Saturday, February 28, 2015

ምክትል ጠ/ሚ/ር ደመቀ መኮንን እና ሕላዊ ዮሴፍ ሲዋረዱ ተመልከቱ (Video)

ከአንድነት ሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ማህበርና ከሰማያዊ ሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ማህበር የተሰጠ የጋራ መግለጫ!!

እንደሚታወቀው የኢህአዴግ አገዛዝ ከጊዜ ወደ ጊዜ ጸረ ዲሞክራሲ አካሄዱ እየባሰበት የመጣና መሠረታዊ መብቶችን ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ ማፈኑን አጠናክሮ ቀጥሎበታል፡፡ በቅርቡ በአንድነትና በመኢአድ ፓርቲ ላይ አገዛዙ በሚያዝዛቸው የተቋማት ኃላፊዎች ቀጭን ትዕዛዝ የፓርቲዎቹ ሕልውና ለጥቂት ግለሰቦች ተላልፎ ተሰጥቷል፡፡ ይህ ዓይነቱ ህገ-ወጥ ድርጊት መቼዉም ቢሆን ተቀባይነት አይኖረውም! ለአገራችን የሠላማዊ የስልጣን ሽግግር ከባድ መሠናክል ሊሆን እንደሚችል ሁሉም ይገነዘባል ብለን እናምናለን፡፡ የኢህአዴግ የምርጫ ቦርድ እንዲህ ዓይነቱን ክፉ ስራ ሲወስን የአገራችንን የረጅም ሠላም አይተው ሣይሆን በአገዛዙ ቁንጮ ሰዎች በመታዘዝ በተቋም ስም የሚሠሩት የማደናገር የድንቁርና ተግባራቸዉ አንድ አካል ነው ብለን እናምናለን፡፡ ማህበራችን ይህን ድርጊት እጅጉን ያወግዛል። በመሆኑም ድርጊቱን በጋራ እንቃወማለን።
በምርጫ ቦርድ ስም የተወሰነው ህገ-ወጥ ውሣኔ ምክንያት መላ የአንድነትና የመኢአድ አባላት የፖለቲካ እንቅስቃሴአቸው ተገድቧል፡፡ ይሁን እንጂ ለአገራቸው ካላቸው ፅኑ ፍቅር አኳያ ትግሉን ለማስቀጠል ከሠማያዊ ፓርቲ ጋር አብሮ ለመሥራት የአባልነት ፎርም በመሙላት ትግሉን ቀጥለዋል፡፡ ይህ ዓይነቱ የአባላት ቆራጥ ውሣኔ ሊበረታታና ሞራል ሊሰጠው የሚገባ ነው ብለን እናምናለን! እኛም በሰሜን አሜሪካ የምንገኝ የሁለቱ የድጋፍ ማህበራት ሙሉ በሙሉ ድጋፋችንን እንደምንሰጥ እናረጋግጣለን፡፡
ስለሆነም በሰሜን አሜሪካ የምንገኝ የአንድነትና የሠማያዊ የድጋፍ ማህበራት በጋራ በኮሜቴ ደረጃ ተዋቅረን በዋና ዋና ጉዳዬች ላይ ማለትም በፋይናንስ፤ በእስረኞች ጉዳይ እና በዲኘሎማሲው ዙሪያ ሙሉ በሙሉ በትብብር አብረን እየሠራን የሰማያዊ ፓርቲንና ሌሎች በሃገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ሃይሎችን በጋራ ድጋፍ ለመስጠት ውሣኔ አሣልፈናል፡፡ በቀጣይም በጋራ የኮሚቴ ውይይቶችን እያደረግን ለሰማያዊ ፓርቲ የሚያስፈልጉ የሞራልና የማቴሪያል ርዳታ እንደምንሰጥ እናረጋግጣለን፡፡
የሰማያዊና የአንድነት ሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ማህበራት
የካቲት 19 2007 ዓ/ምANAASO-Blue

ያልከፈልነው እዳ አለብን፣ we are proud for you

Emperor Menelik II

አልጀዚራ ኢትዮጵያውያንን በፕሬስ ነፃነት ላይ አሟገተ

አልጀዚራ ኢትዮጵያውያንን በፕሬስ ነፃነት ላይ አሟገተ “መንግስትን ተችቶ መፃፍ በሽብር ያስጠይቃል” - ሶሊያና ሽመልስ 
“ሃሳብን የመግለፅና የፕሬስ ነፃነት በህገ መንግስቱ የተረጋገጠ ነው” - አቶ አብይ ብርሃነ

ሰሞኑን በአልጀዚራ ቲቪ በኢትዮጵያ የፕሬስ ነፃነት ዙሪያ በተካሄደ ውይይት ጋዜጠኞች፣ በሃገሪቱ ሃሳብን የመግለፅ መብት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሸረሸረ ነው ሲሉ የመንግስት ተወካይ በበኩላቸው፤ መንግስት የሃገሪቱን ደህንነት ከአደጋ የመጠበቅ ሚናውን እየተወጣ ነው ብለዋል፡፡ 
ባለፈው ማክሰኞ ምሽት “Ethiopian’s Media War” (የኢትዮጵያ ሚዲያ ጦርነት) በሚል ርዕስ በአልጀዚራ “The Stream” የተሰኘ ፕሮግራም ላይ በተዘጋጀው ውይይት በሽብርተኝነት የተከሰሰችው  የዞን 9 ጦማሪያን መስራችና አባል ሶሊያና ሽመልስ፣ የ“ፎርቹን” ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር ታምራት ገ/ጊዮርጊስ፣ የቀድሞ “አዲስ ነገር” ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ታምራት ነገራና በእንግሊዝ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የፐብሊክ ዲፕሎማሲና ኮሙኒኬሽን አማካሪ አቶ አብይ ብርሃነ ተሳትፈዋል፡፡ 
የዞን 9 ፀሐፊ ሶሊያና ሽመልስ፤ በኢትዮጵያ በህገመንግስቱ የሰፈረውን ሃሳብን የመግለፅ መብትን ተጠቅሞ መንግስትን መተቸት በቀጥታ በአሸባሪነት እንደሚያስጠይቅ ጠቁማ በአጋሮቿና በእሷ ላይ የተመሰረተው ክስም ለዚህ ማስረጃ እንደሆነ ተናግራለች፡፡ “ህገ መንግስቱ ይከበር ብለን ስለጻፍን ነው አሸባሪዎች ተብለን የተከሰስነው” ብላለች- ለአልጀዚራ፡፡ 
የቀድሞ “የአዲስ ነገር” ጋዜጣ መስራችና ዋና አዘጋጅ ታምራት ነገራ በበኩሉ፤ እሱና በርካታ  የሙያ አጋሮቹ ለስደት የተዳረጉት መንግስት ሊያሰራቸው ባለመቻሉ መሆኑን ጠቅሶ “አዲስ ነገር” ጋዜጣን አቋርጠው ከሃገር ከወጡ በኋላ በሁለቱ የስራ ባልደረቦቹ ላይ የቀረበው የአሸባሪነት ክስ በሃገሪቱ የፕሬስ ነፃነት መብትን ተጠቅሞ መንግስትን መተቸት ዋጋ እንደሚያስከፍል ያመላክታል ብሏል፡፡ 
የ“ፎርቹን” ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር ታምራት ገ/ጊዮርጊስ በሰጠው አስተያየት፤ ሃገሪቱ የፕሬስ ነፃነትን ሊያስጠብቁ የሚችሉ የህግ ማዕቀፎች ቢኖራትም ካለፉት 10 እና 15 ዓመታት ወዲህ በፖለቲካ፣ በርዕዮተ ዓለምና በህግ  ረገድ የፕሬስ ነፃነት እየተሸረሸረ መሆኑን ተናግሯል፡፡ ጋዜጠኞች በየጊዜው መታሰራቸው ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትና የፕሬስ ነፃነት ፈተና እንደበዛባቸው ያሳያል ብሏል - ታምራት፡፡ 
መንግስት የሃገሪቱን ህግ የማስከበር ኃላፊነት እንዳለበት በአፅንኦት የተናገሩት በእንግሊዝ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የፐብሊክ ዲፕሎማሲና ኮሙኒኬሽን አማካሪ አቶ አብይ ብርሃነ በበኩላቸው፤ ሃገሪቱ ካለችበት ነባራዊ ሁኔታ አንፃር የፕሬስ ነፃነቱ በአግባቡ ጥቅም ላይ ስለመዋሉ መንግስት ማረጋገጥ መቻል አለበት ብለዋል፡፡ የፕሬስ ነፃነትና ሃሳብን የመግለፅ መብት በህገ መንግስቱ የተረጋገጠ መሆኑን በመጥቀስም አቶ አብይ ተከራክረዋል፡፡ “አንዳንድ ሰዎች ይሄን መብት በአግባቡ እየተጠቀሙበት አይደለም” ያሉት አቶ አብይ፤ መንግስት ይሄን ዲሞክራሲያዊ መብት ለማጠናከር ከምንጊዜውም በላይ እየተጋ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የመለስ ትሩፋቶች ደራሲ ኤርሚያስ ለገሰ ለዲያቆን ዳንኤል ክብረት የጻፈው ግልጽ ደብዳቤ

