OPPOSITION PARTIES WEBSITES
▼
ETHIO NEWS & VIEWS
▼
RADIO & TV
▼
በሰሜን ጎንደር ዳባት ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት ውስጥ የከረረ ተቃውሞ በፖሊስ አባላቱ በመነሳቱ በርካታ ቁጥር ያላቸው ፖሊሶች መታሰራቸው ተሰማ -
ቅዳሜ ዕለት ሰኔ 27 2007 ዓ.ም ዳባት ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት በተካ…ሄደው ስብሰባ ላይ የከረረ ተቃውሞ የተነሳ ሲሆን ተቃውሞውን ተከትሎ የበርካታ ፖሊስ አባላት እስር እና ከአካባቢው መሰወር ተከስቷል፡፡ በስብሰባው ላይ የተነሳው ተቃውሞ ዋነኛ ምክንያትና ሰበብ የፖሊስ ፅ/ቤቱ ዋና ኃላፊ ሆኖ የተሾመው ሰው ከትግራይ ክልል የመጣ የህወሓት አባል መሆኑ ነው፡፡ በስብሰባው ላይ ጠንካራ የተቃውሞ ድምፃቸውን ካሰሙት የዳባት ፖሊስ አባላት መካከል ካሳው ማሞ እና ሰጡ እጥናፉ የተባሉት ይገኙበታል፡፡ ካሳው ማሞ እና ሰጡ አጥናፉ “ተጠሪነታችን ለአማራ ህዝብ ሆኖ እያለ ለምን በህወሓት አባል እንመራለን? ተጠሪነታችን ለትግራይ ክልል ፖሊስ ሆኖ ከሆነ የተቋሙን ስም ቀይሩት፤ አለበለዚያ ከስራ አሰናብቱን… ዘረኝነት ይቁም…” በማለት ተናግረዋል፡፡ ከስብሰባው በኋላ ካሳው ማሞንና ሰጡ አጥናፉን ጨምሮ በስብሰባው ላይ የዘረኝነት አገዛዝ ተቃውሞ ድምፃቸውን ያሰሙ በርካታ የዳባት ፖሊስ አባላት እግረ ሙቅ እያጠለቁ ወደ ዘብጥያ ወርደዋል፡፡ ሦስት ፖሊሶች ደግሞ ድንገት ከአካባቢው የተሰወሩ ሲሆን በህወሓት ይታፈኑ ወይንም አምፀው ወደጫካ ይውጡ እስካሁን ምንም የታወቀ ነገር የለም፡ -
No comments:
Post a Comment