አመሃን የሚዲያ አስተያት ተከትሎ
ጦማሪ ናትናኤል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሳይቀር በተከሳሾች ላይ የወንጀለኛነት ንግግር ሲያደርጉ መደመጣቸውን በማስታወስ የፍርድ ቤቱ ማሳሰቢያ ለእሳቸውም ይሁን በማለት ንግግሩን ለማብራራት ሲሞክር ፍርድ ቤቱ ‹‹ይሄ የአቶ አምሃ ጉዳይ እንጂ እናንተን አያገባችሁም›› በሚል አቋርጦታል፡፡ ጦማሪ ዘላለም ክብረትም አንዲሁም ጋዜጠኛ አስማመው ሃይለጊዬርጊስ በተመሳሳይ ሀሳቡን ለመግለጽ ጠይቀው ተከልክለዋል፡፡ ጦማሪ ናትናኤል ፍርድ ቤቱ ሳይፈቅድለት ተናግሯል ወደጎንም ዞሮ አውርቷል በማለት ፍርድ ቤቱ ለጥያቄ አንዲነሳ ሲታዘዝ የናትናኤል ጥያቄ የሁላችንም ጥያቄ ነው በማለት ሁሉም ተከሰሶች አብረውት ተነስተዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ ሎሎቹ ተከሳሾ አንዲቀመጡ ቢያሳስብም አንቀመጥም በማለት አብረውት ቆመዋል፡፡
ናትናኤል መናገር ሲከለከል ‹‹ከአሁን በፊትም ሀሳባችን እንዳንገልጽ ገደብ ባደረጉብን ዳኛ ላይ አቤቱታ ማሰማታችን ይታወሳል፡፡ ህገ መንገስታዊ መብታችንን አክብሩ…ሀሳባችንን እንግለጽ›› ሲል ተናግሯል፡፡ ፍርድ ቤቱ ግን ንግግሩን አስቁሞ በመሐል ዳኛው አማካኝነት ‹‹ወዳልሆነ ነገር አታስገቡን›› ሲል ዛቻ መሰል ማሳሰቢያ ሰጥቷል፡፡
በዚህ ያላበቃው የተከሳሾችና የፍርድ ቤቱ ውዝግብ ጦማሪ አቤል አሁንም ለመናገር አድሉ አንዲሰየው ሲጠይቅ ” ስነስርአት ያዙ ” በማለት ፍርድ ቤቱ በመከልከሉ ጦማሪ አቤል ” እኛ ብቻ ሳንሆን ራሳችሁም ስነስርአት አድርጉ ጥያቄ አለን ሰምታችሁ ምላሽ ስጡን” በማለት ምላሽ ሰጥቷል፡፡ ይህንን ምላሹን ፍርድ ቤቱ ችሎት መድፈር ነው ብሎታል፡፡ ይህንን ተከትሎ ጠበቆች ጣልቃ በመግባት ደንበኞቻቸው አንዲደመጡ ፍርድ ቤቱን በማሳሰብ አቤልም ይህን እድል በመነፈጉ በስሜታዊነት የተናገረው በመሆኑ በተግሳጽ አንዲታለፍ ጠይቀዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ አቤልን በዚህ የጠበቃው ሃሳብ ይስማማ እነደሆነ ሲጠየቅ የጠየቁት መብቴን ነው የምጠይቀው ይቅርታ የለም በማለቱ የችሎት መድፈሩን አስመልክቶ ውሳኔ ለመስጠት ለግንቦት 25 ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
ይህንን ተከትሎ የአቤል ሀሳብ የሁላችንም ሃሳብ ስለሆነ ሁላችነም በዚያ ቀን ልንቀርብ ይገባል የሚል አቤቱታ ሁሉም ተከሳሾች ቢያሰሙም ፍርድ ቤቱ ፓሊስን አንዲያስወጣቸው በመታዘዙ ችሎቱ ወጥተዋል፡፡ በኋላ ከተከሳሾች ጠበቆች አንደገለጹት የጦማሪ አቤል ጥያቄ አንደኛ ተከሳሽ ሶልያና ሽመልስ ላይ የሚቀርበው የተባለውን የዶክመንተሪ ማስረጃ ሎሎች ተከሳሾችም አንዲያዩት ለመጠየቅ ነበር ፡፡
የዞን 9 ማስታወሻ
1. ዘግይቶም ቢሆን የተወሰደውን የፍርድ ቤቱን የሲዲ ማስረጃዎቸን መሰረዝ አንዲሁም ለአቃቤ ህግ ተጨማሪ ጊዜ አለመስጠት ውሳኔ እናበረታታለን ፡፡ ይህ ውሳኔ ከሶስት ቀጠሮ አስቀድሞ መወሰድና የጓደኞቻችን የተፋጠነ ፍትህ የማግኘት መብት ሊከበር ቢገባውም አሁንም ቢሆን ከመቅረት ይሻላል ፡፡ ፍርድ ቤቱም ይህንን መሳይ ፈጣን ምላሾችን በመስጠት ጓደኞቻችን ጦማርያን እና ጋዜጠኞች መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነጻ ማሰናበት የሚቀጥለው ብይን ሊሆን ይገባል፡፡ ያልተሰራ ወንጀል ምስክርም ሆነ ማስረጃ ለአመታት ቢፈለግም አይገኝለትም ፡፡
2. ፍርድ ቤት ውስጥ ያለውን ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት አሁንም አሳሳቢ ነው ፡፡ ተከሳሾች ሃሳባቸውን አንዲሰጡ መፍቀድ አንድ ገለልተኛ ፍርድ ቤት ለተከሳሾች ሊሰጠው የሚገባ መሰረታዊ መብት ሆኖ ሳለ ተከሳሾች ይህንን መብት በተደጋጋሚ መነፈጋቸው ከዚም አልፎ ይህንን መብት በመጠየቃቸው ችሎትን አንደደፈሩ መቆጠሩ በጣም አሳዛኝ ነው፡። የዞን9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች እንኳን አሁን ታስረንና ተሰደን መስዋእትነት እየከፈልንበት እያሉ ቀርቶ ቀድሞም ሃሳብን የነጻነት የመግለጽ መብት የማይቀየር ቋሚ እሴታችን አንደሆነ ይታወቃል፡፡ ፍርድ ቤቶች ይህንን ቀላል መብት መንፈጋቸው ደግሞ የተለመደውን የስራ አስፈጻሚው አካልነታቸው ሃሜት የሚያጠናክር ከመሆን ውጪ ሌላ ፋይዳ የለውም ፡፡
አሁንም ስለሚያገባን እንጦምራለን
ዞን9

ከገዢዎቻችን ለምን አንማርም ? – ግርማ ካሳ

ethiopian-election-2015“ኢህአዴግ የግንቦት15ቱን ምርጫ መቶ በመቶ ማሸነፉ ከተገለጸ በሁዋላ የኢህአዴግ ደጋፊዎች ከሁለት ተከፍለዋል። ምንጮች እንደገለጹት በርካታ ፊደል ቀመስ አባሎቹ ኢህአዴግ አሸነፍኩ ያለበትን የድምጽ ልዩነት አልተቀበሉትም። ውጤቱን የሚቃወሙ የግንባሩ አባላት ” ህዝቡ ከእንግዲህ በሰላም መንግስት እቀይራለሁ የሚለው እምነቱ ተሟጦ የሃይል አማራጭን ብቻ እንዲመለከት ከማድረጉም በላይ፣ የሃይል አማራጭን የሚከተሉ ሃይሎች በህዝቡም ሆነ በአለማቀፉ ማህበረሰብም የተሻለ ተቀባይነት እንዲያገኙ ያደርጋቸዋል” በማለት ለድርጅቱ አስተያየታቸውን እየሰጡ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ተገኘ የተባለውን ውጤት ከመደገፍ አልፈው፣ ህዝቡ እንዴት ለተቃዋሚዎች ይህን ያክል ድምጽ ሊሰጥ ቻለ በማለት በቁጭት አስተያየት የሚሰጡ ደጋፊዎች መኖራቸውንም ምንጮች ገልጸዋል።”
የሚከተለው ኢሳት ከዘገበው የተወስደ ነው። ዜናውን ለመቀበል አላዳገተኝም። “የሰላም በር ሲዘጋ የአመጽ በር ይከፋታል” እንዳለው አብርሃ ደስታ፣ ፍጹም አሳፋሪ የሆነው የምርጫው ሂደትና የምርጫው ዉጤት፣ ብዙ ዜጎች ሰላማዊዉን እና ሕጋዊዉን መንገድ ትተው ሌላ የትግል አማራጭ እንዲከትሉ ነው የገፋፋቸውና የሚገፋፋቸው።
ሆኖም አንድ ነገር ጠንቅቀን ማወቅ አለብን። መለስ ዜናዊ የሞተ ጊዜ ተከፋፈሉ ወዘተረፈ እያልን ስናወራ ነበር። ግምገማ ተደራረጉ ብለንም ስለነርሱ ስንተነትን ጊዜ አጠፋን። ምናልባት እነርሱ እርስ በርስ ከተከፋፈሉ በግርግር ለዉጥ ይመጣል ከሚል ተስፋ።
ሰዎቹ እርስ በርስ ይጠማመዱ ይሆናል። ነገር ግን መቼም አይለያዩም። ያውቃሉ፣ አንዱ ከወደቀ ሌላዉም እንደሚውድቅ። እነ አባዱላ ፣ እነ አዲሱ ለገሰ፣ እነ ሬድዋን ሁሴን ፣ ሕወሃት ከሌለ የነርሱ እጣ ምን ሊሆን እንደሚችል ይዉቃሉ። ስለዚህ አንዱ በአንዱ ላይ እንደ መዥገር ተጣብቆ ነው የሚጓዙት። ሥር የሰደደም ልዩነት ቢኖራቸውም፣ ተያይዘው ፣ ጀርባ ለጀርባ እየተታከኩ የግፍ አገዛዙን ይቀጥላሉ።
በነርሱ መካከል እርስ በርስ ልዩነቶች ተፈጥረው፣ ሞደሬት የሆኑት አይለው ቢወጡና አገር መረጋጋት ብትችል ደስ ነው የሚለኝ። ግን የሚሆን ነገር አይደለም። እነርሱ አይለያዩም። አንድ ናቸው።
በተቃራኒው እኛ ግን ትናንሽ ልዩነቶች እያለያዩን በጋራ መንቀሳቀስ አልቻልንም። በአገር ቤት ሰማያዊ፣ አንድነት፣ መኢአድ ፣ ትብብር …እንዲሁም ሌሎች ለምን በአንድ ላይ መስራት አልቻሉም ? መድረኮች ከነሰማያዊ ጋር ለምን መስራት አልቻሉም ? ወደ ዉጭ አገር ስንመጣ ደግሞ ሸንጎ፣ የሽግግር ምክር ቤቱ፣ ግንቦት ሰባት፣ ሶሊዳሪቲ ….ለምን አብረው ፣ አንድ አማራጭ ኃይል አቋቁመው መስራት አልቻሉም? ሁሉም ነጻነት ፈላጊ አይደሉም እንዴ ? ሁሉም ፍትህና ዴሞክራሲን ናፋቂ አይደሉም እንዴ ? ሁሉም ለአንዲት ኢትዮጵያ የቆሙ አይደሉም እንዴ ? ታዲያ ለምን መተባብር ቸገራቸው ?
ወገኖቼ, ደግሜ እላለሁ ገዢዎቻችን አይለያዩም። እነርሱ አንድ ሆነው፣ እኛ ደግሞ ተለያይተን እስከቀጠልን ድረስ ረግጠው፣ አዋርደው ይገዙናል። አራት ነጥብ። በተናጥል በባዶ፣ እንጮሃለን፣ እንኮንናችቸዋለን፣ ዘራፍ እንላለን ፣ የመግለጫ ዉርዥብኝ እናወርዳለን ። ግን የምናመጣው ነገር አይኖርም።
ስለዚህ ለዉጥ ክአገዛዙ ከራሱ ቢመጣ እስየው። ስንማጸንና ስንጎተጎት የነበረ ስለሆነ። ሆኖም ከአሁን በላይ ተስፋን እነርሱ ላይ ሳይሆን፣ አምላካችን እና አምላክ በሰጠን የተባበረው ክንዳችን ላይ መሆን ነው ያለበት። እመኑኝ ስርዓትቱ የበሰበሰ ስርዓት ነው። ገና ድሮ መወገድ የሚችል ስርዓት ነበረ። እስከ አሁን የቆየው እኛ ስለፈቀድንለት ብቻ ነው። አሁንም በአንድነት መንቀሳቀስ ካልቻልን፣ በአፋችን ብንናገረዉም ስርዓቱ እንዲቀጥል እየፈቀድንለት ነው።
ገዢዎቻችን ለክፋት አንድ ከሆኑ፣ እኛ ለመልካም ነገር እንድ መሆን እንዴት ያቅተናል ?

በሃመር ወረዳ ከፍተኛ እልቂት መድረሱን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ

electionግንቦት ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን በሃመር ወረዳ በዲመካ ከተማ እና አካባቢዋ የሚኖሩ አርብቶአደሮች ” እኛ ድምጽ ሳንሰጥ” እንዴት ኢህአዴግ አሸነፈ ይባላል በሚል ካለፈው ሰኞ ጀምሮ ከጸጥታ ሃይሎች ጋር ሲታኮሱ መቆየታቸውን የሚናገሩት የአካባቢው ነዋሪዎች፣ አንድ ሻለቃ ጦር እና የፌደራል አባላት ወደ አካባቢው በመንቀሳቀስ በወሰዱት እርምጃ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል። አንዳንድ የአካባቢው ነዋሪዎች አደጋ የደረሰባቸውን ሰዎች ቁጥር በመቶዎች ያደርሱታል። የአካባቢው ሰዎች እንደሚሉት አርብቶ አደሮች 5 የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ያቆሰሉ ሲሆን፣ ቁስለኞችም በሄሊኮፕተር ተወስደዋል። በአርብቶ አደሮች በኩል የተገደሉትን ሰዎች በትክክል ለማወቅ እንደማይቻል የሚናገሩት የአካባቢው ነዋሪዎች አስከሬን በየቦታው ወደቆ እንደሚታይ እየገለጹ ነው። በዞኑ የሚኖሩ አንድ ታዋቂ ግለሰብ እንደተናገሩት ደግሞ ትናንት አርብቶ አደሮች ዲመካን በሌሊት ለመያዝ ጥቃት በፈጸሙበት ወቅት የመንግስት ወታደሮች ከባድ መሳሪያ በመተኮስ በወሰዱት የአጸፋ እርምጃ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንደተገደሉ መረጃው እንደደረሳቸው ገልጸዋል። በሶስት ፒካፕ መኪኖች የተጫኑ ቁስለኛ ወታደሮች ጂንካ ሆስፒታል መግባታቸውንም አክለው ገልጸዋል። ሁለቱም ወገኖች ለወራት የጦርነት ዝግጅት ሲያደርጉ መቆየታቸውን የሚናገሩት ግለሰቡ፣ የችግሩ ምንጭ ከምርጫ ጋር ብቻ ሳይሆን ከመሬት ጋር የተያያዘ መሆኑም ይገልጻሉ። ሌላ የአካባቢው ነዋሪም እንዲሁ በተወሰደው እርምጃ ከ100 በላይ ሰዎች መገደላቸውን መረጃ እንደደረሳቸው ተናግረዋል ። የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ በርጤ ዢላ መግለጫ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ተናግረዋል። ኢሳት በሁለቱም ወገን የሞቱትን ሰዎች ከገለልተኛ ወገን ለማጣራት ያደረገው መኩራ አልተሳካለትም። ኢሳት ከሶስት ቀናት በፊት አርብቶአደሮች 3 ፖሊሶች ማቁሳለቸውን ዘግቦ የነበረ ሲሆን፣ ሆቴል ቤቶችና ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አሁንም ድረስ እንደተዘጉ ነው። ለወራት የዘለቀው ውጥረት ምርጫውን ሰበብ አድርጎ መጀመሩን ነዋሪዎች ይገልጻሉ። ሰመጉ ከሁለት ሳምንት በፊት ባወጣው ልዩ መግለጫ ከጥር 7 ቀን 2007 ዓ.ም ጀምሮ በተከሰተ ግጭት 7 ሰዎች መገደላቸውንና 9 ሰዎች መቁሳለቸውን በጥናት አረጋግጦ ይፋ አድርጓል። ሰመጉ በሪፖርቱ ህዳር 7 ቀን 2007 ዓም አቶ ዑልዴ ሃይሳ በሐመር ወረዳ ሸንቆ ወልፎ ቀበሌ ውስጥ ነዋሪ የነበረ አርብቶ አደር ሲሆን፣ በድንገት በተነሣ አለመግባባት ምክንያት ባሌ ኢልዴ በተባለ የፖሊስ አባል ኩላሊቱ ላይ በከባድ እርግጫ በመመታቱ የአቶ ዑልዴ ህይወት በእለቱ ህዳር 7 አልፏል። የሐመር ብሔረሰብ አባላት አቶ ዑልዴን የገደለው የፖሊስ አባል ሕግ ፊት ቀርቦ ባለመጠየቁ ከፍተኛ ቅሬታ አድሮባቸውና የመበደል ስሜት ውስጥ ገብተው እንደነበር የሰብአዊ መብት ድርጅቱ አስታውቃል። ማንጐ ተብሎ በሚጠራው ፓርክ ጎሽ የገደሉ የሐመር ብሔረሰብ አባላትን ለመያዝ ከደቡብ ኦሞ ዞን ፓሊስና ልዩ ኃይል የተውጣጡ አባላት ጥር 7/ 2007 ሥፍራው ሲደርሱ ለሽምግልና የተቀመጡ የአካባቢውን ሽማግሌዎች ጎሽ ገዳዮችን እንዲያወጡ በጠየቁዋቸው ጊዜ “በቅርቡ የተፈጸመውን የአቶ ዑልዴን ግድያ ሳታጣሩና ገዳዩን ይዛችሁ ለፍርድ ሳታቀርቡ፣ ከረዥም ጊዜ በፊት ጎሽ ገደለ የምትሉትን ሰው ለመያዝ እንዴት መጣችሁ?” የሚል ጥያቄ ማቅረባቸውን ይሁን እንጅ ” የፖሊስና ልዩ ኃይል አባላቱ በወቅቱ የተሰጣቸው ግዳጅ ጎሽ የገደለን ሰው መያዝ ብቻ መሆኑን በመግለጽ፣ ፖሊስ የተላክሁበትን ግዳጅ እፈጽማለሁ በማለቱ የሐመር ሽማግሌዎችና የማኅበረሰቡ አባላት ደግሞ የአቶ ዑልዴ ሃይሳን ገዳይ ሳትይዙ የጎሽ ገዳይ ልትይዙ አትችሉም በሚል አለመግባባት መፈጠሩን ሪፖርቱ ያስረዳል። አለመግባባቱ እየተካረረ ሄዶ በዚያው ቀን ጥር 7 ቀን 2007 በሐመር ማኅበረሰብ አባላትና በፖሊሶች መካከል ተኩስ ተጀምሮ፣ ሰፋ ወዳለ ግጭት ያመራ ሲሆን በግጭቱም 7 ሰዎች ሲሞቱ 9 ሰዎች መቁሰላቸውን ማረጋገጡን የሰመጉ 134ኛ ሪፖርት ያስረዳል። ሰመጉ ባወጣው የሟቾች ስም ዝርዝር አብዛኞቹ የሞቱትና የቆሰሉት የደቡብ ኦሞ ዞን ፖሊስና የልዩ ሃይል አባላት ናቸው። ሰመጉ በግጭቱ ተሳታፊ ከነበሩት የሐመር ብሔረሰብ አባላት በኩል ምን ያህል ሰዎች ጉዳት እንደደረሰ ለማወቅ አለመቻሉን በመግለጫው አስታውቋል። በሃመር ወረዳ ከ45 ሺ በላይ ነዋሪዎች ይኖራሉ። ዲመካ የወረዳው ዋና ከተማ ናት። -

ነጻነት በሌለባት ኢትዮጵያ ሕዝባዊ አስተዳደር መትከል ዘበት ነው!!!

Blueሰማያዊ ፓርቲ በ2007 ዓ.ም ጠቅላላ ምርጫ ለመሳተፍ ሲወስን በዚህች ሐገር ገለልተኛና ብቃት ያላቸው ተቋማት እንደሌሉና ገዥው ቡድንም እውነተኛ ምርጫ እንደማይፈቅድ እያወቀ መሆኑን ከዚህ በፊት በሰጣቸው የአቋም መግለጫዎች ግልፅ አድርጓል፡፡ በሒደቱም እንደታየው ገና ከመጀመሪያው ምርጫ ቦርድ የሰማያዊ እጩዎችን ከምዝገባ ሰርዟል፡፡ ገዥው ቡድን ስልጣኑን ላለማጣት የአፈና መዋቅር በመዘርጋት የዜጎች በነፃነት የመምረጥ መብትን በእጅጉ አፍኗል፡፡ የገዥው ቡድን ካድሬዎችና የፀጥታ ኃይሎች የተቃዋሚ ፓርቲዎች ተዋዳዳሪዎችን፣ ታዛቢዎችንና አባላትን በማን አለብኝነት ደብድበዋል፣ አስረዋል፣ አለፍ ሲልም ገድለዋል፡፡ ዜጎች ያላቸውን አማራጮች ሊያውቁባቸው የሚችሉ የመገናኛ ብዙሃንና የሲቪክ ማሕበራት በሐገሪቱ እንዳይኖሩ ተደርገዋል፡፡ በህገ መንግስቱ በግልፅ የተከለከለውን ቅድመ ምርመራ በመተላላፍ የፓርቲያችን የቅስቀሳ መልዕክቶች ለህዝብ እንዳይደርሱ የመንግስት የመገናኛ ብዙኃን ከፍተኛ ደባ ፈፅመዋል፡፡ ሃሳባቸውን በነፃነት የገለፁ አባሎቻችን ከየቤታቸውና ከሚሰሩባቸው ቦታዎች እየታደኑ ታስረዋል፣ አሁንም በእስር እየማቀቁ ይገኛሉ፡፡
በእነዚህና በሌሎችም ህገ ወጥ አሰራሮች ታጅቦ የተካሔደው ምርጫ በምንም መመዘኛ ፍትሃዊ፣ ነፃና ተአማኒ ሊሆን እንደማይችል ሒደቱ በግልፅ አመላካች ነው፡፡ በውጤቱም በሐገራችን የዲሞክራሲና የመድብለ ፓርቲ ስርዓት መኖርን ወደ መቃብር የከተተና ኢትዮጵያ የአንድ ፓርቲ ስርዓት ሐገር መሆኗን ያረጋገጠ በውጤቱም የገዥውን ቡድን 100% አሸናፊነት አከናንቦታል፡፡ ይህ ውጤት ለኢትዮጵያ ዴሞክራሲ የጨለማ ዘመን መምጣቱን ከማሳየቱ ባሻገር ኢህአዲግ በፍርሃት ተውጦ ሁሉንም ለመቆጣጠር ባደረገው ሩጫ ለመግለፅ እስኪያፍር ድረስ የሚያሸማቅቅ ውጤት እንዲከናነብ ሆኗል፡፡
በርካታ ኢትዮጵያውያን በምርጫው ሂደት ተስፋ በማጣት የመራጭነት ካርድ እንዳልወሰዱ የታወቀ ቢሆንም በአፈና ስርዓቱ ኢህአዲግን እንዲመርጡ በከፍተኛ ጫና የመራጭነት ካርድ የወሰዱ ዜጎች ሰማያዊ ፓርቲ ያቀረባቸውን የፖሊሲ አማራጮችና ለሐገራችን ያለውን ቀናኢ አመለካከት በመገንዘብ ሳይገደዱ፣ በጥቅም ሳይታለሉ ወይም ሌላ ማንኛውንም ስጦታ ሳይጠብቁ ለሰማያዊ ፓርቲ የሰጡት ድምፅ እጅግ የሚያስደምም ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ ፓርቲያችን በዚህ አፈናና ጭቆና ውስጥ ከሕዝብ የተሰጠውን ክብርም ያከብራል፣ ያመሰግናል፡፡ በምርጫ ሂደቱ የተደበደባችሁ፣ የተሳደዳችሁ፣ የታሰራችሁ እና የተንገላታችሁ የፓርቲያችን አባላትና ደጋፊዎች ፓርቲያችን ዛሬ በኢትዮጵያ ሕዝብ ተዓማኒ፣ ተወዳጅና ተስፋ የተጣለበት እንዲሆን እናንተ ላይ የደረሰው መከራና በደል ትልቁን ድርሻ ይወስዳልና ክብርና ምስጋና ይገባችኋል፡፡
በመጨረሻም ከላይ በተዘረዘሩት ሕገወጥና የአፈና ስርዓት የተካሔደው የ2007 ዓ.ም ጠቅላላ ምርጫ የሚያመላክተው ኢትዮጵያ አሁንም ነፃና ፍትኃዊ ምርጫ ልታካሂድ ቀርቶ በኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ከተካሔዱት ምርጫዎች ጋር እንኳ ሊወዳደር የማይችል እጅግ ኢፍትኃዊ፣ ወገንተኛና ተዓማኒነት የሌለው በመሆኑ ሰማያዊ ፓርቲ ሂደቱንም ሆነ ውጤቱን አይቀበለውም፡፡ በኃይል በተቀማ ድምፅ የሚመሰረት መንግስትም በሕዝብ ተቀባይነት የለውም፡፡ የዜጎች ነፃነት ሳይከበር ነጻና ፍትኃዊ ምርጫ ሊደረግ ስለማይችል አሁንም ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶቻችን እስከሚከበሩ ድረስ ሰማያዊ ፓርቲ በሚያካሂደው የነጻነት ትግል ኢትዮጵያውያን ከጎኑ እንዲቆሙ እየጠየቀ ለነፃነት የሚደረገው ትግል ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ያሳውቃል፡፡
ግንቦት 21 ቀን 2007 ዓ.ም
አዲስ አበባ
11392881_715789008546760_7142204330075555507_n

Thursday, May 28, 2015

የዛሬ 24 ዓመት ኢህአዴግ አዲስ አበባን ባይቆጣጠር ኖሮ ዛሬ የኢትዮያ እድገት ከብራዚል ጋር ይስተካከል ነበር 28 (የጉዳያችን ማስታወሻ) -

addis-ababa-realethiopia-141ደርግ 17 ዓመታት ሙሉ በህወሓት እና ሻብያ የተከፈተውን ጦርነት ሲዋጋ እንደነበር እና ጦርነቱ በቀን ብቻ በሚልዮን የሚቆጠር ብር ያስወጣ ነበር።በመቶሺዎች የሚቆጠር ሰራዊት መግቦ፣ታንክ እና ብረት ለበስ ተሽከርካሪ ነዳጅ እና ግዥ ፈፅሞ ማደር በራሱ ከፍተኛ ወጪ ነበር።ይህ ገንዘብ እንዳሁኑ የእርዳታ እና የብድር ገንዘብ ሳይሆን ህዝቡ ለእናት ሀገር እያለ ከሚያዋጣው እንደነበር ይታወቃል።በእርግጥ የሩስያ እርዳታ እና ብድር እንዳለ ሆኖ። በአንድ ወቅት ኮ/ል መንግስቱ ኃይለማርይም የሰሜኑ ጦርነት ባይኖር በጥቂት አመታት ውስጥ ኢትዮጵያን ከሰሜን እስከ ደቡብ ከምዕራብ እስከ ምስራቅ በባቡር ማገናኘት በተቻለ ነበር።ሲሉ መደመጣቸው ይታወሳል።በተለይ ህወሓት በዋነኛነት ድልድዮች እና መንገዶችን ማፍረስ ስራዬ ብሎ ይዞ ስለነበር እነርሱን ተከታትሎ መጠገን ሌላው ሥራ ነበር።የመከላከያ ኮንስትራክሽን ድርጅት (መኮድ) የተሰኘው ድርጅት አንዱ ስራው ህወሓት ያፈረሰውን ድልድይ እና መንገድ መልሶ መጠገን ነበር። በደርግ የመጨረሻ አመታት ታድያ ኮ/ል መንግስቱ የመንግስታቸውን ቅርፅ ለመቀየር ወስነው ነበር።ቅይጥ ኢኮኖሚ ታወጀ።ሚኒስትሮች በአዲስ መልክ ተሾሙ።ብዙዎቹ በምዕራብ ዓለም የተማሩ ነበሩ።ኢኮኖሚውም ሆነ ፖለቲካው ለቀቅ ያለ መስሎ ነበር።በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው የመመለስ ዕድል እንዳላቸው ምህረት እንደሚደረገም ተወራ።ፕሮፌሠር መስፍን ወ/ማርያምን ጨምሮ ሌሎች ምሁራን ከአመታት በኃላ እንደገና ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትን የማናገር፣በሀገሪቱ መፃኢ ዕድል ላይ የመነጋገር ዕድል አገኙ። በወቅቱ በተያዘው መልክ የሀገሪቱ ሰላም ቢረጋጋ እና የኢትዮጵያ ሕዝብ የህወሃትን የጎሳ ፖለቲካ እና የሻብያ ኤርትራን የመገንጠል አጀንዳ እንደመጥላቱ በነበረው ሕብረት ቢቀጥል ኖሮ፣በውጭ ይኖር የነበረው ሕብረተሰብ ወደሀገር ቤት ገብቶ የመስራት፣በሀገር ውስጥ ያለው ካለ ምንም የጎሳ ክፍፍል የመስራት እና ትላልቅ ኩባንያዎችን የመመስረት እድሉ ሰፊ ነበር። ዛሬ ኤፈርት እና ጥቂት ባለ ሀብቶች የሃገሩትን ሀብት ሁሉ እንዲህ ጠቅልለው ሚልዮን ኢትዮጵያውያን በድህነት ውስጥ አይዳክሩም ነበር። አሁንም በተጀመሩ የሽግግር ሂደት ደርግ ስልጣኑን ቢለቅ እና የሽግግር መንግስት ተመስርቶ ቀጥሎም ወደ እውነተኛ ምርጫ ኢትዮጵያ ሄዳ የእራሷ የሆነ መንግስት ቢኖራት ኖሮ ዛሬ ከ 24 ዓመታት በኃላ ኢትዮጵያ ካለምንም ጥርጥር ብራዚል ከደረሰችበት የእድገት ደረጃ የመድረስ ዕድል ነበራት።እዚህ ላይ ብራዚል ቀደም ብላ በውጭ ኃይሎች የመገዛቷ እና በርካታ የባህል ተቃርኖ ቢኖርም እኛ ካለን የባህል ሀብት ጋር በምጣኔ ሀብት ደረጃ እና በፈጠራ እንዲሁም በአዲስ ቴክኖሎጂ ክህሎት ሁሉ በእጅጉ የምንራመድበት የመነቃቃት አመታት ነበሩ።በእነኝህ 24 አመታት ውስጥ ከተባለው ደረጃ ለመድረስ እንችል እንደነበር እንደማሳያ የምረዳኝን ኢትዮጵያ ሊኖሯት እና ላይኖሯት የሚችሉት ነገሮች ሁለት ክፍል ከፍዬ ለማሳየት እና እነኝህ ጉዳዮች ማለትም ኢትዮጵያ ሊኖሯት የሚችሉት ነገሮች ምን ያህል ወደፊት እንደሚያራምዱን እና ላይኖሩ የሚችሉት ደግሞ ምን ያህል ወደኃላ እንደወሰዱን ለመመልከት ይረዳናል።እነኝህን ነጥቦች ለመንደርደርያ አነሳሁ እንጂ ጠለቅ ያለ ጥናት ቢደረግ ብዙ ጉዳዮችን ሊያሳየን እንደሚችል መረዳት ይቻላል። ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ዓመታት ውስጥ ሊኖሯት የሚችሉት 1/ የባንክ ኢንዱስትሪያችን ቢያንስ በ 5 የአፍሪካ ሁለት የመካከለኛው ምስራቅ እና አንድ አውሮፓ እንዲሁም 3 በአሜሪካ ቅርንጫፍ ከፍተው ግዙፍ የፋይናንስ ተቋም በሆኑ ነበር፣ 2/ እነ ጣና በለስ የመስኖ ልማት በአፍሪካ እና በመካከለኛው ምስራቅ ሞደል የተባለ ምርቶቹ ከኢትዮጵያ አልፈው ለመላው ዓለም የሚልክ በአውሮፓ የስቶክ ኤክስቸንጅ ገበያ የሚገባ ኩባንያ ይሆን ነበር፣ 3/ ኢትዮጵያ ከሻብያ ጋር በኤርትራ ጉዳይ ባትግባባ ቢያንስ በአሰብ ጉዳይ ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተደራድራ ወደቧን ታስከብር ነበር።በሌላ በኩል እንደ ህወሓት በመሃል ሀገር የሚኖሩ ትውልደ ኤርትራውያንን ከሀገር ስለማታስወጣ በሂደት እነኝሁ ትውልደ ኤርትራውያን የኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር አብሮ መኖር ሽንጣቸውን ገትረው የሚከራከሩ በሆኑ ነበር።እዚህ ላይ በደርግ ዘመን ከፍተኛ ተደማጭ የነበሩ የኤርትራ ቆላው ተወካዮች የነበራቸውን ተሰሚነት ማሰብ ይገባል።እነኝህ ሁሉ በህወሓት ስሳደዱ እና ሲገፉ 24 ዓመታት ተቆጠሩ። 4/ ኢትዮጵያ የመከላከያ ኃይሏ ጠንካራ ስለነበር በደቡብ ሱዳን ጉዳይም ሆነ የሱማልያ አልሸባብ ፈፅሞ ስጋት ሊሆኑ አይችሉም ይልቁንም በአካባቢው ሃያል ሀገርነቷ እስከ ግብፅ እና መካከለኛው ምስራቅ ድረስ ይናኝ ነበር።የአይኤስ ኤስ ጥቃት መፈፀሙ በተሰማ በ24 ሰዓታት ውስጥ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ከደብረ ዘይት ተነስተው የሱዳንን የአየር ክልል ጥሰው በርካታ የአሸባሪው ይዞታዎችን ሊብያ ውስጥ ያጠቁ ነበር።በእዚህም ሌሎች ተቀናቃኝ ሀገሮችን ሊያስደምም ይችል ነበር። 5/ በጦርነት ውስጥ የነበረ ኢኮኖሚ ያንን ያህል የስራ ዕድል ለወጣቱ መፍጠር ከቻለ ከጦርነት በኃላ ላለፉት 24 ዓመታት ውስጥ ቢያንስ ከ አስር ያላነሱ ከባድ የብረት ኢንዱስትሪዎች፣የነዳጅ ማውጣት ሥራ (ሱዳን ባቅሟ ነዳጅ ስታወጣ ኢትዮጵያ በሙስና ያልባለገ መንግስት ቢኖራት ኖሮ እስካሁን የነዳጅ ምርት በጀመረን ነበር)፣ 6/ በኢትዮጵያ ተጀምረው የነበሩት የመካናይዝድ እርሻ ልማቶች በሰፊ ይስፋፉ ነበር።ኢትዮጵያ ጤፍ በብዛት በማምረት ለዓለም ብቸኛ አምራች እና ላኪ ሀገር ትሆን ነበር። 7/ የበርካታ ሃገራት ትላልቅ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ መዋለ ንዋይ ለማፍሰስ ይጎርፉ ነበር።በተለይ ደርግ የወደቀበት ወቅት የምስራቅ አውሮፓ ሃገራት ገና ከሩስያ ተፅኖ እየወጡ፣በርካታ የአፍሪካ ሀገራትም እየተነቃቁ ስለነበር ከወቅቱ ጋር የሚሄድ የድርጊት መርሃ ግብር እና ከሙስና በተቻለ መጠን የፀዳ መንግስት ስለሚኖር ኩባንያዎቹ ከማንም የአፍሪካ ሃገራት ኢትዮጵያን እንደሚመርጡ ሳይታለም የተፈታ ነበር።ይህም ባለፉት 24 ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያ ከብራዚል እኩል የምትጠራ ሀገር ትሆን ነበር። 8/ ናዝሬት የተጀመረው የትራክተር መገጣጠምያ ፋብሪካ ምርቱን አሻሽሎ በሌሎች ቦታዎች ማምረት እና የኢትዮጵያን ገበሬ በከፊልም ቢሆን ከበሬ አስተራረስ ዘዴ እንወጣ ነበር። 9/ ወላጆቻቸው የሞቱባቸው ማሳደጊያ እና መንከባከቢያ ማዕከል ”ሕፃናት አምባ” በሁሉም ክፍለ ሀገሮች ተመስርቶ እናት አባት የሞቱባቸውን በተለይ ባለፉት 24 ዓመታት ቁጥራቸው በመቶ ሺዎች የሆኑትን ሕፃናት ወደ ማዕከሉ አስገብቶ ኃላፊነት የሚሰማቸው ትውልድ ማፍራት ይቻል ነበር።የማዕከሉም አስተዳደር በባለሥልጣን ደረጃ ተዋቅሮ ኢትዮጵያውያን በወር ከደሞዛቸው እያዋጡ በርካታ እናት አባት ያጡ ሕፃናትን ሕይወት መታደግ ይቻል ነበር።ኢህአዴግ ማዕከሉ የነበሩ ሕፃናትን የደርግ ልጆች ብሎ በምሽት እንዳባረራቸው እና ማዕከሉን አንዴ የካድሬ ማሰልጠኛ ሌላ ጊዜ የግብርና ማሰልጠኛ እያደረገው መሆኑ ይታወቃል። ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ዓመታት ውስጥ ላይኖሯት (ላይሆንባት) የሚችሉት 1/ ሀገሪቱ በጫት እንዲህ አትበከልም ነበር።ወጣቶቿ በስፖርት እና በልዩ ልዩ ሙያ ላይ እንጂ የጫት ተገዢ አይሆኑም ነበር፣ 2/ ከሶስት መቶ ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን እህቶቻችን ወደ መካከለኛው ምስራቅ ለግዳጅ ሥራ አይጋዙም ነበር፣ 3/ የጣና በለስ ፕሮጀክት አይፈርስም ነበር፣ 4/ ኢትዮጵያ የባህር በር የሌላት ሀገር አትሆንም ነበር፣ 5/ ኢትዮጵያ በጎሳ የተደራጀ ፓርቲ አይኖራትም ነበር።ሀገሩም በጎሳ የተከፋፈለ አስተዳደር አይኖራትም ነበር። 6/ ኢትዮጵያውያን ጎሳቸው ሳይሆን ኢትዮጵያዊነታቸው ብቻ በፈለጉት ቦታ ሄደው የመስራት መብት ይኖራቸው ነበር፣ 7/ ኢትዮጵያውያን በመላው ዓለም ክብራችን ዝቅ ተደርጎ እንዲታይ አይደረገም ነበር። አንድ ችግር ሲገጥመን ወደ ኤምባሲያችን ሄደን ችግራችንን እንፈታ ነበር፣ 8/ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለሁለት የተከፈሉ አባቶች አስተዳደር አይኖራትም ነበር፣ 9/ ከ11 ቢልዮን ዶላር በላይ ገንዘብ ከሀገር በሕገ ወጥ መንገድ አይወጣም ነበር፣ 10/ የብሔራዊ ባንክ በቀትር ፀሐይ ወርቁን ለሌቦች አስረክቦ አርተፍሻል ወርቅ አይቀበልም ነበር፣ 11/ የተማረ የሚከበርባት እና ሥራ የምያገኝባት እንጂ ኮብል ስቶን ተራቢ እንዲሆን አይደረገም ነበር፣ 12/ የሕፃናት አምባ ወላጆቻቸው የሞቱባቸው ሕፃናት በምሽት በኢህአዴግ ወታደር አያባረሩም እና ሴቶች ለሴተኛ አዳሪነት ወንዶቹ ለጎዳና ተዳዳሪነት አይዳረጉም ነበር። 13/ ኢትዮጵያ ሕፃናቶቿን በጉዲ ፈቻነት በመሸጥ በአፍሪካ ቀዳሚ አትሆንም ነበር። ባጠቃለይ ኢትዮጵያ በህወሓት አገዛዝ ስር እሩብ ክ/ዘመን (25 ዓመታት) ሊሞላት አንድ ዓመት ብቻ ቀራት።ሃያ አምስት አመታት በርካታ ሃገራት ወደ መካከለኛ ገብ ደረጃ የደረሱበት ነው።የዛሬ 24 ዓመት አንጎላ ጦርነት ላይ ነበረች።ዛሬ አንጎላ በከፍተኛ እድገት ላይ የምትገኝ ሀገር ነች። የዛሬ 24 ዓመት ቦትስዋና ብዙም የምትደነቅ ሀገር አልነበረችም ዛሬ ቦትስዋና የአልማዝ አምራች ሀገር ነች።የዛሬ 24 ዓመት ጋና ስሟ እምብዛም አይነሳም። ዛሬ ጋና በዲሞክራሲያዊ ምርጫ መንግስት የምትቀይር እና የነዳጅ ሀብት ባለቤት የሆነች ሀገር ነች።ሃያ አራት ዓመት እንደ ኢትዮጵያ ላለ ጠንካራ ሰራተኛ ሕዝብ፣በብዙ ውጣ ውረድ ላለፈ ሕዝብ እና በርካታ እድሎች ከፊቱ ላሉት ሕዝብ ዛሬ ብራዚል ለደረሰችበት ደረጃ የመድረስ አቅም ነበረው።ነገር ግን በጎሰኛ መንግስት ተጠልፎ የጥቂቶችን የተንደላቀቀ ሕይወት እየተመለከተ እንዲኖር ተፈርዶበታል።አሁንም ከነገ ዛሬ ይቀድማል እና ለኢትዮጵያ ነፃነት አንድነታችንን እናጠናክር።ከጎሰኞች ማዶ ለምትመሰረተው የሁላችንም ኢትዮጵያ የበኩላችንን እናድርግ። ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG ግንቦት 20/2005 ዓም (ሜይ 28/2015) - 