ከአንድ ሰአት በላይ የፈጀውን ጥናታዊ ጵሁፍህን ሰማሁት። ሰምቼ ስጨርስ ደነገጥኩ። ከራሴም ጋር ለሰአታት ሙግት ገጠምኩ ። ኢህአዴግን ለቅቄ የወጣሁት ልቤ ermias copyየፈቀደውን በነጳነት ለመናገር ነውና የማውቀውን እና የሚሰማኝን መናገር እንዳለብኝ ተሰማኝ ። ርግጥ በሐይማኖት ጉዳዬች ላይ መናገር ከባድ እንደሆነና ዋጋ እንደሚያስከፍል ጠንቅቄ አውቃለሁ ። በሌላ በኩል የሚያውቁትን አለመግለጵም የፀፀት ዋጋ አለው። በመሆኑም ባለመናገሬ ከሚሰማኝ ሙግት መናገሩን ስለመረጥኩ የሚከተለውን አጭር አስተያየት ለመስጠት ተገደድኩ። 1• ያቀረብከውን መረጃዎች እንዴት እንዳሰባሰብካቸው የተገለፀ ነገር የለም። በተለይም በድህረና ቅድመ ምርጫ 97 ባሉት ሶስት አመታት( ከኃላም ከፊትም) ያቀረብካቸውን መረጃዎች ምንጭ ማወቅ እፈልጋለሁ ። ይህን ጥያቄ የማነሳበት መሰረታዊ ምክንያቶች ስላሉኝ ነው። 1•1• በኢትዮጵያ አቆጣጠር 2001 አ• ም• ኢሕአዴግ ለሕዝቡ ይዞለት የመጣው እቅድ ” በአክራሪነት ” ስም ሀይማኖቶችን ማዳከም ነበር። ይህንንም ለማቀጣጠል እንዲረዳው በኢህአዴግ ቢሮ፣ በኮሙዩኒኬሽን ጵ/ ቤት፣ ፌደራል ጉዳዬች እና ፌደራል ፓሊስ መረጃ እንዲሰባሰቡ ተደረገ። የእስልምና ጉዳዬች ላይ ዝርዝር ጥናቱን እንዲሰራ የቤትስራ የተሰጠው ሽመልስ ከማል ነበር። ዛሬ አንተ ካቀረብክልን ውስጥ ግማሹ የቃላት ለውጥ እንኳን ሳይደረግለት በሽመልስ ከማል ጥናታዊ ፅሁፍ የቀረበ ነበር። በወቅቱ እጅግ ከመደንገጤ የተነሳ ሽመልስ እንዴት እንዲህ አይነት ጥናት እንደሰራ ለማወቅ ከጀርባው መጓዝ ነበረብኝ ። መጓዜ ያልጠበኩትን ውጤት አመጣ። ሽመልስ በእስልምና ላይ ከፍተኛ ጥላቻ የያዘው በቤተሰቡ ውስጥ በተፈጠረው ምስቅልቅል እድገት መሆኑን ተገነዘብኩ። አባቱ በአንድ ወቅት የመስኪድ አስተዳደር ነበሩ። በኃላ የሳውዲ ጉዞ አድርገው ሲመለሱ አስተዳደሩን በመነጠቃቸው ከሀይማኖቱ በተቃራኒ ተሰለፋ ። ” ከመካ መዲና ደርሶ መልስ” የሚል መጵሀፍ አሳትመው ክርስትና ተነሱ። ስማቸውም ወደ ሀይለየሱስ ተቀየረ። ባስታወቀው እርምጃ ቤታቸው ተመሰቃቀለ።ወንድማማች እና እህታማቾች የሚጠሩበት የአባት ስም እስከ መለያየት ደረሰ። ባጭሩ የሽመልስ ፀረ -እስላም የመሆን ምንጩ ይሄ ነው። በመሆኑም በሽመልስ ሲቀርቡ የነበሩ ዳታዎችና ትንታኔዎች እንደወረዱ ከአንተ ሲቀርቡ ስሰማ የመረጃ ምንጭህን ተጠራጠርኩ። በተለይ ቴኳንዶ ፣አክሱም፣ መያዶች …ወዘተ ብለህ የገለጵከው የካርቦን ግልባጭ ሆኖ አግኝቸዋለሁ። 1•2• ሌላኛው ዳታ የሰበሰበው የፌደራል ጉዳዬች ሚኒስተር የነበረው ዶክተር ሽፈራው ከፓሊስ ጋር በመሆን ነበር። ዶክተሩ ያጠናቀረው መረጃ ተመሳሳይ ሲሆን በማጠቃለያው ” የኦርቶዶክስ አክራሪነት አለ” የሚል ነበር። የአክራሪነቱ አስኳል ማህበረ ቅዱሳን እንደሆነ አፅንኦት ሰጥቶበት ነበር። ይህ የዶክተሩ መረጃ በአንተ ጥናታዊ ፅሁፍ ላይ አልቀረበም ። ( ግምቴን አስቀምጬ ለማለፍ ይህን የዶክተር ሽፈራው ዳታና ትንታኔ ለሌላ የእስልምና መምህር እንዲደርሰው ይደረግና እንደአንተ እንዲያቀርብ ይደረጋል ። ርዕሱንም ” የኦርቶዶክስ አክራሪነት ” ብሎ እንዲጠራው ይደረጋል ።) 2• የመረጃዎቹ ምንጭ እንደተጠበቀ ሆኖ ኩነቶቹ ሲፈጠሩ ሀገሪቷ የነበረችበትን ፓለቲካዊ ሁኔታ ከግምት አላስገባህም። ለምሳሌ ከምርጫ 97 በኃላ በኦሮሚያ የተከሰቱት የሐይማኖት ግጭቶች የተጠነሰሱት በአቶ መለስና ደህንነት ጵ/ ቤት ሲሆን ዋነኛ አሰፈጳሚዎቹ እነ አባዱላና የኦህዴድ ካድሬዎች ነበሩ። ” ቅንጅት የክርስቲያን ጠበቃ ነው” የሚለው መልእክት የተቀረፀው አንተ በጥናታዊ ጵሁፍህ ላይ ” ውሸት ሲደጋገም እውነት ይሆናል” የሚለው መርሆ አቀንቃኝ የሆነው አቶ በረከት ነው። በየጉራንጉሩ መልእክቱን ያሰራጩት ደግሞ ” እኔ ከሞትኩ… ” በሚለው ብሂል እነ አባዱላና ጁነዲን ናቸው። በተለይ በድሬደዋ የጠነሰሱት ሴራ ባይከሽፍ ኖሮ ዘግናኝ እልቂት ይከሰት ነበር። በመሆኑም ከምርጫ 97 በኃላ የተከሰቱት ግጭቶች ( በተለይ በኦሮሚያ) ጠንሳሾቹ አሁን እየመሩን ያሉት ፓለቲከኞች ሲሆኑ መንስኤውም ፓለቲካው የፈጠረው ነበር። አንተ ግን በየትኛው ቦታ ላይ የፓለቲከኞቹን ሚና ማንሳት አልፈለክም ። ይልቁንስ መንግስት አበረደው፣ መከላከያ አረገበው ማለትን መርጠሀል። ጥናትህን ሰፋ ብታደርገው ኢትየጵያ ውስጥ አክራሪነት በዋነኛነት እየሰፋ የሄደው በፓለቲካው መበላሸት ምክንያት የተፈጠረ መሆኑን ትደርስበት ነበር። አሁንማ በድጋሚ ለማየት ጊዜው አልረፈደም። 3• በጥናታዊ ጵሁፍህ ላይ በአሁን ሰአት ያለውን የኢትየጵያ ሙስሊሞች ” ኢትዬጲያዊነት የተላበሰ፣ ሰላማዊና ፍትሐዊ ጥያቄ” ማንሳት አልፈለክም ። እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የተቃወሙት የመንግስት ጣልቃ ገብነት ነው።ኢህአዴግ ከሀይማኖቱ ላይ እጁን እንዲያነሳ ነው በሰላማዊ መንገድ እየጠየቁ ያሉት። አመራራችን በእኛ ይመረጡ፣ ተቋማችንን ራሳችን እናስተዳድር የሚል ነው። ለዚህ ደግሞ እኔ በየትኛውም ቦታና ሰአት ምስክር መሆን እችላለሁ። ታዲያ አክራሪን፣ አክራሪ ካልሆነው ለይቶ የማስረዳት አላማ ካነገብክ ለምን ፍትሐዊ የሆነውን ይህን ጥያቄ ሳታነሳ ቀረህ? እንደ ገዥዎቻችን ” የሙስሊሙ ጥያቄ አክራሪነት የወለደው ነው” የምትለን ከሆነም ወደ መድረክ አውጣውና እንነጋገርበት ። 4• አጀንዳህ ስለ ” ሙስሊም አክራሪነት ” ሆኖ ወደ ማጠቃለያህ ላይ በውጭ ሀገር ያለውን ሲኖዶስ ወደ መዝለፍ ለምን ተሸጋገርክ። ከአንደበትህ የወጣው ቃል ” የሐሰት ሲኖዶስ ተቋቁሞ መንጋ የማይጠብቅ ጳጳሳት ይሾማል ” የሚል ነው። ይህ ንግግር በራሱ አንድነት የሚያመጣ ነው? ውጭ ያለው ሲኖዶስ የሐሰት ነው / አይደለም ከሚለው ትርክት በፊት ይህ እንዲፈጠር ያደረገው ምክንያት ምንድነው የሚለውን ብታነሳ የተሻለ መልስ ታገኝ እንደነበር እገምታለሁ። ሐገር ቤት ያለውን ሲኖዶስ ማን ከጀርባ ሆኖ እንደሚያሽከረክረው ካላወክ በኢትዮጵያ ምህዳር ላይ መኖርህን እንድጠራጠር ያደርገኛል። 4• ሌላኛው ” ለምን አሁን?፣ ምን አዲስ ነገር አለ?” የሚል ጥያቄ እንዳነሳ አድርጐኛል ። የሙስሊሞች ሰላማዊ ትግል በተጠናከረበት፣ መንግስት በጅምላ ማሰር በጀመረበት ፣ ማህበረ ቅዱሳን ላይ በተዛተበት ወቅት ለምን የሚከፋፍል አጀንዳ ይዞ ብቅ ማለት ተፈለገ? የማን አጀንዳ ነው እየተራመደ ያለው የሚለውን ማየት ተገቢ ይሆናል Ermias Legess / የ መለስ ትሩፋቶች/ 

ESAT Yehasab Mengede 27 February 2015 | ESATTUBE

Bilderesultat for esat newsESAT Yehasab Mengede 27 February 2015 | ESATTUBE

Hiber Radio: የህወሓት አስተዳደር የክርስትና ዕምነት ተከታዮችን ሀሳብን በነፃ የመግለፅ መብት እየተጻረረ መሆኑ.. ኢትዮጵያ የበርበራን ወደብ ለመጠቀም ማቀዷ… የኢ/ር ይልቃልና የዶ/ር መረራ ወቅታዊ ቃለምልልስ… አንዳርጋቸው እንዲፈቱ የሚጠይቅ ከ70 ሺህ በላይ ፊርማ ተሰባስቦ ለእንግሊዙ ጠ/ሚ/ር መሰጠቱ… የቬጋስ የደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ አወዛጋቢው የሰበካ ጉባኤ ምርጫ ያስከተለው ክፍፍልና ሌሎችም

Hiber Radio: የህወሓት አስተዳደር የክርስትና ዕምነት ተከታዮችን ሀሳብን በነፃ የመግለፅ መብት እየተጻረረ መሆኑ.. ኢትዮጵያ የበርበራን ወደብ ለመጠቀም ማቀዷ… የኢ/ር ይልቃልና የዶ/ር መረራ ወቅታዊ ቃለምልልስ… አንዳርጋቸው እንዲፈቱ የሚጠይቅ ከ70 ሺህ በላይ ፊርማ ተሰባስቦ ለእንግሊዙ ጠ/ሚ/ር መሰጠቱ… የቬጋስ የደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ አወዛጋቢው የሰበካ ጉባኤ ምርጫ ያስከተለው ክፍፍልና ሌሎችም

Hiber Radio: ወይንሸት “ከምርጫው ተወዳዳሪ ዕጩነት እኔን እጣ አልደረሰሽም ብለው አስወጥተውኛል” ማለቷ… እቴጌ ጣይቱ በታሪክ ሲታወሱ የሚኖሩ ታላቅ ሴት (ልዩ ጥንቅር).. አበበ ገላው የሀሰት ዲግሪ የሰበሰቡ የስርዓቱ ሰዎችን የተመለከተ ሰሞኑን አዲስ መረጃ እንደሚያቀርብ ገለፀ… አገዛዙ በኢትዮጵያ በሙስሊም ወጣቶች ላይ የከፈተው የእስር ዘመቻ የድል ዋዜማ ጠቋሚ ነው መባሉና ሌሎችም

Hiber Radio: ወይንሸት “ከምርጫው ተወዳዳሪ ዕጩነት እኔን እጣ አልደረሰሽም ብለው አስወጥተውኛል” ማለቷ… እቴጌ ጣይቱ በታሪክ ሲታወሱ የሚኖሩ ታላቅ ሴት (ልዩ ጥንቅር).. አበበ ገላው የሀሰት ዲግሪ የሰበሰቡ የስርዓቱ ሰዎችን የተመለከተ ሰሞኑን አዲስ መረጃ እንደሚያቀርብ ገለፀ… አገዛዙ በኢትዮጵያ በሙስሊም ወጣቶች ላይ የከፈተው የእስር ዘመቻ የድል ዋዜማ ጠቋሚ ነው መባሉና ሌሎችም

ESAT Interview with Isaias Afwerki, President of the State of Eritrea, ...

