OPPOSITION PARTIES WEBSITES

ETHIO NEWS & VIEWS

RADIO & TV

Wednesday, June 3, 2015

በሕወሓት ውስጥ ለጠቅላይ ሚኒስትርነት ስልጣን ሽኩቻ አገርሽቷል::ብአዴን እና ኦሕዴድ ተለጉመዋል -

EPRDFበተጭበረበረ ምርጫ እና በጠበንጃ ሃይል ለሚቀጥሉት አመታት ስልጣንን የሚያልሙት በስብሰባ ተወጥረው የሚገኙት የሕወሓት አምባገነን ባለስልጣናት ሃይለማርያም ደሳለኝ የሚባለውን አሻንጉሊታቸውን አሽቀንጥረው ጥለው የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ስልጣኑን ወደ ሕወሓት መልሶ በግለሰብ ደረጃ ለመቆጣጠር እርስ በእርስ ሽኩቻ ውስጥ መሆናቸውን ለድርጅቱ ቅርብ የሆኑ ምንጮች በመናገር ላይ ናቸው::
በሁለት ቡድን ተከፍሎ እየጦዘ ያለው የስልጣን ሽኩቻው ባንድ በኩል ደብረጺሆን ገብረሚካኤል ሲሆን የደህንነት ሹማምንቱን እና የሰራዊቱን አንዳንድ ጄኔራሎች በማስከተል እየተሯሯጠ ሲሆን በሌላኛው ጽንፍ ደሞ አርከበ እቁባይ የሕወሓት አንዳንድ አንጋፋ ታጋዮችን ይዞ በጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ አብረውት የሚሰሩ የሕወሓት ባለስልጣናት እንደ አባይ ጸሃዬ እና አለቃ ጸጋይን እና ወጣት እጅግ በዘረኝነት የሰለጠኑ የሕወሃት ትኩስ አባላትን ይዞ እየተቀናቀነ ቢሆንም ከሕወሓት ማእከላዊ ኮሜቴ ስለተባረረ ይህን ያህል እድሉ የለውም ቢባልም በአሸናፊነት ገኖ መውጣት ከቻል ድርጅቱ ሕወሓት የሃገሪቱን የስልጣን መንገድ ሕጎች መቀየር መናድ ይሁን መጣስ እንደለመደው እንደሚያደግ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ::ምንጮቹ ለምንሊክ ሳልሳዊ እንዳሉት ሃይለማርያም በስልጣን ቢቀጥል ምንም አደጋ እንዳልሆነ የሚያምነው ቴዎድሮስ አድሃኖም መሃል ሰፋሪ ሲሆን ጥሩ ለነፈሰለት እንደሚያደላ ታውቋል::
ሃይለማርያም ደሳለኝን በ ቢ አብጠልጥሎ የደመደመው የድርጅቱ ግምገማ ከስልጣኑ አንስቶ አምባሳደር ሊያደርገው ይችላል ቢባልም መሃል ሰፋሪ የሆኑ እነ ቴዎድሮስ አድሃኖም አይነቶቹ ሃይለማሪያም በሰለጠነ ስትራቴጂ ስልጣኑን ይዞ እንዲቀጥል እንደሚፈልጉ ሲታወቅ ባለፍው ግምገማ የሃይለማርያም ስራ እንቅፋቶች ከጠቅላይ ሚኒስትሩ በላይ ስልጣን ያላቸው እንደሆኑ ወዲ አድሃኖም ከበላይ የመጣለት ት እዛዝ ነው በማለት ከአፉ አምልጦት በሃገሪቱ ከጠቅላይ ሚኒስትር በላይ ስልጣን ያላቸው ወሳኝ አካላት እንዳሉ አጋልጧል::የፌስ ቡክ ሚኒስትሩ ቴዎድሮስ አድሃኖም በመሃል ሰፋሪነት ቢሆኑም የተወሰኑ የሕወሃት አባላት እና ከተማ ቀመስ ደጋፊዎቻቸው ለተቅላይ ሚኒስትርነት ካጯቸው መሰነባበታቸው ይታወቃል::
አቶ አርከበ ይህን ሰሞን የሃገሪቱ እድል በተመለከተ አስር አመት መርሃግብር አለኝ የምን የመለስ ራእይ የምን ትራንስፎርሜሽን የምን ዝባዝንኬ በማለት ለሃገሪቱ ፖሊሲ ነድፌአለሁ እያሉ የሕወሓት አባሎችን በመቀስቀስ ላይ ሲሆኑ መለስ ዜናዊ የሚባል ስም እንዳይነሳ የሚፈልጉ ናቸው በመባል ይታማሉ::አቶ አርከበን ለመቆታጠር ሳሞራ የኑስን ይተካሉ በሚባሉት የኢንሳው ጄኔራል ገብረኪዳን በኩል የሚመራ የስለላ ቡድን እየተከታተላቸው መሆኑን እና አቶ አርከበ ተሰብስበው እንዲቀመጡ ሰበብ እየተፈለገላቸው መሆኑ ታውቋል;;ይህ በእንዲህ እንዳለ በተጭበረበረ ድምጽ ስልጣኑን አረጋግቶ ማጥበቅ የያዘው ሕወሓት በሚያደርጋቸው የቁልፍ ስልጣናት ድልደላ ላይ ማንኛውም የሕወሓት ይሁን የኦሕዴድ አመራሮች እንደማይሳተፉ እና እንደማያውቁ ውስጥ አዋቂዎች ሲገልጹ አመራሮቹ በዝምታ ከቢሮ ወደ ቤት ከመመላለስ ውጪ ምንም አይነት ጥያቄዎች እንዳይጠይቁ አሊያም እርስ በእርስ እንዳይነጋገሩ ከፍተኛ ቁጥጥር እየተደረገባቸው መሆኑን መለጎማቸው ታውቋል::

No comments:

Post a Comment