OPPOSITION PARTIES WEBSITES

ETHIO NEWS & VIEWS

RADIO & TV

Friday, May 15, 2015

የወያኔን ሰላም ከራሱ በላይ እያመሰ የሚገኝ ሃይል እንዳለ እና መረጃ ሊገኝ አለመቻሉን የደህንነት ቢሮው ጠቆመ: -

tplf (3)የፌዴራል ፖሊስ መስሪያ ቤት በጊዜያዊነት ተጠሪነቱ በግልጽ ለደህንነት ቢሮ መደረጉ ታወቀ::
“በሰልፉ ላይ ለተነሳ አመጽ መረጃ አልተገኘም:: ያልተደረሰበት አንድ ሃይል ሰላማችንን እያመሰው ነው::” ያሉት አቶ እሳያስ ወልደጎርጊስ የደህንነት ቢሮ ሹም “የህዝቡን ቁጣ የሚመራው ሃይል አሁንም እየሰራ ነው” ሲሉ አምነዋል::
በከፍተኛ አለመረጋጋት እየታመሰ ያለው የወያኔው ስርአት በዚህ ሰሞን ብቻ ከመጪው ምርጫ ጋር በተያያዘ እንዲሁም ከውስጥ መፍረክረክ እና አለመተማመን ጋር ተዳምሮ በስጋት ላይ በመሆኑ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትን ጨምሮ የተለያዩ የለውጥ ሃይሎችን እያፈሰ በማሰር ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል::ከዚሁ ጋር በተያያዘ እየታሰሩ የሚገኙት የለውጥ ሃይሎች ንጽህናቸው እየታወቀ ሌላውን ሕዝብ ለማስደንገጥ እና ለማሸበር መሆኑ ሲታወቅ ባለፈው በሊቢያ የታረዱ ወገኖቻችንን ተከትሎ የተነሳው የሕዝብ ቁጣ የቀሰቀሰው የተደራጀ ሃይል መኖሩን እና መረጃው ግን በበቂ ሁኔታ ካለመገኘቱም በላይ የሚገኙ ፍንጮች የሚጠቁሙት ቦታ ሁሉ ምንም ውጤት እንዳልተገኘበት እና የወያኔን ሰላም እያመሰው የሚገኘው ሃይል በደህንነት ቢሮው እንዳልተደረሰበት ታውቋል::
ከዚህ ጋር ከደህንነት ቢሮ አከባቢ በተገኘ መረጃ መሰረት ሰባቱ የሕወሓት አመራሮች የሚያንቀሳቅሱት ቡድን የፌዴራል ፖሊስ መስሪያ ቤቱን ለመምራት ሃላፊነት መውሰዱን እና የፖሊስ መስሪያ ቤቱ ተጠሪነቱ ለደህንነት ቢሮው ቡድን መደረጉ ታውቋል:: በዚህም መሰረት ሰባቱ የሕወሓት አመራሮች በመላው አገሪቱ ተከፋፍለው የፌዴራል ፖሊሱን በጊዜያዊነት እንደሚመሩት ታውቋል:: የፌዴራል ፖሊስ መስሪያ ቤት ካሁን በፊት የሚተዳደረው በአለቃ ጸጋዬ እና በአቶ ኢሳያስ አመራር መሆኑ ሲታወቅ የሕወሓት አመራሮች እንደፈለጉ ያዙታል::አሁን ይህ አመራር ተጠናክሮ እንዲቀጥል በጊዜያዊነት ሽፋን ስልጣኑን ለደህንነት ቢሮ ተሰቷል::
የአገሪቱ የበላይ አካል ተብሎ ለይስሙላ የተሰየመው ተቅላይ ሚኒስቴር ይሁን ፓርላማ በዚህ ጉዳይ ላይ እንደማያገባ እና የደህንነት ቢሮ ከዚህ ቀደም እና አሁን እንደ አዲስ በመደባቸው የፖሊስ ካኪ ለባሽ ኮማንደሮች እየተመራ ስጋቱን ለማቅለል እየተራወጠ ነው:;የህዝብን ቁጣ ማስቆም እንደማይቻል እና በወያኔ ውስጥ ያለው መፍረክረክ እና አለመረጋጋት እየሰፋ መምጣቱ አሁንም አለመተማመጡ ተንክሮ መውጣቱን እንዲሁም በራስ አለመተማመን እና የችሎታ አለመኖር ድርጅቱን ውስጥ ውስጡን እየተቦረቦረ እንደሆነ በገሃድ የሚታይ እውነታ ሲሆን ስልጣናቸውን ለማስረዘም የማይቧጥጡት ነገር የሌለውን የወያኔ ሹምባሾን ለመደምሰስ አንድነታችንን አጠናክረን በመታገል ነጻነታችንን ልናረጋግጥ ይገባል::

No comments:

Post a Comment