ኢህአዴግ 98 ቢሊዮን ብር ነጠፈበት!! – “ታላቅ ሥራ ተሰርቷል! እናመሰግናለን!” ኦባንግ

birr4123111ይህ ዘገባ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ዘገባ ነው ኢህአዴግ በዓለም ባንክ በኩል ከእንግሊዝ የዓለምአቀፍ ልማት ተራድዖ መ/ቤት ሊለግስለት ታቅዶ የነበረው 4.9 ቢሊዮን ዶላር (98ቢሊዮን ብር) የገንዘብ ድጋፍ ነጠፈበት፡፡ አቶ ሬድዋን አልነጠፈብንም ይላሉ፡፡ ኦባንግ ሜቶ በበኩላቸው “የታላቅ ሥራ ውጤት ነው፤ እናመሰግናለን” ብለዋል፡፡ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ጥቅምት 2፤2005 (October 12, 2012) “ኢህአዴግ በ600 ሚሊዮን ዶላር አጣብቂኝ ውስጥ ገባ!! ብያኔው ከጸና ኪሣራው በቢሊዮን ዶላር ሊደርስም ይችላል!” በሚል ርዕስ የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ ያካሂድ ስለነበረው ፕሮግራም በዘገበበት ወቅት የሚከተለውን ዜና አትሞ ነበር፡- “ከ1998ዓም ጀምሮ የመሠረታዊ አገልግሎት ጥበቃ ፕሮግራም (Protection of Basic Services “PBS Program”) በሚል በአራት ተከታታይና ሁለት ተጨማሪ የገንዘብ ድጎማ የሚደረግባቸውን ፕሮግራሞች የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡ ይህ መሠረታዊ የሆኑ አገልግሎቶችን ለማሟላት ተወጥኖ የሚካሄድ ፕሮጀክት በትምህርት፣ በጤና፣ በእርሻ፣ በንጹህ ውሃ አቅርቦት፣ በገጠር መንገድ ሥራ፣ ወዘተ መስኮች ላይ እንዲውል (PBS I, PBS I-AF (Additional Financing), PBS II, PBS 11-AF, PBS-Social Accountability Program and PBS III) በማለት በተለያዩ ደረጃዎች ለተከፋፈለው ኦፐሬሽን ማስፈጸሚያ የሚውለው ገንዘብ ከ13ቢሊዮን ዶላር የሚበልጥ ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ ከፍተኛው የዓለም ባንክ ድርሻ 2ቢሊዮን ዶላር ሲሆን የተቀረው በሌሎች ለጋሽ መንግሥታት እና ድርጅቶች የሚሸፈን ነው፡፡ PBS III የተሰኘውን በሦስት ንዑሳን ፕሮግራሞች የተከፋፈለውን ፕሮጀክት ለማስፈጸም በአጠቃላይ የሚፈጀው 6.3ቢሊዮን ዶላር በላይ ነው፡፡” ይህ ለመሠረታዊ ልማት እንዲውል በዓለም ባንክ በኩል የሚሰጠውን ገንዘብ የሚደጉሙት ምዕራባውያን አገራት ሲሆኑ አንዷ ተጠቃሽ አገር እንግሊዝ ናት፡፡ ሆኖም ኢህአዴግ ከምዕራባውያን በዓለም ባንክ በኩል የሚያገኘውን ገንዘብ ለራሱ የፖለቲካ መጠቀሚያነት እያዋለው መሆኑ ለዓለም ባንክ ተደጋጋሚ መረጃዎች ሲቀርቡ ቆይተዋል፡፡ በተለይ ሟቹ መለስ በቀጥታ በሰጡት ትዕዛዝ 424 የአኙዋክ ተወላጆች ከተገደሉ በኋላ ኢህአዴግ በቦታው ያሰማራው የመከላከያ ሠራዊት በሥፍራው የሚኖሩትን ከመኖሪያ ቀያቸው በማፈናቀል እምቢ ያሉትን በግድ በማስነሳት፣ በመግደል፣ አስገድዶ በመድፈር፣ በማሰቃየት፣ ወዘተ ግፍ ሲፈጽም መቆየቱ በተለያዩ ዓለምአቀፋዊ ዕውቅና ባገኙ ዘገባዎች ሲነገር ቆይቷል፡፡ የዓለም ባንክ ለመሠረታዊ ልማት በማለት የሚሰጠው ገንዘብ ኢህአዴግ ወታደሮቹን የግፍ ሥራ ላይ በማሰማራት ደመወዝ የሚከፍልበት መሆኑን በመጥቀስ ወደ ኬኒያ የተሰደዱ የክልሉ ነዋሪዎች አቤቱታ አቅርበው እንደነበር ጎልጉል በወቅቱ የዘገበው ዜና ነበር፡፡ ““ኢህአዴግ አንገቱን ታንቋል”፤ዓለም ባንክ ርምጃ ለመውሰድ ጫፍ ደርሷል” በሚል ርዕስ የተጻፈውን ዜና ለማንበት እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ “ሚስተር ኦ” በመባል የሚጠሩት አኙዋክ ተወላጅ ኢህአዴግ የዕርዳታ ገንዘብ ለሰብዓዊ መብት ረገጣና ለራሱ የፖለቲካ መጠቀሚያነት እንዳዋለው በመጥቀስ የእንግሊዝ መንግሥት ከግብር ከፋይ ዜጎቹ የሚያገኘውን ገንዘብ አምባገነንነት እየደገፈበት መሆኑን በተለይም የዓለምአቀፍ ልማት ተራድዖ መ/ቤቱ ተጠያቂ ስለሆነ ከዚህ እንዲታቀብ ክስ መመሥረታቸው ይታወቃል፡፡ የክሱ ሒደት እየተካሄደ ባለበት ባሁኑ ወቅት ሚስተር ኦ በተደጋሚ እንደመሰከሩት ኢህአዴግ ነዋሪዎችን በግዳጅ ከቀያቸው በማፈናቀል የሚያካሂደው የግዳጅ ሰፈራና የመንደር ምሥረታ ሕገወጥ መሆኑ በመቃወማቸው በተደጋጋሚ ከፍተኛ ድብደባ እንደረሰባቸው ተናግረዋል፡፡ ብዙዎች ለአካላዊ ሥቃይ ደርሶባቸዋል፣ ሴቶች ክብረንጽህናቸው ተደፍሯል፣ አዛውንትና ህጻናት ለአሰቃቂ መከራ ተዳርገዋል፤ ይህንንም እርሳቸው እንዳዩ ሚስተር ኦ ይመሰክራሉ፡፡ የሚስተር ኦ የፍርድቤት ጉዳይ ወደ ውሳኔ ሊደርስ ባለበት ወቅት የልማት መ/ቤቱ ይህንን ዓይነት ውሳኔ መውሰዱ ከፍርድ ቤቱ ጉዳይ ጋር የሚያያዝ እንደሆነ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ይናገራሉ፡፡ የልማት ተራድዖ መ/ቤቱ ቃል አቀባይ ግን የመ/ቤታቸው ውሳኔ ከሚስተር ኦ የፍርድቤት ጉዳይ ጋር ያልተያያዘ እንደሆነ መናገራቸውን የእንግሊዙ ዘጋርዲያን ጋዜጣ ዘግቧል፡፡ መ/ቤቱ ለዚህ ውሳኔ የደረሰው ኢትዮጵያ “የዕድገት ስኬት” እያስመዘገበች በመምጣቷ የመሠረታዊ ልማት አገልግሎት የገንዘብ ዕርዳታ የማያስፈልጋት በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡ ይህ መጠኑ እጅግ ከፍተኛ የተባለውና ለኢህአዴግ ንጹህ የውጭ ምንዛሪ ምንጭ የሚያስገኝ ገንዘብ እንደነጠፈበት መሰማቱን አስመልክቶ ጋዜጣው የኢህአዴግ ፅ/ቤት ሃላፊ የሆኑትን ሬድዋን ሁሴን በጠየቃቸው ወቅት የመለሱት አልነጠፈብንም የሚል እንድምታ ያለው ነው፡፡ “እነርሱ ያሉት ዕርዳታውን አንሰጥም ወይም እናቆማለን ሳይሆን ዕርዳታ አሰጣጡ እንደገና ይዋቀራል ነው” በማለት ሬድዋን ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡ ሆኖም 4.9 ቢሊዮን ዶላር (98ቢሊዮን ብር) ዕርዳታ ለመስጠት ከዓለምባንክ ጋር ስምምነት የነበረው የእንግሊዝ የልማት ተራድዖ መ/ቤት “ኢትዮጵያ አድጋለች” በማለት በ2015/2016 በፓውንድ 256ሚሊዮን ብቻ (5በመቶ) ዕርዳታ ለመስጠት መወሰኑን የኢህአዴግ ጽ/ቤት ሃላፊው ሬድዋን ሁሴን አላብራሩም፡፡ ኢህአዴግ ለዕርዳታ የሚሰጠውን ገንዘብ ዜጎችን ለማሰቃየት፣ ወታደር ለመቀለብ፣ ወዘተ እንደሚጠቀምበት በተደጋጋሚ ዘገባዎች እና ማስረጃዎች ሲወጡበት የከረመ ቢሆንም ማስረጃዎቹን ተከትሎ የዓለም ባንክ በዕርዳታ አሠጣጡ ላይ አንዳች ውሳኔ እንዳያደርግ ብዙ ሲደክም ቆይቷል፡፡ በዚህም ምክንያት ጉዳዩ ውሳኔ ሳይሰጥበት እንዲስተጓጎል በማድረግ ለሁለት ዓመታት ያህል እንዲጓተት ማድረጉን ከጉዳዩ ጋር ቅርበት ያላቸው ወገኖች ይመሰክራሉ፡፡ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ኦባንግ ሜቶ ጉዳዩን ገና ከጅምሩ የሚያውቁትና ድርጅታቸው ለዓመታት ሲሰራበት የነበረ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ በመሆኑንም ይህንን የእንግሊዝ የልማት ተራድዖ መ/ቤት ውሳኔ የጋራ ንቅናቄያቸው ከደጋፊዎቹ ጋር በመሆን ያገኘው ድል እንደሆነ በፌስቡክ ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት አስታውቀዋል፡፡ “ገና ከጅምሩ ከጋራ ንቅናቄያችን ጋር በመሆን ይህንን ሥራ በመደገፍ የተባበራችሁንን ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ፤ ታላቅ ሥራ ተሰርቷል፤ እናመሰግናለን” ብለዋል “ጥቁሩ ሰው” ኦባንግ ሜቶ፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ አቶ ኦባንግ በተለይ ከጎልጉል ለቀረበላቸው አጭር ጥያቄ በሰጡት አስተያየት የጋራ ንቅናቄያቸው ደስታውን የገለጸው የልማት ገንዘብ በመቋረጡ ሳይሆን በልማት ስም የሚሰጠው ዕርዳታ ለሰብዓዊ መብት ረገጣ በመዋሉና ለዚህም ደግሞ ከበቂ በላይ ማስረጃ ድርጅታቸው ያለው በመሆኑ ነው፡፡ “አገር ብትለማ የሁሉም ደስታ ነው” ያሉት ኦባንግ አገርን በማልማት ሽፋን ደጋፊና ተቆርቋሪ የሌላቸውን ንጹሃን መበደልና የመኖር መብታቸውን መንፈግ ግን በየትኛውም መልኩ እርሳቸውም ሆነ አኢጋን የሚቀበለው እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡ ኢህአዴግ በቅርቡ አካሂዳለው ለሚለው ምርጫ እንደ ዕቁብ ዕጣ በማውጣትና በማስወጣት “አልደረሳችሁም” እያለ የተቀናቃኝ ፓርቲ አመራሮችን ከምርጫ እያስወገደ ባለበት፤ ሌሎችንም ሕጋዊ አይደላችሁም እያለ በተለጣፊ ድርጅት በማስበት ኅልውናቸውን እያሳጣ ባለበት ባሁኑ ወቅት በዜጎቹ ላይ የሚያካሂደውን መረን የለቀቀ የመብት ገፈፋ ለሥልጣን ያበቁትን ምዕራባውያንን ያስደሰተ እንዳልሆነ ይነገራል፡፡ የአውሮጳ ኅብረት ምርጫውን አልታዘብም ከማለቱ በተጨማሪ በሚዲያ ላይ የተጫነው አፈና በዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ድርጅት ይፋ ከሆነ ወዲህ ማነቆው በኢህአዴግ ላይ እየከረረ መምጣቱን ያሳያል፡፡ ኢህአዴግን ለሥልጣን ከማብቃት አልፋ ነፍጥ አንጋቢዎቹን የህወሃት መሪዎች ጸጉርና ጺም ከርክማ፤ ልብስ አልብሳ፤ ቋንቋ አስተምራ፤ የከተማ አኗኗር እንዴት እንደሆነ አሠልጥና፣ ቶሎ ባይገባቸውም ፕሮቶኮል አስተምራ፣ እስካሁንም ተንከባክባ እዚህ ድረስ ያቆየቻቸው እንግሊዝ እንዲህ ያለውን የውጭ ምንዛሪ ምንጭ ስታደርቅ “ቀጣዩስ ምን ይሆን?” የሚል ጥያቄ እንዲነሳ አድርጓል፡፡ “ምዕራባውያን መግደልም ማንሳትም ያውቁበታል” በማለት አስተያየት የሚሰጡ ወገኖች እንደሚሉት ቀጣዩ የኢህአዴግ ጉዞ በከፍተኛ ሁኔታ ለህወሃት ሲቀጥል ለኢህአዴግ አስጊ ከመሆን ባሻገር በውጭ ምንዛሪ እጥረት በየጊዜው የሚፈጠረውን ግሽበት በዕርዳታ ገንዘብ የሚያስተካክለው ኢህአዴግ እንዲህ ያለው የገንዘብ ማዕቀብ ክፉኛ ያነጥፈዋል ሲሉ ግምታቸውን ይሰጣሉ፡፡ ሙስናው መረን በለቀቀባት አገር ከሕዝብ እየተዘረፈ በተለያዩ አገራት ባንኮች በውጭ ምንዛሪ የሚከማቸውን ገንዘብ በሚካፈሉትም ላይ የድርሻ ቅነሳ የማስከተሉ ጉዳይ አብሮ የሚታይ እንደሆነ ይነገራል፡፡ ከዚህ ዜና ጋር ተያያዥነት ያለውን ጥቅምት 2፤2005 (October 12, 2012) ያተምነውን ዜና ከዚህ በታች እንደሚከተለው እንደገና አትመነዋል፡፡ ኢህአዴግ በ600 ሚሊዮን ዶላር አጣብቂኝ ውስጥ ገባ!! ብያኔው ከጸና ኪሣራው በቢሊዮን ዶላር ሊደርስም ይችላል! ኢህአዴግ ከዓለም ባንክ ያገኘውን 600 ሚሊዮን ዶላርና በተመሳሳይ ፕሮጀክት ወደፊት ሊያገኝ የሚችለውን ከፍተኛ ገንዘብ በተመለከተ አደጋ ውስጥ መውደቁ ተሰማ። ኢንስፔክሽን ፓናል (Inspection Panel – IP) የተሰኘ ተቋም ይፋ ያደረገው መረጃ እንደሚያመለክተው ኢህአዴግ የቀረበበት ውንጀላ ከተረጋገጠ የሚያጣው ገንዘብ በቢሊዮን ዶላር እንደሚደርስ ታውቋል። ይፋ የሆነውን መረጃ አስመልክቶ ከኢህአዴግ ወገን እስካሁን በይፋ የተሰጠ ምላሽ የለም። ግፍ የሚፈጽሙ መንግስታትን፣ በልማት ስም የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚፈጽሙ ወንጀሎችን መረጃዎችን በስፍራው በመገኘትና ከመሠረቱ ዘልቆ በመግባት አደራጅቶ ተጠያቂ የሚያደርገው ኢንክሉሲቭ ዴቨሎፕመንት ኢንተርናሽናል Inclusive Development International (IDI) ከሰለባዎቹ ውክልና ተሰጥቶታል። ተቋሙም በውክልናው መሰረት ለኢንስፔክሽን ፓናል በዝርዝር የሰለባዎቹን በደል በማተት አሳውቋል። የኢህአዴግ መከላከያ ሠራዊት የሚያደርሰውን እስራት፣ ግርፋት፣ አስገድዶ መድፈር፣ ከመኖሪያ ቦታ ማፈናቀል፣ የግዳጅ ሰፈራ ወዘተ በማምለጥ ወደ ኬንያ የተሰደዱ የጋምቤላ ነዋሪዎች ይህ ሁሉ ግፍ የሚፈጽምባቸው የኢትዮጵያ መንግሥት በልማት ስም ከዓለም ባንክ በሚያገኘው የዕርዳታ ገንዘብ በመሆኑ ለባንኩ በላኩት የአቤቱታ ደብዳቤ አመልክተዋል። አቤቱታውን መሠረት በማድረግ የሚደረገው ምርመራ ውጤት ይፋ ሲሆን፣ በሌሎች አገሮች እንደተደረገው በዕርዳታ ስም የሚገኝን ገንዘብ ኢህአዴግ ለፖለቲካ ተግባር መጠቀሙ ሲረጋገጥ፣ በመስከረም ወር መጀመሪያ አካባቢ ከዓለም ባንክ ተፈቅዶ የነበረው 600ሚሊዮን ዶላር ሊከለከል ይችላል፡፡ የዛሬ ዘጠኝ ዓመት አካባቢ በሟቹ ጠ/ሚ/ርና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ መለስ ዜናዊ ቀጥተኛ ትዕዛዝ በጋምቤላ ክልል በተለይ የተማሩ ወንዶች ላይ በማተኮር 424 ንጹሐን የአኙዋክ ተወላጆች በተገደሉበት ወቅት በሺዎች የሚቆጠሩት ወደ ጎረቤት አገር ኬንያ መሰደዳቸው ይታወሳል፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ክልሉ ሰላም የለም፡፡ በየጊዜውም የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ሲካሄዱበት ቆይቷል፡፡ በተለይም ለም የሆነውን እጅግ ሰፋፊ መሬት ለውጪ ባለሃብቶች በሳንቲም በመሸጥ ላይ የሚገኘው የኢህአዴግ አገዛዝ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቀድሞው የደርግ ዘመን ሲካሄድ ከነበረው ባለፈ መልኩ እጅግ በሚያሰቅቅ ሁኔታ በመንደር ምስረታና አስገድዶ የማስፈር ፖሊሲ ከመኖሪያ ቀዬ የማፈናቀል ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን የኦክላንድ ተቋም፣ ሂውማን ራይትስ ዎች፣ … የመሳሰሉ ድርጅቶች ያወጧቸው ዘገባዎች ይጠቁማሉ፡፡ ከ1998ዓም ጀምሮ የመሠረታዊ አገልግሎት ጥበቃ ፕሮግራም (Protection of Basic Services “PBS Program”) በሚል በአራት ተከታታይና ሁለት ተጨማሪ የገንዘብ ድጎማ የሚደረግባቸውን ፕሮግራሞች የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡ ይህ መሠረታዊ የሆኑ አገልግሎቶችን ለማሟላት ተወጥኖ የሚካሄድ ፕሮጀክት በትምህርት፣ በጤና፣ በእርሻ፣ በንጹህ ውሃ አቅርቦት፣ በገጠር መንገድ ሥራ፣ ወዘተ መስኮች ላይ እንዲውል (PBS I, PBS I-AF (Additional Financing), PBS II, PBS 11-AF, PBS-Social Accountability Program and PBS III) በማለት በተለያዩ ደረጃዎች ለተከፋፈለው ኦፐሬሽን ማስፈጸሚያ የሚውለው ገንዘብ ከ13ቢሊዮን ዶላር የሚበልጥ ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ ከፍተኛው የዓለም ባንክ ድርሻ 2ቢሊዮን ዶላር ሲሆን የተቀረው በሌሎች ለጋሽ መንግሥታት እና ድርጅቶች የሚሸፈን ነው፡፡ PBS III የተሰኘውን በሦስት ንዑሳን ፕሮግራሞች የተከፋፈለውን ፕሮጀክት ለማስፈጸም በአጠቃላይ የሚፈጀው 6.3ቢሊዮን ዶላር በላይ ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ የባንኩ ድርሻ የሆነውን 600ሚሊዮን ዶላር ቦርዱ መስከረም 5ቀን 2005ዓም አጽድቋል፡፡ በአስገድዶ ማስፈር፣ መንደር ምስረታና ሌሎች በርካታ የሰብዓዊ መብቶቻቸው የተጣሱባቸው በኬንያ የሚገኙ ሦስት የአኙዋክ ስደተኞች ተወካይ ድርጅቶች በሰሜን አሜሪካ ከሚገኙ ሌሎች የሰብዓዊ ድርጅቶች ጋር በመሆን ባንኩ ሊሰጥ የወሰነውን ገንዘብ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጥቅም ከመዋል ይልቅ ለኢህአዴግ የፖለቲካ ዓላማ ማስፈጸሚያ እየዋለ መሆኑን በመጥቀስ ለባንኩ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጂም ዮንግ ኪም መስከረም 6፤ 2005ዓም ደብዳቤ ልከዋል፡፡ በጥያቄያቸውም መሠረት በዓለም ባንክ በኩል ወደ ኢትዮጵያ የሚፈሰው ገንዘብ “በልማት ስም የኢትዮጵያ መንግሥት በጋምቤላ ክልል ለሚያካሂደው የመንደር ምስረታ እየዋለ ነው” በማለት ይከሳል፡፡ ሲቀጥልም የአኙዋክ ሕዝብ ለዘመናት ከኖረበት መንደር በማፈናቀል “የተሻለ አገልግሎት ይሰጣችኋል” በማለት በግድ የማስፈር ተግባር እየተፈጸመ ሲሆን “የተባለው አገልግሎትም ሆነ ለእርሻ የሚሆን በቂ ቦታ እንዲሁም ለከብቶች የሚበቃ የግጦሽና የውሃ ቦታ የላቸውም” በማለት ሰፈራውን የተቃወሙ ሁሉ እጅግ ከፍተኛ የሆነ የሰብዓዊ መብት ረገጣ እየደረሰባቸው እንደሚገኝ ጠቁሟል፡፡ ይህንን ግፍ የሚፈጽሙት ደግሞ የዓለም ባንክ ለመሠረታዊ አገልግሎት ጥበቃ ፕሮግራም (Protection of Basic Services “PBS Program”) ስም ለልማት እንዲውል ከሚሰጠው የዕርዳታ ገንዘብ በመንግሥት ተቀጥረው ደመወዝ የሚከፈላቸው ሠራተኞች መሆናቸውን ገልጾዋል፡፡ ይህንን ጉዳይ ከዓለም ባንክ ጋር እንዲነጋገሩላቸው Inclusive Development International (IDI) የተባለውን ድርጅት መወከላቸውን አስታውቀዋል፡፡ (የደብዳቤው ሙሉ ቃል እዚህ ላይ ይገኛል) ተመሳሳይ ጉዳዮችን በዓለምአቀፍ ደረጃ በመከታተልና በማስፈጸም የታወቀው IDI በመስከረም ወር አጋማሽ ላይ ጉዳዩ በቀጥታ ለሚመለከተው የመልሶ ማቋቋምና ልማት ዓለምአቀፍ ባንክና (International Bank for Reconstruction and Development (IBRD)) የዓለምአቀፍ ልማት ማኅበር (International Development Association (IDA)) ሥር ለሚገኘው የኢንስፔክተር ፓናል ባለ 18ገጽ ደብዳቤ ጽፏል፡፡ (የደብዳቤው ሙሉ ቃል እዚህ ላይ ይገኛል) ይህ የኢንስፔክተር ቡድን ከፍተኛ ሥልጣን ያለው መ/ቤት ሲሆን የዓለም ባንክ የሚሰጠውን ገንዘብ በትክክለኛ ቦታ ላይ አለመዋሉን በመጥቀስ ክስ የሚያቀርቡ ወገኖችን ጉዳይ በመከታተልና ቦታው ድረስ የራሱን ምርመራ በማካሄድ ውጤቱ ተግባራዊ እንዲሆን የባንኩን እጅ የማስጠምዘዝ ዓቅም ያለው እንደሆነ ከዚህ በፊት ያካሄዳቸው የምርመራ ውጤቶች ይጠቁማሉ፡፡ ይህ የመርማሪ ቡድን የቀረበለትን አቤቱታ መቀበሉንና በጉዳዩ ላይ የማንም ተጽዕኖ የማይደረግበትን የራሱን ምርመራ እንደሚያደርግ ከትላንት በስቲያ ባወጣው ባለ 8ገጽ መግለጫ ላይ አሳውቋል፡፡ ይህ የአቤቱታ ፋይል ቁጥር የተሰጠው ጉዳይ በግልባጭ ለባንኩ ፕሬዚዳንትና ለከሳሽ ተወካይ ድርጅት (IDI) እንዲደርስ ተደርጓል፡፡(የደብዳቤው ሙሉ ቃል እዚህ ላይ ይገኛል) የጎልጉል የሰሜን አሜሪካ ዘጋቢ ባጠናከረው መረጃ መሠረት ቡድኑ ከያዝነው ዓመት የጥቅምት አጋማሽ በኋላ ወደ ምስራቅ አፍሪካ ያቀናል። ቡድኑ ስደተኞቹ የሚገኙባቸውን፣ እንዲሁም ጉዳዩን በሚመለከት አስፈላጊ የሚላቸውን ቦታዎችና ግለሰቦች ሙሉ በሙሉ ያነጋግራል። ለስራው መሳካት የሚሆነውን ሁሉ በሚፈለግበት ቦታ በመገኘት በግንባር እንደሚያከናውን ለማወቅ ተችሏል። በተለያየ ጊዜ ኢህአዴግ የሚፈጽመውን ግፍና በደል በማደራጀት ሥርዓቱ ላይ ከትጥቅ የጠነከረ ትግል ማካሄድ እንደሚቻል አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል:: አያይዘውም በመላው አገሪቱ የሚፈጸመውን የሰብአዊ መብት ረገጣና የመብት ጥሰት በማሰባሰብ የኢህአዴግን የገንዘብ ምንጭ የማድረቅ፣ ብሎም በእርዳታ ገንዘብ የሚገነባቸውን የአፈና ተቋማት ማስለል እንደሚቻል አስታውቀዋል። ይህንን ታላቅ ስራ የሰሩትን አካላት ልምዳቸውን ለሌሎች በማካፈል አስፈላጊውን ስራ ሊሰሩ እንደሚገባም አሳስበዋል። (የመግቢያው ፎቶ የተወሰደው: ዘጋርዲያን)   