ግንቦትና ግንቦታውያን

mengistu hailemariam(ዘ-ሐበሻ) ኢህአዴግ እና አጋር ድርጅቶቹ የዘንድሮውን አሳፋሪ ምርጫ 100% ማሸነፋቸውን ምርጫ ቦርድ ይፋ ባደረገው ሪፖርት ገለጸ:: ምንም አይነት ተቃዋሚ ፓርቲ በፓርላማው ውስጥ መቀመጫ እንዳላገኘም ተገልጹዋል:: የገዢው ፓርቲ መሳሪያና ገለልተኛ ያልሆነው ምርጫ ቦርድ ይፋ ባደረገው ሪፖርት ኢህአዴግ አዲስ አበባ ላይ ከ23 መቀመጫዎች ኢህአዴግ 23ቱንም መቀመጫዎች አግኝቷል። – ከትግራይ ክልል ቦርዱ ከደረሱት የ31 መቀመጫዎች ውጤት ህውሃት/ኢህአዴግ 31 መቀመጫዎችን – ከአማራ ክልል ከደረሱት የ107 መቀመጫዎች ውጤት ብአዴን/ኢህአዴግ 107 መቀመጫዎች ከኦሮሚያ ክልል ቦርዱ ከደረሱት የ150 መቀመጫዎች ውጤት ኦህዴድ/ኢህአዴግ 150 መቀመጫዎችን – በኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል ቦርዱ ከደረሱት የ16 መቀመጫዎች ውጤት ኢሶዴፓ 16 መቀመጫዎችን – ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከደረሱት የሰባት መቀመጫዎች ውጤት ሰባቱንም ቤጉዴፓ; – ከደቡብ ክልል ከደረሱት የ95 መቀመጫዎች ውጤት ዴኢህዴን/ኢህአዴግ 95 መቀመጫዎች፣ – በጋምቤላ ክልል ጋህዴፓ ከሶስት መቀመጫዎች ሶስቱንም፣ በሀረሪ ክልል ሀብሊ ከ2 መቀመጫዎች አንዱን ሲያገኝ አንዱን ኦህዴድ/ኢህአዴግ፣ – በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከሁለቱ መቀመጫዎች አንዱን ኦህዴድ/ኢህአዴግ ቀሪውን ሶህዴፓ አግኝተዋል – ከአፋር ክልል ከደረሰው ከደረሰው የስድስት መቀመጫዎች ውጤት አብዴፓ ስድስቱንም መቀመጫ አግኝቷል። በአሳፋሪነቱ የሚጠቀሰው የዘንድሮውን ምርጫ የአውሮፓ ሕብረት; የአሜሪካ መንግስትና ሌሎች ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ፍትሃዊ ያልሆነ ምርጫ ሲሉ አውግዘውታ:: ተቃዋሚዎችም የምርጫውን ውጤት እንደማይቀበሉት አስታውቀዋል::

ምርጫ ቦርድ የአስቂኙን ምርጫ ውጤት ይፋ አደረገ * ኢሕአዴግ 100% አሸነፈ አለ * ምንም አይነት ተቃዋሚ ፓርቲ የፓርላማ ወንበር አላገኘም -

election board(ዘ-ሐበሻ) ኢህአዴግ እና አጋር ድርጅቶቹ የዘንድሮውን አሳፋሪ ምርጫ 100% ማሸነፋቸውን ምርጫ ቦርድ ይፋ ባደረገው ሪፖርት ገለጸ:: ምንም አይነት ተቃዋሚ ፓርቲ በፓርላማው ውስጥ መቀመጫ እንዳላገኘም ተገልጹዋል:: የገዢው ፓርቲ መሳሪያና ገለልተኛ ያልሆነው ምርጫ ቦርድ ይፋ ባደረገው ሪፖርት ኢህአዴግ አዲስ አበባ ላይ ከ23 መቀመጫዎች ኢህአዴግ 23ቱንም መቀመጫዎች አግኝቷል። – ከትግራይ ክልል ቦርዱ ከደረሱት የ31 መቀመጫዎች ውጤት ህውሃት/ኢህአዴግ 31 መቀመጫዎችን – ከአማራ ክልል ከደረሱት የ107 መቀመጫዎች ውጤት ብአዴን/ኢህአዴግ 107 መቀመጫዎች ከኦሮሚያ ክልል ቦርዱ ከደረሱት የ150 መቀመጫዎች ውጤት ኦህዴድ/ኢህአዴግ 150 መቀመጫዎችን – በኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል ቦርዱ ከደረሱት የ16 መቀመጫዎች ውጤት ኢሶዴፓ 16 መቀመጫዎችን – ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከደረሱት የሰባት መቀመጫዎች ውጤት ሰባቱንም ቤጉዴፓ; – ከደቡብ ክልል ከደረሱት የ95 መቀመጫዎች ውጤት ዴኢህዴን/ኢህአዴግ 95 መቀመጫዎች፣ – በጋምቤላ ክልል ጋህዴፓ ከሶስት መቀመጫዎች ሶስቱንም፣ በሀረሪ ክልል ሀብሊ ከ2 መቀመጫዎች አንዱን ሲያገኝ አንዱን ኦህዴድ/ኢህአዴግ፣ – በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከሁለቱ መቀመጫዎች አንዱን ኦህዴድ/ኢህአዴግ ቀሪውን ሶህዴፓ አግኝተዋል – ከአፋር ክልል ከደረሰው ከደረሰው የስድስት መቀመጫዎች ውጤት አብዴፓ ስድስቱንም መቀመጫ አግኝቷል። በአሳፋሪነቱ የሚጠቀሰው የዘንድሮውን ምርጫ የአውሮፓ ሕብረት; የአሜሪካ መንግስትና ሌሎች ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ፍትሃዊ ያልሆነ ምርጫ ሲሉ አውግዘውታ:: ተቃዋሚዎችም የምርጫውን ውጤት እንደማይቀበሉት አስታውቀዋል::

የሳምንቱ ማስታወሻ – ኤርሚያስ ለገሰ

ermias copyእሁድ ግንቦት 16 ቀን 2007 ” እናት ሬስቶራንት” አሌክሳንድሪያ እሁድ ምሳ ሰአት ላይ አትላንታ የሚገኘው ማህደር ሬዲዬ አዘጋጅ የሆነው አቶ ሰይፋ ደወለልኝ። በቀጥታ እየተላለፈ ባለው ፕሮግራማቸው ላይ አጫጭር ጥያቄዎች ስላሉት ሊጠይቀኝ እንደሚፈልግ ገለፀ። አጭር ከሆነ ለመመለስ ፍቃደኛ መሆኔን ነገርኩት። ” በዛሬው ምርጫ የወያኔ መንግስት ለተቃዋሚዎች ስንት ወንበር የሚለቅላቸው ይመስልሀል?” በማለት ጠየቀኝ። ብዙም ማሰብ ሳይጠይቀኝ፣ ” ምንም ወንበር አይሰጣቸውም!” አልኩት። መልሴ ብዥታ የፈጠረበት ስለመሰለኝ ምክንያት ያልኩትንም ጨምሬ ለማስረዳት ሞከርኩ። ከማህደር ሬዲዬ ጋር የነበረን ቃለምልልስ ሲጠናቀቅ “በእናት ሬስቶራንት” ምሳ የጋበዘኝ ጋዜጠኛ ወዳጄ በአስተያየቴ አለመስማማቱን ነገረኝ። አገርቤትን የሚያስታውስ ክትፎ መመገብ ትቶ ይሞግተኝ ጀመር። በስስት የሚቀርበውን ቆጮ የምሻማበት ጊዜ በማግኘቴ ወጉን እንዲቀጥል አደረኩ። እንዲህ በማለት ጀመረ፣” ለማየት ያብቃህ እስከ ሀያ ወንበር ይፀድቁባቸዋል። ለሰማያዊ 2፣ ለመራራ ፓርቲ እስከ 15፣ ለበየነ እስከ 3 ወንበር ይሰጧቸዋል። ከጀርባቸው ቢታረዱ ሰባራ ወንበር የማይሰጡት ለገብሩ አስራት ፓርቲ ነው” አለኝ። ” ሌሎቹም ፓርቲዎች ከአረና ፓርቲ የተለየ እጣ ፋንታ አይደርሳቸውም” አልኩት። ” እንዴት?፣ ለምን? መነሻህ ምንድነው?” በጥያቄ አጣደፈኝ። ድሮም የጋዜጠኛ ነገር! ” የህውሀትን ባህሪ በደንብ መረዳት ያስፈልጋል። የህውሀት ባለስልጣናትና ካድሬዎች አስተሳሰብ፣ ባህሪ፣ እምነትና ተግባር ጠንቅቆ ማወቅ የስርአቱን ምንነት ለመረዳት እድል ይሰጣል። ሲጀምር ህውሀት የበታችነት ስሜት የተጠናወተው ድርጅት ነው። በዚህ ምክንያት ቀንና ለሊት የፍርሀት ማእበል የሚንጠው ነው። በሁለተኛ ደረጃ ህውሀት እወክለዋለው ብሎ የሚያስበው ህዝብ ከኢትዬጲያ ህዝብ ከ7% በታች ስለሆነ የስልጣኑ ምንጭ ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ በሚካሄድ ምርጫ አይደለም። ይልቁንስ ህዝብን የመግዛት ሌጅትመሲው የሚመነጨው በዘረጋው የፀጥታ መዋቅርና የጠመንጃ አፈሙዝ ነው። በሶስተኛ ደረጃ ሁሉን የጠቀለለ ስልጣን ፍላጐት የሚመነጭ ነውር የማያውቁ ስግብግቦች ናቸው። አንዲትም ቀዳዳ መክፈት አይፈልጉም። በዛ ላይ ልባቸው አይገኝም” አልኩት። ” ልባቸው አይገኝም ስትል ምን እንዳስታወስከኝ ታውቃለህ? አስመራ የሄድኩ ጊዜ አንድ እጅግ ጠመዝማዛ ፣ በጣም ረጅምና የሚያስፈራ መንገድ ጐብኝቼ ነበር። ” ንግግሩን አቋርጬው ፣ ” ከሊማሊሞ ይብሳል?” አልኩት። በአንድ ወቅት አቶ መለስ ተቃዋሚዎችን ሲያስፈራራ የሊማሊሞን መንገድ ማንሳቱ ትዝ ብሎኝ። ” ሊማሊሞን አላውቀውም። ኤርትራ እንዳየሁት ጠመዝማዛ መንገድ ከሆነ ግን በጣም ያስፈራል። …እናም የገረመኝ ምኑ መሰለህ? የመንገዱ ስያሜ!” ” ምንድነው የሚባለው?” አንገቱን አየነቀነቀ ” ልበ-ትግራይ ” አለኝ። ” አውቃለሁ አልኩት ” ርግጥም አውቅ ነበር። አስከትዬም “ታዲያ ጃንሆይ በዚህ መንገድ ላይ ከኤርትራውና ከትግራዩ ገዥ ጋር ሲሄዱ የተበሻሸቁትን አልነገሩህም?” አልኩት። ” አልነገሩኝም!” አለ ጆሮውን አቁሞ። ” እንዳትናደድ ብለው ነው። ለማንኛውም ሌላ ጊዜ አጫውትሀለሁ። አሁን ቅድም ወደ ጀመርነው የምርጫ አጀንዳ እንመለስ። …ህውሀቶችን እስከማውቃቸው ድረስ ሁሉን ካልጠቀለሉ እንደ ውርደት የሚቆጥሩ ናቸው። በዛ ላይ ተቃዋሚዎችን ” ጠላቶች”፣ ” እንቅፋቶች”፣ ” የጥፋት ግንባሮች” በሚል የማጭበርበሪያ ስትራቴጂ የሚፈርጁ ናቸው። እንደዚህ አይነት አመለካከት ኖሯቸው ወንበር ይለቃሉ ማለት ከእባብ እንቁላል እርግብ የመጠበቅ ያህል ነው” አልኩት። ” እኔ እኮ ይሄ አዳፋና እኩይ ባህሪያቸው ጠፍቶኝ አይደለም። ግን ቢያንስ ምእራባውያንን ለማስደሰትና እርዳታና ብድር ለማግኘት የተወሰነ ወንበር ሊለቁ ይችላሉ ከሚል ምልከታ ተነስቼ ነው።” ” የኢሳቱ ብእረኛ ገብረጳዲቅም እንደዛ አይነት ሀሳብ ያለው ጵሁፋን አዳምጫለሁ። እነዚህ ሰዎች የለከፋቸው የጠባብነት ደዌ ወደ ካንሰር ከተቀየረ ቆይቷል። ከድሮ አስተሳሰባቸው መላቀቅ አይችሉም። እንደውም የመራራን ቃል ልዋስና ‘ ጫካው ከእነሱ ወጣ እንጂ፣ ‘እነሱ ከጫካው አልወጡም ‘ … ከተጣባቸው የዜሮ ድምር ፓለቲካ መላቀቅ አይችሉም” በማለት ምላሽ ሰጠሁት። ” አንተ ያልከው ከሆነ አሜሪካንን ጉድ አደረጓት። በተለይ የውጭ ጉዳይ መስሪያቤቱና በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠ መንግስት ብላ የተናገረችው ሴትዬ ምን ይውጣታል? እውነቴን ነው የምልህ! ስቴት ዲፓርትመንቱ አመታዊ ሪፓርቱን ሲያወጣ ምን ብሎ ሊጀምር ነው? ” በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠው የኢትዬጲያ መንግስት…” ብሎ ሊጀምር ነው?” በማያቋርጥ ሳቅ ውስጥ ሆኖ ተናገረ። ” አየህ! አሜሪካኖቹ ብዙ የገባቸው የማይመስለኝ ህውሀት አሜሪካንን ማዋረድ እንደ አንድ ዋነኛ ስራው ከወሰደ መቆየቱን ነው። ለዚህ የተለያየ ምክንያት አላቸው። ሲጀመር አሜሪካኖች ስታዋርዳቸውና ፊትህን ስታዞርባቸው ይቀርቡሀል የሚል አመለካከት አላቸው። ሲቀጥል በምስራቅ አፍሪካ የአሜሪካን ፍላጐት ወታደራዊ ድጋፍ ማግኘት ነው። ይህን ፍላጐት ያለማቅማማት ማሟላት የሚችሉት እነሱ እንደሆነ ጠንቅቀው ያውቃሉ። ለዚህም ነው በብዙ ኢትዬጲያውያን ዘንድ የሱማሊያ ጦርነት ” ለአሜሪካን ቀብድ ማስያዣ የተደረገ የውክልና ጦርነት” የሚል ስያሜ የተሰጠው። በነገራችን ላይ ከኢትዬጲያ አንጳር የአሜሪካ ወታደራዊ አታሼዎቹ ከውጭ ጉዳይ መስሪያቤቱ በላይ ስልጣን እንዳላቸው ህውሀቶች ያምናሉ። ሌላው ቀርቶ በቅርቡ የሳሞራ የኑስ ወደ አሜሪካ መምጣት ለምን እንደሆነ መገመት ትችላለህ” አልኩት። ” እና አሜሪካን የምርጫ ውጤቱን ትቀበለዋለች ብለህ ታስባለህ?” ” ብትቀበለውም/ ባትቀበለውም ለራሷ ጥቅም ስትል ከህውሀት መራሹ መንግስት ጋር እጅና ጓንት ሆና ለተወሰነ ጊዜ ትቀጥላለች።” ” እስከመቼ?” ” የሐይል ሚዛኑ እስኪያጋድል ድረስ!” *** ግንቦት 18 ቀን 2007, ክሪስታል ሲቲ አሜሪካኖቹ የነጳነት ቀናቸውን እያከበሩ ነው። ስራ ተዘግቷል። ዋሽንግተን ዲሲ ከየግዛቱ በመጡ ሞተረኞች ተጨናንቃለች። አንዳንድ የቀለበት መንገዶች ተዘግተዋል። መዝናኛዎች እስከ አፍጢማቸው ሞልተው ህዝቡ እደጅ ፈሷል። እኛም ወጉ አይቅርብን ብለን የአሜሪካኖቹን የነጳነት ቀን ለማክበር ከጋዜጠኛው ጓደኛዬ ጋር ወደ ክሪስታል ሲቲ ተያይዘን ሄደናል። አላማችን የአሳዳሪዎቻችንን የነጳነት ቀን ለመዘከር ቢሆንም ወጋችን በሙሉ በብዙ ሺህ ማይሎች ተጉዞ የሀገራችን ሁኔታ ላይ አርፋል። ውጤቱ አስቀድሞ የሚታወቀው ምርጫ!! እውነት ለመናገር ለምርጫው ሂደት ትኩረት ያልሰጠው የኢትዬጲያ ህዝብ በየቦታው በሚሰማው የሰማይና የምድር ልዩነት ያለው ውጤት እጅግ መገረሞች ታይተዋል። የህውሀት ንቀት መረን ማጣቱ ብዙ ኢትዬጲያውያንን አስቆጭቷል። በማህበራዊ ድረገጶችም መወያያ የሆነው ይህ ለከት ያለፈው የህውሀት ነውረኝነት መሆኑ አልቀረም። ቀኑን ሙሉ መረጃ ሲሰበስብ የዋለው ጋዜጠኛ ወዳጄ የነበረው ፊት መገረሙን የሚያሳብቅ ነበር። ንግግሩንም የጀመረው እሱ ነበር፣ ” የአፍሪካ ህብረት ታዛቢ ያለውን ሰማህ?” በማለት ጠየቀኝ። ” ለምንድነው የምንሰማው?… መጀመሪያውኑ የሟሸሸና ለይስሙላ የመጣ ነው። በሀገሪቱ ኢህአዴግ ያዘጋጃቸው ምርጫ ጣቢያዎች ከ45,000 በላይ ናቸው። የአፍሪካ ታዛቢዎች ማዳረስ የቻሉት 356 ጣቢያዎች ብቻ ነው። ይህ ማለት በአጠቃላይ ማዳረስ የቻሉት ከአንድ ፐርሰንት በታች (0•8% ) ብቻ ነው። መሰረታዊ የስታስቲክስ ናሙና ጥናትን ገደል የከተተና ተቀባይነት የሌለው ነው። በዛ ላይ እንደ አፋር ያሉ ምርጫው ከመካሄዱ በፊት ኮሮጆ የሚጠቀጠቅባቸው ቦታዎች ታዛቢ አላኩም” በማለት ምላሽ ሰጠሁት። ” ቢሆንም ባልተለመደ ሁኔታ ከተመለከቷቸው ቦታዎች 21% ኮሮጆዎች ቀድመው ህጉ ከሚፈቅደው በፊት ተከፍተው አይተናል ማለታቸው ትልቅ ጅምር ነው። በዛ ላይ ምርጫው ፍትሀዊ፣ ዲሞክራሲያዊ፣ ነጳ የሚሉ ቃላትን ከመጠቀም ተቆጥበዋል። ይህ ለህውሀት መጥፎ ምልክት ነው” በማለት ከሰበሰበው መረጃ በመነሳት ተናገረ። አስከትሎም፣ ” ይልቁንስ አስገራሚ ውጤቶች ልንገርህ። ሀይለማሪያም ደሳለኝ በተወዳደረበት በሎሶ በምትባል ምርጫ ክልል 100% ሲያገኝ፣ የሰማያዊና ኢራፓ ፓርቲ እጩዎች 0% አግኝተዋል። ” በማለት እፍረት አፋን ሞልቶት ተናገረ። እኔም ከአፋ ተቀብዬ፣ ” ባይሆን ነበር የሚገርመኝ። ጋሽ ሀይሌ እኮ በልቡ አቶ መለስን አስቀምጦ ነው የሚንቀሳቀሰው። እሱ ያደረገውን ማድረግ አለበት። እሱ የተናገረውን መናገር አለበት። ቀድሞ አቶ መለስ እንደሚያገኘው አህያ የማይሸከመው ድምጵ ማግኘት አለበት። በአካባቢው ያለውን ተቀባይነት በመቶ ፐርሰንት ካላሳደገ ሌላው ጋር ያለው ክብር ወደ ታች ይወርዳል ብሎ ማሰቡ አይቀርም። ጋሽ ሀይሌ ለህዝብ በሚታይ ችሎታው ተፈትኖ ሰለወደቀ ያለችው ብቸኛ አማራጭ ይህቺ ብቻ ናት። አማኑኤልና ጋዜጠኛ ወንድሙ ይህን ተልእኮ የፈፀሙ ይመስለኛል” አልኩት። ” ሆዳሙ በሬ?” “በነገራችን ላይ ከማን አንሼ በሚመስል መንገድ አማኑኤል አብርሀ ( ኢህአዴግ ቢሮ) በወላይታ አንድ ምርጫ ክልል 1182 ሲያገኝ ተቀናቃኙ አንድ ድምጵ ብቻ እንዲያገኝ አድርጓል። የሚገርምህ በምርጫ 97 አማኑኤል የወላይታ ህዝብ ይጠላዋል ብሎ በረከት በመጨረሻው ሰአት ጋሽ ሀይሌን ትእዛዝ ሰጥቶት እንዲሰረዝ ተደርጓል። ” ታዲያ ዛሬ ለውድድር ሲቀርብ ህዝቡ ተሳስቶ ነበር ማለት ነው? ወይንስ በረከት ተደቆሰ?” ” እሱ ጊዜ ይፈታዋል። ከዛ ይልቅ ህዝቡ ተሳስቶ ነበር የሚለውን እንቀበል! አይመስልህም?” አልኩት። ” ህዝብማ መሳሳቱን እማ በፕሮፌሰር በየነ ድምጵ አሳዩን። እስቲ እግዜር ያሳይህ የሾኔ ህዝብ ” በየነ ክብራችን” የሚል ዘፈን ያለው ህዝብ ነው። ሾኔ ስለበየነ ክብርና ዝና አውርታ የምትጠግብ አይደለችም። በእሱ መማል ብቻ ነው የሚቀራቸው። በነገራችን ላይ ብዙ ልጆች ስማቸው በየነ ነው። እንደዚህ በምታከብረው ወረዳ ዬሴፍ ዳይሞ የሚባል ማንም የማያውቀው የኢህአዴግ ተወካይ 10,961 ሲያገኝ በየነ 252 አገኘ ብሎ ማወጅ አሳፋሪ ነው። ቢገባው ለሀይለማርያም ራሱ ውርደት ነበር? ” ” ሀይሌ ከተዋረደ ቆየ እኮ!” የለበጣ ሳቁን ለቀቀው። ” ለነገሩ ጋሽ ሀይሌ መቼ እንደበቃኝ ታውቃለህ? አንድ ጊዜ በድሬደዋ የሀገር ሽማግሌዎችን ለማነጋገር ወደ ድሬ ያቀናል። ሽማግሌዎቹ አርብቶ አደሮች ስለነበሩ በርካታ ግመሎች አላቸው። በጥያቄና መልስ ጊዜ በድሬደዋ የተሰራው ድልድይ አጭር ስለሆነ ግመሎቻቸውን ማሳለፍ እንደቸገራቸው ይነግሩታል። ምን ብሎ ምላሽ የሰጠ ይመስልሀል?” ” ምን አለ በእናትህ?” ” ፕላኑን የሰሩት ቻይናዎች ስለሆኑ የግመል ቁመት ስንት እንደሆነ አያውቁም። ኢትዬጲያዊ መሀንዲሶቹም ከደጋ አካባቢ ስለመጡ የግመል ቁመት አያውቁም። - 

