OPPOSITION PARTIES WEBSITES

ETHIO NEWS & VIEWS

RADIO & TV

Tuesday, May 5, 2015

የሕወሃት/ኢሕአዴግ ሽብር በደቡብ ጎንደር ዞን – የሚሊዮኖች ድምጽ

g onየደቡብ ጎንደር (ባህር ዳርን ጨምሮ) ዞን እንደ ሌሎች በርካታ የአገሪቷ ክፍሎች ጠንክራ የአንድነት መዋቅር ያለባት ዞን ናት። ሕወሃት/ኢሕአዴግ ተለጣፊ ፓርቲ በማዘጋጀት የአንድነትን ፓርቲ ሕጋዊነት ቢነጥቅም፣ የደቡብ ጎንደር መዋቅር መለዮ በመቀየር በሰማያዊ ፓርቲ ሥር ትግሉን ቀጥሏል። በደቡብ ጎንደር ዞን 19 የፓርላም ወረዳዎች ነው ያሉት። አንድነት ፓርቲ ሊያሰልፋቸው ካዘጋጃቸው 19 ተወዳዳሪዎች መካከል 15 የሚሆኑት አሁን በሰማያዊ ፓርቲ ስም ለምርጫ እየተወዳደሩ ነው። ከነዚህም መካከል አንዱ አለማየሁ አደሜ ይባላል።
እጩ የፓርላማ ተወዳዳሪና የደቡብ ጎንደር ዞን መዋቅር ሰብሳቢ የሆነዉ አለማየሁ አደመ፣ ሚያዚያ 20 ጧት «አማን አዉለኝ» ብሎ ሀገር ሰላም ይሁን እያለ ወደ ስራ ቦታዉ አመራ። የገዛ ወንድማቸዉን ደም በማፍሰስ የሚደሰቱ የህወሀት አገልጋይ፣ ሆድ አደር ባለስልጣን፣ « ወጣቱን በማደራጀት ስልጣናችን ያሳጣናል» ብለዉ በመስጋታቸው ፣ ከጧቱ 3 ሰአት ያለ ምንም ጥያቄ ወስደዉ አሰሩት።
ቀጥሎም ከቀኑ11ሰአት ላይ አዉጥተዉ «በሰዉ ልጅ ላይ እንዲህ ይሆናል» ተብሎ በማይታሰብ ሁኔታ እጅግ ዘግናኝ፣ በባህላችን ታይትቶና ተሰምቶ በማይታወቅ መልኩ፣ ተሰባስበው ቀጠቀጡት። በህይወትና በሞት መካከል እያለ፣ የአካባቢዉን ነዋሪ ተሰባስቦ በመምጣቱ ድብደባው ለማስቆም ተችሏል። በአካባቢ የታጠቁ የሕወሃት አሽከሮች፣ « ሳትገድሉ እንዳትለቁ ተብለናል» ብለዉ ወደ ህዝቡም አፈሙዝ እንዳዞሩ ፣ ከስፍራዉ ያገኘነዉን መረጃ አመልክቷል።
በአሁኑ ሰአት ይህ ጠንካራ ታጋይ የህይወቱ ነገር በጣም አሳሳቢ የሆነ ሲሆን፣ ጎን አጥንቱ እግሩና እጁ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል።

No comments:

Post a Comment