OPPOSITION PARTIES WEBSITES

ETHIO NEWS & VIEWS

RADIO & TV

Tuesday, August 9, 2016

በባሕር ዳር የዐማራ ፖሊስ በንዴት አምስት ፌደራሎችን ገድሎ ራሱን አጠፋ

የብአዴን ምክትል ሊቀመንበርና የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው(የገዱ አንዳርጋቸው መነሳት የዐማራን ተጋድሎ ወደፊት ያስፈነጥረዋል!!)
• የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር የነበረው ድርድር ያለስምምነት ተበትኗል
• በባሕር ዳር የዐማራ ፖሊስ በንዴት አምስት ፌደራሎችን ገድሎ ራሱን አጠፋ
• ‹‹አታልቅሱ፤ ልጄ ለተቀደሰ ዓላማ ተሰውቷል›› በባሕር ዳር ልጃቸውን ያጡ እናት
• ወረታ ከተማ የመጠጥ ውኃ ውስጥ መርዝ ሊጨምር የነበረው ግለሰብ እብድ ነኝ በማለት እያጭበረበረ ነው
ኹመራ፤ በአሸባሪነት ስም የማንነት ጥያቄያቸውን ሊያደፋፍኑት ቢጥሩም እንደማይሳከ የወልቃይት ጠገዴ ዐማሮች ተናግረዋል፤
ሙሉቀን ተስፋው
ዛሬ በኹመራ፣ በዳንሻና በአዲረመጥ ከተማ ያነጋገርናቸው የወልቃይት ጠገዴ ዐማሮች እንደሚናገሩት የማንነት ጥያቄያችን ለማዳፈን የአሸባሪነት ስም እየሰጡ በየሰአቱ ይፈትሹናል፡፡ አማርኛ የሚናገር ሰው ሁሉ እንዲሸማቀቅ ከፍተኛ ጥረት ይደረጋል ብለዋል፡፡ ከኹመራ ያገኘነው ግለሰብ ‹‹አሁን የማወራህ ከፎቅ ላይ ወጥቼ ነው፤ በየቦታው እኛን የሚከታተል የትግራይ ሰው በየቦታው ነው፡፡ ያለንበትም ሁኔታ ያስጠላል›› ሲል የሚደርስበትን ጫና ገልጧል፡፡
የወያኔ ሰዎች አንዳንድ ዐማሮችን በገንዘብ በመግዛት መሣሪያ አስታጥቀው ወደ በርሃ በመላክ ከተወሰ ቀን በኋላ ‹‹ምሕረት ጠይቀናል›› ብለው ይመለሳሉ፡፡ በኋላም የወልቃይት ጠገዴ ዐማሮች እንዳስታጠቋው በመግለጽ ድራማ እንደሚሠሩ ገልጸዋል፡፡ በዚሁ አያይዘውም አንዳንድ መገናኛ ብዙሃንና የተቃዋሚ ድርጅቶች የወልቃይት ጠገዴን ዐማራ የማንነት ጥያቄ ዘገባ ሲሠሩ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ብሎም በእውነት ላይ የተመሠረተ እንዲሆን አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

No comments:

Post a Comment