የዞን 9 ጦማርያን የዛሬ የፍርድ ቤት ውሎ

10501881_1449029642077225_8570967205812429537_nበእነ ሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ በፌደራል አቃቤ ህግ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው ጉዳያቸው እየታየ ከሚገኙት ሰባት የዞን 9 ጦማርያን እና ሶስት ወዳጅ ጋዜጠኞች ስድስቱ ጦማርን እና ሶስቱ ጋዜጠኞች ዛሬ ግንቦት 18/2007 ዓ.ም የፌደራሉ ከፍተኛው ፍ/ቤት ቀርበዋል፡፡ መዝገቡ ለዛሬ ተቀጥሮ የነበረው ሁለት ጉዳዮችን ለማየት ሲሆን፣ አንደኛው አቃቤ ህግ በኤግዚቢትነት አሉኝ ያላቸውን ኤግዚቢቶችና 12 ሲ.ዲዎች መዝገብ ቁጥራቸውን በመጥቀስ አሟልቶ እንዲያቀርብ በታዘዘው መሰረት ማቅረቡን ለመመልከት ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ የአቃቤ ህግ ቀሪ የደረጃ ምስክሮችን ለመስማት ነበር፡፡
በዚህ መሰረት አቃቤ ህግ በኤግዚቢትነት የያዛቸውን ላፕቶፕ፣ ሞባይል፣ ሲምካርድ፣ ሃርድ ዲስክ ይዞ ቀርቧል፡፡ ሆኖም ግን ሲ.ዲዎችን በተመለከተ ሲጠየቅ ‹‹ሲ.ዲዎቹ እየመጡ ነው››የሚል ምላሽ በመስጠቱ እና የተከሳሾች ጠበቆች ሲዲዎቹ ሳይመጡ ምስክሮች መሰማት የለባቸውም ብለው በመቃወማቸው ሲዲው ከማእከላዊ ምርመራ እስኪመጣ ምስክሮች አያሰሙም ተብሎ ለከሰአት ተቀጥሮ ነበር ፡፡
ከሰአት በኋላ አቃቤ ህግ ቀሪ ናቸው ካላቸው 16 ምስክሮች መካክል 3ቱን ብቻ ይዞ የቀረበ ሲሆን 13ቱን ማግኘት አለመቻሉን ገልጿል፡፡ የቀረቡት ሶስቱንም ፍተሻ ሲከናወን ያዩ የደረጃ ምስክሮች ሲሆኑ ፍተሻ ሲከናወን ከማየታቸው በስተቀር ተጨማሪ ነገር መመስከር አልቻሉም ፡፡
የምስክሮች ቃል
11377311_813263972095430_8478348994541914774_n19ኛ ምስክር፡- ቸርነት ተፈራ ይባላል፤ 23 አመቱ ነው፡፡ ደንብ በማስከበር ስራ ላይ እንደተሰማራ የገለጸው ይኸው ምስክር አድራሻው አ.አ ጉለሌ ክ/ከተማ መሆኑን ተናግሯል፡፡ በጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬ ላይ ነው ምስክርነቱን አሰምቷል፡፡ “ቤት ሲፈተሽ አይቻለሁ፣ ሲ.ዲ፣ ላፕቶፕ፣ አሮጌ ካሜራ፣ ሚዲያ ኤንድ ኢሌክሽን የሚል ጽሑፍ፣ መጽሐፍ፣ ወረቀቶች፣ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ተገኝተዋል፡፡ የላፕቶፑን አይነት አላስታውስም፡፡ ሲ.ዲዎች ሁለት ናቸው፣ ይዘታቸውን ግን አላውቅም፡፡ እሷ የፈረመችበትን አንዳለ ፈርመናል ብሏል፡፡
ለምስክሩ ‹‹ሲ.ዲው ባዶ ይሁን የተጻፈበት ይሁን ያየኸው ነገር ነበር›› የሚል መስቀለኛ ጥያቄ ሲቀርብለት ‹‹አላየሁም›› ሲል መልሷል፡፡ ሲ.ዲው ላይ ፈርመሃል ሲባልም መፈረሙን አስረድቷል፡፡ በዚህ ጊዜ የፈረመበትን ሲ.ዲ እንዲያሳይ ተጠይቆ አቃቤ ህግ ጣልቃ በመግባት ‹‹ኤዶም ላይ ሲ.ዲ በማስረጃነት አልያዝንም›› የሚል አስገራሚ መልስ ሰጥቷል፡፡ በተመሳሳይ ምስክሩ 30 ገጽ የእንግሊዝኛ ጽሁፍ የተጻፈበት ወረቀት ላይ መፈረሙን ስለገለጸ ፊርማውን እንዲለይ ሰነዱ ይቅረብላቸው ሲባልም አቃቤ ህግ ‹‹በማስረጃነት አላያያዝንም›› ብሏል፡፡ ምስክሩ ሁለት በማስረጃነት ባልተያዙ ሰነዶች ላይ ነበር ምስክርነቱን የሰጠው ፡፡ በተጨማሪም በፍተሻ ወቅት የተገኘውን ላፕቶፕ እነዲያሳይ የተጠየቀው ምስከሩ የጦማሪ አቤል ዋበላን ላፕቶፕ አሳይተዋል፡፡
20ኛ ምስክር፡- እኒህ ምስክር ደግሞ ቢላል ሙሄ የሱፍ የሚባሉ ሲሆን 38 አመታቸው ነው፡፡ ‹‹ሚያዝያ 2006 ፌደራል ፖሊስ የተስፋለምን ቤት ሲፈትሽ በታዛቢነት አይቻለሁ፡፡ ቤቱን የከፈተው ተስፋለም ነው፡፡ ቤቱ ውስጥ ብዙ መጽሔትና ጋዜጦች፣ መጽሐፎች፣ ወረቀቶች፣ መቅረጸ ድምጽ፣ ላፕቶፕ ተገኝተዋል፡፡›› ተስፋለም ቤት 28 ሲዲዎች ተገኝተዋል ያሉት ምስክሩ ምን አይነት ይዘት አንደነበራቸው ባዶ ይሁኑ ጽሁፍ ያላቸው አላውቅም እነዲሁም ሲዲዎቹ ወጥቶ የታተመ ነገር አላስታውስም ብለዋል፡፡
21ኛ ምስክር፡- ሚሊዮን አሸብር ደግሞ የ31 አመት በንግድ ስራ ላይ የተሰማራ የአ.አ ነዋሪ ነው፡፡ ለምስክርነት መምጣቱን የገለጸው ሚሊዮን በማን ላይ ልትመሰክር ነው የመጣኸው ሲባል በአማኑኤል ፈለቀ ላይ ሲል መልሷል፡፡ ሆኖም ግን ዳኞች ደጋግመው ሲጠይቁት ስሙን አስተካክሎ በናትናኤል ፈለቀ ላይ ሊመሰክር መሆኑን ገልጹዋል፡፡
‹‹ሚያዝያ 17/2006 ቂርቆስ ክ/ከተማ ኮንስትራክሽን ባንክ ፌደራል ፖሊስ የፍርድ ቤት ወረቀት አሳይቶ ፍተሻ ሊያደርግ ስለሆነ እንድታዘብለት ጠይቆኝ ታዝቤያለሁ፡፡ ናትናኤል ፍተሻው እንዲካሄድ ፈቃደኛ ነበር፡፡ በዚህ መሰረት ተፈትሹዋል፤ ፍተሻውንም አይቻለሁ፡፡ ላፕቶፕ፣ ሲ.ዲዎች (በቁጥር ወደ 16 የሚሆኑ) እና ሰነዶች ተገኝተዋል፡፡ የተገኙት ነገሮች ላይ ፈርሜያለሁ ፡፡ ሲዲም ሆነ ላፕቶፑ ውስጥ ያለውን ነገር ይዘት አላየሁም አላውቅምም ብሏል ፡፡ ላፕቶፑንም ቀርቦ አሳይቷል ፡፡
ሲዲዎቹ
አወዛጋቢዎቹ ሲዲዎች ዛሬም ቀርበዋል ተባለ እነጂ በአቃቤ ህግና በጠበቆች መካከል ያለው ክርክር አልተቋጨም ፡፡ ሲዲዎቹ ኤግዚቢት ስለሆኑ ለተከሳሾች ለማድረስ አልገደድም ሲል የነበረው የአቃቤ ህግ ክርክር ዛሬ ሲዲዎቹ የሰነድ ማስረጃው ላይ የተያያዙትን ሰነዶች ከላፕቶፕ የገለበጥንባቸው ናቸው ብሎ የሰነድ ማስረጃ አካል አድርጓቸዋል ፡፡ የተከሳሽ ጠበቆች ሲዲዎቹ ማስረጃ ከሆኑ ሊሰጠን ይገባል ሲሉ አመልክተዋል፡፡ ሲዲዎቹ አንድ ወይም ሁለቱ ናቸው የቪዲዮ ማስረጃ ያላቸው ሌላው ከክሱ ጋር የተያያዘውን ሰነድ የገለበጥንበት ነው፣ ሁሉም በሰነድ የተያየዙ ናቸው ሲል አቃቤ ህግ አዲስ የህግ ፍሬ ነገር አቅርቧል፡፡
የአንደኛ ተከሳሽ ላይ የቀረበ ማስረጃ
አቃቤ ህግ በዛሬው ውሎው አዲስ ግኝት ይዞ መጥቷል፡፡ የሲዲ ውዝግቡ መሃል ላይ “አንድ ዶክምንተሪ አንደኛ ተከሳሽ ላይ የቀረበና ቡድኑ ለቅስቀሳ ይጠቀምበት የነበረ አለንና ፍርድ ቤቱ ሌሎች ማስረጃዎችን አቅርበን ሰንጨርስ ይሄንን ሲዲ እንዲያይልን” ብሏል፡፡ አንደኛ ተከሳሽ ሶልያና ሽመልስ ላይ በማስረጃነት አለኝ ያለው ሲዲ መቼ የተገኘ አንደሆነ ምን ይዘት እንዳለው የተጠቀሰ ነገር የለም ፡፡
በመጨረሻም አቃቤ ህግ ቀሪ 13 የደረጃ ምስክሮቹን ፈልጎ ለማቅረብ ተጨማሪ ጊዜ ይሰጠኝ ብሏል፡፡ የተከሳሽ ጠበቆችም ሲዲዎቹ የሰነድ ማስረጃዎች ከሆኑ እንዲሰጣቸው ካልሆነም ኢግዚቢትነታቸው ምዝገባ እንዲለይ ጠይቀዋል፡፡ በሁለቱ ጉዳዬች ላይ ለመወሰን ለነገ ጠዋት ግንቦት19 ከጠዋቱ 3 ሰአት ተቀጥሯል፡፡
የዞን9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች በከፍተኛ የአካልና የመንፈስ ደህንነት ሆነው የታዬ ሲሆን ቀኑን ሙሉ ፍርድ ቤት ጊቢ ውስጥ አብረው ለመዋል እድል አግኝተዋል፡፡
የዞን ማስታወሻ
ከዚህ በፌት በተደጋጋሚ አንደጠቀስነው ያልተሰራ ወንጀል ማስረጃና ምስክር አይገኝለትምና ተከሰሾችን መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነጻ በማሰናበት ፍርድ ቤቱ ሃላፌነቱን በመወጣት ከህግ የበላይነት ጎን መሆኑን አንዲያሳይ በድጋሚ አንጠይቃለን፡፡

የአሜሪካ መንግስት ምርጫውን አሽሟጠጠው::

5b8b5d11ወያኔን በጓንትነት የሚተቀመው የአሜሪካ መንግስት በተቃዋሚ የለውጥ ሃይሎች ላይ በሲቭል ሶሳይቲ በነጻ ሚዲያዎች እና በነጻነት ድምጾች ላይ የሚደረገው ወከባ እንደሚያሳስበው በመግለጽ የአሜሪካ መንግስት ዲፕሎማቶች ምርጫውን እንዳይታዘቡ መከልከሉንና መደረጉን በለሆሳስ አንስቶ ከአፍሪካ ሕብረት ታዛቢዎች ያገኘውን መረጃ ዋቢ በማድረግ የተቃአሚ ሃይሎች ታዛቢዎች በምርጫው ላይ እንዳይታዘቡ መደረጉ እንዳሳዘነው በመግለጽ በምርጫው ወቅት የነበረው የአፍሪካ ሕብረት ታዛብ ቡድን እንኳን የወከባዎች ተጋሪ እንደነበር ተናግሯል መግለጫው::
ለፍትሃዊ እና ነጻ ምርጫ አስፈላጊ የሆኑ ነጻ እና ለቅስቀሳ የሚሆን የመረጃ ማሰራጫ ሚዲያ የዲሞክራሲ እና የሰብአዊ መብቶች ሲቭክ ማህበራት እንዲሁም የተላያዩ አለም አቀፍ እና ሃገር አቀፍ ሕብረተሰቦች በታዛቢነት ባልተወከሉበት ምርጫ ማካሄድ አያስኬድም ሲል መግለጫው አሽሟጧል::ጋዜጠኞችን በማሰር እና በማሳደድ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን ገደብ በመስጠት የፖለቲካ ድርጅቶች ውስጥ ጣልቃ በመግባት የፖለቲካ ምህዳሮችን በማጥበብ ምርጫ ማካሄድ አይሞከርም ሲል መግለጫው ተናግሯል::
የአሜሪካ መንግስት ከኢትዮጵያ እና ከሕዝቧጋር ጠንካራ ግንኙነት አለው ያለው መግለጫው ዲሞክራቲክ ተቋማት ዕንዲጠናከሩ የፕሬስ ነጻነተ እንዲያብብ በሃገሪቱ የታፈነው የፖለቲካ ምህዳር ሁሉ ክፍት እንዲሆኑ ኢትዮጵያ የፈረመችውን የአለም አቀፍ ሰባዊ መብቶች ድንጋጌ ግዴታዎች እንድታከብር አብረን እንሰራለን ብሏል::
-

መድረክ ባለፈው እሁድ የተካሄደውን አምስተኛው አገር አቀፍ አጠቃላይ ምርጫ ውጤትን እንደማይቀበል ገለፀ -

11050696_1596569733947557_2286534849872328917_nየመድረኩ አመራር የሆኑትን ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ Bbnradio Mereja Mekebeya አግኝቶ ያነጋገራቸው ሲሆን ከርሳቸው ጋር ያደረገነውን ቆይታ በዛሬው ዝግጅታችን ይጠበቁን :: የመድረክ ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፥ በምርጫው ሂደት ላይ ችግሮች የነበሩ በመሆኑ ውጤቱን አንቀበልም ብለዋል። አፍንጮ በር አከባቢ በሚገኘው የመድረክ ዋና ፅህፈት ቤት መግለጫ የሰጡት የመድረክ የወቅቱ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ፣ ዶ/ር መረራ ጉዲና እና ሌሎች የመድረኩ አመራሮች ናቸው።
ምርጫ ቦርድ በዛሬው እለት ያወጣው ጊዜያዊ ውጤት ተቀባይነት የለውም ሲሉ የመድረክ ፓርቲ አመራር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ለቢቢኤን ገለጹ
ቢቢኤን ዜና
ምርጫ ቦርዱ በዛሬው እለት ይፋ ባደረገው ጊዜያዊ የምርጫ ውጤት መግለጫ ኢህአዴግ 100 ፐርሰንት በደረሱ ጊዜያዊ ውጤቶች ማሸነፉን ገልጽዋል፡፡ ከፍተኛ የህዝብ ድጋፍ ያለው መድረክ በበኩሉ በዛሬው እለት በሰጠው አስቸኳይ መግለጫ ይህንን እንደማይቀበለውና በምርጫው ጊዜ የደረሱትን ችግሮች በመዘርዘር ለሁለት ሰአታት መግለጫ ሰጥቷል፡፡
የመድረኩ አመራር የሆኑትን ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ቢቢኤን አግኝቶ ያነጋገራቸው ሲሆን ከርሳቸው ጋር ያደረገነውን ቆይታ በዛሬው ዝግጅታችን ይጠበቁ
-