ሰበር ዜና: የወያኔ ሰላይ ከሆላንድ ተባረረ!


ከመሃል ያለው ኢዛና (እስራኤል ገደቡ) ለ'ኢንቨስትመንት" አዲስ አበበ ያለፈው ወር በሄደ ጊዜ
ከመሃል ያለው ኢዛና (እስራኤል ገደቡ) ለ’ኢንቨስትመንት” አዲስ አበበ ያለፈው ወር በሄደ ጊዜ

ሂሩት መለሰ – ከሮተርዳም
ሮተርዳም፣ ጥቅምት 28 ቀን 2015 – በስደት ስሙ አለማየሁ ስንታየው በመባል የሚታወቀው የህወሃት ሰላይ ከኔዘርላንድስ ተባረረ። አለማየሁ ስንታየሁ ቋሚ ነዋሪ ከነበረበት ከኔዘርላንድስ እንዲባረር የተደረገው በዚያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በከፈቱበት የስለላ ክስ መሆኑም ታውቋል።
የሮተርዳም ከተማ ፍርድ ቤት በአለማየሁ ላይ የተመሰረተውን የስለላ ክስና ማስራጃ ለረጅም ጊዜ ሲመረምር ከቆየ በኋላ የግለሰቡ የመኖርያ ፈቃድ እና ቤት እንዲነጠቅ፣ የሆላንድን ምድርም በአስቸኳይ ለቆ እንዲወጣ ውሳኔ አስተላልፏል። ከሆላንድ የምመራ ቡድን እንደተረዳነው ከሆነ – የግለሰቡ ቤት ሲፈተሽ ወያኔ የሰጠው እውነተኛ መታወቂያ እና በርካታ የስለላ ሰነዶች ተገኝተውበታል። በእርዳታ ስም የተቋቋመለት ድርጅትም ተፈትሾ ማስረጃዎች እንደተገኙ ለማወቅ ተችሏል።
alemayehu-sentayehu
ይህ ሰው ትክክለኛ ስሙ ዘለቀ ፎላ ይባላል። በደርግ ጊዜ የኢትዮጵያ ሰራዊት አባል ሆኖ ለረጅም አመታት አገልግሏል። ወያኔ ስልጣን ሲቆጣጠር ለፖለቲካ ተሃድሶ አዋሳ ደቡብ ጦር ቅጥር ግቢ ተላከ። በተሃድሶ በነበረበት ጊዜ ቁጥራቸው ብዙ የሆኑ የሰራዊቱ አባላትን ለወያኔ በማጋለጥ ታማኝነቱን ሲያሳይ እንደነበር የዚህ ዜና ዘጋቢ እማኝ ነው። የበርካታ ኢትዮጵያውያን ደም በእጁ ያለው አለማየሁ ከተሃድሶው ከወጣ በኋላ እስራኤል ገደቡ (የፓልቶክ ስሙ ኢዛና) ከተባለ ወታደር ጋር በመሆን የሰላም ተጓዥ ነኝ ብሎ በመገናኛ ብዙሃን ሲታይ ነበር። አለማየሁ እና ኢዛና በየሃገሩ እየዞሩ ስለ አዲሱ ስርዓት መልካምነት ሲሰብኩ ከረሙ። ከዚያም አስመራ ድረስ ተልከው የሻእቢያውን መሪ ኢሳያስ አፈወርቂን በወታደሩ ስም ይቅርታ ጠይቀዋል።
አለማየሁ እና ኢዛና ለወያኔ በሰሩት ውለታ ሆላንድ ገብተው እንዲቀሩ ተደረገ። ይህም የተደረገበት ምክንያት በአውሮፓ የሚኖሩ ኢዮጵያውያንን ተቃዋሚ በመምሰልና በረቀቀ መንገድ እንዲያበጣብጡና እንዲሰልሉ ነው።
በሆላንድ ሃገር የፖለቲካ ጥገኝነት ጠይቆ ለወያኔ ቡድን የስለላ ስራ መስራት ወንጀል ነው። አለማየሁ የሆላንድ ዜግነት ቢኖረው ኖሮ ቅጣቱ የከፋ ይሆን እንደነበር ጉዳዩን እየተከታተሉ ያሉ የህግ ባለሙያዎች ተናግረዋል።
የአለማየሁ መባረር በተሰማ ግዜ በሮተርዳም ያሉ የህወሃት ደጋፊዎች የአቤቱታ ደብዳቤ በመጻፍ ፊርማ ማሰባሰብ ቢጀምሩም ሊሳካላቸው አልቻለም። የአቤቱታ ደብዳቤው ግለሰቡ እዚህ የተወለዱ ሁለት ለጆቹን እየመጣ እንዲጎበኝ ይፈቀድለት የሚል ነበር።
አለማየሁ ስንታየሁ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከሆላንድ ተባረረ። ኢዛና ግን አሁን የተቃዋሚ ጭንብሉን አውልቆ በግልጽ ወያኔ መሆኑን መናገር ጀምሯል። ኢዛና የሆላንድ ዜግነት ቢኖረውም በሆላንድ ሃገር ስራ ሰርቶ አያውቅም። የቀንና ማታ ስራው በፓልቶክ ላይ ነው። ባለፈው ወር ኢትዮጵያ የተጓዙ ዲያስፖራ ኢንቨስተሮችን እየመራ በቴሌቭዥን መግለጫ ሲሰጥ አይተነዋል። ይህ ትርኢት የወያኔ ኢንቨስተሮች በጨበጣ እንደሚንቀሳቀሱም ያሳየናል

Mr. Obang Metho’s speech to the Ethiopian in Las Vegas, Nevada.


Oband Metho
Mr. Obang Metho

Thank you for inviting me to speak to you here in Las Vegas. We are here to celebrate two different occasions. First, this is the time that Ethiopians all over the world remember the victory of Ethiopians over the invading Italians in the Battle of Adwa in 1896. Secondly, we are here to commemorate 5th Year Anniversary of Hiber Radio and give our congratulations to its chief producer, journalist Habtamu Assefa, for his five years of dedicated communication service to Ethiopians. THANK YOU!
I would also like to thanks Hiber Radio committee members and supporters, namely Tamiru Geda, Dr Mulugeta Kassahun, Eyayu Wende, Girma Zaid, Yonas Cherkos, Yared Tadesse, Michel Emiru, Abereham Aklilu, Mesefen Haile, Rahel Solomon, Getu Amare, Hailu G/Mariam, Bizuwork G/Eyesus and others. You had a vision to create a radio program that connects the people to each other and that helps people know what is going on back home as well as more locally. Inside Ethiopia, information is denied, manipulated, and fabricated to advance the agenda of the TPLF/EPRDF power holders. In such an environment, our journalists and other members of the media have not fared well.
Ethiopia’s many committed journalists have been blocked at every turn from the free expression of ideas and information. The ethnic apartheid regime of the TPLF/EPRDF sees them as a serious threat to their control of Ethiopia. As a result, they end up jailed or fleeing the country for safety. Of those Ethiopians who flee the country, some continue to fulfill their calling even with few resources, like you. All of us should appreciate and support these people who are not only focusing on their own personal lives, but who are trying to do something of service to the people.
The role of the media:
The role of the media is vital in any society. It has the role of informing us about our surroundings, our way of life, our values, our principles, our morality, and our identity. For example, in a society where there is no media, how do you know the truth? When the people are denied the truth and information about what is going on around them, they are denied the opportunity to be creative, innovative and to move forward. Compare America and other free countries where there is an active, free and strong media to places like Ethiopia where an elite few purposely hold people back while the world is moving forward.

African democratic activist, author, and advisor to the SMNE, Dr. George Ayittey, has observed that because a well informed and well educated people are such threats to repressive regimes; the media and all its members and components are generally the first target of a dictatorial government. This includes radio and TV stations, newspapers, magazines and control of the Internet and telecommunications. Those in the media within Ethiopia must self-censor if they are to survive in their professional field; but for some, it becomes more difficult to compromise the truth then to face the repercussions for speaking out. Because of the dangers associated with speaking out, it makes it all the more important to support the voices of truth here in the free world. If Ethiopians are to join the global world, we in the Diaspora must help shine the light to expose the manmade darkness covering Ethiopia.

If we were in Ethiopia today, what I am going to say related to the Battle of Adwa, a defining moment in our history, might be considered a threat and not be allowed. However, because we are in a free country, I am free to speak about the victory of the Ethiopians over the Italian colonialists and reflect on it in light of the current repressive conditions in our country. The Battle of Adwa is a proudly acclaimed moment in our history that continues to shape our current identity; but, it forces us to ask, why has life not measurably improved for the vast majority of Ethiopians of today?     
Why is it that 119 years later, a repressive regime in Ethiopia has been forced on the people of Ethiopia? Why is it that this ethnic apartheid regime is now manipulating our history to create division between Ethiopians today? How should we respond? As I have previously stated, for Ethiopia to move forward, we must own the truth—which includes not only celebrating the proud moments of our history and learning lessons from it, but also accepting the bad and ugly parts so we might also learn from them. This must start by talking to each other rather than about each other—a way to bring about greater unity.

A primary factor leading to the victory at Adwa was the fact that greater unity among Ethiopians was achieved as Menelik and the people of Ethiopia came together to face a foreign enemy intent on the colonization of Ethiopia. What went wrong that we overcame Italy, but yet, have not overcome oppression?

It cannot be by chance that of the fifty-five countries of Africa, the only one never colonized is Ethiopia. Was this a God-given gift given to the people of Ethiopia for purposes we have not yet fully understood or utilized? Year after year we cannot celebrate the victory of our ancestors without considering our current state of affairs in Ethiopia. I will say a few words about Adwa, why it was an opportunity for Ethiopians and how we might use the lessons of Adwa to create a victory that will contribute to the lives of all our people as well as those beyond our borders. As we look at what happened then and what is happening now, we should look for the parallels; choosing to pursue what is good and figuring out how to avoid the traps.    

During the last part of the 19th century, most every African country had been colonized with the exception of Ethiopia. Colonization meant slavery, subjugation and exploitation—the lack of freedom, justice and self-determination. With it comes inequality and lack of opportunity. Power is in the hands of a few. The people are not allowed to think, speak or be educated unless natives align with the colonial power. The people have no choice of leaders as such a choice would lead to a reversal of power and the loss of unmerited privileges and wealth. Colonizers were greedy for resources, power, and glory. For Italy, it may have been all three. The fact that they were defeated so soundly was a source of deep humiliation that many believe led to the later invasion of Ethiopia in 1935.

Menelik came to power in 1889 during one of the most severe famines in Ethiopia’s history. Early on, he signed the Treaty of Wechale, which gave away the northern part of Ethiopia, later to become Eritrea, to Italy. In return, Menelik was assured of sovereignty over the remaining parts of Ethiopia; however, the treaty’s two versions were deceptively different. In his book, A Guide to Ethiopia, Phillip Briggs states, “What Menelik didn’t realize was that the Italians had inserted a clause in the Italian version of the document, but not in the Amharigna equivalent, which demanded that Ethiopia make all her foreign contacts through Italy, in effect reducing Ethiopia to an Italian protectorate.”

When it was presented at the Berlin Conference, the deception was accepted by the other members. He goes on to say, “Italy further undermined the spirit of the treaty when, in 1891, they successfully courted several Tigrean princes into alliance with Eritrea. When the princes revolted against the prospective colonizers in 1894, Italy was left with one course open to attain its goal of colonizing Ethiopia: military confrontation.” 

The Italians did not expect this kind of unification and believed they could depend on some of the vassal kings to rise up against Menelik, essentially hoping to defeat them by internal division. However, in 1895, the Tigrean princes instead joined forces with Menelik in order to all defend themselves from what Menelik described to be “a foreign menace.”[i] In other words, the Italians did not expect such a large force of united Ethiopians.

The Italians decided on a surprise attack on Adwa on Sunday, March 1, 1896 because it was a feast day in the Ethiopian Orthodox Church. They hoped the soldiers would be at church celebrating; however, the Ethiopians were ready for them. As a result, the Italians were greatly outnumbered. Two additional factors contributed to the victory over the Italians. Due to rain, some within the three detachments of Italians were slowed down in their movement, causing one group to arrive before the others. Additionally, the inaccuracy of the maps used by the Italians led to a further dividing of the Italian detachments from each other. An African guide is said to have alerted them to the faultiness of their maps, but the Italians decided to trust their maps instead. When the Ethiopians attacked the first detachment, the Italians were overpowered.
Among the fighters, were many Africans, including some from Eritrea, who were fighting with the Italians. When their defeat was certain, they ran, leaving the Italian officers alone. The Italian officers were then forced to surrender. Ethiopian troops then cut off the other two detachments.

