OPPOSITION PARTIES WEBSITES

ETHIO NEWS & VIEWS

RADIO & TV

Saturday, May 2, 2015

ለወገኖቻችን ደም መፍሰስ ግንባር ቀደም ተጠያቂው አሁን በስልጣን ላይ ያለው የወያኔ መንግስት ነው !

libyaበኖርዌ በርገን ከተማ እና አካቢቢ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ለዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያዊያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌ በርገን ቅርንጫፍ አዘጋጂነት የዓለም የሰራተኞች ቀን (MAY DAY)ን ምክነያት በማድረግ ሰሞኑን በሊቢያ፣በደቡብ አፍሪካ እና በየመን በሚኖሩ ንፁሃን ኢትዮጵያዊያን ወገኖችችን ላይ ለደረሰው ዘግናኝ ጭፍጨፋ ተጠያቂው አሁን በስልጣን ላይ ያለው መንግስት መሆኑን በማሳየት ግንቦት 1. 2015 ዓም ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ ተደረገ ::
ላለፉት 24 ዓመታት በኢትዮጵያዊያን ጫንቃ ላይ ስልጣኑን አንብሮ ያለው ገዢው የወያኔ ቡድን ኢትዮጵያዊያን በሀገራቸው እራሳቸውን እንደሁለተኛ ዜጋ እንዲቆጠሩ ከማድረጉም ባሻገር ገበሬውን መሬቱን እየነጠቀ ከነቤተሰቡ በጠኔ እንዲያልቅ በማፈናቀል ፣ ወጣቱ በሀገሩ ተምሮ ምንም ተሰፋ እንዳያይ ድንጋይ ፈላጭ፣ ስራእጥ ሆኖ ሞራሉ እንዲኮላሽ እና የሱስ ተገዢ እንዲሆን በማድረግ ፣ የተማረው በካድሬ ቁም ስቅሉን እያየ ሀገሩን እንዲጠላ በማድረግ፣ ጋዜጠኞች ሀሳባቸውን በመግለፃቸው በተፈበረከ ክስ ሽብርተኛ እየተባሉ በእስር እንዲማቅቁ በማድረግ፣ ፖለቲከኞች፣ የሰባዊ መብት ተከራካሪዎች፣የሃይማኖት አባቶች ወዘተ  በሀገራቸው ሰርተው በሰላም እንዳይኖሩ በማድረግ ወገኖችችን በገፍ እንዲሰደዱ ያደረገው መንግስት እየደረሰባቸው ላለው አደጋ ተጠያቂ እሱ እና እሱ ብቻ ናቸው ::
እኛ ለዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያዊያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌ በርገን ቅርንጫፍ አባላትና ደጋፊዎች በወገኖችችን ሞት የተሰማን ሀዘን እና ቁጭት ጥልቅ ነው: ሀገራች ኢትዮጵያ እና ህዝቦችዋ እንዲህ ያለ ስደት ና ውርደት በታሪካቸው አጋጥሙዋቸው አያውቅም :ለዜጎች ህይወት ደንታ የሌለው የወያኔ መንግስት ችግር እየደረሰባቸው ያሉት ህገወጥ ስደተኞች ናችው በማለት ለገዳዮች ቢላ መሳሉን ና ጥይት ማቀበሉን ቀጥሎበታል :
45
ሀዘናቸውን ለመግለፅ እንባ ፈንቅሎቸው ወደ አደባባይ የወጡ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን በቆመጥ ጭንቅላታቸውን እያፈረስ መንገድ ላይ ሲዘርራቸው የሚያሳየውን ዜና ያለም የመገናኛ ብዙሃን ዘግበውታል: ይህ አልበቃ ብሎት ከስልጣን ውጪ ምንም ዓይነት ሰባዊነት ያልፈ ጠረበት የዘራፊዎች ቡድን በሊቢያ በዘግናኝ ሁኔታ ተገለው ቤተሰብ በቀጥታ እንዲያይ በኢንተርኔት የተለቀቀን የግፍ ዜና ለፖለቲካ ፍጆታ ለማዋል ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር ለማያያዝ ደፍ ቀና ማለቱን ተያይዞታል:
እኛም ይህንን ታላቅ ዝግጂት ማለትም የዓለም የሰራተኞች ቀን (MAY DAY)ን በመጠቀም አሁን ኢትዮጵያዊያ እና ህዝቦቾዋ ያሉበትን የሰቆቃ ህይወት ያለም ህዝብ እንዲያውቅ በድምፅ እና በምስል የተደገፉ መረጃዎችን ለተሰላፊው አሰርጭተናል :: በሰልፉ ላይ በብዙህ ሺ የሚቆጠሩ የተለያየ የኖርዌጃን  ማህበረሰብን የወከሉ ሰልፈኞች ፣  የመንግስት ባለስልጣናት ፣ ተማሪዎች ፣የሀገር ውስጥ እና ዓለም ዓቀፍ ጋዜጠኞች ተገኝተዋል ::
በመጨረሻም የዓለም ህብረተሰብ ከጎናችን በመሆን በወገኖችችን ላይ የደረሰውን ጭፍጨፋ እንዲያወግዝ እና አሁንም በሊቢያ እና በየመን በጦርነት መሀል ሆነው የድረሱልኝ ጥሪ የሚያቀርቡትን ከመቶ ሺህ በላይ ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን ምላሸ እንዲሰጥ ጥሪ  በማስተላልፍ የሰልፉ ፍፃሜ ሆኑዋል : :

No comments:

Post a Comment