ምርጫው ተብዬውን ቧልት ላለመታዘብ ወሰንን – አና ጎምሽ

EADFE4F6-EF84-4416-8B7C-D1A00F9A1E6A_w640_r1_sለኢትዮጵያ የፖለቲካ ችግሮች ተቀያቂዎቹ ተቃዋሚዎቹም ናቸው – ቴድ ዳኘ
የዘንድሮው ኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ተካሄደ፡፡ የምርጫውን ሂደት የታዘበው ብቸኛ ዓለምአቀፍ ተቋም የአፍሪካ ኅብረት ነው፡፡
ለወትሮ የኢትዮጵያን ምርጫዎች ይታዘቡ የነበሩትና አሁንም በዓለም ዙሪያ እየተንቀሣቀሱ የሚታዘቡት የአውሮፓ ሕብረትና የአሜሪካው የካርተር ማዕከል ግን አልተገኙም፡፡ ለምን?
የአውሮፓ ፓርላማ አባል የሆኑትና የ1997ቱ ምርጫ የኅብረቱ የታዛቢዎች መሪ የነበሩት አና ጎምሽ የአውሮፓ ኅብረት ያልታዘበው ምርጫው “ቧልት ስለሆነ ነው” ብለዋል፡፡
“የአውሮፓ ኅብረት የታዛቢዎችን ቡድን በመላክ ለገዥው ፓርቲ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ያካሄደ የማስመሰያ ማኅተም መስጠት ስላልፈለግን የደረስንበት የፖለቲካ ውሣኔ ነው” ብለዋል፡፡
ለመሆኑ የኢትዮጵያ መንግሥት አሁን ባለው አቋሙ ዴሞክራሲያዊ፤ ፍትሐዊና ነፃ ምርጫ ለማካሄድ ብቁ ነው?
“አይደለም ብሎ የሚያሣምነኝ እስካልመጣ፤ አዎ ብቁ ነው” ይላሉ በደቡብ ሱዳን የፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ልዩ አማካሪ እንዲሆኑ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የላካቸው፤ በዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት የአፍሪካ ስፔሻሊስት ሆነው ለሃያ አራት ዓመታት ያገለገሉት አቶ ቴዎድሮስ ዳኘ፡፡
“ኢትዮጵያ ውስጥ የፖለቲካ ችግር አለ የሚባል ከሆነ ብዙውን ጊዜውን እርስ በራሣቸው በመጣላትና በውጭ ሃገሮች በመኖር ጊዜያቸውን የሚያጠፉት ተቃዋሚ ፓርቲዎችም ተጠያቂነቱን ሊወስዱ ይገባቸዋል” ብለዋል አቶ ቴዎድሮስ፡፡

Tuesday, May 26, 2015

« በጉልበት ወደ ዘመናዊነት » የጀርመን ታዋቂ ዕለታዊ ጋዜጣ ስለ የኢትዮጵያ ሀገር አቀፋዊ ምርጫ ሲዘግብ

11244905_10202996338428430_6077217837534585327_nእሁድ በመላው ኢትዮጵያ የተካሄደውን 5ኛ ሀገር አቀፍ ምርጫ ለመታዘብ የአውሮፓ ህብረት ልዑካን ወደ ኢትዮጵያ ባይሄዱም ፤ የዶይቸ ቬለን ሬዲዮ እና ቴሌቪዥንን ጨምሮ የጀርመን ጋዜጦች ስለምርጫው ዘግበዋል። የጥቂቱን የጀርመን ጋዜጦች ዘገባ እንደሚከተለው ነበር።
የጀርመን ታዋቂ ዕለታዊ ጋዜጣ « ዙድ ዶይቸ ሳይቱንግ» ስለ የኢትዮጵያ ሀገር አቀፋዊ ምርጫ ሲዘግብ ርዕሱን« በጉልበት ወደ ዘመናዊነት » ነው ያለው። የጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ ፓርቲ ኢሀዲግ እንደሚያሸንፍ ጥርጥር የለውም ሲል የዘገበው ይህ ጋዜጣ ፤ «ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት በርግጥ ጥሩ የኢኮኖሚ እድገት ያስመዘገበች ሀገር ብትሆንም አሁንም ድረስ እንደ « ልማታዊ አምባገነን» ነው የምትታየው፣ መንግሥት የኤኮኖሚውን አቅጣጫ ብቻ ሳይሆን ህብረተሰቡንም ይቆጣጠራል ሲልም አትቷል ።ጋዜጣው የሰብዓዊ መብት ተማጋች ድርጅቶችን ዋቢ በማድረግ፤ ሂስ ሰንዛሪ ጋዜጠኞች በሀገሪቱ ቦታ እንደሌላቸው ወህኒ ቤት የሚገኙ ጋዜጠኞችን እና የኢንተርኔት ዘጋቢዎችን በምሳሌነት ጠቅሶ ያብራራል። ጋዜጣው ስለ ሃገሪቱ ልማትም ፅፏል። ምንም እንኳን ልማቱ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ማህበረሰበብ ጋር ባይደርስም፤ በአዲስ አበባ ትላልቅ ፎቆች እየተሰሩ ስለመሆኑና በቅርቡ የቀላል ባቡር አገልግሎት ስራውን እንደሚጀምር ይጠቁማል።
« ዙድ ዶይቸሳይቱንግ»የኢትዮጵያ ምርጫ ሀተታውን ከማጠናቀቁ በፊትም፤ የተቃዋሚዎች እጣ ፋንታ ከባለፈው ምርጫ ጋር ሲነፃፀር አለመሻሻሉንም አንስቷል። እንደ ጋዜጣው ቀውስ ውስጥ ከሚገኙት ከሶማሊያ እና ከደቡብ ሱዳን ጋር ስትነፃፀር ምዕራባውያን ኢትዮጵያን የተረጋጋች ደሴት አድርገው ስለሚመለከቷት የዲሞክራሲ ርዕስ ሲነሳ ፤ ጆሮ ደባ ልበስ ብለው ያልፉታል።
ሌላው ስለ ኢትዮጵያ ምርጫ የዘገበው «ታገስሻው» የተባለው የጀርመን የዜና ማሰራጫ ነው። «ተቃዋሚ ድምፅ የለውም» በሚለው ርዕሱ፤ የምርጫው አሸናፊ ፓርቲ ኢሀአዲግ እንደሚሆን እንደማያጠራጥር ያትታል። ታገስሻው ከዚህም በተጨማሪ ፤ በቴሌቪዥን ሥርጭቱ እና በድረ ገጹ ከሀገር ሸሽቶ ናይሮቢ ውስጥ ጥገኝነት ስለጠየቀው ጋዜጠኛ የትነበርክ እና ደረሰብኝ ስለሚለው በደል ዘግቧል።

11053317_953419194690034_5249946199555285607_n«ፍራንክፈርተር አልገማይነር » የተባለው የጀርመን ጋዜጣም ቢሆን እንደሌሎቹ ጋዜጦች ፤ማን ምርጫውን እንደሚያሸንፍ ግልፅ ነው ይላል፤
 « እንደ ብረት የጠጠረ አገዛዝ ባላት ሀገር» በሚለው ርዕሱ ከ457 የምክር ቤት መቀመጫ 456ቱን ኢሀአዲግ ይዞ የመራው ሀገር እንደሆነ በመግለፅ፣ ጋዜጣው ፤ የተቃዋሚዎችን ነፃ አለመሆን እና ብሶት ያትታል። ከዚህም በተጨማሪ ጋዜጣው ፤ ምናልባትም ነፃ ምርጫ ታይቶበታል ያለውን የ97ቱን ምርጫ እና ከዛም በኋላ ስለተነሳው አመፅ እና በወቅቱም ከ200 በላይ ሰዎች ስለመሞታቸው አውስቷል። ከዚህም በተጨማሪ የኢትዮጵያ መንግሥት ፣ አሸባሪ ቡድናትን በመዋጋት የዩናይትድ ስቴትስ ስልታዊ አጋር መሆኑን ጋዜጣው ጠቅሷል ።

©ዶይቸ ቬለ
- See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/7283#sthash.R8FSiJ7V.dpuf

ወያኔ ኢሕአዴግ በምርጫ ተሸንፎ እያለ አጭበርብሮ በሥልጣን ለመቀጠል በሚያደርገዉ መፍጨርጨር ለሚከተለዉ ማንኛዉም ሕዝባዊ ተቃዉሞ ተጠያቂ ነዉ -

11295762_1596174137320450_3064661602950094415_n

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ አለም አቀፍ ድጋፍ ሰጪ ቡድን

 2007 ብሄራዊ ሀገር አቀፍ ምርጫ የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ከምርጫው ቅስቀሳ ጊዜ ጀምሮ ያለው ሁኔታ ነፃና ፍትሃዊ አለመሆኑን ባወጡት ሪፖርት አረጋግጠዋል::ወያኔ በምርጫው ቅስቀሳ ሂደት ድብደባ፣ አፈና ፣እስራት ፣ግድያ እና እንግልት በግልጽ ፈጽሟል:: (በምዕራብ ሸዋ ዞን ሚዳቀኝ እና በአርሲ ኮፈሌ የተፈጸመው ግድያ ፤ በእነ በቀለ ገርባ ላይ በበደሌ፣ ጅማ እና በነቀምቴ የተፈጸመውን ድብደባ ልብ ይሏል)
ተቃዋሚዎች ወያኔ ኢሕአዴግን በምርጫ ክርክር አዋረዷት:: ህዝቡ ለመድረክ የሰጠው ድጋፍ ስላስደነገጠው ሃይልን በመጠቀም ጫና ቢያደርግም አልተሳካላትም:: ተስፋ ስቆርጡ ለምርጫው ሁለት ቀናት ሲቀሩት ጠ/ሚኒስትሩ ፓርላማው በማይጠራበት ወቅት ስብሰባ በመጥራት ማስፈራሪያ እና ዛቻ በተቃዋሚዎች ላይ ሰንዝረዋል:: ይህም አስቀድሞ የምርጫውን ውጤት ለመቀልበስ በሃይል ምርጫውን ለማጭበርበር ቅድመ ዝግጅት እያደረጉ እንደነበር የሚያስይ ነበር :: የኢሕዴግ ካድሬዎች የምርጫው ዋዜማ ሌሊት ከአለቆቻቸው የተላለፈውን ትእዛዝ ለመፈጸም አስቀድመው ኮሮጆ በመሙላት በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች የፌዴራል ፖሊስ: ሚሊሺያዎች: ፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ እና አድማ በታኝ ፖሊሶችን በማዝመት የምርጫ ቦርድ ተወካዮችን እና የተቃዋሚ (የመድረክ) የምርጫ ታዛቢዎችን መታወቂያቸውን በመቀማት እያስፈራሩ እየደበደቡ በርካቶችን (90%) ሙሉበሙሉ ማለት ይቻላል ከምርጫ ጣቢያ በሀይል አባረዋል።በርካታ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የምርጫ ካርድ ተከልክለዋል። የመምረጥ መብታቸዉን ተነፍገዋል።
ስለሆነም: ፀረ ሠላም እና ፀረ ዴሞክራሲ የዘረፋ ቡድን የፈጸመው ምርጫን ማጭበርበር ፣ የህዝብ ድምፅ መዝረፍ፣ ንጹሃን ዜጎችን መግደል እና የማሰር ድርጊት አጥብቀን እያወገዝን የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ አለም አቀፍ ድጋፍ ሰጪ ቡድን ይህን መግለጫ አውጥቷል።
1. ኦፌኮ/ መድረክ በኦሮሚያ ክልል ምርጫዉን ሙሉ ለሙሉ አሸንፏል።
2. የተፈፀመው ድርጊት በማንኛውም አለም አቀፍ የምርጫ መስፈርት ተቀባይነት የሌለው እና ህገ ወጥ መሆኑን እንገልጻለን:: በጽኑ እናወግዛለን::
3. ይህንን የህዝብ ድምፅ ዝርፊያ እና የምርጫ ማጭበርበር ተከትሎ ለሚነሳው የህዝብ ተቃውሞም ሆነ መንግሥት ለወሰደው እና ለሚወስደው እርምጃ ተጠያቂው እራሱ ኢሓዴግ ነው።
4. የህዝቦች ህገመንግስታዊ መብቶች በተጣሰበት፣ በማፈንና በማስፈራራት ምርጫ አስፈፃሚዎች እና የምርጫ ታዛቢዎች ተባረው ምርጫ ተካሂዷል ለማለት አንችልም።
5. ህዝባችን የመረጠው ድርጅት ኦ.ፌ.ኮ /መድረክ/ የሚያደርገውን ቀጣይ የትግል ጥሪ ዝግጁ በመሆን እንዲጠብቁ እናሳስባለን ።
6. የወያኔን አፋኝ ስርአት እድሜ ለማሳጠር በትግል ላይ የምትገኙ ሃይሎች: ወያኔ ይህን ያህል ረጅም ዓመታት በስልጣን ላይ ሊቆይ የቻለው በራሱ ድርጅታዊ ጥንካሬ ሳይሆን የተቃዋሚ ሃይሎች ትግሉን በተቀናጀ ሁኔታ ያለመምራት በመሆኑ በቀጣይ ለሚደረገው ትግል የፖለቲካውን ክፍተት በመዝጋት ትግሉን ወደ ቀጣይ ምዕራፍ ለማሸጋገር በመተባበር እና ልዩነቶችን በማጥበብ እንድንታገል ጥሪ እናቀርባለን።
ትግሉ ይቀጥላል !!!!!!!!
የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ አለም አቀፍ ድጋፍ ሰጪ ቡድን

ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም፣ ዶ/ር ደብረጽዮን ወይስ ዶ/ር ቴዎድሮስ? ቢቢሲ ቀጣዩ የሀገሪቱ መሪ ስለሚሆነው ሰው ከወዲሁ ይተነብያል -

Current Prime Minister, Hailemariam Desalegn (L), is favourite to retain the post but faces competition from leading challengers Debretsion Gebremikael (C) and Tewodros Adhanom (R) Current Prime Minister, Hailemariam Desalegn (L), is favourite to retain the post but faces competition from leading challengers Debretsion Gebremikael (C) and Tewodros Adhanom (R)
ቢቢሲ ስለከትናንት በስቲያው አምስተኛው የኢትዮጵያ ምርጫ ከዘገቡት ታላላቅ ሚዲያዎች በቀዳሚነት ይጠቀሳል፡፡   ቢቢሲ(BBC)
በዚሁ ዘገባው የምርጫው ጊዜያዊ ውጤት በአንድ ሳምንት ውስት የሚታወቅ እንደሆነ ቢገልጽም እንኳን ገዢው ኢህአዴግ ፓርቲ በዘንድሮው ምርጫ ያን ያክል ፉክክር እንደማይገጥመውና ማሸነፉም ከወዲሁ የተተነበየ መሆኑን ነው የገለጸው፡፡ የተቃዋሚ ፖለቲካ አባላትን፣ መራጮችንና የፖለቲካ ምሁራንን ተዟዙሮ የጠየቀው ይህ ዘገባ የኢህአዴግ ማሸነፍን የሚደግፍ አስተያየቶቻቸውን ያስነብበናል፡፡ ከዚህ ውጪ ኢህአዲግ ካሸነፈ የሀገሪቱ መሪ ማን ይሆናል የሚለውን ለማጠያየቅ የሞክረው ዘገባው የአሁኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ተቀዳሚ ተመራጭ ይሆናሉ የሚለው እንዳለ ቢሆንም ሌሎችም እንደ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም እንዲሁም በምክትል ጠቅላይ ሚነስትር ማእረግ የመልካም አስተዳደር ክላስተር አስተባባሪውና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ሚኒስትሩ ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል በፓርቲው ውስጥ ቀዳሚ ከሆኑ እጩዎችና አቶ ሀይለማሪያምን ተፎካካሪ ይሆናሉ ከሚባሉት ውስጥ ይጠቀሳሉ ሲል ነው ያተተው።

የሻዕቢያ “የተሀድሶ” ስትራተጂ አካሄዱና አንደምታው

issayas afewerkiየሻAቢያ “የተሀድሶ” ስትራተጂ Aካሄዱና Eንደምታው
Aክሊሉ ወንድAፈረው
ሜይ 22፣ 2015
በAቶ Iሳያስ Aፈወርቂ የሚመራው Aስመራ ላይ የተሰየመው የሻAቢያ መንግሥት ለ 23
ዓመታት የተከተለውን Aካሄድ Eንዳላዋጣው በመገንዘብ ይመስላል በተወሰነ ደረጃ ለየት
ያለ ገጽታን ለማሳየት Eና ራሱን Aለሳልሶና የሰላም Aባወራ ሆኖ ለመቅረብ በመሯሯጥ ላይ
ይገኛል። ይህ ምን መልክ ይዞ ነው የሚራመደው? ለሀገራችን Iትዮጵያስ ምን Eንደምታ
Aለው? የሚለው የዚህ ጽሑፍ ዋና Aላማው ነው።
የAቶ Iሳያስ Aፈወርቂና የሸAቢያ የኩርፊያና የማን Aለብኝ ዓመታት

Aቶ IሳAስ Aፈወርቂ Eና ድርጅታቸው ሸAቢያ Aስመራ ላይ Eንደመንግሥት ከተሰየሙ
በሁዋላ ስለራሳቸው Eጅግ የተጋነነ Eይታ ይዘው ነው ያካባቢውንም ሆነ Aለም Aቀፉን
ህብርተሰብ የተቀላቀሉት። በዚህም መሰረት በየሄዱበት በሽክላ Eቃ የተሞላ መደብር ውስጥ
Eንደገባ Eንሰሳ በግራም በቀኝም ያገኙትን ሁሉ Eያተረማመሱ ቆይተዋል። በዚህም
መሰረት ባጭር ጊዜ ውስጥ፣
• Eንደ Aውሮፓ Aቆጣጠር ከየመን ጋር በ 19961

• ከጅቡቲ ጋር ከ 1994 Eስከ 20082
• ከሱዳን ጋር ደግሞ ከ1994 Eስከ 200 ድረስ ዲፕሎማቲክ ግንኙነትን Eሰከማቋረጥ
የደረሰ ውዝግብ ውስት ገብተው ነበር3

• ከIትዮጵያ ጋር ደግሞ በ1998 ጦርነት ውስጥ ገብቷል።

ይህ ብቻ ሳይሆን Aቶ Iሳያስ Aፈወርቂ Eና ድርጅታቸው ሸAቢያ ከተለያዩ ሀገሮች ጋር
የሚያጋጥማቸውን Aለመግባባት በኩርፊያና ቶሎ ብለው በማካረር ዲፕሎማቲካ ግንኙነትን
Eስከማቋረጥ በሚደርስ Aካሄድ ለመቋጩት ሲሞክሩ ደግሞ ደጋግሞ ታይቷል። ይህ
Aያያዛቸው ባንድ በኩል ለራሳቸው ከሚሰጡት Eጅግ ተፈላጊ ነኝ፣ ታላቅ Aርበኛ ነኝ፣
ታላቅ የፖለቲካ ሊቅ ነኝ ወዘተ ከሚል Eጅግ የተጋነነ ግምት የሚመነጭ ሲሆን በሌላ
በኩል ደግሞ ያስተሳሰብ ደካማነታቸውን Eና ስሜትን የመቆጣጠር ችሎታቸው Eጅግ
ዝቅተኛ Eንደሆነ የሚወስዱትም Eርምጃ ሊያሰከትልባቸው የሚችለውን ጉዳት ማገናዘብ
Aለመቻላቸውን ያመለክታል።
በዚህ ድንገተኛ ኩርፊያ Eና ነገርን ቶሎ የማካረር ባህሪይና Eርምጃ Iሳያስ Aፈወርቂ Eና
ድርጅታቸው ሸAቢያ ራሳቸውን Eጅግ የከፋ ችግር ውስጥ የጣሉበት (ከIትዮጵያ ጋር
ከነበረው የ 998ቱ ጦርነት ውጭ) Aንድ ምሳሌ Eንዳውሮፓውያኑ Aቆጣጠር በ 2007
ከምስራቅ Aፍሪካ በይነ መንግስታት የልማት ድርጅት (Iጋድ) ውስጥ ኤርትራ ራሷን
ድንገት ማግለሏን በጽሁፍ ባስታወቀች ጊዜ ነበር4