This was the first time any African army had so soundly defeated the much-better equipped and militarily-educated Europeans. The defeat was so humiliating it resulted in a petition in Italy, signed by 100,000 Italians demanding an Italian withdrawal from Ethiopia. In 1941, the Italians again tried to take control of Ethiopia, but were again defeated, leaving Ethiopia to be the only African country to remain independent at the end of the scramble for Africa in both the 19th and 20th centuries. Many believe that the Europeans were so successful overall only because they were able to gain the help of African collaborators. Fomenting internal division has greatly contributed to the suffering of Africans both then and now. In the case of the Battle of Adwa, without the unification of Ethiopian ethnic groups, the outcome could have been vastly different.

Was this a lasting victory or only the short-lived victory of those who united together in 1896? We Ethiopians face the same obstacles in this next century. The 21st century scramble for Africa is in process. The colonizers are not the Italians. A Zulu adage says it all:  “The enemy of an African is he, himself.”

If Ethiopians are not free to choose our leaders; not free to express ourselves on the radio or in other media, not free to utilize our own land and resources; are we Ethiopians really better off? Who defeated us? Ethiopians cannot feed themselves. To get a job, many leave the country. Tribal affiliations open doors to basic rights that should be given to everyone simply based on our humanity and citizenship. Who did this to us? Was it an outsider or us? We are dealing with internal colonizers. We defeated the external, but not the internal. Among those much needed to overcome the new colonization of Ethiopia are our journalists and members of the media. The repression of this sector of our society has greatly impacted the flow of truthful information, but the dedication of these Ethiopians that leads them to speak out is like the sprout of grass growing between the hard rocks. Despite being fragile, these sprouts find a way to grow in difficult places. 

During the time of the 2005 election and the time leading up to that; most of the journalists realized, more fully than ever, the importance of the media in bringing change to the country. If Ethiopians were to succeed, the media had to play a bigger role. At that time, the majority of them did something that was unprecedented. They put aside competition and began a cooperative effort between themselves.

Many of them, including Journalist Habtamu Assefa, worked free of charge. Some even slept on the floor at newspaper offices to make sure the work was done. Sometimes, four or five of them would share offices to make sure that something new would come out every day, whether in the newspapers, in a magazine, on the radio, or through varying media sources. They supported each other. It became a goal that was not about themselves; but instead, it was about serving the people and the shared dream for a better Ethiopia for all. This is what made the 2005 election different to the very end.

We know what happened during the election when their dreams were crushed. Many of their friends and colleagues were put in jail; some lost their lives in the street protest following the flawed election. Of those remaining, the majority had to leave the country, becoming refugees. Ten years later, new voices are rising up, trying to revive the same struggle for freedom again. But many more obstacles exist now than at the time of the 2005 election. The Charities and Societies Proclamation has closed down civil society. The Anti-terrorism law has criminalized dissent. Despite it all, the champions of truth continue to put their lives on the line. Many of those names we already know; people like Eskinder Nega, Woubshet Taye, Reeyot Alemu, Aziza Mohamed, Temesghen Desalegn and many more.

Even after they were put in jail, it did not prevent a new wave of voices from the younger generation from emerging. They have risen from the ashes of these repressive laws. Some of them, like the Zone9 bloggers and the Oromo students who protested against the urban land grabs are now in jail.

The TPLF/EPRDF tried to extinguish their flame that was intent on exposing the truth about what was happening in the dark corners of Ethiopia. However, in trying to prevent their voices from being heard, the TPLF/ERPDF actually mistakenly created an international backlash due to their obviously unjust treatment.  
Because the ethnic apartheid regime is so afraid of the light, they continue to repress these emerging voices as well as other facets of the media industry. Even Ethiopian printing shops are monitored and face stiff penalties for publishing anything perceived to be anti-government. As we have learned from the recent report released by Human Rights Watch, Ethiopia is the second greatest jailor of journalists in Africa. We now have 26 exiled journalists in Kenya alone and many more in other places on the globe. Those still remaining in Ethiopia are at risk.

We can look at this in two different ways, the first, negatively and the second, positively. First, on the negative side, the regime is determined to do anything to close the mouths of those telling the truth. Secondly, on the positive side, the truth tellers are not giving up. The regime can silence ten of them at a time, but ten more will rise up. They can lock up the body, but they cannot lock up their conscience and commitment to truth and morality.

What should we do?
Appreciating the sacrifices of these great people and their families is not enough. We have to back them up and go to a greater extent in our support of them. I call on Ethiopian journalists abroad to establish an Ethiopian media institution to work together and become the voice of the silenced Ethiopians within the country. Civil society is blocked in Ethiopia, but consider just a few of the strategic people now living abroad: the former head of the Ethiopian Press Association, the former head of the Ethiopian Women Lawyers Association, the former head of theEthiopian Labor Association, the former head of the Ethiopian Teacher’s Association and the former head of the Ethiopian Lawyer’s Association, just to name a few. These organizations can do much to support the many Ethiopians who are suffering in places like Kenya or the families of Ethiopians who are in jail. However, there are even more possibilities than these if Ethiopians are wanting a more lasting victory over oppression.

All of these institutions should be re-established abroad. If it cannot be done from within Ethiopia, we can start the preparations for the development of strong institutions here and now—in every field. If the TPLF/ERPDF did not exist tomorrow, would we be ready? Do we think the next leadership group would be any different if there were no institutions to hold them accountable? Is it not simply “magical thinking”, left over from our childhood, that leads us to believe that simply getting rid of the TPLF/EPRDF will make everything better? If there were no strong institutions in place, would it not be easy to become the new dictator, never changing the oppressive system? We must be building them now—equipping, preparing, and strategically planning how to create a strong institutional framework for the country that can be ready to secure—not a short victory—but a sustainable one. There are strategic roles for many among us who will take the initiative and organize. We should not waste this precious time we now have.

Different people and groups can contribute, but success will come when many contribute their diverse skills, experience, gifts and knowledge to the whole while at the same time, sharing common core values—like the US Bill of Rights—that is inclusive of everyone. To make it clear, the Solidarity Movement for a New Ethiopia (SMNE) was established due to the human rights abuses that were widespread yet never confronted with one voice.

It was a destructive system that had to be replaced with a different worldview based on putting humanity before ethnicity or any other distinctions and caring about each other because no one is free until all are free. Look at the lessons of Adwa. Are we free? In other words, together, and with God’s help, it is up to we the people to bring about a transformation in Ethiopia that will lead to meaningful change. We need help from many directions as the SMNE cannot do it all, nor should we.

The SMNE will be concentrating on reconciliation, peace-building and establishing a healthier, more moral and more principled Ethiopian society, but to do this will require wide participation from many, including the faith community. Yet, many more areas need preparation—our media, security of our people, the constitution, the issue of private land ownership, business and industrial development, our judiciary, legal matters as they pertain to many areas of life, our educational system, our environment, the development of infra-structure, the areas of health and medicine, telecommunications, and how to deal with social problems—the list goes on.


Loving Ethiopia, celebrating the victory of Adwa, or being proud of being an Ethiopian without doing anything to make it better is not enough. Those remaining in Ethiopia should not hold on to the hope that someone will come and liberate them. Each Ethiopian should not simply count on others to do the work but do what you can to contribute.  

Who is it that God wants us—or Ethiopia—to be or to become? Does Ethiopia have a role to play to the benefit of those beyond our borders? If we were people who loved God and neighbor and who lived out God-given principles towards others, what would happen? If we did, would we see a new victory that would be more lasting? How do you liberate a nation that has fallen so far from its calling without spiritual transformation; meaning embracing the moral change? We must face the truth about ourselves. This means repenting of the wrongs we have done and facing the ugly part so we could be refreshed as people who live out truth, justice, compassion, integrity, reconciliation and generosity in our daily lives.

We can go back to the victory of yesteryears, but it is time for a new victory. In 1896, Ethiopians banded together to defend what they had. In doing so, they became the only country out of 55 African states to never be colonized. Perhaps God had a bigger purpose, not only for us but beyond us. Have we squandered this opportunity? It is not too late. Let us fight the battle for a more lasting victory that will bring about an Ethiopia that values others and holds on to what is important in this short life of ours. 

May God free us from our fears, our divisions, our apathy, our jealousies and whatever is standing in the way to our freedom, justice, equality, the rule of law and the blessings that come from living rightly. Like the Zulu proverb, may God help us to realize that the enemy of Ethiopia may be us, the people of Ethiopia, ourselves.

Thank you!
______________________
- See more at: http://www.zehabesha.com/mr-obang-methos-speech-to-the-ethiopian-in-las-vegas-nevada/#sthash.iKoEQtWa.dpuf

Thursday, February 26, 2015

አብዛኞቹ የመንግሰት ጋዜጠኞች የኢህአዴግ አባላት መሆናቸውን መረጃዎች አመለከቱ

Bilderesultat for etv newsየካቲት ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመንግስት የመገናኛ ብዙሃን ውስጥ ተቀጥረው የሚሰሩ ጋዜጠኞች አብዛኞቹ የኢህአዴግ አባላት መሆናቸውን ኢሳት በደረሰው የአባላት ስም ዝርዝርና የስራ ድርሻ ሰነድ ለማረጋገጥ ችሎአል።
በቀድሞው ኢቲቪ በአዲሱ አጠራሩ ኢቢሲ እና በኢትዮጵያ ሬዲዮ  ስር የሚሰሩ ዳይሬክተሮች፣ የዜና አዘጋጆች፣ የወቅታዊ ዘገባ አቀናባሪዎች፣ የስፖርት ጋዜጠኞች ፣ የካሜራ ባለሙያዎች፣ ቴክኒሻኖችና የተለያዩ የድጋፍ ሰራተኞች የህወሃት፣ የብአዴን፣ ኢህዴድ ወይም የደህዴግ አባላት መሆናቸው በሰነዱ ላይ በዝርዝር ተቀምቷል። ጋዜጠኞቹ የኢህአዴግን ፖሊስ ለህዝብ ከማስተዋወቅ ጋር በተያያዘ በየጊዜው በተደራጁበት ህዋስ ስር ግምገማ እንደሚደረግባቸውና ከኤ እስከ ዲ የሚደርስ ውጤት እንደሚሰጣቸው ከሰነዱ ለመራዳት ይቻላል።
የመንግስት የመገናኛ ብዙሃን በህዝብ ንብረት የሚተዳዳሩ ቢሆንም፣ የአንድ ፓርቲ አገልጋይ ለመሆናቸው ከዚህ በላይ ማስረጃ እንደሌለ አስተያየታቸውን የሰጡን አንድ የሚዲያ ባለሙያ ተናግረዋል።
ጋዜጠኞች የኢህአዴግ አባላት የሚሆኑት ጥቅማቸውን አስበው እንጅ በድርጅቱ አምነውበት ላይሆን እንደሚችል፣ ከሚሰሩት ስራ መናገር ይቻላል የሚሉት አስተያየት ሰጪው፣ አብዛኞቹ አጋጣሚውን ሲያገኙ ወደ ውጭ ወጥተው መቅረታቸው አባልነቱ ለጥቅም መሆኑን ያረጋግጣል ብለዋል፡፡ በሌላ ዜና ደግሞ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ህዳሴ የሚባለውን የኢህአዴግ አዲስ ልሳን ስፖንሰር እንዲያደርጉ እየታዘዙ ነው።
ኢሳት ከአዲስ አበባ ኢህአዴግ ኮሚቴ ጽ/ቤት በአስተዳደርና ፋይናንስ መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ቅድስት ወ/ጊዮርጊስ ተፈርሞ በወጣ ደብዳቤ ላይ ለማረጋገጥ እንደቻለው፣  በሁለት ሳምንት አንድ ጊዜ ታትሞ የሚወጣው ህዳሴ የተሰኘው የኢህአዴግ የፖለቲካ ልሳን ጋዜጣ በስፖንሰር ሺፕ ሰበብ በመንግስት መ/ቤቶች ባጀት ወጪ እንዲታተም እየተደረገ ነው።
ከጽ/ቤቱ የካቲት 5 ቀን 2007 ዓ.ም ከ5 በላይ ለሚሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር መ/ቤቶች በአድራሻቸው ተጽፎ የተሰራጨው ደብዳቤ እንደሚያመለክተው እያንዳንዱ መ/ቤት ስፖንሰር ለማድረግ የተስማማበትን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድነት ቅርንጫፍ በአዲስ አበባ ኢህአዴግ ኮሚቴ ጽ/ቤት ስም ወደሚታወቀው ባንክ አካውንት ገቢ እንዲያደርጉ የሚያሳስብ ሲሆን ለአንድ ጊዜ ማሳተሚያ እስከ 300,000 ብር እንዲከፍሉ ታዘወዋል።

