OPPOSITION PARTIES WEBSITES

ETHIO NEWS & VIEWS

RADIO & TV

Saturday, May 2, 2015

የመድረክ ዶር መራራ ጉዲናና ብዙ ሕዝብ

15የአንድነት ፓርቲ ከታገደ በኋላ፣ በርካታ ተወዳዳሪዎች ለምርጫዉ አሰልፎ እንቅስቃሴ እያደረገ ያለው መድረክ ነው። መድረክ በኦሮሚያና በትግራይ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተወዳዳሪዎችን ያሰለፈ ሲሆን፣ በደቡብ ክልልም በበርካታ ቦታዎች ይወዳደራል።
በወላይታ ዞን አቶ ኃይለማሮያም ደሳለኝ በሚወዳደሩበት ወረዳ መድረክ እጩ ተወዳዳሪ አዘጋጅቶ የነበረ ቢሆም፣ እጩ ተወዳዳሪው ከፍተኛ ወከባና ጫና ስለደረሰበት፣ ከዉድድሩ ራሱን ማግለሉን አሳዉቋል። በመሆኑም አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ከዚህ በፍት ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማሪያም ብቸኛ እጩ እንደነበሩት፣ እርሳቸው ብቸኛ እጩ ተወዳዳሪ ነው የሚሆኑት።
የመድረኩ ዶክተር መራራ ጉዲና በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ካደረጉት ሕዝባዊ ስብሰባዎች መካከል የሚከተለው ስብሰባ አንዱ ነው።
ቁጥሩ እጅግ በጣም ብዙ የሆነ ሕዝብ፣ በኦህደድ ሲዘነዘር የነበረዉን ዱላ ሳይፈራ፣ ፍርሃትን ሰብሮ በዚህ መልኩ መድረክን ለመደገፍ መሰብሰቡ፣ ኦህደድ/ኢሕአዴግ እንደከሰረ የሚያሳይ ነው።

No comments:

Post a Comment