1 http://www.ipsnews.net/1996/08/yemen-eritrea-hanish-islands-conflict-ends-questionsremain/
2 http://military.wikia.com/wiki/Djiboutian%E2%80%93Eritrean_border_conflict
3 http://news.bbc.co.uk/2/hi/africa/590910.stm
4 http://reliefweb.int/report/eritrea/eritrea-suspends-membership-igad
ይህ Eጅግ ድንገተኛ ያልተለመደና በዲፕሎማቲክ Aለምም Eንደ በሳል Eርምጃ
የማይታየው Aካሄድ Aቶ Iሳያስ Aፈወርቂን ፣ ድርጅታቸውንና Eወካላታለሁ የሚሏት
ኤርትራን ከAካባቢያዊ፣ Aህጉራዊውና Aለም Aቀፋዊ መድረክ Aግልሏቸው በምንም
መልኩ ድምጻቸው Eንዳይሰማ Aድርጓቸው ከEለት ወደ Eለት የተነጠሉ ብቸኛ ሆነው
ቆይተዋል።
ይህ ብቻ Aይደለም፣ Iሳያስ Aፈወርቂ Eንዳውሮፓውያን Aቆጣጠር በ2008 Aመተ ምህረት
ድንገት ተነስቶ Aለም Aቀፍ የEርዳታ ድርጅች ሁሉ ጠቅልላችሁ ከኤርትራ ውጡልኝ
ኣሉ፡፡ በወቅቱ የኤርትራ ህዝብ ችግር Aለበት፣ በረሀብም የሚሰቃየው ህዝብ ቁጥር ሰፊ
ነው፣ ይህን ጉዳይ ለመታደግ Eርዳታው ያግዛል ቢባሉም፣” ነገሩን ሁሉ Aጡዘው
“Eርደታችሁን ረሀብተኛ ለሆኑት ስድስት Eና ሰባት ሚሊዮን Iትዮጳያውያን ሕጻናት
ወይም በቅኝ ግዛት ለተያዙት (Oኪፔሽን ) የOጋዴን ሶማሌ ህዝብ ስጡት ነበር ያሉት” 5
ጉድ ሳይሰማ መስከረም Aይጠባም Eንዲሉ የEርዳታ ድርጅቶችን ድንገት ተነስተው
በጅምላ ማባረራቸው ያሰከተለው ትዝብት ሳይቀዘቅዝ፣ በሜይ 2008 ከAልጀዚራ
ቴሌቪዥን ፕሮግራም ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ፣ ተመልካችን ሁሉ በሚያሰደነግጥ ሁኔታ
ራሳቸውን ለመቆጣጠር Aቅቷቸው የተሳከረ Eና ካንድ “የሀገር መሪ” የማይጠበቅ
Aቀራረባቸው ሲታይ በሌሎች ዘንድ የነበራቸውን ጥቂት ከበሬታ ያሳጣቸው ይመስለኛል።6

ከላይ ከተጠቀሰው በተጨማሪ፤ “Aንችው ታመጭው Aንችው ታሮጭው” Eንደሚባለው
በ2007 ድንገት ተነስተው በኩርፊያ ከIጋድ ለቅቄ ወጥቻለሁ Eንዳላሉ ሁሉ በ2011
ደግሞ ድንገት ወደ ድርጅቱ Aባልነት ልመለስ ብለው የIጋድን በር ያንኳኩት ያው Aቶ
Iሳያስ ነበሩ። ይህ ብቻ ሳይሆን ወደ Iጋድ ለመመለስ ያቀረቡት ጥያቄ ደርሶናል ሆኖም
የዚህ Aይነቱ ጉዳይ ውሳኔ የሚሰጠው በድርጅቱ የመሪወች ጉባኤ ስለሆነ በትEግስት
ይጠብቁ ተብሎ ቢነገርም Eንዴት ይሆናል Aሁኑኑ ካላስገባችሁኝ ብለው በዲፕሎማሲው
Aለም Eጅግ ባልተለመደና Aሳፋሪ በሆነ መልክ ሳይጋበዙ መልክተኛ ልከው በስብሰባው
ጉባኤ ላይ ካልተሳተፍኩ ብለው ግርግር የፈጸመት ያው Aቶ Iሳያስ Aፈወርቂ ነበሩ።78

Eነዚህ ከላይ የተጠቀሱት መረጃወች Eንደሚያሳዩት፣ የAቶ Iሳያስ መንግስት ከምስረታው
ጀምሮ Eኔ ያልኩት ካልሆነ በሚል ዘዬ ፣ ባካባቢው የራሳቸውን የበላይነት ለማስፈን
ባደረጉት ሙከራ Eጅግ Aጥፊ የሆነ ባህሪን ሲያንጸባርቁ ለረጅም ጊዜ ቆይተዋል። ይህ
ሁኔታም፤ በስርAቱ ላይ Eጅግ ብዙ ተቃውሞ Aስነስቶባቸዋል፣ ከAካባቢውም ሆነ ከAለም
Aቀፉ ህብረተሰብ ነጥሏቸው ቆይቷል።

Aዲሱ የሸAቢያ Aካሄድ

5 https://www.youtube.com/watch?feature=player_embedded&v=UAXKsZ8OsWo
(ከ12ተኛው ደቂቃ ጀምሮ ያለውን ያዳምጡ)
6 https://www.youtube.com/watch?feature=player_embedded&v=UAXKsZ8OsWo
7 http://www.diretube.com/ethiopian-news/eritrean-representative-thrown-out-of-igad-meeting-inethiopia-video_e219074e8.html
8 http://www.africareview.com/News/IGAD+bars+Eritrea+from+Addis+Ababa+mee
ting/-/979180/1224476/-/5wmtfkz/-/index.html
Aቶ Iሳያሰ ወደስልጣን ሲመጡ ዴሞካራሲያዊ ብቻ ሳይሆን Aብዮታዊም ተብሎ
ሰለተገመቱ Eሳቸውም ቢሆኑ ዴሞካራሲን Eውን ለማድረግ Eችላለሁ በማለት Aለም
Aቀፉን ህብረተሰብ ለተወሰነ ጊዜ ከጎናቸው ለማሰለፍ ችለው ነበር። Aሁን ከ 20 Aመታትን
ያስቆጠረው ተግባራቸው ግን ዴሞክራሲያዊም፣ ዘመናዊም መሪ Eንዳልሆኑ በተግባር ሰላሳየ
ባካባቢው የሚከሰቱ ቀውሶችን EንደEግር ማስገቢያ በመጠቀም ታላላቆቹን መንግስታት
መልሶ ለመወዳጀት ከፍተኛ መገለባበጥ ለማድረግ ሲጣጣሩ ይታያል። ይህን ሲያደርጉ ግን
ቀደም ሲል ይዘዋቸው የሚጓዟቸውን ፍላጎቶች ፣ ለምሳሌ በሀገር ውስጥ ስልጣንን
በብቸኛነት ይዞ መቀጠሉን፣ Iትዮጵያን በተመለከተ ድንበሩን በሚፈልገው መልክ
ማስከለል Eና ከ1998 ጦርነት በሐላ የተቋረጠበትን ጥቅም መልሶ መመስረት በዋናት
ሳይቀየር ነው።
የAቶ Iያሳያስ Aዲሱ Aካሄድ በዋናነት የተጀመረው ባውሮፓውያኑ Aቆጣጠር በ2011
Aምባሳደር ግርማ Aስመሮምን ባፍሪካ Aንድነት ድርጅት Aምባሳደር Aድርገው በሾሙበት
ጊዜ ነበር። የAቶ ግርማ ሹመት ተራ Aምባሳደርነት ሙያ መጫወት ብቻ ሳይሆን የAቶ
Iያሳያስን Aዲሱን ዲፕሎማቲክ Aካሄድ በዋናነት Eንዲመሩም ነበር። Aምባሳደር ግርማ
በሀይለስላሴ ዘመን የIትዮጵያ Eግር ኳስ ብሄራዊ ቡድን ተጫዋች የነበሩና ሁዋላም
በIትዮጵያ ውስጥ የAቶ Iሳያስ መንግስት Aምባሳደር ሆነው ያገለገሉ ናቸው ። በዚህም
የተነሳ የIትዮጵያን ፖለቲከኞችና የዜጎችንም ባህሪይ “ ጠንቅቄ Aውቃቸዋለሁ” ባይ
ናቸው። Aምባሳደር ግርማ በቀጣይነት ይህንኑ የAቶ Iሳያስን Aጀንዳ በዋናነት
ለማስፈጸም በተባበሩት መንግስታት ዋና Aምባሳደር ተደርገው በ2014 መሾማቸው
ይታወሳል።9

ፈረንጆች “ብዙ ትንኞችን ከኮምጣጤ ይልቅ ማርን በመጠቀም ማጥመድ ትችላለህ” “ You
can catch more flies with honey than with vinegar “ Eንደሚሉት የAቶ Iሳያስ
መንግስትም Aላማውን፣ ራEዩን ወዘተ ሳይለውጥ ተቀባይነት ያሰገኛል ብሎ በገመተው
ሰላም Eና መረጋጋትን ባካባቢው ለማሰፈን፤ በግንባር ቀደምነት Aስተግባሪ መስሎ
መሯሯጥን መርጠወል። ለዚህም የሚከተሉትን Eንመልከት
በየመንና መካከለኛው ምስራቅ
ኤርትራን “ከIትዮጵያ ግኝ ገዥነት ነጻ ለማውጣት” Aቶ Iሳያስና ድርጅታቸው ባካሄዱት
ትግል የAረቡ Aለም በሁሉም መልኩ ግንባር ቀደም Aጋር Eንደነበር ይታወሳል።
በገንዘብና በዲፕሎማቲካ ብቻ ሳይሆን ለምሳሌ የIራኑ Aያቶላ ኮሚኒ በሳምንታዊ የEለተ
Aርብ (የጁምA) ሳይቀር ለኤርትራ ነጻነት ተከታታይ ጸሎት ያደርጉ ነበር።10
ከ“ነጻነት” በሁዋላ ግን Eንደተመኙት Eንክብካቤው Aልቀጠለም። በAረቡ Aለምና
በመካከለኛው ምስራቅ ቦታ ተነፍጓቸው የቆየት Aቶ Iሳያስ የየመን ግጭትና የሳውዲ
የሚመራው ትብብር ጣልቃገብነት ሲከሰት በግንባር ቀደምትነት ነው “ሁኔታውን
ለማረጋጋትና ሰላም ለማውረድ” በሚል ሰበብ ዘለው የገቡት። በዚህም መሰረት በAፕሪል

9 http://www.caperi.com/new-permanent-representative-of-eritrea-to-un-presentscredentials/

10 https://www.youtube.com/watch?feature=player_embedded&v (ከሰባተኛው ደቂቃ ጀምረው ያዳምጡ) 
2015 በሳውዲ Aረቢያ ጉብኛት Aድርገው በዚሁ ጉዳይ ላይ ከሳውዲ ንጉሰ Eና ሌሎችም
ባለስልጣናት ጋር ተወያይተው Aንዳንድ ስምምነትም ላይ Eንደደረሱ ተዘገቧል።11

በማስከተልም “ባካባቢው ሰላምን ለማምጣት” በሚል ሰበብ ቀደም ሲል ይረዷቸው ነበር
Eየተባለ በሚጠረጠረው የሁቲ Aማጽያን ላይ ጀርባቸውን Aዙረው በሳውዲ ለሚመራው ጸረ
ሁቲ ወታደራዊ ዘመቻ Eግረኛ ጦር ለመላክ Eንደሚፍልጉ ተናግረዋል።12
የAቶ Iሳያስ መንግስት በAንድ Eስላማዊ ሀገር የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ገብቶ መገኘቱ
በራሱ በኤርትራ የEስልምና ሀይማኖት ተከታዮች ዘንድ ሊያስከትለው የሚችለው Eንደምታ
ምን Eንደሚሆን ወደፊት የሚታይ ይሆናል። Aሁን ባለው ሁኔታ ግን፣ በውስጥ የሚመጣን
የህዝብ ቁጣ ለሳውዲ Aረብያና Aጋሮቿ ድጋፍ በመስጠት ሊመጣ ከሚችለው ጠቀሜታ
ጋር ሲወዳደር ሚዛን Aይደፋም ተብሎ Eንደተደመደመና ሊመጣ የሚችለውንም ግፊት
ለመቋቋም ቆርጠው Eንደተነሱ ያመለክታል።

በደቡብ ሱዳን
ቀደም ባሉት Aመታት ኤርትራ የደቡብ ሱዳን ነጻነት ደጋፊ ሆና መኖሯ ይታወቃል።
ደቡብ ሱዳን ነጻነቷን ከተቀናጀች በሁዋላ ግን Aቶ የIሳያስ ተጽEኖ Eዚህ ግባ የሚባል
Aልነበረም፡ በቅርቡ የደቡብ ሱዳን ድርጅቶች የEርስበርስ ግጭት ሲከሰትም Aቶ Iሳያስ
ችግሩን ለመፍታት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ምንም ቦታ Aላገኙም ነበር።
በIጋድ Aጋፋሪነት ተይዞ በነበረው የደቡብ ሱዳን ተፋላሚዎች Eርቅ ጉዳይ
በወያኔ/IህAዴግ ሊቀመንበርነት Eና በሌሎች የምሰራቅ Aፍሪካ መንግስታት ተባባሪነት
Eየተካሄደ ቆይቷል። በዚህ ሂደትም ኤርትራ ሙሉ በሙሉ ተገልላ ቆያታለች። በማርች
2015 የEርቅ ሂደቱ Eንደተደናቀፈ ግልጽ ሲሆን ነበር ኤርትራ ድንገት በዚህ ሁኔታ
ውስጥ ዋና ተዋናይ ሁና ለመቅረብ የሞከረችው። በዚህም መሰረት የደቡብ ሱዳኑን መሪ
Aስመራ ድረስ በመጋበዝ ላካባቢው ችግር ኤርትራ ዋና ተጫዋች ነች የሚለውን ማስጨበጥ
ነበር የሞከሩት። ዋና ምክራቸውም “ሊበጠብጢAችሁ ከሚፈልጉ መንግስታት ተጠንቀቁ”
የሚል ነበር።13
በAለም Aቀፍና ያካባቢ ድርጅቶች ውስጥ (Iጋድ)
ኤርትራ በ2007 ድንገት በቃኝ ብላ ከIጋድ Eንዳልወጣች Eና በወቅቱ ይህ Eርምጃችሁ
ትክክል AይደለምEና Aስቡበት ቢባሉም Aሻፈረኝ ብሎ የቆየው የAቶ Iሳያስ መንግሰት
ማንም ሳይጠይቀው ነበር ድንገት ተነስቶ በ2011 መልሶ ለመቀላቀል ጥያቄ ያቀረው።14
ይህ ጥረት Aቶ Iሳያስ ቀደም ሲል ያጡትን ቦታ መልሶ ለመያዝ የሚደረገው ሙከራ
Aንድ Aካል ለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም።

11 https://www.middleeastmonitor.com/news/middle-east/18347-saudi-arabia-eritreaagree-to-boost-red-sea-security
http://www.madote.com/2015/04/pictures-eritreanpresident-visits.html
12 http://ethiomedia.com/100leads/4825.html 13 http://sudantribune.com/spip.php?article54751
14 http://stesfamariam.com/2014/04/10/eritreas-igad-suspension-and-reactivation-decisionssacrosanct-and-legal/
ከIትዮጰያ ጋር
Iትዮጰያን በተመለከተ Iሳያስ Aፈወርቂ Aሁን የሚከተሉት Aካሄድ
• መሰረታዊ መስሎ የሚታያቸውን የድንበር ጉዳይ Eሳቸው በሚፈልጉት መንገድ
Eንዲደመደም ማድረግ
• ተቃዋሚውን በማግባባት፣ በመሞት ላይ ካለው የወያኔ ስርAት ጋር ማበር ሳይሆን
የመጭው ጊዜ ባለስላጣናት ጋር መወዳጀት
• ከIትዮጵያዊ ተቃዋሚዎች ጋር በማበር የቆሽሽውን የራሳቸውን ገጽታ ማደስና፣
ተቀባይነት ማግኘት
ጥቂቶቹ ናቸው።
ለIሳት ሰራተኞች በፌብሯሪ 2015 በኤርትራ ውስጥ የሰጡት Eጅግ ረጅም ቃለምልልስ
ተቃዋሚውን ለማግባባት ያዘጋጁት Eቅድ Aንድ ገጽታ ይመስላል። በዚያ ቃለ ምልልስ
ውስጥ Aቶ Iሳያስ፤ የ ኤርትራና Iትዮጵያን ጉዳይ የተመለከተ ስብሰባ በያካባቢው
መደረግ ያገባዋል “ በማለት የሰነዘሩት ምክር መሰል መመሪያ ፤ በቅርቡ ደግሞ በማይ 9
Eና 10 በዋሽንግተን ዲሲ “ ያፍሪካ ቀንድ ሁኔታን” የመረመረው ስብሰባ ይዘት በከፊልም
ቢሆን ከAቶ Iሳያስንና ከሻAቢያን የተሀድሶ ስትራተጂ ጋር Eጅግ Eንደሚጣጣም
ይታያል።