ESAT Daily News Amsterdam February 26 2015 Ethiopia | ESATTUBE

ESAT Daily News Amsterdam February 26 2015 Ethiopia | ESATTUBE

Wednesday, February 25, 2015

የምርጫ ሂደቱ በኢህአዴግ ዓይን

•    ኢህአዴግ ዲሞክራሲን የሚያየው በእውነተኛ ገፅታው ነው 
•    ምርጫ በውጤት አይመዘንም፤ ዋናው ሂደቱ ነው 
የግንቦቱን ምርጫ እየተቃረበ ነው፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በምርጫ ሂደቱ ላይ የተለያዩ ቅሬዎችንና ተቃውሞዎችን እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡ ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግስ ምን ይላል? የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ አለማየሁ አንበሴ በኢህአዴግ ምክር ቤት ፅ/ቤት የህዝብና ውጭ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደስታ ተስፋውን በምርጫው ዝግጅትና ሂደት ዙሪያ አነጋግሯቸዋል፡፡ 
እስካሁን ያለው የምርጫ ሂደት ምን ይመስላል?
በኛ በኩል የምርጫው ሂደት በተቀመጠለት አቅጣጫ መሠረት እየሄደ ነው፡፡ ቀድመን ስትራቴጂና እቅድ አዘጋጅተናል፡፡ ካለፉት ምርጫዎች በተሻለ ለመንቀሳቀስ ዝግጅት አድርገን ነው እየሰራን ያለነው፡፡ ሃገሪቱን እንደሚመራ ገዢ ፓርቲና ተወዳዳሪ ፓርቲ ሁለት ሚናዎች ነው ያሉት፡፡ በመንግስት በኩል (ሀገሪቱን የሚመራ ፓርቲ እንደመሆኑ) ምርጫውን ፍትሃዊ፣ ዲሞክራሲያዊና ሠላማዊ በማድረግ ረገድ እየተሠራ ነው፡፡ እንደ ተወዳዳሪ ፓርቲ ደግሞ አሸናፊ ሆነን የምንወጣበትን አጠቃላይ ዝግጅት እያደረግን ነው፡፡ እንደ ድርጅት፣ በስነምግባር ደንቡና በአጠቃላይ በምርጫ ህጐቹ ሂደት ላይ የአሠልጣኞች ስልጠና በከፍተኛ የአመራር ደረጃ ሰሞኑን ተሰጥቷል፡፡ 
በየደረጃው ለሌሎችም ስልጠናው ይሰጣል፡፡ ካለፉት ምርጫ ልምዶች ተነስተን 5ኛው ሃገራዊ ምርጫ ሠላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ፣ ወሳኙ ህዝብ ስለሆነ የህዝቡን ወሳኝነት ለማረጋገጥ እየተንቀሳቀስን ነው፡፡ 
ከህዝብ ታዛቢዎች ምርጫ ጋር ተያይዞ ተቃዋሚዎች፤ “ኢህአዴግ የ1ለ5 አደረጃጀቱን ተጠቅሞ አባላቱን አስመርጧል” ሲሉ ይወቅሣሉ፤ በዚህ ላይ የእናንተ ምላሽ ምንድን ነው?
የህዝብ ታዛቢዎች ምርጫን በተመለከተ አንዳንድ ፓርቲዎች መሠል አስተያየቶችን ሲያቀርቡ ሰምተናል፡፡ አንደኛው ወቀሳቸው፣ የታዛቢዎች ምርጫ የተካሄደው ለኛ ሣይነገረን ኢህአዴግ ብቻ ተነግሮት ነው የሚል ነው፤ ይሄ በጣም መሠረታዊ ስህተት ነው፤ ምክንያቱም ኢህአዴግም እነዚህ ፓርቲዎችም ባሉበት የምርጫ ጊዜ ሠሌዳው ቀርቦ ውይይት አድርገንበታል፡፡ ምርጫ ቦርድ ያወጣው የጊዜ ሠሌዳ ኢህአዴግን ጨምሮ ለእያንዳንዱ ፓርቲ አቅርቧል፡፡ ስለዚህ ታህሣሥ 12  የህዝብ ታዛቢዎች ምርጫ እንደነበር ይታወቃል፡፡ የምርጫ ቦርድ ሃላፊዎች በሚዲያም ቀርበው ታህሣሥ 12 የህዝብ ታዛቢዎች ምርጫ እንደሚካሄድ ተናግረዋል፡፡ ስለዚህ በሚስጥር የተደረገ ነው፤ የሚለው የተሣሣተ ነው፤ በይፋ በደብዳቤም በሚዲያም ተገልጿል፡፡ 
በእለቱም ኢህአዴግ አባሎቹ እንዳይመረጡ ጥንቃቄ አድርጓል፡፡ አንዳንድ ቦታ እንኳ አባሎቻችን ሲጠቆሙ “እኔ አባል ነኝ፤ አልችልም” ብለው ከምርጫው የወጡበት ሁኔታ አለ፡፡ ስለዚህ ይህ የተቃዋሚዎች ውንጀላ የተለመደ ሂደቱን ከጅምሩ ጥላሸት የመቀባት አካል ነው፡፡ የተመረጡት የህዝብ ታዛቢዎች ገለልተኛ አይደሉም ለማስባል የሚረዳ ተራ የስም ማጥፋት ሂደት ነው፡፡ 
1ለ5 የሚባለው ለመንግስት የልማት ስራ የተደራጀ ነው እንጂ የፓርቲው አደረጃጀት አይደለም፡፡ የተቃዋሚም የኢህአዴግም አባል የሆነ ሊኖር ይችላል፤ ስለዚህ የ1ለ5 አደረጃጀትን ሂዱና የህዝብ ታዛቢ ምረጡ ቢል ችግር የለውም ማለት ነው፡፡ ኢህአዴግን ምረጡ ወይም ደጋፊ የሆነን ሰው ምረጡ የሚባል ነገር የለም፡፡ ስለዚህ በ1ለ5 አደረጃጀት ላይ ብዥታ ሊኖር አይገባም፤ አደረጃጀቱ የልማት አደረጃጀት ነው፡፡ ይህን አደረጃጀት ሂዳችሁ ታዛቢ ምረጡ ወይም በምርጫው ተሳተፉ ቢል ነውር አይደለም፡፡ ከዚህ አንፃር ህዝቡ ገለልተኛ ናቸው ያላቸውን ታዛቢዎቹን መርጧል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ እነዚህ ውንጀላዎች ተቀባይነት የሌላቸው፣ ሂደቱን ጥላሸት ለመቀባት ሆነ ተብሎ የሚደረጉ ናቸው፡፡ የኢህአዴግ አባል ተመርጧል የሚሉ ከሆነና የተመረጠበትን ቦታ ከጠቆሙ እኛም ለማጣራት  ዝግጁ ነን፡፡ ድንገት ሾልኮ የገባ ካለም እንዲወጣ እናደርጋለን፡፡ እስካሁን ግን እንዲህ ያለ ነገር ስለመኖሩ ምንም መረጃ የለንም፡፡ ህዝቡ  ምርጫውን ማካሄዱ መብቱን ማረጋገጫ መንገድ ነው፡፡ 
የምርጫ ስነ ምግባር ደንቡን ካልፈረሙ ፓርቲዎች ጋር ኢህአዴግ ለመወያየት የማይችልበት መሠረታዊ ምክንያት ምንድን ነው? ደንቡን መፈረምን እንደ ግዴታ ማስቀመጥ የውይይት በርን መዝጋት አይሆንም?  
ደንቡ ሲዘጋጅ ብዙ ሂደት አልፏል፡፡ በወቅቱ የነበሩት ፓርቲዎች በእርጋታ እየተወያዩ ያለፉበት ሂደት ነበር፤ በዚህ ሂደት መድረክ ሶስት ጊዜ ረግጦ ወጥቷል፡፡ መጀመሪያ ሂደቱ ሲጀመር ወደ ውይይቱ ተጋብዞ መጣ፤ ያኔ ከኢህአዴግ ጋር እንጂ ከሌሎች ተቃዋሚዎች ጋር መወያየት የለብኝም አለ፡፡ ኢህአዴግ ደግሞ ብዙ ፓርቲዎች ባሉበት ሃገር፣ የተናጥል ውይይት ከእያንዳንዱ ጋር ማድረግ አይችልም፡፡ መድረክ፤ ሌሎች ፓርቲዎች ተቃዋሚዎች አይደሉም የሚል አመለካከት ስለለው ወጣ፡፡ በሌላ ጊዜም ተጋበዘ፤ ሂደቱን ትቶ ወጣ፡፡ ለ3ኛ ጊዜ 65 ፓርቲዎች ሲወያዩ ገብቶ ሂደቱን ለመበተን ነው ጥረት ያደረገው፤ ግን መጨረሻ ላይ 65 ፓርቲዎቹ ተስማምተው ህግ ሆኖ ወጣ፡፡ ህግ ሆኖ ሲወጣ በህጉ ውስጥ የተቀመጠ ቅድመ ሁኔታ አለ፡፡ 
የጋራ ምክር ቤቱ አባል ሆኖ ለመቀጠል የፈለገ ፓርቲ ህጉን መፈረም አለበት፡፡ ይሄ ማለት የፖለቲካ ቁርጠኝነት ማረጋገጫ ነው፡፡ ስለዚህ የስነ ምግባር ደንቡ ህግ ሆኖ እንዲወጣ ፓርቲዎቹ በራሳቸው ሊገፉት ይገባል ማለት ነው፡፡ የፊርማ ቅድመ ሁኔታን ኢህአዴግ አላስቀመጠም፤ ራሱ ህጉ ያስቀመጠው ነው፡፡ እያንዳንዱ ፓርቲ በስነምግባር መመራቱን, የፖለቲካ ቁርጠኝነቱን ቀድሞ ማረጋገጥ አለበት ነው የሚለው ህጉ፡፡ ይህን ያረጋገጡ የጋራ ምክር ቤት ውስጥ እየሠሩ ነው፡፡ ከኢህአዴግ ጋር እነዚህ ፓርቲዎች በፕሮግራም የተለዩ ናቸው፡፡ በምርጫ ሂደቱ ላይ ግን በጠረጴዛ ዙሪያ ቁጭ ብለው የበሠለ ውይይት እያደረጉ ነው፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ስነ ምግባሩ ያስረናል ብለው ስለሚያስቡና አመፅና ብጥብጥ ለማስነሳት ያግደናል ብለው ስለሚያስቡ ቁርጠኝነት ስላነሣቸው ነው እንጂ ኢህአዴግ በተናጥል አልደራደርም ስላለ አይደለም፡፡ ከዚህ አንፃር ተስማምተን ህግ ሆኖ በወጣ ጉዳይ ላይ lምንድን ነው ተመልሰን ወደ ድርድር የምንገባው? የሚለው ጥያቄ መመለስ አለበት፤ ስለዚህ ተመልሰን ወደ ድርድር የምንገባበት ምንም ምክንያት የለም፡፡ አሁንም ምርጫ ቦርድ በሚጠራቸው ስብሰባዎች ላይ አብረን እንሣተፋለን፤ የጋራ ምክር ቤት ውስጥ ለመግባት ግን ድርድር አያስፈልገውም፤ በስነምግባር ለመገዛት መስማማት ብቻ ነው፡፡ ኢህአዴግ ያለፈባቸውን ሂደቶች ስናይ ሁልጊዜም በድርድር የሚያምን መሆኑን እንገነዘባለን፡፡ 
