OPPOSITION PARTIES WEBSITES

ETHIO NEWS & VIEWS

RADIO & TV

Thursday, June 4, 2015

ኦህዴድ፣ብአዴንና ደኢህዴን የሚባሉ ህያዋን የሉም – ዳዊት ሰለሞን

OPDOመቶ ከመቶ ደፈንኩ ያለን ‹‹ሰነፉ››ተማሪ ኢህአዴግ በቀጣይ በሚያደርገው የግምባሩ ጠቅላላ ጉባኤ በኃይለማርያም ደሳለኝ ወንበር ላይ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል ፡፡ወርሃ መስከረም የሚሰየመው ‹‹የኢህአዴግ መንግስታዊ ጉባኤም››(ፓርላማ ለማለት ቢቸግረኝ ያወጣሁለት ስያሜ ነው) የሚቀርብለትን እንደወረደ ያጸድቃል፡፡

ይህንን የሚጠብቁ ፌስ ቡከሮች በበኩላቸው የራሳቸውን ጥንቆላ እያስነበቡን ነው፡፡ማንም ይምጣ ያው ነው ያሉ ወገኖችም ቢሆኑ ቢያንስ በወንበሩ ላይ የሚቀመጠው ግለሰብ ‹‹ጉልቻው››በመሆኑ መቀያየሩ ወጡን (አገሪቱን)እንደማያጣፍጠው በመግለጽ ሐሳባቸውን ሰንዝረዋል ልንል እንችላለን፡፡
የደህዴኑ አቶ ኃይለማርያም መለስ ዜናዊ በተፈጥሮ ሞት ገለል በማለታቸው ያገኟትን የድንገቴ ወንበር ‹‹በእየሱስ ስም››ገዝተው ለመጪዎቹ አመታት ካላቆዩት በስተቀር (በተአምር ለማለት ነው)በወንበሩ በአሻንጉሊት ደረጃም ቢሆን መቀጠል መቻላቸው አከራካሪ ሊሆን ይችላል፡፡
ግን ኃይለማርያም ቢነሱ በግላቸው ጫማ ጠራጊም በመሆን በፓርቲያቸው እንደሚቀጥሉ በመናገራቸው (እዚህ ላይ ኢንጂነሩ ከመለስ ለየት ብለውብኛል፡፡መለስ ፓርቲዬ ከፈለገኝ በወንበሩ እንደተቀመጥኩ እቀጥላለሁ ይላሉ እንጂ ጫማ፣ቀበሌ ገለመሌ አይሉም)ዕጣ ፈንታቸው ምን ይሆናል ብለን የጥንቆላን ጥበብ ለመጠቀም መቸገር የለብንም፡፡

ቀጣዩ ሰው ማንና ከየትኛው የኢህአዴግ ድርጅት ይሆናል በሚለው ዙሪያ ወደ ብዙዎች ልብ የሚመጣው ህወሓት ነው፡፡
ብአዴኖች (ኢህዲን ተሰኝተው የራሳቸው ፕሮግራም የነበራቸው ቢሆኑም በህወሓት አሰላለፋቸውን እንዲያስተካክሉ ተደርገው ብአዴን ሲሰኙ እንዴት ለምን ያለ አላየንም በዚህ ላይ የተፈራ ዋልዋን ‹‹ህወሓቶች ሲዋጉ እናንተ ዛፍ ላይ ተንጠልጥላችሁ መመልከታችሁን እንዴት ትረሳላችሁ ››ማለቱን ስናስታውስ ) የሻዕቢያ ምርኮኞች የነበሩት እነ ምናሴ ለህወሓት ተላልፈው ከተሰጡ በኋላ የዳቦ ስም ወጥቶላቸው አባ ዱላ ተሰኝተው ኦህዴድን መስርተዋል ደኢህዴንም ከዚህ የዘለለ የተፈጥሮ ታሪክ የለውም፡፡በዚህ ሁኔታ ውስጥ በተፈጠረው ኢህአዴግ ውስጥ አራት ድርጅቶች ይገኛሉ ፡፡ እነዚህ ድርጅቶችም የራሳቸውን ጠቅላላ ጉባኤ ያደርጋሉ፣መሪዎቻቸውን ይመርጣሉ ፣ዕኩልነታቸውን ያስጠብቃሉ፣ግምባሩ በአንዱ የበላይነት ሲዘወር እምቢ የማለት መብት አላቸው፣በድርጅቱ ውስጥ ያለውን ግምባሩን ኃላፊነት ድርጅቶቹ በየተራ በመያዝ የአገሪቱን ስልጣን ሲይዙ ስልጣኑ በሚወክሉት ክልል ስፋት መሰረት እንዲሆን ያደርጋሉ ወዘተ በማለት መዘርዘር ጉንጭ ማልፋት ነው፡፡

ሶስቱ ድርጅቶች በፈጣሪያቸው ህወሓት ላይ እስካሁን ድረስ የነሷቸው የልዩነት ነጥቦች አልተመዘገቡም፡፡የራሳቸውን ህልውና የሚያሳዩባቸው አጋጣሚዎችን የጎርፍ ውሃ እንደመጣበት ሰው ጥግን በመያዝ ከማሳለፍ ውጪ ሲንፈራገጡ እንኳን አልተስተዋለም፡፡

ታዲያ እነዚህ ድርጅቶች በየት በኩል ነው ቀጣዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ከእኔ ድርጅት ሊመረጥ ይገባዋል የሚሉት በዚህስ ላይ የትኛው መተማመናቸው ነው ከድርጅታቸው አንዱ እንዲወጣ ስምምነታቸውን የሚለግሱት?ብአዴን ስንቱን ተነጠቀ፣ኦህዴድስ ሲፋቅ ኦነግ ነው ተሰኝቶ ስንቱን ለህወሓት ዱላ አሳልፎ ሰጠ ከዚህ የተረፉት አባዱላ፣ሙክታር፣ሬድዋን ወይም በረከት ቦታውን ሊይዙ ?የህወሓቱ ቴድሮስ አድሃኖም ኃይለማርያምን በይፋ ቢረከቡ ብአዴኖች፣ኦህዴዶችና ደኢህዴኖች አገር ሊቀውጡ ?አይመስለኝም ፡፡ባይሆን ህወሓቶች በይፋ የማይዟቸውን ቦታዎች ለመረከብ እጅ ያወጡ ይሆናል፡፡

No comments:

Post a Comment