Aቶ Iሳያስ በIሳት ቃለመጠቅ ላይ Aበክረው የገለጹት ለIትዮጵያ Aንድነት የቆሙ፣
ለIትዮጵያ ከመልካም ነገር ውጭ የሚመኙት ነገር Eንደሌለ ፣ የIትዮጵያ ህዝብ መብት
Aለመከበር Eንቅልፍ Eንደነሳቸው Eና Eንዲያውም Iትዮጳያ መፈራረስ Aለበት ተብሎ
በተለያዩ መንግስታት ሲሰነዘር Eርሳቸው Aይሆንም ብለው Eንዳስቆሙ ወዘተ ነበር።
ይሀ ሁሉ ግን Iትዮጰያውያን ለAመታት ከምናውቀው የIሳያስ Aፈወርቂ ንግግሮች Eና
ተግባር ጋር Eጅግ የሚጋጭ ነው።
ሰበብ ፈልገው በIሳያስ Aፈወርቂ ለመጭበርበር በተጠንቀቅ ከሚጠባበቁት ወይም
በIትዮጵያ ኪሳራ ላይ ወዳጅነትን ለመመስረት ከሚፈልጉት በስተቀር ሁኔታውን
በትክክል ለመረዳት ለሚሞክር ሁሉ የAቶ Iሳያስ Aቋም Aሁንም ቀድም ሲል ከነበረበት
ቦታ ፈቀቅ Eንዳላለ መገንዘብ ያቻላል። ለዚህም በዚያው በIሳት ቃለምልልስ Eና
በተለያዩ የዜና Aውታሮች ውስጥ ደግመው ደጋግመው የ ኤርትራና የIትዮጵያ ድንበር
ጉዳይ ያለቀለት Eንደሆነና Iትዮጵያም “ከወረረችው የኤርትራ ግዛት መውጣት Eንዳለባት
መናገራቸውን ማስተዋል በራሱ በቂ መረጃ ነው” ባለፈው Aመት (2014) Aምባሳደር ግርማ
Aሰመሮም ለ ገለልተኛ Aገራት ስብሰባ ካደረጉት ንግግር ውስጥ ደግመው ደጋግመው
ያሰመሩበትም ይህንዩ ነበር። http://www.madote.com/2014/05/ambassador-girmaasmeroms-speech-at.html
በመጨረሻም በቅርብ በሜይ 9 Eና 10 የተካሄደው የዋሸንግተኑ የሰብAዊ መብት ስብሰባ
ጉዳዩ ስለ Aፍሪቃ ቀንድ ነው Eየተባለ፣ በመላው Aፍሪካ በመብት ረገጣ ያፋሪካዋ ሰሜን
ኮርያ (the north Korea of Africa) Eየተባለች የምትታወቀውን ኤርትራ የምታካሂደው
ግፍ በጨረፍታ Eንኳ Aለመናገሩ (Aንዳንድ ጠቃሚ የውይይት ዶክመንቶች መቅረባቸው
Eንዳለ ሆኖ) ጉባIውን ከሰብAዊ መብት ጉባኤነት ይልቅ የሻቢያ የህዝብ ግንኙነት መሳሪያ
Aስመስሎታል። ስለ ኤርትራ መናገር ካላሰፈለገ፣ ስብሰባውን የምስራቅ Aፍሪካ ብሎ
Aለመሰየም ነበር። የምስራቅ Aፍሪካ ከተባለ በሁዋላ ዋናዋን ሰብAዊ መብት ረጋጭ
Aለመተቸት ግን Eጅግ Aሰተዛዛቢ ብቻ ሳይሆን የIትዮጵያውያንን Eና ያርትራ
ወገኖቻችንንም ቁስል Aለመረዳት ነው።
የዚህ Aይነቱ Aያያዝ ደግሞ ለኤርትራም ሆነ ለቀሪው Iትዮጵያ ህዝብ የሚሰጠው
ጠቀሜታ የለውም። የAቶ Iሳያስ ዘግናኛ Aገዛዝ Eንኳንስ የኤርትራ ነዋሪዎች Aለም
Aቀፉ ህብረተሰብም በያደባባዩ የሚናገረው Eና Aበክሮ የሚታገለውም ነው።
ቢያንስ ቢያንስ Eኛ Iትዮጵያውያን Eንደ ዋቢ Eየጠቀስን የምንሟገትባቸው ድርጅቶች
ማለትም ሂውማን ራይትስ ዋች፣ 15 Aምንስቲ Iንተርናሽናል Eና ሌሎቹም ስለ Aቶ
Iሳያስ Aገዛዝ Eና የኤርትራ ነዋሪዎች ሰቆቃ የዘገቡትን በጥቂቱ ማየት በቂ ግንዛቤን
ይሰጣል።
የህዝቡን ትግልም ሆነ ነጻነት ማንም ሀይል Aያግደውም። የሌላው መብት ሲረገጥ የሁሉም
መብት Eንደተረገጠ ማሰታወስ ለሁሉም ተገቢ ነው። ሰለኤርትራ ነዋሪዎች መብት መረገጥ
Eኔ ምን Aገባኝ የሚል ሰው ደግሞ፣ የኔ መብት ስለተረገጠ ለመብቴ በማደርገው ትግል
ሌሎች Eርዳታ ይስጡኝ ብሎ መጠየቁ መሰረት የሌለው ነው16
በመጨረሻም የኤርትራን ጉዳይ በተመለከተ ብዙ Eጅግ ብዙ የሚያነጋግሩ ጉዳዮች Eንዳሉ
መረዳት ተገቢ ነው፡ ይህን ለመረዳት ደግሞ በሀገር ቤት የሚነቃነቁ የIትዮጵያ ተቃዋሚ
ፓርቲወች (Aድርባይ የሚባሉት ሳይቀሩ) የሚሉትን ማዳመጥ በቂ ነው። በዚህ ውስጥ
ያልተዘጋውን የሀገራችንን Aጀንዳ ወደጎን ከማለት Aልፎ ለAቶ Iሳያስና ለመንግስታቸው
ፕሮፓጋንዳ፤ የህዝብ ግንኙነትና Aገዛዙን የማጠናከር ስራ ተባባሪ መሆን ግን ሀላፊነት
የጎደለው ብቻ ሳይሆን መስመር ማለፍም ጭምር ይሆናል።
ማጠቃለያ
የAቶ Iሳያስ ያለፉት ጥቂት Aመታት የተሀድሶ Eንቅስቃሴ Aገዛዛቸውን ከደረሰበት
የውስጥም የውጭም መገለል Eና የፖለቲካ ግፊት፣ Aላቅቆ Eንደገና ለማንሰራራት
የሚደረገው ጥረት Aካል ነው።
Aለም Aቀፍ ሁኔታው ያመቸኛል ባሉት መንገድ Aቶ Iሳያስ ራሳቸውን Eንደገና
Aጠናክረው Eየተንገዳገደ ያለው Aገዛዛቸውን መልሰው ለማጥናከር፣ Iትዮጵያን በተመለከተ
ደግሞ ነባር Aቋማቸውን ለማስፈጸም ያልተዘጉና በEንጥልጥል የሚገኙ Aጀንዳወችንም
በAለም Aቀፍ ግፊትና በተባባሪ Iትዮጵያውያን ለማስፈጸም ሁኔታውን Aያመቻቹ
ይገኛል።
Aንድ የAለም Aቀፍ ሁኔታዎችን የሚተነትን ጸሀፊ የዩክሬን ነጻነት ከየትኛውም ሀያል
መንግስት በላይ በደካማዋና ትንሿ ቡልጋሪያ መዳፍ ስር ሊሆን Eንደሚችል ገልጦ ነበር።
ይህን ያለውም፣ ራሽያ የIኮኖሚዋ መሰረት የሆነው የነዳጅ ምርቷን ወደውጭ ለማስተላለፍ
Eየሰራችው ያለችው የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ በቡልጋርያ በኩል ስለሆነ ደካማዋ
ቡላጋሪያ የቧኒቧውን ስራ Aልደግፍም ብትልና ብታቋርጠው ምን ያህል ታላቋን ራሽያን
ለማሽመድመድ Eንደምትቸል ለማሳየት ነበር።
የEኛም የነጻነት ትግላችንና ሀገራዊ ነጻነታችን በመሞት ላይ ለሚገኝ ጨካኝ ጸረ
Iትዮጵያ ሀይል ማንሰራሪያ ብቻ ሳይሆን በዚሁ ቡድን መዳፍ ስር በድጋሜ Eንዳይወድቅ

15 http://www.hrw.org/world-report/2014/country-chapters/Eritrea
16 https://www.youtube.com/watch?feature=player_detailpage&v=e2rP5alopBE
በጥንቃቄ ማሰተዋል ይገባል። ለዚህም በሬ ሆይ ሳሩን Aይተህ ገደሉን ሳታይ የሚለውን
የAበውን ብሂል Eናሰታውስ። ጎበዝ ነገሩ ሁሉ Eየተስተዋለ ቢሆን መልካም ነው።

4 የሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ታዛቢዎች ተደበደቡ * በክፍለሃገራት ኢሕአዴግ ራሱን በራሱ እየመረጠ ነው -

election 2015 ethiopiaሰማያዊ ፓርቲ የመደባቸው 4 የምርጫ ታዛቢዎች በገዢው ፓርቲ ተላላኪዎች መደብደባቸው ተዘገበ:: ምስራቅ ስቴ የተበደቡ የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢዎች 1. ታደለ ግዛው (ዳጉት ቀበሌ) 2. እሱ ያውቃል በላይ (ለዋዬ ቀበሌ) 3. ገብሬ ተፈራ (ደንጎልት ቀበሌ) 4. መልካሙ ነጋ (አበርጉት ቀበሌ) በተጨማሪም ይስማው ወንድሙ የተባለ የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢ በጥይት መሳቱን የሰማያዊ ፓርቲ አስተባባሪዎች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ***** ‹‹ጋሞ ጎፋ አርባ ምንጭ ከተማ ብርብር ምርጫ ክልል የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢዎችን አዋክበው እንዳይታዘቡ አድርገዋል፡፡ ካቢኔ ኮሮጆው ክፍል ድረስ ገብተው ኢህአዴግ ላይ ምልክት እንዲያደርግ ጫና አድርገዋል፡፡ በተለይ ሴቶችንና ሽማግሌዎችን በግዳጅ ነው ያስመረጧቸው፡፡ በአጠቃላይ በጋሞጎፋ የህዝብ ታዛቢዎች የተመረጡት በኢህአዴግ ነው፡፡ ይህን ቀድመንም ተናግረናል፡፡›› አቶ ወንድሙ የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩ ***** ‹‹ከ8 ሰዓት በኋላ ካርዱን ራሳቸው ነው እያጠፉ እያስገቡ ያሉት፡፡ ማንን ነው የምትመርጡ ሲባል የምንመርጠውን እኛ እናውቃለን ያሉት ተደብድበዋል፡፡ በተለይ አንዱ ይህን የሞተ መንግስት አልመርጥም ብሎ በመናገሩ ክፉኛ ተደብድቧል፡፡ ህዝብ በዱላ ሊያልቅ ነው፡፡›› ከስናን ወረዳ ***** ‹‹ትናንት ቤቴ ተከቦ አደረ፡፡ እንደምንም ምርጫ ጣቢያ ልመርጥ ስሄድ መምረጥ አትችልም ተብዬ ተመለስኩ፡፡ የቀበሌ አመራሮች ናቸው የሚመርጡት›› ቄስ ዋልተንጉስ አባተ የሰማያዊ ፓርቲ የክልል ምክር ቤት ዕጩ/ከደጀን ***** ገዳም ሰፈር ምርጫ ጣቢያ አንድ እና ምርጫ ጣቢያ ዘጠኝ ሰማያዊ ፓርቲ በዕጣ ምክንያት ዕጩ ባለማቅረቡ ምክንያት ሰማያዊ የለም የተባሉ 10 ወጣቶች ‹‹ሰማያዊ ከሌለማ ማንንም አንመርጥም›› ብለው ሲወጡ ታፍነው ታስረዋል፡፡ **** ‹‹የኢህአዴግ አባላት ናቸው የምርጫ ወረቀቱን እየተቀበሉ ምልክት የሚያደርጉት፡፡ ታዛቢ የሚባሉት ራሳቸው የኢህአዴግ አባላት ናቸው፡፡›› ከዱር ቤቴ ***** ‹‹ባለስልጣናት ምርጫ ጣቢያው በር ላይ ቁጭ ብለው እጅ ይዘው እያስፈረሙ ነው፡፡ ከኢህአዴግ ውጭ እንመርጣለን ያሉ ወጣቶች ከአካበቢው ተባረዋል፡፡ ችግሩን ለሌሎች ይገልጻል የተባሉ ወጣቶች ስልካቸውን ተነጥቀናል፡፡ እኛ ከአካባቢው ርቀናል፡፡›› ስልጤ ዞን ላንፎሮ ወረዳ አርጢማ ቡላ ቀበሌ (ነገረ ኢትዮጵያ እንደዘገበው) -

የወያኔው ሚዲያ ኢሕአዴግ አ.አን እና ጎንደርን 100% አሸነፈ ሲል ዘገበ * ዶ/ር መራራና ዶ/ር በየነ ተሸነፉም አለ የወያኔው አይጋ -

የማያፍረው ወያኔ ይህ ሁሉ ሕዝብ ዶ/ር መረራ ጉዲናን ደግፎ አደባባይ ወጥቶላቸው ዶ/ር መረራ ተሸነፉ ሲል ከምርጫ ቦርድ በፊት በአይጋ ፎረም በኩል ይፋ አድርጓል:: የማያፍረው ወያኔ ይህ ሁሉ ሕዝብ ዶ/ር መረራ ጉዲናን ደግፎ አደባባይ ወጥቶላቸው ዶ/ር መረራ ተሸነፉ ሲል ከምርጫ ቦርድ በፊት በአይጋ ፎረም በኩል ይፋ አድርጓል:: የወያኔው ምርኩዝ ምርጫ ቦርድ የምርጫውን ውጤት ይፋ ሳያደርግ አይጋ ፎረም የተሰኘው አፍቃሪ ወያኔ ድህረ ገጽ፣ ወያኔ በአዲስ አበባ በአዲስ አበባ፣ በጎንደር ዞኖች 100% እንዳሸነፈ ገለጸ። ቁጥሩ እጅግ በጣም በርካታ ነዋሪ ድጋፉን ለመድረክ በሰጠበት፣ ዶር መራራ ጉዲና በተወዳደሩበት በአምቦ/ጉደር፣ እንዲሁም ዶ/ር በየነ በተወዳደሩበት ሃዲያ ዞን ኢሕአዴግ እንዳሸነፈም አይጋ ጠቅሷል። አዲስ አበባ፣ ሙሉ ጎንደር ዞኖችን 100% ወይኔ እንዳሸነፈ ነው የተገለጸው። አይጋ ከህወሃት ጋር በቅኝት የሚሰራ ድህረ ገጽ እንደመሆኑ፣ ወያኔ ይፋ ሊያደርገው የሚችለው ዉጤት ምን ሊሆን እንደሚችል የሚያሳይ እንደሆነ አንድንዶች ይናገራሉ። ሆኖም የሕዝቡን ስሜት አስቀድሞ ለመለካት ሆን ተብሎ እንደ ታክቲክ የተደረገ ዘገባ ሊሆንም ይችላል። አይጋ የሚከተለውን ነው የዘገበው “Although some expected Dr Merara and Dr Beyene to reclaim their lost seat in parliament preliminary count suggests EPRDF has won both seats and 100% sweep in the Capital City as well as other regions! The only region opposition has a chance to win some seats is in Amhara Kilil but that is not certain either so far Gondor is all gone to EPRDF” ከዚህ ቀጥሎ ያለው በአምቦ/ጉደር መድረክን ደግፎ የተሰበሰበው ህዝብ ነው። እንግዲህ ይሄ ሁሉ ህዝብ እያለ ነው ወያኔ አሸነፍኩ የሚለው። -

Hiber Radio: ዶ/ር አክሎግ ቢራራ እና የአረናው አምዶም ገ/ሥላሴ ልዩ ቃለምልልስ ስለምርጫው * አገዛዙ የሕዝቡን ድምጽ ወደጎን አድርጎ ለራሱ የሰጠውን የምርጫ ውጤት ይፋ ለማድረግ ተዘጋጅቷል * በኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎች ተማሪዎች የሕዝብ ድምፅ እንዲከበር መጠየቅ ጀምረዋል * በአዲስ አበባ የ17 ዓመቷን ወጣት ሃና ሌላንጎን የደፈሩት ከ17 ዓመት እስከ እድሜ ልክ እስራት ተፈረደባቸውና ሌሎችም -

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋየህብር ሬዲዮ የግንቦት 16 ቀን 2007 ፕሮግራም
< …የምርጫው ውጤት አስቀድሞ የተገመተ ገዢው ፓርቲ የፈለገውን ድምጽ ለራሱ የሚሰጥበት የይስሙላ ነው … በአገር ውስጥም በውጭም ያለው ለውጥ እንዲመጣ የሚሰራው ሀይል ግን በአንድነት ፈጣን ውሳኔ መውሰድ አለበት። በአገር ውስጥ አብዮት መቀስቀስ እንዲችል… >
ዶ/ር አክሎግ ቢራራ የአገር ቤቱን የይስሙላ ምርጫ አስመልክቶ ለህብር ሬዲዮ ከሰጡት ማብራሪያ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)
<…በምርጫው ድምጽ መሰረቅን አስመልክቶ ገበሬውም ተማሪውም መምህሩም በአጠቃላይ ሁሉም ተመሳሳይ ግንዛቤ አለው። ድምጼ እንዳይሰረቅ ብሎ ነበር በድፍረት ስቃይ እየደረሰበት ታዛቢ ልሁን ለው….ተቃዋሚዎች ተባብረው በጋራ የህዝቡን ድምጽ ለማስከበርና አስገድደው ወደ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ለማምጣት መታገል ለባቸው …>
የአረና የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ ወጣት አምዶም ገ/ስላሴ (ከመቀሌ ምርጫውን አስመልቶ ለህብር ሬዲዮ ከሰጠው ማብራሪያ የተወሰደ )
በየመን ያሉ ኢትዮጵያውያን አጣብቂኝ እና የተባበሩት ሀይሎች የአየር ድብደባ ያደረሱት ጉዳቶች(ልዩ ዘገባ)
የኢሳት የገቢ ማሰባሰቢያ በቬጋስ(ከበዓሉ አዘጋጆች አንዱ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ)
አስተያየት በአገር ቤቱ ውጤቱ አስቀድሞ የታወቀ ምርጫ ላይ
ሌሎችም
ዜናዎቻችን
የተቃዋሚ የምርጫ ታዛቢዎች ጥቃት ሲፈፀምባቸው ዋለ
አገዛዙ የሕዝቡን ድምጽ ወደጎን አድርጎ ለራሱ የሰጠውን የምርጫ ውጤት ይፋ ለማድረግ ተዘጋጅቷል
ሕዝቡ በተዘረፈው ድምጹ ጉዳይ ተቃውሞ እንዳያቀርብ በሚል የሰብዓዊ ጥሰቱ ቀጥሏል
በኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎች ተማሪዎች የሕዝብ ድምፅ እንዲከበር መጠየቅ ጀምረዋል
በአዲስ አበባ የ17 ዓመቷን ወጣት ሃና ሌላንጎን የደፈሩት ከ17 ዓመት እስከ እድሜ ልክ እስራት ተፈረደባቸው
ኬኒያዊው ጠበቃ ፕሬዝዳንት ኦባማ ልጃቸውን ከዳሩልኝ ለጥሎሽ 50 ከብቶች 70 በጎችና 30 ፍየሎች እሰጣለሁ ማለቱ ተሰማ
የኤርትራ መንግስት ለአገሪቱ ወጣቶች ስድትና ሞት የሰብዓዊ ተሟጋች ድርጅቶች ጭምር ይጠየቃሉ አለ
ኢትዮጵያና ኤርትራ በኮንፊዴሬሽን እንዲዋሃዱ የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ጠየቁ
የሔጉ ውሳኔ በአዲስ መልክ እንዲቀየር አንድ ታማኝ የተቃዋሚ መሪ ገልፀዋል
ሁቨር በኔቫዳ ስራ እንዲጀምር ህጉ ፀደቀ
ስራ ከመጀመሩ በፊት ለተቆጣጣሪው ኩባንያ ማመልከት አለበት ተብሏል
የሚሉና ሌሎችም ዜናዎች አሉን

በአዲስ አበባ አቃቂ ክፍለ ከተማ የሚገኘው የተቃጠለው የአረቄ ፋብሪካ የኩማ ደመቅሳና አዲሱ ለገሰ ንብረት መሆኑ ታወቀ -

IMG_4071በአዲስ አበባ አቃቂ ክፍለ ከተማ የሚገኘው የአረቄ ፋብሪካ የኢህአዴግ ባለስልጣኖች መሆኑን ያወቁ ሰዎች እንዳቃጠሉት ታወቀ።በአዲስ አበባ አቃቂ ክፍለ ከተማ የሚገኘው አረቄ ፋብሪካ ንብረትነቱ የከፍተኞች የኢህአዴግ አመራሮች የኩማ ደመቅሳና አዲሱ ለገሰ መሆኑን የተገነዘቡ ወገኖች ይህ ፋብሪካ በሃገርና በህዝብ ገንዘብ ተሰርቶ ለባለስልጣኖች ጥቅም ብቻ መዋል የለበትም በማለት ግንቦት 11/2007 ዓ.ም እንዳቃጠሉት የሚስጥሩ አዋቂ ምንጮቻችን ከከተማዋ ገለፁ።
ፋብሪካው እየተቃጠለ በነበረበት ወቅት ሲመለከት የነበረው ነዋሪው ማህበረስብ፣ እሳቱን ለማጥፋት ምንም አይነት እገዛ ማድረግ ያለመቻሉን የተመለከቱት የስርዓቱ ካድሬዎች ወሮበላ ተከታዮቻቸውን በማሰባሰብ ነዋሪውን ህዝብ ማን አቃጠለው ከእናንተ አልፎ ሌላ የሚያውቅ የለም ተናገሩ እያሉ ላይና ታች ቢሉም እንኳን ነዋሪው ህዝብ ግን እኛ የምናወቀው የለንም የምታውቁት ካለ ደግሞ እናንተ ንገሩን በማለት ለጥያቄአቸው በጥያቄ መልክ በመመለስ ምንም አይነት መረጃ ከመስጠት እንደተቆጠበ ለማወቅ ተችሏል።

ሰበር ዜና የተሰረቀውን ምርጫ በማውገዝ በኦሮሚያ የዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ተቃውሞ መጀመራቸው ተሰማ -