ለምንድን ነው የአለማቀፍ መስፈርቶችን ያሟላ ስነምግባር ተገዥ ሆናችሁ፣ ለፍትሃዊና ሠላማዊ ምርጫ ውድድር ዝግጁ ያልሆናችሁት የሚለውን ጥያቄ ተቃዋሚዎች መመለስ አለባቸው፡፡ በስነምግባር እንመራ የሚል ውይይት ማካሄድ እንዴት ይቻላል፡፡ 
ደንቡን ያልፈረሙ መድረክን የመሣሠሉ ድርጅቶች ከኢህአዴግ ጋር መወያየት ቢፈልጉ እንዴት ነው የሚስተናገዱት?
በተቀመጡ ማዕቀፎች መሠረት ይስተናገዳሉ፡፡ ገለልተኛ የሆነው የምርጫ ቦርድ አለ፡፡ ያልተሟሉ ነገሮች ካሉ ለምርጫ ቦርድ እያቀረቡ ሊፈቱ ይችላሉ፡፡ ኢህአዴግ ደግሞ በተቋማዊ አሠራር የሚያምን ድርጅት ነው፡፡ የስነምግባር ደንቡ በሌለበትና የጋራ ምክር ቤቶች ባልተቋቋሙበት ሁኔታ ጥያቄው ቢቀርብ ትክክል ነው፡፡ ከእያንዳንዱ ፓርቲ ጋር ኢህአዴግ እየተወያየ ሊሄድ ይችላል፡፡ አሁን ግን የጋራ ማዕቀፍ  በተዘረጋበት ኢህአዴግ እንዴት ብሎ ነው ከ70 ፓርቲዎች ጋር በተናጠል መወያየት የሚችለው? አሁን ተቋዋሚ አሠራር ተዘርግቷል፡፡ ለመወያየት የፈለገ የጋራ ምክር ቤቱ ውስጥ መግባት አለበት፡፡ ችግሮች ሲፈጠሩ ምክር ቤቱ አጣሪ ኮሚቴ አቋቁሞ ያጣራል፤ መፍትሔ እንዲያገኙም ያደርጋል፡፡ ከዚህ ውጪ በተናጠል መወያየት አይቻልም፡፡ እነዚህ ፓርቲዎች በራሳቸው የሚፈጠረውን ችግር እንኳ ሣይቀር ኢህአዴግ ፈጠረው ነው የሚሉት፡፡ በአመራር እንኳ የተፈጠረባቸውን ችግር በኢህአዴግ የተፈጠረ ጥፋት አድርገው ይወስዱታል፡፡ ስለዚህ ይሄን መፍረድ ያለበት ህዝቡ ነው፡፡ ህዝቡ ሁሉንም ነገር ያያል፡፡ ማን ነው ጥፋተኛ? ኢህአዴግ ነው ለዲሞክራሲያዊ ስርአትና ፍትሃዊ ምርጫ ዝግጅ ያልሆነው ወይስ ሌላው? የሚለውን መፍረድ ያለበት ህዝቡ ነው፡፡ 
ኢህአዴግ የገዢነቱን ኃይል ተጠቅሞ በተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚደረጉ ሰላማዊ ሰልፎችን ለማፈን ይጥራል የሚሉ ቅሬታዎች ይቀርባሉ፡፡ ኢህአዴግ እንደፓርቲ በሰላማዊ ሰልፍ ላይ ያለው አቋም ምንድን ነው?
ፓርቲያችን ሰላማዊ ሰልፍ ለዜጎች የተሰጠ ህገ መንግስታዊ መብት ነው ብሎ ያምናል፡፡ ይሄ መብት ተግባራዊ የሚሆንባቸው አሰራሮች እንደሚዘረጉ ህገ መንግስቱም አስቀምጧል፡፡ በህገ መንግስቱ ዜጎች በጋራ ሆነው ቅሬታ የማቅረብ፣ ሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ የማድረግ መብት አላቸው ይላል፡፡ ይሄን መብት ተግባራዊ ለማድረግ አሰራሮች ሊዘረጉ እንደሚችሉ ተቀምጧል፡፡ ሰላማዊ ሰልፍ አድራጊዎች የህዝቡን ሰላም፣ ክብርና የመሳሰሉ መብቶችን መጣስ እንደሌለባቸው ህገ መንግስቱ አስቀምጧል፡፡ 
አንድ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ማሳወቅ እንደሚጠበቅበትም ተቀምጧል፡፡ የእውቅናውን ጥያቄ የሚያየው አካል የተጠየቀበትን ቦታና ጊዜ ይመለከትና በእውቅና ጥያቄው ላይ ምላሽ ይሰጥበታል፡፡ ቦታ ቀይር ወይም ቀን ቀይር የሚል ምላሽ ይሰጥበታል ማለት ነው፡፡ ዘጠኙ ፓርቲዎች የጠየቁት ቦታ መስቀል አደባባይ ነው፡፡ መስቀል አደባባይ ደግሞ ትልቅ የልማት እንቅስቃሴ እየተደረገበት ያለ ቦታ ነው፡፡ ለ24 ሰዓት ቆመ ማለት ብዙ ነገር ያስተጓጉላል፡፡ ስለዚህ ቦታው ተገቢ አልነበረም ማለት ነው፡፡ በዚህ የተነሳ የተጠየቀው አካል አልተቀበለውም፡፡ እነዚህ ፓርቲዎች ዕቅዳቸው ልማትን ማደናቀፍ፣ ህዝብን ወደ አመፅ መንዳት እንደሆነ ከዚህ መረዳት ይቻላል፡፡ ኢህአዴግ እንደ ፓርቲ ግን ሰላማዊ ሰልፍ የዜጎች መብት ነው የሚል አቋም አለው፡፡ 
ኢህአዴግ ለምርጫው ያስቀመጠው ግብ ምንድን ነው? አንዳንድ ወገኖች ሙሉ ለሙሉ አሸናፊ እንዳይሆን ተጠንቅቆ እስከ 15 በመቶ ወንበሮችን ለተቃዋሚዎች ሊለቅ ይችላል የሚል አስተያየት ይሰነዝራሉ?
ኢህአዴግ መንግስት ለመመስረት የሚያስችለውን ወንበር ማግኘት ነው ግቡ፡፡ ይሄ ሲባል ድምፁ እንደ እጩ ቁጥራችንም ይወሰናል በአገሪቱ ባሉ የምርጫ ክልሎች ሁሉ እንወዳደራለን፡፡ በእያንዳንዱ የምርጫ ክልል ለማሸነፍ እንሰራለን ማለት ነው፡፡ ኢህአዴግ ዲሞክራሲን የሚያየው በእውነተኛ ገፅታው ነው፡፡ ዲሞክራሲ በአርቴፊሻል ገፅታ መታየት የለበትም፡፡ ዲሞክራሲ የህዝብ ወሳኝነትን ማረጋገጫ መሳሪያ ነው፡፡ በእያንዳንዱ የምርጫ ክልል ተወዳድረን ህዝቡ የሚመርጠን ከሆነ እሰየው ብለን እንወስዳለን፤ ባይመርጠንም እንቀበላለን፡፡ ከዚህ ውጭ አርቴፊሻል በሆነ መንገድ፣ የህዝብን ውሳኔ ባላከበረ መንገድ የተወሰነ ወንበር እንለቃለን የሚል ሃሳብ የለም፡፡ ወሳኙ ህዝብ ነው፡፡ ምርጫ በውጤት አይመዘንም፤ ዋናው ሂደቱ ነው፡፡ ሂደቱ ማማር አለበት፡፡ 
በየጊዜው በሚደረጉ ምርጫዎች ላይ የአለማቀፍ ታዛቢዎች ቁጥር እየቀነሰ ሄዶ ዘንድሮ የአውሮፓ ህብረትም ቀርቷል፡፡ አለማቀፍ ታዛቢዎች ከምርጫው ለምን ተገለሉ?
 የኛ ምርጫ ማንም ሊታዘበው የሚችል ምርጫ ነው፡፡ በድብቅ የሚካሄድ ምርጫ ሳይሆን ማንም ሊያየው የሚችል ምርጫ ነው፤ ነገር ግን ምርጫን የአውሮፓ ህብረት ካልታዘበው ችግር ይኖርበታል ብሎ ማሰብ በራሱ የምርጫው ወሳኝ ማን ነው የሚለውን ጥያቄ ውስጥ ያስገባዋል፡፡ ህብረቱ ምርጫውን ለመታዘብ የበጀት እጥረት አለብኝ የመሳሰሉ ምክንያቶችን ነው ያቀረበው፡፡ ስለዚህ ምርጫውን የአፍሪካ ህብረት ይታዘበዋል፣ ከሃገር ውስጥም የተለያዩ የሲቪል ማህበራት ይታዘቡታል፡፡ ዋናው ወሳኙ የኢትዮጵያ ህዝብ ነው፡፡ ይሄ ህዝብ ነው ውሳኔ የሚሰጠውም የሚታዘበውም፡፡ 
አለማቀፍ ታዛቢዎች የምርጫውን ገለልተኛነት ከማረጋገጥ አንጻር ምንም ዓይነት ሚና አይኖራቸውም እያሉን ነው?
 ሊታዘቡ ይችላሉ ግን ዋናው ሚና የህዝብ ነው፡፡ እያንዳንዱ ሂደት ከህዝብ ጋር የተገናኘ ነው አለማቀፍ ታዛቢ ተጨማሪ ነው፤ ወሳኝነት የለውም፡፡ 
ኢህአዴግ በዚህ ምርጫ ሊወዳደረኝ የሚችል ፓርቲ አለ ብሎ ያምናል?
ይሄን ህዝቡ ነው የሚመዝነው፡፡ ቀድመን ባንመዝነው እመርጣለሁ፡፡ ፓርቲዎች ምን እንደሚመስሉ የራሳችን ግምት አለን፡፡ የህዝብን ጥቅም ሊያስጠብቅ የሚችል ሌላ ይህች አገር የጀመረችውን ልማት፣ ዲሞክራሲ በቁርጠኝነት ይዞ ሊሄድ የሚችል ፓርቲ አለ ብለን አናምንም፡፡ በተለያዩ መንገዶች መመዘን እንችላለን፡፡ ከራሳቸው ባህሪ ተነስተን ማለት ነው፡፡ ፓርቲ ማለት የህዝብን ህይወትና ኑሮ ለመቀየር የሚሰራ ፓርቲ ነው፡፡ የትኛው ፓርቲ ነው ህዝቡ ለልማት ሲንቀሳቀስ ከጎኑ ተሰልፎ የሚሳተፈው? የትኛው ፓርቲ ነው ህዝቡ ተግዳሮቶች ሲያጋጥሙት አብሮ እየተንቀሳቀሰ ያለው? የትኛው ፓርቲ ነው ግልፅ የሆነ ሃገር የሚቀይር አማራጭ ፕሮግራም ያለው? የሚለው ስንጠይቅ፣ ሃገርን በዚህ መንገድ ወደፊት የሚያሻግር ጠንካራ ተቃዋሚ ፓርቲ የለም የሚል ድምዳሜ ላይ ያደርሰናል፡፡ ይሄን ግን ህዝቡ ነው ገምግሞ ሚዛን ላይ ማስቀመጥ ያለበት፡፡ አሁን ቅስቀሳ ባልተጀመረበት ሁኔታ በዚህ ጉዳይ ብዙ አስተያየት መስጠት አይቻልም፤ ግን ህዝብ ይታዘባል፡፡ እናሸንፋለን አናሸንፍም የሚለውም ቅስቀሳ ስለሚሆን የምረጡን ቅስቀሳ ሲካሄድ ብናየው የተሻለ ነው የሚሆነው፡፡ 
ኢህአዴግ በምርጫ ቦርድ ወይም በምርጫ ሂደቱ ላይ ቅሬታ አለው?
ምርጫ ቦርድ ጋ ቅሬታ የለንም፡፡ ቦርዱ በገለልተኝነት እየሰራ ያለ ተቋም ነው፡፡ ስብሰባ ሲጠራን አስተያየት እንሰጣለን፤ እስካሁን ግን ምንም ቅሬታ የለንም፡፡ ሌሎች ፓርቲዎች የሚያቀርቡትም አብዛኛው ቅሬታ ትክክል አይደለም ብለን እናምናለን፡፡ ፓርቲዎቹ ራሳቸው መጨረስ ያለባቸውን የቤት ስራ ሳይሰሩ፣ በቦርዱ ላይ የሚያቀርቡትን አብዛኞቹን ቅሬታዎች ስንገመግም፣ ቦርዱ ገለልተኛ አይደለም የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ የሚያደርጉት ጥረት መሆኑን እንገነዘባለን ነው፡፡ ምርጫ ቦርድ ለኛ የሚያደላልን ነገር የለም፡፡