OPPOSITION PARTIES WEBSITES

ETHIO NEWS & VIEWS

RADIO & TV

Thursday, May 21, 2015

በኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስትሩ ሲቪል በመኾኑ በስብሰባው ሱፋቸውን ለብሰው መታደማቸው (ፎቶ መነሳታቸው) አግባብ ነው።

yenusየጄነራል ሳሞራ ፎቶ የዩናይትድ ስቴትስ እና የኢትዮጵያ የመከላከያ ባለሥልጣናት ሰሞኑን በአሜሪካ ባደረጉት ስብሰባ ላይ የተወሰደ ፎቶ ነው። በኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስትሩ ሲቪል በመኾኑ እነ ሲራጅ ፈርጌሳ በስብሰባው ሱፋቸውን ለብሰው መታደማቸው (ፎቶ መነሳታቸው) አግባብ ነው። የጦር ኃይሎች ኢታማዦር ሹሙ ሳሞራ ዩኑስ እንዲህ ለብሰው የመታየታቸው አግባብነት ግን አልታየኝም። የአሜሪካ የመከላከያ(ወታደራዊ) ባለሥልጣናት በአግባቡ ከነ ማዕረጋቸው ገጭ ባሉበት ሁኔታ፤ ጄነራል ሳሞራ ከታላቅ ወንድሙ ሱፍ ተውሶ የሄደ የልማታዊ አርሶ አደር ሰርግ አጃቢ መስለው መታየታቸው ግር አሰኝቶኝ ነው። ይባስ ብሎ ሱፉ ሰፍቷቸዋል፣ ረዝሟቸዋልም።መቼም የኃይሌን ተውሰው ሄደው ሊሆን አይችልም። ስጠረጥር ሊሆን የሚችለው እዚያው ዲሲ ሬድዋን ተቃውሞ ከቀመሱባት ሱቅ “ካ’ሁን አሁን ተቃዋሚዎች መጡብኝ” በሚል ሥጋት በደንብ ሳይለኩ በችኮላ ገዝተውት ይሆናል። 

No comments:

Post a Comment