Bilderesultat for dr merera gudina electionበኦሮሚያ የዮኒቨርስቲ ተማሪዎች በምርጫው ሂደት ተቃውሞዋቸውን አሰሙ የተሰረቀውን ምርጫ በማወገዝ ተቃዎሞ ተጀምሯል !!!! በአምቦ፣ ነቀሜት፣ ባሌ ..በብዙ ቦታዎች ካርድ የለም ተብለው ብዙ ዜጎች ምርጫ እንዳይመርይጡ ተደርጓል። በባህር ዳር ተመሳሳይ ችግር እንዳለ የደረሰን መረጃ ጠቁሟል።
ቁጣው የተጀመረው የወያኔ ኢቢሲ በብዙ ቢታዎች ኢሕአዴግ ከ90 በመቶ በላይ እየመራ እንደሆነ በመናገሩ ነው።
ያሉ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት የምርጫውን ዉጤት ወያኔ ነገ እንደማያሳወቅ ነው።

ትግስቱ አወሉ, ልደቱ አይሌው እና አያለ ጫሚሶ ምርጫዉ ችግር እንደሌለበት በኢቢሲ (EBC) ተናገሩ -

tigstuተዋዋሚዎች አገዛዙን እንኳን ደስ አለህ ማለት አለባቸው – ልደቱ አይሌው ኢቢሲ ትግስቱ አወሉን እና አያለ ጫሚሶን አቅርቦ ምርጫ ችግር እንደሌለበት ሲናገሩ ነበር። በዛሚ ደግሞ አቶ ልደቱ እኔ ለመምረጥ በሄድኩበት ምንም ችግር አላየሁም ብለዋል። ያ ብቻ አይደለም። “የምርጫውን ዉጤት በጸጋ መቀበል አለብን ! ተቃዋሚዎች ኢሕአዴግን እንኳን ደስ አለህ ማለት አለባቸው። ምርጫው ፍጹም የሆነ አምባግነንነት የነገሰበት ነው ማለት የላባቸው” ብለዋል። ልደቱ አያሌዉን ድርጅታቸው ኢዴፓ ሶስተኛ መንገድ የሚል ፖለቲካ እናካሂዳለን ይላሉ። ሆኖም አቶ ልደቱ ሶስተኛ አማራጭ የሚያራምዱ ሳይሆን፣ 100% የ”ህወሃት” ቃል አቀባይ መሆናቸውን ነው ያሳዩት -

ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የሰቆጣ አርሶደአሮች በረሃብ ምክንያት ተሰደዱ

sekotaኪላችን እንደዘገበው በሰቆጣ አካባቢ የተከሰተውን ከፍተኛ ድርቅ ተከትሎ አርሶደአሮቹ ወደ ምእራብ ጎጃምና ሌሎች የአማራ ክልል አካባቢዎች በመሰደድ ላይ ናቸው።
ተፈናቃዮቹ ከክልሉ ባለስልጣናትም ይሁን ከፌደራል መንግስቱ ምንም አይነት እርዳታ አለማግኘታቸውን ገልጸዋል።
ብዙዎቹ ተፋናቃዮች ወጣት ወንዶችና ሴቶች ሲሆኑ፣ በሰፈሩባቸው አካባቢዎች ስራ ሰርተው ራሳቸውን እንዲያስተዳድሩ እየጠየቁ ነው።
ተፈናቃዮቹ በዝናብ እጥረት ምክንያት ሰብላቸው ሙሉ በሙሉ መውደሙን ገልጸዋል።
መንግስት በአካባቢው ስለተከሰተው ድርቅ እስካሁን የሰጠው ምንም አይነት መልስ የለም።

ኢዴፓ የእሁዱን ምርጫ ውጤት ለመቀበል እንደሚቸገር ገለጸ

safe_imageየኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ፕሬዘዳንት ዶክተር ጫኔ ከበደ በትናንትናው ምርጫ ፓርቲያቸው ከሞላ ጎደል በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች ባሉ አባላቱና ታዛቢዎቹ ላይ ጫና ሲደረግባቸው እንደነበር ገለጹ፡፡
አጠቃላይ የምርጫው ሂደት አሳፋሪ ነው ያሉት ፕሬዘዳንቱ በርካታ ምርጫ ታዛቢዎቻችን የታዛቢነት ካርዳቸው ተነጥቆ ከምርጫ ጣቢያዎች ተባረዋል ሲሉ ከሰዋል፡፡ “በዚህ ሁኔታ የሚካሄድ የድምጽ ቆጠራ በትክክል ይካሄዳል ብለን አናምንም፡፡ የዚህን ምርጫ ውጤት ለመቀበልም አስቸጋሪ ሆኖ ነው ያገኘነው” ሲሉ ነው ዶክተርጫኔ ለድሬ ቲዩብ አስተያየታቸውን የሰጡት፡፡
ከዚሁ የፖለቲካ ዜና ሳንወጣ የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ፓርቲያቸው ለወደፊቱ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር በጥምረት ለመስራት አልያም በርካታ ፓርቲዎችን ባስጠለለው መድረክ ስር ራሱን ለማዋቀር እያጤነበት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ አቶ ዮናታን ፓርቲው ስለዚህ ሁኔታ ለመነጋገር ራሱን ዝግጁ እንዳደረገ የገለጹ ሲሆን በዚህ በኩል ራሱን ማጠናከር እንደሚፈልግም ጠቁመዋል፡፡

Friday, May 22, 2015

የአርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀመንበር ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያቀረቡት አስቸኳይ ጥሪ

Official Site for Ginbot 7 Movement for Justice, Freedom and Democracyየተከበራችሁ ወገኖቼ፤ ከሰላሳ በላይ የሆኑ ወገኖቻችን አይ ሲስ በተሰኘ ህሊና ቢስ፣ ፀረ-ሰው እና ፀረ-ስልጣኔ ቡድን በሊቢያ በአሰቃቂ ሁኔታ የመገደላቸው መርዶ ከትናንት ወዲያ ሚያዝያ 11 ቀን 2007 ዓም ደርሶን ኢትዮጵያዊያን በያለንበት በመሪር ሀዘን ውስጥ ነን። ዛሬ “እግዜር ያጥናህ” ወይም “እግዜር ያጥናሽ” የሚባል ሰው የለም። ሁላችንም ሀዘንተኞች ነን። ካጣናቸው ቁጥራቸው በብዙ እጥፍ የሚበልጥ ወገኖቻችን አሁንም በአራዶች መዳፍ ውስጥ መሆናቸው ሀዘናችን እጅግ የበረታ ያደረገዋል። ቁጥራቸው በትክክል የማይታወቅ ሆኖም በሺህ የሚገመቱ ኢትዮጵያዊያን ዛሬም ሊቢያ ውስጥ ናቸው። በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን አሁንም ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ ናቸው። ሌሎች በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ደግሞ በየመን ከሰማይም ከምድርም በቦንብና በጥይት እየተማገዱ ነው።

ለምንድነው ኢትዮጵያዊያን እንዲህ እሳት ውስጥ ለመማገድ የምንደፍረው? መልሱ ግልጽ ነው። አገር ውስጥ ተስፋ የለም፤ ወያኔዎች ተስፋችንን አጨለሙት። ከሳዉዲ በመከራ የተመለሱ ወንድሞቻችን ናቸው በሊቢያ በኩል ለመሰደድ ሲሞክሩ በአይ ሲስ ተይዘው የታረዱት። ወያኔዎች አገራችንና ክብራችን ዘረፉን። ወያኔዎች ስብዕናችንን ገፈፉን።
የዘመኑ ጥቂት የህወሓት ቱጃሮች ፎቆችን እየገነቡ በነሱ መጥገብ እኛ እንድናገሳላቸው ይፈልጋሉ። የኢትዮጵያ ሕዝብ መራቡ፣ መታረዙ፣ መደህየቱ እውነት ነው፤ ሆኖም ግን “ተራብኩ”፣ “ታረዝኩ”፣ “ደኸየሁ” ብሎ መናገር አይችልም። እውነት መናገር ያስቀጣል፣ ያስወነጅላል። በፍርደ ገምድል ችሎት እውነት መናገር “ሽብርተኛ” ያስብላል። እስር ቤቶችን የተሞሉት ለእውነት፣ ለፍትህ፣ ለነፃናትና ለእኩልነት በቆሙ ሰዎች አይደለምን?
በአይ ሲስ ያሳረደን ማነው? መልሱ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ግልጽ ነው። ያዋረደን፣ በአይ ሲስ ቢላዋ ያሳረደን ህወሓት ነው። እንደ አገርና እንደ ሕዝብ የደረሰብን ውርደት የትም ብንሄድ የምናመልጠው አልሆነም። በአገር ውስጥ የደረሰብንን ውርደት ለማምለጥ ስንሰደድ ውርደት ተከትሎን ይመጣል።
ወገኖቼ፤ ለኛ ለኢትዮጵያዊያን ከኢትዮጵያ የተሻለች አገር ሊኖረን አይችልም። ዛሬ የመሸሻ ጊዜ አይደለም። አገራችንን ከወያኔ ነጥቀን፤ በአገራችን ኮርተን በሰላም መኖር እንሻለን። ይህ መብታችን ነው። አገራችን የኛ ነች። አገራችን የጥቂት ወያኔዎች መፈንጫ አይደለችም።
ወገኔ፤ ዛሬ ሚያዝያ 13 ቀን 2007 ዓም በአርበኖች ግንቦት 7 ስም የማደርግልህ ጥሪ አድምጠኝ። በሀይማኖት፣ በብሔር፣ በጾታ ልዩነት ሳታደርግ ዛሬ በአንድነት እንደተሳህ አንድነትህን እንደጠበቅህ ቀጥል። አንድነትህን ለመሸርሸር ወያኔ የማይፈነቅለው ድንጋይ አይኖርም፤ ለወያኔ ዱለታ ጆሮህን አትስጥ። የወያኔ አገዛዝ እንዲያበቃ በአንድነት ተነስ። ዛሬ የጀመርከው ትግል እዳር ሳይደርስ እረፍት የለንም።
አርበኞች ግንቦት 7፣ ከትግራይ፣ ከኦሮሚያ፣ ከአፋር፣ ከኦጋዴን፣ ከጋምቤላ፣ ከቤሻንጉል ድርጅቶች ጋር በመጣመር የአገር አድን ኃይል የመገንባት ሥራውን እያጠናቀቀ ነው። እኛ ልጆችህ በብሔርም ሆነ በሀይማኖት ሳንከፋፈል፤ ከትግራይ እስከ ኦጋዴን፤ ከአፋር እስከ ጋምቤላ ሁሉንም የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ባካተተ ስብስብ ውስጥ አብረን ህወሓትን እየታገልን ነው። ይህ ትግል ግን የአንተ የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግል ነው። የትግሉም የአገሪቷም ባለቤት አንተ ነህ። ስለሆነም ተነስ! “እንቢኝ” በል። ዘርፈ ብዙ የትግል ስልቶችን በመጠቀም ወያኔን አዳክም። የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! በትግልህ ፍሬ የአገርህ ባለቤት ሁን።
የመከላከያና የፓሊስ ሠራዊት አባላት ሆይ!እናንተ የሕዝብ አካላት ናችሁ። የደረሰብንን ብሔራዊ ውርደት እያያችሁ፤ እሮሮዓችን እየሰማችሁ በሕዝብ ላይ መተኮስ በራሳችሁ ጭንቅላት ላይ መተኮስ ማለት መሆኑን ለደቂቃ እንኳን አትዘንጉ። ይልቁኑ ዛሬውኑ ነፃነትና ፍትህ ከጠማው ወገናችሁ ጎን ቁሙ።
የኢትዮጵያ ወጣቶች፤ የወጣትነት የፈጠራ ችሎቻችሁ መፈተኛው አሁን ነው። ለእያንዳንዱ ጥቃቅን ጉዳይ መመሪያ እስኪሰጣችሁ አትጠብቁ። እያሰላችሁ፣ እያጠናችሁ፣ እያደባችሁ፣ ወያኔን ታገሉ።
የታፈረች፣ የተከበረችና የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን እናደርጋለን።


ብርሀኑ ነጋ
የአርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀመንበር
ሚያዝያ 13 ቀን 2007 ዓም

ዋ ተማሪ መሆን!(ቁጥር ኣንድ)

11350515_693074467487256_9018663485103835397_nባለቅኔ መንግሥቱ ለማ ባውሮፓ በሚማርበት ወቅት ሜሪ ታደሰ ከተባለች ኢትዮጵያዊት ኮረዳ ጋር ጉም የሚያስጨብጥ ፍቅር ይዞት ነበር፡፡ዝርዝሩን “ደማሙ ብእረኛ”በሚለው ግለ-ታሪክ ውስጥ ተርኮታል፡፡ ያን መጽሃፍ በጎደሎ ቀን ላንዱ ኣውሸው ኣለመለሰልኝም፡፡ስለዚህ ቃል በቃል መጥቀሱን ወደ ጎን ትቼ በራሴ በራሴ ኣማርኛ ኣሳጥሬ ላወጋችሁ ተገድጃለሁ፡፡
(በነገራችን ላይ ይህ ወግ፤ ከዘንድሮው ምርጫ ጋር በግርጌም ሆነ በራስጌ ኣይገናኝም ፡፡ ወጉ ስለጠበሳና ስለ ግጥም ነው፡፡በዚህ ታሪካዊ ወቅት ላይ ስለ ጠበሳና ስለግጥም ማውጋትን እንደ ቅብጠት የምትቆጥሩ ኣርበኞች ከዚህ ተመለሱ፡፡)
ወደ ጨዋታው ስንመለስ፤መንግሥቱ ለማ ኮረዳዋ ከንፈር ላይ ከንፈሩን ለማስቀመጥ የሚያስችለውን የረጅምና ያጭር ጊዜ እቅድ ነደፈ፡፡ ሴትን በመማረክ ረገድ፤ በመንግሥቱ ለማ ጊዜ እና በኣባቱ በኣለቃ ለማ ዘመን መካከል ከባድ ልዩነት ኣለ፡፡በኣለቃ ለማ ዘመን ኣንዲት ሴት ከፈለግካት ጉልበትክን ተጠቅመህ ትማርካታለህ፡፡ መፍትሄው ኣበባ ሳይሆን የወይራ ሽመል ማበርከት ነበር፡፡ በፈረስህ ኣባረህ እንሥራዋን ጀርባዋ ላይ ሰብረህ ወደ ጫጉላ ይዘሃት ትዘምታለህ፡፡
መንግሥቱ ለማ ላቅመ- ኣምሮት በደረሰበት ዘመን ላይ የነበረው ስልጣኔ ሴቶችን ከተጠቂነት ወደ ኣጥቂነት ኣሸጋግሯቸዋል፡፡ ቆነጃጅትን “የሚታዩ እንጂ የማይበሉ ፍሬዎች” ኣድርጓቸዋል ፡፡ በዚያ ዘመን ህጉን ሳትጋፋ ልጂቷንም ሳታስከፋ ኣንዲት ቆንጆ ሴት ከንፈር ላይ ለመድረስ ረጅምና መራራ ትግል ማለፍ ይጠበቅሃል፡፡
“የደጋ ማርና፤ የቆንጆ ልጅ ከንፈር
ወድቀው ካልተነሡ፤ በዋዛ ኣይደፈር”
እንዲል ገጣሚው ሙሉጌታ ተስፋየ፤ በኣበበ ተካ ዜማ፡፡
ከእለታት ኣንድ ቀን መንግሥቱ ለማ የከጀላትን ልጅ እንደምንም ኣግባብቶ ሲኒማ ጋበዛት፡፡ሲኒማው እንዳከተመ፤ ቤቷ ድረስ ሸኝቷት በር ላይ ካደረሳት በኋላ በሲኒማው ውስጥ ያሉት ፈረንጆች እንደሚያደርጉት በ“ጉድ ባይ ኪስ” ሊያቀልጣት ከንፈሩን ከሰገባው መዘዝ ኣደረገ፡፡ከዚያ በኋላ ባካባቢው የተሰማው እምጵዋዋዋዋዋ የሚል ሳይሆን ጦዋዋዋዋዋዋ የሚል ድምጽ ነው፡፡የዚያን ቀን ምሽት በመንጌ ፊት ላይ ያረፈው ጥፊ ለኣማርኛ ስነግጥም ትልቅ ኣስተዋጽኦ ኣድርጓል፡፡
በጠራ ጨረቃ
በጠራ ጨረቃ፤ በእኩለ ሌሊት
ዓይኖቿ እያበሩ፤ እንደ ከዋክብት
ሳማት ሳማት ኣሉት፤ እቀፍ እቀፋት
ኣላወላወለም፤ ወጣቱ ታዘዘ
ወገቧን ኣንገቷን ፤በእጅና እጁ ያዘ
ምንም እንኳ ጡቷ፤ እንደሾህ ቢዋጋ
ጣቷ በመሆኑ፤ የጉማሬ ኣለንጋ
ጆሮ ግንዱን ሰማው ፤በጥፊ ሲናጋ
በጠራ ጨረቃ፤ በእኩለሌሊት
ዋ ጀማሪ መሆን፤ ዋ ተማሪነት
(መንግስቱ ለማ)
በምትመለከቱት ፎቶ ውስጥ የግጥሙ ቀስቃሽ የሆነችው ሜሪ ታደሰ ትታያለች፡፡ ፎቶ ግራፉን ባየሁ ቁጥር ኣይኔ ኣስቀድሞ የሚያርፈው መዳፏ ላይ ነው፡፡“ጆሮ ግንዱን ሰማው በጥፊ ሲናጋ”የሚለው መስመር ግነት ኣለመሆኑን ለመረዳት የእጇን መዳፍ ግዙፍነት ማየት ይበቃል፡፡

በጎንደር፤ በደብረብርሃን፤ በደሴ የወያኔ የምረጡኝ ፖስተሮች እየተቀደዱ ሲሆን ጎንደር ከዚሁ ጋር ተያይዞ ዜጎች እየታሰሩ ነው -

imagesየጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ሚያዚያ 1/2007 ዓ.ም በብአዴን ኢህአዴግ ስርዓት የተለጠፈውን የምረጡኝ መቀስቀሻ ፖስተር በማየት ለውጥ ለማያመጣ ስርዓት አንመርጥም እያሉ እየቀደዱት መሆናቸውን ምንጮቻችን ገለፁ፣
በጎንደር ከተማ ቀበሌ 04 በኢህአዴግ የተለጠፈውን የምርጡኝ መቀስቀሻ ፖስተር በማየት ለውጥ ለማያመጣ ስርዓት አንመርጥም በማለት እየቀደዱት መሆናቸውን የገለፀው ይህ መረጃ በህብረተሰቡ ተግባር የተናደዱት የስርዓቱ ካድሬዎች ምንም አይነት ወንጀል ላልፈፀመ ዜጋ አንተነህ የለጠፍነውን ፖስተር የቀደድከው እያሉ በማሰር ተግባር ላይ ተሰማርተው እንደሚገኙ ታውቋል፣
የደረሰን መረጃ ጨምሮ- የኢህአዴግን ፖስተር ቀድዳችኋል ተብለው በስርዓቱ ታጣቂዎች ከታሰሩት ውስጥም። ታደሰ ታፈሰ፤ አቶ ጫቅሌና ሌሎችም በርካታ ዜጎቻችን የሚገኙባቸው በእስር ቤት እየተሰቃዩ እንደሚገኙና ህብረተሰቡ ደግሞ በላዩ ላይ እያወረደ ያለውን ግፍ ለማስቆም ለሚመለከታቸው አካላት እያደረገ ያለው አቤቱታ ምንም አይነት ውጤት እንዳላመጣለት ከምንጮቻችን ያገኘውነው መረጃ አመለከተ፣
በተመሳሳይ በደብረብርሃንና ደሴ ከተሞች በየቀበሌው የተለጠፈ የብአዴን/ኢህአዴግን የምረጡኝ መቀስቀሻ ፖስተር ቀለም በመቀባትና በማበላሸት ልማት ይሁን እድገት ለማያመጣ ስርዓት አንመርጥም በማለት ተቃውሞአቸውን በመግለፅ ላይ እንደሚገኙ ምንጮቻችን ከቦታው አክለው አስታውቀዋል፣